💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
እሽ ምሳ እየበላን ብናወራስ የኔ ልጅ ምን ትላለህ ብላ ወሬ ጀመረች
አይ አይሆንም እህቴ እና ወንድሜ እቤት ብቻቸውን ናቸው ገና ከማለቴ ከአፌ ቀምታ ቶሎ ብላ ማማ እና ባባ ናቸው ይዘሀቸው ና አብረውን መሄድ ይችላሉ አለችኝ የዚች ሴትዮ ነገር ይበልጥ ግራ እያጋባኝ መጣ አንደኛ ነገር የግቢውን በር ማን እንደከፈተላት ሳላቅ ገባች።
ምን አልባት ከተከራዮቹ ውስጥ አንድሰው ከፍቶላት ይሆናል ብዬ አለፍኩት ቀጥላ እናቴ አንድም ቀን እንኳን ጓደኛ ይቅር እና እህት ወንድም ኖሯት አያቅም ዛሬ የእናትህ ጓደኛ ነኝ ብላ መጣች እሺ የድሮ ጓደኛዋ ነች ይባል ለምን ስትሞት ጠብቃ መጣች ጭራሸ ደሞ ስለ እነ ማማ ማወቋ ብቻ ግን ትንሽም ቢሆን ሁኔታዋ አልጣመኝም።
እሺ እንዳልክ ይሁን ስሜ አመለ እባላለሁ ነብሷን ይማረው እና የእናትህ የረጅም ግዜ ጓደኛዋ ነኝ ጥሩውንም ደጉንም አብረን አሳልፈናል ከእናትህ ጋር አብረን ነው የተማርነው ይገርምሀል እናትህ እንዴት ያለች ጎበዝ ተማሪ ነበረች መሰለህ ደሞ በዛ ላይ መልካም ሰው ነበረች እያለች መቀባጠር ጀመረች ከሰማኋት ያልሰማኋት ይበልጣል ።
ብዙ እውነት የማይመስሉ ነገሮችን ቀባጣጥራ ስጨርስ እና አሁን ለምን መጣሽ ምን ፈልገሽ መጣሽ ብዬ ጠየኳት
እሷም እየውልህ ቅዱሴ እናትህ ትምህርትቤት እያለን ትልቅ ውለታ ውላልኝ ነበር ብላ ማውራት ስጀምር ወሬዋ ውሸቷ ሰለቸኝ በቃ ከምችለው በላይ ሆነችብኝ ውሸት በትልቅ ሰው እንደዚ ያስጠላል ኸረ በስማም ቀላ ታየች ድምጿ እራሱ አስጠላኝ በቃሽ በሚል ቁጣ በታዘለበት ጬኸት ወሬዬን ጀመርኩ ከዚ በላይ ውሸትሽን መስማትም ሆነ ላዳምጥሽ አልፈልግም በቃ ድጋሜ በስህተት እራሱ ላይሽ አልፈልግም ደሞ ከእህቶቼ እራቂ እነሱ ስር ባገኝሽ አጠፍሻለሁ ተግባባን ብዬ እጮኩ የምታወራው እስኪጠፍት ተደናግራ እስክትርበተበት ድረስ ጮኬ ተናግሪያት ከመኪናው ወርጄ በሩን ወርውሬ ዘጋሁት።
ቤት ከገባሁ በኋላ እናቴ ስለ እሷ የነገረችኝን ታሪክ ፎቶዋን እያየሁ ማስታወስ ጀመርኩ አስታውሳለሁ ቡና እያፈላች ነበር የነገረችኝ በዛው ቅፅበት ስለ እሷ እያሰብኩ እንባዬ ግጥም ብሎ ያለችኝን ማስታወስ ጀመርኩ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
እየውልህ ቅዱሴ እኔ ያው እንደምታውቀው የወሎ ልጅ ነኝ እና ቤተሰቦቼ በጣም ሀብታም እና የተከበሩ ነበሩ በዛ ላይ ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ ነኝ ሀብት ወራሽ ስም አስጠሪ የቤተሰቤ መኩሪያ ነበርኩ አይ ነበርኩ ምን ያደርጋል ቁጭት ብቻ በል ወደ ታሪኬ ልመለስልህ ልጄ።
እኔም እንደ ገጠር ልጅ ከብት ጥበቃ በጎች እረኝነት አልወጣሁም አባቴ እረኛ ቀጥሮ ነበር ከብት የሚያስጠብቀው ከቤት የምወጣበት ምክንያት የለኝም ከእኩዮቼ ጋር እንድጫወትም አይፈቀድልኝም ጭቃ ሳቦካ ገደል ለገደል ስሮጥ ውሀ ስረጫጭ መታየት አልችልም ጓደኛም መያዝ አልችልም አባቴ ትልቅ የተከበረ ባለሀብት ስለሆነ የ አየለ ልጅ እኮ ወንዝ ውሀ ስትረጫጭ ጭቃ ስታቦካ ታየች ከ እንትና ልጅ ጋር ከ እገሌ ልጅ ጋር እዛ መንገድ ዳር ቆማ ታየች መባልን አይፈልግም ይልቅስ እሱ ሚፈልገው የ አቶ አየለ ልጅ እኮ ቤት ውስጥህ በክብር የተቀመጠች እራሷን የምጠብቅ የቤተሰቧንም ክብር የምታስጠብቅ ቆንጆ እዩኝ እዩኝ የማትል መልከመልካም ልጅ ናት በዛ ላይ ፀባይዋ መባልን ስለሚፈልግ ነበር ነፃነቴን ያጣሁት።
ታድያ ቅዱሴ ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ እንዴት ይእወዱኛል መሰለህ በልቼ ምጠግብ አይመስላቸውም ነበር በተለይ አሰግድ ምትባል ሰራተኛ ነበረችን እሷ ደሟ ለእኔ ያላት ፍቅር እና እንክብካቤ ይለያል ከእናቴ በላይ ነበር ምትንከባከበኝ መሀንም ስለነበረች ይመስለኛል ለኔ ያላት ፍቅር ያየለው።
እናም እኔ 14 አመት ሲሟላኝ አባትህ እኛ ቤት አራሽ ሆኖ የተቀጠረው አስታውሳለሁ እኛ ቤት ሲገባ ከእኔ ጋር ምንም አይነት ቅርበት አደለም ቅርበት እኔ በማልፈበት እንዳያልፍ ቀና ብሎ እንኳን እንዳያየኝ አስጠንቅቆ ነበር አባቴ የቀጠረው ።
እሱም በታዘዘው መሰረት አጠገቤ ሳይደርስ እኔ ባለሁበት ሳይገኝ ስራውን መስራት ጀመረ እኔ ግን እንዴት አያየኝም እንዴት ችላ ይለኛል እዚ የተቀጠሩት በሙል እኮ አባቴ የሰጣቸውን ትዛዝ ትተው እኔ ያለሁበት አይጠፉም በዚ ምክንያት ከ አንድ ሳምንት በላይ የቆየ ወንድ ሰራተኛ አልነበረም አባትህ ግን ሳምንታትን አለፎ ወራት በታዛዥነት ስራውን አክብሮ ኖረ።
አባቴም በጣም የሚመካበት ሰራተኛው ሆነ ላገኘው ሰው ሁላ ታማኙ አገልጋዬ ነው እያለ ያስተዋውቀዋል እኔ ደሟ ሲወጣም ሲገባም ጠብቄ እወጣለሁ እሱ ግን ዞሮም አያየኝ ይሄ ነገር እልህ እያስያዘኝ መጣ እንዴት 1 አመት ሙሉ ተሳስቶ እንኳን አያየኝም እዚ ቤት ከነበሩት ሌሎች ሰራተኞች በምን ይለያል አያልኩ መብከንከን ጀመርኩ ጭራሽ እንደውም ፍቅር አስዤ ባላሳብደው እኔ ምንትዋብ አይደለሁም ብየ ዛትኩ በቃ ከዛን ቀን በኋላ እሱ ለእኔ ስሜት እንዲኖረው እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ የነረ ሚሆንበትን መንገድ እሱ እንዲያየኝ እንዲቀርበኝ ለማድረግ ማሰብ እና ማውጠንጠን ጀመርኩኝ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
እሱ ሚወጣበትን ስዓት ⌚ እየጠበኩ አውቄ እንዲያየኝ እንዲያዋራኝ እወጣለሁ ሆን ብዬ ሰላም ብዬው የማላውቀውን ሰላም እለዋለሁ እሱ ግን እንኳን ሰላም ሊለኝ ጭራሽ ቀና ብሎ እንኳን አላይ ሲለኝ አይ በቃ ጠዋት ስለሆነ ሰዎች ያዩኛል ብሎ ነው ብዬ አሰብኩ እና ማታ ሲመጣ ልጠብቀው ወሰንኩ ።
እንዳሰብኩትም ማታ ውጪ ማንም የለም እስኪመጣ ጠበኩት አሁንም ጠዋት እንዳረኩት ሰላምታ ሰጠሁት እሱ ግን ምንም ሳይለኝ እራቱን ሊበላ ሳይመለከተኝ እንኳን ገባ።
ክፍሌ ገብቼ እንደው በቃ ተብከነከንኩ የምይዘው ምጨብጠው ጠፍኝ ንዴት አንገበገበኝ እንዴት ይህን ሁሉ ግዜ አያየኝም ጭራሽ ደሟ ለሱ ብዬ እየወጣሁ ወይኔ ወይኔ እያልኩ እየተብከነከንኩ ምን ልሰራ እንደሆነ አላቅም እራት የሚበሉበት ቤት ሄድኩኝ ሲስቅ አየሁት አቤት ፈገግታ አቤት ሳቅ በዛ ላይ ጥርሱ እንዴት አባቱ እንደሚያምር የጥጥ ፍልቃቂ ነው ሚመስለው ሳያዩኝ ቀስ ብዬ ወደ ክፍሌ አመራሁ።
ክፍሌ ቆይቼ ሳብሰለስለው እንደዚ ተጫዋች ሳቂታ ከሆነ ለምን እኔ ጋር እንደዛ አይሆንም እኔ አስጠልቼው ነው አልታይ ያልኩት እኔ መጠላት እችላለሁ ሁሌም እኮ እንደምወደድ ነበር ማስበው ለካ ሰው እኔን መጥላት ይችላል ብዬ ከልቤ ከፍቶኝ ለመጀመሪያ ግዜ አለቀስኩ።
እዛው በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ጠዋት ተነሳሁ እንደ ሁልግዜው እሱን ለማየት አልወጣሁም እሱ ከሚወጣበት ሰዓት አረፋፍጄ ተነሳሁ ምንም ምሰራው አልነበረም ትምህርት እንኳን የኔታ እቤት ድረስ እየመጡ ነበር የሚያስተምሩኝ እሳቸውን ተዘገጃጅቼ መጠበቅ ጀመርኩ ሲመጡ አስተምረውኝ ለነገ የቤት ስራ ሰጥተውኝ ሄዱ።
እኔም የቤት ስራውን ሰበብ አድርጌ ከቤት አልወጣሁም ነገር ግን ሲመጣ ቀስ ብዬ ተደብቄ በቀዳዳ አየዋለሁ የዛኔ ደስ ይለኛል።
እየውልህ ልጄ በእልህ የጀመርኩት ነገር መልሶ እራሴ ላይ ችግር አመጣ አፈቀርኩት መቅናት መነጫነጭ ከሰው ጋር አለመቀራረብ ጀመርኩ ላፍታ ውጭው የሚናፍቀኝ ልጅ ከቤት አልወጣም ምወጣውም እራት ለመብላት ወደ እነ አበይ የሚቀመጡበት ቤት ነው በልቼ ትንሽ አውርቼ ወደ እራሴው ክፍል እመለሳለሁ ይህ የየእለት ተግባሬ ሆነ።
እሱን ግን ሳላየው አልውልም ነበር ጭራሽ ደሟ ከሴቶች ጋር ካየሁት ደሜ ፍልት ይላል ከሱ ጋር ስትስቅ ያየኋት ልጅ እንዴ ለአይኔ ትቀፈኛለች ባላያት እኔ ጋር ባትመጣ እንደው ደስታዬ ግን እነሱን መግፋት ማንቋሸሽ ስለ ማልፈልግ ምንም አልላቸውም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ለመያዝ እሞክራለሁ እንጂ ከአፌ ክፍ አይወጣም ነበር።
እኔ ብቻ እያፈቀርኩት ሲስቅ ደስ ይለኝ ስለነበር ተደብቄ እያየሁት አንዳንዴም ሳላየው ከዋልኩ ልክ ግቢ ውስጥ እንደ ሚዞር ሰው በበሩ በኩል አልፌ እንዳለ እና እንደሌለ አይቸው እገባለሁ ።
እኔ 16 አመት ሲሞላኝ አባቴ በሰው እጅ ተገደለ እናቴ መገደሉን ልክ ስትሰማ ታመመች ለ አልጋ እስክትዳረግ ድረስ ታመመች። እንደማትድን ስታውቅ አባትህን አስጠርታ ቤት ውስጥ ያሉትን ከብቶች እና እህል አውጥቶ እንዲሸጥ ነገረችው እሱም እንደታዘዘው ሸጦ መጣ ለሁሉም ሰራተኞች ደሞዛቸውን እየከፈለች ሸኘቻቸው።
አሰግድ ግን ምንትዋብን ትቼ የትም አልሄድም ልጄን ለማን ጥዬ ብላ እንቢ አለች እናቴ ግን አይሆንም አሷን ሁነኛ ሰው ገር ነው የማሳርፋት አትስጊ ብላ ሸኘቻት።
በመጨረሻ እኔ እና አባትህን አንድ ላይ ጠርታ በሉ ልብ ብላችሁ አዳምጡኝ አውርቼ እስክጨርስ ድረስ እንዳታቋርጡኝ ብላ ወሬዋን ጀመረች
አንተ እንደምትወዳት ባታሳያትም እንደምትወዳት አቃለሁ አንችም ልብሽ ለሱ እንደከጀለ አቃለሁ በሉ ይሄ አባትሽ በህይወት ዘመኑ የቆጠበው ገንዘብ ነው ይህ ደሞ ከብቶቹ እና አህሉ ተሽጦ ለሰራተኞቹ ከፍዬ የተረፈ ገንዘብ ነው አዲስአበባ ደሟ አባትሽ በአጎትሽ አማካኝነት በስምሽ የገዛ ባዶ መሬት አለ በዚ ገንዘብ ቤት ስሩበት እና አብራችሁ ኑሩ እኔ ከዚ በላይ አብሬ አችሁ ልቆይ አልችልም ልጄን ጠብቃት አደራ ብላ አረፈች።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
በዛን ወቅት ሀዘን ተደራረበብኝ የአባቴን ሀዘን ሳልወጣ የእናቴ ተደረበ ይበልጥ ሀዘኔን ያበረታው ደሞ አባትህ አዲስ አበባ እንድንሄድ አጥብቆ ይፈልግ ነበር ምክንያቱ ደሞ የ እናትሽ አደራ ነው መጠበቅ አለብኝ ብሎ ቤቱን ለመስራት አዲስ አበባ መጥቶ ስለነበር ሀዘኔን ብቻዬን መጋፈጥ ግድ ሆኖብኝ ነበር።
ታድያ ቤቱ በተሰጠን ገንዘብ እንደምታየው ቆንጆ አድርጎ ሰራው እኔም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ እጃችን ላይ ገንዘብ ስላልነበር እኔ ጉሊት ድንች እና ሽንኩርት ችርቻሮ አባትህ ደሞ የቀን ስራ እየሰራን መኖር ጀመርን ከዛም ብር እየቆጠብን የምታያቸው የክራይ ቤቶች ቀስ እያልን ሰራን እና የገቢ መጠናችንን ጨመርን የ እዛኔ አንተ ተወልደህ ገና 5 አመትህ ነበር።
አባትህ ግን በግዜ ሂደት ጤና ማጣት ጀመረ እሱን ለማሳከም ብዙ ገንዘብ አጠፋን ዳነ ስል ሲታመም ታመመ ስል ሲድን አንተ 10አመት ሲሞላህ እነ ማማዬን ደሞ የ2 ወር ነፍሰጡር ሆኜ አባትህ ላይመለስ አሸለበ ሲሞት ግን የአባቴን ሞት እና የ እናቴን ህመም ምክንያት ነግሮኝ ነበር ያረፈው ።
እየውልሽ አባትሽ በሰፈሩ ሌላ ተቀናቃኝ ሰው ነበረው። አባትሽ ያኔ እናትሽን ሲያገባት ሰውየውም ይወዳት ስለነበር እናትሽን እናትሽ በተሰቦች እናትሽ እንድትመርጥ አደረጉ በወቅቱ እናትሽ ደሟ ከአባትሽ ጋር የፍቅር ግኑኝነት ስለነበራት አባትሽን መረጠች ከዚን ግዜ ጀምሮ ነበር ከአባትሽ እናትሽን በማግባቱ ከሰውየው ጋር ከባድ የሆነ ፀብ ጀመሩ ያው በሴት የመጣ ፀብ ይባል የለ ቀን ጠብቆ አባትሽን ገደለው ብሎ ነገረኝ።
በወቅቱ ለምን አልነገርከኝም ብዬ ስጠይቀው እናትሽ ማስተዋል መረጋጋት ሳትጀምር እንዳትነግራት ትሞትብኛለች አደራ ብለው አስጠንቅቀውኝ ነው ብሎ ነግሮኝ ትቶኝ ሄደ ልጄ አነ ማማዬ እን ስወልድ እራሱ ከአንተ በቀር አጠገቤ የነበረ ሰው አልነበረም አንተ ደሞ ምንም ማድረግ አትችልም ነበር ልጄ አራስ ቤት ሆኜ በባዶ ቤት አንተንም በርሀብ እኔም በርሀብ ስንጎዳ ገና በለድኩ በ10 ቀኔ ደሜ ሳይደርቅ ወደ ጉሊት ስራዬ ገባሁ ይኸው የዛኔ የተጎዳሁት ነው መሰለኝ ልጄ አሁን ጤና አጣሁ።
የዛኔ ስትነግረኝ በጣም እያለቀሰች ስለነበረ ልጄ ከዚ በላይ አላውራ የራሳሁትን ቁስሌን አልነካካው ደና የሻረውን አልነካካው አሁን ላይ የመሸከሙ አቅም የለኝም ልጄ ሌላ ግዜ እናወራለን ይብቃኝ አለች እንባዋን እየጠራረገች።
ይህንን ነግራኝ በነጋታው እኔ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ዩንቨርስቲ የምገባበት ወቅት ነበር እና ቢያንስ መኪና ላሳፍርህ ብላኝ ወጣን ለካ የዛን ቀን የሷ መጨረሻ ነበር እሷ ልሸኘኝ ወጥታ እኔ ሸኝቻት ተመለስኩ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
እማ ናፈቀችኝ ከምንም በላይ ያሳለፈችውን ሳስበው ደሟ ይበልጥ ናፈቀችኝ ምንም ሳላረግላት መሞቷን ሳስበው ልቤን አደማው አቆሰለው ሳይደላት እንዲሁ እንደተንከራተተች ሄደች።
የዛች ሴትዮ ነገር ግን ጭራሽ ከአይምሮዬ ሊወጣ አልቻለም እናቴ ምንም ጓደኛ የሚባል ጭራሽ የላትም ይቺ ሴት ደሞ ስለ እኛ ቤት ሁሉንም ታቃለች ባይባልም የሆነ ምታቀው ነገር አለ ሲቀጥል ደሞ ያለ ምንም ምክንያት ስለ እኛ አጣርታ እቤት አትመጣም።
ከሁሉም በላይ ደሞ ያሳሰበኝ እናቴን የገጫት መኪናም ሆነ ሹፌር አለመገኘቱ ነው።
ይኸው እናቴ ከሞተች ጀምሮ ጣቢያ እመላለሳለሁ እስካሁን ምንም ፍንጭ የለም ነው የሚሉኝ እንደውም መረጃ የማናገኝ ከሆነ ፋይሉን እንዘጋዋለን ብለውኛል ፈጣሪ ካልረዳኝ በቀር ተስፋ ያለው አይመስለኝም ፈጣሪ ይርዳኝ እንጂ።
ሰሞኑን እነ ባባ ትምህርት ስለጀመሩ ዞር ዞር እያልኩ ስራ መፈለግ ጀመርኩኝ ሁሉም የሚወጡት ማስታወቂያዎች በሙሉ ድግሪ ዲፕሎማ ይጠይቃሉ አለፍ ሲሉም የስራ ልምድ እስከመጠየቅ ይደርሳሉ እኔ ደሞ እንኳን የስራ ልምድ ቀርቶ ያለኝ ውጤት እራሱ የ12ተኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ብቻ ነው ያለኝ ስለዚ ተቀጥሮ መስራት ከባድ ሆነብኝ እቤትም የሚያስፈልጉ ነገሮችን ያው ከኪራይ በምናገኘው ገንዘብ ነው ምገዛዛው በዛ ላይ እነ ባባ የግል ትምህርትቤት ነው ሚማሩት በቤት ኪራይ ብቻ የቤት ወጪን መሸፈን ከባድ ነው ስለዚ የሀብታም ልጆችን የማስጠናት ስራ መፈለግ ጀመርኩኝ።
በአንድ ልጅ የጀመርኩት የማስጠናት ስራ ወደ 4 ልጅ አደገ ስራውም ጥሩ ነበር በዛ ለይ ተምሬው ያለፍኩት ስለነበር ያን ያክ አልከበደኝም ነበር።
የማስጠናቱ ስራ የሚያደክም ስራ ነው ግን ቋሚ ስራ አይደለም ክረምት ክረምት ስራ አይኖርም ድጋሚ ለመስራት ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን መጠበቅ ይኖርብኛል ስለዚ ክረምት ሳይገባ ስራ መፈለግ አለብኝ ብዬ አሰብኩ።
በእኔ አቅም የሚሰራ ስራ ሳፈላልግ አንድ ጎሚስታ ቤት ስራ አገኘሁ ትምህርት እስኪዘጋ ልጆቹን ቅዳሜ እና አሁድ በሰፊ ግዜ እያስጠናሁ የቀሩትን ከቀናቶች ጎሚስታ ቤቱ መስራት ጀመርኩኝ ስራው ግን በጣም አድካሚ ነው በዛ ላይ አምሽቼ ነው እቤት ምገባው
አምሽቼ ገብቼ ደሞ እነ ማማን አስጠንቼ እራት አብልቼ እተኛለሁ በለሊት ተነስቼ ደሞ ምሳቸውን ቋጥሬ ቁርሳቸውን አብልቼ አለባብሼ ጎረቤት አደርሳቸዋለሁ ትምህርትቤት እንዲወስዷቸው።
እነሱን ለጎረቤት ከሰጠሁ በኋላ እማዬን ሰላም ልል እሄዳለሁ ዛሬ ትንሽ አወራታለሁ እማዬ እንዴት ነሽ እኛ ደና ነን እንደት እንደናፈቅሽን አልናፈቅንሽም?
አሁን ነው የገባኝ እማ ለካ እኛን መንከባከብ ብቻ ከባድ ስራ ነው እንኳን የውጪ ስራ ተጨምሮበት እኔ በዚች አጭር እንኳን እነ ማማን መንከባከብ በጣም ከብዶኛል።
አንቺ ስንቱን ችለሽ ነበር አሁን ገና የለፍሽው የደከምሽው ድካም ገባኝ መከራሽን በጥቂቱም ቢሆን የተካፈልኩሽ ይመስለኛል ደሞ እንዳታስቢ እነ ባባን በደንብ እንከባከብልሻለሁ እኔን ተንከባክበሽ እንዳሳደግሽኝ ምንም ቢከብደኝ ተስፍ ግን አልቆርጥም በቃ እማዬ ስራ እረፈደብኝ እሁድ ከ ማማ እና ባባ ጋር እመጣለሁ ቻው።
ሄጄ ስላወራኋት ደስ ብሎኛል እንደዚ ሳዋራት የምትሰማኝ አጠገቤ ያለች አይዞህ በርታ ልጄ የምትለኝ የምትኮራብኝ የምታበረታኝ ያክል ይሰማኛል ሳላያት ስራ አልገባም ጭራሽ ጠዋት ባላያት ማታ ግን ሳላያት አላድርም ሳላያት ካደርኩ ውስጤ ሲረበሽ ስፈራ ስሜቴ ግልብጥብጥ ሲልብኝ ነው ማድረው ስለዚ ሳላያት አላድርም ያየኋት ቀን ደሞ ቀኔም አዳሬም ያመረ ይሆንልኛል ብቻ በቃ ሳላያት አላድርም።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
ትምርት ተዘጋ እነ ማማም እቤት መዋል ጀመሩ እኔም የማስጠናት ስራዬን ስለጨረስኩ ነተወሰነ ሰዓት እረፍት አግኝቻለሁ በዛ ስዓት ከነ ማማ ጋር ግዜ አሳልፍለሁ እማዬ እንደሌለች እንዳይሰማቸው የቻልኩትን አደርጋለሁ እናትንም አባትንም አጥቶ መኖር ከባድ ነው እነ ማማ አባታቸውን አያውቁትም እናታቸውንም ሳይጠግቧት አጧት ጓደኞቿቸው ደሞ እናቴ እንዲ አርጋልኝ አባቴ እንዲ ገስቶልኝ ሲሏቸው በጣም ያዝናሉ ይሰማቸዋል እኔም የነሱን መከፋት ስለማልፈልግ ያለኝን ትርፍ ግዜ በሙሉ ከነሱ ጋር አሳልፋለሁ።
የክረምቱ ግዜ በጣም አስቸጋሪ ነበር ለስራም ጥሩ አልነበረም ስራ የምንሰራበት አካባቢ የመብራት መቆራሪጥም ነበረበት በዚ ምክንያት ስራው እየከሰረ መጣ እሱም እቃውን በርካሽ ሸጦ ከሀገር ለመውጣት እንደ አሰበ ከሰው ሰማሁ
ስለዚ እኔ ሌላ የገቢ ምንጭ መፈለግ እንዳለብኝ ተረዳሁ እኔ ደሞ ከ ጎሚስታ ስራ ውጪ ያለኝ ችሎታ የማስጠናት ችሎታ ነው ለዛ ደሞ ክላስ መጀመር አለበት ለዛ ደሞ ቢያንስ 1 ወር መጠበቅ አለብኝ ስለዚ ሌላ የሚሆነኝን ስራ እያብሰለሰልኩ ወደ ቤት ተመለስኩ።
እንደ ተለመደው በጠዋት ተነስቼ እነ የነ ባባን ምግብ ሰራርቼ እማዬ ጋር ሄድኩ በስራዬ ላይ የተፈጠረውን ነግሬያት ወደ ስራዬ ሄድኩ ስገባ አለቃዬ ቀድሞኝ ገብቶ ነበር ሰላምታ ሰጥቼው ልብሴን ልቀይር ገባሁ ቀይሬ ልክ ስወጣ "ቅዱስ ና እስኪ ማውራት ያለብን ነገር አለ ብሎ ጠራኝ" ምን ሊለኝ ነው ብዬ አልተጨነኩም ምክንያቱም ሊሸጠው እንደሆነ ስምቻለሁ እኔም ስራ እንደማጣ አውቄአለሁ ምንም አዲስ ነገር አልጠበኩም ነበር።
እየውልህ ቅዱስ እኔ ቤተሰቦቼ ከሃገር ውጪ እንዳሉ ታቀለህ እኔም ይሄን ስራ የምሰራው እንደ ትርፍ ግዜዬ ነው እና አሁን የውጪ ፕሮሰሴ ስላለቀ ልሄድ ነው እናም አንተ ደሞ ስራ ልታጣ ነው ማለት ነው
የምታውቁትን ነገር ሰው ደግሞ ሲነግራችሁ እንዴት ነው ሚሰለቸው ኡፍ።
እና ቅዱስ አንተም ስራ ፈት ሆነህ ከቀረህ ለ ማማ እና ለባባ የሚያስፈልጋቸውን በቤት ኪራይ ብቻ ሟሟላት የምትችል አይመስለኝም ባለህበት ሁኔታ ደሞ ከማስጠናት እና ከጎሚስታ ስራ በቀር ሌላ ሰርተህ አታቅም ስለዚህ ላንተ ይከብድሃል ብዬ አስባለሁ።
ወይ ጉድ ሰውዬው ምን ሆኗል እኔ እራሴ የነገርኩትን ታሪኬን ጭራሽ አጣፍጦ አሰማምሮ ይነግረኛል ምን አይነት ሰው ነው ለምንድነው ማውራት ወደ ፈለገው ነጥብ አይገባም ወሬው ሁላ ሰለቸኝ።
እና ቅዱስ ካለህበት ችግር አንፃር መፍትሄ አዘጋጅቼልሀለሁ ይህን እያወራ በመሀል ስልክ ጠራ አንድ ጥሩ ነገር መናገር ቢጀምር ምቀኛው በዛ ምን አለ አሁን አውርቶ ሲጨርስ ቢደውሉ ደሞ አይጨርስም ለወሬው ጓጉቼ ሳይሆን መፍትሄውን ለመስማት ጓጉቼ ነው ኧረ ጭራሽ ማታ እናወራለን ብሎ ጥሎኝ ሄደ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
ወይ ማታ እናወራለን እንኳን እስከማታ ይቅር እና ስልክ አውርቶ እስኪጨርስ ድረስ እንዴት እንደተቁነጠነጥኩ አላወቀ ያልሆነ ነገር ሲቀበጣጥር ቆይቶ አሁን ጥሩ ነገር ሊያወራ ነው ብዬ ሰፍ ስል ማታ እናወራለን ይላል አታውራ እንደውም ተወው ይሄን ያህል ለወሬ ደሞ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳወራ የሚሰራ ጎማ መጣ እና መስራት ጀመርኩ።
የዛሬው ስራ ከመብዛቱ የተነሳ ለምሳ እራሱ አልወጣሁም መምሸቱን እራሱ ያወኩት አለቃዬ መቶ በቃ ቅዱሴ ሰዓት ደርሷል እንውጣ ሲለኝ ሰዓቱን ሳየው 12 ሰዓት ሆኗል ተነስቼ ልብስ ቀያይሬ በመኪና አብረን ሄድን።
የሆነ የሚያምር በጣም ደስ የሚል ሆቴል ሄድን እዛም አንድ ወደ 40 ዎቹ አካባቢ የሚሆን ሰውዬ ልክ ስንገባ እጁን አንስቶ በምልክት ጠራን አለቃዬም ፈገግ ብሎ ና ብሎኝ ሰውዬው ወደ ተቀመጠበት ቦታ ሄደን ወንበር ስበን ተቀመጥን ሁለቱ ትንሽ ካወሩ በኋላ አለቃዬ አስተዋወቀን
አቶ አሰፍ እባላለሁ ለ አለቃህ አጎቱ ነኝ ብሎ እጁን ዘረጋ እኔም ቅዱስ እባላለሁ ብዬ ለሰላምታ የተዘረጋውን እጁን ጨበጥኩት
ወዲያው አቶ አሰፋ እጁን አጨብጭቦ አስተናጋጇን ጥሩ እራት አዘዛት እሷም ሜኑ(የምግብ ዝርዝር) ያለበት የሆነ ደብተር ነገር ይዛ መጣች ያለው የምግብ አይነት መቼም ይሄ ሁሉ እዚ ቤት ይሰራል እንዳይሉኝ አንድ ክፍለከተማ እራሱ ያሉት ቀበሌዎች ዝርዝር ቢመጣ እዚ ቤት ካለው የምግብ ዝርዝ ጋር ምንም አይወዳደርም ሆ ጉድ እኮ ነው
የሚገርማችሁ የመጀመሪያው ገፅ ላይ ያሉትን ዝርዝሮች አንብቤ ሁለተኛው ገፅ ማንበብ ስጀምር የጀመሪያው ገፅ ላይ ያለው ዝርዝር ይጠፍኛል ከዛ መጨረሻ ላይ
ሽሮ አለ ብዬ አስተናጋጇን ጠየኳት
አይ ሽሮ ሳይሆን ተጋቢኖ አለ አለችኝ በቃ እሱ ይሁንልኝ አልኳት
እሷም መልሳ ደሞ ሚጠጣስ ነገር ምን ይሁንልህ አለችኝ ኮስተር ብዬ ውሀ አልኳት እሺ ብላ የነሱንም ትዛዝ ተቀብላ ሄደች።
ያዘዝኳት ሽሮ መጣች ስትመጣ በቃ በአትክልት በዳቦ በሰላጣ ምንምን በዛ ላይ በሸክላ ተደርጋ አምሮባት በክብር መጣች ለካ ሀብታም ቤት ሲገባ የማይቀየር የለም እማዬ ጊድሽን አላየሽ የምትወጃት ሽሮ እንኳን ለሀብታም አጨበጨበች።
አይ ደሀ ያለው ቀሪ ሀብቱ ሽሮ ነበር አሷንም ሀብታም እያንቀባራት ጥላን ልትሄድ ነው። ደሀ ግን ሲያሳዝን የኔ የራሴ የሚለው ነገር በቃ የለውም አይደል።
እራቱን በልተን ስንጨርስ አቶ አሰፋ ማውራት ጀመሩ
እየውልህ ልጅ ቅዱስ እኔ እዚ ሀገር አልኖርም ከባለቤቴ ጋር ከሀገር ውጪ ነው ምኖረው ከ ሳምንት በኋላም ከ አለቃህ ጋር ወደ አሜሪካ እንሄዳለን
እናም እኔ የ12ኛ ክፋል ተማሪ አለችኝ እሷ ከሀገር መውጣት ስለምትፈልግ እዚሁ ከ አያቷ ጋር ነው ምትኖረው እንደ ሰማሁት ከሆነ በጥሩ ነጥብ 12ን አልፈህ እንደነበር ስምቻለሁ ስታስጠናም እንደነበር ጭምር እናም እኔ ዳጎስ ያለ ገንዘብ እከፍልሀለው ልጄን አስጠናልኝ ታዲያ እሷን ብቻ ነው ምታስጠናው ተደራቢ የምታስጠነው ተማሪ መያዝ አትችልም ብለው ነገሩኝ
ተጨማሪ ስራ ካልሰራሁ እንዴት አድርጌ ለእህቴ እና ወንዲሜ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟላለሁ ብዬ ጠየኳቸው
ለ እሱ አታስብ የትምህርት ቤት ክፍያቸውን እኔ እከፍላለሁ የቀረውን እኔ በምከፍልህ እና በቤት ኪራይ በምተገኘው ብር ታሟላላቸዋለህ ለእነሱም ግዜ ትሰጣቸዋለህ አሉኝ
እኔም ስራውም እድሉም አሪፊ ስለ ህነ እሺ አልኳቸው አለቃዬም ወደ ቤት ልሸኝህ ብሎ ሸኘኝ በመንገዳችንም የ ጎሚስታ ቤቱን በስሜ እንዳዞረው እና ከዚ በኋላ የኔ ንብረት እንደሆነ ነገረኝ ስራውንም ስለማቀው አነሰድ አጋዥ ቀጥሬ እንድሰራ እራሴንም በስራ ብዙ እንዳላደክም ገና ብዙ የሚቀረኝ ወጣት እንደሆንኩ ነግሮኝም መክሮኝም ቁልፉንም ሰጥቶኝ ተሰናብቶኝ ሄደ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
ፈጣሪ ሁሉንም ነገር በግዜው እና በወቅቱ ያስተካክለዋል።
እንደዛ መሽቶ ለእማዬ ልነግራት ሄድኩ ከደስታዬ ብዛት እየተፍለቀለኩ ነበር ለእማ ሁሉንም ነገርኳት ከዛ ወደ ቤት ገባሁ እነ ባባ ተኝተው ነበር እኔም ስለጠገብኩ ገብቼ ተኛሁ።
በነጋታው ጠዋት ተነስቼ የሚያግዘኝ ሰራተኛ ለመፈለግ ደላላ ቤት ሄድኩኝ እና አነጋግሬአቸው ወደ ስራዬ ተመለስኩኝ። በነጋታው ደላላው አንድ ልጅ እንዳገኘ ነገረኝ ሄጄ አየሁት
ገና ልጅ ነው ደሞ በዛ ለይ አዳዲስ አበባ ሲመጣ የመጀመሪያ ግዜው ነበር
በቃ እዛው እያደረ ስራውን እንዲሰራ በሳምንት አንድ ቀን እረፍት እንዳለው ነግሬው ደሞዝ ተስማምተን ቦታውን ላሳየው ይዤው ሄድኩኝ ስሙም በላይ እንደሆነ ነገረኝ መንገድ ላይ ስንሄድ ስለ እራሱ እንዲነግረኝ ጠየኩት ምንም ሳይደብቅ ነገረኝ።
እየውልህ ጋሼ እኔ የመጣሁት ከ ደብረ ማርቆስ ነው ስሜ ታሪኩ ነው እኖር የነበረው ከታላቅ እህቴ ጋር እና እናቴ ጋር ነው። አባታችንን ገና በልጅነታችን ነው ያጣነው እናታችን ነበረች ሙሉ ቤተሰቡን እርሻ እየሰራች ምታኖረው አሁን ግን እናቴ ስለ ሞተች አንዲሁም እህቱም የእናታቸንን ሞት ሀዘን መሸከም አቅቷት እራሷን አጥፍታ እንደሞተች እኔም በአካባቢዬ ገፊ ስባል ከተማውን ለቅቄ ወጣሁ።
በቃ ታሪኬ በአጭሩ ይሄ ነው ብሎ ጨረሰ ሲናግ በእንባ ታጅቦ ነበር እያወራ ስራ ቦታ የደረስነው።
ታሪኩ በጣም ነበር ያሳዘነኝ ምክንያቱም በተወሰነ መልኩ ታሪኩ ከእኔ ይመሳሰላል ልዩነቱ እናቴብቻዬን እንዳልሆን ለእኔ እነ ባባን ትታልኝ ነው የሄደችው እሱ ግን ማንም ማንም የለውም በዛ ላይ ሲያለቅስ እኔም እማዬ ትዝ ብላኝ ላለቅስ ነበር።
ታሪኩ በጣም ቶሎ ተግባቢ ስራው ላይ ትኩረት የሚያረግ የነገሩትን የማይረሳ ትጉህ እና ታታሪ ሰራተኛ ነው።
ስራውን ለአንድ ሳምንት አሳየሁት አንድ ሳምንት ደሞ ብቻውን እንዲሰራ አደረኩት ከጠበኩት በላ አገኘሁት ስራውን ለእሱ ትቼ መሄድ እንደምችል አመንኩኝ።
ይሄኛው አመት አልቆ ቀጣዩ መጣ ትምህርት ሊጀመር ሁለት ሳምንት ቀረው እንዳስጠናት የተነገረችኝ የአቶ አሰፍ ልጅ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ሄጄ ማነጋገር ነበረብኝ
በተሰጠኝ አድራሻ መሰረት ወደ ቦሌ አካባቢ የሚገኘው ቤታቸው ማለቴ ቤተመንግሥታቸው ሄድኩ።
ያው ከቤቱ ውበት እና ትልቀት አንፃር ነው ቤተመንግሥት ያልኩት።
ጥበቃው በሩን ከፍቶ አስገባኝ ከዛ ወደ 90ዎቹ አካባቢ የምትሆን ግን ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለች አንድ ቀይ ሴትዮ ልጅ ቅዱስ እንኳን ደና መጣህ ና ግባ ብለው የሞቀ ሰላምታ ሰተው አስገቡኝ።
ልክ ስገባ ቤቱ በሚጣፍጡ የምግብ ሽታዎች ታውዷል
እኔ በምግቡ ሽታ የት ነው ምነው ባገኘሁት እያልኩ በአይኔ ምግቡን ፍለጋ ሳማትር አንድ ቀይ የምሰታምር የደስ ደስ ያላት ቆንጅዬ ልጅ ከደረጃ ወርዳ ወደ እኔ መጥታ በፈገግታ ተሞልታ
ቅዱስ እንኳን ደና መጣህ ሳቤላ እባላለሁ ብላ እጇን ዘረጋች እኔም ሰላም አልኳት
እ የምታስጠናው እኔን ነው አለች ቀስ ብላ
እሺ መልካም ሳቤላ ብቻ አልኳት ከዛ በመሀል ዝምታ ሰፈነ።
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
በመሀል አያትየው መተው የምናጠናበትን ክፍል አሳይው አሏት እና ወደ ላይ ወጣን አንድ ክፍል ከፍታ እዚ ነው ምናጠናው አለች።
ሙሉ ክፍሉ የተሸፈነው በመፅሀፍ ነበር ምንም ሌላ ነገር የለውም። መፅሀፎቹ በስርአቱ በ ቤቱ ዙርያ ላይ በመደርደርያ ላይ ፅዳታቸው ተጠብቆ ተቀምጧል መሀል ላይ ጠረጴዛ ከነ ወንበሮቹ ተቀምጧል ከሱ እራቅ ብሎ ደሞ ኮምፒውተር አለ በጣም የሚያምር የማጥኛ ክፍል ነው በዛ ላይ ለማንበብ የሚጋብዝ መንፈስ አለው ብቻ ደስ ይላል። ክፍሉን አይቼ ስጨርስ ስለ አጠናናችን ማውራት ጀመርን።
እየውልሽ ሳቤላ አንቺን ብቻ ነው የማስጠናው እና ከ ሰኞ እስከ አርብ እኔም ስራ ስላለኝ አንቺም ትምህርት ስላለሽ ከ 11:00 ሰዓት እስከ 1:00 ሰዓት እናጠናለን ቅዳሜ ቀን ደሞ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ማጥናት እንችላለን ለግዜው ማትሪክ እስኪደርስ ድረስ እሁድ አይኖረንም መሰላቸት እንዳይኖር ያልተመቸሽ ነገር ካለ ማስተካከል እንችላለን ንገሪኝ ብያት ንግግሬን ጨርሼ እሷ ምትለውን ለመስማት እራሴን አዘጋጀሁ
ጥሩ እኔ ይመቸኛል ግን ከሰኞ እስከ አርብ ያለው ግዜ ማታ ስትወጣ አይመሽብህም ብላ ተየቀችኝ
ይመሽብኛል ግን አንቺን ለማትሪክ ፈተና ብቁ ለማድረግ ግዴታ ማምሸት አለብኝ ብዬ መለስኩላት እነሰዲ እየተነጋገርን ድንገት በሩ ተንኳኳ ሄጄ ከፈትኩ ሰራተኛቸው ነበረች ምግብ ቀርቧል ኑ ብሉ ልትለን ነበር እኛም ስለጨረስን ተከትለናት ወረድን።
አቤት እታች ስወርድ ጠረጴዛው ላይ ተደርድሮ የጠበቀኝ ምግብ እንኳን በእውኔ በህልሜ እራሱ አይቼው አላቅም በጣም ጣፍጦኝ በላሁ በዛ ላይ አያትየው በየ ደቂቃው ብላ አሰያሉ ይጨምራሉ በቃ ቁንጣን እስኪይዘኝ በላሁ ቡና ተፈላ አያትየው ተጫዋች እና ቀለል ያሉ ነበሩ የወጣትነት ታሪካቸውን እየነገሩኝ ስንስቅ አምሽተን እኔ የምመጣበትን ቀን ነግሬ ወደ ቤቴ ጉዞ ጀመርኩኝ።
በታሪኩ ስራ በጣም ስለ ተደሰትኩ ስልክ ገዝቼ ሰጠሁት ከልቡ አመሰገነኝ ደስ አለው ግን እንዲ ብሎ ጠየቀኝ
ቅዱስ ስለገዛህልኝ አመሰግናለሁ ግን ማን ጋር ልደውልበት የትኛው ዘመዴ ጋር የትኛው ወዳጄ ጋር ልደውልበት ብለህ ገዛህልኝ እኔ እኮ ማንም ወዳጅ እንደሌለኝ ታቃለህ ብሎ ጠየቀኝ እኔም ማስተማሪያ ከሆነው ብዬ ታሪኬን በሙሉ አጫወትኩት ከልቡ ሰማኝ እና
ታድያ አንተ እኮ እናትህ ቢያንስ አጫዋች ትታልሀለች አለ
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
💙 መራራው እውነት 🌹🔸
#ክፍል_
አዎ ትታልኛለች ነገር ግን እኔ እንዳተ ለአንድ ነብስ ለ እራሴ ብቻ አላስብም አልሳሳም አየህ ሁለታችንም ወላጅ አልባ ነገር ግን አንተ እራስህን ለማዳን ስትል ትለፍለህ እኔ ደሞ እህት እና ወንድሜን ለማዳን ለማኖር ስል እለፍለሁ ገበህ አይደል ታሬ ብዬ ለጥያቄው መልስ ሰጠሁት።
ትንሽ ዝም ካለ በኋላ መወለድ ቋንቋ አይደል ታድያ ለምን ወንድምህ አልሆንም ወንድሜ አትሆንም ካመንክበት እኮ እኔመረ አንተም ወንድማማቾች ነን አለኝ እና ከ እኔ መልስ በመጠበቅ አይነት እይታ እያየኝ መልሴን መጠበቅ ጀመረ
እሺ ህይወት ያገናኛቻቸው መቼም ማልይለያዩ ወንድማማች ከሆነ እሺ አልኩት ምኔ እኔ ጋር እንደደረሰ በላቅም ዘሎ አቀፈኝ እና አመሰግናለሁ ወንድሜ አለኝ እኔም አቀፍኩት ትንሽ ካወራን በኋላ ወደ ሳቤላ ጋር ለመሄድ ተሰናብቼው ሄድኩኝ።
ከሳቤላ ጋር ዛሬ በይፍ ጥናት ምንጀምርበት ቀን ነው እኔ በግዜ ለመድረስ ቶሎ ስለወጣሁ እነሱ ጋር 30 ደቂቃ ቀደም ብዬ ደረስኩኝ ዛሬም ጥበቃው ከፈተለኝ ወደ ውስጥ ገባሁ ትንሽ ከአያትየው ጋር ካወራን በኋላ በሰዓታችን ወደ ጥናት ገባን ከልቧ ሆና ነበር ምታዳምጠኝ በዛ ላይ ጎበዝ ናት የማታሰለች አይነት ልጅ ስለሆነች ስይሰለቸኝ አስጠኝቻት ጨረስኩ።
ወደ ቤት ለመሄድ ልወጣ ስል አያትየው እራት ስትበላ አትወጣም ብለው ጥሩ እራት አብልተው ሸኙኝ።
ልክ ሰፈር ልደርስ ስል ታሪኩን ደውዬ ጠርቼ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ቤት ይዤው ሄድኩ ከነ ማማም ጋር አስተዋወኩት።
ስሞኑን ግን እናቴ በህልሜ እየመጣች የኔን ነገር ተውከው አይደል እረሳኸው አይደል ትለኛለች ምን እንደሆነ ግን ልረዳው አልቻልኩም ምን አልባት ሳልጎበኛት ቀርቼ ነው ብዬ ስላሰብኩ በጠዋት ሄጄ አየኋት አሁንም ግን እየመጣች ተመሳሳይ ነገር ተሰለኛለች ይሄ ነገር አይምሮዬን ሰላም እየነሳው መቷል
ከሳቤላ ጋር ያለን ቅርበት ጨምሯል በዛ ላይ በግዜ ተዘገጃጅታ ነው ምጠብቀኝ የሰጠኋትን የቤት ስራዎች ምንም ሳታስቀር ትሰራለች አንዳንዴ እኔ ከወጣሁ በኋላ ያለገባሽ ጥያቄ ካገኘሽ ደውይልኝ ብዬም ስልኬን ሰጥቻታለሁ።
ሕይወት በዚ መልኩ ቀጠለ ከታሪኩም ጋር በጣም መቀራረብ ጀመርን ምንም አልደብቀውም ሁሉንም ነው ምነግረው የሚመልስልኝ መልስ ደሞ ከሱ አልጠብቀውም ያለ እድሜው የበሰለ አርቆ አሳቢ ልጅ ነው እሱን ስለ ሰጠኝ ፈጣሪዬን አመሰገንኩ።
ዛሬየ እማዬ ሙት አመቷ ነው ታሪኩንም ጨምሬ ከነ ባባ ጋር ለመሄድ አስቤአለሁ ለ ሳቡም እንደማልመጣ ደውዬ ነገርኳት ለምን እንደሆነ ጠየቀችኝ ነገርኳት መምጣት እንደምትፈልግ ነገረችኝ እኔ ግን አይሆንም አልኳት እሷ ግን እመጣለሁ ብላ ድርቅ አለች እኔም ምርጫ ሳጣ እሺ አልኳት።
ጠዋት እማዬ ጋር ሄደን አየናት ሰላም ብለናት በስሟ ለ ነዳያን መፅውተንላት ወደ ቤት ተመለስን ትንሽ ቁጭ እንዳልን ሳቡ ደወለች አቅጣጫውን ነግሬአት ነበር በዛ ላይ በሹፌር ስለ ነበር የመጣችው ብዙም አልተቸገረችም ልቀበላት ወደ መኪናው ስሄደረ አያቷም መተው ነበር ማዘር ሀምን ተቸገሩ ስላቸው ስላልነገርኳቸው እራሱ እንደተቀየሙኝ ነገሩኝ ያልጠራኸኝ እንደ እናትህ ስለማታየኝ ነው አይደል ብለው ተቆጡኝ እኔም እንዳይደክሙ አስቤ እንደሆነ ነግሬ ይቅርታ ጠየኳቸው።
ሲመጡ የሚበላ ይዘው መተው ስለነበር እሱን አቅርበን በላን ከዛ እማዬ ከሞተች በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ የሳቡ አያት እማዬ ምትቀመጥበት ቦታ ቁጭ ብለው አፈሉ ልክ እሳቸውን ሳያቸው እማዬ ትዝ ብላኝ እንባዬን ዘረገፍኩት እነሱም ልጆቹ ፊት እንዲ መሆን እንደሌለብኝ ነግረው አባበሉኝ እነ ባባም የ እኔን ማለሰቀስ ሲያዩ መተው አቅፈው እንባዬን ጠረጉልኝ።
ባባም ለመጀመሪያ ግዜ እንዲ አለኝ ወንድሜ የእማዬ አለመኖር በጣም እንደጎዳህ አቃለሁ ግን ደሞ እኛ አለንልህ እኮ ብቻህን አይደለህም አለኝ
ማማም ቀጠለች እና ወንድሜ አንተ ስትከፍ እኮ ማየት አንችልም ያላንተ ማን አለን አንተን ካጣን እኮ እኛ ባዶ ነን አለችኝ በደንብ አቀፍኳቸው እና ሳምኳቸው እሺ አላለቅስም አልኳቸው ለካ አድገዋል አልኩኝ እኔ ነኝ ህፃን የማደርጋቸው እንጂ እነሱ በስለዋል ተመስገን ብዬ ፈጣራዬን አመሰገንኩት ደሞ ነገ የነሱን ፍሬ ያሳየኝ።
እነ ሳቡም አመሻሽ ላይ ሄዱ እኛም ትንሽ ተጫውተን ተኛን የዛሬው አዳሬ ግን ከባድ ነበር እማዬ ከምንግዜውም በላይ በህልሜ መታ ዛሬ ስላረኩላት ነገር አመሰገነችኝ እና ልጄ የኔን ጉዳይ እንደተውከው ቀረ ደሜ ፈሶ እንዲቀር አንተም ጨከንክ ልጄ ሳላዝንብህ ልጄ የፈሰሰውን ደሜን እፈሰው ደመሸ የልጆቼን ነገር አደራ ብላኝ ሄደች ወዲያው ባንኜ ተነሳሁ ስነሳ ዝናብ እንደ ደበደበው ሰው ሰውነቴ በላብ እርሷል ከዛን ስዓት በኋላ ምንም መተኛት አልቻልኩም እንቅልፍ ካይኔ ጠፍ ያለችኝ ነገር እንቅልፍ ነሳኝ
ይቀጥላል.....
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact