#ክፍል_
#ከሁለት_አመት_በኋላ
...🖌መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ታናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል የመቅደስና የጌዲዮ ትውውቅ ድፍን ሶስት አመት ሊሞላው አንድ ሳምንት ብቻ ነው የቀረው አሁን አመቱ አዲስ ነው የረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው መቅደስ ያራተኛ አመት ጌዲዮ ደግሞ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ነገ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ይጓዛሉ በተለይ ለጌዲዮ ይህ አመት ልዩ ነው ዛሬ ላይ እንዲቆም በትምርቱ ገፍቶ ሰው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፈጣሪ በታች መሰላል የሆነችውን የናቱን አደራ የሚወጣበት ተመርቆም ለቁም ነገር የሚበቃበት ልዩ አመት ነው እንኳን ለናቱ እንኳን እራሱ መቅደስም የዚህን አመት መጨረሻ ናፍቃለች ደወለችለት
....ሄሎ ጌዲ ወዬ ፍቅር እንዴት ነህልኝ እግዚያብሄር ይመስገን ደናነኝ አንቺ እንዴት ነሽ እማ ደናነኝ አንተ ግን እያመመህ ነዋ አለችው አረ ደናነኝ ደሞ ደናነኝ ትላለሀ ቅድም እኮ ስደውል ማዘር አንስተው እንዳመመህ ነግረኛል ውይ መቅዲ እማን አታውቂያትም እና ነው እራሴንም ስል እኮ ነው አቋረጠችው በቃ እራስ ምታት ላንተ በሽታ አይደለማ ለማንኛውም ነገ መናህሪያ እንደደረስክ ደውልልኝ አባዬ አደርሳችኋለሁ ብሎኛል ለሊት ስለምትነሳ አሁን ተኛ አለችው እሺ ደናደሪልኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ እሺ ቻው።
.......በንጋታውም ልክ እንዳለችው ተያይዘው ባባቷ መኪና ተያይዘው ጅማ ገቡ አባቷም ምሳ ጋብዞ ግቢ አድርሷቸው ወደአ.አ ተመለሰ.......መቅደስና ጌዲዮ ግቢ እንደገቡ ከሁሉም ጓደኞቻቸው ጋር ተገናኙ ወይና ብርሀን ሰአዳ በለጠው ሌሎቹም ተሰባሰቡና ቡና ለመጠጣት ሻንጣዎቻቸውን አሳርፈው ወጡ.......
በለጠው በጓጓው ልቡ እናንተ የተገናኛችሁበትን ሶስተኛ አመት እንዴት ነው የምታከብሩት አላቸው መቅደስም እንዳምናው ነዋ አለችው በቃ ይቀወጣል አላት ብርሀንም ሙድ ስትዪዝበት የሰውንማ ለማሞቅ አንደኛ ነህ ግን ያንተ መቼ ነው ስትለው ሁሉም ሳቁበት እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ ባንድ ሳምንት አንድ ሴት እቀይራለሁ ታዲያ እኔ ለየትኛዋ ፓርቲ ላዘጋጅ ስታዪኝ ከበርቴ ቱጃር መሰልኩሽ እንዴ ጌዲዮም ቀጠለና አንድ መያዝ ነዋ አለው ወይ አንድ ትቀልዳለህ መሰል እንደዛ ሲል ሰአዳ ወሬ ቀይር አለችው ከዛም ትንሽ እንደተዝናኑም ጌዲዮ አመመው ብዙም ሳይዝናኑ ወዲያው ወደግቢ ተመለሱ።......
........ሶስተኛ አመት የትውውቅ ልደታቸውንም በደመቀ መልኩ እያከበሩት ሳለ ዛሬም ጌዲዮ አመመው ቢሆንም እስኪነቃ ጠብቀው ሻማቸውን አብርተው ሲደሰቱ ነው ያደሩት
ቢሆንም ግን መቅደስ የፍቅረኛዋ ነገር እያሳሰባት ነው ጭራሽ እንቅልፍ አልወሰዳትም ጌዲዮ ሲነቃ እንቅልፍ አልያዛትም መቅዲ ምን ሆንሽብኝ ለምን አተኚም ሲላት እንቅልፌ ስላልመጣ ነው አንተ ተኛ አለችው ፊቷ ተቀያይሮ ስለነበር ጌዲዮ ወዲያው አወቀባት ምን እያሰብሽ ነው ስለኔ ነዋ አላት አዎ ስላንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንዲህ በሽታህን ተሸክመህ የምትኖረው መቅዲዬ እሺ ምን ላርግ ምን ላርግ አትበለኝ ይኸው ሀኪም ቤት ለመሄድ አይደል እንዴ ዛሬ ነገ እያልክ ስንት ጊዜ የሆነክ መቅዲ ብሄድም ምንም ለውጥ አይኖረውም እኮ እንዴት አወክ መቅዲዬ የኔ በሽታኮ አትጨርሰው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ልትለኝ ነዋ አዎ ደሞኮ ሰዎች ሲያወሩ እንደሰማሁት ከሆነ እጀ ሰብ ነው ይባላል አረ ጌዲ እንደተማረ አስብ ለስሙ ነው እንዴ አራት አመት ሙሉ አገር አቀፍ ውጤት አሸንፈህ የተሸለምከው ለነገሩ ጌዲ ሀሳቧን እንድትቀይር እንጂ በንደዚህ አይነት ነገር አያምንም
.....መቅዲዬ ምንም አልሆንም ደሞ ፀበል እየሄድኩ አይደል ይሻለኛል ጌዲ ልታባብለኝ አትሞክር እኔ እንቅልፍህም ያስፈራኛል እንባ ባይኗ ሞልቶ ፈሰሰ ደግሞ የትኛው ፀበል ነው ሀኪም የሚከለክለው ሁሌ ይሻለኛል ትላለህ ግን እያባሰብህ ነው ጌዲ አንተን ካጣን እኔም ሆንኩ እናትህ አንድ ቀን አናድርም መቅደስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲም ሊያስቀይሳት ፈልጎ ማታ ወድቄ አሳፈርኩሻ አላት መቅደስ ባንዴ አራስ ነብር ሆነች ባለ በሌለ አቅሟም በጥፊ ሞላችለት ለመናገር ተስኗት ትንፋሿ ተቆራረጠ ጌዲዮም ጉንጩን ይዞ እየሳቀ አረ እየቀለድኩ ነው አመረርሽ እኮ ሲላት በንዴት ደረቱን እየወቀረች እኔ ጨንቆኛል አንተ ትቀልዳለክ ጌዲዩ በፍቅር የሚመቱትን ሁለት እጆቿን ግጥም አርጎ ይዞ አቀፋት መቅደስ ይበልጥ አለቀሰች የምታጣው የምታጣው እየመሰላት ነው ጌዲዮም ሁኔታዋ ግራ ገብቶት አረ በቃ አንቺ ደስ ካለሽ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እኔዳለን አላት እስኪ ማሪያምን በል አለችው በንባና በሳቅ መሀል ሆና ማሪያምን እኔዳለን ብሎ አባበላትና አቅፏት ተኙ።..........
.......መቅደስ ከጌዲዮ ቀድማ ነቃች ሻውር ወስዳ ለባብሳ ስትጨርስ ልትቀሰቅሰው ጌዲ አለችው መልስ አልሰጣትም አሁንም ተጣራች ዝም አላት አንተ ጌዲ ተነስ ሰአት እረፍዷል ግቢ ክላስ መግባት አለብን አለችው አሁንም መልስ አልሰጣትም ክው አለች ከወንበሯም ተነስታ ወዳልጋው አመራች በጆቿም እየደበደበች ብጠራውም ሊሰማት አልቻለም እንደበረዶ ቀለጠች ሰውነቷ ደነዘዘ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋ ጌዲ ጌዲ ደጋግማ እየተጣራች አቤት በለኝ አለች ጌዲዮ ግን...
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
❤የልብ ቋንቋ❤
🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact
⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE
Contact