Ye Fikr gitm 😍😘
1.2K subscribers
20 photos
5 videos
24 links
የስነፅሁፍ ተሰጥኦዎች
📜ግጥም
💆የጭንቅላት ጨዋታዎች
💭አባባሎዎች፣
👽Psychology Facts
😭old music😘🍫🍫
❤️ልብ_ወለድ እና ጠቃሚ ምክሮች ያለገደብ #ከልብ_ዲያሪ ወደናንተ ይደርሳሉ
በተጨማሪም💎
ግጥም 💖የፍቅር❤️ የይቅርታ🙏 የመልካም ምኞት መግለጫ እና የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች ያገኙበታል ተቀላቀሉት ትወዱታላችሁ
ችግር ካለ @Oneday678 በዚህ አናግሩን
Download Telegram
     የተጠገነ ቃል
          
🤥

የተሰበረ ልብ በምን ይጠገናል፣
       ጊዜ ሽሮት እንኳን
       ጠባሳውም ያማል፣
በታወሰ ቁጥር ህመም ያገረሻል፣
        ስንት ነው ተመኑ
        ዋጋ ወጥቶለታል፣
        ያፈቀረን መግፋት
      እንደው ስንት ያወጣል።

  ከረፈደ ነቅተው የቦዘዙ አይኖች፣
 በእርጅና የደከሙ የዛሉ ጉልበቶች።
         ማስተዋል ሲያገኙ
         ሲነቁ ከህልማቸው፣
 እንደው ቢጠየቁ ቢሰማ ድምፃቸው፣
          የገፉትን ማግኘት
        ይሆን ወይ መልሳቸው።

                  እንጃ፣
ብቻ፣ ባላወኩት አለም በሃሳብ ተሰድጄ፣
  የጎዳሽኝ አንቺን በሀሳብ አስረጅቼ።
           ድንገት ባስብ ጊዜ፣
   ስለሰበርሽው ልብ ፀፀቱ ሲገልሽ፣
            ከሀሳብ መለስ ብዬ
            ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፣
     እርሺኝና ኑሪ ሀዘን አይብዛብሽ፣
  አለም አሰቃይታ ቁጭት አይግደልሽ፣
ሺህ ብታደሚኝም ይኸው ይቅር አልኩሽ፣
 በሄድሽበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምሽ፣
    በእንባዬ አትሜ ይቅርታን ላኩልሽ፣
      እውነት መልካሙ ይግጠምሽ።

━━━━━━━━✦
😥✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

Join us
👌

@yefikrgitm8
4
ግጥም ማፃፍ ወይም መፃፍቹ ማስለቀቅ የምትፈልጉ ለፍቅረኛችሁ/  ጓደኛ / ለእናት / ለአባት / ለእህት / ወንድም መጋበዝ የሚትፈልጉትን በእኛ በኩል ላካችሁ እኛ ደግሞ ቀጥታ እንለቀዋለን ቻናላችን ላይ በውስጥ መስመር አውሩኝ @Dagim197 or @oneday678   24/7 አለን

@yefikrgitm8
👍7
አሞኝም አያውቅ😏

ምን ውስጤ ቢቆስል ብትደማም ነብሴ
እንዴት አለሽ ሲሉኝ ይመስገን ነው መልሴ
አሞኛል ብላቸው መድሃኒት ላይሆኑኝ
ደከመኝ ብላቸው ደርሰው ላይደግፉኝ
እንዴት ነሽ ይሉኛል
እኔን ግን በቅቶኛል
ያኔም ቀን አሳስቶኝ
አሞኛል ያልኳቸው ምንም አልበጁኝም
ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ መፍትሄ አልሰጡኝም።

ሰመረ ስል ተፈታ ህልሜ
በቃ ተሳካልኝ ተረሳ ድካሜ
ቢዬ ሳላበቃ ነገር ቢበላሽም
ደህና አለመሆኔን ለሰው አላሳይም
ደህና ነኝ
ከእጄ ቢርቅ የኔ ያልኩት
ባይሆንልኝ ብዙ ያለመኩት
አገኘሁ ስል በዕጥፍ ባጣም
ቁስሌ የኔ ነው አላሳይም
የበለጠ እንጨት ሰዶ ከሚወጋኝ
እፍ ብሎ አይዞሽ እኔን ለማይለኝ
ለምን ብዬ እህህ ልበል ላሳይ ውስጤን
ላይጋራኝ አለው ብሎ ክምር ሸክሜን
አልናገር እንዳመመኝ
ካ'ሁን ወዲህ ለጠየቀኝ
ካ'ንድ ውጭ ምላሽ የለኝ
ክብሩ ይስፋ ይመስገን ነው ደህና ነኝ!።
👏42👍2
ስንብት
-----------------                                                                   ተሰነባብተንም አይቆሮጥልኝ ፍቅርህ                                      በኔ ላይ ካስቻለህ ያው መንገዱ ይቅናህ ።                              ሁሌ ማወዛገብ ሁሌ ማስፈራራት                                           ሁልጊዜ መታመም ሁሌ መሰቃየት                                          ለኔ ካሰብክልኝ እስኪ ልቤን ያዛት ።                                    ጭንቀትህን ንገረኝ ህመምህን ልታመም                                 ልሞት ነው አትበለኝ ..........                                                    ፍቀድልኝ እና እንይ ይቺን አለም።                                    እጅህን ልያዛት                                                                 ከሞትንም አብረን ነው                                                        አይተን ያለም ግዛት።                                                       እየተሰናበትክ ነፍሴን አስጨነካት                                                        የኔ ፍቅር                                                       ፍቀድልኝ እና ነፍስህን ልያዛት ።                                                                               
👍62
በመኖር  አጸድ ውስጥ


ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::
👍6
🥲ትናንት እና ዛሬ🥲

አላወቅሺም እንጂ አፍቅሬሽ ነበረ

       ዳሩ ምን ያረጋል
ሌላው ይዞሽ ሲሄድ ልቤ ተሰበረ።

የሆነው ሆነና እንዳሰብኩት ሳይሆን
         ከጎኔ ባጣሽም

በትናንት ሀዘኔ የዛሬው ህይወቴን
          ከቶ አላበላሽም።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝 @Remu890

@onelove58
👍62
አንተ መሄድ ስትወድ
  ከኔ የበለጠ
    የሚያደርስ መች አጣህ
እንደት አክብረኧኝ
  ከጀርባዬ ወጣህ
ኪሩቤል ሱራፌል
  ዙፋን የሚሸከም መላይክት እያለህ
ከኔ ከተናኩት
ጀርባ ላይ ለመውጣት
  እንደምን አስቻለህ
ምን አገኘህብኝ ሳለሁ የተጠላሁ
እንዴት ተሸክሜህ ቤተልዬም ገባሁ
👍6
🌹🌹በእሾህ ተከበሽ🌹🌹

ፅገሬዳ አበቦች በድንገት ሳያቸው
             ትዝ ትዪኛለሽ

እሾህሽ ብዙ ነው የግሉ ሊያረግሽ
            ከልብ ለተመኘሽ

እኔ ግን ከርታታው ጉልበተኛ ባልሆን
            ገንዘብ ባይኖር ኪሴ

እውነተኛ ፍቅሬን ተጠቀምኩኝና
              አረኩሽ የራሴ።

📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️
one day
👍31
​​​​​​​┉✽‌»‌‌🌺ማን ይሆን🌺‌‌✽‌┉
                :¨·.·¨:
══════❁✿❁ ══════
:
ማን ይሆን

🌹 አይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ
  ……… የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ
………  አካዊ ወረት ያረገጠ ወዳጁን
አለ ወይ ከሰዎች ያልጎዳ ወዳጁን
ውድ ፍቅረኛውን ልቡን እንዳፈቀረ።
🌹  ……በሷ ተወስኖ ዘላለም የኖረ
እስከመጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ
ከሚወዳው በቀር ያልተመኘ ሌላ
ማናው ይህንን የሰራ በቃሉ የሚገኝ ባስቀመጡት ስፍራ ያልተለዋወጠ
ማን  ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
👍53
🙏

       በእርሱ ቁሰል 😢

ተገረፈ
ተወነጀለ
ተተፋበት ተሰቀለ

እሱ ስለ እኛ ሞትን ተቀበለ

አቤት ትህትና አቤት አቤት ፍቅር
ኢየሱስ መጣ እኛን ሊያድን ወደምድር

       በእለተ አርብ መስቀል አሸከሙት
       ይህም አልበቃቸው በጅራፍ ገረፉት
        ህዝቡም በጥላቻ ምራቅ ተፉበት
        ያኔ ያመሰገኑት አሁን ሰደቡት

ይሰቀል ይሰቀል እያሉ ሲጮሁ
አላወቁም ነበር ለእኛ መሆኑን?

እሱ እኮ ንጉስ ነው የሰማይ የምድር
ዝቅ ያለው ፍቅርን ሊያስተምር
እግር ያጠበው ትህትናን ሊያሳይ
በሰው እጅ ተሰቅሎ ሆነ ለሰው ሲሳይ

ከ99 በጎቹ አንዱ ቢጠፋበት
ለፈጠረው ፍጡር በጣም ሳስቶለት
ወረደ ወደምድር ሊሆን መስዕዋት

እናቱስ ግን እንዴት ቻለች
እንባዋን ወደምድር ረጨች
ፀሀይም አኩርፋ ብርሀኗን አጠፋች
የአምላኳን ገላ አላሳይም አለች
ጨረቃም ከእሷ አቅም ደም ለበሰች

ጴጥሮስም አላውቀውም ብሎ ካደው
ዶሮ ሲጮህ ትዝ አለው አምላኩ ያለው
አዎ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
በእኛ ሀጥያት እሱ ተሰዋልን

በሱ ፍቅር ከሀጥያት ነፃን

መገረፍ ያለብን እኛ የተገረፈው እሱ
መሰቀል ያለብን እኛ የተሰቀለው እሱ
መከራን ተቀበለ  አስጠጋን ወደራሱ

ይህ ነው እግዜአብሄር 

ለሰው ልጆች ብሎ እራሱን ሚያዋርድ
ፍቅርን ለማስተማር ፍቅር ሆኖ የሚወርድ
ይህ ነው እግዘብሔር  ፍጥረቱን ሚወድ


ተፃፈ በሽልማት

​​​​​​​​​​​​
Join us 👇👇👇

@yefikrgitm8
8
"መስሏት ነበር እሷ"

ያኔ ጥላኝ ስትሄድ _ ከጎኔ ስትርቅ
ሁሌም  የማለቅስ _ደግሜ የማልስቅ

መስሏት ነበር እሷ 😏

ያኔ ስትገፋኝ  _ ቀልዳ በፍቅሬ
ወድቄ የምቀር  _ እዛው አቀርቅሬ

ቆይ ምኔ ሞኝ ነው 🤔

አንድ ሴት ብትሄድ  _ ሊያውም የማትወደኝ
አንገቴን  ደፍቼ  _  ሁሌ እንባ ሚወርደኝ
                     
ንገሯት ለዛች ሴት  _ ለዛች ለማታውቀኝ
            አንድ ተራ እንቅፋት
ከሂወት መንገዴ  _  አይችልም ሊያግደኝ
  
#ሼን


━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን  ❤️

      
👍84👏1
ችርስ ለማይሆን ፍቅር ብለን ብዙ ዋጋ ከፍለን ክህደት ለተከናነብነውና ሠው ማመን ላቃተን🥂🍻🥂🥂
👍6
ዛሬ ላይ ስመጥር ከሆኑ ባለሀብቶች💰 መሀከል አንዱ #እንሆን_ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ በዓለም ካሉ አዋቂዎች እና ምሁሮች አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትኛውም ሀብታችን🚘 ፣ የትኛውም ዕውቀታችን አይደለም ሞትን እንድናመልጥ በህይወታችን ላይ የአንድ ሰከንድ ዕድሜን አይገዛልንም፡፡

ታዲያ ያለን ሀብት ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ይሄን ማድረግ ካልቻለ ለምን ለሰዎች ክፉ እንሆናለን? ለምን እራስ ወዳድ እንሆናለን?

ዛሬም ፣ ነገም ፣ ከነገ ወዲያም ሁሌም ለሰዎች መልካም እናስብ፤ መልካም እናድርግ🙏



መልካም ቀን 🥰

@yetsberaleb
4👍1
* በዝምታዬ *


በዝምታዬ ነው ያፈንኩት ስቃዬን፣
ለሰው ሳላወጋ ደብቄ ህመሜን፣
ደብኜ የቻልኩት ካንች መለየቴን፣

በዝምታዬ ነው ሳጣሽ የሸኘሁሸ፣
በልቤ አንብቼ የተሰናበትኩሽ፣
ምልጃም አላሰማው እያልኩኝ ተመለሽ፣

ብቻ እያየሁት የእግርሽን ዳና፣
ተመኘው ምቾትን በመራሽ ጎዳና፣
ስትሄጂ ሸኘሁሽ እኔም ዝም አልኩና፣

አቅሜ እሱ ነበር ያለው በመዳፌ፣
ክደት ከርችሞታል አይናገር አፌ፣
ዝም አልኩኝ ሲዘረፍ ሲከፈት ደጃፌ፣
የኔ ያልኳት ርቃኝ ሀዘኔን ሸክፌ፣
ልቤ ተቀዳዶ ላይጠግነው መርፌ፣
አልከስሽ ለዳኛ የውስጤን ጡር ፅፌ፣
ለፍቅር ተማርኬ ላንቺ ተሸንፌ፣
ዝም አልኩ ስትሄጂ ሲደፈር ደጃፌ፣

ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
እንደው ተብከነከንኩ፣
ትፋሼን አርዝሜ ቁናውን ተነፈስኩ፣
ዕንባዬን ሳላፈስ አምርሬ አለቀስኩ፣
በፍቅር እየኖርኩ ፍቅርን ረገምኩ፣
መሞሸሬ ቀርቶ ይባስ ብቸኛ ሆንኩ፣
ውስጤ እሬታ በዛ ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
ከራሴ ተላተምኩ፣
ለሽንፈት ተሸነፍኩ፣

ዝም ብዬ ልሸኝሽ፣
ቸው እንኳን ሳልልሽ፣
መልካሙን ምኞቴን 'ባፌ ሳልገልፅልሽ፣
ይሄን የማረግው ስለምን መሰለሽ፣
ደጅ ደጁን እንዳይ ነው ብዬ ትመጫለሽ፣




         @yetsberaleb 😢😥
2
የኔና ያንቺ ህይወት
━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት...
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት....

እውነት እውነት ስልሽ...
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።

                     
                            

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱

        @yetsberaleb
🥰8👍3
❤️‍🔥👑#እማ👑❤️‍🔥
                          
                 
🪔የማላድገው ልጅሽ🪔🤱

ሁሌ ምትናፍቂኝ ፣ከጉያሽ ሳልጠፋ፣
ማትሆኚው የለም ፣እኔ እንዳልከፋ፣
እንደ ቅጠል ረገፍሽ ፣ቀስ በቀስ እናቴ፣
አንቺ ባትኖሪማ ፣ እቺ እለም ምንድናት ባዶ ናት ሕይውቴ፣
ስስት የለብሽም ፍቅርሽን፣ ስሰጭን፣
እኩል ነው ምታይን ፣ሳታበላልጭን፣🙎‍♀🙎
ምን ብዬ ልግለፅሽ፣ እኔ የሉኝ ቃላት፣
ክንቱ ነው ቃላቴ ፣ ቢናርም አይገልፀው ያንቺን እናትነት፣
እንችን ክፋ አይንካሽ ፣ምንም አትሁኚ፣
ካንቺ ያስቀድመኝ ፣የማላድገው ልጅሽ ሁሌ ያንቺ ሞኚ፣
ለፍተሽ አሳደግሺኝ ፣የሰው ፊት እንዳላይ ፣
እናት ብቻ አይደለሽ ፣ ከእናትም በላይ፣
ብቻ ምን ልንገርሽ ፣ሕይወቴ ነሽ አንቺ፣
የፍቅር ቅኔ ነሽ ፣ መቼም ማትፈቻ፣
እማ እውድሻለው ፣ነፍሴ እክትወጣ፣
ሕልምም አያሳየኝ ፣ብሞት ይሻለኛል፣እኔ አንችን ከማጣ፣
እማ አምላክ ቢጥርው፣ ወትሮም ከእድሜሽ፣ላይ፣
ምንም አትሁኚብኝ፣nefffffffአመት ኑሪልኝ ፣ውስደሽ ከኔ ላይ❤️

🤱
🤱                                
    🤱🤱
         🤱.          
         🤱🤱🤱.    🤱🤱🤱🤱🤱
         🤱      🤱.   🤱 🤱.   🤱.🤱
         🤱       🤱.   🤱. 🤱🤱👩‍🍼                                                     🤍
          🦋      🦋.                        🤱
                                                   🤱
                                                  🤱
        
ለእናታችሁ እንብቡላት ደስታዋንም አጋሩን በComment 🥰🥰


𝙷𝚊𝚙𝚙𝚢 𝚖𝚘𝚝𝚑𝚎𝚛'𝚜 𝚍𝚊𝚢❤️‍🔥
           🌼👑👑🌼



@yetsberaleb 😢😢
👍10
አንድ ሰው አለ...!

እኖራለሁ ብሎ፥ ራሱን ለማየት፥ ልጁን ያባበለ፤
እግሩን በእሾህ አጥሮ፥ አፈር እየጋጠ፥ ፍቅርን የተከለ፤
.
ዘሩን ለማሳደግ፥ ራሱን የገታ፥ ርኀቡን አምቆ፤
ነጌውን ለማንገሥ፥ አቀርቅሮ ታይቷል በእንባ ጎርፍ ደምቆ፤
.
₁አለ፥ በውሳጣዊ ዓይን 'ሚ^ታይ ነው ዘልቆ!
.
.
እኔን የሚል አጥቶ፥ ሳይደላደለው በመቃተት ቆሞ፤
ሰው ሰው ሳይሸትት፥ በሲቃ እየኖረም፥ በዝቶበት ተቃውሞ፤
ክብር ሳይከጅለው፥ ለማክበር ሲታገል፥ እሱነቱን ጥሎ፤
እሱ ተጎንጕኖ፥ ደስታን የሚያሳይ፥ ከድኅነት ታግሎ፤
.
፩ሰው አለ ያይደለ ጎዶሎ...!
.
.
ማሳደግ፥ ትልቅ ድል፥ በሚል ብሂል ታጥሮ፤
በልብ ሞገሥነት፥ ኃይል ለራ
ሰጥቶ፥ ሳያሳይ ሮሮ
መኖርን ያኖረ፥ ዝቅ በማለት ቤት፥ ከፍታን ያሳየ፤
ከምንሰማው ውጪ፥ ፍቅርን የሚሠራ፥ ለልጁ የተለየ፤
.
1ሰው አለ ለዝና የዘገየ...!
.
.
ሲሰቃይ፦ ልጅ በጀርባ አዝሎ፥ ምግብ እስከ ማብሰል፤
የምሬቱ ውጤት፥ ፊቱ ያጠቆረው፥ ከሰል እስከ መምሰል፤
ውርጭ ሳይበግረው፥ ማልዶ እየተነሣ፥ ከሥራ እየዋለ፣
ና፥ አንድም ብርቱ፥ ልጁን ጀግና ያስባለ፤
.
1ሰው አለ...!
.
ማቀርቀሩን ለክ
ር፥ ማልቀሱን ለፍቅር፥ ብለን ብንሰይመው፤
አባትም'ኮ አለ፥ የሰው ክፉ ሲያይ፥ እምባ የሚቀድመው!

አባት...! ... አባት...! ...


━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን  ❤️

       Join us 👇👇👇

@yetsberaleb
3🔥1
ማለዳ ነበርን🌅🌄

ለወግ ማዕረግ ባይደርስም ዳር
ማፍቀር ኪሳራ የለውም....
ትዝታም ቢሆን የውብዳር
ባይደርስም እስከ ፍፃሜ...
ባይቆይም እስከዘላለም
የእውነት ፍቅር አለው ቀለም🥰
ተሳክቶልን ባንዘልቅም
ባሳለፍነው አትርፈናል...
ለልብ ሰማይ ቀን አይጠልቅም
በተሳሳምንበት በተቃቀፍንበት😌
በዚያ ጎዳና ላይ...
ምን ዛሬም ባናልፍም
መሽቶብናል ብለን...
ማለዳ እንደነበርን
አንዋሽም አንድ ቀን

አዎ....
ፍቅርማ ነበረን....
በአፍላነት የተቋጨ🥺
በለጋነት የተቀጨ
እስከሞትም ባያኖረን...
ድልድይ ሆኖ ያሻገረን
ባሳልፍነው ያለፍንበት
ፈፅሞ የማንከስርበት☺️
አዎ....
ፍቅርማ ነበረን
ለወግ ማዕረግ ባይደርስም ዳር
ማፍቀር ኪሳራ የለውም..
ትዝታም ቢሆን የውብዳር🤗

ዘውድአክሊል
3
አወቅሽኝ

አወኩሽ
.
.
.
ተዋወቅን
በፍቅር ነጠቅን

ጨረቃን ዳሰስናት ኮኮቦችን ቆጠርን
ቅዳሴ እና አዛንን
አስቀደስን አፈጠርን
አወኩሽ
ወደድኩሽ
ከልብ ተመኘሁሽ
ለነብሴ ፈለኩሽ

አጌጥን በፍቅራችን አስቀናን ላገሩ
            ኮራን በመንደሩ
ወጣቶች ተያይተው
     "ሲያምሩ...ሲያምሩ" እየተባባሉ

ወደድሽኝ

ወደድኩሽ
.
.
.
ተዋደድን
በፍቅር አበድን
ነጎድን...ነጎድን...ነጎድን

ከአፍ ባልወጣ ቃል
መፋቀራችንን ሀገር ምድሩ ያውቃል
መገረም መደነቅ ለኛ ምንም ነው
         ተፋቅረን አየነው
ደላኝ ባንቺ ፍቅር
        ደላሽ በኔ ፍቅር
እኔ ለንቺ
አንቺ ለኔ ካለን ሁሉም ነገር ይቅር

አፈቀርሽኝ

አፈቀርኩሽ
.
.
.
ተፋቀርን
የዛሬን ትዝታ ለነገ ወቀርን።



ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ

@yetsberaleb
@yetsberaleb
6🤔1
አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል ጥገና ሱቅ ሔዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ" ብለው ሰጡት። የሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ "አባባ ስልክዎ ምንም አልሆነም ይሠራል" አላቸው።

ሽማግሌው ዓይናቸው ዕንባ አቀረረና  "ስልኩ ካልተበላሸ ... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድን ነው?" አሉ በደከመ ድምፅ።

ለወላጆቻችን የምናደርገው ትልቁ ሥጦታ ቢኖር ጊዜ መሥጠት ነው። የመኖራቸው ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። ዕድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በሕይወት ካሉ አሁኑኑ እንደውል። ይህንን ለማንበብ ጊዜ ካገኘን መቼም ለነሱ ለመደወል ጊዜ አናጣም።

"በምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር" ዘዳ 5:16

©® One Heart

━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
  ❤️
20