የግጥም መንደር
1.71K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
"እርሳስና ላጲስ አብረው ይኖራሉ ግብራቸው ተቃርኖ፣
የሚፅፈው ከታች አጥፊው ከላይ ሁኖ።"
❤️መልካም ምሽት❤️

🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር 🇪🇹

@yebezigetmoch
የዘላለም ሀብት ማለት
በባንክ ዉስጥ ያለ ገንዘብ ሳይሆን 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በልብ ዉስጥ ያለ ፍቅር
እና መልካምነት ነዉ።

መልካም ምሽት
#ሼር
@yebezawit2
❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹
።።።።።​​ምርጥ ባህሪ ።።።።።
➩ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ
➩አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን
➩ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ
እንዲሆን አትጎትጉት
➩ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን
አስወግድ
➩ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን
➩አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ
➩በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን
➩የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር
➩ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ
➩ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን
ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ
የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች
ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ
➩ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል
ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ
ያሳምናቸዋል።
........... ............
@yebezigetmoch ❤️
እንኳን ደህና መጣቹ
፡ ሼር በማረግ ወዳጆን ይጋብዙ
ሰውየው ገብጋባ ቢጤ ነበር ታዲያ ወደ ቦሌ ለመሄድ
ፈልጎ
ታክሲ ያስቆምና "ባለ ታክሲ አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ
በስንት
ትውስደኛለህ?" ሲል ይጠይቀዋል ባለ ታክሲውም
"ሁለት ብር"
ሲል ይመልስለታል::
"ለሻንጣዬ ስንት ታስከፍለኛለህ ማለት ነው?"
"ግዴለም ሻንጣውን በነፃ እጭንሎታለው"
"እንግዲያውስ አንተ ሻንጣውን ይዘህልኝ ሂድ እኔ
በእግሬ
እድርሳለው
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
@yebezigetmoch @yebezigetmoch
🌹🌹አንቺ የሌለሽ ጊዜ🌹🌹
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ #በቤዛዊት የተፃፈ
ክፍል ሶስት
.....ከሆስፒታሉ ወጥቼ ወደሰፈር እየገባሁ ነበር የትላንትናዋ እማሆይን አየሗቸው ምን ብዬ ልነግራቸው ነው ቅዱስ አመላክ ሆይ ኧረ እርዳኝ ብዬ በልቤ ፈጣሪዬን ተማፀንኩት፡፡አማሆይ ወደእኔ እየቀረቡ እኔም ወደእሳቸው እየቀረብኩ ነበር ገና ሰላም ሳይሉኝ ምን ሆና ነው ልጄ ደህና ናት ብለው ጠየቁኝ እኔም መራመዴን አቆምኩኝ ደህና ናት ማለት አልችልም አይደለችምና ግን እሳቸውን ማስደነገጥ አልፈለኩም መቆሜ አስደነገጣቸው እንደምንም አፌን ከፍቼ ደህና ናት እናቴ አማኑኤል ወሰዷት አልኩኝ ቁና ተንፍሼ፡፡ ደነገጡና መለስ ብለው ይሁን እግዚአብሔር ያውቃል የእኔ ልጅ አይ ሳላያት እኮ ወደ ፅዮን ማርያም ልሔድ ነው አሉኝ ከፊትለፊቴ ቆመው፡፡እኔም ወይ እናቴ በቃ አይጨነቁ እኔ አለሁ ድና ይመጣሉ አልኳቸው መነኩሴዋ ፈገግ አሉ ፈገግታቸው አስደነገጠኝ ምን መሆኔ ነው አልኩኝ እሳቸውም የኔ ልጅ ከፍ በል ተባረክልኝ አዎ እመጣለሁ እግዛሐር ከፈቀደ አልያም ትመጡ ይሆናል አደራህን ልጄን በምድር የሰጠሁህን በሰማይ እቀበልሀለው አሉኝ ደነገጥኩኝ አደራ እኮ ነው አማን እሺ እንዳትል አለኝ አእምሮዬ ልቤ ደግሞ በመታመኑ ደስ ብሎታል እሺ እናቴ አልኩኝ ልቤ አሸንፎኝ መነኩሴዋ በደስታ አመስግነውኝ ስማቸውን ጠየኳቸው እማሆይ ወሰኔ ይባላሉ እኔም አማኑኤል እባላለሁ አልኳቸው እና ወደቤቴ ገባሁ ቤት ስገባ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደቤተሰብ ሆነው እያወሩ ነበር ለመቀላቀል አሰብኩኝ ግን ካወራን አመታት አልፈዋል ዝም ብዬ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁኝ እና አልጋዬ ላይ ተወርውሬ በጀርባዬ ተኛውና ጣሪያው ላይ እያንጋጠጥኩኝ የመኝታ ቤቴ በር ተንኳኳ ሰራተኛችን ነበረች አማን እራት ላምጣልህ አለችኝ እኔም አዎ አምጪልኝ ከሻይ ጋር አልኳት ሰራተኛዋም በሩን ዘግታ ወጣች አምላኬ ሆይ እህቶቼን ጠብቅልኝ አደራህን ብዬ ከፈጣሪዬ ጋር ማውራት ጀመርኩኝ፡፡ የውስጤን ለብቻዬ ስለማብሰለስል ይጨንቀኛል የበፊት ህይወቴ ታወሰኝ ከቤት ስገባ ሰላም የምንባባለው ከወንድሞቼ ጋር በሪሞት ስንጣላ ከአባቴ ጋር ሚስጥር ስናወራ ብቻ ከልዕልት በፊት ቤተሰብ ነበርኩ ከልዕልት በሗላ ግን ባዳ ሆኛለሁ እንባዬ በጉንጮቼ ሲወርዱ ነበር የውስጥ ሰላሜን ማጣቴ የታወቀኝ ልዕልት ቤተሰቦቼ ያልወደዷት ከብዙ ወንዶች ጋር ያዯት ነበር ግን እኔ አልቀበላቸውም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከእንጀራ እናቷ ጋር ተጣልታ እኔ ጋር መጣች ብር ስለአልነበረኝ እኛ ቤት እንድትኖር ለምኜ አስገባሗት እሷ ከመጣች ጊዜ ጀምሮ ብርእና ዕቃ መጥፋት የጀመረው ልዕልት ወጥታ ስትመጣ እጇ ላይ ብር አይጠፋም በዚህ ምክንያት ሁሌ መጣላት ስለጀመርኩ ባገኘሁት ብር ቤት ተከራይተን ወጣሁኝ አጎቴ በውሳኔዬ ቢናደድም ብር ላከልኝ እኔም የዛን ቀን ብሩን ከምንተኛበት ፍራሽ ስር ቆጥሬ በፊትለፊቷ አስቀምጥኩት እቅዳችን ቅዳሜ ዕቃ ልነገዛ ነበር፡፡ነገር ግን ሌላ ሆነ በእሷ ምክንያት ከወጣሁበት ቤት ልብሴን ላመጣ ሔድኩኝ የዛን ቀን አባቴ ሲያየኝ አንተ ልጅ ግን ምነው ቀልብ አጣህ አለኝ እኔ ግን ዝም ብዬው ልብሴን ሰብስቤ ስወጣ መጨረሻህ አያምርም አለኝ እውነትም ቤት ሰገባ ልዕልት የለችም ፍራሹ እንደተነሳ ያስታውቃል ብሩን ሳየው የለም ያስቀመጥኩት መቶሺ ብር የለም ትመጣለች ብዬ ብጠብቃት አልመጣችም ሳምንት ሙሉ ጠበኳት እሷ ግን ቀረች በስተመጨረሻ ግን ዱባይ ሀገር ከሔደው አብሯ አደጌ ጋር ተጋብታ ሄደች አሉኝ እንባ ሳቅ ጩኸት ስሜቴ ተዘበራረቀ የምወደው አብሮ አደጌ ከአፈቀርኳት ጋር ለማመን ከበደኝ የግድ ታምሜ ስለነበር ወደቤቴ ተመለስኩ ከዛን ጊዜ በሗላ ነው አጎቴ ስለሚወደኝ እንዳልጨነቅ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አስገባኝ ታክሲውንም የሰጠኝ እሱ ነበር፡፡ አጎቴ የሚኖረው አሜሪካ ነው፡፡ ብቻ ግን አሁን ሌላ ነው ሁሉም ተቃራኒ ፡፡ ከሐሳቤ ባነንኩኝ.....ሰራተኛችን እራቴን ይዛ መጣች አቀራረቧ በጣም ነው የምወደው የቀረበልኝን ምግብ በትኩስ ሻይ አጣጥሜ ተጠቅልልዬ ተኛሁ የወጣቷ ነገር አሳስቦኛል ምን ይዤ ነው የምሔደው እየጨነቀኝ በዛው ድብን ያለእንቅልፍ ወሰደኝ
ፀሐይ ከአድማሱ ፍንትው ብላ ወጥታ በወፎች ዜማ ታጅባ ወጥታለች፡፡እኔም ከተኛሁበት ያባነነኝ የእማዬን ድምፅ ስሰማ ነበር ተንጠራርቼ ከአልጋዬ ላይ ወርጄ ከመኝታ ቤቴ ወጣሁ፡፡ስወጣ ሁሉም ገበታ ላይ ተሰብስበው በተለያየ ሳህን እየበሉ ነበር እኔም ፊቴን ታጥቤ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ አንድ ሳህን አንስቼ ተቆረጠውን እንጀራ እየዘረጋሁ ቡርቴ(የቤት ሰራተኛችን) ቆንጆ ለታመመ ሰው የሚሆን ሾርባ ስሪልኝ አልኳት ቡርቴም እሺ ብላኝ ወደኩሽና ሄደች፡፡እኔም ወጥ እየጨለፍኩ ከፈቀዳቹልኝ እማዬ ለተደፈረች እና የአእምሮ ህመም ላለባት ምን ላድርግላት አልኳቸው ቀና ብዬ ሳላያቸው ሁሉም ዝም አሉ አውርቼ አላውቅም ነበርና እግሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ ቀና ማለት ፈራሁኝ............

😔ክፍል አራት እንዲቀጥል 👍 ድምፅ ይስጡን
👍 ማንን ገደለ😉
@yebezawit ላይ እስኪ ጫር ጫር ያርጉልን፡፡
ደራሲ ቤዛዊት
🌹በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ የፍቅር ታሪክ❤️
በግጥም መንደር #ብቻ
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💐 #አንቺ_የሌለሽ_ጊዜ❤️
📚
📚አንቺ የሌለሽ ጊዜ📚
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ #በቤዛዊት የተፃፈ
🍁ክፍል አራት🍁
.......የሰውነቴ መንቀጥቀጥ እየጨመረ ሲመጣ ታወቀኝ "ለዛሽ ሴት ነው" አባዬ አናገረኝ ቀና ሳልል አየደለም አባዬ ሌላ ናት ስሟን አላውቀውም አልኩኝ እንጀራውን በወጥ እየለወስኩ እህቴ ቀጠለች ወይኔ ታዲያ ግን የት ናት የት አገኘሀት ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ እኔም እዚህ ሰፈር ነበረች ከትላንት ወዲያ ለሊት ነውያየሗት ጠዋት ምግብ ልሰጣት ስሔድ ሰውነቷ በደም ተለውሶ......ሲቃ አነቀኝ፡፡ አባቴም አማን ታዲያ እኛ ምን እናርግልህ አለኝ፡፡ ቀናአልኩኝ ሁሉንም አየሗቸው እና ደህና ስትሆን እዚ ትመጣ ለማለት ፈልጌ ቃላትን አማጣኩኝ፡፡ግን አቃተኝ ምን አይነት እንክብካቤ ነው የሚያስፈልጋት አልኩኝ በዚህ መሐል ቡርቴ ሾርባውን ይዛው መጣችና የምግብ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጣ ተመለሰች እናቴም ቀጠለች ትምህርትህን ሳታቆም እየሔድክ እያት ምግብ ምናምን እኔ ጠዋት አዘጋጅልሀለው አለችኝ እንባዬ መጣ፡፡ ለማልቀስ ግን አልሞከርኩም ያንከባለልኩትን እንጀራ ሳልጎርስ አመስግኛቸው ወደ መኝታ ቤቴ ሮጥኩ.........................ልብሴን ለባብሼ ቡርቴ የሰራችውን ሾርባ ይዤ ወጣሁኝ መንገዱ ረዘመኝ አመት የተጓዝኩ እያህል አቁነጠነጠኝ መድረሴ አይቀርምና ደረስኩ አማኑኤል ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ገባሁኝና በአይኔ መቃኘት ጀመርኩ ስፖርት የሚሰሩ ህመሟን አሉ ለእነሱ ይሄ ሆስፒታል አለማቸው ነው በነፃነታቸው ውስጥ ሳቅ ረብሻ ለቅሶ ንዴት ደስታ ያስተናግዳሉ ግን አያውቁትም አለማወቃቸው ግን ጠቅሟቸዋል ሰው አያስከፉ ብቻ እነሱንም እግዚአብሔር ያስባቸዋል አልኩኝ ለራሴ ወጣቷን ያየቻት ዶክተር ቢሮ አቀናሁ እና የእንጨት በሩን ሁለቴ አንኳኳሁ ይግቡ የሚል ድምፅ ተሰማኝ በሩን ቀስ ብይ ስከፈት ሲጥጥጥጥ የሚል ድም ፅ ከበሩ ወጣ ልገባ ዶክተር አልኩኝ መነፅሯን አያወለቀች ግባ አለችኝ በሚያምር ፈገግታ እኔም በሩን ዘግቼ ፊትለፊቷ ካለው ወንበር ጫፍ ላይ ተቀመጥኩኝ ቀጠል አርጌ ትላንት መጥቼ ነበር ከአንዲት ወጣት ጋር አልኳት ዶክተሯም አዎ አስተውሼሀለው ለመግባባት ያመቸን ዘንድ ዶክተር ሊያ እባላለሁ አለችኝ እኔም ስሜን አቆላምጬ አማን አልኳት ዶክተሯ ቀጠለች እሺ አማን ያው ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊውን ምርመራ አድርገንላታል፡፡ እናም በጣም የአእምሮ ጭንቀት ነበረባት ይህ ነገር ደግሞ ሲፈጠር በይበልጥ........አላስጨረስኳትም እሷ እኮ እብድ ናት አልኩኝ ቃሉ ለራሴ ዘገነነኝ ይቅርታ ዶክተር እኔ ሳውቃት የአእምሮ ችግር ነበረባት አልኩ አስተካክዬ ዶክተሯም ተሽከርካሪ ወንበሯን እያንገላታች አዎ የዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ብዙ ህመሟን ገጥመውኛል የእሷ ደግሞ ከዚህ የተለየው የደረሰባት ጥቃት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የሚያቃት ሰው ብናገኝ ምርመራችንን ያረጋግጥልህ ነበር ወጣቷ በጣም በመጨነቋ የመጣ የጤና መቃወስ ሲሆን አስፈላጊውን ህክምና ክትትል ማግኘት ከቻለች በቀላሉ ትድናለች ግን ለመዳን የሚያስፈልጓት ቅድመ ሁኔታወች አሉ ብላ ከፊቷ ያለውን ካርድ ከፈተች እኔም ለመስማት ተመቻችቼ ተቀመጠኩኝ ቀጠለች "ለእሷ ጥቅም ሲባል ካላስፈላጊ ጭንቀት ከዚህ መውጣት አለባት፡፡ ይሔን ያለነው ለሊት ላይ ለሌሎች ታከሚዎች የእንቅልፍ መድሀኒት ሲሰጣቸው በመረበሿ እና እንቅልፍ በማጣቷ ነው ሲቀጠል በደረሰባት ፆታዊ ጥቃት ምክንያት ወንዶችን ማየትም መስማት አትፈልግም እና ቅርቧ የምትሆን እንስት ወይም ነርስ ታስፈልጋታለች የታዘዘላትን መድሀኒት ለመስጠት ለመመገብ እንዲሁም በየቀኑ እኔ ጋር በማምጣት የስነልቦና ህክምናዋን ትወስዳለች ሲቀጥል በትንሹ ወጣ እያለች አካባቢዋን ማየት ከተፈጥሮ ጋር ማስተዋወቅ አለብን ይሄ ደግሞ ለማድረግ የጀገነ ልብ ነው የሚያስፈልገው አለችኝ አፍጠጥጣ እያየችኝ እኔም ሁሉንም እችላለሁ አልኳት....................እኔ እና ዶክተሯ ከተነጋገርን በሗላ ከሶስት ቀን በሗላ እንደምወስዳት ተስማምተን ወደክፍሏ ልትወስደኝ ከክፍሏ ወጣን የወጣቷ ስሟ ግን ማነው አልኳት ዶክተሯም ይሄ በሂደት እናጣራለን ለጊዜው ግን ሚስጥር ብለናታል አለችኝ፡፡ ሚስጥር ዋው አልኩኝና በልቤ ዶክተሯን ተከትዬ ወደ ሚስጥር ክፍል ገባሁኝ አልጋው ላይ የሆስፒታሉን ፒጃማ ለብሳ ተኮራምታለች አሳዘነችኝ ገና ስታየኝ ፊቷ ተቀየረ ዶክተሯም ብዙ አትቆይ እንዳታስገድዳት ብላኝ ወጣች እኔም ጠጋ ብዬ ከፊቷ ቆምኩኝ ማልቀስ ጀመረች እንባዎቿ ልቤ ላይ ያለቁስል የነካኝ ያህል ህመሟ ተሰማኝ፡፡ ሚስጥር አልኳት ቀስ ብዬ እሷ ቀና ብላ አየችኝ እኔም ያመጣሁትን ሾርባ እያስቀመጥኩ አይዞሽ እሺ ትወጪዋለሽ አታልቅሺ አልኳት ሚስጥርም በእጇ አንሶላዋን እየፈተለች በአትኩሮት አየችኝ እኔም ነፍሷ መጨነቁ ገብቶኝ በሩን ከፍቼ ወጣሁ፡፡

ሚስጥርን በተከታታይ ቀናት ከክላስ መልስ እየሔድኩ ጠየኳት፡፡ታክሲዬን መንዳት ካቆምኩኝ ቀናት አልፈዋል ኪሴ ላይም ብሬ ተመናምኗል፡፡ የዛሬው ማለዳ ደግሞ ደምቆቦኛል ሚስጥር ልመጣ ስለሆነ መሰለኝ ውስጤም ደስታና ሰላም እየተሰማኝ ነው የራሴ መኝታ ቤት ተፅድቶ ተዘጋጅቷል ቤተሰቦቼም ቢሆኑም የሆነውን በሰሙ ጊዜ ልባቸው አዝኗል ታላቅ ወንድሞቼም አማን አብረንህ እንምጣ እና እናግዝህ አሉኝ ልወጣ የታክሲዬን በር እየከፈትኩ በደስታ መዝለል ብቻ ነው የቀረኝ ልቤ ደስታ በዝቶባት ልቧን እስክታጣ በደስታ ጮቤ ረግጣ እየዘለለች ነው፡፡ እኔም እሺ ብያቸው አብረን በእኔ ታክሲ ወደ ሆስፒታል አቀናን፡፡...................................................................... ክፍል አምስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ፡፡
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ

💓አንቺ የሌለሽ ጊዜ💓
በግጥም መንደር ብቻ
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@Yebezawit2
📚📙📘ከመፅሐፍት ጓዳ📗📕📒
በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም
የሚጠፋባቸው በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን
ወንዶች ደግሞ በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡

@yebezigetmoch
# like_share በማድረግ ይቀላቀሉን።
​​❍✰✰ቀልድና ቁምነገር┈━═☆
➣ዛሬ ለህይወትህ ዋጋ ካልሰጠሀት
ነገ ህይወት በተራዋ ዋጋህን
ትሰጥሀለች።
━━━━ ━━━━
➣ሰዎች ካደረጉልህ ይልቅ
ያላደረጉልህን እያሰብክ አትተቻቸው አትጥላቸው ምክንያቱም
አላስተዋልክም ይሆናል እንጂ ለራሳቸው ማድረግ
የማይችሉትን ለአንተ አድርገውልህ
ይሆናል።
━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━
❤️የግጥም መንደር❤️
😒ማጣትን ከፈረድክብኝ😔

የኔ ብዬ ጓደኛዬ ካልኩት
ደስታውን ሳልጠግብ ካጣሁት
የያዝኩት በረከት ካጣ
በልቤ የገባውም ከወጣ
በል አስቸልኝ ብቸኝነቴን
እንዳልሞት አርቅልኝ መርዙን
ብቸኝነቱን አደራ አስወድደኝ
አበረታኝ ማጣትን ከፈረድክብኝ፡፡
😢ቤዛዊት😢
25/11/2011
ለ...........ነው😒
😍አንቺ የሌለሽ ጊዜ😍
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
👉ክፍል አምስት👈
*****እኔና ወንድሞቼ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ገብተናል ዶክተሯ ከሩቅ አይታኝ በፈገግታ ወደእኛ መጣች፡፡እንኳን ደህና መጣቹ አለች እጇን ለሰላምታ እየሰነዘረች እኔም ለፈገግታዋ ፈገግታዬን እየመለስኳላት ታላቅ ወንድሜ ቀድሞ ጨበጣት እና እንኳን ደህና ቆያቹን አላት፡፡ሁኔታው ገርሞኛል ታላቅ ወንድሜ አናንያ ይባላል የሁላችንም ታላቅ ነው የተመረቀው በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ነው ከእሱ ቀጥሎ ባርኮት አለ ባርኮት ደግሞ በሆቴል ማኔጅመንት ተመርቆ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ነው የሚሰራው ከባርኮት ቀጥዬ እኔ ከእኔ ቀጥለው ደግሞ ሄለን ሜሮን ናቸው፡፡የአናንያ እንደዚህ መሆን እየከነከነኝ ወደ ሚስጥር ጋር ሄደኩኝ ሚስጥር ለሌሎች ህመሟን ስፖርት ከሚሰሩበት ቦታ ላይ ተቀምጣ እያለቀሰች ነበር እንባዋን ባለየው ደስ ባለኝ ቀስ ብዬ ከአጠገቧ ተቀመጥኩኝ እሷ ግን ቀና ብላም አላየችኝም እንባዋ ሽቅብ እየወረደ ሳሩን እያራሰ ነው፡፡ሚስጥር አልኳት ቀና ብላ እንድታየኝ መልሷ ዝምታ ሆነ እንደዛ በአንድ ምሽት ስትፈነጥዝ አይቻት አሁን ላይ ከማልቀስ ውጪ የሀዘንሲቃ ድምፅም የለም ቀና ብዬ ሰማዩን አየሁት በነጭ ደመና ሸማ ግርማ ሞገስ ተላብሷል ፈጣሪን ጋርዶት ይሆን አልኩኝ በልቤ የሀጥያትን ወሬ እየፈተልኩኝ፡፡ ነፃነት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት ከተማዋ በእርግጥ ያበደ ብቻ ነው ያላት የለየለት ነገን እና ሰውን ረስቶ በራሱ አለም ይኖራል እኔን የመሰለ ደግሞ በልቡ ሰማይ እያጉረመረመ በራሱ ነፃነቱን ተቀምቶ ነገን እያመለከ ሰው የሚባለውን ፍጥረት ከራሱ በላይ ፈርቶ እንደራሱ ሳይሆን እንደሌላው ይኖራል***************************አንተማነህ አለች ሚስጥር ደነገጥኩኝ እየቀዘፍኩ የነበረውን ሀሳብ አቆምኩኝ፡፡ማን ነኝ ልበላት ቀጠለች ይዘኸኝ ጥፋ!!!አስወጣኝ!!! በሀይለ ቃል ጮኸች፡፡ከተቀመጥኩበት ተነሳሁኝ ነርሷ እየሮጠች መጣች ሚስጥርም ፀጉሯን እየነጨች አስወጡኝ አስወጡኝ.......................ደም ከአፍንጫዋ መፍሰስ ጀመረ ሽባ ሆንኩኝ አይኖቿ አንባን እያፈሰሱ ቀልተዋል ዶክተሮች እና ነርሶች ተረባርበው ወደክፍሏ አስገብተው መድሃኒት ሰጧት፡፡ እውነትም ጨንቋታል ዶክተሯ ጠራችኝ እኔም እንደምንም እግሬን ከመሬት ላይ አላቅቄ ተራመድኩኝ የዶክተሯ ቢሮ ክፍት ነበር እና ሳላንኳኳ ገባሁ ባርኮትና አናንያም ውጪ ነበሩ ዶክተሯ ከመቀመጤ ማውራት ጀመረች አማን እንደምታያት ሚስጥር ተጨንካለች አእምሮዋ በመታወኩ ነው እንደዚህ የምትሆነው ይሄ ደግሞ እስከምታገግም ያጋጥማል በመሆኑም አሁን ስትወስዷት ይሄን መድሀኒት ግዙ ጠዋት ምሳ ሰአት ማታ እና ለሊት ነው የምትወሰደው አለችኝና ወረቀት ሰጠችኝ ቀጠል አርጋም ያው እዚህ መመለስ የለባትም እኔ በቻልኩት አቅም እየመጣሁ አያታለው አልያም ደግሞ ጎበዝ ጓደኛ አለኝ እሱ ጋር እልካችሗለው አለች፡፡ እኔም ይሆናል የምትይውን አርጊ አልኳት ዶክተሯም በቃ አስሬ ከምንቀያየርባት ዶክተር እዮ ይባላል የስራ ቦታውም ሜክሲኮ ነው ብላ የቢዝነስ ካርድ አውጥታ ሰጠችኝ እኔም እሺ ዶክተር ሁሌ ነው የምወስዳት አልኩኝ ዶክተሯም አዎ ነገ ውሰዳት እና ከእሱጋር ትወስናላቹ አለችኝ እኔም እሺ ብያት ተነስቼ ልወጣ ስል ዶክተሯም አማን የምረዳቹ ነገር ካለ ዝግጁ ነኝ ጉዳዩን ህግ ስለያዘው አትጨነቁ አለችኝ እኔም አመስግኛት ወጣሁ፡፡
.................ሚስጥር እንደተኛች ነበር ወደታክሲ ያስገባናት እነአናንያ አብራዎት ነበር የተቀመጡት እሷን እላያቸው ላይ አስተኝተው እኔም በፍጥነት በዝምታ ውስጥ ሆኜ ታክሲውን አበረርኩት፡፡መንገዱ ዝግ ባለመሆኑ ቶሎ ነበር የደረስነው አእናቴም ቤቱን አዘጋጅታ ነበር ከታክሲው አቅፌ አወረድኳትና ብቻዋን እንዳትሆን ሳሎን ካለው ሶፋ ላይ አስተኝቼ ጋቢ አለበሰኳት እና ዶክተሯ የሰጠችኝን መድሀኒት መግዣ ወረቀት ለባርኮት እየሰጠሁት መግቢያው ጋር ካለ ፋርማሲ ገዝተህ ና አልኩት ባርኮትም ተነስቶ ወጣ አናንያ ለእናቴ እና ለአባቴ ስለዶክተሯ ቁንጅና እየተረከላቸው ነው፡፡እኔም ከሚስጥር ጎን መሬት ላይ ተቀምጬ እያየሗት ነበር፡፡ባርኮት መድሀኒት ገዝቶ መጣ እና ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው እኔም ልብሴን ልቀይር የራሴ መኝታ ቤት ተሳስቼ ገባሁኝ ለሚስጥር እንደሚሆን ሆኖ ተዘጋጅቷል በጥግ በኩል የኪዳነምህረት ስዕለ አድኖ አለ የመኝታ አምፖል ጋርም የፀሎት መፅሐፍ እና መፅሐፍ ቅዱስ ተደርድሮ ተቀምጧል አባዬ እንዳስቀመጠው ገባኝ አባቴ ነው ከእኛ ቤት በእግዚአብሔር ቃል የሚበረታ ሁላችንም ደካሞች ነን አናነብም እሱግን ይወዳል፡፡መኝታቤቴን ዘግቼ ወጣሁኝና የባርኮት ክፍል ገብቼ ቀየርኩኝ ያረኩትን ልብስ በሰማያዊ ቲሸርት በዳልቻ ቁምጣ ተክቼ ወጣሁኝ ሚስጥር እስከ ምሽት ድረስ አልተነሳችም ነበር የሰጧት ምንአልባት የእንቅልፍ መድሀኒት ይሆናል አልኩኝ ሁሉም አይኑን ሚስጥር ላይ አርጓል ለቤቱም አዲስ ናትና፡፡ እኔም እማዬ አልኳት እናቴ ግን ዝም አለች ሰምታ እንዳልሰማች ደግመን ልንጣላ ባልሆነ አልኩኝ ግን የሚመልስ ጠፋ ልብሴን ቀይሬ ስመጣ ሁሉም ተቀይሯል ሁፍፍፍፍ አሁንስ አልኩኝ እናቴም እኔን ነው ሁፍፍፍ በቃ የምትፈልገውን አረካ ምንም ንግግር አያስፈልግም ብላኝ ተነስታ ወደኩሽና ወጣች ምንድነው አልኩኝ ሄለንም ያናገርንህ እስክታመጣት ነው እንጂ ይቅር ብለንህ አይደለም አለችኝ ቆይ እኔ አይደለሁ የተጎዳሁት እናንተ ምን ጨነቃቹ አልኩኝ በብስጭት ሚስጥር ጩኸቴ አባነናት ..........ሚስጥር አልኩኝ ሚስጥርም ቤቱና ሰዉ አዲስ ሆኖባት በመንቀጥቀጥ ማየት ጀመረች እኔም ጠጋ ብዬ ተረጋጊ ተረጋጊ ቤትሽ.............ማልቀስ ጀመረች ተሰፈንጥራ ከሶፋው ላይ ተነሳች አባቴም ዊልቸሩን ወደእኛ ነድቶ የኔልጅ ብሎ ሊነካት እጁን ሲሰነዝር ወደእኔ ተጥግታ ተጣበቀች እና አስወጡኝ አስወጡኝ የቅድሙ ስሜታዊነቷ ተመለሰ እኔም አቅፌ ወደተዘጋጀው ክፍሏ ወሰድኳት እና አልጋ ላይ አስቀምጥኳት በጭንቀት ፀጉሯን እየነጨች ነበር እጇን ያስኩት እና አቅፌ አባበልኳት እንባዋ ደረቴላይ ሲፈስ ታወቀኝ...............
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
💜ክፍል ስድስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ💜

በቤዛዊት

👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch
@yebezawit2 👈
@yebezawit2 👈
@yebezawit2 👈
❤️❤️እውነታዬ❤️❤️
★★★★ሰዎችን ለመርዳት የግድ ገንዘብ አያስፈልግህም ምን አልባትም ያንተን ጊዜ እንክብካቤ ፍቅር❤️ ፈልገው ይሆናልና ገንዘብ የለኝም ብለህ ሌሎችን ላለመርዳት ምክንያት አትደርድር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ላንተ ትንሽ የምትመስልህ እርዳታ የሌላውን ሰው ህይወት የምትቀይር ልትሆን ትችላለች፡፡ነገር ግን ካለህ ላይ መስጠት ያቆምክ ቀን መኖርህ ያኔ ያከተማል!!....😍
........የተወደዳቹ የግጥም መንደር ቤተሰብ እና ጓደኞቼ ባለፉት ጊዜያት ነድያንን እና አዛውንቶችን ለመርዳት መንቀሳቀሳችን ይታወሳል አሁን ላይ ደግሞ #ለሕግ_ታራሚዎች መፅሐፍ በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ መፅሐፍ ማበረከት የምትፈልጉ የቀና ልብእናሀሳብ ባለቤቶች ያነበባቹትን መፅሐፍ በማስረከብ ውጪው የናፈቃቸውን በፀፀት ያሉትን ወጎኖቻችንን እንጠይቅ፡፡🙏

"ለራሳችን የምናደረገው ሁሉ ከእኛ ጋር አብሮ ወደ መቃብር ሲወርድ፤ ለሌሎች የምናደረገውና ለዚህች አለም የምናበረክተው ነገር ግን #ዘላለማዊ ነው፡፡" በሚል መሪ ቃል አብረን እንስራ፡፡

@yebezawit2 ላይ ያናግሩን

+251983744901 ይደውሉ🙏

የግጥም መንደር
አንድ መፅሐፍ ለወዳጆ
ሼር በማረግ ያግዙን 🙏☝️
🌹ብጨክንም ትናፍቂኛለሽ😒

ጨክኜ እንለይ ብዬ ብነግርሽ
ዳግም ላንገናኝ ለዘላለም ብለይሽ
ውዴ ምንም ብጨክን እውነት ልንገርሽ
....ትርጉም ያለው ውብ ጨዋታሽ
ነፃነት ያለው ደስ የሚለው እብደትሽ
ሰበብ ፈልጎ ስቆ የሚያስቀኝ ጥርስሽ
አልዋሽም በማንም እንደማልተካው
አንቺ ጋር እንጂ የትም እንደማላገኘው፡፡
ብቻ ብዙ ነው ስለአንቺ ካወራሁኝ
ግን ደግሞ እውነቱን እወቂልኝ
አፈቀርኩሽ ማለቱ ከብዶኝ
ወደድኩሽ ማለት ቃላት ቸግሮኝ
ወይ አንቺ አልተረዳሽ ጭንቀቴን
አልፈታሽው ትርጉም ያለውን ዝምታዬን
ማፍቀርሽን ለማረጋገጥ ባልታደልም
አፈቀርኩሽ ብዬ ከማስከፋሽም
ልራቅ ከአንቺ መጥፎ ሰውነኝ ብዬሽ

#ውዴ_ብጨክንም_ትናፍቂኛለሽ

ቤዛዊትየሴትልጅ

26/11/2011

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

@Yebezawit2
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
💙አንቺ የሌለሽ ጊዜ 💜
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
ክፍል ስድስት
......ከደረቴ ላይ ቀና ብላ ይገሉናል አለችኝ፡፡ አስደነገጠችኝ እሷ በትላንት ጊዜ ዛሬን እየቆጠረች መሆኗ ገባኝ እንማን አልኳት አዎ ሊገሉን ነው ይገሉኛል አይፈልጉኝም ብላ እያለቀሰች ከደረቴ ተሸጎጠች ላስጨንቃት አልፈለኩም አንድ የሚያስፈራት ነገር እንዳለ እርግጥ ነው ዶክተሯ ልክ ናት አልኩኝ ፀጉሯን እየዳበስኩኝ እኔ አለው እሺ አሁን ተረጋጊ አልኳት በዚህ መሐል የመኝታ ቤቱ በር ሲንኳኳ ከስሬ ወጣችና መጡ..መጡ አለችና የምትገባበት ጠፋት መደነገጧ በእኔ ላይም አስተጋብቶ ደነገጥኩኝ ማነው አልኩኝ ቡርቴ ነበረች አማን እራት አምጥቼ ነው አለች እኔም ተነስቼ በሩን ልከፍት ስል ሚስጥር እግሬ ላይ ተደፍታ ተማፀነችኝ እኔም ቡርቴ እሱጋር አስቀምጪውና ሂጂ አልኳት እሷም ምግቡን መሬት ላይ አስቀምጣ ተመለሰች ሚስጥርን እንደምንም አሳምኛት በሩን ከፍቼ ምግቡን ወሰድኩኝ፡፡ አልጋው ላይ ተመልሳ ተቀምጣ በጭንቀት እጇን በእጇ እያሸች አየሗት ትበያለሽ አልኳት ፊቷ ምግቡን እያስቀመጥኩ ሚስጥርም በዝምታ ምግቡን ቶሎቶሎ አጨማልቃ መብላት ጀመረች ዘገነነኝ ምግብ ስበላ ወጥ ከነካኝ ያስጠላኛል የእሷግን በተቃራኒ ነበር ልታጎርሰኝ እጇን ሰነዘረችልኝ የበላሁትን ሳይሆን ያልበላሁትን ሊያስመልሰኝ ነው አይ ብይ አንቺ አልኳት እሷ ግን በእብደቷ ውስጥ ድርቀት እየታየባት አይሆንም እንካ ብላ ይጥማል አለችኝ እንደማትሰማኝ ገባኝ እና አፌን ከፈትኩላት አጨማልቃ አጎረሰችኝ በግድ ፊትለፊቴ በነበረው ውሃ እወራረድኩ፡፡የተሰራው ምስር ወጥ ሌላ ነገር መስሏል በልታ ልጨርስ ነው ስትል ሁለተኛ ጉርሻ ዘረጋችልኝ ጥያት ብጠፋ አልኩኝ፡፡ ብላ ጉረስ አለችኝ የህፃን ጭንቅላት የሚያክል ጉርሻ ይዛ ምርጫ የለኝም እንድትድን ይሄ ትንሹ ትዕዛዟ ይሆናል ብዬ ተቀበልኳት አፌን ወጥበወጥ አርጋ አጎረሰችኝ እና እጇን ልብሷ ላይ ልጠርግ ስትል ያዝኳት ምን ሆንክ አለችኝ አይኖቿን አፍጥጣ ከመፅሐፍ ቅዱሱ አጠገብ ሶፍት አንስቼ እጇን ጠረኩላት በረጅሙ ሳቀች ጩኸቷ አልኩኝ ለራሴ ጉንጯ ሳይቀር በወጥ ተለውሷል እሱንም ጠረኩላት እና መጣሁ ውሃ ይዤ ብያት ሳህኑን እና ብርጭቆውን ይዤ ወጣሁኝ ወደሳሎን ስሄድ ሁሉም ተሰብስቦ እያወሩ ነበር በሽተኛህ በላች የእማዬ ቃል አንገፈገፈኝ አይባለም አላት አባዬ እኔም በዝምታ ወደኩሽናው ገባሁኝ ቡርቴ ቡና እየፈጨች ነበር ሳህኑን መታጠቢያ ሲንኩ ላይ አርጌላት ውሃ ቀድቼ ወጣሁኝ በነገር ከዚህ በሗላ መጎሸም አይቀርም ይሄ ገብቶኛል ለሚስጥር ስል ግን በዝምታ ማለፍ አለብኝእና አንገቴን ደፍቼ ወደመኝታ ቤቴ አቀናሁ የቀረበ ጩኸት ተሰማኝ ሚስጥር ናት በሩን በርግጄ ስገባ ክፍሉ አይሆኑ ሆኖ ተመሰቃቅሏል ዝብርቅርቅ አለብኝ አሁንበአሁን ምንሆነች???ለራሴ ጠየኩት ከአንዱ ጥግ ጋር ተሸሽጋ ቆማ ታወራለች ብርጭቆውን አስቀምጬ ሄጄ አፏን አፈንኳት እጄም አፍኗት ትለፈልፋለች አልጋ ላይ አስቀምጥኳት እንደህፃን ስታየኝ በሳቅ ደከመች አብደሀል አንተ ልጅ አለችኝ ጥያቄዋ ከልቤ አሳቀኝ ለራሴ ሳቄን ወደድኩት ድጋሜ ተያይተን ሳቅን ያዘበራረቀችውን ቦታ ቦታ መልሼ መድሀኒቷን ሰጠሗት እና በተኛችበት መፅሐፍ ቅዱስ አነብላት ጀመር ካነበብኩ አመታት አልፈዋል አይ ጉዴ አልኩ ለራሴ ሚስጥር እየሳቀች ነበር የምትሰማኝ ብዙም ሳትቆይ ግን እንቅልፍ ወሰዳት አይኖቿ ተከደኑ "ምን አይነት እብድ ናት?" እያልኩ መፅሐፉን አስቀምጬ ከመኝታ ቤቷ ቀስ ብዬ ወጣሁኝ፡፡በሩን ዘግቼ ትንሽ ከቆምኩ በሗላ ወደ ባርኮት ክፍል ገብቼ በጀርባዬ ተኛሁ፡፡
************አትንኩኝ አትንኩኝ ...አስወጡኝ በቃ ልቀቁኝ!!!!ጩኸት ያለው ድምፅ ከእንቅልፌ አባነነኝ ሚስጥር ብዬ ተስፈንጥሬ የመኝታቤቱን በር ከፍቼ ወደሚስጥር ክፍል ገባሁ ማንም የለም ዞር ስል እማዬ ፊቴ ተደንቅራ ነበር የት ሄደች አልኳት በአግራሞት እያየችኝ እያበደች ወጣች አለችኝ፡፡....ምን ወዴት ብዬ ጥያት ወደውጪ ወጣሁኝ እኩለሊት መሆኑ ያሳብቃል ጨረቃዋ ከኮከቦች ጋር ደምቀዋል የለሊቱ ንፋስ አስፈሪ ሆነብኝ ሚስጥር ብዬ ተጣራው የግቢውም በር ተከፍቷል ዘልዬ ወጣሁኝ አንሶላ እየጎተተች ስትሮጥ አየሗት እየሮጥኩ ተከትዬ ያዝኳት ድንጋጤው እና ብርዱ እያንቀጠቀጣት ነው ዶሮ ጫጬቷን እንደምታቅፈው በሰፊው ደረቴ ላይ እቅፍ አረኳት እና አይዞሽ አልኳት እና አቅፌ ወደቤት ግቢ አስገብቻት በሩን ዘጋሁትና ክፍሏ ልወስዳት ስል እምቢ አለች እኔም እዚህ ትሆኛለሽ አልኳት ሚስጥርም አዎ ብላ አቀፈችኝ፡፡ በረንዳው ላይ ያዘችውን አንሶላ አብረን ለብሰን ተቀመጥን ሚስጥር አልኳት በክንዴ እያቀፍኳት ........ሚስጥር አይደለም ስሜ ብላ ተቆጣች እኔም እሺ ስምሽ ማነው አልኳት እሷም ሚስጥር አለችኝ ፈገግ አልኩ እና እሺ በቃ ተኚ አልኳት፡፡ ሚስጥርም መዝፈን ትችላለህ አለችኝ እኔም አልችልም ግን እሰማለሁ አልኳት ሚስጥርም እግሬ ላይ እየተኛች እኔ ግን እዘፍናለሁ ከማለቷ....አማን የሚል ድምፅ ሰማሁ እማዬ ናት ውይ አምላኬ አስቸልኝ ከማለቴ ሚስጥር በጩኸት ሂጂልኝ እያለች ጮኸችባት እኔም ሚስጥር ይዣት ተረጋጊ እናቴ እኮ ናት አልኳት ዝም አለች በረንዳው ላይ አስቀምጫት እናቴ ጋር ሄድኩኝ አቤት አልኳት እናቴም ትሰማኛለህ በቤቴ ማረፍ እፈልጋለሁ አባትህ ታማሚ ነው ታውቃለህ አለችኝ እኔም ታማሚ አይደለም አካል ጉዳተኛ እንጂ እሷ እኮ ፈልጋ አይደለም እረብሻውን አልኳት ውስጤ የቁጣ ነበልባል እየተቀጣጠለ..........
ምንም አይመለከተኝም ስትፈልግ መልሳት አለችኝ በጭካኔ እኔም እማዬ ስለፈጠረሽ ትንሽ ጊዜ ብቻ ስጭኝ አልኳት እማዬም ለማንኛውም እንቅልፌን አታሳጠኝ ብላ ጥላኝ ሄደች በአንድ ለሊት ይሄ ሁላ ችግር ብዬ ወደሚስጥር ጋር ተመለስኩ ያየሗት ጊዜ እንደነበረችው ጨረቃን እያወራች ነበር አንዴ ትስቃለች ታለቅሳለች ከሗላዋ ሆኜ ዝም አልኳት እና ተቀመጥኩ አውርታ እንደጨረሰች እዛው ተደፍታ ተኛች አሳዘነችኝ ተኮማትራ ላያት ሆድ ታስብሳለች እኔ እመጣለሁ እንዳልኳት ረስታዋለች እኔም ብርድ ላይ በዛ ስስ ቲሸርትና ቁምጣ ተኛሁ መንጋቱን ያወኩት ሚስጥር ተነስታ ስታወራ ነው፡፡በስመአብ....ብዬ አይኖቼን በግድ ገልጬ አየሗት ግቢ ውስጥ ያለውን ሳር እየነቀለች ነው እናቴ ካየቻት ትገላታለች ቶሎ ብዬ ተነስቼ አስቆምኳት ሚስጥርም የያዘችውን ሳትለቅ ሄዱ እኮ አለችኝ እንማን ስላት እየሳቀች አየችኝ ሳቋ ያስቀኛል እንደ ልጅ ቧንቧ ጋር ወስጄ ፊቷን እና እጇን አጠብኳት እና እኔ ልታጠብ ስል እጄን ያዘችኝ ቀናብዬ አየሗት እኔነኝ የማጥብህ አለች በትዕዛዝ እጄን መለስኩት ረጃጅም ጣቶቿን አጥፋ ውሃ አቆረችበትና ፊቴን አራሰችኝ ዝም ብዬ አየሗት ፊቴን በውሃ አርሳ እጄንም አጠበችና በቃ ንፁህ ሆንን አለችኝ የልብ ንፅህናዋ እንደሚበልጥ አልገባትም፡፡

............እያወራን ወደ ሳሎን ገብተን መመገቢያ ጠረጴዛው ጋር ወንበር ስበን ተቀመጥን አባዬ ዊልቸሩን እየገፋ ሲመጣ የሚስጥር እጆች መፋተግ ጀመሩ መጨነቋ ያስታውቃል አባቴ ነው አልኳት ጭንቀቷ ከቀለለ ብዬ በዝምታ ፈዛ አየችው አባቴም ከእሷ ጎን ዊልቸሩን አቆመ አባዬን ተከትለው ሁሉም ተሰበሰቡ ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ዶክተር እዩ ጋር ልወስዳት ነው እሱንም እያሰብኩ ነው፡፡ ብርቴ ሻይ ቀድታልን ወጣች እኔም ሳህን አንስቼ እንጀራውን ዘረጋሁ እና ወጡን ጨምሬ ለሚስጥር ሰጠሗት እነእማዬ ዳቦ በማርማራታ እየበሉ ነበር አባዬ ደግሞ እንጀራ ሚስጥር ዝም ብላ እንጀራውን ጠቅልላ አስቀያሚ ጉርሻዋን ለአ
ባዬ ሰነዘረችለት አባዬ ግን እንደእኔ እንቢ አላለም ጎረሳላት ፈርቼ ነበር ሚስጥርም ለአባዬ ደገመችው አባዬም አጎረሳት ደስ አላት በጣም በስሟ ደሴት የተሰየመ ያህል ነበር ደስታ ከፊቷ የሚነበበው እኔም ሻይ ብቻ ጠጣሁና ሚስጥር ልብስ ቀይረን የሆነ ቦታ እንሒድ አልኳት እሷም በደስታ ተነሳች እኔም እጇን ልብሷ ላይ እንዳትጠርግ ወደኩሽና ወስጄ አጥብያት ወደክፍሏ አስገብቼ እነእማዬ ያስቀመጡትን ልብስ አንስቼ ሰጠሗት እሷም ተቀብላኝ በለበሰችው ልብስ ላይ ለመልበስ መታገል ጀመረች ወይ ጉዴ ልብስም እያልኩ ....ያለኝ ምርጫ መቀየር ነውና ልብሷን ቀይሬላት ሳሎን ወሰድኳት ሶፋ ላይ አስቀምጬ ልብሴን ልቀይር ወደክፍሌ ገባሁ ልብሴን ቀይሬ ስወጣ እዛው ተቀምጣ ነበር ተመስገን ብዬ ነይ ሚስጥር ስላት ደስ ብሏት ተነሳችና ተከተለችኝ ቀጠል አርጋም ቆይ መጣሁ ብላ ሁሉንም ሳመቻቸው እማዬ ተፀየፈቻት ወንድሞቼ ግን በፈገግታ ነበር የሚያዯት ሄሉም አቅፋ ሳመቻት ሜሪ ግን ዘገነናት አባዬንም እቅፍ አርጋ ስማ ተመለሳ ወደእኔ መጥታ እጄን ያዘችኝ እኔም ግቢውስጥ ያቆምኳትን ታክሲዬን በር ከፍቼ አስገባሗት ውስጤን አንድ የማላውቀው ስሜት እየተሰማኝ ነው ደስ የሚል እና የሚያሳዝን ነው፡፡.......ምን ይሆን ምክንያቱ እኔም አላውቅም የታክሲውን ሞተር አስነስቼ ወደ ዶክተር እዩ ጋር መንዳት ጀመርኩኝ ሚስጥርም መንገዱ ንፋሱ አዲስ ሆኖባታል........ደነገጥኩኝ አይሆንም አማን ብዬ መኪናውን አቆምኩት ሚስጥር ደንግጣ ታየኛለች መድሃኒቷን ሳልሰጣት ነው ይዣት የወጣሁት ራሴ ላይ እየተበሳጨው ወደ ቤት ተመለስን ቤት ስንመለስ ግን ያላሰብኩት ተፈጠረ...........


ምን ይሆን ክፍል ሰባት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ፡፡
👍ከወደዱት
👎ካልወደዱት

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
ሼር በማረግ ወዳጆን ይጋብዙ
💝አንቺ የሌለሽ ጊዜ💝

@yebezigetmoch
@Yebezigetmoch
@Yebezawit2
💓ይቀጥላል💓
የተቆለፈበት ቁልፍ.pdf
12.4 MB
@Yebezigetmoch
በዚህ ክረምት ሊያነቡት የሚገባ የዶክተር ምህረት ደበበ መፅሐፍ📚
የማንን ይፈልጋሉ??
@yebezawit2 ላይ ያድርሱን
ውድ የግጥም መንደር ቤተሰቦች እንዴት አላቹልን???
❤️በቅርቡ በጀመርነው ለሕግ ታራሚዎች መፅሐፍ የመሰብሰብ ፕሮጋራም ከአብዛኞቻቹ ቀና እና እጅግ ደስ የሚል መልስ በማግኘታችን እያመሰገንኩ🙏
📚መፅሐፎቹን ለመለገስ በምትፈልጉበት አንድ ቀን ቀደም ብላቹ
በ0983744901 ቤዛዊት
በ0966796259 ሔኖክ
በ0921661616 አቡሽ
በመደወል ያሳውቁን ያሉበት ድረስ በመጥጣት እንረከባለን📓

😍 ካለን ላይ መስጠት ያቆምን ቀን መኖራችን ያከትማል😍

ሼር በማረግ ሐሳብ በመስጠት በማስባበር አብረን በመልካም ልቦች ጎዳና እንጓ፡፡
@yebezigetmoch
@yebezawit2
@yebezawit2
🙏ለምትተባበሩን በእጅጉ እናመሰግናለን፡፡ ጋዜጠኛ ነቢል ከልብ እናመሰግናለን🙏
🌸ከሐገር ውጪ ያላቹም ልትደግፉም የምትፈልጉ በ imo ላይ ያናግሩን፡፡🙏💐
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥀አንቺ የሌለሽ ጊዜ🌗
ክፍል ሰባት
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
..............ሚስጥር የታክሲውን በር ከፍታ ተወረወረች መኪናውን እንዴት እንዳቆምኩት አላውቅም ሚስጥር እዛው በፊት ለፊቷ ተደፍታለች ሰውነቴ ሲቀዘቅዝ ታወቀኝ ልሞት መሰለኝ ለነገሩ ሞት በስንት ጣዕሙ ሄጄ አነሳሗት በአፍንጫዋ የሚፈሰው ደም ከአፏ ጋር ከሚወጣው ደም ጋር ተቀላቅሎ የደም ኩሬ ሊሰራ ነው የሚሄድበት ጠፋኝ መድሀኒቷን አለመውሰዷ መሆኑን ገባኝ የወደቀችው አጉል ቦታ ነው ምነው አስበሽ ብትወድቂ አልኩኝ እና ታክሲ ውስጥ አስገብቻት ወደተላክንበት ዶክተር ጋር ይዣት ሄድኩኝ አቅፊያት ወደ ቢሮው ስገባ የታክሲ እስፖኪዮ መስታወት የሚያክል አጉሊ መነፅር እንደ ስልክ እንጨት የተገተረው አፍንጫዋ ላይ አድርጋ ኮምፒተሯ ላይ አፍጥጣ ቃሉትን እየጠነቆለች ነበር ዶክተር አለ አልኳት በጩኸት ዶክተሩ በሩን ከፍቶ ወጣ እና ሚስጥርን ሲያያት አስገባት አለኝ በሩን ለቆልኝ እኔ ብዙ መፅሐፍ ከተደረደረበት መደርደሪያ ፊት ከተዘረጋ አልጋ ላይ በጀርባዋ አስተኛሗት ዶክተሩ ግን አስነስቶ አስቀመጣት እና ከጭንቅላቷ ወጣ እንድትል አረጋት ፀሐፊዋ መጥታ የሆነ ጨርቅ ነገር በክንዷ ላይ ጠቅልላ በአነስተኛ ቦርጫም ቲቪ ነገር ቁጥር ማየት ጀመረች ዶክተሩም ምን ሆና ነው አለኝ እኔም ዶክተር ናት ወደአንተ የላከችኝ እእእ ስሟን ጠፋኝ ወይኔ አልኩኝ ዶክተሩም ኦ ከአማኑኤል ነዋ አለኝ እኔም አዎ አልኩኝ በፍጥነት በማስታወሱ አስገርሞኝ ፀሐፊዋም ግሉኮስ አምጥታ ለዶክተሩ ሰጠችውና ተቀጠለላት፡፡ነስሩ ሲቆም ጠራርገዋት አስተኟት ግን አይኗን እንደከደነች መሆኑ ውስጤ ፈርቷል፡፡ዶክተሩም ተቀመጥ አለኝ የእጁን ጓንት በቄንጥ እያወጣ ወይ አብዝቶ መማር አልኩኝ ለራሴ ከጠረጴዛው ፊት ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ ዶክተሩም ተሽከርካሪ ወንበሩ ላይ ስቦ ተቀመጠና ለምን እንደዚህ ሆነች አለኝ ተሳሳትኩ እንዴ ለራሴ አጠያየቁ የፖሊስ ቢሆንብኝ እኔም መድሐኒት ሳልሰጣት ረስቼ ነበር እና ስንመለስ ራሷን ወረወረች አልኩት ጠያቄውን ቀጠለ እንዴት ምን ላይ ወደቀች ስትወድቅ ወዲያው ነው ራሷን የሳተችው.............አሁን ገባኝ ዶክተር ፖሊስ ነው አልኩኝ አምላኬ አሁን ምን ላይ ይወደቃል ኮብል ላይ ነው እሱም በጥድፊያ ተሰርቶ ፋሽኑ አልፎበት በሰበብ ባስባብ እንቆፍራለን***********በቦታው አልነበርክም እንዴ አለኝ ለመልሱ መዘግየቴን ለማሳወቅ በብሰጭት ነበርኩ በፊትለፊት ነው የወደቀችው ኮብል ላይ ነው ወዲያው ራሷን ሳተች አልኩት አሁን ከዚህ ጋር ነው አማን የምትዘልቀው ተነስቼ ግንባሩን ባልኩት አልኩኝ ደረቅ ወይ ፈገግታ የለው************ያስጠላኝ ጥያቄው ቀጠለ ምኗ ነህ?? ለራሴም የማላውቀው ጥያቄ እራሱ ቢመልስልኝ የሚሰማኝን ደስታ ብነግረው በታደልኩ................."የሉም እዚህ የሉም ወንድሜ ነው ድምፁን ሰማሁት ዋይይይይይይይይይይይይይይይይ" እንደ መብረቅ ጮሀ ተነሳች ሚስጥር አልኳት እና ሄጄ አቀፍኳት ዶክተሩም እስኪ አየር እንዳታጣ ተዋት ብሎ እንድትተኛ አረጋት ትዕግስቴን እየፈተነው በማያገባው እኔ አሁን በርሜል አይደለሁ አላፍናት ኧረ ዶክተር ጠላሁ አልኩኝ ........................................እንደምንም ጥያቄዎቹን መልሼ ሚስጥርን እንዲያናግራት ትቼው ወጣሁ እና ፀሐፊዋ ጋር እያንጎራጎርኩ ተቀመጥኩ ወይ ጉድ አልኩኝ በልቤ፡፡

ውጪ ከወጣሁ ብዙም ሳልቆይ ሚስጥር ዘላ ወጣች እያለቀሰች አስደነገጠችኝ የሚስጥር እንባዎች ከእናቴ የሚወጡ ያህል ያመኛል ተወርውራ አቀፈቸኝ እና ውሰደኝ አለችኝ እንደ ኑግ የጠቆረውን ፀጉሯን እያሻሸው እሺ እወስድሻለሁ እንሔዳለን አልኳት በር ላይ የቆመውን ዶክተር በአግራሞት እያየሁት ወንበሩ ላይ አስቀምጫት ዶክተሩ ጋር ሄድኩኝ በጣም በመንቀባረር በጣም የቤት ስራ ይጠይቃል አለኝ እኔም በዝምታ የቀጠሮ ቀኑን ተቀብዬ ከዛ ወጣን ሚስጥርም መኪና ጋር ስንደርስ "አንተ እብድ አለችኝ" እብድ መሆን የተምታታባት እብድ እያልኩ "አቤት ምን ፈለከሽ አልኳት" ወድቃ ስተነሳ ነቃ ማለቷ እየደነቀኝ በእግር እንሒድ አለችኝ እኔም ፈገግ አልኩና በሗላ እንሔዳለን አሁን ግን ቤት እንዳርስ መኪናችንን አልኳት እንደ ልጅ በቶሎ ተስማማች፡፡ ወደ መኪና ገብተን ሙዚቃ በስሱ ከፍቼ ነበር እሷም ቤልቷን አስሬላት ሙዚቃውን በተመስጦ እየሰማች ነበር የሙሉቀን ዘፈን ልክ እንዳለቀ የጎሳዬ ዘፈን ጀመረ የሚስጥር ፊት ከሙዚቃው ጋር አብሮ ተቀየረ እኔ የጎሳዬ አፍቃሪ ነኝ
..እንዴት አርጎሻል አንቺስ ናፍቆቱ
አይታይሽም ወይ አብሮ መብላቱ
ጤንነት አጣሁ ደስታ እንደ ጥንቱ..

ሚስጥር ጭንቅላቷን ይዛ አጥፋው አለችኝ እንደጅረት የሚወረደው እንባዋ ጉንጯን እያራሰ ሙዚቃውን አጠፋሁት ምን ሆንሽ ሚስጥር ምንድነው አልኳት መኪናውን ከአንድ ጥግ ጋር አቁሜ እንባዋ ያለማቋረጥ እየወረደ ከአፍንጫዋ የሚወጣውን ቀጭን ፈሳሽ እየናፈጠች አንገቷን ወደ መሬት አቀርቅራ....የዛን ቀን ማታ ይሄ ዘፈን ነበር አለችኝ፡፡"መቼ ነው ሚስጥር የትኛው ቀን" አልኳት ሚስጥርም የተደፈርኩ ቀን እዬዬ አለች ጉልበቷ ላይ ተደፍታ ይህቺ ልጅ ለስንተኛ ጊዜ ነው የደፈሯት ለራሴ ጠየቁት ከጉልበቷ ቀና አለችና ሳልጠይቃት ታሪኳን በእንባ እየታጀበች ማውራት ጀመረች.........እኔ ያደኩት ከእናቴ ጋር ነበር እና እናቴ ከጊዜ በሗላ አያትሽ የወሰደችው ወንድምሽ ነው ብላ ከአባቴ ጋር ይዛው ቤት አምጥታ አስተዋወቀችኝ የዛኔ የ8ልጅ ነበርኩ እሱ ደግሞ 13 አመቱ ነበር እና ደስ አለኝ ቤተሰቦቼ ሀብታም ናቸው ያሉት ወደ ቦሌ ሚካኤል ናቸው.........ራሷን ሳተች ደነገጥኩኝ እና መስኮቱን ከፍቼ ውሐ ማርከፍከፍ ጀመርኩ ምን እንደሚደረግ ባላውቅም ክሊኒክ ወስጄ ይባስ ከማስጨንቃት ብዬ እያራገብኩ ቆየው ከደቂቃ በሗላ ቀስ ብላ ቀና አለች ከተኛችበት እኔም ደህና ነሽ አልኳት እሷም አዎ ደህና ነኝ አለችኝ በመመርመር አይን እያየችኝ እኔም በቃ ቤት እንሒድ እና እረፍት ታረጊያለሽ አልኳት እሷም በአውንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡እኔም መኪናዬን በፍጥነት እያሽከረከርኩ ቤት ደረስን የግቢውን በር ቡርቴ ከፍታልን ገባን እና የመኪናውን ሞተር አጥፍቼ ቀበቶውን ሰፈታ " እባክህን የኔ የግሌ ሚስጥር ነው" አለችኝ እጄን ይዛ እኔም እጇን በእጄ ይዤ መቼም እንዳትሰጊ አልኳት ሚስጥርም አምንሐለው አለችኝ እኔም ቆይ አትውረጂ እኔ አስገባሻለሁ አልኳትና ከመኪናው ወርጄ አቅፌ አወረድኳት ሚስጥርም ደና ነኝ አውርደኝ አለችኝ እኔም አወረድኳት ቀስ ብላ ተራምዳ የቤቱን በር ከፍታ ገባች፡፡ እቤት ውስጥ ወንድሞቼ ብቻ ናቸው ደህና ዋላቹ አለቻቸው አናንያም ዋልን ዋልሽልን አላት እሷም ውያለሁ ብላ መሐላቸው ገብታ ተቀላቀለች ቆሜ አየሗት እና ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ የባርኮት ክፍል ለጊዜው የእኔ ስለሆነ ገብቼ አልጋው ጫፍ ተቀመጥኩኝ ይሄ ሚስጢር ምንድነው?? ለምን ይጨንቃታል ?? ለራሴ ብዙ ጥያቄዎች ተደረደሩብኝ የሀሳብ ሸማዬን እየሸመንኩ በሐሳብ የመኝታ ቤቱ በር በሐይል ተንኳኳ.............

❤️ክፍል ስምንት ይቀጥላል❤️
ደራሲ ቤዛዊት

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ

ከወደዱት 👍

ካልወደዱት👎
ድምፅ በመስጠት አብሮነታቹን አሳዩን‼️
💐የግጥም መንደር 💐
@yebezigetmoch
@yebezawit2
❤️የተወደዳቹ የመልካም ልብ ባለቤት እና የውድ ሐገር የኢትዮጵያ ልጆች በጀመርነው ለሕግ ታራሚዎች የመፅሐፍ ማሰባሰብ ፕሮግራም በዛሬው እለት የቀና ልብ ባለቤት ከሆነው ከአቶ ፍቃዱ 70 መፅሔቶችን እንዲሁም ከአንድ ቸር ለጋሻችን አንድ መፅሐፍ ተረክበናል💐🙏
❤️ላበረከታቹልን መፅሐፍ ቀና አመለካከታቹ ከልብ #እያመሰገንን
በመልካም ልብ መለገስ የምትፈልጉ 👇👇👇
0983744901 ቤዛዊት
0966796259 ሔኖክ
0921661616 አቡሽ
👆👆👆 በለው ይደውሉልን ካሉበት ድረስ መጥተን እንረከባለን‼️


💯💯ካለን ላይ መስጠት ያቆምን ቀን መኖራችን ያከትማል‼️‼️

በመልካም ልብ ወደፊት ብዙ ተጉዘን ሰው የለንም ተረስተናል ላሉ ወገኖቻችን የተስፋ #ፀሐይ በመሆን ነገን አሻገረን እናሳያቸው!
🌹🌹ሰናይ ምሽት🌹🌹
@yebezawit2

@yebezigetmoch