የግጥም መንደር
1.71K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
ፅናት ወዳንቺ የሚወስደኝ ከሆነ እስኪበቃሽ ድረስ ፀንቼ ጠብቅሻለው ።💔😔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስህተት የ5ብር ካርድ ወደ ስልኬ ልከው
ማንም ሳይጠይቀኝ ለባለቤቱ መልሻለሁ 😁😋
ህይወት ሁሉ ጊዜ ሁለት አማራጭ አላት አንዱ
ምን አባሽ ብሎ ጥሎሽ ሲሄድ አንዱ ደሞ ምን
አባቴ ልሆንልሽ ምን ጎደለብሽ ብሎ ይመጣል ..
"ደስታ በዙሪያህ የምትጠብቀው ነገር አይደለም,
አንተ ራስህ የምትፈጥረው ነገር ነው."
@yebezigetmoch 😍
join 💗
?❤️‍🩹 መድኃኒት❤️‍🩹🥹

ክፍል ፩

በቤዛዊት የሴት ልጅ

የስልኩ ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ ተናደድኩ...... ያቋረጡኝ ምን ከመሰለ ህልም ነበር። የህይወቴ የመጨረሻዋ ስኬቴ ናት አምላኬ እሷን የሰጠኝ ዕለት እውነት በዓለም ላይ ሾሞኛል ማለት ነው። "ባሮክ ባሮክ" ጩኸቷማ እህቴ ነበረች ወደ ቆጡ መውጫ መሰላል ላይ ሆና የምትጠራኝ። "ተነስ ኧረ እንዳትበቅል" አለችኝ። ብበቅል ደስ ባለኝ እሷን እያሰብኩ ጥርሴ ቢረግፍ ጸጉሬ ቢሸብት አልኮነንም ነበር።

እንደ ምንም ተነስቼ ወረድኩኝ። ምሳ ቀርቧል የእህቴ ቆንጆ ሽሮ እንጀራው ላይ ራስ ሆኖ ይታያል ተጣጥቤ ከማዕዱ ተቋድሼ ወደ ጓደኛዬጋር ሄድኩኝ።
ባሮክ እባላለሁ በኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ከተመረኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል እንደማንኛውም ወጣት የመንግስት ስራ ባይኖርኝም ለራሴ ባመስነፍ ከአንድ ሞል ላይ አንዲት ልጅ ቀጥሬ ቡና ጠጡ እየሰራሁ ነው። አብሮ አደጌም ሳሚም የራሱ የስፖርት ቤት ከፍቶ እየሰራ የሚገኝ የቅባት ልጅ ነው። ከሁለተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ተምረን ያደግን ልጆች ነን። አሁንም ወደ እሱ ነው የምሄደው። ገና ስደርስ ሽሮ በልቶ የሚያድረው ህዝቤ ይሄን ብረት እየገፋ ነበር የተጨማደደ ፊቴን ፈገግ አድርጌ ወደ ሳሚ ቢሮ ገባሁ።
"እ ብሮ ቆየህ እኮ" ገና እንዳየኝ ሳሚ ተናገረ።
"ምን ከመሰለ ህልም ላይ እንደተነሳሁ ብታውቅ እንዲህ ባላልክ" አልኩት ሰላም ብዬው እየተቀመጥኩ።
"ቅዠታም ደግሞ አገረሸብህ" አለኝ ፋይሉን እየከተተ።
"የምሬን ሳም በአሁኑ እኮ ሳገባት ነው ያየኋት" አልኩት ውስጤ ያለውን ደስታ ከፊቴ እያስነበብኩት።
"ቆይ ለምን ሱባኤ አትይዝላትም እንዴ ተቆጣጠረችህ እኮ" አለኝ የባከንኩ የመሰለው አብሮ አደጌ።
"ሳምዬ ብትቆጣጠረኝማ እየበተነ ያለው በረከቴ በሰበሰብኩት የተዘጋው በሬ በተከፈተልኝ እውነት እንዴት ውብ ሆና ስታየኝ እንደነበር በተለይ የምወደው ጥርሷ ብልጭ አድርጋ ስታሳየኝ እኮ....." አቋረጠኝ።
"ተነስ ባክህ እንሂድ" አለኝ። ተናደድኩ ተኮሳትሬ ቀድሜው ወጣሁኝ። መኪና ውስጥ እየሄድን ዝም አልኩኝ ዕቃቃውን እንደተቀማ ህፃን እጄን አጣምሬ በመስኮቱ ወደ ውጪ እያየሁ ነበር እንደማላወራው የተረዳው ሳሚ ሙዚቃውን ከፈተው።

🎧🎧🎧🎧🎧
ኤፍሬም እኔን የጠየቀኝ ይመስል ስለ ውበቷ የዘፈነልኝ የሚመስለኝን የምወደውን ሙዚቃ ነበር
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶

ዞሬ አየሁት እና ፈገግታዬን ሰጠሁት። "ኧረ ወንድሜ ለአንተ ብዬ ነው አልነገርካት ነገር ልጅቷ በየት ትወቀው ሁሌ እየተያዩ መሳቅ በአይን መሸኛኘት ይጎዳሃል። በህልምህ አትቃዥ ንገራት" አለኝ አፍ ሆኖ የሚነግርልኝ ይመስል። እኔም ሌላ ክርክር ውስጥ ላለመግባት የወሬውን ርዕስ አስቀይሬ ስለ ምንሄድበት ስራ ማውራት ጀመርኩ። ከደቂቃዎች በኋላም የምንገባበት ህንጻ ጋር ደርሰን መኪናውን ፓርክ እያደረግን እኔም ሳሚም የደነገጥነው። ህልሜ ናት......

ክፍል ፪ይቀጥላል

❤️‍🩹🥹መድኃኒት አዲስ ተከታታይ ታሪክ ❤️‍🩹🥹

በማንበብ አስተያየት ስጡ ወዳጆቻችሁን ጋብዙ!
https://t.me/yebezigetmoch
መስዋዕት ሁኚ


ሴት አይደለሽ ነይ ወደ ወደፊት
ትማሪ ዘንድ ስለ መስዋዕት
መላሽ ጆሮ አድርገሽ በልብሽ ከትቢ
ለመስዋዕት ተዘጋጅተሽ አበቢ።

ትኩስ ነው ውበት እሳተ ነበልባል
አላፊ አግዳሚ የሚበላ ዳግም የሚያባብል
አይራ'ቅም ከእሳት መድኃኒት ለክረምት
አይተው ደግሞ ተፈርቶ መፈጀት

ይህ ውበት እንዳው ከረገፈ
ከጊዜው ጎዳና ካለፈ
ጸጸት ነው ጸሀይ ስትዘቀዝቅ
ነፍስ ካላገኘች ሃቅ!

የሴትነትሽ ሃቅሽ መስዋዕት መሆን ነው
በአንቺ ነውና አዳም የሚበረታው
ስህተቱ ብትሆኚ ድኅነትም ሆነሻል
የእልፍ ዘመን መከራ በሴት ተፈጽሟል።

ለአዳምሽ ተሸሸጊ ለሁሉ አትታይ
በዘመን አትለኪ በሴት ልኬት ብቻ ታ'ይ
ለመወደድ ውደጂ ልብሽን ገብሪ
በአዳምሽ ጎን ፍቅር ዝሪ
በዕድሜሽ ከውበት በላይ ምግባርን ዘክሪ።

ያከብርሽ ዘንድ የልባምነት ዘውድ እንድትደፊ
የስጋ ሃሳብሽን በነፍስሽ በልጠሽ እለፊ
ጌጥሽ ይሁን ትህትና
እንግዳ ይመላለስ ከእልፍኝሽ ጓዳ።
ፋሲካ ሁኚ ደስታሽን ይትረፍ ለሌላ
ትንሳኤ ሁኚ ለድሃ ከለላ።

ራስሽን ተይ ከመታበይ ውጪ
መስዋዕት ሁኚ ለሴትነትሽ ከስጋ ድካም አምልጪ
ለክብር ልዕልና በራስ ዜግነት በሴትነት ታጪ።

🥰

ሴትነትሽ ከዓለም ለይቶ ይፈትንሻል የማትወጪው የመሰለሽ ነገር ሁሉ የሚታለፍ መሆኑን አስበሽ ከመልክሽ ይልቅ በልቦናሽ ላይ ስሪ። በፈጣሪሽ ቤት የምታበሪው መብራት ምግባር መሆኑን አስበሽ ስጋሽን ሰቅለሽ ለነፍስሽ ድከሚ ለአዳምሽ ታዘዢ ለቤትሽ መልካም ፍሬ ሁኚ ለልጆች እናት ለሰራተኞችሽ ሰብሳቢ ለወዳጆችሽ መጽናኛ ሁኚ።

✍️ ቤዛዊት የሴትልጅ

ሚያዝያ 14/2017 ዓመተ ምህረት
አደራ ጠርጥሪኝ

ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ

እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
....ማለቱን ካበዛሁ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ


አደራ......
https://t.me/yebezigetmoch
.......... ''ኪሎ ስንት ነው?'' እንድታየኝ ነበር የጠየኳት። እሷ ግን ስራዋ ላይ እየተዋከበች ''65'' ብላ ለሚያጣድፋት ደንበኞቿ ትመዝናለች። የትላንት ውበቷ እና መኮሳተሯ ዛሬም ደምቆ ይታያል። አንዴ እንኳን አታየኝም እንዴ እያልኩ ሰርቃ አየችኝ። የምገዛትን መጠኑንን እንደነግራት ይመስላል። ''በቃ ሁሉንም ልውሰድ '' አልኩኝ። ከልቤ! ሁሉም አፈጠጠ የእሷ ደግሞ ግልምጫም አለው። '' ዞር በል በናትህ '' ብላ አመናጭቃ ማስተናገዷን ቀጠለች። የቀሩት አንድ ያረጁ እናት ነበሩና 5ኪሎ እንድትመዝን አድርጌ ቅድሚያ ብሩን ሰጠኋት። ቡናማ ሻሽ ያሰሩት እናትም መረቁኝ ና ተቀብለው ከፊቷ ዘወር አሉ።

እኔ ግን ከመሸጫዋ ቦታ አልተንቀሳቀስኩም። '' ሌላውን ትመዝኚልኝ?'' አልኳት። እኔን አለማወቋ እየደነቀኝ። በምደነግጥለት ግልምጫዋ እምቢታዋን አሳየችኝ። ፈገግ ብዬ '' አላወቅሽኝም?'' መነጽሬን እያወጣሁ ጠየኳት። አየችኝ ውስጥ ድረስ መረመረችኝ። '' ስራ የፈቱትን አላውቅም '' አለች። የተናደውን እየደረደረች። ''የምርሽን ነው ጹጹ'' አልኩ። ጣረ ሞት ከፊቷ የቆመ ይመስል አፈጠጠች። መላ አካሏ ደረቋላ ከግንባሯ ላይ ችፍ ያለው ላብ ድንጋጤዋን አልደበቀም። '' ጹጹ'' ደገምኩላት። ሀሞት የቀመሰች ይመስል ተርገፈገፈች። '' ምን አይነት ቅሌታም እና ደፋር ነህ ከፊቴ የቆምከው'' ብላ ተነሳች።

ያልጠበኩት ነው የተፈጠረው። እታቀፋለሁ ብዬ ልቀጸፍ መሆኑ ቢገባኝ ወደኋላ ፈቅ አልኩ። ''ተረጋጊ እንጂ ጽዮን '' አልኩ በመታወቂያ ስሟ። '' ውረደት ሳላከናንብህ ከዚህ ጥፋ'' አለች። '' ቆ...ይ...እ....'' አላስጨረሰችኝም። ''ዞር በል አንተ ሰውዬ ሬሳህ እንዳይጎተት'' አለች እንደ ነጎድጓድ በሚያስገመግም ድምጿ። ዙሪያዋ ያሉት የሆነው ባይገባቸውም ከተቀመጡበት ተነስተዋል። አንድ ወጣት ጎረቤቷ ከሱቁ ዘሎ ወጥቶ ወደ እኔ መጣ። እጄን እየጎተተ መንገዱን እየመራኝ '' ይቅርብህ ከጹጹ ጋር ሙግት። ከተነሳባት ለእኛም ይተርፋልና ፍንጣሪው ሌላ ቀን ተመለስ። '' አለኝ። ዞር ብዬ ሳያት ወደ ስራዋ ተመልሳለች። የትላንት እልኋ ዛሬም ነበልባል ነው። ወጣቱ ትንሽ ሸኝቶኝ አሰናበተኝ። እኔም ያቆምኩትን መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቤቴ መንገድ ጀመረኩ።

ጽዮን እልኸኛ ጽዮን ጣይቱ ዛሬም በኑሮ ስብራትም አልደቀቀችም። እንደትላንት በሚያውቋት ፊት ክቡር ናት። እሳተ ነበልባሏ ያስፈራል። ዘንድሮም ትፈጃለች። በመስኮቴ የሚገባው ንፋስ ትላንትን እየጎተት ያሳየኛል። ሰው እንዴት እንዲህ ይኖራል ከዕድሜ ብዛት አይበርድም አይደክምም። ጽዮን ያው ጽዮን ናት። መልኬን መርሳቷስ የዚህን ያህል ምን ጋር ተቀይሬ ትላንት የምትወደው የታመነችለት ፍስሃ ነኝ። እንዴት ረሳችኝ። እሳቷ ራሷን ፈጃት እንዴ። ...............ነገ አገኛታለሁ።


✍️ርዕስ የለውም❤️‍🩹
🥀🌿🌱ክፍል 1🍁🍁🍁🍁

🖋️የቤዛዊት ሃሳብ

@yebezigetmoch
#story #time
ቅንድቧን እንደ ሴት ፥ ኩል አልተኳለችው
ፀጉሯ ቢንጨባረር ፥ ጉዳዬ አላለችው
ከንፈሯን በቀለም ፥ አልለቀለቀችው
እንደነገሩ ነው ፥ ልቤን የረታችው ።

እንደ ነገሩ ናት
ካፈር የተሰራች ፥ አመለ ውሃ ናት

እንደ ነገሩ ናት
ባያምር ባይደምቅ ፥ ልብሷና ቀሚሷ
እግረመንገዷን ነው ፥ የምታምረው እሷ

እንደ ነገሩ ናት
በደበዘዘ መልክ ግልገል ፀሐይ አዳይ
ያለ ጋሻና ጦር በዝምታ ገዳይ
እንደ ነገሩ ናት
በጭብጨባ ብዛት የማትደናበር
በተቺ ዘለፋ የማትሰባበር
እንደ ነገሩ ናት
የገዛ ክንፎቿን አጣጥፋ የምትበር ።

#ግጥም
ለዓመታት የተቋረጠ የፍቅር የቤተሰብ ልብ አንጠልጣይ ታሪኮቻችንን ይዘን በአዲስ መልክ መጥተናል።
💫 ኮከብ
አዲስ ድርሰት በ ✍🏾ቤዛዊት
ድምጻችሁን በምርጫው አሳውቁን
ዛሬ ማታ 👍 / ነገ ማታ 💓
በእናንተ ድምጽ ብልጫ ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ከምሽት ላይ እናደርሳለን። 🌸
መልካም ንባብ
🥀ኮከብ⭐️

ክፍል 1

የልቤ '' ብላ ስትጠራኝ የልቤን ያወቀችልኝ ያህል ደስ ይለኛል። ለስሙ በአንድ የውጭ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ውስጥ አመራር ነኝ። ሰራተኞቼን ሳናግር እና ፕሮጀክቶች ስመራ ለሚያውቀኝ አማርኛ አጣሁ ብል ፌዝ ነው የሚመስለው። ኮከብ ትባላለች። ሥሟም እሷነቷም የገጠሙላት ኮከብ ናት። ኮከቤ ብዬ እየጠራሁ አጽናናለሁ። እሷም ልጅነት እና እብደት የሚያጠቋት ልባም ናት ወዬ የልቤ ብላ ታሳርፈኛለች። ትውውቃችን ታክሲ ውስጥ ነበር። እንደዛሬ የጥሩ ደሞዝ እና ሥራ ባለቤት ሳልሆን ስኳትን ነው ያገኘኋት። ታላቋ ነኝ። ቅርርባችን እንደ ማንም ሰው የመጀናጀን ቢሆንም ወደ ጠንካራ አብሮነት የቀየረችው እሷ ናት። ከስራ ፍለጋ ስዞር ውዬ ከእናቴ ቤት ተኝቼ በብሶት ስደውልላት ያለመዳኘት ታደምጠኝ እና ውይ በቃ እንጸልይባት ትለኛለች። ታዲያ በስልክ ብቻ ከአምስት ወር በላይ አውርተናል ያውም የኔ ሀዘን እና የቀን ውሎ ይበዛዋል። ስለምታዳምጠኝ ይሆን ወይ ደግሞ ወሬ ወድጄ ምክንያቱ ሳይገባኝ አወራታለሁ። እሷም አስታውሳ ትጠይቀኛለች።

@yebezigetmoch

የሆነ ቀን ነው ትዝ ይለኛል ከአድካሚ የሥራ ኢንተርቪው ወደ ቤት እየተመለስኩ ደወልኩላት። ያለችበት ድምጽ ሲረብሸኝ የት ነሽ አልኳት። ልደታ አለችኝ። እኔም እዛው ነኝ ልምጣ አልኳት ፍቃዷን ለማወቅ ''ና እጠብቅሀለሁ'' አለችኝ። እኔም ወደ አብነት የሚወስደውን መንገዴን ትቼ በፍጥነት ወደ እርሷ ሮጥኩ።
@yebezigetmoch
ረጅም ቀይ አባባ የተበተነበት ጥቁር ቀሚሷ ላይ ነጠላ ደርባበት ትልቅ ሰው መስላለች። በእርግጥ ከግማሽ ዓመት በኋላ እንደመገናኘታችን ለውጧ ሊገርመኝ አይገባም። ተሳልሜ ወደ እርሷ ተጠጋሁ። ያልሞተ ሰው ይገናኛል ብላ ሊጨብጥ የተዘረጋውን እጄን አልፋ አቀፈችኝ። ደነገጥኩ። ያ ሁሉ ድካሜ በእሷ እቅፍ ሲረግፍ ተሰማኝ። ''ደህና ነህ ''አለችኝ። ደህና ነኝ እንዴት ነሽ አልኳት ወንበሩ ላይ እየተቀመጥን። ወይኔ አልጠፋሁብህም አለችኝ። ፈገግ ብዬ ትንሽ አረጀሽ አልኳት። ፊቷ ከሰል መሰለ። ይመስለኛል ያኔ ነው ቀልድ ያቆምኩት። ''ሀዘን አጋጥሞኝ ነበር ''አለችኝ። ደነገጥኩ። እንዴት በየቀኑ እያወራኋት ያላወኩት። ውሸቷንም መሰለኝ። መቼ ምነው አልኳት። ''ወር አለፈ ወንድሜ ነው አሳዳጊዬ ነው። '' በድንጋጤ የምላትን አጣው። ቀጠለች ''ያው ትንሽ ታሞ ነው የጭንቅላት ኢጢ ነበረበት'' አለችና አይኖቿ የቋጠሩትን እንባዎች ለቀቀቻቸው። ኮከቤ ይቅር በይኝ ለሀዘንሽ አለመድረሴ ግን አልነገርሽኝም አልኳት። እሷም ''ካለህበት ሁኔታ የኔን ሁኔታ ትከሻህ የሚችል ስላልመሰለኝ ነው'' አለችና በመሀላችን ጸጥታ ሰፈነ።

ከደቂቃዎች በኋላ ''ከየት ነው '' አለችኝ ጸጥታውን ለማባረር በውስጤ እያጉረመረምኩ ከማመልከቻ ነው አልኳት እሷም ''ለእናቴ ንገራትና እንውጣ ''አለችኝ። እኔም ወደ ዓውደምህረቱ ሄጄ እንደ ጎበዝ ጸሎተኛ ተደፍቼ ሥራ የሌለኝ ኳታኝ ሚስቴ አድርጊያት አልኩኝ ለልደታ ማርያም። አፈርኩ። ኧረ አትታዝቢኝ አናቴ ልጅቷን እንዳላጣት ነው ደግሞ ቁንጅናዋ። ጸሎቴ የማመልከቻ ደብዳቤ ሆኖ አረፈው። ለራሴ አየሳኩ ተነስቼ ጉልበቴን እያራገፍኩ አብሪያት ከግቢው ወጣሁ። ኮከብም ''በቃ ቻው እግዚአብሔር ይርዳህ ሲሳካልህ እዚህ እንመጣለን '' ብላኝ የኔን የሻይ እንጠጣ ግብዣ ከአፌ አሰቀረችው። ተሰናብቻት ባዶዬን ተመለስኩ። ሰው እንዴት እነኘደዚህ ያምራል። ምን ሆናነው? ለራሴ እጠይቃለሁ::

..........ይቀጥላል.......
⭐️ኮከብ ⭐️
✍🏾ቤዛዊት የሴትልጅ ✍🏾
🥀ኮከብ ⭐️

ክፍል~2

ያቺየፍቅር ጸሎቴ ሳትሰማ ያልጸለይኩት ጸሎት ሰምሮልኝ አሁንያለሁበት ሥራ ተቀጠርኩ። ስራን ከመፈለግ እና አትችልም ተው ባሉኝ ፊት ላለማፈር በእልህ ብዛት ለዘበኝነት ያመለከትኩት እኔ ችኩል መሆኔን አመራር ሆኜ ስቀጠር አወኩት። ለእናቴ ደውዬ ከነገርኳት በኋላ ለኮከብ ደወልኩላት እንመጣለን ስላችኝ ሳይሆን ውስጤ ስላዘዘኝ ነበር። የጨለማ ጊዜ መብራቴ አይደለች።የደስታ ድምጿ ይገባል እሷ የተቀጠረች ይመስል ፈነጠዘች። ''እንኳን ደስ አለህ በቃ እንገናኛለን ''አለችኝ። እኔም የምንገናኝበትን ሰዓት ጠየኳትና ዘጋሁት። እውነት ለመናገር ከሥራውበላይ ለእሷ ጥሩ ዜና በመንገሬደስ አለኝ። ከተሰጠኝ ቅድመ ክፍያ ሰዓት ልገዛለት ወደ መሸጫ ስገባ ቆንጆ ሀብል አየሁኝ። ዋጋው ለኔ ለጀማሪ ስጦታ ሰጪ ስላልሆነ በቀጣይ ልሰጣት ወስኜ ስጦታውን ትቼ ወደ ልደታ ለመሄድ ታክሲ ተሳፈርኩ። አዕምሮዬ ለምንድነው የምትቸኩለው ስጦታው ምንድነው ብሎ የበሰለ ጥያቄ ሲጠይቀኝ ልቤ ደግሞ ፍቅር ነዋ ብሎ የማይሞገት ርዕስ ይዞ ጸጥ ያሰኘዋል። በዚህ ሙግት እያለሁ ልደታ ቤተክርስቲያን ደረስኩ እና ደወልኩላት። ደርሻለሁ ብላ ስልኩን ዘጋችው። እኔም በአይኔ ሳማትር መንገድ ስትሻገር አየኋት። ዝምታ የማያውቀው ልቤ ወይኔ ውብት ኮከብ በምድርላይ እያለ ሲያስጨንቀኝ ይሰማኝነበር። እየተፍለቀለቀች አቀፈችኝና እንኳን ረዳህ እግዚአብሔር ብላ የያዘችውን ፌስታል ሰጠችኝ። ምንድነው አልኳት። ፈገግ ብላ ፍቅር ና ደስታ በመስጠት ነውና የሚገለጹት የጌታህን ፍቅር ለድሆች በመመጽወት ግለጽ ብዬ ነው ትንሽ ብትሆንም አለችኝ። ሰውነቴን ብርድ ብርድ ሲለኝ ተሰማኝ ወንድነትን የሚፈታተን ልባምነት በእሷሴትነት ውስጥ አየሁት እኔ ለእሷ ሳንስቀጠሮ ስሰጥ ለኔ በዝታ ተገኘች በአቅሟ። ስከፍተው ሽታው የሚያውድ ምስር ወጥ ነበር። አብሪያት እየዞርኩ ለተቀመጥኩት አከፋፈልኩና ከግቢው ገብተን ተቀመጥን። ፈገግ ብላ እያየችኝ ንጹህ ልብ ነው ያለህ አለችኝ። አፈርኩ ኧረ ተሸኮረመምኩ ሁላ አይ ነው ብለሽ ነው አልኳት። አዎ በአንዴ የተሰማኸው ንጹህ ብትሆን ነው ታድለህ አለችኝ። እኔም በልቤ የአንቺን ልብ ባገኘሁ አልኩ። ትንሽ ደቂቃ እንደተለመደው ጸጥታ ነገሰ። ለእሷ ሲሆን ያሳሳኛል ማውራትም አልችልም። እእ ሻይ እንጠጣ አልኳት እየፈራሁ። እሺ እንውጣ ብላኝ ከቤተክርስቲያኗ ወጣን።
@yebezigetmoch
ከካፌው በረንዳ ቀድማኝ ተቀመጠች። ያደረገችው አጓጉል ቀሚሷ እና አጭሯ ቲሸርቷ ልጅነቷን አጉሉቷል። አስተናጋጁም ሁለት ተቆራጭ እና ሻይ አመጣልን። ለምን እንደ ሆነ በማላውቀው ሁኔታ ተፍለቀለቀች ለኬክ እንደዚህ እስክል ድረስ ደስ ብሏት ከበላች በኋላ ተከዘች መጠየቁ ድፍረት ይሆንብኛል ብዬ ወደድሽው አልኳት አዎ ቆንጆ ነው። እና ነገ ነው ሥራውን የምትጀምረው ብላ ጨዋታውን ቀጠለችው አዎ ነገ ነው የምጀምረው አልገባሽም ጓግቻለሁ አልኳት። የመጀመሪያ ደሞዜን ስቀበል ለእኑ ለደሬ ለማርካን ወርቅ ነው የምገዛላቸው አልኳት። ለስሞቹ አዲስ በመሆኑ እንዳብራራላት በሚመስል ዝም አለችኝ። እኔም እኑ ማዘሯ ናት ደሬ ፋዘር ነው ማርካን እህቴ ናት አልኳት። ደስ አላት ያድርግልህ ደስታቸውን እንደማየት ምን ትርፍ አለ አለችኝ። እኔም አዎ ማለት ብዙ ወርቅ እኮ አላቸው ግን በኔ የተገዛ የመጀመሪያወርቅ ነው የሚሆናቸው አልኳት። ቅባትነን እያልክ ነው አለች ሻዩን ፉት እያለች። አይ እንደዛ ሳይሆን በራሴ ነገሮችን ማድረግ ደስ ይለኛል ነጻነት ይሰጠኛል። አልኳት። አይ የማይገናኝ መልስ አይዞህ ላቦሮ አይደለሁም ብላ ሳቀች። ከእሷ ጋር ያለኝን ነገር እወደዋለሁ። ሳናውቀው ራሴን እየተረኩላት ሰዓታት ተቆጥሮ ጨለማ አይን መያዝ ጀምሯል። በቃ እንሂድ ልታሳድረኝ ነው አለችኝ። እኔም ባደረገው እያልኩ በልቤ ከፍዬ ወደ እሷ ሰፈር ወደ ሚወስዳት ታክሲ መያዣ ማዝገም ጀመርን። ካፌ ውስጥ የጀመርኩላት ታሪኬን እንድቀጥል እና የእናንተ ገንዘብ አልፈልግም አልካቸው አለችኝ። እኔም አዎ አባቴ በመሰረተው ድርጅት ውስጥ ካልሆነ በቀር እኔ ውስጥ ስላለው ህልም ስባሪ እንደማይሰጠኝ ሳውቅ ሁሉንም ተውኩት በቃ ታክሲም ባስም መጠቀም ጀመርኩ ብሬ አለቀ። ስራ ፍለጋው አደከመኝ ተስፋ ልክ ስቆርጥ ጠብቆ አንቺን ኮከብን ሰጠኝ ብዬ ወደ ራሴ አስጠግቼ አቀፍኳት። እጄ የተመቻት ይመስል ዝም አለችኝ። እኔም እቅፌ ውስጥ ሆና በጨረቃ መታየቴ ደስ አለኝ። እግዚአብሔር በመንገድህ አይለይህ የታገልክለት ህልምህ አንድ ቀን ያስከብርሃል በቃ ቻው ብላ የኔን አሜን ሳትጠብቅ ተሰናብታኝ እየጮኸ ወደ ሚጣራው ባዶ ታክሲ ገባች። ረገምኩት ልሳኑይዘጋ! ይሄኔ እኮ እየጠበቅን ትንሽ ደቂቃ አብራኝ ትቆይ ነበር እያልኩ ፊቴን አዙሬ ወደ መንገዴ ማዝገም ጀመርኩ።

ይቀጥላል....

⭐️ኮከብ⭐️
✍🏾ቤዛዊት የሴትልጅ ✍🏾
🥀ኮከብ⭐️

ክፍል~3

እኔም ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ከዛች ዕለት ጀምሮ ነው እኔና ኮከብ ቶሎ ቶሎ መገናኘት የጀመርነው። እየሮጥኩ ሄጄ የቀን ውሎዬን እተርክላታለሁ የዕለት ዲያሪዬ ሆነች ስታደምጠኝ ያለመሰልቸት ነበር። ሃሳቧን ያለ ስስት ስትሰጠኝ እደነቃለሁ። አንዳንዴ የምታነሳው የበሉይ ጥያቄዋ ያዝናናኛል። ደግሞ በእሷ ምክንያት የበራውን የውስጤን ድቅድቅ ጨለማ አይቼ እኔ እንደምወዳት ትወደኝ ይሆን እያልኩ አስባለሁ። በትጋት ነበር የምሰራው የእውነት ለስራዬ ያለኝ ታማኝነት ሳየው ይደንቀኛል። በልጅነቴ ለራሴ ቃል የገባሁት ራሴን በነጻነት መንገድ ማግኘትና ህልሜን መገንባት የደሬ ልጅ ከመባልና በቤተሰብ ሀብት ከመመካት ወጥቼ እሱ ተብዬ የራሴን ታሪክ በራሴ የህይወት መዝገብ መጻፍ ነው የምሻው። በዚህ ጥረቴ የማትለየው የህይወቴ ሌላኛዋ ገጽ ኮከብ ናት። በእሷ ላይ ያለኝ ድክመት ጥንካሬዬም ነው። ዛሬ የመጀመሪያ ደሞዜን ተቀብያለሁ። ከብሩ ብዛት ይልቅ ትላንት በልጅነት ልቤ ላይ ያለ ስርዝ ድልዝ የተከተበ ህልሜ መሳካት ሲጀምርና ትንሹ እኔነቴ ፈገግ ብሎ ሲያየኝ ይሰመኛል። ኮከብን ጠርቻታለሁ አብሪያት ወርቁን ለመግዛት። ከያዝኩት የግል ታክሲ ውስጥ ስትገባ ሰውነቴም ዙሪያዬም ደስ የሚል ነገር ሲነፍስ ተሰማኝ። ደረቅ ሃቅ....እየሞትኩ እወዳታለሁ። ተያይዘን ነበር የሄድነው። እሷም የመረጠቻቸውን ወርቆች እያየሁ ፈገግ አልኩኝና። ኧረ ኮከቤ ተይ አሁን አይስቁብኝም ቀጭን አመጣህ ብለው ብዬ ወፍራም ወርቆችን ገዝቼ ወጣሁኝና ሻይ ቡና ብለን እንደሁልጊዜው ወደ ቤቷ መግቢያ ድረስ ሸኘኋት። በማግስቱም ሳገኛት የቤተሰቦቼን ደስታ ስነግራት ደስአላት። እንኳን ሆነልህ ቀጣይ ደግሞ ለራስህ ትሸልማለህ አለችኝ። በዚህ ሁኔታ ሆነን የምሰራበት ተቋም ለመንቀሳቀሻ መኪና የሰጠኝ። መጀመሪያ የገባችው ኮከብ ነበረች በመኪና ውስጥ ሆኜ ስታየኝ በረጅሙ የሳቀችው ሳቅ አይረሳኝም። የደረጃ ዕደገት ጨምሮ ብዙ በጎ ነገሮች የተጨመሩልኝ በኮከብ ብርታት እንደሆኑ ይሰማኛል።
@yebezigetmoch
ቀኑ የሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ነበር። ከኮከብ ጋር ተቀጣጥረን ስለነበር በጠዋት ጸጉሬን ተስተካክዬ ውድ ሰዓቴን አድርጌ እና ሽቶዬን አርክፍክፌ መኪና አስነስቼ በእናቴ ምርቃት ወደ ቀጠርኳት ሆቴል ቀድሚያት ደረስኩኝ። ሙሽራውን የሚጠብቅ ሙሽራ መስያለሁ። በእርግጥ ለደማቋ ኮከብ እኔ ግማሽ ጨረቃ ብቻ ነው የምሆነው እሱንም ከፈቀደችልኝ ነው። ቀድሚያት እየጠበኳት ሰዓቴን አያለሁ ከፊቴ ያለውን ውሃ እጎነጫለሁ ተቀበዘበዝኩ። ሰው በገባ ቁጥር የመጣች እየመሰለኝ አይኔን እወረውራለሁ። ከተቀጣጠርንበት ሰዓት ላይ ኮከብ ደረሰች። የጨመረችው የቀነሰችው ሽራፊ ሰንከንድ የለም። ያለምንም ማድመቂያ የደመቀች የወርቅ ፍልቃቂ መስላለች። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ወንበር ስቤ ተቀመጠች። ፈገግ ብላ እያየችኝ። ''ደግሞ ከመቼ ጀምሮ እንደዚህ ''አለችኝ። እኔም ከአሁን አልኳት አይኖቿን አተኩሬ እያየሁ። አስተናጋጁም ማዘዣ ደብተሩን ሰጠንና መምረጥ ጀመርን እየሳቀች ''ኧረ የልቤ ሰው የማውቀው ነገር የለም ''አለችኝ። እኔም እሺ እኔ ልምረጥልሽ ብዬ ለአስተናጋጁ ደብተሩን እየመለስኩ ለሁለታችንም አዘዝኩ። ምግቡ እስኪመጣም የዛሬ ግብዣዬን ምክንያት ለማስረዳት ጉሮሮዬን ጠርጌ መናገር ጀመርኩ። ኮከቤ አልኳት። አየችኝ። እኔ አንቺ ጋር ለምን እንደሆነ ሳላውቅ ንግግር አልችልም። ብቻ ግን በምችለው ላስረዳሽልሞክር። ድሮ ከአንዴም አራት ጊዜ ፍቅር ይዞኛል ብዬ ተንሰቅስቄ ምግብ አቁሜ አውቃለሁ ታውቂያለሽ ታሪኬን። አሁን ጠንክሮ መስራት ነገን መናፈቅ በተስፋ መበርታት ነው የሚሰማኝ። አንቺ እኔን ከመደገፍ ቦዝነሽ አታውቂም። ...... አስተናጋጁ ምግቡን ከፊታችን ማስቀመጥ ሲጀምር ንግግሬን አቆምኩ። አስቸናጋጁ መልካም ምሳ ብሎን ሄደ። እሷም ከምግቡ በላይ ያጓጓትን ንግግሬን መጠበቅ ጀመረች። ቀጠልኩ ሰዎች አንቺ የምታውቂውን እኔነቴን አያውቁትም አንቺ ጋር ደካማ ና ግልጽ የሆንኩ ይመሰለኛል። ስረዳው ግን ጠንካራና ሚስጥሮቼ በእሳት እንደሚጠበቁ ነው የገባኝ። ከዚህ በላይ ማሰብና መድከም አልፈልግም። አንቺ የኔ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ ረዳቴ ልልሽ እሻለሁ በአንቺ ብርታት ነው ሊይዘኝ የሚያንዣብብ ስንፍናዬን የገደልኩት። እባክሽ ብዬ ባላስጨንቅሽም እጅሽን በእምነት ልብሽንም ያለጥርጥር ብትሰጪኝ እኔም ከሞት በቀር ያለድካም አፈቅርሻለሁ ብዬ ተነፈስኩና ግንባሬ ላይ ችፍ ያለ ላቤን በሶፉቱ ማድረቅ ጀመርኩ። ድንጋጤው ለረጅም ሰዓት በጸጥታ እንድንበላ አስገደደን። ዝም አለች። መልሷን ፈራሁት ጨነቀኝ። ምሳ በልተን ስንወጣም በመሃላችን ምንም ንግግር አልነበረም። አስደበርኩሽ አልኳት። ኮከብም ወደ ጥላ ሥር ጠጋ ብላ ቆመችና። የልቤ ሰው አንተ እኮ ስለኔ የማታውቀው ብዙ ነገር አለ። አለችኝ። እኔም በጓደኝነት ጊዜ የነገረችኝ ታሪኮቿን ስለማልረሳቸው ቀላልና የማይከብዱን እንደሆኑ ነገርኳት። ብቻ ኮከቤ አንቺ የኔ ሁኚ እንጂ ለአንቺ የማልሆነው የለም አልኳት በአፍቃሪው ልቤ ተማምኜ። ታዲያ እሺ ነው የምልህ አሁን ወይስ ፈቅጃለሁ ነው ወይስ ይመችህ ነው። በረጅሙ ሳቀች። አቀፍኳት።
ከዛች ዕለተ ጀምሮ የሳቋ ምክንያት ለመሆን ለልቤ ነገርኩት። በቃ እንዲሁ እንዳማረባት እንዲሁ እንዳፈቀርኳት ለዘለዓለም ከጎኔ እንድትሆን በእቅፌ ሆና ተመኘሁኝ። ከሥራ ወደ ኮከብ መሮጥ አይደክመኝም። እሷም ከዛች ዕለት ጀምሮ ወደ እኔ ስትመጣ ተሽቀርቅራ ተወርዋሪ ኮከብ መስላ ነበር። የፍቅር ህጓ የኔ ህግ ሆኖ የኔ መመሪያ የእሷ መተዳደሪያ ሆኖ ተግባብተን አብሮነታችን ጠፏል። ባየችኝ ቁጥር የምታሳየኝ ፈገግታዋ ለእኔ ደስታ የምትጥረው ድካሟ ይበልጥ እንድወዳት አደረገኝ። ለካ ፍቅር ይጨምራል። አደገ! ትንሹ በራሱ ብርታት የሌለው እኔነቴ እሷ ጋር ብርቱ እና ትልቅ ሆኗል። ኮከብ ሳምሶንን ያሸነፈች ያቺ ሴትም መሰለችኝ ኃይለውን የረታች።

ለመኖር እየጓጓሁ ነው።

@yebezigetmoch
ኮከብ እንባ እና ሳቅ እኩል የሚያደክሟት የጠዋት ጸሃይ ናት ልስልስ ያለው ልጅነቷ መልክ አለው። አለማወቋ እንኳን ውበቷ ነው። በጨወታ መሃል የምታስቀምጠው ሃሳብና ምክር ለኔ የህይወት ማዕዘን ድንጋይ ነው። መሰረቴን የምጠለው በእሷ ነው። ደክሞኝ እንኳን ካላገኘኋት ይጨንቀኛል። የህጻን ያህል ወድቃ የምትሰበር ወጥታ የምትጠፋ ስለሚመስለኝ እየደወልኩ ደህና ነሽ ከማለት አልቦዝንም። ዛሬ በፍቅር ከሆንን አምስት ወራችን ነውና ቤት ላስተዋውቃት ተቀጣጥረናል።

ይቀጥላል......
⭐️ኮከብ🥀

✍🏾ቤዛዊት የሴትልጅ ✍🏾
@yebezigetmoch
🥀ኮከብ⭐️

ክፍል ~4


ስልኬተቅለጨለጨ ኮከብ ናት። ስልኩን በትከሻዬ አስደግፌ ወዬ ኮከቤ ደረሽ አልኳት ለእናቴ እንደመጣች ምልክት እየሰጠኋት። ኮከብም አዎ እየደረስኩ ነው ግን ምን ይዤ ልምጣ አለችኝ። ምንም ሁሉም ሙሉ ነው አንቺን ነው የሚጠብቁሽ ብዬ ልቀበላት ወጣሁኝ። አክስቶቼን ጨምሮ ከውጪ የመጡበት ጊዜ ስለሆነ በራሱ የሚተማመነው ቆራጡን ሰው የልብ ወዳጅ ለማየት ጓግተዋል። አባቴም የክብር አለባበሱን ለብሷል ቤታችን የፋሲካ በዓል ድባብ ይዟል። ወደ ሰፈራችን መግቢያ ጋር ስደርስ ኮከብ ከሰማያዊ ላዳ ታክሲ ሰላም ተባብላ ስትወርድ አየኋት ልቤ ትርክክ አለ ለእኔ የምታሳየኝን ፈገግታ እያሳየች በሩን ስትዘጋው አየኋት። በእጇ የሆነ ትንሽ ነገር ይዛለች። ወደ ግራዋ ሰትዞር አየችኝ። አባቱን እንዳየ ህጻን ነበር ስትፈነድቅ ወደኔ የመጣችው። የለበሰችው ጥቁር የእራት ቀሚስ የእሷን የደም ገንቦነት አድምቆ ስሟን መስላለች። ''ቆየሁ እንዴ የልቤ። ''አለችኝ። ጸጉሯን ከአይኗ እየመለሰች። እኔም አይ ገና መውጣቴ ነው። አምሮብሻል አልኳት። ኮከብም ''አመሰግናለሁ ተከፍሎበታል ብላ አለባበሷን ተሽከርክራ አሳየችኝና ቆመች። ቅናትና ጥያቄ የቆነጠጠው ውስጤ አላስችል ቢለኝ የቅድሙ ሰው ማነው ብዬ ሳላውቀው በቁጣ ጠየኳት። እንደ ደደረቅ ኩበት ደርቃ ቀረች በድንጋጤ ፈዘዘች ድንጋጤዋ አላወሰኝ። ምን ያስቆታጣሃል በቀስታ አጠይቀኝም ባለፈው የመኪናህን ጎማ የቀየረልህ መካኒኩ ዳዊት ነው አለችኝ። መደንገጧ መልሶ ቢያስደነግጠኝም በራሴ አፈርኩኝ። አስታውሳለሁ ያን ዕለት አብረን ውለን ወደ ሰፈሯ ስሸኛት የመኪናዬ ጎማ ፈነዳ። የማውቀው ጥበበኛ አለ ብላ የጠራችው ኮከብ ናት ስባሪ ሳንቲም ሳይቀበለኝ ነበር ሰርቶልኝ የሄደው ምን አልባት እንዲህ ንጹህ ሆኖ በመኪና ሳየው እንዴት እንዳልመጣለኝ እንጃ ማፈሬን እንዳላሳብቅ አቅፊያት ምን ይዘሽ ነው አልኳት። ኮከብም የእነሱነው ብላኝ ወደ እኛ ቤት አቀናን። የግቢውን በር ከፍቼ እንድትገባ ጋበዝኳት ወደውስጥ ዘለቀችና በአይኗ ማማተር ጀመረች። ስፋቱንና የቆሙትን መኪናዎች እያየች ቤተመንግሥት መሆኑን ብትነገረኝ ሻል ያለ ነገር ለብሼ ወዳጆቼን ሰብስቤ ነበር የምመጣው። ቤታችሁ ሲያምር አለችኝ። ነገሮችን በአስተውሎት እንደምታይ ከልቧ እንደምታደነቅ ቀልድ እንደምታበዛ የማውቀው እኔም እየመራሁ ወደ ሳሎን አደረስኳት አክስቶቼ እናት አባቴቴ ሁሉም ቆመው ነበር የጠበቋት። ሁሉም በፈገግታ ስማቸውን እየነገሯት ለእሷ እኔ አፍ ሆኜ ስሟን እየደገምኩላቸው ተዋወቋትና መጨረሻ ላይ የአጎቴ ልጅ የሆነው እዮኤል ከመታጠቢያ ክፍሉ ወጥቶ ወደ እኛ ተጠጋ። ኮከብ ጣረ ሞት ያየች ይመስል ደነገጠች።

''ዶክተር'' አለችቃሉን አምጣ። የብርጭቆ ጠርሙስ የወጋኝ ያህል ውስጤን ቀጽፎ ያዘኝ። እዩኤል የቤታችን ብቸኛ ሀኪምና እንደ ሀገርም ተወዳጅ የብዙ ባለስልጣናት ሀኪም ነው።
''እኔ አላምንም ኮከብ?'' እዩኤል መለሰ።

የሚሆነው ነገር ለሁላችንም ግራ ሆኖብናል። ሁሉም እኔን እያየ እነሱን ያያል።

ተቃቀፉ! አይኔ እያየ ኮከብ በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ አየኋት የእሶት ጎመራ እየፈነዳ ሲያነደኝ ይሰማኛል።
''ትተዋወቃላችሁ?'' አክስቴ ጠየቀችው።

በጣም በአግራሞት እና በፈገግታ ኮከብን እያያት እጁን ትከሻው ላይ ጭኖ

''ከዛሬ ሶስት ዓመት አካባቢ ወደ ኩባ ከመሄዴ በፊት ያከምኳት ታካሚዬ ናት'' በኩራት ነበር የሚያወራው።

''ልታስረጂኝ ትችያለሽ ኮከብ?'' አፈጠጥኩባት።

''አዎ '' እንባዋ ቀደማት። ልቤ ሲጨክንበትና ለአንዲት ጠብታዋ መራራት ሲያቆም ተሰማኝ። ኮከብ ቀጠለች
'' በሰንሰለት ታስሬ ለብዙ ጊዚያት በር ተዘግቶብኝ ነበር። ''

''እብድ ነበርሽ?'' ከአፍ የመለጠ አፋፍ ተናገርኳት።

'' አዎ እብድ ነበርኩ የሚቀርበኝ የኔን ጭንቀት የሚረዳኝ ማንም ስላንበር አብጄ ነበር!'' ለመጀመሪያ ጊዜ የኮከብን ጩኸት ሰማሁት። ደነገጥኩ። እየነደደ እየጨመረ የሚመጣው የጋለ ኃይለኝነቷ አንበረከከኝ። ቃል ከአፌ ቀርቶ መተንፈስ ከበደኝ።

''ጉድ ደስታን ስንጠብቅ'' እናቴ በሽሙጥና በሃዘን ተናገረች። ዛሬ መሰለኝ ኮከብን የገደልኳት የወገርኳት።

''የማይታወቅ መስሎሽ ነው የደበቅሽው?'' ቁጣዬ መልሶ አናገረኝ።

@yebezigetmoch

''ኮከብ ነኝ ሳበራም ስደበዝዝም በግልጽ ነው። የአንተ ታሪክ በሶፍት መዝገብ የተጻፈ ለስላሳ መዝገብ ነው። የኔ ግን በእንባ እና በህመም ነው የተከተበው። የልብህን ስታወራኝና ስትተርክልኝ ለሚሰሙህ ሰዎች ክብር ያለህ መስሎኝ ነው። ልጅ ነበርኩ እንደ አንተ ህልም ነበረኝ። ከልብስ አጣቢዋ እናቴ እየዞረች ከምትደክመው ጸጉር ሰሪዋ እኅቴ እና እየደከመ ከሚመጣው አባቴ ትከሻ ወርጄ በነጻነት መብረር እፈልግ ነበር። እነሱን ማሳረፍ እፈልግ ነበር። ቤተሰቤ ተሳካለት እንዲህ ገጠመኝ የሚሉ የዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ታሪክ ስሰማ ለእነሱ እልፍ የህይወት ፈተና እኔ ስፈተን ለራሴ ስዳክር ማዕበሉ አሳስቆ ወሰደኝ። እንቅልፋ አልባ ለሊቶች የቁም ቅዠቶች በሰንሰለት ሲያሳስሩኝ ቅድም አይተህ የተበሳጨህበት ዳዊት ነው በሰፈር ሰው መዋጮና በዶክተር አጋዥነት ህክምና ያገኘሁት። '' እንባዋ በቀይ ጉንጮቿ አልፎ ሽቅብ ይፈጠፈጣል። የአፍንጫዋን ቀጭን ፈሳሽ ወደ ላይ እየጎተተችና በእጇ ፊቷን እየሞዠቀች ''ተረጋግተህ እንኳን ለመጠየቅ እኔን ቀርቶ ራስህን ያላከበርክ ራስ ወዳድ ነህ''

''ምነው እናቴ! አላበዛሽውም እንዴ በሰው ቤት ማበድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው!'' እናቴ ተበሳጨች።
ዶክተሩ ወንድሜ
''ምንድነው ይሄ ሁሉ ግርግር''። ኮከብ ከቤቱ ለመውጣት ፊቷን ስታዞር እጇን ያዛት። '' እኔ እንድናገር እድል ስጡኝ አጎቴ እንረጋጋና እንቀመጥ'' አለ በዝምታ ውስጥ ያለውን አባቴን እያየ። አክስቴም ''አዎ ኑ እንቀመጥ አንቺም ተረጋጊ'' አለች እየተንቀጠቀጠች። ሁሉም ተቀመጠ። ኮከብ እያየችኝ ታነባለች። ውስጤ መደበቁ ላስተዋዉቅ በአልኩበት ቅጽበት አዲስ ታሪክ መስማቴ እጎፈላ የመጣው ንዴቴን አባብሶታል። እዩኤል ቀጠለ

''አዚህ ጋር እብድ የሚባል ነገር የለም። ስስ ልብ ስላላት በተደጋጋሚ ባጋጠማት ጭንቀትና በሰው ተከባ ብቸኛ እንደመሆኗ የውስጥ ሰላሟን በማጣቷ የተፈጠረ የአእምሮ ጤና ጭንቀት ነው። ይሄ ደግሞ በእሷ ለመዳን ለመኖር መጓጓት ነው በህክምናው መዳን የቻለችው። የሚገርመው የገዛ ጠላትና ስትወድቅ ያላነሷት ጓደኞቿ ናቸው። እሷ ግን ለይቅርታ የሚሆን ሰፊ ልቧን አክማ ድናለች። ታዲያ ለምን በትላንት ቁስሏ የምትከሰሰው። እኔ ስላገኘኋት በዚህ መንገድ ደስ ስላለኝ እና በመሃላችሁ የተፈጠረውን ባለማወቄ የተናገርኩት ነው። '' እዩኤል እንድታረም አየኝ።

እኔም '' ቀድም ያፈረችበትእሷ ናት ''።
''ነገስ አለመታመሟ?'' አባቴ ተነፈሰ።
ኮከብ ተነሳች በእጇ የያዘችውን እያስቀመጠች ''እንኳን የኔ ነገ የእናንተም አሁን በሰሪው እጅ ናት። '' በክብር ከገባችበት ቤት በለቅሶ እየሮጠች ወጣች።

ይቀጥላል.....
🥀ኮከብ🥀
✍🏾ቤዛዊት የሴትልጅ ✍🏾

@yebezigetmoch
መልካም ንባብ 📖 አስተያየታችሁን በድምጽ መስጫ ላይ አሳውቁኝ።