የግጥም መንደር
1.72K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
💟❤️❤️🇪🇹🇪🇹💒💒

💙ትህትና የሚመነጨው በራስ ከመተማመን ነው።

💜ተግዳሮቶችህን ሳይሆን በረከትህን ቁጠር።

💛የምር እንዲሳካልህ ከፈለክ ሳትጨርስ አታቁም።

🖤አብዛኞቻችን እርግፍ አድርገን የምንተወው ሊሳካልን ጥቂት ሲቀረን ነው።

💚የበረዶ ተራራን እየወጣህ ወይም እየተዎጋህ አንዲት ስህተት ለሞት ልትዳርግህ ትችላለች ስለዚህ ስህተትህን ቀንሳቸው።

💚ለመባል ሳይሆን ለመሆን ጣሪ ምክንያቱም ስትሆኚ መባሉ አይቀርም እና።

❤️አብኛዎቹ ሰዎች የሚወድቁት ችሎታ ወይም ክህሎት ስላነሳቸው ሳይሆኑን ስለሚተውት ነው።
❤️💛💚💙💜🖤🖤💜💙💚
እግዛብሔር በቸር ያውለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@yebezawit2
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😜እብድ ነኝ እንዴ?😃

እሷን ሳያት ገና እንዲ የሚያደረገኝ
ሄጃለው ብዬ የሚመልሰኝ
ከሄድኩበት ቦታ የማያሳርፈኝ
ምን ይሆን የልቤ ምክንያቱ
የሩቅ ሰው ከሩቁ መናፈቅ መጎተቱ
ፍቅር ነው ወይስ እብድ ነኝ
ከአበደች 😉ጋር አብሬ ያበድኩኝ
ከቁምነገር በላይ ሳቋ ከጎተተኝ
ከቤት በሀሳብ ወጥቼ እመለሳለሁ
ባያሁት ነገር ሁላ እስላታለሁ
ሚስጥሩ ጠፋ እንጂ እሷን ለመውደዴ
እሷን ያስባለኝ ግን፡እብድ ነኝ እንዴ???😜

ገጣሚ ቤዛዊት
መነሻ ሀሳብ K
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💪 ወንድነት💪

መልበስ ማጌጥ መዘነጥ
ሴት ላይ ሴት ማማረጥ
ይሄ አይደለም ልኩ የወንድነት
ክብር የሚሰጥ ለሁሉም ሴት
ታማኝ ለፍቅሩ ዘማች
ለፍቅሩ ለቤተሰቡ ሟች
ይሄ ነው ለእኔ ልኩ የወንድነት
ለልብሱ ሳይሆን የማጨነቅ ለማንነት
ክፋ የማይወጣው ቁጥብ ለቃላት
የሰውም ሳይሳደብ አክባሪ የራሱን እናት
ይሄ ነው ለእኔ #ወንድነት 💪💪

ገጣሚ ቤዛዊት
👉 ለማንኛውም ሀሳብ ነቀፋ @yebezawit2 ላይ ጫር ጫር ያርጉልን👈
Tewodros Mosisa
መልኬ
🔊Only At @yebezigetmoch

💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ስለወደድኩት 😉
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Yebechaye | የብቻዬ
Mulugeta Alemu
🎵 @yebezigetmoch 🎵

❤️የህግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ነው❤️
❤️❤️አንቺ የሌለሽ ጊዜ❤️❤️
ክፍል 2 የፍቅር ታሪክ
#ቤዛዊት
አነሳሷ አስደነገጠኝ ከሮጥኩኝ በያዘችው ድንጋይ አትስተኝምዝም ብዬ ቆምኩኝ ፍርሀቴ ፊቴ ላይ ቢነበብም ግን ቆምኩኝ ተስፈንጥራ ብትነሳም በዝግታ ነበር የቀረበችኝ ጠጋ አለችና ምግብ ምግብ ብላ ጮኸችብኝ ከየት ላምጣው ከማላምጠው ማስቲካ ውጪ ምግብ ቀርቶ ምግብ ቤት የለም የደረቀው ከንፈሯ ሳበኝ ስትጮህ ከመደንገጥ ውስጤን ደስ አለው እኔም እኛ ቤት ልውሰድሽ አልኳት በረጅሙ ሳቀች እና በጣም በፍጥነት በእንግሊዝኛ አወራች ለራሴ ጠየኩት አልተማርኩም እንዴ አልኩኝ ውስጤ የተማረች መሆኗን ጠረጠረ አንቺ አውቆ አበድ የሚል ድምፅ ከበስተሗላዬ ተሰማኝ ዞር ብዬ አየሁኝ አንድ መነኩሴ ናቸው በአረንጓዴ ሳህን ላይ በጥቁር እንጅራ ሽሮ ወጥቶበታል ቀፈፈኝ የእኔ ልጅ አንተስ ምን ሁነህ ነው አሉኝ ምግቡን ለወጣቷ እየሰጡ እኔም በዚህ ጋር ነበር መንገዴ እሷን አይቼ ነው የቆምኩት አልኳቸው ፍፁም ትህትናቸው ገርሞኝ የምትነካህ መስሎህ ነው አሉኝ እኔም አይ አይደለም አልኳቸው ቀጠል አርጌም አሳዝናኝ ነው አልኩ በሽንፈቴ እንዳይስቁ ዋሽቼ መነኩሴዋም የማያዝን ማን አለ ብለህ ይቺን የመሰለች ልጅ ከማለታቸው ወጣቷ ጮኸች እና ሳቀች ሽሮው እና አመጋገቧ አፒታይት ይዘጋል መነኩሴዋም ቀጠሉልኝ መድሀኒት እኮ አላት እዚህ ስትመጣ ግን ምን ዋጋ አለው ማን ይስጣት በትና ጨረሰችው አሉኝ በሀዘን ስሜት እኔም ታሪኳን ለማወቅ ጓጓሁኝ ለሊት መሆኑ ተረሳኝ እዚህ አልነበረችም እንዴ አልኩኝ መነኩሴዋም አዎ እኔም ያገኘሗት በቀደም ነው ግን ሰዎች የነገሩኝ ከሌላ ቦታ መምጣቷን የምስለኛል ከአረብ ነው የመጣችው አሉኝ እኔም ስታሳዝን አልኩኝ በልቤ መነኩሴዋም መሽቷል ልጄ ሳታይህ እለፍ ብለው በእናትነት ስሜት ሸኙኝ፡፡
የግቢውን በር ከፍቼ ቀስ ብዬ ገባሁ የቤቱ ሰው ሁሉ ተኝተዋል የምኖረው ከእናት ከአባቴ ጋር ቢሆንም እድሜ ለልዕልት አንነጋገርም የድሮዋ ፍቅሬ ህይወቴን አንግታው ነው የሄደችው ወደ ሳሎኑ ቀስ ብዬ ገብቼ ሳፋ ላይ የተቀመጠውን ጋቢ ለብሼ ሰለ ወጣቷ እያሰብኩኝ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ መንጋት አይቀርም እና ምድር በፀሐይ ነበልባል እየተቀጣጠለች ነው በመስኮቱ የሚገባው ጨረር ቀሰቀሰኝ እና በግድ ተነሳሁኝ አጠገቤ ያለውን ስልክ አብርቼ ሰአቱን አየው ሶስት ሰአት ሊሆን ነው ከመቅፅበት ተነሳሁኝ የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ምግብ በፌስታል ገልብጬ ልብሴን ቀይሬ ወጣሁ ይሄን ሳደረግ አባቴም እናቴም በትዝብት እያዩኝ ነበር እኔ ግን ምንም አላልኩም አባቴ አካል ጉዳተኛ ሲሆን በዊልቸር ነው የሚንቀሳቀሰው ባያኮረፈኝ ብዙ አወራው ነበር ምክንያቱም ከእናቴ በላይ እሱን ነበር የምቀርበው አባቴ ኢንጂነር ነበር ከሚሰራበት ፎቆላይ ወድቆ ነው እንደዚህ የሆነው ውጪ የሚወጣው አሁን በስንት ጊዜ አንዴ ህይወቱ ላይ የገጠመው ነገር ውስጡ ገና አልተቀበለውም እና ሰዎች ሲያዩት ይሸማቀቃል እናቴ ደግሞ ተደራጅታ ሆቴል ቤት ዋና ሆና ትሰራለች ሁለት ታላቅ ወንድም እና ሁለት ታናሽ እህቶች አሉኝ፡፡ የጊቢውን በር ወርውሬ ዘግቼ ማታ ያየሗት ወጣት ጋር አቀናሁ ስደርስ ግን ሌላ ታሪክ ተፈጥሯል ሰዎች ከበዋት አየሗት ልብሷ በደም ተጨማልቆ በጀርባዋ ራሷን ስታ ወድቃለች የያዝኩትን ፌስታል ለቀኩት አይኔ የዋሸኝ መሰለኝ ጠጋ ብዬ ሰዎቹን አሳልፉኝ ብዬ ተጠጋሗት እና የተዘረጋውን እጇን በእጆቼ ያስኩት በጣም ቀዝቅዟል የተመታ የሰውነት ቦታ የለም ተደፍራ ነው እያሉ የሚያወሩ የሰዎችን ወሬ ሰማሁ አቅፌ አነሳሗት ሰውም ኧረ ፓሊስ ይመጣ አሉኝ እኔ ግን ይዣት ሮጥኩኝ ምን እንደማስብ እራሱ አላውቅም ብቻ የሆነ ክሊኒክ ጋር ስደርስ እየጮኹ ገባሁኝ ተቀምጣ የነበረችው ቀጭን ነርስ ተሰፍንጥራ ተነስታ ዶክተር ነርስ ብላ እየተጣራች የተዘረጋው አልጋ ላይ እንዳስተኛት አግዛኝ ትንፋሿን አየችና ኦክስጅን ሰካችላት እና ግሉኮስ ሰጠቻት ዶክተሩም መጥቶ አያት እኔ በሩ ጥግ ላይ ደርቄ ከያቸዋለው የልብሷ መቆሸሽ የእግር ተረከዟ መሰነጣጠቅ የሰውነቷ መገርጣት ከቤት እንዳልመጣች ተረድተው ዶክተሩ ምኗ ነህ አለኝ እኔም እ..እ...እ ዘመዷ ማለት ጓደኛዋ ...እ...ተንተባተብኩኝ ዶክተሩም ከየት ነው የመጣቿት አለኝ አይኗን ገልጦ በመብራት እያየ እኔም ከታችኛው ጎዳና አልኩት ስሟ ማነው አለችኝ ሌላኛዋ ነርስ እኔም አላውቅም ማለት እብድ እኮ ናት አልኩኝ ቃሉ እየዘገነነኝ ዶክተሩም እህት እህት እያለ ሊቀሰቅሳት መኮረ እጇ ላይ የለጠፉላት ጨርቅ ነገር በኮምፒውተር በሚመሰል ላይ ቁጥር ያነባል የደም መጠኗን ነበር ቁጥሩ ይቀንሳል እንጂ አይጨምርም ዶክተሩም ፍሉድ ጨምሩ አለ እና እኔ እንድወጣ አረጉኝ ጨነቀኝ ምን እንደማረግ ከበደኝ ተከትሎኝ የመጣም የለም የማታዋም እናት መነኮሴም የሉም ልቤን በአፌ ልተፋት ነው ሁሉም ይሯሯጣል ፈጣሪዬ አታርግባት አልኩኝ ስልኬ ጠራ ከክፍል ነበር የደወሉልኝ ፈተና መኖሩን አስታወስኩ ፋይናል ግን አይደለም ዘጋሁት ከመስማት በላይ ጭንቄን የማወራው ሰው ናፍቆኛል፡፡ ከንድ ሁለት እያለ ሰአቱ ሰድስት ሰአት ሆነ ነርሷ ጠራችኝ ፊቷ ላይ ምንም አይነበብም መሯሯጥ አቁመዋል ቀስ ብዬ ገባሁኝ የገባሁት ዶክተሩ ጋር ነበር ዶክተሩም ተቀመጥ አለኝ የወንበሩ ጫፍ ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ እንዴት ናት አልኩኝ መልሱን ለማወቅ እየጓጓሁ ዶክተሩም ከአሁን ጥሩ ላይ ናት ደሟ ተስተካክሏል ነቅታለች አለኝ ለዘብ ብሎ አለመደሰቱ አስደነገጠኝ ምነው ዶክተር ሌላ ችግር አለ አልኩኝ ዶክተሩም አዎ አለ አንተ ለልጅቷ ምንድነህ አለኝ እኔም ትላንት ነው ያወኳት አልኩት ዶክተሩም ነርሷም ተደነቁብኝ እኔ ግን ችግር የተባለው ነገር ሳላውቀው ችግር ሆኖብኛል ዶክተሩም እኛ ሰዎች ሞት እና መከራ ያነሰን ከንቱ ፍጥረቶች ነን አለኝ ቀጠል አርጎም በአሁን ሰአት የሚረዳት የሚያግዛት ሰው ያስፈልጋታል አለኝ እኔም የአቅሜን ሳይሆን ከአቅሜ በላይ አረግላታለው ብቻ ትዳን አልኩት፡፡ዶክተሩም አሁን የምነግርህ ነገር ህግ ሊያውቀው ይገባል ልጅቷ ተደፍራ ነው እንደዚህ የሆነችው አለኝ የምድር አፍ ናፈቀኝ እያቃዠው በሆነ አልኩኝ ደነገጥኩኝ ጉልበቴ ካደነኝ ምንም አላልኩም እንደምንም ከዶክተሩ ክፍል ወጣሁኝ እንዴት ያለ ጭካኔ ነው እንዴት ማስቢያውን ያጣል አልኩኝ ፡፡ ነርሷም መጥታ ማየት ትችላለህ አለችኝ እኔም ገባሁኝ እና በድፍረት አይኗን አየሁኝ እጇን ከአልጋው ጋር ጠፍንገው አስረውታል አይኗ ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላ አቅጣጫ እየተንከባለለ ህመም ይጭራል ቀስ ብዬ የታሰረውን እጇን ልነካት ስል እንደመሸሽ ብላ ጮኸች እኔም ራኳትኝ እንደዛ ትላንት ከእግዜሩ ስራ ከሆነችው ጨረቃ ጋር እንዳላወራች አሁን ግን ያ በእብደት ውስጥ ያየሁት ነፃነት አይታየኝም ነርሷ አማኑኤል እንደሚልኳት ነገራኝ ነበር እና እዛስ ምን ትሆን አለኩኝ ትላንት መሳቅ ና መጮህ ነበር አሁን ግን ለቅሶ ጩኸት የማይገቡ ቃላት ናቸው ህመሟ ውስጥ ድረስ ተሰማኝ፡፡
ነርሷ በአምቡላንስ ከሁለት ፓሊሶች ጋር ላከችኝ የአማኑኤል ግቢ ገብተን ወሰዷት እጇን ከእጇ ላይ አጣብቃ የነካትን ሰው ሁሉ ትሸሻለች የልጅነት ወዟ ግን እንዲህም ሆና ትስባለች ፓሊሶች ጥያቄበጥያቄ አጣድፈውኝ አድራሻዬን ወስደው ተመለሱ እኔ ግን ግቢ ውስጥ ነበርኩ ብዙ ህመሟንን እያ"ሁ ከህፃናት እሰከ አዛውንት የኔዋን ወጣት ክፍል ሰጥተው ነርሶቹ አስተኟት እኔም ዶክተሯን አውርቼ ነገ ለመመለስ ከራሴ ጋር እያወራሁ ከሆስፒታሉ ወጣሁኝ.....

አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ
💔አንቺ የሌለሽ ጊዜ💔
ደራሲ ቤ
ዛዊት
ክፍል ሶስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ
👍 ማንን ገደለ 😉
😊 @yebezigetmoch 😊
☺️ @yebezawit2 🙂
🤡ደስ የሚል ምሽት🤡

ይቀጥላል
Forwarded from ጥበብ እና ጦቢያ
🌸🌸ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡

@tebeb_ena_tobeya
አዲሱን ቻናል ተቀላቀሉ @tebeb_ena_tobeya 😉😉
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
"እርሳስና ላጲስ አብረው ይኖራሉ ግብራቸው ተቃርኖ፣
የሚፅፈው ከታች አጥፊው ከላይ ሁኖ።"
❤️መልካም ምሽት❤️

🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር 🇪🇹

@yebezigetmoch
የዘላለም ሀብት ማለት
በባንክ ዉስጥ ያለ ገንዘብ ሳይሆን 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በልብ ዉስጥ ያለ ፍቅር
እና መልካምነት ነዉ።

መልካም ምሽት
#ሼር
@yebezawit2
❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹
።።።።።​​ምርጥ ባህሪ ።።።።።
➩ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ
➩አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን
➩ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ
እንዲሆን አትጎትጉት
➩ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን
አስወግድ
➩ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን
➩አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ
➩በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን
➩የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር
➩ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ
➩ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን
ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ
የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች
ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ
➩ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል
ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ
ያሳምናቸዋል።
........... ............
@yebezigetmoch ❤️
እንኳን ደህና መጣቹ
፡ ሼር በማረግ ወዳጆን ይጋብዙ
ሰውየው ገብጋባ ቢጤ ነበር ታዲያ ወደ ቦሌ ለመሄድ
ፈልጎ
ታክሲ ያስቆምና "ባለ ታክሲ አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ
በስንት
ትውስደኛለህ?" ሲል ይጠይቀዋል ባለ ታክሲውም
"ሁለት ብር"
ሲል ይመልስለታል::
"ለሻንጣዬ ስንት ታስከፍለኛለህ ማለት ነው?"
"ግዴለም ሻንጣውን በነፃ እጭንሎታለው"
"እንግዲያውስ አንተ ሻንጣውን ይዘህልኝ ሂድ እኔ
በእግሬ
እድርሳለው
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
@yebezigetmoch @yebezigetmoch
🌹🌹አንቺ የሌለሽ ጊዜ🌹🌹
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ #በቤዛዊት የተፃፈ
ክፍል ሶስት
.....ከሆስፒታሉ ወጥቼ ወደሰፈር እየገባሁ ነበር የትላንትናዋ እማሆይን አየሗቸው ምን ብዬ ልነግራቸው ነው ቅዱስ አመላክ ሆይ ኧረ እርዳኝ ብዬ በልቤ ፈጣሪዬን ተማፀንኩት፡፡አማሆይ ወደእኔ እየቀረቡ እኔም ወደእሳቸው እየቀረብኩ ነበር ገና ሰላም ሳይሉኝ ምን ሆና ነው ልጄ ደህና ናት ብለው ጠየቁኝ እኔም መራመዴን አቆምኩኝ ደህና ናት ማለት አልችልም አይደለችምና ግን እሳቸውን ማስደነገጥ አልፈለኩም መቆሜ አስደነገጣቸው እንደምንም አፌን ከፍቼ ደህና ናት እናቴ አማኑኤል ወሰዷት አልኩኝ ቁና ተንፍሼ፡፡ ደነገጡና መለስ ብለው ይሁን እግዚአብሔር ያውቃል የእኔ ልጅ አይ ሳላያት እኮ ወደ ፅዮን ማርያም ልሔድ ነው አሉኝ ከፊትለፊቴ ቆመው፡፡እኔም ወይ እናቴ በቃ አይጨነቁ እኔ አለሁ ድና ይመጣሉ አልኳቸው መነኩሴዋ ፈገግ አሉ ፈገግታቸው አስደነገጠኝ ምን መሆኔ ነው አልኩኝ እሳቸውም የኔ ልጅ ከፍ በል ተባረክልኝ አዎ እመጣለሁ እግዛሐር ከፈቀደ አልያም ትመጡ ይሆናል አደራህን ልጄን በምድር የሰጠሁህን በሰማይ እቀበልሀለው አሉኝ ደነገጥኩኝ አደራ እኮ ነው አማን እሺ እንዳትል አለኝ አእምሮዬ ልቤ ደግሞ በመታመኑ ደስ ብሎታል እሺ እናቴ አልኩኝ ልቤ አሸንፎኝ መነኩሴዋ በደስታ አመስግነውኝ ስማቸውን ጠየኳቸው እማሆይ ወሰኔ ይባላሉ እኔም አማኑኤል እባላለሁ አልኳቸው እና ወደቤቴ ገባሁ ቤት ስገባ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደቤተሰብ ሆነው እያወሩ ነበር ለመቀላቀል አሰብኩኝ ግን ካወራን አመታት አልፈዋል ዝም ብዬ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁኝ እና አልጋዬ ላይ ተወርውሬ በጀርባዬ ተኛውና ጣሪያው ላይ እያንጋጠጥኩኝ የመኝታ ቤቴ በር ተንኳኳ ሰራተኛችን ነበረች አማን እራት ላምጣልህ አለችኝ እኔም አዎ አምጪልኝ ከሻይ ጋር አልኳት ሰራተኛዋም በሩን ዘግታ ወጣች አምላኬ ሆይ እህቶቼን ጠብቅልኝ አደራህን ብዬ ከፈጣሪዬ ጋር ማውራት ጀመርኩኝ፡፡ የውስጤን ለብቻዬ ስለማብሰለስል ይጨንቀኛል የበፊት ህይወቴ ታወሰኝ ከቤት ስገባ ሰላም የምንባባለው ከወንድሞቼ ጋር በሪሞት ስንጣላ ከአባቴ ጋር ሚስጥር ስናወራ ብቻ ከልዕልት በፊት ቤተሰብ ነበርኩ ከልዕልት በሗላ ግን ባዳ ሆኛለሁ እንባዬ በጉንጮቼ ሲወርዱ ነበር የውስጥ ሰላሜን ማጣቴ የታወቀኝ ልዕልት ቤተሰቦቼ ያልወደዷት ከብዙ ወንዶች ጋር ያዯት ነበር ግን እኔ አልቀበላቸውም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከእንጀራ እናቷ ጋር ተጣልታ እኔ ጋር መጣች ብር ስለአልነበረኝ እኛ ቤት እንድትኖር ለምኜ አስገባሗት እሷ ከመጣች ጊዜ ጀምሮ ብርእና ዕቃ መጥፋት የጀመረው ልዕልት ወጥታ ስትመጣ እጇ ላይ ብር አይጠፋም በዚህ ምክንያት ሁሌ መጣላት ስለጀመርኩ ባገኘሁት ብር ቤት ተከራይተን ወጣሁኝ አጎቴ በውሳኔዬ ቢናደድም ብር ላከልኝ እኔም የዛን ቀን ብሩን ከምንተኛበት ፍራሽ ስር ቆጥሬ በፊትለፊቷ አስቀምጥኩት እቅዳችን ቅዳሜ ዕቃ ልነገዛ ነበር፡፡ነገር ግን ሌላ ሆነ በእሷ ምክንያት ከወጣሁበት ቤት ልብሴን ላመጣ ሔድኩኝ የዛን ቀን አባቴ ሲያየኝ አንተ ልጅ ግን ምነው ቀልብ አጣህ አለኝ እኔ ግን ዝም ብዬው ልብሴን ሰብስቤ ስወጣ መጨረሻህ አያምርም አለኝ እውነትም ቤት ሰገባ ልዕልት የለችም ፍራሹ እንደተነሳ ያስታውቃል ብሩን ሳየው የለም ያስቀመጥኩት መቶሺ ብር የለም ትመጣለች ብዬ ብጠብቃት አልመጣችም ሳምንት ሙሉ ጠበኳት እሷ ግን ቀረች በስተመጨረሻ ግን ዱባይ ሀገር ከሔደው አብሯ አደጌ ጋር ተጋብታ ሄደች አሉኝ እንባ ሳቅ ጩኸት ስሜቴ ተዘበራረቀ የምወደው አብሮ አደጌ ከአፈቀርኳት ጋር ለማመን ከበደኝ የግድ ታምሜ ስለነበር ወደቤቴ ተመለስኩ ከዛን ጊዜ በሗላ ነው አጎቴ ስለሚወደኝ እንዳልጨነቅ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አስገባኝ ታክሲውንም የሰጠኝ እሱ ነበር፡፡ አጎቴ የሚኖረው አሜሪካ ነው፡፡ ብቻ ግን አሁን ሌላ ነው ሁሉም ተቃራኒ ፡፡ ከሐሳቤ ባነንኩኝ.....ሰራተኛችን እራቴን ይዛ መጣች አቀራረቧ በጣም ነው የምወደው የቀረበልኝን ምግብ በትኩስ ሻይ አጣጥሜ ተጠቅልልዬ ተኛሁ የወጣቷ ነገር አሳስቦኛል ምን ይዤ ነው የምሔደው እየጨነቀኝ በዛው ድብን ያለእንቅልፍ ወሰደኝ
ፀሐይ ከአድማሱ ፍንትው ብላ ወጥታ በወፎች ዜማ ታጅባ ወጥታለች፡፡እኔም ከተኛሁበት ያባነነኝ የእማዬን ድምፅ ስሰማ ነበር ተንጠራርቼ ከአልጋዬ ላይ ወርጄ ከመኝታ ቤቴ ወጣሁ፡፡ስወጣ ሁሉም ገበታ ላይ ተሰብስበው በተለያየ ሳህን እየበሉ ነበር እኔም ፊቴን ታጥቤ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ አንድ ሳህን አንስቼ ተቆረጠውን እንጀራ እየዘረጋሁ ቡርቴ(የቤት ሰራተኛችን) ቆንጆ ለታመመ ሰው የሚሆን ሾርባ ስሪልኝ አልኳት ቡርቴም እሺ ብላኝ ወደኩሽና ሄደች፡፡እኔም ወጥ እየጨለፍኩ ከፈቀዳቹልኝ እማዬ ለተደፈረች እና የአእምሮ ህመም ላለባት ምን ላድርግላት አልኳቸው ቀና ብዬ ሳላያቸው ሁሉም ዝም አሉ አውርቼ አላውቅም ነበርና እግሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ ቀና ማለት ፈራሁኝ............

😔ክፍል አራት እንዲቀጥል 👍 ድምፅ ይስጡን
👍 ማንን ገደለ😉
@yebezawit ላይ እስኪ ጫር ጫር ያርጉልን፡፡
ደራሲ ቤዛዊት
🌹በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ የፍቅር ታሪክ❤️
በግጥም መንደር #ብቻ
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💐 #አንቺ_የሌለሽ_ጊዜ❤️
📚
📚አንቺ የሌለሽ ጊዜ📚
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ #በቤዛዊት የተፃፈ
🍁ክፍል አራት🍁
.......የሰውነቴ መንቀጥቀጥ እየጨመረ ሲመጣ ታወቀኝ "ለዛሽ ሴት ነው" አባዬ አናገረኝ ቀና ሳልል አየደለም አባዬ ሌላ ናት ስሟን አላውቀውም አልኩኝ እንጀራውን በወጥ እየለወስኩ እህቴ ቀጠለች ወይኔ ታዲያ ግን የት ናት የት አገኘሀት ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ እኔም እዚህ ሰፈር ነበረች ከትላንት ወዲያ ለሊት ነውያየሗት ጠዋት ምግብ ልሰጣት ስሔድ ሰውነቷ በደም ተለውሶ......ሲቃ አነቀኝ፡፡ አባቴም አማን ታዲያ እኛ ምን እናርግልህ አለኝ፡፡ ቀናአልኩኝ ሁሉንም አየሗቸው እና ደህና ስትሆን እዚ ትመጣ ለማለት ፈልጌ ቃላትን አማጣኩኝ፡፡ግን አቃተኝ ምን አይነት እንክብካቤ ነው የሚያስፈልጋት አልኩኝ በዚህ መሐል ቡርቴ ሾርባውን ይዛው መጣችና የምግብ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጣ ተመለሰች እናቴም ቀጠለች ትምህርትህን ሳታቆም እየሔድክ እያት ምግብ ምናምን እኔ ጠዋት አዘጋጅልሀለው አለችኝ እንባዬ መጣ፡፡ ለማልቀስ ግን አልሞከርኩም ያንከባለልኩትን እንጀራ ሳልጎርስ አመስግኛቸው ወደ መኝታ ቤቴ ሮጥኩ.........................ልብሴን ለባብሼ ቡርቴ የሰራችውን ሾርባ ይዤ ወጣሁኝ መንገዱ ረዘመኝ አመት የተጓዝኩ እያህል አቁነጠነጠኝ መድረሴ አይቀርምና ደረስኩ አማኑኤል ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ገባሁኝና በአይኔ መቃኘት ጀመርኩ ስፖርት የሚሰሩ ህመሟን አሉ ለእነሱ ይሄ ሆስፒታል አለማቸው ነው በነፃነታቸው ውስጥ ሳቅ ረብሻ ለቅሶ ንዴት ደስታ ያስተናግዳሉ ግን አያውቁትም አለማወቃቸው ግን ጠቅሟቸዋል ሰው አያስከፉ ብቻ እነሱንም እግዚአብሔር ያስባቸዋል አልኩኝ ለራሴ ወጣቷን ያየቻት ዶክተር ቢሮ አቀናሁ እና የእንጨት በሩን ሁለቴ አንኳኳሁ ይግቡ የሚል ድምፅ ተሰማኝ በሩን ቀስ ብይ ስከፈት ሲጥጥጥጥ የሚል ድም ፅ ከበሩ ወጣ ልገባ ዶክተር አልኩኝ መነፅሯን አያወለቀች ግባ አለችኝ በሚያምር ፈገግታ እኔም በሩን ዘግቼ ፊትለፊቷ ካለው ወንበር ጫፍ ላይ ተቀመጥኩኝ ቀጠል አርጌ ትላንት መጥቼ ነበር ከአንዲት ወጣት ጋር አልኳት ዶክተሯም አዎ አስተውሼሀለው ለመግባባት ያመቸን ዘንድ ዶክተር ሊያ እባላለሁ አለችኝ እኔም ስሜን አቆላምጬ አማን አልኳት ዶክተሯ ቀጠለች እሺ አማን ያው ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊውን ምርመራ አድርገንላታል፡፡ እናም በጣም የአእምሮ ጭንቀት ነበረባት ይህ ነገር ደግሞ ሲፈጠር በይበልጥ........አላስጨረስኳትም እሷ እኮ እብድ ናት አልኩኝ ቃሉ ለራሴ ዘገነነኝ ይቅርታ ዶክተር እኔ ሳውቃት የአእምሮ ችግር ነበረባት አልኩ አስተካክዬ ዶክተሯም ተሽከርካሪ ወንበሯን እያንገላታች አዎ የዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ብዙ ህመሟን ገጥመውኛል የእሷ ደግሞ ከዚህ የተለየው የደረሰባት ጥቃት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የሚያቃት ሰው ብናገኝ ምርመራችንን ያረጋግጥልህ ነበር ወጣቷ በጣም በመጨነቋ የመጣ የጤና መቃወስ ሲሆን አስፈላጊውን ህክምና ክትትል ማግኘት ከቻለች በቀላሉ ትድናለች ግን ለመዳን የሚያስፈልጓት ቅድመ ሁኔታወች አሉ ብላ ከፊቷ ያለውን ካርድ ከፈተች እኔም ለመስማት ተመቻችቼ ተቀመጠኩኝ ቀጠለች "ለእሷ ጥቅም ሲባል ካላስፈላጊ ጭንቀት ከዚህ መውጣት አለባት፡፡ ይሔን ያለነው ለሊት ላይ ለሌሎች ታከሚዎች የእንቅልፍ መድሀኒት ሲሰጣቸው በመረበሿ እና እንቅልፍ በማጣቷ ነው ሲቀጠል በደረሰባት ፆታዊ ጥቃት ምክንያት ወንዶችን ማየትም መስማት አትፈልግም እና ቅርቧ የምትሆን እንስት ወይም ነርስ ታስፈልጋታለች የታዘዘላትን መድሀኒት ለመስጠት ለመመገብ እንዲሁም በየቀኑ እኔ ጋር በማምጣት የስነልቦና ህክምናዋን ትወስዳለች ሲቀጥል በትንሹ ወጣ እያለች አካባቢዋን ማየት ከተፈጥሮ ጋር ማስተዋወቅ አለብን ይሄ ደግሞ ለማድረግ የጀገነ ልብ ነው የሚያስፈልገው አለችኝ አፍጠጥጣ እያየችኝ እኔም ሁሉንም እችላለሁ አልኳት....................እኔ እና ዶክተሯ ከተነጋገርን በሗላ ከሶስት ቀን በሗላ እንደምወስዳት ተስማምተን ወደክፍሏ ልትወስደኝ ከክፍሏ ወጣን የወጣቷ ስሟ ግን ማነው አልኳት ዶክተሯም ይሄ በሂደት እናጣራለን ለጊዜው ግን ሚስጥር ብለናታል አለችኝ፡፡ ሚስጥር ዋው አልኩኝና በልቤ ዶክተሯን ተከትዬ ወደ ሚስጥር ክፍል ገባሁኝ አልጋው ላይ የሆስፒታሉን ፒጃማ ለብሳ ተኮራምታለች አሳዘነችኝ ገና ስታየኝ ፊቷ ተቀየረ ዶክተሯም ብዙ አትቆይ እንዳታስገድዳት ብላኝ ወጣች እኔም ጠጋ ብዬ ከፊቷ ቆምኩኝ ማልቀስ ጀመረች እንባዎቿ ልቤ ላይ ያለቁስል የነካኝ ያህል ህመሟ ተሰማኝ፡፡ ሚስጥር አልኳት ቀስ ብዬ እሷ ቀና ብላ አየችኝ እኔም ያመጣሁትን ሾርባ እያስቀመጥኩ አይዞሽ እሺ ትወጪዋለሽ አታልቅሺ አልኳት ሚስጥርም በእጇ አንሶላዋን እየፈተለች በአትኩሮት አየችኝ እኔም ነፍሷ መጨነቁ ገብቶኝ በሩን ከፍቼ ወጣሁ፡፡

ሚስጥርን በተከታታይ ቀናት ከክላስ መልስ እየሔድኩ ጠየኳት፡፡ታክሲዬን መንዳት ካቆምኩኝ ቀናት አልፈዋል ኪሴ ላይም ብሬ ተመናምኗል፡፡ የዛሬው ማለዳ ደግሞ ደምቆቦኛል ሚስጥር ልመጣ ስለሆነ መሰለኝ ውስጤም ደስታና ሰላም እየተሰማኝ ነው የራሴ መኝታ ቤት ተፅድቶ ተዘጋጅቷል ቤተሰቦቼም ቢሆኑም የሆነውን በሰሙ ጊዜ ልባቸው አዝኗል ታላቅ ወንድሞቼም አማን አብረንህ እንምጣ እና እናግዝህ አሉኝ ልወጣ የታክሲዬን በር እየከፈትኩ በደስታ መዝለል ብቻ ነው የቀረኝ ልቤ ደስታ በዝቶባት ልቧን እስክታጣ በደስታ ጮቤ ረግጣ እየዘለለች ነው፡፡ እኔም እሺ ብያቸው አብረን በእኔ ታክሲ ወደ ሆስፒታል አቀናን፡፡...................................................................... ክፍል አምስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ፡፡
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ

💓አንቺ የሌለሽ ጊዜ💓
በግጥም መንደር ብቻ
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@Yebezawit2
📚📙📘ከመፅሐፍት ጓዳ📗📕📒
በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም
የሚጠፋባቸው በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን
ወንዶች ደግሞ በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡

@yebezigetmoch
# like_share በማድረግ ይቀላቀሉን።
​​❍✰✰ቀልድና ቁምነገር┈━═☆
➣ዛሬ ለህይወትህ ዋጋ ካልሰጠሀት
ነገ ህይወት በተራዋ ዋጋህን
ትሰጥሀለች።
━━━━ ━━━━
➣ሰዎች ካደረጉልህ ይልቅ
ያላደረጉልህን እያሰብክ አትተቻቸው አትጥላቸው ምክንያቱም
አላስተዋልክም ይሆናል እንጂ ለራሳቸው ማድረግ
የማይችሉትን ለአንተ አድርገውልህ
ይሆናል።
━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━
❤️የግጥም መንደር❤️
😒ማጣትን ከፈረድክብኝ😔

የኔ ብዬ ጓደኛዬ ካልኩት
ደስታውን ሳልጠግብ ካጣሁት
የያዝኩት በረከት ካጣ
በልቤ የገባውም ከወጣ
በል አስቸልኝ ብቸኝነቴን
እንዳልሞት አርቅልኝ መርዙን
ብቸኝነቱን አደራ አስወድደኝ
አበረታኝ ማጣትን ከፈረድክብኝ፡፡
😢ቤዛዊት😢
25/11/2011
ለ...........ነው😒
😍አንቺ የሌለሽ ጊዜ😍
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
👉ክፍል አምስት👈
*****እኔና ወንድሞቼ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ገብተናል ዶክተሯ ከሩቅ አይታኝ በፈገግታ ወደእኛ መጣች፡፡እንኳን ደህና መጣቹ አለች እጇን ለሰላምታ እየሰነዘረች እኔም ለፈገግታዋ ፈገግታዬን እየመለስኳላት ታላቅ ወንድሜ ቀድሞ ጨበጣት እና እንኳን ደህና ቆያቹን አላት፡፡ሁኔታው ገርሞኛል ታላቅ ወንድሜ አናንያ ይባላል የሁላችንም ታላቅ ነው የተመረቀው በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ነው ከእሱ ቀጥሎ ባርኮት አለ ባርኮት ደግሞ በሆቴል ማኔጅመንት ተመርቆ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ነው የሚሰራው ከባርኮት ቀጥዬ እኔ ከእኔ ቀጥለው ደግሞ ሄለን ሜሮን ናቸው፡፡የአናንያ እንደዚህ መሆን እየከነከነኝ ወደ ሚስጥር ጋር ሄደኩኝ ሚስጥር ለሌሎች ህመሟን ስፖርት ከሚሰሩበት ቦታ ላይ ተቀምጣ እያለቀሰች ነበር እንባዋን ባለየው ደስ ባለኝ ቀስ ብዬ ከአጠገቧ ተቀመጥኩኝ እሷ ግን ቀና ብላም አላየችኝም እንባዋ ሽቅብ እየወረደ ሳሩን እያራሰ ነው፡፡ሚስጥር አልኳት ቀና ብላ እንድታየኝ መልሷ ዝምታ ሆነ እንደዛ በአንድ ምሽት ስትፈነጥዝ አይቻት አሁን ላይ ከማልቀስ ውጪ የሀዘንሲቃ ድምፅም የለም ቀና ብዬ ሰማዩን አየሁት በነጭ ደመና ሸማ ግርማ ሞገስ ተላብሷል ፈጣሪን ጋርዶት ይሆን አልኩኝ በልቤ የሀጥያትን ወሬ እየፈተልኩኝ፡፡ ነፃነት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት ከተማዋ በእርግጥ ያበደ ብቻ ነው ያላት የለየለት ነገን እና ሰውን ረስቶ በራሱ አለም ይኖራል እኔን የመሰለ ደግሞ በልቡ ሰማይ እያጉረመረመ በራሱ ነፃነቱን ተቀምቶ ነገን እያመለከ ሰው የሚባለውን ፍጥረት ከራሱ በላይ ፈርቶ እንደራሱ ሳይሆን እንደሌላው ይኖራል***************************አንተማነህ አለች ሚስጥር ደነገጥኩኝ እየቀዘፍኩ የነበረውን ሀሳብ አቆምኩኝ፡፡ማን ነኝ ልበላት ቀጠለች ይዘኸኝ ጥፋ!!!አስወጣኝ!!! በሀይለ ቃል ጮኸች፡፡ከተቀመጥኩበት ተነሳሁኝ ነርሷ እየሮጠች መጣች ሚስጥርም ፀጉሯን እየነጨች አስወጡኝ አስወጡኝ.......................ደም ከአፍንጫዋ መፍሰስ ጀመረ ሽባ ሆንኩኝ አይኖቿ አንባን እያፈሰሱ ቀልተዋል ዶክተሮች እና ነርሶች ተረባርበው ወደክፍሏ አስገብተው መድሃኒት ሰጧት፡፡ እውነትም ጨንቋታል ዶክተሯ ጠራችኝ እኔም እንደምንም እግሬን ከመሬት ላይ አላቅቄ ተራመድኩኝ የዶክተሯ ቢሮ ክፍት ነበር እና ሳላንኳኳ ገባሁ ባርኮትና አናንያም ውጪ ነበሩ ዶክተሯ ከመቀመጤ ማውራት ጀመረች አማን እንደምታያት ሚስጥር ተጨንካለች አእምሮዋ በመታወኩ ነው እንደዚህ የምትሆነው ይሄ ደግሞ እስከምታገግም ያጋጥማል በመሆኑም አሁን ስትወስዷት ይሄን መድሀኒት ግዙ ጠዋት ምሳ ሰአት ማታ እና ለሊት ነው የምትወሰደው አለችኝና ወረቀት ሰጠችኝ ቀጠል አርጋም ያው እዚህ መመለስ የለባትም እኔ በቻልኩት አቅም እየመጣሁ አያታለው አልያም ደግሞ ጎበዝ ጓደኛ አለኝ እሱ ጋር እልካችሗለው አለች፡፡ እኔም ይሆናል የምትይውን አርጊ አልኳት ዶክተሯም በቃ አስሬ ከምንቀያየርባት ዶክተር እዮ ይባላል የስራ ቦታውም ሜክሲኮ ነው ብላ የቢዝነስ ካርድ አውጥታ ሰጠችኝ እኔም እሺ ዶክተር ሁሌ ነው የምወስዳት አልኩኝ ዶክተሯም አዎ ነገ ውሰዳት እና ከእሱጋር ትወስናላቹ አለችኝ እኔም እሺ ብያት ተነስቼ ልወጣ ስል ዶክተሯም አማን የምረዳቹ ነገር ካለ ዝግጁ ነኝ ጉዳዩን ህግ ስለያዘው አትጨነቁ አለችኝ እኔም አመስግኛት ወጣሁ፡፡
.................ሚስጥር እንደተኛች ነበር ወደታክሲ ያስገባናት እነአናንያ አብራዎት ነበር የተቀመጡት እሷን እላያቸው ላይ አስተኝተው እኔም በፍጥነት በዝምታ ውስጥ ሆኜ ታክሲውን አበረርኩት፡፡መንገዱ ዝግ ባለመሆኑ ቶሎ ነበር የደረስነው አእናቴም ቤቱን አዘጋጅታ ነበር ከታክሲው አቅፌ አወረድኳትና ብቻዋን እንዳትሆን ሳሎን ካለው ሶፋ ላይ አስተኝቼ ጋቢ አለበሰኳት እና ዶክተሯ የሰጠችኝን መድሀኒት መግዣ ወረቀት ለባርኮት እየሰጠሁት መግቢያው ጋር ካለ ፋርማሲ ገዝተህ ና አልኩት ባርኮትም ተነስቶ ወጣ አናንያ ለእናቴ እና ለአባቴ ስለዶክተሯ ቁንጅና እየተረከላቸው ነው፡፡እኔም ከሚስጥር ጎን መሬት ላይ ተቀምጬ እያየሗት ነበር፡፡ባርኮት መድሀኒት ገዝቶ መጣ እና ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው እኔም ልብሴን ልቀይር የራሴ መኝታ ቤት ተሳስቼ ገባሁኝ ለሚስጥር እንደሚሆን ሆኖ ተዘጋጅቷል በጥግ በኩል የኪዳነምህረት ስዕለ አድኖ አለ የመኝታ አምፖል ጋርም የፀሎት መፅሐፍ እና መፅሐፍ ቅዱስ ተደርድሮ ተቀምጧል አባዬ እንዳስቀመጠው ገባኝ አባቴ ነው ከእኛ ቤት በእግዚአብሔር ቃል የሚበረታ ሁላችንም ደካሞች ነን አናነብም እሱግን ይወዳል፡፡መኝታቤቴን ዘግቼ ወጣሁኝና የባርኮት ክፍል ገብቼ ቀየርኩኝ ያረኩትን ልብስ በሰማያዊ ቲሸርት በዳልቻ ቁምጣ ተክቼ ወጣሁኝ ሚስጥር እስከ ምሽት ድረስ አልተነሳችም ነበር የሰጧት ምንአልባት የእንቅልፍ መድሀኒት ይሆናል አልኩኝ ሁሉም አይኑን ሚስጥር ላይ አርጓል ለቤቱም አዲስ ናትና፡፡ እኔም እማዬ አልኳት እናቴ ግን ዝም አለች ሰምታ እንዳልሰማች ደግመን ልንጣላ ባልሆነ አልኩኝ ግን የሚመልስ ጠፋ ልብሴን ቀይሬ ስመጣ ሁሉም ተቀይሯል ሁፍፍፍፍ አሁንስ አልኩኝ እናቴም እኔን ነው ሁፍፍፍ በቃ የምትፈልገውን አረካ ምንም ንግግር አያስፈልግም ብላኝ ተነስታ ወደኩሽና ወጣች ምንድነው አልኩኝ ሄለንም ያናገርንህ እስክታመጣት ነው እንጂ ይቅር ብለንህ አይደለም አለችኝ ቆይ እኔ አይደለሁ የተጎዳሁት እናንተ ምን ጨነቃቹ አልኩኝ በብስጭት ሚስጥር ጩኸቴ አባነናት ..........ሚስጥር አልኩኝ ሚስጥርም ቤቱና ሰዉ አዲስ ሆኖባት በመንቀጥቀጥ ማየት ጀመረች እኔም ጠጋ ብዬ ተረጋጊ ተረጋጊ ቤትሽ.............ማልቀስ ጀመረች ተሰፈንጥራ ከሶፋው ላይ ተነሳች አባቴም ዊልቸሩን ወደእኛ ነድቶ የኔልጅ ብሎ ሊነካት እጁን ሲሰነዝር ወደእኔ ተጥግታ ተጣበቀች እና አስወጡኝ አስወጡኝ የቅድሙ ስሜታዊነቷ ተመለሰ እኔም አቅፌ ወደተዘጋጀው ክፍሏ ወሰድኳት እና አልጋ ላይ አስቀምጥኳት በጭንቀት ፀጉሯን እየነጨች ነበር እጇን ያስኩት እና አቅፌ አባበልኳት እንባዋ ደረቴላይ ሲፈስ ታወቀኝ...............
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_ተመስርቶ_በቤዛዊት_የተፃፈ
💜ክፍል ስድስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ💜

በቤዛዊት

👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch
@yebezawit2 👈
@yebezawit2 👈
@yebezawit2 👈
❤️❤️እውነታዬ❤️❤️
★★★★ሰዎችን ለመርዳት የግድ ገንዘብ አያስፈልግህም ምን አልባትም ያንተን ጊዜ እንክብካቤ ፍቅር❤️ ፈልገው ይሆናልና ገንዘብ የለኝም ብለህ ሌሎችን ላለመርዳት ምክንያት አትደርድር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ላንተ ትንሽ የምትመስልህ እርዳታ የሌላውን ሰው ህይወት የምትቀይር ልትሆን ትችላለች፡፡ነገር ግን ካለህ ላይ መስጠት ያቆምክ ቀን መኖርህ ያኔ ያከተማል!!....😍
........የተወደዳቹ የግጥም መንደር ቤተሰብ እና ጓደኞቼ ባለፉት ጊዜያት ነድያንን እና አዛውንቶችን ለመርዳት መንቀሳቀሳችን ይታወሳል አሁን ላይ ደግሞ #ለሕግ_ታራሚዎች መፅሐፍ በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ መፅሐፍ ማበረከት የምትፈልጉ የቀና ልብእናሀሳብ ባለቤቶች ያነበባቹትን መፅሐፍ በማስረከብ ውጪው የናፈቃቸውን በፀፀት ያሉትን ወጎኖቻችንን እንጠይቅ፡፡🙏

"ለራሳችን የምናደረገው ሁሉ ከእኛ ጋር አብሮ ወደ መቃብር ሲወርድ፤ ለሌሎች የምናደረገውና ለዚህች አለም የምናበረክተው ነገር ግን #ዘላለማዊ ነው፡፡" በሚል መሪ ቃል አብረን እንስራ፡፡

@yebezawit2 ላይ ያናግሩን

+251983744901 ይደውሉ🙏

የግጥም መንደር
አንድ መፅሐፍ ለወዳጆ
ሼር በማረግ ያግዙን 🙏☝️