የግጥም መንደር
1.72K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
kako Getachew
Adeye | አደዬ
👥Kako Getachew
🎵አደዬ

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
Ur #1 Choice 🎼
ተጋበዙልኝ ሰናይ ቅዳሚት😍😍
🌺💞🌺💞🇪🇹#ፍቅር 🇪🇹🌺💞🌺💞

የንብ ቀፎ እና የመልካም ሰዎች
ጭንቅላት አንድነው፡፡ በንብ ቀፎ ውስጥ
ጣፋጭ ማር እደ ምታገኝ ሁሉ . . .
በመልካም ሰዎች ጭንቅላትም ውስጥ
ደግሞ ጣፋጭና ማራኪ የሆኑ ቃላቶች ታገኛለህ፡፡

🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🇪🇹 #ሸጋ_ቅዳሚት! 🇪🇹
#ፍቅር_ያሸንፋል



@yebezawit2 @yebezigetmoch
አብነት አጎናፍር
የእውነት መንገድ
🎙 • አብነት አጎናፍር
🔊 • የእውነት መንገድ
@yebezigetmoch
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በዛሬው እና በነገው እለት ጋብቻቹን ለምትፈፅሙ ጥንዶች በሙሉ እንኳን ለዚህ ቅዱስ ቀን አበቃቹ 🌹 ቀሪ ዘመናቹ የፍቅር እንዲሆን ተመኘው 🙏
እንዲሁም ለእኔ እብድ ዴቭዬየደጓ ልጅለአንተም ነው
#እንኳን_ደስ_አለህ
#ላኮራሽ_ነው

አንቺ ተጨንቀሽ ተምረሽ
እኔን ሰው ልታረጊ ሰውነትሽን አጣሽ
መከራ በልተሽ ይኸው ደረስኩልሽ
በአንቺ ፀሎት በእርሱ ቸርነት
ለዚህ ክብር በቃው የኔ እናት
እማ #ላንቺ_ነው ይሄ የሚሆነው
በ21 እማ #ላኮራሽ ነው
ገጣሚ ቤዛዊት
@yebezawit2
💐🎓❤️🎓❤️🎓❤️🎓❤️🎓
"ለእኔዋ እናቴ እወድሻለሁ"

በነገው እለት ለምትመረቁ የቅድስት ልደታ ኮሌጅ ተማሪዎች ጓደኞቼ እንኳን ደስ አላቹ፡፡

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓


#ይገባናል 😉💐🎓
የኔ ወዳጅ

ለውድ ወዳጀ #ቤዚ_የራጉኤል የፃፍኩት

በአባቶቸ ልሳን ልመርቅሽ እቴ
ደስታሽ ደስታየ ነው ምኞትሽ ምኞቴ
የዚህ አለም ዕጣ መንገዱ ባይገባን
አንዱን ስንጨርስ ነው ሌላው የሚጠራን
እምነት እውነት ተስፋ
በሄድሽበት ሁሉ አብሪው እንዳይጠፋ
ሁሌ እንደምትይኝ ፅናት ነው የኛ አለም
ዛሬን ስንጀግን ነው ነገ የሚታለም
እና የኔ ወዳጅ ለነገው መንገድሽ
እንኳን ዛሬን በለጥሽ
በኩራት አሸነፍሽ

ውድ ወዳጀ እንኳን ለዚህ ቀን በቃሽ ነገን ደግሞ እናሸንፋለን።

አማኑኤል ደርበው

👈 @kene_tobeya
👈 @kene_tobeya
👈 @kene_tobeya
አማንዬ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
*የኔ ተመራቂ*****
ሠንበት እሁድ ልዩ ቀን ነው
የአመታት የድካምሽ ፍፃሜ ነው
እናም ውዴ ደስ ይበልሽ
ተደገመ ምርቃትሽ
ድሮ በእናት ድሮ በአባት
አሁን ደሞ በእውቀት መአድ እውቀት ሀብት
የኔ ጀግና ከፍ አልሽልኝ በምርቃት፡፡
::::::::::::::::::::://::::::::::::::::::::
********(Bk)************

ብሮክዬ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
Congra ለእኔ 😉😉👍
🌸ምን አልባት🌸
ክፉ ቃል ከወጣው አንደበቴ
ከአሳዘንኩህ አንተን አባቴ
ምን አልባት እኔ አልሆንም
አንተን ያሰከፋሁህ ስመልስም
ጥያቄህ ይሆናል ምን አልባት
የከፋህ በድንገት
ጠይቀው ጥያቄህን ለራስህ
እናቴ ናት ክብሬ ልንገርህ
መመለሴ ሳይሆን ያናደደህ
ምን አልባት ይሆናል ጥያቄህ
🌸🌸🌸🌸👍👍👍
@yebezawit2
@yebezigetmoch
ገጣሚ፡ቤዛዊት የሴት ልጅ
#21
📚አንቺ የሌለሽ ጊዜ📚
ደራሲ ቤዛዊት
ክፍል1
....የጎሳዬ ዘፈንን እየሰማሁ በጨለማው አቀበቱን እየወጣሁ ነበር ጨለማው በከተማው መብራት የተሸነፈ ይመስላል አማኑኤል እባላለሁ የሙዚቃ ተማሪ እና የታክሲ ሹፌር ነኝ ቀን ቀን ብማርም ባለኝ ጊዜ ደግሞ እሰራለሁ ከ4:00 በሗላ ትንሽ አርፌ ለወክ እወጣለሁ የለሊት ወክ ደስ ይለኛል ንፋሱም ሀይል አለው ጨረቃም ድምቀት ነው ከሰው ርቄ መኖሩ ባያስደስተኝም አይከፋኝም ለዚህ ሁሉ ምክንያት የድሮዋ ፍቅረኛዬ ናት ልዕልት ትባላለች የተዋወቅነው በአጋጣሚ ነበር አስታውሳለሁ የዛን ቀን ከግቢ ወጥቼ ታክሴን እያሽከረከርኩ ነበር ሀይለኛ ዝናብ እየዘነበ ነበርና ልዕልት ደግሞ ድልድይ ስር ተጠላ ነበር ሳያት ደስ አለኝ አልፊያት ሄጄ ተመለስኩ እና መስኮቱን ከፍቼ የት ነሽ አልኳት እሷም ጊዮርጊስ አለችኝ እኔም እዛው ነኝ ነይ ግቢ አልኳት ግን ወደዛ አልነበርኩም፡፡ልዕልትም ወደመኪናዬ ገባች ከዛን ቀንበሗላ ስልክ ተቀያይረን ማውራት ጀመርን እኔም ክንፍ አልኩኝ በተለይ ሳቋ አይጣል ነው በደቂቃ ትናፍቀኛለች በየቀኑ እንገናኛለን እንዴት ፍቅረኛሞች እንደሆንን ግን አላስታውስም ብቻ ግን ከቤት ተባራ እኔ ጋር የመጣች ጊዜ ነው አፈቅርሀለሁ ያለችኝ፡፡ እኔ እና ልዕልት ያላየነው ያላሳለፍነው የፍቅር ጊዜ የለም ለዚህም ነው ከልቤ ያልወጣችው የተለያየነው ለእኔም ጥያቄ ነው ብቻ ግን በአንተ ደስተኛ አይደለሁም ብላ ነበር የተለየችኝ አሁን የት እንዳለችም አላውቅም...............አቀበቱን ወጥቼ ወደሰፈሬ መግቢያ ጋር ስታጠፍ ፀጉሯን አንጨፋራ ጥላሸት የመሰለ ፒጃማ ለብሳ ጨረቃዋ ላይ አፈጥጣ እያናገረች አንዲት ወጣት እንስት አየሁኝ ደነገጥኩኝ የያዘችው ድንጋይ የተጨማደደ ሀይላንድ ዝም ብዬ ቆምኩኝ ሲያሻት ትስቃለች አንዴ ታለቀሳለች እድሜዋ ከ23 አያልፍም እሱም ይበዛል ድንገት እያየሗት ፊቷን አዞረች ከተንበረከከችበት ተስፈንጣራ ተነሳች..............
❤️አንቺ የሌለሽ ጊዜ❤️

ከፍል ሁለት ይቀጥላል
እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ👍
ደራሲ ቤዛዊት ብቻ
@yebezigetmoch 👌
@Yebezigetmoch 👌
@yebezigetmoch 👌
ለሐሳብ አስተያየት @yebezawit2 ላይ ጫር ጫር አርገው ቅረጫታችን ላይ ጣል ያርጉልን መልሰን ወደእናንተ እናደርሳለን፡፡
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
💟❤️❤️🇪🇹🇪🇹💒💒

💙ትህትና የሚመነጨው በራስ ከመተማመን ነው።

💜ተግዳሮቶችህን ሳይሆን በረከትህን ቁጠር።

💛የምር እንዲሳካልህ ከፈለክ ሳትጨርስ አታቁም።

🖤አብዛኞቻችን እርግፍ አድርገን የምንተወው ሊሳካልን ጥቂት ሲቀረን ነው።

💚የበረዶ ተራራን እየወጣህ ወይም እየተዎጋህ አንዲት ስህተት ለሞት ልትዳርግህ ትችላለች ስለዚህ ስህተትህን ቀንሳቸው።

💚ለመባል ሳይሆን ለመሆን ጣሪ ምክንያቱም ስትሆኚ መባሉ አይቀርም እና።

❤️አብኛዎቹ ሰዎች የሚወድቁት ችሎታ ወይም ክህሎት ስላነሳቸው ሳይሆኑን ስለሚተውት ነው።
❤️💛💚💙💜🖤🖤💜💙💚
እግዛብሔር በቸር ያውለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@yebezawit2
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😜እብድ ነኝ እንዴ?😃

እሷን ሳያት ገና እንዲ የሚያደረገኝ
ሄጃለው ብዬ የሚመልሰኝ
ከሄድኩበት ቦታ የማያሳርፈኝ
ምን ይሆን የልቤ ምክንያቱ
የሩቅ ሰው ከሩቁ መናፈቅ መጎተቱ
ፍቅር ነው ወይስ እብድ ነኝ
ከአበደች 😉ጋር አብሬ ያበድኩኝ
ከቁምነገር በላይ ሳቋ ከጎተተኝ
ከቤት በሀሳብ ወጥቼ እመለሳለሁ
ባያሁት ነገር ሁላ እስላታለሁ
ሚስጥሩ ጠፋ እንጂ እሷን ለመውደዴ
እሷን ያስባለኝ ግን፡እብድ ነኝ እንዴ???😜

ገጣሚ ቤዛዊት
መነሻ ሀሳብ K
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💪 ወንድነት💪

መልበስ ማጌጥ መዘነጥ
ሴት ላይ ሴት ማማረጥ
ይሄ አይደለም ልኩ የወንድነት
ክብር የሚሰጥ ለሁሉም ሴት
ታማኝ ለፍቅሩ ዘማች
ለፍቅሩ ለቤተሰቡ ሟች
ይሄ ነው ለእኔ ልኩ የወንድነት
ለልብሱ ሳይሆን የማጨነቅ ለማንነት
ክፋ የማይወጣው ቁጥብ ለቃላት
የሰውም ሳይሳደብ አክባሪ የራሱን እናት
ይሄ ነው ለእኔ #ወንድነት 💪💪

ገጣሚ ቤዛዊት
👉 ለማንኛውም ሀሳብ ነቀፋ @yebezawit2 ላይ ጫር ጫር ያርጉልን👈
Tewodros Mosisa
መልኬ
🔊Only At @yebezigetmoch

💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ስለወደድኩት 😉
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Yebechaye | የብቻዬ
Mulugeta Alemu
🎵 @yebezigetmoch 🎵

❤️የህግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ነው❤️
❤️❤️አንቺ የሌለሽ ጊዜ❤️❤️
ክፍል 2 የፍቅር ታሪክ
#ቤዛዊት
አነሳሷ አስደነገጠኝ ከሮጥኩኝ በያዘችው ድንጋይ አትስተኝምዝም ብዬ ቆምኩኝ ፍርሀቴ ፊቴ ላይ ቢነበብም ግን ቆምኩኝ ተስፈንጥራ ብትነሳም በዝግታ ነበር የቀረበችኝ ጠጋ አለችና ምግብ ምግብ ብላ ጮኸችብኝ ከየት ላምጣው ከማላምጠው ማስቲካ ውጪ ምግብ ቀርቶ ምግብ ቤት የለም የደረቀው ከንፈሯ ሳበኝ ስትጮህ ከመደንገጥ ውስጤን ደስ አለው እኔም እኛ ቤት ልውሰድሽ አልኳት በረጅሙ ሳቀች እና በጣም በፍጥነት በእንግሊዝኛ አወራች ለራሴ ጠየኩት አልተማርኩም እንዴ አልኩኝ ውስጤ የተማረች መሆኗን ጠረጠረ አንቺ አውቆ አበድ የሚል ድምፅ ከበስተሗላዬ ተሰማኝ ዞር ብዬ አየሁኝ አንድ መነኩሴ ናቸው በአረንጓዴ ሳህን ላይ በጥቁር እንጅራ ሽሮ ወጥቶበታል ቀፈፈኝ የእኔ ልጅ አንተስ ምን ሁነህ ነው አሉኝ ምግቡን ለወጣቷ እየሰጡ እኔም በዚህ ጋር ነበር መንገዴ እሷን አይቼ ነው የቆምኩት አልኳቸው ፍፁም ትህትናቸው ገርሞኝ የምትነካህ መስሎህ ነው አሉኝ እኔም አይ አይደለም አልኳቸው ቀጠል አርጌም አሳዝናኝ ነው አልኩ በሽንፈቴ እንዳይስቁ ዋሽቼ መነኩሴዋም የማያዝን ማን አለ ብለህ ይቺን የመሰለች ልጅ ከማለታቸው ወጣቷ ጮኸች እና ሳቀች ሽሮው እና አመጋገቧ አፒታይት ይዘጋል መነኩሴዋም ቀጠሉልኝ መድሀኒት እኮ አላት እዚህ ስትመጣ ግን ምን ዋጋ አለው ማን ይስጣት በትና ጨረሰችው አሉኝ በሀዘን ስሜት እኔም ታሪኳን ለማወቅ ጓጓሁኝ ለሊት መሆኑ ተረሳኝ እዚህ አልነበረችም እንዴ አልኩኝ መነኩሴዋም አዎ እኔም ያገኘሗት በቀደም ነው ግን ሰዎች የነገሩኝ ከሌላ ቦታ መምጣቷን የምስለኛል ከአረብ ነው የመጣችው አሉኝ እኔም ስታሳዝን አልኩኝ በልቤ መነኩሴዋም መሽቷል ልጄ ሳታይህ እለፍ ብለው በእናትነት ስሜት ሸኙኝ፡፡
የግቢውን በር ከፍቼ ቀስ ብዬ ገባሁ የቤቱ ሰው ሁሉ ተኝተዋል የምኖረው ከእናት ከአባቴ ጋር ቢሆንም እድሜ ለልዕልት አንነጋገርም የድሮዋ ፍቅሬ ህይወቴን አንግታው ነው የሄደችው ወደ ሳሎኑ ቀስ ብዬ ገብቼ ሳፋ ላይ የተቀመጠውን ጋቢ ለብሼ ሰለ ወጣቷ እያሰብኩኝ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ መንጋት አይቀርም እና ምድር በፀሐይ ነበልባል እየተቀጣጠለች ነው በመስኮቱ የሚገባው ጨረር ቀሰቀሰኝ እና በግድ ተነሳሁኝ አጠገቤ ያለውን ስልክ አብርቼ ሰአቱን አየው ሶስት ሰአት ሊሆን ነው ከመቅፅበት ተነሳሁኝ የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ምግብ በፌስታል ገልብጬ ልብሴን ቀይሬ ወጣሁ ይሄን ሳደረግ አባቴም እናቴም በትዝብት እያዩኝ ነበር እኔ ግን ምንም አላልኩም አባቴ አካል ጉዳተኛ ሲሆን በዊልቸር ነው የሚንቀሳቀሰው ባያኮረፈኝ ብዙ አወራው ነበር ምክንያቱም ከእናቴ በላይ እሱን ነበር የምቀርበው አባቴ ኢንጂነር ነበር ከሚሰራበት ፎቆላይ ወድቆ ነው እንደዚህ የሆነው ውጪ የሚወጣው አሁን በስንት ጊዜ አንዴ ህይወቱ ላይ የገጠመው ነገር ውስጡ ገና አልተቀበለውም እና ሰዎች ሲያዩት ይሸማቀቃል እናቴ ደግሞ ተደራጅታ ሆቴል ቤት ዋና ሆና ትሰራለች ሁለት ታላቅ ወንድም እና ሁለት ታናሽ እህቶች አሉኝ፡፡ የጊቢውን በር ወርውሬ ዘግቼ ማታ ያየሗት ወጣት ጋር አቀናሁ ስደርስ ግን ሌላ ታሪክ ተፈጥሯል ሰዎች ከበዋት አየሗት ልብሷ በደም ተጨማልቆ በጀርባዋ ራሷን ስታ ወድቃለች የያዝኩትን ፌስታል ለቀኩት አይኔ የዋሸኝ መሰለኝ ጠጋ ብዬ ሰዎቹን አሳልፉኝ ብዬ ተጠጋሗት እና የተዘረጋውን እጇን በእጆቼ ያስኩት በጣም ቀዝቅዟል የተመታ የሰውነት ቦታ የለም ተደፍራ ነው እያሉ የሚያወሩ የሰዎችን ወሬ ሰማሁ አቅፌ አነሳሗት ሰውም ኧረ ፓሊስ ይመጣ አሉኝ እኔ ግን ይዣት ሮጥኩኝ ምን እንደማስብ እራሱ አላውቅም ብቻ የሆነ ክሊኒክ ጋር ስደርስ እየጮኹ ገባሁኝ ተቀምጣ የነበረችው ቀጭን ነርስ ተሰፍንጥራ ተነስታ ዶክተር ነርስ ብላ እየተጣራች የተዘረጋው አልጋ ላይ እንዳስተኛት አግዛኝ ትንፋሿን አየችና ኦክስጅን ሰካችላት እና ግሉኮስ ሰጠቻት ዶክተሩም መጥቶ አያት እኔ በሩ ጥግ ላይ ደርቄ ከያቸዋለው የልብሷ መቆሸሽ የእግር ተረከዟ መሰነጣጠቅ የሰውነቷ መገርጣት ከቤት እንዳልመጣች ተረድተው ዶክተሩ ምኗ ነህ አለኝ እኔም እ..እ...እ ዘመዷ ማለት ጓደኛዋ ...እ...ተንተባተብኩኝ ዶክተሩም ከየት ነው የመጣቿት አለኝ አይኗን ገልጦ በመብራት እያየ እኔም ከታችኛው ጎዳና አልኩት ስሟ ማነው አለችኝ ሌላኛዋ ነርስ እኔም አላውቅም ማለት እብድ እኮ ናት አልኩኝ ቃሉ እየዘገነነኝ ዶክተሩም እህት እህት እያለ ሊቀሰቅሳት መኮረ እጇ ላይ የለጠፉላት ጨርቅ ነገር በኮምፒውተር በሚመሰል ላይ ቁጥር ያነባል የደም መጠኗን ነበር ቁጥሩ ይቀንሳል እንጂ አይጨምርም ዶክተሩም ፍሉድ ጨምሩ አለ እና እኔ እንድወጣ አረጉኝ ጨነቀኝ ምን እንደማረግ ከበደኝ ተከትሎኝ የመጣም የለም የማታዋም እናት መነኮሴም የሉም ልቤን በአፌ ልተፋት ነው ሁሉም ይሯሯጣል ፈጣሪዬ አታርግባት አልኩኝ ስልኬ ጠራ ከክፍል ነበር የደወሉልኝ ፈተና መኖሩን አስታወስኩ ፋይናል ግን አይደለም ዘጋሁት ከመስማት በላይ ጭንቄን የማወራው ሰው ናፍቆኛል፡፡ ከንድ ሁለት እያለ ሰአቱ ሰድስት ሰአት ሆነ ነርሷ ጠራችኝ ፊቷ ላይ ምንም አይነበብም መሯሯጥ አቁመዋል ቀስ ብዬ ገባሁኝ የገባሁት ዶክተሩ ጋር ነበር ዶክተሩም ተቀመጥ አለኝ የወንበሩ ጫፍ ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ እንዴት ናት አልኩኝ መልሱን ለማወቅ እየጓጓሁ ዶክተሩም ከአሁን ጥሩ ላይ ናት ደሟ ተስተካክሏል ነቅታለች አለኝ ለዘብ ብሎ አለመደሰቱ አስደነገጠኝ ምነው ዶክተር ሌላ ችግር አለ አልኩኝ ዶክተሩም አዎ አለ አንተ ለልጅቷ ምንድነህ አለኝ እኔም ትላንት ነው ያወኳት አልኩት ዶክተሩም ነርሷም ተደነቁብኝ እኔ ግን ችግር የተባለው ነገር ሳላውቀው ችግር ሆኖብኛል ዶክተሩም እኛ ሰዎች ሞት እና መከራ ያነሰን ከንቱ ፍጥረቶች ነን አለኝ ቀጠል አርጎም በአሁን ሰአት የሚረዳት የሚያግዛት ሰው ያስፈልጋታል አለኝ እኔም የአቅሜን ሳይሆን ከአቅሜ በላይ አረግላታለው ብቻ ትዳን አልኩት፡፡ዶክተሩም አሁን የምነግርህ ነገር ህግ ሊያውቀው ይገባል ልጅቷ ተደፍራ ነው እንደዚህ የሆነችው አለኝ የምድር አፍ ናፈቀኝ እያቃዠው በሆነ አልኩኝ ደነገጥኩኝ ጉልበቴ ካደነኝ ምንም አላልኩም እንደምንም ከዶክተሩ ክፍል ወጣሁኝ እንዴት ያለ ጭካኔ ነው እንዴት ማስቢያውን ያጣል አልኩኝ ፡፡ ነርሷም መጥታ ማየት ትችላለህ አለችኝ እኔም ገባሁኝ እና በድፍረት አይኗን አየሁኝ እጇን ከአልጋው ጋር ጠፍንገው አስረውታል አይኗ ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላ አቅጣጫ እየተንከባለለ ህመም ይጭራል ቀስ ብዬ የታሰረውን እጇን ልነካት ስል እንደመሸሽ ብላ ጮኸች እኔም ራኳትኝ እንደዛ ትላንት ከእግዜሩ ስራ ከሆነችው ጨረቃ ጋር እንዳላወራች አሁን ግን ያ በእብደት ውስጥ ያየሁት ነፃነት አይታየኝም ነርሷ አማኑኤል እንደሚልኳት ነገራኝ ነበር እና እዛስ ምን ትሆን አለኩኝ ትላንት መሳቅ ና መጮህ ነበር አሁን ግን ለቅሶ ጩኸት የማይገቡ ቃላት ናቸው ህመሟ ውስጥ ድረስ ተሰማኝ፡፡
ነርሷ በአምቡላንስ ከሁለት ፓሊሶች ጋር ላከችኝ የአማኑኤል ግቢ ገብተን ወሰዷት እጇን ከእጇ ላይ አጣብቃ የነካትን ሰው ሁሉ ትሸሻለች የልጅነት ወዟ ግን እንዲህም ሆና ትስባለች ፓሊሶች ጥያቄበጥያቄ አጣድፈውኝ አድራሻዬን ወስደው ተመለሱ እኔ ግን ግቢ ውስጥ ነበርኩ ብዙ ህመሟንን እያ"ሁ ከህፃናት እሰከ አዛውንት የኔዋን ወጣት ክፍል ሰጥተው ነርሶቹ አስተኟት እኔም ዶክተሯን አውርቼ ነገ ለመመለስ ከራሴ ጋር እያወራሁ ከሆስፒታሉ ወጣሁኝ.....

አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ
💔አንቺ የሌለሽ ጊዜ💔
ደራሲ ቤ
ዛዊት
ክፍል ሶስት እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ
👍 ማንን ገደለ 😉
😊 @yebezigetmoch 😊
☺️ @yebezawit2 🙂
🤡ደስ የሚል ምሽት🤡

ይቀጥላል
Forwarded from ጥበብ እና ጦቢያ
🌸🌸ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡

@tebeb_ena_tobeya
አዲሱን ቻናል ተቀላቀሉ @tebeb_ena_tobeya 😉😉
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
"እርሳስና ላጲስ አብረው ይኖራሉ ግብራቸው ተቃርኖ፣
የሚፅፈው ከታች አጥፊው ከላይ ሁኖ።"
❤️መልካም ምሽት❤️

🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር 🇪🇹

@yebezigetmoch
የዘላለም ሀብት ማለት
በባንክ ዉስጥ ያለ ገንዘብ ሳይሆን 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በልብ ዉስጥ ያለ ፍቅር
እና መልካምነት ነዉ።

መልካም ምሽት
#ሼር
@yebezawit2
❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹
።።።።።​​ምርጥ ባህሪ ።።።።።
➩ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ
➩አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን
➩ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ
እንዲሆን አትጎትጉት
➩ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን
አስወግድ
➩ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን
➩አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ
➩በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን
➩የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር
➩ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ
➩ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን
ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ
የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች
ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ
➩ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል
ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ
ያሳምናቸዋል።
........... ............
@yebezigetmoch ❤️
እንኳን ደህና መጣቹ
፡ ሼር በማረግ ወዳጆን ይጋብዙ