የግጥም መንደር
1.71K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
🌹🌹ክብሮም 👉ለሳሪዬ👈
ተጋበዢለት


❤️❤️ ለእናንተ ለእኔ ምርጦች እና ፍቅሮች ጋበዝኩአቹ ❤️❤️

😘😘😘😘😘😘😘😘😘

የሕግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ነው

እናንተም ሙዚቃ ለምትወዱት ወዳጆ ለመጋበዝ @yebezawit2 ቅርጫት ላይ ጣል ያርጉልን፡፡
💋💋ፍቅር ከልብ እንጂ ከአፍ አይደለም❤️
❤️ የዋህ ሰዎች ልባቸው ንፁህ ነው
በሰዎች ዘንድ ግን ተቀባይነት የላቸውም💐

❤️የዋሕ ልብ ፈጣሪ ያድለን 🙏

ሸጋ ቅዳሚት @yebezigetmoch
#ብስራት_ሱራፌል ❤️
#ቃል_በቃል😍
@Yebezigetmoch

ከቃል በቃል ስጦታ
አየሁ ህልሜ ሲፈታ
ደስታ ሆኖ የኔ እጣ
ገርሞኝ ባንቺ ሲመጣ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ሳይ የልቤን ትርታ
ሞልተሽዋል በደስታ
አሁንማ ምን ልልሽ
ዝም ብዬ ልውደድሽ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ደስ ደስ ደስ

እንደኔ በሆነ ❤️ፍቅሯ እያልኩ ልቤን ሳስጨንቅ
አረግሽኝ በሀሴት ጥልቅልቅ
ያብሮነት ጥጉ በግዜያት ከአይን አልፎ ልብ ሲላመድ
እንዲ ነው ለካ መዋደድ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አቆምኩኝ ለክብርሽ የዘንባባዬን ዳስ
ምን ልካስ
ያስባለኝ ፍቅርሽ ነው ህልም እንዴት ይፈታል
ቃል በ ቃል
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
@yebezigetmoch
ከቃል በቃል ስጦታ
አየሁ ህልሜ ሲፈታ
ደስታ ሆኖ የኔ እጣ
ገርሞኝ ባንቺ ሲመጣ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ሳይ የልቤን ትርታ
ሞልተሽዋል በደስታ
አሁንማ ምን ልልሽ
ዝም ብዬ ልውደድሽ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ደስ ደስ ደስ
😍
ያላንቺ ካለፈው ጊዜ የምድር ብዙ ስጦታ
ይበልጣል የዛሬው ደስታ
እንግዲህ በሱ በረከት እስካለች በአለም ህይወቴ
ፍቅርሽ ነው መክበሪያ እርስቴ
አቆምኩኝ ለክብርሽ የዘንባባዬን ዳስ
ምን ልካስ
ያስባለኝ ፍቅርሽ ነው ህልም እንዴት ይፈታል ቃል በ ቃል
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
😍ልዑል ሊባኖስ ላለሽው ለኤልዳና

የምትፈልጉትን የዘፈን ግጥም ለወዳጆ ለመጋበዝ @yebezawit2 ቅርጫት ላይ ጫር ጫር ያርጉልን፡፡


በየጊዜዉ የዘፈን ግጥሞች እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን
#join_እና_share ያድርጉ!

👉@yebezigetmoch 👈

👉 @yebezigetmoch 👈
መጠሪያዬ💕

❤️It is easy to be a father but it is not easy to be
a daddy❤️

@Yebezigetmoch

አባትነት ሃላፊነትን በፍቅር የመሸከም ጉዳይ ነው።
ራስን ድጋሚ የመውለጃ አጋጣሚ ነው!!!
አባትነት በልጆች አለም መኖር የመቻል የአዋቂ ሰው
ልጅነትም ነው !!!
አባትነት ለልጆች ልብስ እና ጫማ ብቻ መግዛት ሳይሆን
የተጫሙትን ጫማ ለብሰው በሰላም የሚወጡ እና
የሚገቡበት አገር በደምም ቢሆን ታግሎ ማቆየት እና
ማስተላለፍ መቻል ነው !!😍

@yebezigetmoch
❤️ላንቺ ስል❤️
ክፍል 7
እኔም ራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አቃተኝ ማውራት አለመቻሌ ደግሞ ይባስ አስጨነቀኝ ያብም በስስት አይን እያየችኝ ነጭ ጋውን ያረገ ዶክተር መጣና ሰናይት ሰናይት አለኝ አቤት ለማለት አቃተኝ እና በአውንታ ራሴን አነቃነኩኝ አጠገቡ ያለችው ወጣት ነርስም አሁን የት እንዳለሽ ታውቂያለሽ አለችኝ አሁንም በአውንታ ራሴን ነቀነኩኝ ያብም ለምን አታወራም አለቻቸው ዶክተሩም ይሄ ጊዚያዊ ችግር ነው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም መናገሯ አይቀርም አላት እንባን አፈሰስኩኝ እና አይኔን ጨፈንኩኝ ግን ላስታውስ አልቻልኩም ብቻ ሳን እማ ብሎ ሲጠራኝ ትዝ ይለኛል ነርሷ የተቀጠለልኝ ግሉኮስ ቀየረችልኝ እና ለያብ የሚያስፈልጋቹ ነገር ካለ መጥራት ትችያለሽ አለቻትና ለእኔ ፈጣሪ ይማርሽ ብላ ወጣች ድንገተኛ ክፍሉ ብዙ ታካሚዎች አሉት ወንበር ላይ መሬት ላይ ብቻ እርዳታ ፈላጊዎች ሞልተዋል የመንግሥት ሆስፒታል ነው አልኩኝ በልቤ ያብም አጠገቤ ተቀምጣ በስልኳ መፅሐፍ ቅዱስ እያነበበች ቀስ ብዬ እጇን ነኳሀት አቤት ሰኒዬ አለችኝ እኔም ስልኳን በምልክት ጠየኳት እሷም ስለገባት ሰጠችኝ እኔም ሜሴጅ ላይ ገብቼ ፃፍኩላት ምን ሆኜ ነው ብዬ ያብም ተቀብላኝ አነበበች እና መፃፍ ጀመረች፡፡ምን እንደሆንሽ አላውቅም በአንቺ ስልክ ተደውሎ ነው የተጠራሁት መኪና ሊገጭሽ ነበር እና በድንጋጤ ወድቀሽ እንዳልነቃሽ ያመጡሽ ሰዎች ናቸው የነገሩኝ ብላ ፅፋ ሰጠችኝ፡፡አስታወስኩ ከሳን ተለይቼ መኪና ልሻገር እንደነበረ ሳንስ አልከኳት አሁንም በፅሑፍ አላውቅም አንቺ ብቻሽን ነበረሽ ከነሱሽ ሰዎች ውጪ ብላ መለሰችልኝ ሳን እንዴት አላየኝም አልኩ እና በልቤ ስልኩን መለስኩላት ሆስፒታል ተኝቼ በ3ተኛ ቀን ቤሪ መጣች እናቴ እማ ምንሆንሽብኝ ብላ በሚያምረው ለስላሳ ረጅም ጣቶቿ እየዳበሰችኝ፡፡ ልመልስላት ባስብም አልቻልኩም ቤሪም አታወሪኝም አለች እኔም እጇን ከጉንጬ ላይ አውርጄ መሀል እጇን ሳምኳት አለቀሰች ማልቀሷ አስለቀሰኝ አለማውራቴ አስደንግጧታል ግን ለመደበቅ እየሞከረች አይዞሽ ደህና ትሆኛለሽ አለችኝ እኔም ፈገግ ብዬ አየሗት በመሐል ነርሷ ደህና ዋላቹ ብላ ወደእኛ ጋር ቀረበች ቤሪም እግዚአብሔር ይመሠገን አለቻት እና ከተቀመጠችበት ተነሳች ነርሷም የያዘችውን መድሐኒት ፊቴ ሰብራ በስሪንጅ ቀድታ በደም ስሬ ሰጥታኝ ወጣች ቤሪም በቃ ተኚ ሰኒዬ ነገ ከሳን ጋር እንመጣለን ዛሬ ስላልቻለ ነው ብላ ስማኝ ወጣች እኔም ደስ አለኝ ቤሪዬ ናፍቃኝ ነበር ባላወራትም አይቻታለሁ በደስታ አይኔን ጨፍኜ አሸለብኩ፡፡
የማይነጋ ለሊት የማያልፍ ቀን የለም እና ነግቷል አዲስ ቀን አዲስ ማለዳ ቢሆንም አለማውራቴ የአንደበቴ መዘጋት ለውጥ የለውም ዶክተሩ ግን ዛሬ እንደምወጣ ትላንት ነግሮኛል እና በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ያው የዛኔ ስወድቅ ትንሽ እግሬ ስለተጎዳ ማነከሴ አይቀርም በየግዜው ከተንቀሳቀስኩ ግን ቶሎ ይድናል ተብያለሁ እናአላሳሰበኝም የጠዋት ራውንድ ነበር እና እኔ ጋር መጥተው ትንሽ መክረውኝ ሄዱ እኔ ግን አንዱንም አልሰማሁም ያብ ግን ሰምታቸው ነበር ምክንያቱም ዶክተሮቹ ከመብዛታቸው በላይ ብዙ ወሬ ነው የሚያወሩት የእኔ ልብና ሀሳብ ያለው ሳንዬ እና ቤሪ ጋር ነበር በጣም ጓግቻለሁ ዶክተሮቹ ከወጡ ብዙም ሳይቆዩ እነ ሳንን ያብ ይዛቸው መጣች ሳንንም ሳየው እንባዬን እያፈሰስኩ ሳ.............ን......አልኩኝ፡፡ ሳላስበው ተናገርኩኝ ቃል ከአፌ ወጣ.........
part8 ይቀጥላል
ፀሐፊ ቤዛዊት ብቻ


@yebezigetmoch

ለሐሳብ አስተያየት @yebezawit2 ይወርውሩ



የመጨረሻው ክፍል እየደረሰ ነውና በቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ
🙏💐💐💐💐💐💐💐🙏
🔴እናስተውል ጨለማ የንጋት
ጀርባ ነው።
ጥፋትም የምህረት መንገድ ነው።
ሰው ሆኖ ልታጣው የማይገባው ሰዋዊ ማንነትህን ነው
በልባችን ሊታተም
የሚገባው ክብርና ፍቅር ናቸው
የህይወት እርምጃችን እሾህ ቢበዛው እንደ ፅጌሬዳ ማህዛችን
ሊያውድና
ነገራችን የተዋበ እንዲሆን
እናስብ ለመነሳት መውደቅ ለከፍታም ዝቅታ አለውና ዝቅታችን
በቅንነትና
በደስታ ይሁን
ቀና ስንልም መቃናታችን ከፈጣሪ እንጂ በራሳችን እንደሆነ
✔️ አናስብ ሁሉም
ከርሱ ለእርሱ ነውና በፈተናችን ሁሉ እንታገስ የነገዋ የማለዳ
ፀሀይ ምን
ብስራት ይዛ እንደምትመጣ አስበን እንዘጋጅ
💯ዱብዳም ብታመጣም የሚቀበል ጥንካሬ ይኑረን ሊነጋ ሲል
ይጨልማል ግን
የነገን ማን ያውቃል ???
@yebezigetmoch
መልካም ቀን 😍ይሁንላችሁ
❤️የፍቅር ቀን ተመኘሁ❤️

እንዲቀርብ የምትፈልጉት ካለ @yebezawit2 ቅርጫታችን ላይ ጣል ያርጉልን፡፡ ከወዲው ስለምትሰጡን አስተያየት 🙏 እናመሰግናለን፡፡

የግጥም መንደር በቤዚ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☝️☝️☝️☝️ከማንም በላይ ለምወዳት ስለእኔ ብላ ሰውነቷን ረስታ ለኖረችልኝ ለእናቴ "ኖረሻል እንዴ" 💞

እንዲሁም ለመላው ለኢትዮጵያ እናቶች❤️
💐💐ላንቺ ስል💐💐
ክፍል 8
ፀሐፊ ቤዛዊት ብቻ( @yebezawit2 )
...ሳን...ብዬ ድጋሜ ተጣራው መናገሬን ማመን አቃተኝ ሳንም አቀፈኝ እኔም አቅፌው ሳን አወራሁ አልኩት ቤሪም በተደበላለቀ ስሜት ፈገግ ብላ እያየችኝ እንባዋን ጠረገች ያብም ፈጣሪ ሆይ ምን ይሳንሀል ብላ አመሠገነች ዶክተሩም ነርሷ ተጠርተው አዩኝ እና ዶክተሩም በጣም እደለኛ ናቹ እንኳን ደስ አለሽ አለኝ፡፡ እኔም ደስተኛ እጥፍ ድርብ ሆነ ከእሱ ስለይ ያጣሁትን አንደበቴን እሱ ራሱ መለሰለኝ ከሆስፒታሉ ወጥተን እነ ያብ ቤት ሄድን፡፡ከዛን ቀን በሗል ሳን ቤቴ ድረስ ማለትም አሁን ያለሁበት ቤት እነያብ ጋር በር ድረስ ያደርሰኛል ማታ ማታም ወክ አብረን ነን ይበልጥ መቀራረብ ጀመርን፡፡ዛሬም እንደሁልጊዜው ወክ አርገን የምንቀመጥበት ቦታ ተቀምጠን ጨረቃን እየያየን ሳን ድንገት ጉንጬን ሳመኝ እኔም ፈገግ ብዬ አየሁት ፈገግታውን ግን ፈልጌው አልነበረም ሳንም በጣምምምም ነው የምወድሽ አለኝ እኔም በጣም ነው የምወድህ አንተ ደሜ ነህ ብዬ ሸርተት ብዬ ትከሻውን ተደግፌ ሰማዩን ማየት ጀመርኩኝ ሰአቱ ሳናውቀው ሄዷል ቤት የባሁት 4 ሰአት ነበር ቻው ብሎኝ ከሔደ በሗላ ቤት ገብተንም በቴሌግራም እያወራን አብረሽኝ ትሆኛለሽ የሚል ቴክስት ላከልኝ እኔም አንድላይ እኮነን አልኩት እንዳልገባው ሆኜ ሳንም ገብቶሻል ሰኒ አለኝ እኔም ሳንንዬ እኔ እኮ ላንተ አልሆንም አልኩት ሳንም እንዴት ሰኒ አንቺ እኮ ለእኔ መልካምና የምፈልጋት ሴት ነሽ አለኝእኔም ሳንን እኔ #ድንግል አይደለሁም አልኩት ሳንም ፍቅር እኮ ያ አይደለም አለኝ የሳንን ጥያቄ የልብ ምቴን ጨምሮታል ትንሽ ቆይቶም ደህና እደሪ አለኝ እኔም ምንም ሳልለው እሱን እያሰብኩኝ አደረኩኝ ቀኑ ቅዳሜ ነውና ከሰአት ሳን ጋር ቀጠሮ አለኝና ፅጉሬን እየታጠብኩኝ ቤሪ ደወለች ያብም ስልኬን አምጥታ ሰጠችኝ እጄን ልብሴ ላይ አድርቄ ቤሪዬ እናቴ አልኳት ቤሪም ወዬ ውዴ ደህና ነሽልኝ አለችኝ እኔም ደህናነኝ አሁን ለውጥ አለኝ አንቺሽ ደህና ነሽ ክላስ እየገባሽ ነው አልኳት ቤሪም አዎ ደህናነኝ እስኪ ናፍቀሽኛል ላግኝሽ እና ጁስ እንጠጣ አለችኝ እኔም ሳንን ላገኘው ነው ለምን አብረን አናገኘውም አልኳት እሷም ተይው በቃ አለችኝ እና ተናዳ ዘጋችው አውቃለሁ ደስ አይላትም ግን ለምን አልኩኝ እና ፀጉሬን ታጥቤ ፀጉር ቤት ሄድኩኝ ከዛ ስመለስ ለሳን ደውዬለት ተገናኘን እና እንደሁልጊዜው ወክ እያረግን ሳን ማታ እኮ ስለው ሳንም ሰኒዬ ማታ እኮ ጓደኛዬ ነው የላከልሽ አለኝ እየተንተባተበ ውሸት መሆኑ ቢገባኝም እሺ ብዬ አለፍኩት፡፡ደስ ብሎን አምሽተን ቆይተን ተለያየን እግሬም እየተሻለኝ ስለነበር ነገ ቤሪ ጋር ለመሔድ ወስኜ ተኛሁ ጠዋት ያብዬን አመስግኜ የተከራየሁበት የራሴ ቤት ሄድኩኝ እዛም ልብሴን ቀይሬ ከቤት ወጥቼ ሳልነግራት ወደቤቷ ሄድኩኝ የወጪውን በር አንድ ሁለት ጊዜ ካንኳኳሁ በሗላ በሩ ተከፈተ ቤሪ ነበረች ስታየኝ ብዙም አልተደሰተችም ግን ደግሞ አልተከፋችም አቅፋ ሰላም ካለችኝ በሗላ ወደውስጥ ገብቼ የገዛሁላትን ቸኮሌት ሰጠሗትና ደህና ነሽልኛ አልኳት ቤሪም የሰጠሗትን ቸኮሌት እየከፈተች አለሁልሽ አለችኝ ና አጠገቤ ተቀመጠች ስለአሳለፍናቸው ነገሮች እያወራን ሳን ደወለልኝ እኔም ደስ ብሎኝ አነሰሗት ሳንዬ አልኩት ሳንም ወይ ሰኒዬ አለሽልኝ አለኝ እኔም አለሁ ይመሰገን ከቤሪ ጋር ነኝ አልኩት ሳንም ይቺ በረሮ አለች ግን እስኪ ላናግራት አለ እኔም ቤሪዬ ሳን ነው ብዬ ስልኬን ስሰጣት እንዳያናግረኝ አለችኝ እኔም ለምን አልኳት በቃ ወደዛ!!!!!ብላ ተመናጨከችኝ እኔም ደንግጬ ዘጋሁት እና ምነው ቤሪዬ አልኳት በቃ ተይኝ አለችኝ እኔም ስሜታዊ ሆንኩኝ እና ቤሪ ለምንድነው ሳንን ሳወራው የሚከፋሽ አልኳት ቤሪም አንቺ ሲጀመር ታፈቅሪዋለሽ ከእሱ ጋር ስትሆኚ እኔ አልታይሽም..........እንባዬ ቀደመኝ ልነግራት ያሰብኩትን ማውራት አቃተኝ እየሮጥኩ ከቤቷ ወጣሁኝ........
part 9 ከሰአታት በሗል

እውነተኛ የጓደኝነት ታሪክ 😢
እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ

ታሪኮን ለመላክ @yebezawit

በግጥም መንደር ብቻ 🍁ትረካ
🍁ግጥም
🍁ሙዚቃ
🍁ሁሉን በአንድ ላይ @yebezigetmoch 🤗
⚡️ሥራ ፍቅርና ተስፋ⚡️

(በኪራም ታደሰ)

⚡️ባለቅኔው ጆን ባሮውስ መስኮቱ ላይ ቆም ብሎ ሲቃኝ አንድ ጎረቤቱ በቤቱ ጥግ ሲያልፍ ተመለከተ፡፡ ሰውዬም በደስታና በርካታ መንፈስ ሳይሆን በትካዜና በጭንቀት አቀርቅሮ ነበር የሚንገላወደው፡፡

⚡️ለዚህ ሁኔታው ያበቃው ምን እነደሆነ ጆን ባሮውስ ተረዳለት፡፡ ሰውዬው የሚወደውና የሚመስጠው ጊዜውን ትርጉምና አቅጣጫ የሚሰጥለት ምንም ዓይነት ሥራ አልነበረውም፡፡

⚡️ሥራ ያጣ ሰው ለሥቃይ የተዳረገ ነው ሲል ባሮውስ ማሰላሰል ያዘ፡፡ የደመቀ የወፎች ኅብረ ዝማሬን እያዳመጠና ለስላሳ የነፋስ ሽውታ እየተመገበ ባሮውስ በጉዳዩ ላይ ሲያስብበት ቆየ፡፡

☀️የሥራን ክቡርነትና ህይወት አዳሽነት ከእርሱ ወዲያ የተገነዘበ አልነበረም፡፡ በአንድ ወቅት እርሱም ራሱ በሥራ አጥነት ለሥቃይ ከተዳረጉት ምስኪኖች መኻል አንዱ አልነበር? ያኔ ህይወት ጣዕሟን ነፍጋዋለች ፤ ባዶና ግትር ሆናበታለች፡፡ ያኔ መብላትም ሆነ መተኛት ፣ መጫወትም ሆነ መግባባት ተስኖት ነበር፡፡

☀️ሥራ ነፍስ ዘራለት — እርሻ ላይ የመማሰን ፣ የማረስና የመጎልጎል ፣ የመዝራትና የመትከል ፣ የማረምና የመኮትኮት … ተግባራት ፣ ለም አፈር ጨብጦ በጣቶቹ መኻል የመናኘት ሥራ እርሱነቱን ከሚኖርባት ዓለም ጋር እንዳዋሐደለት በሚገባ ያውቀዋል፡፡

☀️ደስታ ፣ እንደ ህልም ቦግ እልም የማትልና ዘወትር ከአጠገብ የምትገኝ መሆኗን ለሰዎች ለማስረዳት ምንኛ ተጣጣረ! ግን ፣ በዙሪያው የነበሩት ሁሉ ተስፋ በሚያስቆርጥ መንገድ እየዋተቱ ህይወታቸውን ሲከትሩት መመልከቱ አላስችል ብሎት የደስታ ምንጩ ሥራ ፣ መንፈስን የሚመስጥ ሥራ መሆኑን ለማስገንዘብ ቆርጦ ተነሣ፡፡

⚡️ከማንኛውም ነገር ሁሉ በላቀ ሁኔታ ደስታን የሚለግስ አንድ ነገር አለ ፤ ምን ይሆን?… በጣም ቀላልና በእጅ የሚገኝ ነው፡፡ ይህን ምስጢር ለጨረታ ላቀርበው ብችል ምን ያህል ሰው በጎረፈ! ዋጋውም ምንኛ በናረ! ብልሆች ብቻ ናቸው ምንነቱን የሚገምቱት፡፡ አንዳንዶቹ ጤንነት ፣ ወይም ገንዘብ ፣ ወይም ባልንጀራ ፣ ወይም ይህን ወይ ያን ሃብት ይሉ ይሆናል፡፡ ግን ፣ እነዚህ ሁሉ ተሟልተው ደስታ አትኖርም፡፡ ዝናና ሥልጣንም ደስታን አያስገኙም፡፡ ጤንነት ፣ ገንዘብ ፣ ባላንጀራ ፣ የሞቀ ቤት … ሁሉም አስፈላጊ ቢሆኑም ደስታ አያጎናጽፉምና ከእነዚህ ሁሉ የሚልቅ አንድ ነገር አለ፡፡ ያ ነገር — ምን ይሆን? ህመምተኛው ጤና ፣ ድሃው ሃብት ፣ ምሁሩ ዕውቀት ፣ እልቅና የሚሻው ሥልጣን ፣ የደከመው ደግሞ ዕረፍትን ይል ይሆናል በማለት ባሮውስ ማስተማሩን ጀመረ፡፡

⚡️ዓይነተኛውን የደስታ ምንጭ ምንነት አሁን ስነግራችሁ ቅር ትሰኙ ይሆናል ይላል ባሮውስ፡፡ የተለመደ ፣ በቅርብ ያለ ፣ ብዙ ሰዎች በእጃቸው ያስገቡት ፣ ግን አስደሳችነቱን ያልተገነዘቡት ጉዳይ ነው፡፡ ወይ ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል፣ ወይ የሚጥማቸው ሆኖ አላገኙትም፡፡ ጅረት የሚሻው ዋነኛው ነገር ምንድን ነው? ሳያቋርጥ መንኳለሉን ይሆናል፡፡ ከተከተረ ጣጣ ይወስዳል፡፡ ሰውም እንዲሁ የማያቋርጥ እንቅስቃሴን ይሻል — የአካል ፣ የመንፈስ ፣ የጭንቅላት፡፡ ስለዚህ የደስታ ምንጩ ሥራ ፣ የሚጥም ሥራ ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ከሥራ ቢታገዱ ዓለማችን ምንኛ የሥቃይ ቋት በሆነች!

⚡️ሥራ የደስታ ምንጭ መሆኑን ፣ በእርሱም በመጠመዳቸው ህልውናቸውን ከመገዝገዝ መቆጠባቸውን የሚገነዘቡ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ደስታ የምትቀርበው አጥብቀው የሚሿትን ፣ ስለርሷ የሚያብጠለጥሉትን አይደለም — አመች ሁኔታን በመፍጠር እንጂ፡፡ መከተልን እንጂ መምራትን አታውቅም፡፡ ፊት ካለችም እርሷን ለመቅደም መሞከሩ አይበጅም፡፡

⚡️በሙሉ ልብ ተመስጦ ፣ ያለ የሌለ ኃይሉን በሚጥመው ሥራ ላይ የሚያውል ሰው ምንኛ የታደለ ነው! እያለ ባሮውስ የፍልስፍና አቅጣጫውን ጠቆመ፡፡

☀️በምንወደው ሥራ ተጠምደን ደስታና እርካታን ማግኘት ከቻልን ሁላቸንም ስለፍቅር በገባን ጥልቀት እናሰባለን፡፡ እንደ ማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ለልብ ወዳጅነትም ዋናው መመሪያ ለመወደድ ከፈለክ ሰው ወዳድ ሁን የሚለው ነው፡፡ ፍቅርን ልትላበስ ከፈለክ ይላል ዴል ካርኒጊም በበኩሉ ብቸኛው መንገድ እንዲያፈቅሩህ መወትወትህን ትተህ ፍቅርህን ለግስ ፣ ፍቅርን ስትሰጥ ብቻ ነው ፍቅርን የምታገኘው፡፡

☀️ደግነትና መተሳሰብ አስፈላጊ ባሕርያት መሆናቸው የተዘነጋበት ዘመን ከቶ አይገኝም፡፡ ስለራሱ ብቻ የሚያስብ ሰው ፣ ራሱን በራሱ የጠቀለለ ኢምንት ቋጠሮ ነው ያለው ሃሪ ፎስዲክም ይህንኑ እውነታ ከልብ በማጤን ነው፡፡

☀️ብዙ ጊዜ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ሲባል እንሰማለን፡፡ ለራስህ እንዲደረግልህ የምትሻውን ለሌላውም አድርግ የሚለው አባባል ፣ የሰዎችን ግንኙነት ከሚያዳብሩ ጥንታዊና ጊዜ የማይሽራቸው ድንጋጌዎች መኻል አንዱ ሲሆን ፣ በግብረ-ገብ መመሪያነቱ ዛሬም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ኢመርሰን ጓደኛ ለማፍራት ጓደኛ ሁን በማለት ይህንኑ ሃቅ አስተጋብቷል፡፡

⚡️እንግዲህ ይህን ስናደርግ ማናችንም ስለ ነገ የተስፋ ወኔአችንን ከሌሎች ጋር ብንካፈል ምንኛ መልካም ነው፡፡ እርግጥ ነው እንደ ሲድኒ ዳርክ አባባል፤ ቀደም ያሉት አባቶቻችን የመኖርንና የመሞትን ምንነት አስተምረውናል፡፡ እኛም ወራሾቻቸው መሆናችንን አንዘንጋ፡፡ ወደ ጦር ግንባር የሚሄድ ወታደር ጦር ሜዳ መሞት እንዳለ ልቦናው ቢያውቅም እንኳን በድል ብስራት ዜና ከጓዶቹ ጋር እንደሚመለስ ያስባል፡፡ ተስፋ የትም አለ፡፡

⚡️ለህይወት አስፈላጊዎቹ ቁም ነገሮች ሥራ ፣ ፍቅርና ተስፋ ናቸው –ጆሴፍ ኤድሰን፡፡

(ግብአት ከሊሊያን ኤይችለር ውርስ በመንግሥቱ ወ/ማርያም)
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
👌ለሌሎች በማስተላለፍ በማስተማር እንማር

ለማንኛውም አስተያየት @yebezawit2
💐ላንቺ ስል💐
ፀሐፊ ቤዛዊት ( @yebezawit2 ) part09

.......ከቤሪ ቤት እያለቀስኩ ወጥቼ ወደ አያቴ መቃብር ጋር አቀናሁ አያቴ ጋር ሁሌ ነበር የምሄደው ያስተወኝ ደግሞ ሳን ነበር አሁን ግን እዛው ነኝ በጣም ከፋኝ ማልቀስ ሁሉ አቃተኝ ትወጂዋለሽ ማለት ምን ማለት ነው አልኩኝ ግን ትንሽ ተረጋግቼ ቆይቼ ወደቤቴ ገባሁ ትንሽ እንደቆየሁ ሳን ደወለለኝ ቢደብረኝም አነሳሁት እና እዛ ሁሌ ጁስ የምንጠጣበት ቤት እንገናኝ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው እኔም ጥቁሩ ካፓርት ልብሴን ለብሼ ጥቁር ከስክስ በጂንስ አርጌ ወጣሁ አለባበሴ ብዙም አላሰጨነቀኝም ነበር ግን ሰው ለጉድ ነበር የሚያየኝ ለምን ይሆን እያልኩ ጁስ ቤቱ ጋር ደረስኩ ወደ ውስጥ ዘልቄ ገባሁ የምንቀመጥበት ቦታ ቤሪ እና ሳን አንድላይ ሁነው አየሗቸው ደነገጥኩኝ ቀስ ብዬ ተጠጓሗቸው እና ቤሪ አልኳት እና ሳምኳት ፊቷ ግን ተጨራምቷል ሳን አጠገብ ሄጄ ተቀመጥኩኝ ቤሪም ስልኳ ጠርቶ ለማናገር ተነስታ ወጣች የሚሆነው ግራ ገብቶኝ በዝምታ ተውጫለሁ ፈገግ ብሎ የተቀበለኝ የለም ሳንም ተናዳብሻለች አለኝ ይበልጥ ደነገጥኩ እጅ እና እግሬ ሲበርደኝ ታወቀኝ በጣም ጨነቀኝ ከቆየሁ ራሴን ልስት ነው እኔም ምን አጠፋሁ አልኩት ሳንም ጠይቂያትአለኝ ቤሪም ስልኳን እየዘጋች መጣችና ተቀላቀለችን ከአሁን አሁን አወራችኝ ስል መምጣቴን ረስተው ለሁለት መሳቅ ማውራት ጀመሩ እኔ ግን ጨንቆኝ ስለነበር ወደውጪ ወጣሁ ብሄድ ጥያቸው በታደልኩ ነበር ግን አልችልም ንቀት ይመስላልለሚያየኝ ታዛቢ ነው የምመስለው የመጣልኝን የአቮካዶ ጁስእያማሰልኩ እሰማቸው ነበር ግን እረስተውኛል ሰው እንደዚህ ይቀየራል አልኩኝ................ከሰአታት በሗላ ወጣን እና ተለያየን እኔም ምን አረኩሽ ልላት ቤት ገብቼ ፌስቡኬን ስከፍት ብሎክ ተደርግያለሁ
እንባ አነቀኝ ከዚህ በሗላ ከበደኝ ክፍል ስገባ ብቻዬንስራም ስውል ብቻዬን ሆነ ሳንም ቢሆን ተደርቦም ይሁን አስቀይሜው ሳላውቀው ዘግቶኛል በእርግጥ ስወለድም ብቻዬን ነኝ ስሞትም እንደዛው ግን ለሰው ሰው ያስፈልገዋል ይሄ እውነታ ነው፡፡ እኔጃ ብቻ መኖር አስጠልቶኛል መሞት ነው የጠማኝ የምኖርለት የለም የሚኖርልኝ የለም እንደሁልጊዜው ከስራ ወጥቼ ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ ከፊት ለፊቴ ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ ሆነው እየተሳሳቁ እየሄዱ ነበር አልፊያቸው ልሔድ ባስብም አልቻልኩም እራሴን ቤሪን እና ሳንን እየሳልኩ ሳለውቀው አለቀስኩ የለምድኩት ፍቅርን አጥቼ በርዶኛል 😒 ቀዝቃዛ ህይወቴ በእነሱ ነበር የደመቀው ግን አሁን ይባስ በረዶ ሆኗል......ለቤሪ ያለኝን ፍቅር ከልቤ የማወጣው መስሎኝ ነበር ግን ውሸት ነው ራሴን ወሽቼዋለው በአጭር ቃል የሚገልፃት ሙዚቃ የጃኪ ነው "እንደ ቀላል"😢


🍁የመጨረሻ ክፍል እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ፡፡

🌷ለባለ ታሪኳ የሚሏት ካለ @yebezawit2 ቅርጫታችን ላይ ጣል ያርጉልን

🌹እርሶም ታሪኬ ይነገርልኝ ይተረክ ካሉ ይላኩልን በልዩ አቀራረብ ይደርሶታል 💯
በግጥም መንደር ብቻ
👌 @yebezawit2

👍 @yebezigetmoch

💕 @yebezigetmoch ❤️
ክፍል 10....
Ende Kelale
Jacky Gosee
💕ሰኒ ለቤሪ የልቧን መግለጫ ዜማ ❤️

የመጨረሻው ክፍል ምን ይሆን? 💐
🎊🎊የመጨረሻ ክፍል🎉
Part 10
.......ቀኑን እንደሁልጊዜው በሀዘን ጀምሬው ወደማታ ከክላስ ወጥቼ ወደ ቤቴ እያቀናሁ ነበር የተሳፈርኩበት ታክሲ አንድ ሰው ጎሎት ረዳቱ ይጣራል በስሱ የተከፈተው የሀይለየሱስ ዘፈን ቀልቤን ገዝቶታል፡፡ ....እኔ ናፍቀሽኛል አልናፍቅሽም ወይ መለያየቱ ቀርቶ አንገናኝም ወይ 🎶🎵 የሚለው ሙዚቃ ነበር አጠገቤ የተቀመጠው ወጣት ተመችቶሻል አለኝ ለከፋ ይመስል እኔም እንኳን ይሄ ደረቅ ወንበር ላይም ተኝቻለሁ ብዬ አስታወስኩ የሆነ ጊዜ አያቴ ታማ ሆስፒታል እያለን የተኛሁበት ወንበር መቼም አረሳውም እናም ፈገግ አልኩኝም ለካ አያቴም ጥላኝ ሄደለች፡፡ ወጣቱም ከየት ነው አለኝ እኔም በጥፊ ብዬው ብወርድ ደስ ባለኝ ብቻ ልጁ ሲያናግረኝ አበሳጨኝ እኔም ዝም አልኩት ረዳቱም በሩን ዘግቶ መንገድ ጀመርን ሙዚቃው አልቆ ሌላ ሙዚቃ ቀጠለ የድሮ ነው ብቻ ወጣቱን ሳላወራው መውረጃዬ ደርሶ ወረድኩኝ ብቻዬን መሆኔን ሳስብ ለሁሉም ባይተዋር ሆኛለሁ ሰው ለሰላም ቢያናግረኝ ይከፋኛል ግራ እየገባኝ ነው እኔ ፍቅርን እየተጠማሁ እነ ቤሪ ግን ጠግበዋል ያተረፉትንም ነፍገውኛል ሰው የሀዘኑ ምክንያት በይበልጥ ይጎዳል እኔም በጣም በምወዳቸው ሰው ሳይሆኑ ተአምር ናቸው ባልኳቸው ሰዎች ልቤ ተሰብሮ የህይወት ቤቴ የኩራዙ ጋዝ አልቆ የጨለመ ቤት መስሏል እናቴ የምላት አባቴ ያልኩት አጠገቤ የሉም እውነት አይደለም ብዬ ራሴን መዋሸት ብሞክርም ልቤ ግን እውነት ነው ብሎ ውሸቴን ይቃወማል ትምህርትም አስጠላኝ ክፍል ስገባ ቤሪን ሳያት ልቤ ይደነግጣል ከሁሉም በላይ ደርቄ እቀራለሁ ለካ ሰው ወዶ ሰው አይርቅም.............ጥሩ ልጅ ባልሆን እንኳን የዚን ያህል የምገፋ መጥፎ ሰው አይደለሁም ያው ከተገባኝ ምን አረጋለሁ ብዬ በድኔን ይዤ እያለሁ ከሰው የምሰማው ሁሉ ራስምታት ሆነብኝ እኔ ራሴን ስርቼ የማኖር ለፍቶ አዳሪ ነኝ እንጂ ከሰው እጅ አልጠብቅም ግን ብዙ ሰማሁ ጆሮዬ ክፉን ነገር ቢሰማም ልቤ ግን መቀበል አቃተው እኔ አንድም ቀን ቤሪን ሳንንም ለጥቅም አልፈለኳቸውም የሰማሁት ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው እስኪገባኝ ፍቅር ነበር እነሱ ጋር የጣለኝ፡፡
🌞የፀሐይን መውጣት በብስራት ዜማቸው አእዋፋት አድምቀዋታል እያለቀስኩ የተኛሁባት የጭድ አልጋዬ ላይ ተገላብጬ የስልኬን ሰአት አየሁ 1:00 ይላል ስራ የረፈደ መስሎኝ ደነገጥኩኝ ለካ እረፍት ወጥቻለሁ አልኩኝ ለራሴ ስልኬን አስቀምጬ ተጠቅልዬ ለመተኛት ከራሴ ጋር እየታገልኩኝ የእንቅልፍ መአበል ሊወስደኝ እየናጠኝ እያለ ስልኬ ጠራ ሳይለንት አላረኩትም እና የምጥሪያዬ ዘፈን ከልቤ የለኝም የምለው ጓደኛ ማን ይሆን እንደ እኔ የሆነ ብቸኛ....ውይይይይይይይይ ኩኩ ደግሞ ብዬ አጠገቤ ያለች ይመስል እየተነጫነጭኩ ቁጡሩን ሳላይ አነሳሁት ሄሎ አለኝ ስልኩ ውስጥ ያለው ድምፅ ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ሳን ነበር አ...ቤ..ት አልኩኝ ምላሴን በግድ ከላንቃዬ ላይ አላቅቄ፡፡ ዛሬ ላግኝሽ አለኝ ደህንነቴን ሳይጠይቀኝ እኔም አ....እ...እ..እሺ የት አልኩት እሱም ቤተክርስቲያን አለኝ እኔም እሺ አልኩት ይህቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን ልቤ ላይ ላትፈርስ ተገንብታለች ሳን ሲከፋው ነበር የምንሄደው ልቤ ግን ከደስታ ይልቅ ከፍቶታል መቅረትን ግን አልመርጥም ብዬ ዥንጉርጉር ቀሚሴን ለብሼ ፊቴን በውሀ አብሼ በፍጥነት ከደሳሳዋ ቤቴ ወጥቼ ቤተክርስቲያን አቀናሁ ግቢው በር ጋር ስደርስ ያረኩትን ነጠላ ሰብስቤ ተሳለምኩኝ እና ተቀምጠን የምናወራበት ቦታችን ጋር ስመለከት ቤሪን አየሗት ጉልበቴ ካደኝ እንደምንም ተጥግቼ ተቀመጥኩኝ መሀላችን ዝምታ ነገሰ ሰላም እንኳን አላልኳቸውም ቤሪም ምን አይነት ሰው ነሽ አለችኝ ፊቷን የተጨማደደ ጣሳ አስመስላው እኔም አንቺ ንገሪኝ አልኳት ውስጤ የእልህ እሳት ተጭሮቦኝ እሷም እኔ ላይ ልታሳቢ ባልሆነ ብላ የኮሮኮሯት ሳይሆን ሳቅ ያደሏት ይመስል በረጅሙ ሳቀች ቤተክርስቲያን መሆኗን እረሳታዋለች ሳቋ አበገነኝ ልንገርሽ ቤሪ አንቺ ከሳን ጋር ከተዋወኩ ጀምሮ ደስተኛ አይደለሽም አልኳት ቤሪም በማን ቀንቼ በአንቺ ብላ ውሃ የተረጨች ዶሮ ይመስል ተርገፈገፈች እኔም እንባዬ ጉንጬን እያራሰ ቤሪ አንተዛዘብ ታውቂያለሽ እኔ የምወደው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንቺ ግን ወንድሜ ደሜ ባልኩት ሰው ጠረጠርሽኝ እኔ እንዴት ያንቺን የእህቴን ስሜት መረዳት ያቅተኛል አብሮነት እኮ በምግብ አይደለም ልብሽን አውቀዋለሁ እኔ ያንቺን ፍቅር ለምን ላጊጥበት አልኳት እንዴት እንደማወራ አላውቅም እንባዬ ግን ይፈሳል ሳንም በዝምታ እያየኝ ነበር ቤሪ የኔ ፍቅር የኔ ልብ ላንቺ መታሰቢያ ነው በፍፁም ሌላ እንደማለምድ ቤሪም ስሚኝ ሰኒ...አልሰማሽም በቃኝ ቤሪ ለአንቺም ለሳን ያለኝን ቦታ ታውቂያለሽ ሰው የለኝም ቤተሰቦቼ ነበራቹ አሁን ግን ፈርሷል ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ሰው እያየንነበር እኔ ግንደንታ አልሰጠኝም ቤሪ ካልፈለጋቹኝ በቃ ተዉኝ እኔ ባ ዶ ነኝ ባ ዶ ባ ዶ ባ ዶ ብዬ ከቤተክርስቲያኗ ግቢ ወጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም የለቅሶ ኑሮዬ ማብቂያ የሌለው ወንዝ ነው ሀዘኔ ጥልቅ እግሬ የመራኝ የእኔና የሳን ወክ አርገን ማረፊያ ጋር ነው እዛው ተቀምጬ ማልቀሴን ቀጠልኩ ጀምበር ማዘቅዘቅ ጀምራለች የእኔ ደስታ ግን ቀድማ ጠልቃ ቀኔም ጨለማ ሆኗል.....
#ተፈፀመ 😭😥😢😰😨

🌑ጥቁር አለም ተጀመረ🌑

ፀሐፊ ቤዛዊት ብቻ

11/11/11
እውነተኛ የጓደኛ ታሪክ😭😢
Ayne Lay New
Sami Dan
ሰኒ ለቤሪ እና ለሳን የመጨረሻ ግብዣዋ 😨
እውነተኛ አሳዛኝ ታሪክ

እመነት ባጣም ከልብሽ ቤት
ቦታ ባይኖረኝ ብወጣም ከልብህ ያለእውነት
ቤተሰቤ ናቹ የማልክደው ነው ቃሌ 🌹❤️❤️❤️
ስትቀኝ እቀናለሁ


ከሆነ ይከብዳል ያለ እምነት መሻገር
ውድየ አይተሻል ሙሴን ከቀይ ባህር
በእምነቱ ሲከፍለው ሊያውም በአንድ በትር
እና ምን መሰለሽ
የመውደድሽ ጥጉ እምነትሽ ሲፈተን
አዕምሮሽ ፀንሷል ቅናት የሚሉትን
ወደ እኔ አጋብቶታል ይኸው ስሜትሽን
አንዳንዴ ሳስበው መሻገር አቅቶናል ወድቀናል እላለሁ
በእምነትሽ በእምነቴ ስትቀኝ እቀናለሁ


በአማኑኤል ደርበው

💐ፍትህ ከጎንደር ለሰብሊ የፍቅር እናቴ ተጋበዢልኝ 💐

ለመጋበዝ ወዳጆን @yebezawit2 ጫር ጫር ያርጉልን

👈 @yebezigetmoch
👈 @yebezigetmoch
👈 @yebezigetmoch
የፍቅር ቃል
Sara Takele
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
የኔ ብዬ መጥራቱ ባይበቃኝ
ፍቅርህ ከቃል በላይ ቢሆንብኝ
ለአንተ የሚመጥን እስካገኝ
የፍቅር ቃልን ተጋበዝልኝ💐
ያንተው እብድ ቤዚ😘
🌹💕🌹💕ፍቅር🌹🌸🌹🌸
@yebezigetmoch
@yebezawit2
🌸ተሸፈንን እና🙈
@yebezigetmoch

የያዝነው መንገድ ሆኖ አንድ
ሩቅ ቅርብ ሆነን እኛ ስንዋደድ
በመንገዳችን መጥተው የህዝብ ሁሉ ጋጋታ
እኔም ላይሽ ስጋፋ ስንገላታ
አንቺም እኔን ልታይ እየተጋፋሽ
ሁከት በዛውና ቀረው ሳላይሽ
ያጣሁሽ መስሎኝ ሰው ሁሉ ከቦሽ
ለመኖር ብዬ ሌላ መንገድ ጀመርኩኝ
ሰው ሲበተን ከፋኝ ሩቅ ሆነሽ ብታይኝ
ከጎኔ ሴትኖራ አንቺን አስናፈቀኝ
ምነው ቢመለስ አልኩ ትላንት እንደገና
ስህተት ወሰንኩ ተሸፈንን እና😔

በቤዛዊት

★ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት
@yebezawit2
@Yebezawit2
★ላይ ያድርሱን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💐የግጥም መንደር💐
💐አያዋጣም ❤️
@yebezigetmoch

ውዴ ናፍቆት ያንገላታው ልቤን
አንተን የተራበው ከአይኔን
ጨክነህ አትቅርበት
ዛሬ እንኳን ድረስለት

ተስፋ ሳልቆርጥ እየጠበኩህ
ከቀጠርከኝ ቦታ እየፈለኩህ
አትበለኝ አልመጣም
ፍቅሬ ናፍቆት አያዋጣም 😘

ገጣሚ ቤዛዊት
@yebezigetmoch

❤️💕🌸💕🌹💕💕❤️💐😍