የግጥም መንደር
1.72K subscribers
225 photos
6 videos
19 files
30 links
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
Download Telegram
😍😍ለማንኛውም ሐሳብ አስተያየት ጥቆማ @yebezawit2 ላይ ያድርሱን ግጥሞን ድርሰቶን ለአንባቢያን ያድርሱ ❤️❤️❤️❤️
🌹🌹ሰናይ ምሽት🌹🌹🌹
💕💕💕በማንበብ ራሶን በእውቀት ያንፁ❤️❤️👍👌👌
ፈላስፋው አፍቃሪ
.
.
.
ፈላስፋው አፍቃሪሽ እንደተናገረው
ውበትሽ ጨረቃ ልብሽ ውቂያኖስ ነው
ጨለማን ያነጋ ከምድር የሰፋ
ብርሀንሽ ልጅነት ያውም የኔ ተስፋ
ጠልፎኝ ቀረሁ እንጅ
በከንፈርሽ መንደር ያስታጠቁት ፈንጅ
እንኳን ፈላስፋውን አርበኛ የሚጥል
ከነገ የሚያስቀር ዛሬን የሚገድል
ልብሽ ደመኛየ
ከገነት አውጥቶ ሲኦልን ያሳየ
ከሲኦል አውጥቶ በፍቅርሽ ያጋየ


በአማኑኤል ደርበው

👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch
👉 @yebezigetmoch

ግጥም ድርሰት ካሎት @yebezawit2 ላይ ያድርሱን እኛም መልሰን ለአንባቢያን እናደርሳለን

😍😍ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ ተመኘን😘
የግጥም መንደር
( በላይ በቀለ ወያ )
@yebezigetmoch


.
.
.
እኔ ወድሻለሁ ፣
የሚወዱሽ ወንዶች ፣ ሚጠሉኝን ያህል
እንደ ጥኡም ዜማ ፣ ልክ እንደ ውብ ስዕል
እኔ ወድሻለሁ ፣ እንደ ውሃ እንደ እህል
።።።
እኔ ወድሻለሁ ፣ ልክ እንደ መመኘት
አባሮ እንደመያዝ ፣ ፈልጎ እንደማግኘት
ሮጦ እንደመቅደም ፣ ታግሎ እንደማሸነፍ
ታስሮ እንደመፈታት ፣ ደክሞ እንደማረፍ
እኔ ወድሻለሁ
ሚወደውን ያህል ፣ኦነግ ባንክ መዝረፍ
።።።
እኔ ወድሻለሁ
ልክ እንደ ፖወር ባንክ ፣ እንደ ጀነሬተር
እንዳስራ ስድስት ሉክ ፣ የአፍላነት ደብተር
ሞቶ እንደሚነሳ ፣ ልክ እንደ ህንድ አክተር#
።።።
እኔ ወድሻለሁ ፣
ኤልፓ መብራት ማጥፋት ፣ ከሚወደው በላይ
ዳታ የጠፋ ቀን ፣ እንደሚገኝ ዋይፋይ
እንደ ማታ ዝናብ ፣ እንደ ጠዋት ፀሐይ
ልክ እንደ ጣፋጭ ህልም ፣ እንደ ሌት ጨረቃ
ከቴሌ ዳታ ጋር
አብሮ እንደሚጠፋ ፣ የሜሴንጀር ፎንቃ
አንደ ልጅ ጨዋታ ፣ ልክ እንደ እቃቃ
እንደ አኩኩሉ
ልክ እንደ አባሮሽ ፣ ሱዚ ቃጤ ቃጤ
እንደወዳጅ ምክር ፣ እንዳባት ግሳጤ
ልክ እንደ ጥምጣም ኳስ ፣ እንደ ባገረጣ
እኔ ወድሻለሁ ፣ ክረምቱ እስኪወጣ
።።።።።
ተገጠመ ጅግጅጋ ላይ ለክረምት መውጫ ለገዛኋት ሹራቤ

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ኪሩቤል ከአሸዋ ሜዳ ለmamaye

@yebezawit2 📬
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

ለሚያፈቅሩት ሰው መልእክቶን በግጥም በደብዳቤ ለማድረስ💌 @yebezawit2 ላይ ይላኩልን በነፃ ያለማንም ተቃዋሚ በቻናላችን ለሚወዱት ሰው እናደርሳለን
🌹ላንቺ ስል🌹
ክፍል4 አሳዛኝ ገፅ
እኔ ወደ ቤተሰቦቼ ጋር ልሔድ ቦርሳዬን ይዤ ወጣሁ ቶሎ ቶሎ ቤሪ ስለምትናፍቀኝ እሷን ቻው ልላት ለገሀር ተገናኘን እኔም እያወራሗት ሳን ደወለላት ለገሐር መሆናችንን ስትነገረው መጣሁ ጠብቁኝ ብሎ ስልኩን ዘጋው እኛም ካለንበት ካፌ ሳንወጣ ጠበቅነው ያው ብዙም አልቆየም ለነገሩ ቢቅይም አላውቅም ምክነያቱም ከእሷ ጋር ሆኜ ሰአቱ አያሳስበኝም ሳን መጥቶ ጉንጫችንን ስሞ ተቀላቀለን እኔም ቤሪ ያስለመደችኝን ስፕራይት በሎሚ እየጠጣሁ ስራ የለም እንዴ አልኩት ሳንም በእጁ አስተናጋጅ እየጠራ አለ ግን መግባት አልፈለኩም አለኝ እኔም ካልክ እሺ ደስ ይለናል አልኩት ቤሪ ግን ዝም ብላለች ምነው ቤሪ አልኳት ምንም አልሆንኩም አለች ፊቷ ያለውን ጠርሙስ እያሽከረከረች እኔም ዝም ስትይ እኮ ነው ብያት ሌላ ወሬ ማውራት ጀመርን በጣም ሰአቱ ሳይታወቅ ነጎደ እኔ ግን አልጠገብኳቸውም በቃ እንውጣ ብለን ወጣን ቤሪም ቤተሰቦችሽን ሰላም በይልኝ ስትለኝ አይ አልሔድም አልኳት ቀጠል አርጌም ነገ እሔዳለሁ አልኳት ቤሪ በአንዴ ፊቷ ተቀየረብኝ ደነገጥኩኝ ግን ምንም ሳልላት ከሳን ጋር አብረን ወደ ሰፈር አቀናን የተመለስኩት ቤት መሆን ፈልጌ ሳይሆን በቃ ከእሱ ጋር የማሳላፋት አንድ ሰከነድ ለእኔ ትልቅ ዋጋ አላት እናም ተመለስኩ የገባንበት ታክሲ ውስጥ ከአንድ እንግሊዘኛ ሙዚቃ በሗላ የእሱባለው ማሬ ማሬ ሙዚቃ ቀጠለ የትም ይመቸኛል የሚል ነበር አብሬ እየዘፈንኩ ጮክ ብዬ ሳንዬ ለአንተ ነው አልኩት ሙዚቃው እስከሚያልቅ አብሬው እየዘፈንኩ ነበር ስለሰው ደንታ አልነበረኝም ሳንም በሚያምር ፈገግታ ነበር የሚያየኝ እኔም በእሱ ፈገግታ ፈገግ እያልኩ መውረጃችን ጋር ደርሰን በእግራችን ወክ ካረግን በሗላ ሁልጊዜ ምግብ የምንበላበት ቤት ገብተን እራት በላን ምግብ ቤቱ እስከሚዘጋ ድረስ እኔና ሳን እየተሳሳቅን ቆየን ሰአቱን ያወቅነው አስተናጋጁ መጥቶ በትህትና ውጡ ሲለን ነው ከጨዋታችን አለም የወጣነው እኛም ከአስተናጋጁ ጋር ተሳስቀን ሒሳብ ከፍለን ስንወጣ ቤሪ ደወለችልኝ ወዬ ቤሪ አልኳት ቤሪም አለሽልኝ አለችኝ እኔም አለሁልሽ እናቴ አልኳት የሳንን እጅ እየሳብኩ ቤሪም ኑሪልኝ....እእ ምን ልልሽ መሠለሽ የደወልኩት ነገ ወይ ከነገወዲያ ባህርዳር አሄዳለሁ አለችኝ መራመዴን ትቼ ቆምኩኝ የኔ መቆም አስደንግጦት ሳንም ቆመ ለምን አልኳት እሷም አክስቴ ናፍቃኛለች በጣም አለችኝ ቤሪ እንደ አይኗ ብሌን የምትሳሳላት አክስት አላት በሄደችበት ስሟን ሳትጠራ ሳትደውልላት አትውልም እሷ ጋር ስትለኝ፡ ቅሪ ማለት አልቻልኩም እኔም በቃ ነገ ቤት እመጣለሁ አብረን ልብስ እናስተካክላለን ስላት ከሗላችን የመጣው ሲኖትራክ መንገድ ዘግቶ ለቆመው ኒሳን መኪና ክላክስ ሲያረግ የት ነሽ አለችኝ እኔም ከሳን ጋር ነኝ ወደቤት እየሸኘኝ አልኳት ቤሪም አይ ጥሩ በቃ ነጠ ደውይልኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው ሳንም ምን ሆነሽ ነው ምን አለችሽ አለኝ እንደከፋኝ ከፊቴ ላይ አንብቦ እኔም ቤሪ ባህርዳር ልትሔድ አልኩት ሳንም ታዲያ ትመለሳለች እኮ አለኝ እንደዛ ሲለኝ ይበልጥ አይኔ እንባን አረገዘ በጉንጬ ላይ አፍስሼ እሱማ ትመጣለች እስከዛ ግን በጣም ነው የምትናፍቀኝ መብላቷን ደህና መሆኗን በምን አውቃለሁ አልኩት የእውነት ከአይኖቼ የሚወጡትን እንባዎች መቆጣጠር አቃተኝ ከውስጥ ብቻ የሆነ እንባ እንባ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው ሳንም አባብሎኝ ሸኘኝ፡፡
#ፀሐፊ_ቤዛዊት_ብቻ
ክፍል 5 አሳዛኝ ገፅ ይቀጥላል
@yebezigetmoch
❤️ላንቺ ስል❤️
#ፀሐፊ__ቤዛዊት__ብቻ
ክፍል 5 አሳዛኝ ገፅ😢
ነገን እየናፈኩኝ ቤት ገባሁ ከሳን ጋር እንደሁልጊዜው ተደዋውለን ተኛው ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ቤሪ ቤት ሄድኩኝ ቦርሳዋ ተዘጋጅቶ አየሁት በጣም ከፋኝ እውነት ልትሄድ ነው ቤሪም እቅፍ አርጋኝ እንደዚህ አይክፋሽ እመጣለሁ እኮ አለችኝ እኔ ግን በዝምታ እንባዬን አፈሰስኩ እና ከእቅፏ ወጥቼ እንዳልጨነቅ ግን ስልክሽ እንዳይዘጋ ጠዋት ረፋድ ምሳ ሰአት ወደማታ እንደዋወላለን ሲቀጥል በፌስቡክ እናወራለን አልኳትኝ እሷም በሀሳቤ ተስማምታ ክላስ ትገቢያለሻ አለችኝ እኔም አልገባም ከማን ጋር ልማር አልኳት እሷም ሀሳቤን እንደማልቀይር ገብቷት እሺ አለችኝእና ወደ ባህርዳር ሸኝቻት ቤቴ ገባሁ ቤሪም ገና መንገድ ከመጀመሯ ደውላ አናግራኝ ዘጋችው ሳንም እንዳይደብረኝ የአቅሙን ያረግለኝ ጀመረ፡፡ቀን ከሳን ጋር ውዬ ቤት ገብቼ በፌስቡክ ቤሪዬን እያወራሗት ነው ሰሞኑን ደሞ ውስጤ እየፈራ እና ደስታዬን የማጣው እየመሰለኝ ነው እናም ለቤሪ የማጣሽ እየመሰለኝ ነው አልኳት ቤሪም ሰኒዬ እንደዚህ እንዳታስቢ እሺ እኔ ላንቺ ሰጋዬንም ለውሻ እሰጣለሁ አለችኝ፡፡ውስጤ ግን ፍርሓቱ አለቀቀውም ግን ከመቀበል ውጪ ምርጫ የለኝምና እሺ አልኳት መቼ ትመጫለሽ አልኳት እሷም ከሳምንት በሗላ አለችኝ ቀናት በቀናት ሲተኩ ቤሪ መመለሻዋ ቀን ደረሰ ስትመጣ ደውይልኝ ብያት ነበር እና ሰፈር እየተዟዟርኩ እያለ ስልኬ ጠራ ቤሪ ነበረች ፈገግ አልኩኝ ሳላነሳውየሳቄ ምክንያት ሁለተኛ እናቴ 😍 ሄሎ ቤሪዬ አልኳት ቤሪም እናቴ አዲስአበባ ገብቻለሁ አለችኝ ልቤ በደስታ ዘለለች ምክንያቱም በሌለችበት ደስ የማይል ቀን ነበር ያሳለፍኩት ከሳን ጋርም ብዙም አልተገናኘሁም እኔም በቃ እሺ ቤት ልምጣ አልኳት ቤሪም አይ ቤት ገብቼ ሻወር ወስጄ እወጣለሁ እና ሁሌ የምንገናኝበት ካፌ ከአንድ ሰአት በሗላ እንገናኝ አለችኝ እኔም እሺ ብዬ ስልኩን ዘግቼ ለሳን ደውዬ ደስታዬን ነገርኩት ሳንም ሰኒዬ ቤሪዬ ዌቲንግ እየገባች ነው ብሎ ስልኩን ዘጋው እኔም ቤት ገብቼ ልብሴን ቀይሬ ተቀመጥኩ አንድ ሰአት አልሞላ አለኝ መጠበቅ ስለተሳነኝ ብቻ ባትኖርም ወደካፌው ሄድኩኝ ሁሌ ከምንቀመጥበት ጠረጴዛ ጋር ሰው የለውም ነበር እና በደስታ ወንበሩን ስቤ ተቀመጥኩኝ አስተናጋጇ መጥታ ምን ልታዘዝ አለችኝ በሚያምር ፈገግታዋ እኔም እናቴ ትምጣ አልኳት በአግራሞት አይታኝ እሺ ብላ ተመለሰች ብትቆይም ቤሪ መጣች በእጇ በጥቁር ፌስታል እቃ አንጠልጥላለች ዘልዬ አቀፍኳት በእቅፌም ሆና ናፈቀችኝ ተቀምጠን አፍለአፍ ገጥመን እያወራን አስተናጋጇ ተመልሳ መጣች እኔም ስፕራይት በሎሚ አልኳት ለአንቺስ አለች ቤሪን እያየች እሷም ስፕራይት አለቻት አስተናጋጇም የታዘዘችውን ልታመጣ ሄደች ቤሪም ያመጣችውን ጥቁር ፌስታል ወደእኔ ገፋ አርጋ ለአንቺ ነው አለችኝ እኔም ምንድነው ቤሪዬ ብያት ልከፍተው ስል አስተናጋጇ ስፕራይቱን ይዛ መጣች እና ከፍታልን ሄደች እኔም ስፕራይቱን ገፋ አርጌ ልከፍተው በመሀል ስልኬ ጠራ ሳን ነበር ቤሪዬ ሳን ነው አልኳት ቤሪም አንሺዋ! ብላ ተለጥጣ ተቀመጠች እኔም በልቤ ምን ሆና ነው ብዬ ስልኩት አነሳሁት ሳንዬ አልኩት ሳንም የት ነሽ ውዷ አለኝ እኔም ከቤሪ ጋር ካፌ ነን አልኩት ቤሪ በሚጋረፈው ዝምታዋ አየችኝና ስፕራይቱን ተጎንጭታ አስቀመጠችው ሳንም መጣሁ ብሎ ስልኩን ዘጋው እኔም ቤሪዬ ምን ሆንሽ አልኳት ቤሪም ምንም አለች የሆነ ነገር ከእኔ ለመደበቅ እየሞከረች እኔም ላለማስጨነቅ ዝም አልኩና የሰጠችኝን ስከፍተው ደስ አለኝ የማስቀደሻ ነጠላ እና የሚያምር ቀሚስ ነበር ከፈጣሪ መቅረቢያ መሸፋፈኛ እንባ አነቀኝ የሌለኝን ሰጠችኝ ቤሪ የሞላ ላይ መገኘት አትወድም የጎደለን መሙላት አንጂ እኔም አቀፍኳት እና አመሰግናለሁ አልኳት ሳን የምን መተቃቀፍ ነው ብሎ ፊታችን ተደቀነ እኔም ተመልከት ብዬ የመጣልኝን አሳየሁትሳንም ሰላም እያለን ለእኔስ አላት ቤሪም ከፍለኸኛል አለችው እኔም ከአንገቴ ላይ ያለውን የምወደውን ሀብሌን አወጣሁት እና እኔ ደግሞ ለአንተ ልስጥህ ብዬ አንገቱ ላይ አረኩለት እና የጠላኸኝ ለት አውጣው አልኩት ቤሪም ተመናቅራ ተነስታ ቶሌት ነኝ ብላ ሄደች....part6 ይቀጥላል ላይክ ሼር እንዳይረሱ🙏
ፀሐፊ #ቤዛዊት_ብቻ
እንዲቀጥል እና አንብበው ከወደዱ ድምፅ ይስጡ ለወዳጆ ያጋሩ 🙏
📨@yebezawit2 አልያም
+251983744901 ላይ ቴክስት ያድርሱን
💜ላንቺ ስል💜
አሳዛኝ ገፅ ክፍል6
በቤዛዊት #ብቻ
👇👇👇👇👇👇👇👇
ከፈጣሪ መቅረቢያ ነጠላ ወደድኩት የሌለኝን ነበር የሰጠችኝ ቤሪ የሞላ ላይ መገኘት አትፈልግም የጎደለን መሙላት እንጂ ይሄንንም እነግራት ነበር አመሰግናለሁ ብዬ አቀፍኳት ሳንም የምን መተቃቀፍ ነው አለ ፊታችን ቆሞ ቤሪም ገና ከመምጣትህ አለችው እኔም ቤሪ የሰጠችኝን እያሳየሁት አያምርም አልኩት ሳንም ለኔስ ቤሪ አላት ቤሪም የለም አለችው እኔም በጣም የምወደውን ለእኔ ትልቅ ትርጉም ያለውን የብር አንገት ሀብሌን አውጥቼ ይኸው እኔ ደግሞ ለአንተ አልኩት ቤሪም ተኮሳትራ አየችኝ እኔም ሳንዬ ይሄን ሀብል እኔን ስትጠላኝ ከአንገትህ ላይ አውጣው ብዬ አሰርኩልት ሳን የሚለውን ስላጣ ዝም አለኝ ቤሪም ተመናቅራ ተነስታ መጣው መፀዳጃ ነኝ ብላ ሄደች ሳንም አቅፎ ሳመኝ የእኛ ጓደኝነት ቀን ሲቆጥር የጠነከረ አለት እየሆነ መጥቷል የቤሪ መለወጥ ባይገባኝም ቤሪ ከመፀዳጃ ሆና ደወለችልኝ እንድመጣላት ነበር ለሳን መጣው ብዬ እሷ ጋር ሄድኩኝ ፊቷ ቀልቶ ነበር ደነገጥኩኝ ምነው ቤሪ አመመሽ እንዴ ብዬ ፊቷን ልነካው ስል እጄን ገፍትራ አንቺ! ፍቅር ይዞሻል አለችኝ ደነገጥኩ ቤሪ የምን ፍቅር አልኳት ቤሪም መልሺልኝ ከሳን ፍቅር ይዞሻል አለችኝ እኔም ኧረ በወላዲቷ የምን ፍቅር ነው ሳን እኮ ወንድሜ አባቴ ነው አልኳት ኧረ ባክሽ አለችኝ ምነው ቤሪ አልኳት ምንም ብላ ጥላኝ ወጣች እኔም እጅ መታጠቢያ ጋር ያለው መስታወት እያየው ምን ሆና ነው አልኩኝ እና ወጣሁኝ ቤሪም ሳን እንውጣ አለች ሳንም አንቆይም አለ እኔም አዎ እንሂድ አልኩትና ወጣን እሷም ወደቤቷ አቀናች እኔም ከሳን ጋር ወደሰፈር ስንግባ ነበር ያልታሰበ ነገር የተፈጠረው፡፡ሳንን ቻው ብዬው መንገድ ልሻገር እንደነበር አስታውሳለው ከዛውጪ ግን አላውቅም ራሴን ያገኘሁት ነጭ ልብስ አርገው ከሚተራመሱት ነርስ እና ዶክተሮች መሀል ነበር ምን ሆኜ ለማለት አፌ አልከፈት አለኝ ጭንቅላቴ በነጭ ጨርቅ ነገር ተጠምጥሟል እንደምንም ቀና ስል አብሪያት ያደኩት የአብምህረት የምትባል አብሮአደጌን አየሗት ውስጤ ቃላት ቢላወስም አፌ አልከፈት አለኝ እንባዬ ሳላውቅ ይወርድ ጀመር መናገር ለምን አቃተኝ ለምን መጣሁ አላውቅም ግራ ገብቶኛል ማንንም መጠየቅ አልችልም ምክንያቱም ጥያቄዬ ለራሴ ነው የሚሰማው ከአጠገቤ አጣዳፊ እርዳታ የሚደረግላቸውን አየሁኝ አይኔን ግድግዳ ላይ ስልከው እኔ ያለሁበት ጋር ሬድred ዞን ተብሎ ትፅፏል ይባስ ውስጤን መጠየቅ ጀመርኩ ድጋሜ ቀና ስል ያብ መጥታ አስተኛችኝ እና ደህና ነሽ አሁን እሺ እናቴ አለችኝ ለምን መጣሁ አልኩ በልቤ አፌን ብታገልም ከንፈሬ አልላቀቅ አለኝ በእንባ የራሰውን ጉንጬን እየነካች አይዞሽ እኔሁሉንም እነግርሻለሁ ግን አሁን እረፊ አለችኝ ቃላት ላወጣ መታገሌን ተረድታ....ይቀጥላል
part 7
💜ፔጁን ላይክ ማረጎን አይርሱ💜
ለማንኛውም አስተያየት ሀሳብ ጥቆማ ይቀነስ ይጨመር የምትሉትን በኮሜንት ላይ ይፃፉልን🙏
ፀሐፊ #ቤዛዊት ብቻ😍
👉@yebezigetmoch 👈
👉@yebezigetmoch 👈

እንዲቀጥል በፍጥነት ድምፅ ይስጡ
❤️❤️ፍቅር ሲፈርድ❤️❤️
ቤዛዊት

በወደዱኩበት አንተን ባፈቀርኩበት
አንተን ብቻ ባሰበው ልቤ ደግሞ በተጎዳበት
በዚያ አይኔ አንተን አይቼ ሌላ ባላየሁበት
ስምህን ጠርቶ በአንተ የማለበት አንደበት
አይንህን ለማየት እግሮቼ ወደአንተ የገሰገስኩበት
💞💞ፍቅሬን ገፍተህ ስትሄድ 💕
በወደደህ ልቤ ላይ ስትቀልድ
በዝምታ ያየህ ፍቅር እኔን ስታነድ
ጊዜው ደርሶ ይኸው ፍቅር ሲፈርድ

ስቆ የሚያስቀውን ልቤን የሚጠግነው
ከቃሌ በላይ የሰጠውን ፈጣሪ የሚያምነው
ሳይጠረጥረኝ የሚያምነኝ ፍቅሩ የሆነ እውነት❤️
ውድ ፍቅሩን ሰጥቶ የሚያኖረኝ በሰገነት

ፍቅር አመጣልኝ በቆምኩበት መንገድ
አፈቀርኩ እንደ አዲስ ፍቅር ሲፈርድ👫
ጊዜው ደረሰ የፍቅራችን ትዝታ ሊቀደድ
ስለሆነ አንተን እረስቼ ሌላ ልወድ💑

ተፃፈ በእኔ
03/11/2011
👉 @yebezigetmoch 👈
👉 @Yebezigetmoch 👈

💚💛❤️ኢትየጵያ ለዘላለም ትኑር 💚💛❤️

💜ለማንኛውም ሐሳብ ጥቆማ አስተያየት 💌📨 @yebezawit2 ላይ ቅርጫታችን ጣል ያርጉልን
🎀 ዘወትር በስራ ሰአት ለግጥም ትዕዛዝ በ 0983744901 ላይ ይዘዙ🎀
የእናንተው ቻናል 🎈
«ለደስተኛ ሕይወት»
ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን ሼር በማድረግ
ይጀምሩ፡፡
1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ
አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል።
ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር
ማፎካከር ነው።
2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ
ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም።
በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ
ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ
ናቸውና።
3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል
እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን
ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን
ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች
ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት
ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ
መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና
ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው
የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን
ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት
ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦
ሰዎችን አትናቅ፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች
ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡
7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ
በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ
የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤
የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ
በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን
ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት
በማሞካሸት ተንከባከበው፡፡
9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው
ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት
ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ
አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ
አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።
10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን
ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን
ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?
መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡
ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!
☞ቀጣዩን መጽሀፍ እና ፅሁፍ ለማግኘት # Like ያድርጉ
ለወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ አካፍሉ
ምንጭ - (ፅሁፉ ከዶክተር አለ
የተወሰደ)
🌹🌹🌹 @yebezigetmoch
አንድ ሰው እውነተኛ ማንነት ያለው በሚነግርህ ነገር ላይ
ሳይሆን በማይነግርህ ነገር ላይ ነው፡፡ ስለሆነም ፀባዩን
በደንብ ለማወቅ ከፈለክ የሚነገርህን ሳይሆን የማይነገርህን
አዳምጥ፡፡፡፡፡ ቤዚ የራጉኤል ልጅ

❤️❤️ ለምርጦች ብቻ❤️❤️
🍈ሎሚ 🍈ከምግብነት በዘለለ የተለያዩ ህክምናዊ ጥቅሞች ያሉት
ሲሆን ህክምናዊ ጥቅሞቹ እንደሚከተሉት ናቸው (ሼር)፦
@Yebezigetmoch
1. ክብደትን ይቀንሳል!
የሎሚ ጭማቂን ለብ ካለ ውሀና ማር ጋር በመቀላቀል
መጠጣት የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል። የሎሚ
ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል ብላችሁ
ብትጠይቁኝ አዎ በትክክል ይቀንሳል እልዎታለሁ።
2. እርጅናን ለመከላከልና ለቆዳ እንክብካቤ
የሎሚ ጭማቂ እርጅናን የሚከላከል ሲሆን የቆዳ መሸብሸብና
ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን እንዲሁም የተለያዩ
ችግሮችን የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እንዲወገድ
በማድረግ ይሳተፋል። የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል ወዲያው
የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።ወዲያው
የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል
መጠጣት።
3. የጉሮሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል!
ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉልን ፍራፍሬዎች አንድ
ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ (ባክቴሪያን የመከላከል) ሀይል አለው
እናም የሎሚ ጭማቂ ከውሀ ጋር ቀላቅለው ወይም በሻይ
መልክ ቢወስዱት ጥቅሙ ላቅ ያለ ነው።
4. ትኩሳትን ለማስታገስ!
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በብርድ ፣ በሳልና በትኩሳት
ለሚሰቃዩ ሰዎች ፍቱን መድሀኒት ነው።የሰውነታችንን ትኩሳት
ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግሳል። እኩል መጠን
ያላቸውን የተፈጥሮ ማርና የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ወይም
የሎሚ ሻይ በመጠቀም ሳልን መቀነስ የሚቻል ሲሆን ከባድ
የጉሮሮ በሽታን ለማስታገስ ይረዳናል።
5. ለጥርስ እንክብካቤ ይጠቅመናል!
የሎሚ ጭማቂ ለጥርስ እንክብካቤና ህክምና ያገለግላል።
የጥርስ ህመም በሚያጋጥምበት ጊዜ ትኩስ(fresh) የሎሚ
ጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይ ማድረግ ፍቱን ማስታገሻ
ነው።በተፈጥሮ የሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት
ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደግዎታል ። በተጨማሪም
ሁልጊዜ ጥርስዎን ቢቦርሹበት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
6. የቆዳ እብጠትን ያስታግሳል!
የሎሚ ጭማቂ የቆዳ እብጠትን የሚከላከል ሲሆን ሰውነታችን
ላይ ባለው እባጭ ላይ ያድርጉት በተጨማሪም ከዉሀ ጋር
የተቀላቀለ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ
በጣም ጠቃሚ ነው።
7. የተቃጠለ ቁስልን ያስታግሳል!
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን
ቁስል ላይ ማድረግ ጠባሳ (scar) እንዳይዝ (እንዳይኖር)
ያደርጋል። ሎሚ ሰውነታችንን
የማቀዝቀዝ ባህሪ ስላለው በቃጠሎ ምክንያት የሚመጣን
የመለብለብ (የማቃጠል) ስሜት ያስታግሳል።
8. ውስጣዊ የደም መድማትን ይከላከላል!
የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል ምክንያቱም
ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላሉት ነው። የአፍንጫ
መድማትን ለመከላከል በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ
ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።
9. የወባና አተት(Cholera) በሽታዎችን ለመከላከል!
ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ
በሽታዎችን ይከላከላል።
10. ለመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞች!
ይህ ህመም ብዙ ጊዜ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ
የሚስተዋል ሲሆን ሎሚ የማይፈለጉ የሰውነት ፈሳሾችን
እንዲወገድ በማድረግ የመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞችን
ያስታግሳል ከዚህም በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን
ባክቴሪያና መርዛማ ነገሮች እንዲወገድ ያደርጋል።
11. እንዲሁም የደም ግፊት ይቀንሳል!
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት በውስጡ
ፓታሲየም ስላለው በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚ
ነው። ከፍተኛ ደም ግፊትን፣ መንገዳገድ (ማዞር) እና
ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል
ያደርጋል።

@yebezigetmoch
ሼርና ላይክ ያድርጉና ለሌላዉንም ተጠቃሚ ያድርጉ !!!

😍 @yebezawit2 😘

ይጨመር የምትሉትን በቅርጫታችን ጫር ጫር ያርጉልን 👉 @yebezawit2

#የእናንተው ቻናል
ሰናይ ምሽት 💋💋💋
ኢትዮጵያውያን እና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ💚💛❤️
❤️ፍቅርን ሊገዛ የሚል ነገር ቢኖር ፍቅር ብቻ ነው ።❤️
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አስተዋይ ሴት መልክና ብርን ከምታይ ይልቅ የልብን ውበት
ትመለከታለች አምላኳንም ትፈራለች።
@yebezawit2 😉
የተከበርከው ወንድ ሆይ
ሁሏም ሴት ገንዘብህን መኪናህን ውድ ስጥታህን የምትፈልግ
ሊመስልህ ይችላል
ነገር ግን ሴት ልጅ ከአንተ ከምንም በላይ ምትፈለገው
ጊዜህን፤ታማኝነትህን፤ፍቅርህን ከሁሉም በፊት ቅድሚያ
እንድትሰጣት አብረሀት እነድትሆን ነው የምትፈልገው
አንተ እንዚህን ሁሉ ብትሰጣት ታተርፍበታለህ እንጂ
አትከሰርባትም።
💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ለሴት ልጅ ምንም ነገር ስጣት እሷ እጥፍፉን ትሰጥሃለች
# ፍቅር_ብትሰጣት >> ንፁህ ልቧን ያለምንም ትሰጥሃለች ።
💐💐💐💐💐💐💐💐💐
# ቤት_ብትሰጣት >>ምቹ መኖሪያ አድርጋ ትሰጥሃለች ።
# አትክልት_ገዝተህ_ብትሰጣት >> ጣፋጭ ምግብ አድርጋ
ትሰጥሃለች ።
😍😍😍😍😍😍😍😍😍
# ዘርህን_ብትሰጣት >>የአይን ማረፍያና የህይወት ማጣፈጫ
የሆነ # ልጆችን ትሰጥሃለች ።
@Yebezigetmoch
# አዘኔታና_ርህራሄ_ብትሰጣት >>ወኔና ጥንካሬን ትሰጥሃለች ።
❤️አስተውል_ግን አንተ ሰይጣን ብትሆንባት ደግሞ የገሃነም
ህይወት እንደምትሰጥህ እወቅ!
🌹🌹ክብሮም 👉ለሳሪዬ👈
ተጋበዢለት


❤️❤️ ለእናንተ ለእኔ ምርጦች እና ፍቅሮች ጋበዝኩአቹ ❤️❤️

😘😘😘😘😘😘😘😘😘

የሕግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ነው

እናንተም ሙዚቃ ለምትወዱት ወዳጆ ለመጋበዝ @yebezawit2 ቅርጫት ላይ ጣል ያርጉልን፡፡
💋💋ፍቅር ከልብ እንጂ ከአፍ አይደለም❤️
❤️ የዋህ ሰዎች ልባቸው ንፁህ ነው
በሰዎች ዘንድ ግን ተቀባይነት የላቸውም💐

❤️የዋሕ ልብ ፈጣሪ ያድለን 🙏

ሸጋ ቅዳሚት @yebezigetmoch
#ብስራት_ሱራፌል ❤️
#ቃል_በቃል😍
@Yebezigetmoch

ከቃል በቃል ስጦታ
አየሁ ህልሜ ሲፈታ
ደስታ ሆኖ የኔ እጣ
ገርሞኝ ባንቺ ሲመጣ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ሳይ የልቤን ትርታ
ሞልተሽዋል በደስታ
አሁንማ ምን ልልሽ
ዝም ብዬ ልውደድሽ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ደስ ደስ ደስ

እንደኔ በሆነ ❤️ፍቅሯ እያልኩ ልቤን ሳስጨንቅ
አረግሽኝ በሀሴት ጥልቅልቅ
ያብሮነት ጥጉ በግዜያት ከአይን አልፎ ልብ ሲላመድ
እንዲ ነው ለካ መዋደድ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አቆምኩኝ ለክብርሽ የዘንባባዬን ዳስ
ምን ልካስ
ያስባለኝ ፍቅርሽ ነው ህልም እንዴት ይፈታል
ቃል በ ቃል
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
@yebezigetmoch
ከቃል በቃል ስጦታ
አየሁ ህልሜ ሲፈታ
ደስታ ሆኖ የኔ እጣ
ገርሞኝ ባንቺ ሲመጣ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ሳይ የልቤን ትርታ
ሞልተሽዋል በደስታ
አሁንማ ምን ልልሽ
ዝም ብዬ ልውደድሽ
ደስ ደስ አለኝ ደስ
ደስ ደስ ደስ
😍
ያላንቺ ካለፈው ጊዜ የምድር ብዙ ስጦታ
ይበልጣል የዛሬው ደስታ
እንግዲህ በሱ በረከት እስካለች በአለም ህይወቴ
ፍቅርሽ ነው መክበሪያ እርስቴ
አቆምኩኝ ለክብርሽ የዘንባባዬን ዳስ
ምን ልካስ
ያስባለኝ ፍቅርሽ ነው ህልም እንዴት ይፈታል ቃል በ ቃል
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው
ቃል በ ቃል ነው ባንቺ የሆነው
😍ልዑል ሊባኖስ ላለሽው ለኤልዳና

የምትፈልጉትን የዘፈን ግጥም ለወዳጆ ለመጋበዝ @yebezawit2 ቅርጫት ላይ ጫር ጫር ያርጉልን፡፡


በየጊዜዉ የዘፈን ግጥሞች እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን
#join_እና_share ያድርጉ!

👉@yebezigetmoch 👈

👉 @yebezigetmoch 👈
መጠሪያዬ💕

❤️It is easy to be a father but it is not easy to be
a daddy❤️

@Yebezigetmoch

አባትነት ሃላፊነትን በፍቅር የመሸከም ጉዳይ ነው።
ራስን ድጋሚ የመውለጃ አጋጣሚ ነው!!!
አባትነት በልጆች አለም መኖር የመቻል የአዋቂ ሰው
ልጅነትም ነው !!!
አባትነት ለልጆች ልብስ እና ጫማ ብቻ መግዛት ሳይሆን
የተጫሙትን ጫማ ለብሰው በሰላም የሚወጡ እና
የሚገቡበት አገር በደምም ቢሆን ታግሎ ማቆየት እና
ማስተላለፍ መቻል ነው !!😍

@yebezigetmoch
❤️ላንቺ ስል❤️
ክፍል 7
እኔም ራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አቃተኝ ማውራት አለመቻሌ ደግሞ ይባስ አስጨነቀኝ ያብም በስስት አይን እያየችኝ ነጭ ጋውን ያረገ ዶክተር መጣና ሰናይት ሰናይት አለኝ አቤት ለማለት አቃተኝ እና በአውንታ ራሴን አነቃነኩኝ አጠገቡ ያለችው ወጣት ነርስም አሁን የት እንዳለሽ ታውቂያለሽ አለችኝ አሁንም በአውንታ ራሴን ነቀነኩኝ ያብም ለምን አታወራም አለቻቸው ዶክተሩም ይሄ ጊዚያዊ ችግር ነው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም መናገሯ አይቀርም አላት እንባን አፈሰስኩኝ እና አይኔን ጨፈንኩኝ ግን ላስታውስ አልቻልኩም ብቻ ሳን እማ ብሎ ሲጠራኝ ትዝ ይለኛል ነርሷ የተቀጠለልኝ ግሉኮስ ቀየረችልኝ እና ለያብ የሚያስፈልጋቹ ነገር ካለ መጥራት ትችያለሽ አለቻትና ለእኔ ፈጣሪ ይማርሽ ብላ ወጣች ድንገተኛ ክፍሉ ብዙ ታካሚዎች አሉት ወንበር ላይ መሬት ላይ ብቻ እርዳታ ፈላጊዎች ሞልተዋል የመንግሥት ሆስፒታል ነው አልኩኝ በልቤ ያብም አጠገቤ ተቀምጣ በስልኳ መፅሐፍ ቅዱስ እያነበበች ቀስ ብዬ እጇን ነኳሀት አቤት ሰኒዬ አለችኝ እኔም ስልኳን በምልክት ጠየኳት እሷም ስለገባት ሰጠችኝ እኔም ሜሴጅ ላይ ገብቼ ፃፍኩላት ምን ሆኜ ነው ብዬ ያብም ተቀብላኝ አነበበች እና መፃፍ ጀመረች፡፡ምን እንደሆንሽ አላውቅም በአንቺ ስልክ ተደውሎ ነው የተጠራሁት መኪና ሊገጭሽ ነበር እና በድንጋጤ ወድቀሽ እንዳልነቃሽ ያመጡሽ ሰዎች ናቸው የነገሩኝ ብላ ፅፋ ሰጠችኝ፡፡አስታወስኩ ከሳን ተለይቼ መኪና ልሻገር እንደነበረ ሳንስ አልከኳት አሁንም በፅሑፍ አላውቅም አንቺ ብቻሽን ነበረሽ ከነሱሽ ሰዎች ውጪ ብላ መለሰችልኝ ሳን እንዴት አላየኝም አልኩ እና በልቤ ስልኩን መለስኩላት ሆስፒታል ተኝቼ በ3ተኛ ቀን ቤሪ መጣች እናቴ እማ ምንሆንሽብኝ ብላ በሚያምረው ለስላሳ ረጅም ጣቶቿ እየዳበሰችኝ፡፡ ልመልስላት ባስብም አልቻልኩም ቤሪም አታወሪኝም አለች እኔም እጇን ከጉንጬ ላይ አውርጄ መሀል እጇን ሳምኳት አለቀሰች ማልቀሷ አስለቀሰኝ አለማውራቴ አስደንግጧታል ግን ለመደበቅ እየሞከረች አይዞሽ ደህና ትሆኛለሽ አለችኝ እኔም ፈገግ ብዬ አየሗት በመሐል ነርሷ ደህና ዋላቹ ብላ ወደእኛ ጋር ቀረበች ቤሪም እግዚአብሔር ይመሠገን አለቻት እና ከተቀመጠችበት ተነሳች ነርሷም የያዘችውን መድሐኒት ፊቴ ሰብራ በስሪንጅ ቀድታ በደም ስሬ ሰጥታኝ ወጣች ቤሪም በቃ ተኚ ሰኒዬ ነገ ከሳን ጋር እንመጣለን ዛሬ ስላልቻለ ነው ብላ ስማኝ ወጣች እኔም ደስ አለኝ ቤሪዬ ናፍቃኝ ነበር ባላወራትም አይቻታለሁ በደስታ አይኔን ጨፍኜ አሸለብኩ፡፡
የማይነጋ ለሊት የማያልፍ ቀን የለም እና ነግቷል አዲስ ቀን አዲስ ማለዳ ቢሆንም አለማውራቴ የአንደበቴ መዘጋት ለውጥ የለውም ዶክተሩ ግን ዛሬ እንደምወጣ ትላንት ነግሮኛል እና በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ያው የዛኔ ስወድቅ ትንሽ እግሬ ስለተጎዳ ማነከሴ አይቀርም በየግዜው ከተንቀሳቀስኩ ግን ቶሎ ይድናል ተብያለሁ እናአላሳሰበኝም የጠዋት ራውንድ ነበር እና እኔ ጋር መጥተው ትንሽ መክረውኝ ሄዱ እኔ ግን አንዱንም አልሰማሁም ያብ ግን ሰምታቸው ነበር ምክንያቱም ዶክተሮቹ ከመብዛታቸው በላይ ብዙ ወሬ ነው የሚያወሩት የእኔ ልብና ሀሳብ ያለው ሳንዬ እና ቤሪ ጋር ነበር በጣም ጓግቻለሁ ዶክተሮቹ ከወጡ ብዙም ሳይቆዩ እነ ሳንን ያብ ይዛቸው መጣች ሳንንም ሳየው እንባዬን እያፈሰስኩ ሳ.............ን......አልኩኝ፡፡ ሳላስበው ተናገርኩኝ ቃል ከአፌ ወጣ.........
part8 ይቀጥላል
ፀሐፊ ቤዛዊት ብቻ


@yebezigetmoch

ለሐሳብ አስተያየት @yebezawit2 ይወርውሩ



የመጨረሻው ክፍል እየደረሰ ነውና በቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ
🙏💐💐💐💐💐💐💐🙏
🔴እናስተውል ጨለማ የንጋት
ጀርባ ነው።
ጥፋትም የምህረት መንገድ ነው።
ሰው ሆኖ ልታጣው የማይገባው ሰዋዊ ማንነትህን ነው
በልባችን ሊታተም
የሚገባው ክብርና ፍቅር ናቸው
የህይወት እርምጃችን እሾህ ቢበዛው እንደ ፅጌሬዳ ማህዛችን
ሊያውድና
ነገራችን የተዋበ እንዲሆን
እናስብ ለመነሳት መውደቅ ለከፍታም ዝቅታ አለውና ዝቅታችን
በቅንነትና
በደስታ ይሁን
ቀና ስንልም መቃናታችን ከፈጣሪ እንጂ በራሳችን እንደሆነ
✔️ አናስብ ሁሉም
ከርሱ ለእርሱ ነውና በፈተናችን ሁሉ እንታገስ የነገዋ የማለዳ
ፀሀይ ምን
ብስራት ይዛ እንደምትመጣ አስበን እንዘጋጅ
💯ዱብዳም ብታመጣም የሚቀበል ጥንካሬ ይኑረን ሊነጋ ሲል
ይጨልማል ግን
የነገን ማን ያውቃል ???
@yebezigetmoch
መልካም ቀን 😍ይሁንላችሁ
❤️የፍቅር ቀን ተመኘሁ❤️

እንዲቀርብ የምትፈልጉት ካለ @yebezawit2 ቅርጫታችን ላይ ጣል ያርጉልን፡፡ ከወዲው ስለምትሰጡን አስተያየት 🙏 እናመሰግናለን፡፡

የግጥም መንደር በቤዚ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM