ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት(ጫንጮ)
1.66K subscribers
92 photos
4 files
104 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
#ጴንጠው-- ቆይ ግን ታቦት ምንድ ነው? ጥቅስ ብቻ ስጠኝ ለእያንዳንዱ መልስህ?????
#ኦርቶዶክሱ-- ታቦት ማለት ቤተ ሀገሬ ከምለው ከግዕዝ ቃል የወጣ ስሆን "ማደርያ" ማለት ነው። የምን ማደርያ? ካልከኝ የቃሉ ማደርያ ኦ.ዘፀ 25፥22
#ጴንጠው--እና ድሮ ለቃሉ ማደርያ ነው በአድስ ኪዳን ለምን አስፈለገ?
#ኦርቶዶክሱ--- በአዲስ ኪዳን የጌታችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሞ ይፈተትበታክ(በዮሐ .ወ 6፥54) የምታገኘው ይህ ሥጋውና ደሙ የምከብርበት ዙፋን ነው።

#ጴንጠው - ታቦት ጣኦት ነው እግዚአብሔር ከእኔ ባቀር የተቀረፀ ምስል ለራስህ አታድርግ አላለም ወይ?

#ኦርቶዶክሱ - ታቦት ጣኦት ነው ካልክ ታቦትን ቀርፆ ለሙሴ የሰጠው እግዚአብሔር ነውኮ ኦ.ዘፀ 32፥16 እና እግዚአብሔር ከእኔ በቀር ለላ የተቀረፀ ምስል ለራስህ አታድርግ እያለ ለምን ቀርፆ ሰጠ?

#ጴንጠው -- ለሙሴ የሰጠው ታቦት ወድቆ ተሰብሯል።

#ኦርቶዶክሱ -- አው እውነት ነው ነገር ግን እግዚአብሔር እንደገና ሙሴ እንድቀርፅ አዞታል። ኦ.ዘፀ 34፥1 ።

#ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ሙሴ የቀረፀው ሁለት ብቻ ነው ይህ ሁሉ ከየት መጣ??

#ኦርቶዶክሱ -- ከሙሴ ከጥሎ ያሉት ቅዱሳን አባቶች እንድቀርፁ ስልጣን ተሰጣቸው ኦ.ዘፀ 31፥1-6 እንዲሁም ባሰልኤም ታቦትን ቀርጿል ኤ.ዘፀ 37፥1።

#ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ለምን በቅዱሳን ስም ይቀረፃል?

#ኦርቶዶክሱ -- የመታሰብያ ስም እስከተሰጣቸው ድረስ ት.ኢሳ 56፥4 ይቀረፅላቸዋል ነገር ግን በታቦቱ ላይ የምከብረው የጌታችን ሥጋውና ደሙ ነው።

#ጴንጠው -- እኔ አሁንም ያልገባኝ ታድያ ለምን በየሀገሩ በየአህጉሩ ታቦት በዛ ከቅዱሳኑ ቁጥርምኮ ይበዛል?

#ኦርቶዶክሱ -- መልስ ሳልሰጥህ በፊት ጥያቀ አለኝ? መጽሐፍ ቅዱስ ስታተም 1 ነበር አይደል? ታድያ አሁን በእያንዳንዳችን እጅ ላይ የምገኘው ከየት መቶ ነው?

#ጴንጠው -- ያው ተባዝተው ስለታተመ ነዋ

#ኦርቶዶክሱ -- ታቦቱም እንድሁ ለአገልግሎት እንድመች በየስፍራው አለ! ይህ ለምን ይሆናል ካልከኝ ት.ሚልክ 1፥11 ተመልከት። ደግሞም በአድስ ኪዳን እግዚአብሔር ለሰዎች ቅርብ አምላክ ነውና ነው ት.ኤር 23፥23።

#ጴንጠው -- ለምን በታቦቱ ላይ የቅዱሳን ስም ይፃፋል?

#ኦርቶዶክሱ -- በታቦቱ ላይ ብቻ አይደለም በሰማይ ቤትም ተፅፎላቸዋል ሉቃስ 10፥20።

#ጴንጠው -- ታቦት በአድስ ኪዳንኮ ተሽሯል አያስፈልግም

#ኦርቶዶክሱ -- ማነው የሻረው? ጌታ በማቴ 5፥17 ላይ ምን ነበር ያለው? ህግንና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈፅማቸው ነው እንጅ አላለም ወይ?

#ጴንጠው - እናንተ ኦርቶዶክሶች ብቻ አከረራችሁት እንጅ ታቦት የምባል ነገር መኖር የለበትም።

#ኦርቶዶክሱ - አይደለም በምድር ላይ አይደለም በኦርቶዶክሶች መቅደስ ውስጥ በሰማይምኮ አለ ታቦት። ነገ እዛ ስትሄድም ይጠብቅሃል ራእይ 11፥19 ይህንንም ስያመለክት ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሀገራችን በሰማይ ነው እያለ 2ኛ ቆሮ 5፥1-5 የተናገረው።

#ጴንጠው -- እሽ ሁሉም እንዳለ ሆኖ ለምንድ ነው እሽ ታቦት ስሰረቅ ዝም የምለው ሃይል የለውምኮ ሌባ ሰረቀው ምናምን ስባል እሰማለው የሰረቀው ሌባም ስሸጠው ታቦቱ ታምራትን እንኳን አያደርግም።

#ኦርቶዶክሱ -- ምርጥ ጥያቄ ጠየከኝ ገና አሁን!! ለመሆኑ ታቦት ይበልጣል ወይስ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጣል ?? ታቦት ማለት የቃሉ ማደርያ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሞ እራሱ የታቦቱ ባለቤት ነው። እስት ንገረኝ?

#ጴንጠው -- መብለጡንማ ኢየሱስ ነው የምበልጠው

#ኦርቶዶክሱ -- ታድያ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ስሸጠው ለምን ኢየሱስ ዝም አለ?? ሀይል ስለለለው? አቅም ስለለለው? ወይስ ይሁዳንም አይሁዶችንም በአንዴ ማጥፋት ስለማይችል ነውን??

#ጴንጠው -- ዝምምምምምም

#ኦርቶዶክሱ -- አየህ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁዳ አሳልፎ ስሸጠው ዝም ያለው በኃላ እነርሱንና ጠላት ዲያብሎስንም ድል ልነሳው ስለፈለገና አዳምንም ነፃ ልያወጣው ስለወደደ ነው እራሱን አሳልፎ የሰጠው። ዛሬ ታቦታትም ስሰረቁ ዝም የምሉት በኃላ ላይ የእግዚአብሔርን ኃይልና የታቦትን ክብር ለማሳየት ብቻ ነው ለዚህ ደሞ 1ኛ ሳሙ 4,, 5,, 6 እነዚህን 3ምዕራፎችን ካየህ ይበቃሃል።

#ጴንጠው---በኦርት ጊዜኮ ኦዛ ታቦቱን ስነካ ተቀስፏል?
#ኦርቶዶክሱ---አው ተቀስፏል። በኦርት ጊዜ ሰው ሁሉ በመርገም ነውና ያለው እግዚአብሔር ለቁጣው አይዘገይም። በአድስ ኪዳን ግን ዘመኑም "አመተ ምህረት" ይባላልና የምህረት ዘመን ነው አምላክ ቶሎ አይፈርድም ምሳሌ እንድሆንልህ ማቴ 13፥24-30 .....ማቴ 5፥45...አንብብ....
#ጴንጠው---ስግደት ለምን አስፈለገ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ አትስገድ አላለም ወይ?
#ኦርቶዶክሱ---እሽ መልካም ኢያሱ ማለት በመ.ኢያሱ 24፥15 ላይ "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ" ያለ ቅዱስ ነብይ ነው አይደል? ታድያ ለምን በመ.ኢያሱ 7፥6 ላይ ለታቦቱ ሰገደ???????? ስለዚህ እኛ ደሞ ዕብ 13፥7 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለን ሁሉ ይህንኑ እንፈፅማለን።
#ጴንጠው----እኛ የምሸከመንን እንጅ የምንሸከመውን አናመልክም እናንተኮ ታቦትን ትሸከሙታላችሁ?
#ኦርቶዶክሱ---አሁንም መልሼ ልጠይቅህ ከታቦት ኢየሱስ ይበልጣል ተባብለናል አይደል? ታቦት ዙፋኑ ነው እርሱ ደሞ የዙፋኑ ባለቤት ነው።
ጴንጠው----አዎ
ኦርቶዶክሱ---እሽ የሰው ልጅ ይበልጣል ወይስ አህያ?
#ጴንጠው---የሰው ልጅ ነዋ
#ኦርቶዶክሱ---ታድያ የሰው ልጅ ታቦትን ከተሸከመ ምን ይገርምሃል? አህያ የታቦቱን ባሌበት ሰማይና ምድርን በቃሉ ያፀናቸውን አምላክ ጌታችንን በጀርባዋ አልተሸከመችውምን?????
#ጴንጠው----- ለካ እሱም አለ!!!.........
#ኦርቶዶክሱ----ገና ብዙ አለ!!!! እርሱን የተሸከመችው አህያ በብቃቷ በጉልበቷ ሳይሆን በእርሱ ፈቃድና ሃይል ነው። ካህናትም ታቦቱን የምሸከሙት በራሳቸው ጥበብና በስልጣናቸው አይደለም፤ የሾማቸው አምላክ ፈቅዶላቸው በቸርነቱ እንደፈቃዱ ነው እንጅ።
ሃይማኖቴ ተዋህዶ ማለት ይህችው ናት። ኦርቶዶክስ መልስ አላት!!
@yeberehanljoche