ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት(ጫንጮ)
1.66K subscribers
92 photos
4 files
104 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
#ቅዱስ_ላሊበላ

📖ሰኔ ፲፪
https://t.me/yeberhanljoche

ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በላስታ ሮሃ ቤተመንግሥት በዋሻ እልፍኝት ውስጥ ታህሳስ ፳፱ በ፲፩፻ወ፩ ዓ/ም ሲሆን በዛሬው ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ነው።
ይህ ቅዱስ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት እያሰበ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ቅዱሳን መካናትን፤ ወደ ሰማይም ወስዶ የቤተ መቅደሶቹን አሠራር አሳይቶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበትን እግዚአብሔር እንዲገልጥለት ሱባኤ ቢገባ ቤተ ማርያም ከተፈለፈለችበት ቦታ የብርሃን ዐምድ ተተክሎ አይቷል።
ቅዱስ ላሊበላ ጎጃም በመሔድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን ተምሯል። ላሊበላ ከወንድሙ ቀጥሎ እንደሚነግሥ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር ንጉሡ ሊገድለው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው፣ ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ላሊበላን ለመግደል አጋጣሚ ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱን እያሰበ ዓርብ ዓርብ ከጾመ በኋላ ኮሶ ይጠጣ ነበርና እኅቱ አጋጣሚውን በመጠቀም መርዝ ጨምራ ሰጠችው።
ለቅዱስ ላሊበላ መርዝ ጨምራ የሰጠችውን እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረ ዲያቆን ሲቀምሰው ወዲያው ሞተ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አገልጋዩ ለእሱ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ባየ ጊዜ መርዙን ጠጣው፡፡ የጠጣው መርዝም ከሆዱ ውስጥ ሆኖ ያሰቃየው የነበረውን አውሬ አወጣለት። እሱም በተአምር ተረፈ።
በዚህ ምክንያት ቅዱስ ላሊበላ ለሦስት ቀናት አያይም አይሰማም ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ወስዶ ሰባቱን ሰማያት አሳየው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጀመሪያ አክሱም ከዚያም ኢየሩሳሌም ወስዶ በዚያ የነበሩትን ቅዱሳት መካናት አሳየው። ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበርና በሮሐ ዐሥራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን ፈለፈለ።
ቅዱሱ አባት በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በድፕሎማሲም የተዋጣለት ስለነበር በቱርኮች ተይዞ የነበረውና በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን ገዳማችን እንዲመለስልን አድርጓል። ከውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችንም ሠርቷል፣ ንግሥናን ከክህነት፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብሮ የያዘው ቅዱስ ላሊበላ በዚች ሰኔ ፲፪ ቀን አርፏል።
🙏የቅዱሱ አባት የቅዱስ ላሊበላ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!🙏

ለሌሎች መረጃዎች👇
https://t.me/@yeberhanljoche