ጨዋ ነው ቀሚሷ
:::::::::::://::::::::::::
ባለ ቀሚስ ነች ልጅቷ
ጠንካራ ናት በእምነቷ'
:
እኔ እኮ አውቃታለሁ ልኳን ልክ እንደሷ
ምንም ክፉ የለው ጨዋ ነው ቀሚሷ
:
ልብን በሚሰርቅ በውቡ ፈገግታ
ትፈውስሀለች ከማይታይ በሽታ
:
መንፈስ ጠጋኝ ንግግሯ
ክብር አለው ዳር ድንበሯ
:
በረከት' ያለው አረዳዷ
ደስ የሚል የሰከነው ያመጣት መንገዷ
:
ታደስኩኝ' ውዬ አብርያት
ንግግሯ ጣፋጭ ነውር የማያውቃት
:
መንፈሰ ጠንካራ
በአምላኳ ከመጡ ማንንም ማትፈራ
ህይወትን የምትኖር ሁሉን አቻችላ
ስቃ ምታሳልፍ ክፉውን ብላ ችላ
ቁም ነገርስ ቢሆን ማ ኖሮ ከእሷ ሌላ
:
ጤና' እንድትሸልመኝ
ታደልኩኝ አንዴ እንኳ ብትስመኝ
ብዬ እንደጨረስኩኝ ጉንጮቼን ስትስመኝ
:
ነቃሁ ከህልም አለም
ገባሁ ከተፈጥሮ
በረሃ ኖሯል ለካ ቀድሞ የኔ ኑሮ
:
:
በቢኒ-መንግሥቱ ✍️
@ye_wsit_simet
:::::::::::://::::::::::::
ባለ ቀሚስ ነች ልጅቷ
ጠንካራ ናት በእምነቷ'
:
እኔ እኮ አውቃታለሁ ልኳን ልክ እንደሷ
ምንም ክፉ የለው ጨዋ ነው ቀሚሷ
:
ልብን በሚሰርቅ በውቡ ፈገግታ
ትፈውስሀለች ከማይታይ በሽታ
:
መንፈስ ጠጋኝ ንግግሯ
ክብር አለው ዳር ድንበሯ
:
በረከት' ያለው አረዳዷ
ደስ የሚል የሰከነው ያመጣት መንገዷ
:
ታደስኩኝ' ውዬ አብርያት
ንግግሯ ጣፋጭ ነውር የማያውቃት
:
መንፈሰ ጠንካራ
በአምላኳ ከመጡ ማንንም ማትፈራ
ህይወትን የምትኖር ሁሉን አቻችላ
ስቃ ምታሳልፍ ክፉውን ብላ ችላ
ቁም ነገርስ ቢሆን ማ ኖሮ ከእሷ ሌላ
:
ጤና' እንድትሸልመኝ
ታደልኩኝ አንዴ እንኳ ብትስመኝ
ብዬ እንደጨረስኩኝ ጉንጮቼን ስትስመኝ
:
ነቃሁ ከህልም አለም
ገባሁ ከተፈጥሮ
በረሃ ኖሯል ለካ ቀድሞ የኔ ኑሮ
:
:
በቢኒ-መንግሥቱ ✍️
@ye_wsit_simet
👍6❤4👏2
°°°°°°°°° አልገባሽም °°°°°°°°°°°°°
:
ልጀናጀን አይደለም የደወልኩት ላንቺ
የራቀኝ አካልሽ ድምፅሽ ናፍቆኝ እንጂ
ፈገግታሽ በአይኔ ዉል ሲለኝ ያንቺ
ግራ ገብቶኝ ስንገላታ
ልቤም በሴኮንዶች ሺ ግዜ ሲመታ
ባስብ ተጨንቄ የማደርገው ባጣ
እጄን ሰደድኩና ከቀዳዳው ኪሴ
ስልኬንም በማውጣት ወዳንቺ ስመታ
ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ የሚያነሳው ሲያጣ
:
ደገምኩኝ ድጋሚ ድንገት ካነሳችው
እሷ ግን
እንኳን ልታነሳ ጭራሹን ዘጋችው
:
ልሳኗ ይዘጋ !!
:
ብዬ አልረግማትም
ተናደድኩኝ እንጂ መቼም አልጠላትም
:
አፈቅራታለሁኝ እሷ አልገባትም !
:
:
✍️በቢኒ-መንግሥቱ
:
ልጀናጀን አይደለም የደወልኩት ላንቺ
የራቀኝ አካልሽ ድምፅሽ ናፍቆኝ እንጂ
ፈገግታሽ በአይኔ ዉል ሲለኝ ያንቺ
ግራ ገብቶኝ ስንገላታ
ልቤም በሴኮንዶች ሺ ግዜ ሲመታ
ባስብ ተጨንቄ የማደርገው ባጣ
እጄን ሰደድኩና ከቀዳዳው ኪሴ
ስልኬንም በማውጣት ወዳንቺ ስመታ
ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ የሚያነሳው ሲያጣ
:
ደገምኩኝ ድጋሚ ድንገት ካነሳችው
እሷ ግን
እንኳን ልታነሳ ጭራሹን ዘጋችው
:
ልሳኗ ይዘጋ !!
:
ብዬ አልረግማትም
ተናደድኩኝ እንጂ መቼም አልጠላትም
:
አፈቅራታለሁኝ እሷ አልገባትም !
:
:
✍️በቢኒ-መንግሥቱ
👏12❤3👍1
ወተትም ጣዕሙ እርጋታው ውስጥ ነው
ቡናም የሚያነቃው ሰክኖ ሲቀዳ ነው
:
እናም ወዳጄ ስክን እርግት ብለህ ህይወትን ካልኖርካት እና እዚህም እዚያም እያልክ እድሜህን በዋዛ እንዲሁ ካባከንክ እመነኝ ግዜ ጠብቆ ይፀፅትሀል !
:
ስለዚህ የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ጣር ሞክር በእምነትህ ጠንካራ ሁን ወደ ፈጣሪህ ቅረብ ለቤተሰብህ ግዜ ስጥ የዛሬ ጓደኛ ነገ አይኖርም እና ብልጥ ሁን ሁሉንም በልክ ቅረብ እራስህን ችለህ እናትህን እስክትረዳ በተቻለህ አቅም ከፍቅር ግንኙነት እራስህ አርቅ አትጠጣ ራስህን ጠብቅ ብቻ በአጠቃላይ
:
ብልጥ ሁን ለሁሉም ገደብ አበጅለት
አጉዳይ ሁን እራስህ ላይ ስራ
ሰከን እረጋ በል ነገሮችን ለራስህ ብቻ ያዛቸው !!❤
:
በቢኒ-መንግሥቱ ✍️
ቡናም የሚያነቃው ሰክኖ ሲቀዳ ነው
:
እናም ወዳጄ ስክን እርግት ብለህ ህይወትን ካልኖርካት እና እዚህም እዚያም እያልክ እድሜህን በዋዛ እንዲሁ ካባከንክ እመነኝ ግዜ ጠብቆ ይፀፅትሀል !
:
ስለዚህ የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ጣር ሞክር በእምነትህ ጠንካራ ሁን ወደ ፈጣሪህ ቅረብ ለቤተሰብህ ግዜ ስጥ የዛሬ ጓደኛ ነገ አይኖርም እና ብልጥ ሁን ሁሉንም በልክ ቅረብ እራስህን ችለህ እናትህን እስክትረዳ በተቻለህ አቅም ከፍቅር ግንኙነት እራስህ አርቅ አትጠጣ ራስህን ጠብቅ ብቻ በአጠቃላይ
:
ብልጥ ሁን ለሁሉም ገደብ አበጅለት
አጉዳይ ሁን እራስህ ላይ ስራ
ሰከን እረጋ በል ነገሮችን ለራስህ ብቻ ያዛቸው !!❤
:
በቢኒ-መንግሥቱ ✍️
👍6❤1
የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
@ye_wsit_simet
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
@ye_wsit_simet
👏5❤2👍2
ይሄው አመት ሞላን ከተለያየን ዛሬ
ላወጣሽም አልቻኩ ከአፈር ስር ቆፍሬ
የእግዜርንም ትዕዛዝ ቃሉንም አክብሬ
በትዝታሽ ገመድ እራሴን አስሬ
ሁል ግዜ ስላንቺ እያሰብኩ አስ'ሬ
:
ናፍቀሽኛል ግን አለሁ
እንደሌለሽ ጎኔ ሳስብም ፈራለሁ
:
ፈርቼ ምን አመጣሁ ጨንቆኝ ምንስ ጨመርኩ
ከሌላው ቀንሼ እድሜሽን አልጨመርኩ
እንደ እናት አባትሽ እንደ ጓደኝነትሽ በቅጡስ መች አዘንኩ
እያልኩ እንደተብሰለሰልኩ ይሄው አመት ሞላሽ
የግዜውም "ቀመር"
ሰዓታት ቀናትን ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት
ወራትን እየደራረቡ ደረሰ አመትሽ
ያመንሽበት አላህ ለልብሽ ንፅህና ለምለሙን ያውርስሽ
ነፍስሽን ይማረው ጀነት ይወፍቅሽ
:
እኛ በርትተናል ስለኛ አይጭነቅሽ
መቼም ላንረሳሽ ልባችን አትሞሽ 💔🖤
:
:
✍️በቢኒ-መንግሥቱ
@ye_wsit_simet
❤6🕊1
°°°°°°°°°ትዝታሽን ለኔ°°°°°°°°°°°°°°
~~~~~
ለስንት ቀን ጠዋት ጠበኩት ስልክሽን
በደሌን የረሳሽ የድሮዋን መስለሽኝ
ግና ተበቀልሽኝ እርቀሽ ትተሽኝ
:
ትድላሽ ህይወት ሁሌም መልክሽ ይምሰል ጠሀይ
ከእኔ ጋር ተከፍተሽ ፊትሽ አዝኖ ከማይ
ባያስችለውም ልቤ መቁረጡም ቢከደው
ስብራቴን ችዬ ልምሰል ደስስስ እንዳለው
ከማይ ሀዘንሽን ደስታሽን ነጥቄው
ባልችልም ልራቅሽ በውስጤ እያነባሁ
:
ግድ የለም ልጎዳ ልርዳሽ እርቄሽ እኔ
በስስት አልየው አይንሽን በአይኔ
ግን''' ግን ግን ደግሞ
ናፍቆት ስንቅ ይሁነኝ ይኑር ፎቶሽ ከኔ
ጠረን መዓዛሽን አልጣው ከጎኔ
ትዝታሽን ቀስቃሽ እሱ ነውና ለኔ
መልክሽ እንዳይጠፋኝ ሌላ ለምደሽ ከእኔ
አይራቀኝ ትዝታሽ ሁሌም ይሁን ጎኔ
:
:
:
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
7/11/2017
@ye_wsit_simet
ለስንት ቀን ጠዋት ጠበኩት ስልክሽን
በደሌን የረሳሽ የድሮዋን መስለሽኝ
ግና ተበቀልሽኝ እርቀሽ ትተሽኝ
:
ትድላሽ ህይወት ሁሌም መልክሽ ይምሰል ጠሀይ
ከእኔ ጋር ተከፍተሽ ፊትሽ አዝኖ ከማይ
ባያስችለውም ልቤ መቁረጡም ቢከደው
ስብራቴን ችዬ ልምሰል ደስስስ እንዳለው
ከማይ ሀዘንሽን ደስታሽን ነጥቄው
ባልችልም ልራቅሽ በውስጤ እያነባሁ
:
ግድ የለም ልጎዳ ልርዳሽ እርቄሽ እኔ
በስስት አልየው አይንሽን በአይኔ
ግን''' ግን ግን ደግሞ
ናፍቆት ስንቅ ይሁነኝ ይኑር ፎቶሽ ከኔ
ጠረን መዓዛሽን አልጣው ከጎኔ
ትዝታሽን ቀስቃሽ እሱ ነውና ለኔ
መልክሽ እንዳይጠፋኝ ሌላ ለምደሽ ከእኔ
አይራቀኝ ትዝታሽ ሁሌም ይሁን ጎኔ
:
:
:
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
7/11/2017
@ye_wsit_simet
❤7👏2😢1
የመጀመሪያዬ
የኔ ከዋክብት
የኔ ጨረቃ
ምትታየኝ ሁሌ
ህይወት ባንቺ ፈክታ
የኔ ደመና
የኔ ፍላፃ
ጣዕም ያገኘችው
ልቤ ካንቺው አርፋ
አንቺ የኔ ክረምት
ደግሞም የነ በጋ
ሳቅሽ ነፍስን ዘሪ
አልቃትር ሌላ’ ጋ
አንቺ የኔ ፀዳል
የኔ ቋሚ ብራ
ተጊ ለ ህይወቴ ነገን እንዳልፈራ
ቀንዲል ዋስትናዬ
ኩራት ጌጥ ውበቴ
ወርሀ መስከረም
ለኔ’ የመጀመሪያ አለም
‘ ሀ ‘ ብለሽ አብሳሪ
ፍቅርን አስጀማሪ
ጎኔ ስትሆኝ ሁሌ ቀኔንም ቀያሪ
ቅድሚያ የምሰጠው ለኔ እንዳንቺ የለም
እወድሻለሁኝ ባልኖርም ዘላለም
አልቀይረው ፍቅሬን እስከ ወድያኛው አለም
ቃሌን እንቺ ላንቺ
ቃልሽ ይሁን ከኔ
ልቤ ይሙላ ባንቺ
ልብሽ ይስከር በኔ
( ✍️ በቢኒ- መንግስቱ )
የኔ ከዋክብት
የኔ ጨረቃ
ምትታየኝ ሁሌ
ህይወት ባንቺ ፈክታ
የኔ ደመና
የኔ ፍላፃ
ጣዕም ያገኘችው
ልቤ ካንቺው አርፋ
አንቺ የኔ ክረምት
ደግሞም የነ በጋ
ሳቅሽ ነፍስን ዘሪ
አልቃትር ሌላ’ ጋ
አንቺ የኔ ፀዳል
የኔ ቋሚ ብራ
ተጊ ለ ህይወቴ ነገን እንዳልፈራ
ቀንዲል ዋስትናዬ
ኩራት ጌጥ ውበቴ
ወርሀ መስከረም
ለኔ’ የመጀመሪያ አለም
‘ ሀ ‘ ብለሽ አብሳሪ
ፍቅርን አስጀማሪ
ጎኔ ስትሆኝ ሁሌ ቀኔንም ቀያሪ
ቅድሚያ የምሰጠው ለኔ እንዳንቺ የለም
እወድሻለሁኝ ባልኖርም ዘላለም
አልቀይረው ፍቅሬን እስከ ወድያኛው አለም
ቃሌን እንቺ ላንቺ
ቃልሽ ይሁን ከኔ
ልቤ ይሙላ ባንቺ
ልብሽ ይስከር በኔ
( ✍️ በቢኒ- መንግስቱ )
❤8🥰1👏1
የኔ፣የለው፣ቅንጣት፣ውሸት...........
ያንቺን፣ ግን እንጃ፣እኔስ ፈራሁለት
ሄድሽ አሉኝ ወሬ ሰማሁ
ቀድሞስ መቼ ጠፍቶኝ
ልብሽ ርቆ ከ’ኔ "ያንቺ"
ከውስጥሽ እንደወጣሁ
.....................................
አለኝ እኔ አንዳች እውነት
እኔን ከአንቺ ያራኩበት
አይምሰልሽ ከቶ ውሸት
እወድሻለሁ ሁሌ ያልኩበት
ስምሽን ጠቅሼ "ግዳይ" የማልኩበት
የለው አንዳች ውሸት
አ.ፈ.ቅ.ር.ሻ.ለ.ሁ.ኝ ብዬ ያኔ ያልኩበት
የለው ቅንጣት ውሸት
ነበር አንዳች ስህተት
እያልኩኝ ዛሬ ላይ ማልፀፀትበት
በነበር የቀረ ነበር አንዳች ስሜት
...............................................
የአንቺስ ?
መሰለኝ ግዜያዊ
እንደሌላት ቋሚ ስሜት
እንደ ግዜው ሰው እንደ ዘመናዊ
ከለመዱት ነዋሪ
ልክ ነኝ ? ልታረም ?!
ይሰየም ቋሚ ሸንጎ
ይዳኘኝ እስኪ ልብሽ ልቤንም ፈልጎ
ችሎት ልቁም ይገትረኝ
ከረታኝ ያንቺ ጌታ
ልቤ ለትዝታሽ ዘላለም ይረታ
ከፈገግታሽ በቀር አያግኝ ርካታ
................................................
ግንሳ ከረታሁ
ከልብሽ ዘልቄ
እንዲያው ልቤን ካጣሁ
ነገሩ ተይው….
ምንም አልል እኔ አይገርመኝ
ገና ድሮ ነበር ልቤ የነገረኝ……………………
በ’ቢኒ : መንግስቱ ✍️
ያንቺን፣ ግን እንጃ፣እኔስ ፈራሁለት
ሄድሽ አሉኝ ወሬ ሰማሁ
ቀድሞስ መቼ ጠፍቶኝ
ልብሽ ርቆ ከ’ኔ "ያንቺ"
ከውስጥሽ እንደወጣሁ
.....................................
አለኝ እኔ አንዳች እውነት
እኔን ከአንቺ ያራኩበት
አይምሰልሽ ከቶ ውሸት
እወድሻለሁ ሁሌ ያልኩበት
ስምሽን ጠቅሼ "ግዳይ" የማልኩበት
የለው አንዳች ውሸት
አ.ፈ.ቅ.ር.ሻ.ለ.ሁ.ኝ ብዬ ያኔ ያልኩበት
የለው ቅንጣት ውሸት
ነበር አንዳች ስህተት
እያልኩኝ ዛሬ ላይ ማልፀፀትበት
በነበር የቀረ ነበር አንዳች ስሜት
...............................................
የአንቺስ ?
መሰለኝ ግዜያዊ
እንደሌላት ቋሚ ስሜት
እንደ ግዜው ሰው እንደ ዘመናዊ
ከለመዱት ነዋሪ
ልክ ነኝ ? ልታረም ?!
ይሰየም ቋሚ ሸንጎ
ይዳኘኝ እስኪ ልብሽ ልቤንም ፈልጎ
ችሎት ልቁም ይገትረኝ
ከረታኝ ያንቺ ጌታ
ልቤ ለትዝታሽ ዘላለም ይረታ
ከፈገግታሽ በቀር አያግኝ ርካታ
................................................
ግንሳ ከረታሁ
ከልብሽ ዘልቄ
እንዲያው ልቤን ካጣሁ
ነገሩ ተይው….
ምንም አልል እኔ አይገርመኝ
ገና ድሮ ነበር ልቤ የነገረኝ……………………
በ’ቢኒ : መንግስቱ ✍️
💔3👏2
በየት? በኩል ነው መገኛሽ......... :
:
ጎጃም ነሽ ወይስ ደሴ
ፍቅርሽ ሆኗል አይረሴ
አክሱም ነሽ አዲግራት
ናፍቆትሽ ሀያሉ ገረፈኝ በጅራት
ቦረና ነሽ አልያ ጉጂ
ጨርቄን ብጥልልሽ በዛብኝ ፈራጅ
ሲዳማ ነች ቢሉኝ መጣሁኝ ይርጋለም
እዛስ መች አየሁሽ ግራ ገባኝ አለም
ጎራ አልኩኝ ሶዶ አርባምንጭ
ስዞር ብዬ ድክም ጠጣሁኝ ከአንዱ ምንጭ
ስጠይቅ ብውልም አያውቋትም ዝም ጭጭ
ገባሁ ቦንጋ ዋልኩኝ ከፋ
ግና ግና ያጣሽ ልቤ ዛሬ ላይ ተከፋ
አሁንስ መች ቆርጦ ተስፋ
ጅማ ልክተት ልደር ማጂ
በነና አንቺ መሀል ባይኖር አማላጂ
የት አገኝሽ ነበር ባትመጪ ከደጅ
ልክ እንዳየሁሽ አተረፍኩ እዳንጂ
በቢኒ- መንግስቱ ✍🏼
@ye_wsit_simet
:
ጎጃም ነሽ ወይስ ደሴ
ፍቅርሽ ሆኗል አይረሴ
አክሱም ነሽ አዲግራት
ናፍቆትሽ ሀያሉ ገረፈኝ በጅራት
ቦረና ነሽ አልያ ጉጂ
ጨርቄን ብጥልልሽ በዛብኝ ፈራጅ
ሲዳማ ነች ቢሉኝ መጣሁኝ ይርጋለም
እዛስ መች አየሁሽ ግራ ገባኝ አለም
ጎራ አልኩኝ ሶዶ አርባምንጭ
ስዞር ብዬ ድክም ጠጣሁኝ ከአንዱ ምንጭ
ስጠይቅ ብውልም አያውቋትም ዝም ጭጭ
ገባሁ ቦንጋ ዋልኩኝ ከፋ
ግና ግና ያጣሽ ልቤ ዛሬ ላይ ተከፋ
አሁንስ መች ቆርጦ ተስፋ
ጅማ ልክተት ልደር ማጂ
በነና አንቺ መሀል ባይኖር አማላጂ
የት አገኝሽ ነበር ባትመጪ ከደጅ
ልክ እንዳየሁሽ አተረፍኩ እዳንጂ
በቢኒ- መንግስቱ ✍🏼
@ye_wsit_simet
❤5
ሄዳ ምን? ልትጎዳ
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ገደል ትግባ ተዋት
ለምኜ አላስቀራት
ገደል ትግባ ተዋት
ናፍቆቴ ካልገባት
ገደል ትግባ ተዋት
እሱዋ እንድያው
ልማድዋ ከሺው ጋር መዳራት
ልቤ ኩዋተነ እንጅ
‘ፍቅሬ ልኩ ላይገባት
በቃ ትሂድ ተው’ዋት
ፍፁም አትለምኑዋት
ገደል ትግባ ተዋት
እያልኩ አላቆሽሽ
አፌን አላረክሰው
መሄድ የለመደ ‘ገላ’
ማደርያ አያጣም ገብቶበት ከመሸው
ይብላኝ እንጂ ለእሱዋ
አላጣም ከልቡዋ አፍቃሪ ከነፍሱዋ !
ይብላኝላት ለእሱዋ !
በቢኒ - መንግስቱ ✍🏼
@ye_wsit_simet
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ገደል ትግባ ተዋት
ለምኜ አላስቀራት
ገደል ትግባ ተዋት
ናፍቆቴ ካልገባት
ገደል ትግባ ተዋት
እሱዋ እንድያው
ልማድዋ ከሺው ጋር መዳራት
ልቤ ኩዋተነ እንጅ
‘ፍቅሬ ልኩ ላይገባት
በቃ ትሂድ ተው’ዋት
ፍፁም አትለምኑዋት
ገደል ትግባ ተዋት
እያልኩ አላቆሽሽ
አፌን አላረክሰው
መሄድ የለመደ ‘ገላ’
ማደርያ አያጣም ገብቶበት ከመሸው
ይብላኝ እንጂ ለእሱዋ
አላጣም ከልቡዋ አፍቃሪ ከነፍሱዋ !
ይብላኝላት ለእሱዋ !
በቢኒ - መንግስቱ ✍🏼
@ye_wsit_simet
👏4❤1
አደራሽን !
:
አንቺ ምን በወጣሽ ይውጣ ከአይንሽ እንባ ስቀሽ ታዪ ለኔ ላልቅስልሽ መንታ ላንባ
:
እኮ ምን በወጣሽ ይጨንቅሻል ከቶ
እኔ ምን ስሰራ ልቤስ ወዴት ገብቶ
ዘና በይ አይክፋሽ አትእዘኚ አንቺ
ሲሻሽ ከ ክለቡ አልያ ከእግዜር ሂጂ
:
ግን በዚህ ሁሉ ፍቅርሽን አትክጂ
የሳቅሺው ሳነባ መሆኑን ተረጂ
ሲከብሽ ውሎ ወዳጅ ቢያደርስሽ ከቤትሽ ደጅ
ግዜ መጣ ብለሽ ለሳቅሽ ግብሬን
እንዳትረሺ እንባዬን 🥀
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
:
አንቺ ምን በወጣሽ ይውጣ ከአይንሽ እንባ ስቀሽ ታዪ ለኔ ላልቅስልሽ መንታ ላንባ
:
እኮ ምን በወጣሽ ይጨንቅሻል ከቶ
እኔ ምን ስሰራ ልቤስ ወዴት ገብቶ
ዘና በይ አይክፋሽ አትእዘኚ አንቺ
ሲሻሽ ከ ክለቡ አልያ ከእግዜር ሂጂ
:
ግን በዚህ ሁሉ ፍቅርሽን አትክጂ
የሳቅሺው ሳነባ መሆኑን ተረጂ
ሲከብሽ ውሎ ወዳጅ ቢያደርስሽ ከቤትሽ ደጅ
ግዜ መጣ ብለሽ ለሳቅሽ ግብሬን
እንዳትረሺ እንባዬን 🥀
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
❤5😢1
አልነበረም እውነት!!
:
ምዬ በገብርኤል
ምለሽ በአክሱም ፅዮን
ያወጋነው ፍቅርን
የእውነት ልንኖር
ዛሬ ምን ተገኝቶ
ተቀየርሽብኝ በአንዴ
ለኔ ሳትነግሪኝ ሌላ ለመድሽ እንዴ?
የሚል ግጥም ልፅፍ
ተዘጋጅቼ ሳለሁ "ተው"
እንዲህማ አታርግ
የሚል ድምፅ ሰማለሁ
እሽ ብዬ ትቼው ገርበብ ስል
ከቀልቤ ደግሞ እበግናለሁ
አምኖ በተመካት መወጋቱ ልቤ
ስማ እንደ ከዳችኝ ሌክ እንደ ይሁዳ
ለጠየቃት ሁሉ ነው እያለች ባዳ
ልቤን በምግባሯ ደጋግማ ስትጎዳ
የፈራሁት መች ቀርቶ
ልቧ እንደ ለመደው ሄዷል ከእኔ ሸሽቶ
:
የሳሙኝ ነበሩ
እልል እስክል ጉንጬን
ሳልጠረጥር በፊት
ጉያዬ ሸሽጌ ይሁዳን ማቀፌን
✍️በቢኒ-መንግስቱ
@ye_wsit_simet
:
ምዬ በገብርኤል
ምለሽ በአክሱም ፅዮን
ያወጋነው ፍቅርን
የእውነት ልንኖር
ዛሬ ምን ተገኝቶ
ተቀየርሽብኝ በአንዴ
ለኔ ሳትነግሪኝ ሌላ ለመድሽ እንዴ?
የሚል ግጥም ልፅፍ
ተዘጋጅቼ ሳለሁ "ተው"
እንዲህማ አታርግ
የሚል ድምፅ ሰማለሁ
እሽ ብዬ ትቼው ገርበብ ስል
ከቀልቤ ደግሞ እበግናለሁ
አምኖ በተመካት መወጋቱ ልቤ
ስማ እንደ ከዳችኝ ሌክ እንደ ይሁዳ
ለጠየቃት ሁሉ ነው እያለች ባዳ
ልቤን በምግባሯ ደጋግማ ስትጎዳ
የፈራሁት መች ቀርቶ
ልቧ እንደ ለመደው ሄዷል ከእኔ ሸሽቶ
:
የሳሙኝ ነበሩ
እልል እስክል ጉንጬን
ሳልጠረጥር በፊት
ጉያዬ ሸሽጌ ይሁዳን ማቀፌን
✍️በቢኒ-መንግስቱ
@ye_wsit_simet
❤5💔1
ናፍቀሽኛል እኮ
:
ልብሽ እንደራቀኝ
ቀልብሽ እንደሸሸኝ
ቀናቶች በወራት
እኔም ከመቅፅፈት
በሌላው መተካት
:
አንቺ እንደቀለለሽ
አንቺ እንዳልከበደሽ
ሁሉንም አውቃለሁ
ናፍቀሽኛል ግን አለሁ
:
አልናፍቅም ሞት እንዳቺ
ልኑር እንደከፋኝ
አንቺም ክህደት በርቺ
:
የጄን ሰጠኝ ጌታ
አየሁ ሲበቀለኝ
አንቺን እንዳፈቅር
ፍቅርን ሲጭንብኝ
ክደሽኝ ናፈቅሽኝ
አይደል ግን ልመፃደቅ
ልክ እንደ ቅዱስ ሰው
እኔ አንቺ ላይ ልፀድቅ
ማልችል የዛይ መሬት
:
በድለሽኝ ይቅር አልኩሽ
ባንቺ መንገድ ባልበድልም
በዚህ እንኳ ከበለጥኩሽ
የእውነቴን ነበረ ደጋግሜ የናፈኩሽ
የእውነቴን ነበረ ከልብ እኔ ያፈቀርኩሽ
:
ክህደት ሲሆን ያማል ካንቺ የመጣው ምላሽ!!
@ye_wsit_simet
:
ልብሽ እንደራቀኝ
ቀልብሽ እንደሸሸኝ
ቀናቶች በወራት
እኔም ከመቅፅፈት
በሌላው መተካት
:
አንቺ እንደቀለለሽ
አንቺ እንዳልከበደሽ
ሁሉንም አውቃለሁ
ናፍቀሽኛል ግን አለሁ
:
አልናፍቅም ሞት እንዳቺ
ልኑር እንደከፋኝ
አንቺም ክህደት በርቺ
:
የጄን ሰጠኝ ጌታ
አየሁ ሲበቀለኝ
አንቺን እንዳፈቅር
ፍቅርን ሲጭንብኝ
ክደሽኝ ናፈቅሽኝ
አይደል ግን ልመፃደቅ
ልክ እንደ ቅዱስ ሰው
እኔ አንቺ ላይ ልፀድቅ
ማልችል የዛይ መሬት
:
በድለሽኝ ይቅር አልኩሽ
ባንቺ መንገድ ባልበድልም
በዚህ እንኳ ከበለጥኩሽ
የእውነቴን ነበረ ደጋግሜ የናፈኩሽ
የእውነቴን ነበረ ከልብ እኔ ያፈቀርኩሽ
:
ክህደት ሲሆን ያማል ካንቺ የመጣው ምላሽ!!
@ye_wsit_simet
💔3❤2
አቦል ለህይወቴ❤️
:
ሀ’ የመጀመርያ ፊደል ለአለም
:
ቃል’ ቢያጣ እጂ አንደበቴ
:
ፊደል ልክሽ ለአንቺ አይደለም
የመጀመርያ ለእኔ አንቺ
ኦሪት እኔ ላንቺ
:
ሀ ፣ ስትይ በፍቅር አለም
ከአንድ ነገር በቀር ያላየነው የለም
:
አምነሽኝ ስትመጪ እጄን ይዘሽ የኔን
Dhugaa Waaqa keenyaa kett
ያኔ የያሺው እጄ የለው አንዳች ውሸት
ልቤን አይተሽዋል ያኔ ገብተሽበት
ራሱ ፍቅር አለሽ ሚዘልቅ እስከ ሽበት
:
አልጠራጠርም ያንቺን አውቀዋለሁ
ይህን ሁላ ዓመት ከ’ልብሽ እንደቆየሁ
:
ለዚህ ታማኝ ልብሽ ለዚህ ታማኝ ፍቅርሽ
ባላገባሽ እንኳን ጥሎሼን ጥላለሁ
:
አትጠራጠሪ ህልምሽ ይሳካ እንጂ
ድል ባለ ድግስ መድፉን አስተኩሼ
፯ ጥይት አልቆ ፰ቱን ተውሼ ድጋሚ ተኩሼ
ለእናትሽ ለእናቴ ዝርግፍ ጌጥ ገዝቼ
ለአባትሽ ለአባቴ ሱፉን አሰፍቼ
ወንድሞችሽ መተው ‘ህቶቼን ጠርቼ
ታዳሚውን ሳይቀር ከእልፍኙ ሞልቼ
አንቺን ንግስት የኔ አበባ በቀኝ እጄ ይዜ
በኩራት ስገባ፣ከአንቺ ጋር
የዛን ቀን ዘላለም ስጋባ
:
ይታየኛል ውዴ ለጠበቀኝ ልብሽ
ቃል ኪዳን’ አስሬ ባሙን ሰዎች መሀል
ጣቶችሽን ስሜ ግንባርሽን ስደግምሽ
አፍቅርሀለሁኝ የሚል ቃል ሲወጣሽ
ታውቂያለሽ አይደለ አንቺን እንደማምንሽ
:
የኔ ብቻ፣ቆንጆ፣ሁሌም "❤️”
:
:
✍️በቢኒ - መንግስቱ
@ye_wsit_simet
:
ሀ’ የመጀመርያ ፊደል ለአለም
:
ቃል’ ቢያጣ እጂ አንደበቴ
:
ፊደል ልክሽ ለአንቺ አይደለም
የመጀመርያ ለእኔ አንቺ
ኦሪት እኔ ላንቺ
:
ሀ ፣ ስትይ በፍቅር አለም
ከአንድ ነገር በቀር ያላየነው የለም
:
አምነሽኝ ስትመጪ እጄን ይዘሽ የኔን
Dhugaa Waaqa keenyaa kett
ያኔ የያሺው እጄ የለው አንዳች ውሸት
ልቤን አይተሽዋል ያኔ ገብተሽበት
ራሱ ፍቅር አለሽ ሚዘልቅ እስከ ሽበት
:
አልጠራጠርም ያንቺን አውቀዋለሁ
ይህን ሁላ ዓመት ከ’ልብሽ እንደቆየሁ
:
ለዚህ ታማኝ ልብሽ ለዚህ ታማኝ ፍቅርሽ
ባላገባሽ እንኳን ጥሎሼን ጥላለሁ
:
አትጠራጠሪ ህልምሽ ይሳካ እንጂ
ድል ባለ ድግስ መድፉን አስተኩሼ
፯ ጥይት አልቆ ፰ቱን ተውሼ ድጋሚ ተኩሼ
ለእናትሽ ለእናቴ ዝርግፍ ጌጥ ገዝቼ
ለአባትሽ ለአባቴ ሱፉን አሰፍቼ
ወንድሞችሽ መተው ‘ህቶቼን ጠርቼ
ታዳሚውን ሳይቀር ከእልፍኙ ሞልቼ
አንቺን ንግስት የኔ አበባ በቀኝ እጄ ይዜ
በኩራት ስገባ፣ከአንቺ ጋር
የዛን ቀን ዘላለም ስጋባ
:
ይታየኛል ውዴ ለጠበቀኝ ልብሽ
ቃል ኪዳን’ አስሬ ባሙን ሰዎች መሀል
ጣቶችሽን ስሜ ግንባርሽን ስደግምሽ
አፍቅርሀለሁኝ የሚል ቃል ሲወጣሽ
ታውቂያለሽ አይደለ አንቺን እንደማምንሽ
:
የኔ ብቻ፣ቆንጆ፣ሁሌም "❤️”
:
:
✍️በቢኒ - መንግስቱ
@ye_wsit_simet
❤3🥰3
እንጃ ይሄ ልቤ
ምን ምን እንዳለፈ፣
:
እንደተሰበረ
:
እጠላሀለሁ ሳይሆን
እወድሀለሁ ሲሉት
ይፈራ ጀመረ!!
:
እንጃ.......
ምን ምን እንዳለፈ፣
:
እንደተሰበረ
:
እጠላሀለሁ ሳይሆን
እወድሀለሁ ሲሉት
ይፈራ ጀመረ!!
:
እንጃ.......
🥰3😢3
አፈቀርኩህ ስትል
ያኔ ልጅ ነበርኩኝ’
:
ነፍስ ሳውቅ አፈቀርኩ
ነብስ እኪከዳኝ ደጅዋ ላይ ተጎለትኩ
እሱዋ ወረተኛ
አካሉዋ በምናብ ከሌላው እየተኛ
ልቤን ሰበረችው
ልሙትልህ ባለ አፍዋ
ስትፈልግ ሙት አለችው !
:
አቤት ሰውን ማመን 💔
:
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
ያኔ ልጅ ነበርኩኝ’
:
ነፍስ ሳውቅ አፈቀርኩ
ነብስ እኪከዳኝ ደጅዋ ላይ ተጎለትኩ
እሱዋ ወረተኛ
አካሉዋ በምናብ ከሌላው እየተኛ
ልቤን ሰበረችው
ልሙትልህ ባለ አፍዋ
ስትፈልግ ሙት አለችው !
:
አቤት ሰውን ማመን 💔
:
በቢኒ-መንግስቱ ✍️
❤3😁2😢1