Forwarded from Light (Selam 🦋)
#መንፈስ_ቅዱስ
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ #አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
— ዮሐንስ 14፥15-16
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
join & share
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ #አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
— ዮሐንስ 14፥15-16
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
join & share
Forwarded from Light (Selam 🦋)
#ነበር
👉 ሕልመኛ ዮሴፍ ተሽጦ ነበር።
👉 እግዚአብሔርን የታመነው ዳንኤልም አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ነበር።
👉 አብርሃምም ልጅ አልወለደም ነበር።
👉 የእስራኤል ሕዝብ በግብፅ ባርነት ውስጥ ነበር።
👉 ኢየሱስም ሞቶ ነበር።
#በነበር_የሚያልፉ_ታሪኮች_አሉ።
#እግዚአብሔር_ታማኝ_ነው!
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
join & share
👉 ሕልመኛ ዮሴፍ ተሽጦ ነበር።
👉 እግዚአብሔርን የታመነው ዳንኤልም አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ነበር።
👉 አብርሃምም ልጅ አልወለደም ነበር።
👉 የእስራኤል ሕዝብ በግብፅ ባርነት ውስጥ ነበር።
👉 ኢየሱስም ሞቶ ነበር።
#በነበር_የሚያልፉ_ታሪኮች_አሉ።
#እግዚአብሔር_ታማኝ_ነው!
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
join & share
የግጥሙ ርዕስ :- አያረጅም የህይወት
መንገዱ ለተጓዘ ወዶ በፈቃዱ
ገጣሚ : ክብር ሰፈር ታሜ
የተቀበል ነው እውነት -የክብር አደራ
ለጠፋች ነፍስ መድሀኒት-ከሞት የሚጠራ
በታይታ ትምክት-በግብዝነት መባከን
በኃላ ቀር ስርአት-እውነትን ገፍቶ መሸፈን
ራስን በእውነትላይ-አጉልቶ ራሱን ሊያሳይ
የውሸት ካባ ደርቦ-ውበት ጎልቶ ከላይ
ውስጡ ሞቱን ደግሶ-ተቀብሎ የሚያይ
የተሰጠውን እምነት ተስፋ-በልቡ ሳያውቅ
ማንነቱን ሳያስገዛ-የወደደውን ሳያደምቅ
መኖርን ፈልጎ ላልኖረ-መንገዱን አላዋቂ
ምስኪኑ ተኝቶ የቀረ-ስንፍናውን አድማቂ
ለዚያ ሰው ስንፍና-በህይወት መታከቱ
የነፍሱን እረፍት ሰላም-በምድር ማጣቱ
ለተገለጠው እውነት-ልቦናውን አዙሮ
በሀይማኖት ትርክት-ነፍሱን ሽጦ ከስሮ
ልቡን በትዕቢት አሳብጦ-ጉልበቱ አስሮ
ተስፋ አለ በሰማይ-ተስፋ አለ በምድር
በክርስቶስ ገድል-የፈሰሰው ፍቅር
የማይገባውን መርጦ-በክብሩ አስገብቶ
ሞት ሞት ሚሸተውን-በህይወት አሽትቶ
በፍቅር ይጠራል-በሰውኛ አይመርጥም
ዘላለም ህያው ነው-ወንጌላችን አያረጅም
ወንጌል ስለ እርሱ ነው-ስለ እየሱስ
በፍቅር ልብን የሚሞላ-ነፍስየሚያረሰርስ
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መንገዱ ለተጓዘ ወዶ በፈቃዱ
ገጣሚ : ክብር ሰፈር ታሜ
የተቀበል ነው እውነት -የክብር አደራ
ለጠፋች ነፍስ መድሀኒት-ከሞት የሚጠራ
በታይታ ትምክት-በግብዝነት መባከን
በኃላ ቀር ስርአት-እውነትን ገፍቶ መሸፈን
ራስን በእውነትላይ-አጉልቶ ራሱን ሊያሳይ
የውሸት ካባ ደርቦ-ውበት ጎልቶ ከላይ
ውስጡ ሞቱን ደግሶ-ተቀብሎ የሚያይ
የተሰጠውን እምነት ተስፋ-በልቡ ሳያውቅ
ማንነቱን ሳያስገዛ-የወደደውን ሳያደምቅ
መኖርን ፈልጎ ላልኖረ-መንገዱን አላዋቂ
ምስኪኑ ተኝቶ የቀረ-ስንፍናውን አድማቂ
ለዚያ ሰው ስንፍና-በህይወት መታከቱ
የነፍሱን እረፍት ሰላም-በምድር ማጣቱ
ለተገለጠው እውነት-ልቦናውን አዙሮ
በሀይማኖት ትርክት-ነፍሱን ሽጦ ከስሮ
ልቡን በትዕቢት አሳብጦ-ጉልበቱ አስሮ
ተስፋ አለ በሰማይ-ተስፋ አለ በምድር
በክርስቶስ ገድል-የፈሰሰው ፍቅር
የማይገባውን መርጦ-በክብሩ አስገብቶ
ሞት ሞት ሚሸተውን-በህይወት አሽትቶ
በፍቅር ይጠራል-በሰውኛ አይመርጥም
ዘላለም ህያው ነው-ወንጌላችን አያረጅም
ወንጌል ስለ እርሱ ነው-ስለ እየሱስ
በፍቅር ልብን የሚሞላ-ነፍስየሚያረሰርስ
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንግዳዬሁ ዘሪቱ✍️
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
(በእንግዳዬሁ ዘሪቱ)
እኛ ማለት ኮ!
"
ክርሰቶስ ብቸኛ፣ ከመሞት መሸሻ
ፂዮን መቋጫችን፣ የድል መዳረሻ"
የሚል መርህ ይዘን
ለፂዮን ተጉዘን
:
ድንገት በጉዟችን ሆዳችን ቢነካ
ማዕድ ለመቋደስ ወርደን አሜሪካ
ለርሃብ የወሰድነው አንጀት አረስርሶን
ጥም ይቆርጣል ያልነው ዋና ሆኖ ወርሶን
ሶስት አራት ባልነው፣ አጉል አግበስብሰን
ካሳፈን ሹፌር፣
እንደ ዮናስ ጉዞ ውሳኔ ቀልብሰን
(የቀረንኮ ነን)
¶
እኛኮ!
የበርሃው መና፣ ቁምነገሩን አልፎ
ጣፍጦ ያስቀረን ነን ከከነአን ገዝፎ
:
ዶላር ከመነዘርን ሰባት ሁለት አምሳ
የት አባቱ ጉዞ ካሜሪካ ምሳ
(እኛኮ እንዲ ነን!)
ግባችን ከፍ ብሎ እንዲያ ይሰቀላል
ከእግረ መንገድ ምሳ እኩል ግን ይቀላል።
(እኛኮ እንዲህ ነን!)
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እኛ ማለት ኮ!
"
ክርሰቶስ ብቸኛ፣ ከመሞት መሸሻ
ፂዮን መቋጫችን፣ የድል መዳረሻ"
የሚል መርህ ይዘን
ለፂዮን ተጉዘን
:
ድንገት በጉዟችን ሆዳችን ቢነካ
ማዕድ ለመቋደስ ወርደን አሜሪካ
ለርሃብ የወሰድነው አንጀት አረስርሶን
ጥም ይቆርጣል ያልነው ዋና ሆኖ ወርሶን
ሶስት አራት ባልነው፣ አጉል አግበስብሰን
ካሳፈን ሹፌር፣
እንደ ዮናስ ጉዞ ውሳኔ ቀልብሰን
(የቀረንኮ ነን)
¶
እኛኮ!
የበርሃው መና፣ ቁምነገሩን አልፎ
ጣፍጦ ያስቀረን ነን ከከነአን ገዝፎ
:
ዶላር ከመነዘርን ሰባት ሁለት አምሳ
የት አባቱ ጉዞ ካሜሪካ ምሳ
(እኛኮ እንዲ ነን!)
ግባችን ከፍ ብሎ እንዲያ ይሰቀላል
ከእግረ መንገድ ምሳ እኩል ግን ይቀላል።
(እኛኮ እንዲህ ነን!)
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በእንግዳዬሁ መኮንን ✍
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from Light (Selam 🦋)
💕 ሁሌም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። እርሱ የህይወት ውሀ ምንጭ ነው። በእሱ ስትሞሉ #አትደርቁም ጠላትም በቀላሉ አይዛችሁም።
ማቴዎስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴³ ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ #ውኃ_በሌለበት_ቦታ_ያልፋል፥ #አያገኝምም።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
ማቴዎስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴³ ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ #ውኃ_በሌለበት_ቦታ_ያልፋል፥ #አያገኝምም።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
Forwarded from Light (Selam 🦋)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
— ዮሐንስ 3፥36
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
— ዮሐንስ 3፥36
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
Forwarded from Light (Selam 🦋)
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²-³ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
…
¹² በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²-³ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
…
¹² በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
Forwarded from Light (Selam 🦋)
ሕዝቅኤል 36
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
²⁷ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
²⁷ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
እንግዳዬ
በቀኔ ጅማሬ ላገኝህ ቀጥሬ
ሳስውብ ሳሰናዳ ራሴን አሳምሬ
በቀጠርኩህ በቀጠርከኝ
አንተን ማየት ሲናፍቀኝ
ኩሌን አየተኳልኩ ቀሚሴን ለብሼ
እግሮቼን ታጥቤ እድፌን ቀንሼ
በር በር አያየሁ ስጠብቅ እንግዳ
ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን ሳሰናዳ
እየጠበኩህ.....
አይኔ ሲንከራተት ማማተር ሲደክመኝ
ሰዓቱ ሲያልፍብኝ የቀረህ ሲመስለኝ
የተዋበው ቤቴ መዝረከረክ ጀመረ
አንድ ሁለት እያለ በእድፍ ተወረረ
ሰለቸኝ ደከመኝ እኔው አቅም አጣሁ
እስክትመጣ ብዬ አልጋዬ ላይ ወጣሁ
እየጠበኩህ.....
ያጋደልኩት ጀርባ ያሳረፍኩት ጎኔ
ማሸለብ ሲጀምር ተንከራታች አይኔ
ሳላስብ በድንገት ተንኳኳ መዝጊያየዬ
ከደጃፌ ቆሞ ጠራኝ እንግዳዬ
ልቤ ንቁ ሆኖ ሰውነቴ ደክሟል
ቀኔ ተገባድዶ ወደማለቅ ቀርቧል
እግሬ ይቆሽሻል ከወረድኩ ከአልጋዬ
ቀሚሴን አውልቄ ተራቁቷል ገላዬ
እንዴት ልውረድ?....
ግን እርሱ አሁንም ከበራፌ ቆሟል
ድምፁን አያሰማኝ እንድከፍት ያንኳኳል
ብዙ አቆይቼው .....
በሀሳብ ስታገል ከበሬ አቁሜው...
እንደምንም ብዬ ለመክፈት ስማቅቅ
መንኳኳቱ ቆሟል ውዴም ብሏል ፈቀቅ
አመለጠኝ.....
ናፍቆቴን እንዳላይ ስንፍናዬ ያዘኝ
ስፈልግ አጣሁት...
በሬን እየዘጋሁ ሲጠራኝ ገፋሁት
እንግዳዬ እያልኩ ብዙ እቆጥረዋለሁ
ሲመጣ ግን መልሴ እንዴት እወርዳለሁ ?.....
ነፃነት አናቶ✍️Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
በቀኔ ጅማሬ ላገኝህ ቀጥሬ
ሳስውብ ሳሰናዳ ራሴን አሳምሬ
በቀጠርኩህ በቀጠርከኝ
አንተን ማየት ሲናፍቀኝ
ኩሌን አየተኳልኩ ቀሚሴን ለብሼ
እግሮቼን ታጥቤ እድፌን ቀንሼ
በር በር አያየሁ ስጠብቅ እንግዳ
ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን ሳሰናዳ
እየጠበኩህ.....
አይኔ ሲንከራተት ማማተር ሲደክመኝ
ሰዓቱ ሲያልፍብኝ የቀረህ ሲመስለኝ
የተዋበው ቤቴ መዝረከረክ ጀመረ
አንድ ሁለት እያለ በእድፍ ተወረረ
ሰለቸኝ ደከመኝ እኔው አቅም አጣሁ
እስክትመጣ ብዬ አልጋዬ ላይ ወጣሁ
እየጠበኩህ.....
ያጋደልኩት ጀርባ ያሳረፍኩት ጎኔ
ማሸለብ ሲጀምር ተንከራታች አይኔ
ሳላስብ በድንገት ተንኳኳ መዝጊያየዬ
ከደጃፌ ቆሞ ጠራኝ እንግዳዬ
ልቤ ንቁ ሆኖ ሰውነቴ ደክሟል
ቀኔ ተገባድዶ ወደማለቅ ቀርቧል
እግሬ ይቆሽሻል ከወረድኩ ከአልጋዬ
ቀሚሴን አውልቄ ተራቁቷል ገላዬ
እንዴት ልውረድ?....
ግን እርሱ አሁንም ከበራፌ ቆሟል
ድምፁን አያሰማኝ እንድከፍት ያንኳኳል
ብዙ አቆይቼው .....
በሀሳብ ስታገል ከበሬ አቁሜው...
እንደምንም ብዬ ለመክፈት ስማቅቅ
መንኳኳቱ ቆሟል ውዴም ብሏል ፈቀቅ
አመለጠኝ.....
ናፍቆቴን እንዳላይ ስንፍናዬ ያዘኝ
ስፈልግ አጣሁት...
በሬን እየዘጋሁ ሲጠራኝ ገፋሁት
እንግዳዬ እያልኩ ብዙ እቆጥረዋለሁ
ሲመጣ ግን መልሴ እንዴት እወርዳለሁ ?.....
ነፃነት አናቶ✍️Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Forwarded from Light (Selam 🦋)
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
💕@sela3m
@worlds_light
@worlds_light
✨✨✨join & share 💫💫💫
የቶማስ መጠርጠር እጆቹን መዳሰስ
ለእምነት ከሆነ ስለምን ይከሰስ??
በተዘጋው ቤት ውስጥ፣ ክርስቶስ ተገልጦ
አጀብ ሲያሰኛቸው፣ ሰው ገላውን ገልጦ
ሁሉም ግራ ገብቶት
የሚያደርገው ጠፍቶት
ያለማመን ደባ፣ በውስጡ ሲሰካ
የቶማስ ጥያቄ፣ እስኪ አንዴ ልንካ?
"
ያለማመን ልኩ፣ ቢሆን በመጠርጠር
የእምነቱ ግዝፈት፣ ምን ብታህል ጠጠር
ልክ ይሆናል ቶማስ፣ እንዲያ መጠርጠሩ
ከመጠርጠር አለም፣ እምነት ለመፍጠሩ።
ለምን? እንዴት? ከተባለ
አንድ ሚስጥር አለ...
ምናልባት በዚያ ቤት፣ ሰው ሁሉ ሲያነባ
ውስጡ ተሸንቁሮ፣ ያለማመን ደባ
ሐዋሪያቱ ሁላ
ነፍሱ ተርበትብቶ፣ ባጉል ጥራጥሬ
ሸፋፍኖት በእምነት፣ ባልበሰለ ጥሬ
እህ! ብሎ በጣር፣ እንዲያ የበረታው
ምርኩዝ አስደግፎት፣ በድፍረት የረታው
(ፍርሃት ነበረው!)
ለዚያ ሁሉ ታዲያ
በፍርሃቱ አጎንብሶ
በድፍረቱ ተልፈስፍሶ
ነፍስ አካሉ ተጠራጥሮ
ለማመኑ ብቻ ጥሮ
ተሸፋፍኖ በምነት፣ በዝምታ ጓዳ
በጥርጥር ደፍሮ፣ እምነቱን ላልቀዳ
(ቶማስ መልስ ነበር!)
የምነታችን ልኩ፣ የኛ ጥንካሬ
ታግለን ከሸፈነው፣ አጉል ጥርጣሬ
የድፍረታችን ጥግ፣ የግዝፈቱ መኣት
ምርኩዝ አስጨብጦን፣ ከረታነው ፍርኣት
(መጠኑ እንደማያልፍ!)
መምህሩ ሲገለጥ፣ ውስጡ ሳይሸበር
እንዲያ የዳሰሰው፣ ቶማስ መልስ ነበር።
✍ (እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ለእምነት ከሆነ ስለምን ይከሰስ??
በተዘጋው ቤት ውስጥ፣ ክርስቶስ ተገልጦ
አጀብ ሲያሰኛቸው፣ ሰው ገላውን ገልጦ
ሁሉም ግራ ገብቶት
የሚያደርገው ጠፍቶት
ያለማመን ደባ፣ በውስጡ ሲሰካ
የቶማስ ጥያቄ፣ እስኪ አንዴ ልንካ?
"
ያለማመን ልኩ፣ ቢሆን በመጠርጠር
የእምነቱ ግዝፈት፣ ምን ብታህል ጠጠር
ልክ ይሆናል ቶማስ፣ እንዲያ መጠርጠሩ
ከመጠርጠር አለም፣ እምነት ለመፍጠሩ።
ለምን? እንዴት? ከተባለ
አንድ ሚስጥር አለ...
ምናልባት በዚያ ቤት፣ ሰው ሁሉ ሲያነባ
ውስጡ ተሸንቁሮ፣ ያለማመን ደባ
ሐዋሪያቱ ሁላ
ነፍሱ ተርበትብቶ፣ ባጉል ጥራጥሬ
ሸፋፍኖት በእምነት፣ ባልበሰለ ጥሬ
እህ! ብሎ በጣር፣ እንዲያ የበረታው
ምርኩዝ አስደግፎት፣ በድፍረት የረታው
(ፍርሃት ነበረው!)
ለዚያ ሁሉ ታዲያ
በፍርሃቱ አጎንብሶ
በድፍረቱ ተልፈስፍሶ
ነፍስ አካሉ ተጠራጥሮ
ለማመኑ ብቻ ጥሮ
ተሸፋፍኖ በምነት፣ በዝምታ ጓዳ
በጥርጥር ደፍሮ፣ እምነቱን ላልቀዳ
(ቶማስ መልስ ነበር!)
የምነታችን ልኩ፣ የኛ ጥንካሬ
ታግለን ከሸፈነው፣ አጉል ጥርጣሬ
የድፍረታችን ጥግ፣ የግዝፈቱ መኣት
ምርኩዝ አስጨብጦን፣ ከረታነው ፍርኣት
(መጠኑ እንደማያልፍ!)
መምህሩ ሲገለጥ፣ ውስጡ ሳይሸበር
እንዲያ የዳሰሰው፣ ቶማስ መልስ ነበር።
✍ (እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ጥሞና ግሮሰሪ
ተከሳሽ እገሌ፣ በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
*
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
*
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)
አይን አማኙም ከዚሁ፣ ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ክርስቶስ እዳዬን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።
¶
¶
በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።
✍ እንግዳዬሁ ዘሪቱ
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ተከሳሽ እገሌ፣ በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
*
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
*
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)
አይን አማኙም ከዚሁ፣ ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ክርስቶስ እዳዬን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።
¶
¶
በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።
✍ እንግዳዬሁ ዘሪቱ
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ለነገ አልምልም !
ለሰው ልጅ ሞታለሁ፣
እያለ ሲያስተምር ድንገት ከተገኜ
መምህር የገሰፀ፣
ባለም' ላይ ብቸኛ ደቀመዝሙር ሆኜ
ሞት አይንካህ አንተን፣ አትሞትም እያልኩኝ
ነፍሴን ሰጥሃለው፣ እኔ አለው እያልኩኝ
ከልቤ ከረጢት፣
ያሻኝን ፈትዬ እንዲያ ስተረትር
ነገን ከሱ ጋራ፣ እንደዚያ ስመትር
እኔ ጴጥሮስ
በክህደት ሸራ ላይ፣ ስሙን እንድስለው
ያውቅ ነበር እሱ
እስከሞት ካንተ' ጋር፣ እሆናለው ስለው።
ታዲያ
የደፈርኩት ሳይሆን፣ የነገረኝ ሆነ
እንደዚያ ስፎክር፣ ልቤ በሰከነ
ዘራፍ ያልኩት መውደድ፣ በመከራ ራደ
በእንግልቱ ምሽት፣ በእሳት ተማገደ።
ዛሬም
ካንተ በስቲያ ህይወት፣ በፍፁም እያሉ
ትላንት ላይ ቆመው፣ ለዛሬ የማሉ
ቃልኪዳን ጠብቀው፣ በቤትህ የታሉ?
እኔም
ነፍስን እስከመስጠት፣ በቃላት አልልም
ፀደይ ወቅቱ ጣፍጦኝ ፣ ለበጋ አልምልም
ይልቅ ልማፀነው፣ ልደፋ በፊቱ
እንዳልክደው ባሳር'፣ በጣር በእንግልቱ።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ለሰው ልጅ ሞታለሁ፣
እያለ ሲያስተምር ድንገት ከተገኜ
መምህር የገሰፀ፣
ባለም' ላይ ብቸኛ ደቀመዝሙር ሆኜ
ሞት አይንካህ አንተን፣ አትሞትም እያልኩኝ
ነፍሴን ሰጥሃለው፣ እኔ አለው እያልኩኝ
ከልቤ ከረጢት፣
ያሻኝን ፈትዬ እንዲያ ስተረትር
ነገን ከሱ ጋራ፣ እንደዚያ ስመትር
እኔ ጴጥሮስ
በክህደት ሸራ ላይ፣ ስሙን እንድስለው
ያውቅ ነበር እሱ
እስከሞት ካንተ' ጋር፣ እሆናለው ስለው።
ታዲያ
የደፈርኩት ሳይሆን፣ የነገረኝ ሆነ
እንደዚያ ስፎክር፣ ልቤ በሰከነ
ዘራፍ ያልኩት መውደድ፣ በመከራ ራደ
በእንግልቱ ምሽት፣ በእሳት ተማገደ።
ዛሬም
ካንተ በስቲያ ህይወት፣ በፍፁም እያሉ
ትላንት ላይ ቆመው፣ ለዛሬ የማሉ
ቃልኪዳን ጠብቀው፣ በቤትህ የታሉ?
እኔም
ነፍስን እስከመስጠት፣ በቃላት አልልም
ፀደይ ወቅቱ ጣፍጦኝ ፣ ለበጋ አልምልም
ይልቅ ልማፀነው፣ ልደፋ በፊቱ
እንዳልክደው ባሳር'፣ በጣር በእንግልቱ።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
Group : @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Join us
🎯 ♡ ❍ㅤ ⌲
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🥰 ገርሞኝ ነው 🤔🤭
ፍቅር ይሄ አይደለም ሁለት ይዞ መርጫ
ፖለቲካ አይደለም ሚያሸንፍ በእጅ ብልጫ
% እየሰጡ ከ X እና Y እያበላለጡ
የሚኖር አይደለም ከማበላለጥ ዉጡ
ነጭ ጥቁር አይልም ጎሳና ዘርን
ከያዘ ያዘ ነዉ አያቅም ሚዛን
በፍቅር አለም ውስጥ ሁሉ ሚያሸንፈዉ
ፍቅር ፍቅር ላለ ሳይሆን በደንብ ለኖረው ነው
ፍቅር እንደዚህ ነው
ፍቅር ይታገሳል ቸርነትን ያረጋል አይቀናም ፈፅሞም
ፍቅር አይመካም አይታበይ ከቶም
ፍቅር ይታገሳል ደስስ ይለዋል በእውነት
ፍቅር ተስፈኛ ነው ይታገሳል ከውነት
ሁሉንም ደሞ ያምናል አይወደቅም ተስቶት
እምነት ተስፋ ፍቅር ሁሌም አብረው ይኖራሉ
እምነትም ዋና ነው ድርድር የማያቅ
ተስፋማ ተስፋ ነው የመኖር መልህቅ
እኔን የገረመኝ ፍቅር የሌለበት እምነትና ተስፋ ባዶ መቅረቱ ነው ........ሆሆሆሆሆሆሆ
ገጣሚ ወንጌል
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
ፍቅር ይሄ አይደለም ሁለት ይዞ መርጫ
ፖለቲካ አይደለም ሚያሸንፍ በእጅ ብልጫ
% እየሰጡ ከ X እና Y እያበላለጡ
የሚኖር አይደለም ከማበላለጥ ዉጡ
ነጭ ጥቁር አይልም ጎሳና ዘርን
ከያዘ ያዘ ነዉ አያቅም ሚዛን
በፍቅር አለም ውስጥ ሁሉ ሚያሸንፈዉ
ፍቅር ፍቅር ላለ ሳይሆን በደንብ ለኖረው ነው
ፍቅር እንደዚህ ነው
ፍቅር ይታገሳል ቸርነትን ያረጋል አይቀናም ፈፅሞም
ፍቅር አይመካም አይታበይ ከቶም
ፍቅር ይታገሳል ደስስ ይለዋል በእውነት
ፍቅር ተስፈኛ ነው ይታገሳል ከውነት
ሁሉንም ደሞ ያምናል አይወደቅም ተስቶት
እምነት ተስፋ ፍቅር ሁሌም አብረው ይኖራሉ
እምነትም ዋና ነው ድርድር የማያቅ
ተስፋማ ተስፋ ነው የመኖር መልህቅ
እኔን የገረመኝ ፍቅር የሌለበት እምነትና ተስፋ ባዶ መቅረቱ ነው ........ሆሆሆሆሆሆሆ
ገጣሚ ወንጌል
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
መዳኒያለም ...
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
ማህቶት ይሏት ያደፈችው የልቤን ቋት
እንድትበራ ነፍሴን እውቀት መች መገብኳት።
እደርስ ይሆን ለደገስከው የእውነት እራት
በልጓሙ ስሜት ነፍሴን እየመራት።
እበራ ይሆን እንኳን ለሰው ለመንገዴ
አመፅ አይደል በእውነት ቃል ላይ መወንበዴ
በሞቱ ተባበር ሲለኝ ፡ የእውነት ቃልህ ለህሊናዬ
ከጨለማ ከሀጢአት ጋራ ሲተባበር ልቦናዬ
አመፅ አይደል...?
በህሊናዬ የእውነት ሚዛን የራሴን ፈቃድ ስመዝን
በአደባባይ መስክሬልህ በስውር አንተን ሳሳዝን
ታዘበኝ ብቻ ታዘበኝ
ጠላትህን ውደድ የመዳኛ ቃልህ እንዲያድናት ነፍሴን፤
ለ'ኔ እንደ'ኔ የከፋ ስላጣሁኝ ባ'ገር ስወደው ራሴን፤
በሰጠኸኝ ዘመን ድልድይ እንዳሳብህ ሳልሻገር፤
ርኩስ ሃሳብ ጓዳ ጥሎኝ በምህረትህ ቆሜ ባ'ገር፤
የራስ እሳት አጠልሽቶት ሸክላ ማህቶቴ ጨልሞ፤
ተስፈኛው ልቤ አያርፍም አሁንም ይጠይቃል ደግሞ።
መድሃኒያለም ...
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
እንደ ዮሐንስ..... እንደ መጥምቁ
ለሰማይ ፀሐይ ... ለዓለም ድብቁ
በአምላኩ ፈቃድ ራሱን ንቆ
ቀልጦ እንዳለፈው አንተን አድምቆ።
እንደዛ አርበኛ እንደ ጳውሎስ
እንደ ጴጥሮስ...
እንደ ወጣቱ ልጅ ጢሞቲሆስ
እንደ ፃድቁ ቅዱስ ስምዎን
ሸክላ መቅረዜ ይበራ ይሆን ?
ይበራ ይሆን ሸክላ ፋኖሴ
ይኖርስ ይሆን ያልሞተው ነፍሴ
አኔንጃ.....ብቻ ታዘበኝ
መኖር ነው ፡ ለዓለም መሞት ፡ ብሎኝ ቃልህ በመገለጥ
በሞትክበት መስቀል ኖሬ ላለመሞት ስንፈራገጥ
ስፍጨረጨር... ስፍገመገም
ቀንበርን ላለመሸከም...
ላንተ ከመሞት መኖርን ስመኝ
ታዘበኝ ... ብቻ ታዘበኝ
እየው ድክመቴን አመል ሲያዝለኝ
ለመኖር መኖር ስንቴ ገደለኝ
ስንዴ እንደማይሰጥ ያልሞተ ስንዴ
ያልሞተ ሻማ ይበራል እንዴ ?
መድሃኒያለም
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
➫Ⓓየሱመልስ
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
ማህቶት ይሏት ያደፈችው የልቤን ቋት
እንድትበራ ነፍሴን እውቀት መች መገብኳት።
እደርስ ይሆን ለደገስከው የእውነት እራት
በልጓሙ ስሜት ነፍሴን እየመራት።
እበራ ይሆን እንኳን ለሰው ለመንገዴ
አመፅ አይደል በእውነት ቃል ላይ መወንበዴ
በሞቱ ተባበር ሲለኝ ፡ የእውነት ቃልህ ለህሊናዬ
ከጨለማ ከሀጢአት ጋራ ሲተባበር ልቦናዬ
አመፅ አይደል...?
በህሊናዬ የእውነት ሚዛን የራሴን ፈቃድ ስመዝን
በአደባባይ መስክሬልህ በስውር አንተን ሳሳዝን
ታዘበኝ ብቻ ታዘበኝ
ጠላትህን ውደድ የመዳኛ ቃልህ እንዲያድናት ነፍሴን፤
ለ'ኔ እንደ'ኔ የከፋ ስላጣሁኝ ባ'ገር ስወደው ራሴን፤
በሰጠኸኝ ዘመን ድልድይ እንዳሳብህ ሳልሻገር፤
ርኩስ ሃሳብ ጓዳ ጥሎኝ በምህረትህ ቆሜ ባ'ገር፤
የራስ እሳት አጠልሽቶት ሸክላ ማህቶቴ ጨልሞ፤
ተስፈኛው ልቤ አያርፍም አሁንም ይጠይቃል ደግሞ።
መድሃኒያለም ...
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
እንደ ዮሐንስ..... እንደ መጥምቁ
ለሰማይ ፀሐይ ... ለዓለም ድብቁ
በአምላኩ ፈቃድ ራሱን ንቆ
ቀልጦ እንዳለፈው አንተን አድምቆ።
እንደዛ አርበኛ እንደ ጳውሎስ
እንደ ጴጥሮስ...
እንደ ወጣቱ ልጅ ጢሞቲሆስ
እንደ ፃድቁ ቅዱስ ስምዎን
ሸክላ መቅረዜ ይበራ ይሆን ?
ይበራ ይሆን ሸክላ ፋኖሴ
ይኖርስ ይሆን ያልሞተው ነፍሴ
አኔንጃ.....ብቻ ታዘበኝ
መኖር ነው ፡ ለዓለም መሞት ፡ ብሎኝ ቃልህ በመገለጥ
በሞትክበት መስቀል ኖሬ ላለመሞት ስንፈራገጥ
ስፍጨረጨር... ስፍገመገም
ቀንበርን ላለመሸከም...
ላንተ ከመሞት መኖርን ስመኝ
ታዘበኝ ... ብቻ ታዘበኝ
እየው ድክመቴን አመል ሲያዝለኝ
ለመኖር መኖር ስንቴ ገደለኝ
ስንዴ እንደማይሰጥ ያልሞተ ስንዴ
ያልሞተ ሻማ ይበራል እንዴ ?
መድሃኒያለም
የዓለም ብርሃን ጌታዬ ሆይ
የኔ መቅረዝ ይበራል ወይ ?
➫Ⓓየሱመልስ
Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs