ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
15.5K subscribers
335 photos
80 videos
146 files
208 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
ለካህን_መናዘዝና_ቀኖና_መቀበል_ለምን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
333.1 KB
ለካህን መናዘዝና ቀኖና መቀበል ለምን?

* የተሐድሶዎች ትምህርት ለካህን ስለመናዘዝና ቀኖና ስለመቀበል
* በዚህ ጉዳይ ላይ የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች
* ለንስሐ አባት መናዘዝና ቀኖና መቀበል በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
* ቀኖና የሚሰጥባቸው ምክኒያቶች
* ንስሐ አባትና ቀኖና በአበው ትምህርት

~ +++++ ~~

“ነቢዩ ናታን ንጉሥ ዳዊትን ኃጢአቱን ከነገረው በኋላ ወዲያውኑ ኃጢአቱን እንዳመነ አጽናንቶት ነበር፡፡ ሆኖም ብፁዕ ዳዊት ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፡ ኣትሞትም' (2 ሳሙ. 12፡13) የሚለውን የነቢዩን ቃል የሰማ ቢሆንም ንስሐ ከመግባት ግን አልተመሰለም፡፡ ንጉሥ የነበረ ቢሆንም በልብሰ መንግሥት ፋንታ አመድ ለበሰ በወርቅ ዙፋን ላይ በመቀመጥ ፋንታ በመሬት ላይ፣ ያውም በአመድ ላይ ተቀመጠ፡፡ በአመድ ላይ የተቀመጠ ብቻ ሳይሆን አመድንም ምግቡ አደረገ፤ እርሱ ራሱ “አመድን እንደ እህል ቅሜያለሁና፣ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና” (መዝ 101፡9) ብሏልና፡፡ ወደ ኃጢአት የተመለከተው ዓይኑ በዕንባ እስኪሟሟ ደረሰ፤ “ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ፤ ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች” እንዳለ፡፡ መዝ. 6፡6-7 መኳንንቱ እህል እንዲቀምስ በለመኑት ጊዜ እንኳ አልሰማቸውም፡፡ ጾሙን እስከ ሰባት ሙሉ ቀናት አራዘመ፡፡ ንጉሥ የነበረው እርሱ እንዲያ ባለ ሁኔታ ንስሐ ከገባ ተራ ግለሰብ የሆንከው አንተ ንስሐ ልትገባና ልትናዘዝ አይገባህምን?” (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ትምህርት 2 በእንተ ንስሐ ወሥርየተ ኀጢአት፣ ቁ 12)


#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አትጨነቁ

መጨነቅ የበታችነት ስሜትን ይፈጥርባችኋል
ምንም ነገር አትጨምሩም ብዙ ነገር ግን ይጎድልባችኋል

https://youtu.be/bqZoGJ1-Vhw?si=AvCSrtlkBrE8YVDF

#መምህር_ኢዮብ_ይመኑ
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን!››
 
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል(ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም፣ ቤተ ፋጌ በቀረበ ጊዜ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሁለቱን ሐዋርያት ወደ ቤተ ፋጌ ልኮ የታሰረች አህያ እንደሚያገኙና ፈትተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ከመጣ ‹‹…ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ…›› አላቸው፤ (ማቴ.፳፩፥፫) ፈትታችሁ አምጡ ማለቱ ሕዝቡን ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈቱበት ጊዜ እንደ ደረሰ ሲያጠይቅ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም በሥጋዊ ጥቅም በኃላፊ ደስታ ዓይነ ልቡናችንን ጋርዳ፣ ሥጋዊ ፈቃዳችን ከፈቃደ ነፍሳችን አይሎ በኃጢአት ማዕሰር ታስረናል፡፡ ጌታችን በትምህርቱ ‹‹…ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው፤ ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም…›› በማለት እንደገለጸው በበደላችን በኃጢአት ባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን በዲያብሎስ ባርነት ታስረናል ፤ (ዮሐ.፰፥፴፬) ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን››፤ ከታሰርነበት የጥላቻ፣ የቂም፣ የዘረኝነት፣ የጎጠኝነት የኃጢአት ማሰሪያ ይፈታን ዘንድ ‹‹እባክህ አሁን አድነን!›› እንበለው፡፡
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- አይሁድ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የምስጋና ባለቤት ከሆነው ዘንድ በተሰጣቸው ኃላፊነት ምስጋና የባሕርይው የሆነን ፈጣሬ ዓለማት መድኅን ዓለም ክርስቶስን ማመስገን፣ አመስግነው መመስገን፣ ቅዱስ ስሙን ጠርተው መቀደስ ሲገባቸው በተቃራኒው ልባቸው በጥላቻና በቅናት ተመልቶ የሚያመሰግኑት ዝም ይሉ ዘንድ ጠየቁ፤ አንደበትን ለምስጋና የፈጠረ ጌታ ግን ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ›› አላቸው፤ ምንም የሚሳነው የሌለ ጌታም ድንጋዮች ያመሰግኑት ዘንድ አደረገ፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵)
 
ጌታችን በትምህርቱ ‹‹ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም›› በማለት እንደገለጸው የክፋት ሥራቸውን የሚገልጥ፣ ጨለማ አስተሳሰባቸውን የሚያበራ የብርሃን ጌታ ሲመጣ የእርሱ መገለጥና መመስገን እነርሱን የሚያሳንስ ስለመሰላቸው ተቃወሙ፡፡ ክህነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነና  የሰጣቸውም እርሱ እንደሆነ ማስተዋል ቢሳናቸው የራሱን ገንዘብ ምስጋናውን ለማስቀረት ፈለጉ፤ (ዮሐ.፫፥፳) ማድረግ የማይቻላቸውን ሊያስቀሩ ደፈሩ፤ ክፉዎች  የቅኖች ደግነት፣ የመልካሞች በጎ ሥራ፣ የትሑታን የተሰበረ መንፈስና  የአመስጋኞች ምስጋናቸው ይረብሻቸዋል፡፡ ልቡናቸውን ለጠላት ዲያብሎስ ማኅደር ስላደረጉ የቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ሲጠራና ምስጋናው ሲደመጥ ሰላም ይነሳቸዋል። ዲያብሎስ  እግዚአብሔር ሲመሰገን፣ ሰው ንስሐ ሲገባ፣ የምሥራቹ ወንጌል ሲነገር፣ ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ሲበዙ፣ ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች ሲፋቀሩ አንድነት ሲጸና፣ ሕገ እግዚአብሔር ሲከበር፣ ክርስትና ሲሰፋ፣ በዓላት ሲከበሩ ማየትና መስማት አይሻም፤ የግብር ልጆቹን እያሰማራ መንፈሳዊውን ዓለም ያውካል፤ ሁሉም እንደ እርሱ ከፈጣሪው ተጣልቶ በክህደት እንዲኖር ይፈልጋሉ። ዓለም ሳይፈጠር ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ ምስጋናው ሳይቋረጥ የኖረውን ጌታችንን በእናታቸው እቅፍ ያሉ ሕፃናት፣ አዕባን (ድንጋዮች) “ለምን አመሰገኑት” ብለው የቅናት ጥያቄ እንደጠየቁት ማለት ነው።
 
ዛሬም በሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ አድሮ “ለምን አመሰገናችሁ? ለምን አምልኮተ እግዚአብሔር ፈጸማችሁ” በማለት ምስጋናውን ሊያስቀር ይጥራል፤ ግን አይቻለውም! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በስሙ እንዳያስተምሩ፣ ባስፈራሯቸውም ጊዜ  ‹‹… ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል…›› አሉ፡፡ (የሐ. ሥራ ፭፥፳፱) እኛም ልጆቻቸው የአሠረ ፍኖታቸው ተከታይ ነንና! ዛቻና ማስፈራራቱን ሳንፈራ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ  አሁን አድነን››  እንላለን፡፡ አመስግነን እንመሰገን፣ ቀድሰን እንቀደስ ዘንድ ከባለጋራችን ዲያብሎስ የተቃውሞ ዛቻና በትር እንዲታደገን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…መድኃኒት ሁነን›› ብለን እንዘምራለን፡፡
 
ዲያብሎስ በግብር ልጆቹ ልቡና አድሮ በግፍ በትር ሊሸነቁጠን በተስፋ መቁረጥ ገመድ አስሮናልና  ቅዱሳን በቃል ኪዳናቸው ይፈቱን ዘንድ ይልክልን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን›› እንበለው፤ በነቢዩ ዘካርያስ  አማካኝነት ‹‹…የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በይ፥ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል…›› በማለት በተናገረው ቃል መሠረት መምህረ ትሕትና የዓለም ጌታ መድኅን ክርስቶስ በአህያይቱና በውርንጭላይቱ  ዘባን ( ጀርባ) ተቀምጦ ሲመጣ  በኢየሩሳሌም የነበሩ ልብሳቸውን ከምድር አነጠፉ፤ (ዘካ.፱፥፱) “እንኳን ለአንተ ለተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባል” ሲሉ! ትሕትናን ከእርሱ በተግባር ተምረዋልና በትሕትና የለበሱትን ልብስ አውልቀው ከምድር አነጠፉ፤ በጥቂት የትሕትና ሥራቸው ዝቅ ካሉበት ከሰጠሙበት የበደል አዘቅት ከፍ ያደርጋቸውና ያከብራቸው  ዘንድ  ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…!›› በማለት ተማጸኑት፤ እኛም ከልቡናችን እልፍኝ በጎ ሥነ ምግባር ልብሳችንን አንጥፈን ይገባበት ዘንድ ‹‹በሰማይ ያለ መድኃኒት ናልን›› ብለን እንጋብዘው፡፡
 
በሆሣዕና በዓል ዕለት በምስጋናው ጊዜ ዘንባባን እንይዛለን፤ ጌታችን በአህያና በውርንጭላይቱ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ከልብሳቸው በተጨማሪ የዘንባባ ዝንጣፊም ይዘው ነበር፤ በብሉይ ኪዳን ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ወጡ፤ ዮዲት ወገኖቿን ሲያስጨንቅ ንጹሐንን በግፍ ሲገድል የነበረውን ሆሎፎርኒስ የተባለን ሰው ገድላ በተመለሰች ጊዜ ዘንባባን ይዘው ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድም ይላሉ መተርጉማነ አበው ‹‹ዘንባባ እሾኻማ ነው፤ ትእምርተ ኃይል (መዊእ) አለህ›› ሲሉት አንድም ዘንባባን እሳት አይበላውም፤ ለብልቦ ይተወዋል፤ ባሕርይ አይመረመርም›› ሲሉ ነው፡፡ የሰላም አለቃ፣ ኃያል፣ ልዑል፣ ባሕርይው የማይመረመር አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ይሆነን፣ ያድነን ዘንድ በሕጉ ተጉዘን፣ ትእዛዙን፣ አክብረን፣ በትሩፋት ሥራ አጊጠንና የምግባር ዘንባባን ይዘን ጠላት ዲያብሎስን ድል አድርገን ‹‹ሆሣዕና›› እንበለው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አድምታ ትርጓሜ ፳፩፥፰) ዝቅ ካልንበት ከፍ ያደርገን ዘንድ ከእግሩ በታች ራሳችንን እናዋርድ፤ ‹‹… በመጠን ኑሩ፤ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና …›› እንደተባለው፤ (፩ኛጴጥ. ፭፥፰) በአህያ ውርንጭላ ጀርባ ተቀምጦ ስለ እኛ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከፍ አድርጎናል፤ ዳግመኛ በኃጢአት ቀንበር ወድቀን በባርነት እንዳንያዝም በጾምና በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡
 
‹‹አምላካችን ሆይ! እባክህ አሁን አድነን!››
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ! አሜን
 
The Crucifixion of the King of Glory... (Z-Library) (1).pdf
4.5 MB
The Crucifixion of the King of Glory: The Amazing History and Sublime Mystery of the Passion

Dr. Eugenia Scarvelis Constantinou
በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፦

#ኪራላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ
< ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው። #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው።
#እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።
#ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው።
#ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው።
#ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።
Forwarded from Father Sergiy Baranov
Do not despair or be upset. The word "upset" means that you are like an upset mechanism that is good for nothing. You should see your mistake and amend it immediately. When a person repents of a certain misdoing for a long time that seems to last for hours, days, and months, he loses his time for reformation, or metanoia. He simply repeats the same fact, "I sinned, I sinned, I sinned."
To which the Lord answers him, "Yes, I've already heard this. Do something about it."
You should change the situation and work on it.
#archpriestSergiyBaranov
ጸሎተ ሐሙስ!

ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡

በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤ አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡
ጌታችንም ጊዜው ሲደርስ ከሐዋርያት ጋር በአንድነት መጣ፤ ስምዖንም ከቤቱ ወጥቶ ሮጦ ከጌታ እግር ሥር ሰገደ፤ ወደ ቤቱም ከሐዋርያት ጋር አስገባቸው፡፡ ይሁዳ ግን ይህን ሰዓት አልነበረም፤ ውጪ ከሻጭና ለዋጭ ጋር ገንዘብ ሲደራደር ነበር፤ ስምዖንም ለሚስቱ አክሮሲና ጌታና ሐዋርያት የሚገቡበት በእግራቸው የሚረግጡት ምንጣፍ እንድታነጥፍ አዘዛት፡፡ አክሮሲና ግን የጌታን መልክ አታውቀውም ነበር፤ ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎት ሲጸልዩ አይታ ‹‹ከእናንተ ውስጥ መምህሩ ማነው›› አለቻቸው፤እነርሱም ዝም አሉ፤ መልከ መልካም ወደ ሆነውና የጌታ ወዳጅ ወደሆነው ዮሐንስ ተመልክታ እርሱ ይሆን አለች፤ ጴጥሮስ ግን ቀበል አድርጎ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ከውስጠኛው ክፍል ቆሞ ይጸልያል፤ ጌታ እርሱ ነው›› አላት፡፡ እርሷም ገብታ ሰገደችለት፤ ይሁዳም በመጨረሻ ሳጥን ተሸክሞ መጣ፤ ጠባቂውንም እኔ የጌታ ደቀ መዝሙር ነኝ አለው፡፡ በር ጠባቂውም እለእስክንድሮስም የተነጠፈውን እስካጥፍ ጠብቅ ብሎ ዘለፈው፤ ልብሱንም አንስቶ አስገባው፤ /ግብረ ሕማማት ፭፻፹፫-፫፻፹፭/፡፡

በአንደኛው ሰዓት ሌሊት (ሐሙስ ለአርብ ምሽት)፤

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልብሱን አኖረ፤ማበሻ ጨርቅም አንስቶ ወገቡን ታጠቀ፤ ይህችውም ሥራ የምታሠራና የምታስጌጥ ናት፤ ለዛሬው የመነኮሳት መታጠቂያ አብነት ናት፡፡ ለምሳሌ፡- ኢዮአብ ወደ ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረችው ያለ ዓይነት ነው፤ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በጴጥሮስ ጀመረ፤ ጴጥሮስ ግን እኔ ባንተ ልታጠብ አይገባኝም አለ፤ ጌታችንም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)፡፡ ሌሎቹንም ሐዋርያት አጠባቸው፤ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳንም እግሩን አጠበው፡፡ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፤ ፍቅርን ሲያስተምረውና ለንስሐ ጊዜ ሲሰጠው ነው እንጂ፤ እኛንም ለሚወደን ብቻ ሳይሆን ለሚጠላን እንኳን በጎ ማድረግ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው፡፡

ጌታችን ጾመና ጹሙ አለን፤ተጠመቀና ተጠመቁ አለን፤ ጸለየና ጸልዩ፤ ሰገደናም ስገዱ አለን፤ የሐዋርያትንም እግር አጥቦ እናንተም እንዲህ አድርጉ ብሎ መምህረ ትሕትናነቱን ገለጠልን፡፡ ዛሬም ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት በየመአርጋቸው የምእመናኑን እግር በማጠብ የጌታን የትሕትና ሥራ ያስቡታል፡፡

ለሐዋርያት ትሕትናን ሲያስተምራቸው ጌታችን እግራቸውን እንደ አጠባቸው ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ከዚያም ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ ብሎ ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፤ ዛሬም የልጅነት ጥምቀት የሚቀበሉ ምእመናን በዚያኑ ዕለት ከክርስትና ቤት ወደ ቤተ መቅደስ ሔደው የጌታን ክቡር ሥጋና ደም ይቀበላሉ፤ መሠረቱም ጌታችን ለሐዋርያት ያደረገውን ተመርኩዞ ነው፡፡ ከፍ ከፍ ሊል የሚወድ ራሱን ዝቅ ያድርግ ብሎም አስተምሯቸዋል፤ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር ጌታ ለጴጥሮስ ‹‹እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› ያለውን ሲተረጉሙ ‹‹እኔ በአገልጋይ አምሳል እግርህ ካላጠብኩህ አንተም ከበታችህ ላሉት ራስህን ዝቅ ለማድረግ አትችልም፤ ራስህን ዝቅ ዝቅ ካላደረግህ አለቃ ልትሆን አትችልም›› ለማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ ጌታችን ደግሞ አምላክ ፈጣሪ መምህር ሳለ ዝቅ ብሎ እንዳጠባቸው እነርሱም ክህነታቸውንና መምህርነታቸውን በትሕትና እንዲጀምሩ ሲያስተምራቸው ነው፡፡

በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ምሽት፤

ጌታችን ሕብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ፈትቶ ሰጣቸው፤ ዐሥራ ሦስተኛውን እርሱ የሚቀበለው ነውና ነገር ግን የሚረባውና የሚጠቅመው አይደለም፤ ‹‹ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ›› ብሎ ሕብስቱን ባርኮ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ›› ወይኑንም ባርኮ ‹‹ይህ ደሜ ነው እንካችሁ ጠጡ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡አስራ ሦስት አድርጎ መፈተቱ ሐዋርያትን እንዳይገርማቸው (እንዳያስፈራቸው) ነው፤ እራሱም ጥዒሞ አጥዐሞሙ/ቀምሶ አቀመሳቸው/ እንዲል አብነት ለመሆን፤ አንድም ነገ በመልዕተ መስቀል አስራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል እቀበላለሁ ሲል ነው፤ ጌታ ይህን ባያደርግ ኖሮ ዛሬ ካህኑ የጌታን ሥጋና ደም ሳይቀበል አቀብሎ ብቻ በሄደ ነበርና ለእነርሱ ለማስተማር ነው፡፡

ማዕዱንም እየበሉ ጌታችንም ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አላቸው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፩)፡፡ ሐዋርያት ሁሉ ደነገጡ! እርስ በርሳቸው ተያዩ፤‹‹እኔ እሆን? እኔ እሆን?›› ተባባሉ፤ ጴጥሮስም ዮሐንስን ጠጋ ብሎ ‹‹ማነው አሳልፎ የሚሰጠህ ብለህ ጌታን ጠይቀው›› አለው፤ወንጌላዊው ዮሐንስም ጌታን ጠጋ ብሎ ጠየቀው ጌታችንም ‹‹ከእኔ ጋር እጁን ከወጪቱ የሚያገባ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አለ፤ (ማቴ.፳፮፥፳፫/ሉቃ.፳፪፥፳፩)፡፡ ሐዋርያትም ‹‹ሁላችን ከወጪቱ የምንጠቅስ አይደለምን?›› ሲሉ ጌታችን ‹‹እኔ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው ነው›› አላቸው፤ ያንጊዜ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው፤ ስለዚህ ወንጌላውያኑ ይህን ታሪክ ይዘው አንድ ሳለ በተለያየ አገላለጥ ገለጡልን፡፡

ይሁዳም እንደቸኮለ ሰው ይቅበዘበዝ ነበር፤እርሱም ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ጌታም ወደ ይሁዳ ጠጋ ብሎ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ! ልትሠራው የምትሻው ሥራ ካለ ሒድ›› አለው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፯)፤ ይሁዳም ፈጥኖ ወጥቶ ወደ አይሁዳውያን ጌታን አሳልፎ ሊሰጥ ዋጋ ሊነጋገር ሔደ፡፡

ከሦስተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ አምስተኛይቱ ሰዓተ ሌሊት ድረስ

ለደቀ መዛሙርቱ ሲመክራቸው የመንፈስ ቅዱስንም መምጣት አብዝቶ ሲነግራቸው፤ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቀና፤ እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነም ነገራቸው፤ ለብቻው ፈቀቅ ብሎ ወዙ እንደ ደም እስኪፈስ እየሰገደ ጸለየ፤ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመለሰ፤ ተኝተው አገኛቸው፤ ቀሰቀሳቸው፤ ጴጥሮስንም አንድ ሰዓት ያህል እንኳን ከእኔ ጋር መትጋት አቃታችሁን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ አለው! (ሉቃ.፳፪፥፲፬-፵፮)፡፡

የጌታችን በአይሁድ መያዝ (ስድስተኛው ሰዓተ ሌሊት)

ጌታችንም ከአብ ጋር ስላለው አንድነትና ክብር ለሐዋርያት ካስተማራቸው በኋላ ‹‹ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ በዚያም ገባ›› (ዮሐ.፲፰፥፩)፡፡ወንዙን ተሻግሮ ያለውን ዛፍ አልፎ ወዳለው ዱር ገባ፡፡ ይሁዳም ይህችን ስፍራ ቀድሞ ጌታ ይመጣባት ስለነበር ያውቃት ነበርና ጭፍሮችንና የካህናት አለቆችን ፈሪሳውያን ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን አስከትሎ መጣ፡፡ ጌታችንም ‹‹ተነሡ እንሂድ! እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል›› አላቸው ወደ እነርሱ መጥቶ ቀረበ፤ ይሁዳም ወደርሱ ቀርቦ፤ ‹‹መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ ይሁን›› ብሎ ሳመው፤ ይህ መሳም ለአይሁድ ጥቆማ ወይም ምልክት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታ መልክና የወንጌላዊው የዮሐንስ መልክ ይመሳሰልባቸው ነበርና ሲለይላቸው ነው፤ ጌታችንም ‹‹በስኢምኑ ታገብኦ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው፤ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠዋለህን?›› አለው (ሉቃ.፳፪፥፵፰)፡፡
ይሁዳም ከጭፍሮቹ ጋር መጣ፤ ጌታ ኢየሱስንም ከበውት ወደ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ወሰዱት፤ ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ከአንደኛው ቅጥር ግቢ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ አይሁድም በክርስቶስ ላይ ሁለት የሐሰት ምስክሮችን አመጡ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ›› ብሏል ብለው ከሰሱት፤ ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ ‹‹እንዲህ ሲያጣሉህ አትሰማምን›› አለው፡፡ ጌታችን ግን ምንም አልመለሰለትም፤ሊቀ ካህናቱም ‹‹ክርስቶስ ተብሎ የተነገረልህ የእግዚብሔር ልጅ አንተ እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ አልክ›› አለው፤ ያን ጌዜ ሊቀ ካህናቱ ተናዶ ልብሱን ቀደደው፤ራሱንም በብረት ዘንግ መቱት፤ የስቃዩ ጅማሬ ይህን ጊዜ ነበር፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ