ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
22.4K subscribers
380 photos
97 videos
169 files
284 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
እንደ ጋኔን ቅናተኛ የለም፡፡ ቅናቱ ግን በሰው ልጆች ላይ እንጂ እርሱን በሚመስሉ አጋንንት ላይ አይደለም፡፡ ሰው ግን በገዛ ወንድሙ ላይ ይቀናል፤ በአጋንንት እንኳን በጭራሽ የማይደረግ በገዛ ቤተ ሰቡ ላይ ይቀናል፡፡ ታዲያ እንደዚህ ዓይነት ሰው እንዴት ይቅርታን ያገኛል? እንዴት ምሕረት ቸርነትን ያገኛል?

+ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሚያዝያ ፴ በዚህች ዕለት ወንጌልን የጻፈ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ዐረፈ።

በረከቱ ከሁላችን ጋር ትሁን !
አሜን
#ግንቦት_1

#ልደታ_ለማርያም

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
#በእርግጥ_እግዚአብሔር_ይቆጣል_ወይ?

አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ፦ ‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
+++ የዘመኑ ፈተና... +++

የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡

 ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?

 ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡

 ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ?

በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!

እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡

ጸጉር የተቆረጠውም ሰው መልሶ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››

‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2

ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አንዳንድ ሰዎች ልበ ቢሶች ሆነው "እግዚአብሄር ዘወትር ሳቅንና ጨዋታን ይስጠኝ እንጂ ሁልጊዜ ማዘንንስ ከእኔ ያርቅልኝ" ይላሉ። ከዚህ በላይ ምን አላዋቂነት አለ? ዘውትራዊ ሳቅንና ጨዋታን የሚሰጥ ዲያቢሎስ እንጂ እግዚአብሔር አይደለምና። ቢያንስ እስኪ ሳቅንና ጨዋታን ያበዙት ዕጣ ፈንታቸው ምን እንደሆነ አድምጡ። "ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሱ" ይላልና (1ኛ ቆሮ 10:7 ፣ ዘጸ 32:6)። የሰዶም ሰዎችና የኖኅ ዘመን ሰዎች እንደዚህ ነበሩ። የሰዶም ሰዎችን አስመልክቶ ግብራቸውን ሲናገር "ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ስራ መፍታት" ይላልና (ሕዝ 16:49)። በኖኀ ዘመን የነበሩ ሰዎችም ለብዙ ዓመታት መርከቢቱ ስትዘጋጅ እንኳ እያዩ ሊመጣ ያለውን መዓት ምንም ሳያስቡ ሲበሉ፣ ሲጠጡና ሲዘፍኑ ነበር(ማቴ 24:38)

ስለዚህ ይህ ከዲያቢሎስ የምትቀበሉትን ነገር እግዚአብሄር ይሰጣችሁ ዘንድ አትለምኑት። እግዚአብሔር የሚሰጠው የተሰበረና ትሑት ልብን፣ በመጠን መኖርንና ራስን መግዛትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔርን፣ ንሰሐን ኹሉና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የኾነ ኃዘንን ነውና።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአልዓዛርና ለከተማይቱ ዕንባውን አፍስሶአልና፣ በይሁዳ ምክንያትም ውስጡ ታውኮአልና። አንድ ሰው ጌታችን ብዙ ቦታ ላይ እንደዚህ ሲያደርግ በርግጥ ያገኘዋል። አንድም ቦታ ላይ ግን ሳቀ፣ በጥቂቱም ወይም በትንሹም ቢኾን ፈገግ አለ የሚል አያገኝም። ንዑድ ክቡር የሚሆን ጳውሎስም ሶስት አመት ሙሉ ሌሊትና ቀን በዕንባ እነደነበረ እርሱ ራሱ ተናግሯል ሌሎችም ይህንን መስክረውለታል (ሐዋ 20:31)። እንደ ሳቀ ግን እርሱ ራሱም የትም ቦታ አልተናገረም ሌሎችም ቅዱሳንም ስለእርሱም ኾነ እርሱን ስለሚመስሉ ሌሎች ቅዱሳን እንደሳቁ ምንም አልነገሩንም። ሣራ ብቻ እንደ ሳቀች በዚህም አንደተወቀሰች(ዘፍ 18: 12-15) ፣ ነፃ የነበረው የኖኅ ልጅም በመሳቁ ምክንያት የወንድሞቹ ባርያ እንደ ኾነ ግን ይነግሩናል (ዘፍ 9:25)።

እንደዚህ ብዬ ስናገር ግን የልብ አለል ዘሊልነትን ከእናንተ ማራቅ ስለምሻ እንጂ ሳቅን ኹሉ ስነቅፍ አይደለም። ጠቢቡ "ለመሳቅ ጊዜ አለው" እንዲል (መክ 3:4)። ነገር ግን እስኪ ንገሩኝ ብዙ ወቀሳ ሊጠብቀን እንደሚችል፣ በሚያስፈራው የፍርድ ዙፋን ፊት እንደምንቆም፣ በዚኽ ዓለም ለሰራነውም ኹሉ አንድ በአንድ መልስ እንደምንሰጥ እያወቅን ተድላ ደስታን እንዴት እናደርጋለን?? ስለዚህ ዘወትር መሳቅ ፣ ስረአት የለሽና ቅምጥል መሆን ከዲያቢሎስ ጎን ለተሰለፉ ሰዎች ነው እንጂ ለእኛ ለክርስቲያኖች አይደለም።

አሁን የነገርኃችሁን ነገር ሰምታችሁ ካዘናችሁ አመሰግናችኋለው፣ " በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው?" ይላልና (2ኛ ቆሮ 2:2) እንዲህ ማዘናችሁንና መፀፀታችሁንም መቼም ቢኾን መች አታቋርጡ። ይህ ሀዘን በበጎ ለመለወጥ መነሻ ይኾናልና። ንግግሬንም ያበረታሁትም በውስጣችሁ ያለው መርዝ ከምንጩ እንዲወጣ አድረጌ እናንተን ከዚያ ለማውጣትና ፅኑ መድኃኒት ጨምሬ ነፍሳችሁን ጤናማ ለማድረግ ነውና። እነደዚህ ብዬ የተናገርኩት ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ ክብርና ጌትነት የባህርይ ገንዘቡ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ኹላችንም እግዚአብሔር የሚሰጠንን ርስቱና ክብሩን እንድንወረስ ነውና አሜን!

ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
የማቴዎስ ወንጌልን እንዳስተማረው
ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት (#ነገረ_ድህነት) #ክፍል_አራት ( #4.4 )

#መዳን_ማለት_ምን_መሆን_ማለት_ነው?

#4. #እግዚአብሔርን_በመምሠል_ማደግ /ሱታፌ አምላካዊ(θέωσις-Theosis or Divinisation)

.....መዳን ስንል ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ከእርሱ ጋር ፍፁም አንድነትና ሕብረት ለማግኘት የሚደረግ እድገት ነው። ........

ይህ በቅድስና እግዚአብሔርን በመምሰል የማደግ ሒደትም ከእግዚአብሔር ቅድስና የመሳተፍ ሱታፌያዊ ሒደት ነው። የዚህ ትምህርት መሠረቱም መፅሀፍ ቅዱስ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ " ስለ ክፉ ምኞት በአለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባህርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን" ይላል። 2ኛ ጴጥ 1፥4 ታዲያ ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ባህርይ ፍጡር ገንዘብ ማድረግ ይችላል ማለት ነውን? አይደለም። የእግዚአብሔር ባህርይ (οὐσία-God's essence) ለሌላ ለማንም አይተላለፍም፤ አይመረመርምም።ነገር ግን ሐዋርያው ይህን ያለው የባህርዩ መገለጫና መታወቂያ የሆኑትን ኃይላተ እግዚአብሔር (ενέργεια- Divine energies) ቅድስና፣ ቸርነት፣ ደግነት፣ ጥበብ፣ እውነተኛነት፣ ገዢነት ወዘተ የመሳሰሉትን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ የተሠጠን በመሆኑ ነው። ይህም ከpantheism እርሾ የፀዳ መፅሀፍ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርት ነው። ........

መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሀንስ ወንጌል በተፃፈው ትምህርቱ ላይ ለአይሁድ ሲናገር አስቀድሞ በዳዊት " እኔ ግን አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በህጋችሁ የተፃፈ አይደለምን?" በማለት የተናገረው ይህን ለሰው ልጅ የተዘጋጀውን ፀጋ ሲያስረዳ ነው። መዝ 81፥6፤ ዮሀ 10፥34 #የፀጋ_አምላክነት የተባለውም በባህርይ ያይደለ ፈቃድን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር አንድ በማድረግና እግዚአብሔርን እየመሠሉ በመሄድ የሚገኝ ክብር ነው። በዚህም ሰው በባህርዩ ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ነገሮች በኃይለ እግዚአብሔር አማካኝነት ማድረግ እየቻለ ይሔዳል።

አስቀድሞ እግዚአብሔር ሙሴን "ለፈርኦን አምላክ አድርጌሀለው" ብሎት ነበር። ዘፀ 7፥1 መድሀኒታችንም "እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ስራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል" ያለው ለዚህ ነው።ዮሀ 14፥12 እንዲህ ባለው የመዳን መንገድ በመጓዝ እግዚአብሔርን ወደ መምሰል በማደግ ላይ ያሉ ሰዎች " እኛስ የክርስቶስ ልብ አለን" እስከማለት ሊደርሱ ይችላሉ። 1ኛ ቆሮ 2፥16 ......

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር "ሰውን እንደመልካችን፣ እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ካለ በኋላ "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፣ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው" ይላል። ይህም ማለት ሰው አርአያ (መልክ) እግዚአብሔር እና አምሳለ እግዚአብሔር (ምሳሌ) ተሠጥተውታል ማለት ነው።ከእነዚህ የመጀመሪያውን (የእግዚአብሔር መልክ) ሲፈጥረው ሰጥቶታል። ዘፍ 1፥26-27 ሁለተኛውን ማለትም "የእግዚአብሔር ምሳሌን" ግን ከተሠጠው ከእግዚአብሔር "መልክ" ተነስቶ የተሠጠውን ፀጋ በማሳደግ ወደ ፊት ይደርስበት ዘንድ የተቀመጠለት፣ ሆኖም ገና ያልደረሠበት ፀጋ ነው።.......

#መድሎተ_ፅድቅ ቅፅ አንድ፣
ምዕራፍ ሶስት ገፅ 109- 119
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው።

አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ።

አባ መቃርዮስም "ስትሰድባቸው፣ ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት።
የ፹ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ አፋን ኦሮሞ ትርጉም ሂደት በፍጥነት ተጠናቅቆ ለምዕመናን ተደራሽ የሚሆንበት ሂደት ላይ ውይይት ተደርጓል !!!


ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ.ም (ተሚማ/አዲስ አበባ)



+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር  የአፋን ኦሮሞ ፹ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሂደት ላይ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ውይይት ማካሄዱ ይታወሳል።

በውይይት መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂና የቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከትን የሚመሩ ብፁዓን አባቶች ተገኝተው የ፹ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ አፋን ኦሮሞ ትርጉም ሂደት በፍጥነት ተጠናቅቆ ለምዕመናን ተደራሽ የሚሆንበት ሂደት ላይ ውይይት ተደርጓል።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአፋን ኦሮሞ መጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሂደትን ለማፋጠን ከብፁዓን አባቶችና ከሊቃውንት የተውጣጣ ኮሚቴ አቋቁሞ እንደነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በገጠመው በጀት እጥረትና የመጽሐፍ ቅዱስ ሕትመት በሀገር ውስጥ አለመጀመሩ በተግዳሮትነት የቀረቡ ሲሆን በቀጣይ እነዚህን ችግሮች በመፍታት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕትመት ሥራው የሚጠናቀቅበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል ።

#Ethiopia
#Ethiopia_bible_association
#addisababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የሚሠራውን ሥራ በማጠናከር ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለዛሬውና ለነገው የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማዘጋጀት ግብረ ሰላም የተሰኘ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የጀመረ ሲሆን የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን !
እንግዳ ሲመጣ ቆሻሻ ልብስ አይለበስም፡፡ እንግዳ ሲመጣ የሚያስጸይፍ ነገር አይነገርም፡፡ ክርስቶስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲኖር ስንፈልግም ቆሻሻ ልብሳችንን (ማንነታችንን) አውልቀን ልንጥል ያስፈልጋል፤ አስጸያፊ ነገራችንን ልንተው ያስፈልጋል፡፡ እንግዳ ሲመጣ ቤት ያፈራው ኹሉ ይቀርብለታል፡፡ ክርስቶስ ወደ ቤታችን ሲመጣም የሚበላ ነገር ልናቀርብለት ይገባል፡፡

ለመኾኑ የክርስቶስ መብል ምንድን ነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጥያቄ ሲመልስልን እንዲህ ብሏል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4፡34/፡፡ እንኪያስ ክርስቶስ የራበው ይኼው ነውና እንመግበው፤ ኢየሱስ የጠማው ይኼው ነውና እናጠጣው፡፡ እርሱም ይቀበለናል፡፡ አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ብንሰጠው እንኳ ይቀበለናል፡፡ ስለ ብዛቱ ሳይኾን ስለ ፍቅሩ ብሎ ይቀበለናል፡፡ እኛን ስለመውደዱ ይቀበለናል፡፡ የምንወደው ሰው የሰጠነውን የሚቀበለን ስለ መጠኑ አይደለም፤ ስጦታው የወዳጅ ስለኾነበት እንጂ፡፡ ሰው ወዳጁ ጌታም ኹለት ሳንቲም እንኳን ብንሰጥ ብዙ እንደሰጠን አድርጐ ይቀበለናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታችንን የሚቀበለው ድኻ ስለኾነ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድኻውም የባለጸጋውም ስጦታ እኩል የሚቀበለው ስለ ልቡናችን ኀልዮት (Intention) እንጂ ስለ ስጦታው ትልቅነት ወይም ዋጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን እንደምንወደው ለመግለጽ የግድ ብዙ ወይም በውድ ዋጋ የተገዛን ስጦታ መስጠት አያስፈልገንም፡፡ ስጦታችን እርሱ ወደ እኛ ስለመጣ ደስ የመሰኘታችን መግለጫ ነውና ስለ ስጦታችን መጠን ልንመለከት አይገባም፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ሰማዕትነት_አያምልጣችሁ
ተርጓሚ #ገብረእግዚአብሔር_ኪደ
ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት (#ነገረ_ድህነት) #ክፍል_አምስት

#የሚድኑ_እነማን_ናቸው?
በኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት እግዚአብሔር ከመዳን ውጪ ያደረገውና ይህንን ፀጋ የነፈገው ማንም ሰው የለም። ሁሉም የተጠራው ለመዳን ነው። እግዚአብሔር በአጠቃላይ የሰውን ልጆች በሙሉ ይድኑ ዘንድ ይወዳል፤ ይፈቅዳል። 1ኛ ጢሞ 2፥3-4

....በልጁ ሰው መሆን ያመነ ሁሉ መዳን የሚችል መሆኑ ግልፅ ነው። ዮሀ 3፥16-18

ስለዚህ መዳን በእግዚአብሔር ቸርነት ለሰው ሁሉ የተሰጠ ፀጋ እንጂ በቅድመ ምርጫና በቅድመ ውሳኔ (predestination) የሚያምኑ ሉተራውያንና ካልቪኒስቶች እንደሚሉት አስቀድመው ለተወሰኑ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ አይደለም። በተግባር ሲታይ የሚድኑት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ግን እያንዳንዱ በራሱ ስንፍና ምክኒያት ይቀርበታል እንጂ አስቀድሞ ለመዳን የማይችል ሆኖ ስለተወሰነበት አይደለም። እንደ አንዳንዶች አባባል የሚድኑት አስቀድመው የተመረጡት ብቻ ከሆኑ የአምላክ ሰው መሆኑ፣ መከራ መቀበሉ፣ ምስጢራትን መስጠቱ፣ ወንጌልን መስበኩ ወዘተ ሁሉ ከንቱ ድካም መሆኑ አይደለምን? መዳን በዚህ አለም ላሉ ሰዎች ሁሉ እንደ ተዘጋጀ ማዕድ በፊታቸው የቀረበ ነው።መጠቀምና አለመጠቀም ደግሞ የእያንዳንዱ ድርሻ ነው። ጌታችን ግን እያንዳንዱን " ወደ ሰርጉ ኑ በሏቸው" እያለ እየተጣራ ነው። ማቴ 22፤ እንዲሁም "ልትድን ትወዳለህን?" እያለ እየጠየቀ ነው።

#መድሎተ_ፅድቅ ቅፅ አንድ፣
ምዕራፍ ሶስት ገፅ 119- 120
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#ይቀጥላል....
#አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)
ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል

"ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)።
አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።
እንኳን ለጥዑመ ልሳን ፤ ካህነ ስብሐት ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

የቅዱስ ያሬድ በረከቱ ከሁላችን ጋር ትሁን

አሜን
እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአፅሙ፤
እምነ አድባራት ኩሎን ዘተለዓለት በስሙ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ፤
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ
ጻድቁ ተክለሃይማኖት ብዙ ህማም የተቀበለባት ቅዱስ አጽሙ ያረፈባት በስሙ ከታነጹት አድባራት ሁሉ ከፍ ያለች ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የቀደሳት ደብረ ሊባኖስ ታመሰግነዋለች።

እንኳን ለ660ኛው የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

አቡነ ተክለሃይማኖት ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ እቲሣ ተወለዱ፡፡
በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡
በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡
እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋዘአብ ዘንድ እየተማሩ
በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡
በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡
በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡
በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ።
በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡
በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡
ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡
በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡
ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡

አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡

የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡

አልዒልየ ቃለ
በፍልሰተ ዐፅሙ ዘገብረ ተክለሃይማኖት ኃይለ
እኂዛ በእዴሃ ኅብስተ ተዝካሩ ብሱለ
ሶበ ገሠሠት ብእሲት ዐይና ጽሉለ
እምነ ብርሃኑ አድምዓት ብርሃኑ ጽዱለ

ክብረ በዓላቶቻቸው፤
ኅዳር 24 ቀን: ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት
ታኅሣሥ 24 ቀን: ልደታቸው
ጥር 24 ቀን: ስባረ አጽማቸው
መጋቢት 24 ቀን: ጽንሠታቸው
ግንቦት 12 ቀን: ፍልሰተ አጽማቸው
ነሐሴ 24 ቀን: በዓለ እረፍት ናቸው፡፡

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ እምውሳጤ ገዳም ዔላመ
ወእምነ ዔላምኒ ደብረ ሊባኖስ ዳግመ
ተክለሃይማኖት ባህለ ከመ ወንጌላዊ ቀደመ
እመ ረከቡ ደቂቅከ በዓለም ሕማመ
በኀቤከ አባ ይርከቡ ሰላመ፡፡

በረከታቸው ይደርብን !
#የልቡና_ችሎት ፪ኛ ዕትም ወጥተዋል
አንብቡ፤አስነብቡ።
+ #ዝም_ብለን_የምንጠላው_ሰው +

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?
"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"
"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"
"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"
ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::
እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)

የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ