ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
22.4K subscribers
381 photos
97 videos
169 files
284 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤

6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡

10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
ከውዝግብ ባሻገር... ያዳነንን እናውቃለን!
***
1. የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ወልድ ከአብ ጋር ዘላለማዊ ህልውና ያለው የባሕርይ አምላክ ነው። የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ነው። በሁሉ ፍጹም የሆነ የአባቱ የባሕርዩ ነጸብራቅ ነው። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንዲት መለኮታዊ ሥልጣን እና ኃይል ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ነው፤ ከሆነው ያለ እርሱም የሆነ ምንም ምን የለም። ፈጣሪ አምላክ ነው። (ዮሐ. 1፥1-14፣ ዕብ. 1፣ 1ኛ ቆሮ. 8፥6)
2. ይህ ዘላለማዊ ህልውና ያለው እና ፍጥረት ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የአብ አካላዊ ቃል በዘመኑ ፍጻሜ እኛን ለማዳን ራሱን ዝቅ አድርጎ ሰው ሆነ። ሰው ሲሆን ግን አምላክነቱን እና መለኮታዊ ክብሩን አጥቶ አይደለም፤ አምላክነት የሚቀማ እና የሚለወጥ ነገር አይደለምና። ይልቁንስ አምላክነቱን ሳይለቅ ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ሰው ሆነ። ሰው በመሆኑም የትሕትና ነገሮች ተነገሩለት። በባሕርዩ ፍጡር የሆነ ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ስለሆነ አማናዊ ሰውነቱን ለማጠየቅ የባሕርይ አባቱን 'አምላኬ' አለው። ተራበ፤ ተጠማ፤ በላ፤ ጠጣ፤ መከራ ተቀበለ፤ ጸለየ፤ ተኛ፤ ወዘተ...። በዚህ በለበሰው ሥጋው ምክንያት ከኃጢአት በቀር ለሥጋ የሚገቡ ነገሮች ሁሉ ስለ እርሱ ተብለዋል። ይህን ያደረገውም ለእኛ ቤዛ እና መድኃኒት ይሆን ዘንድ በፈቃዱ እንጂ ግዴታ ወድቆበት አይደለም። በዚህም ፍቅሩን እንረዳለን እንጂ እንደ አይሁድ ውለታቢሶች ሆነን አምላካዊ ክብሩን ዝቅ አድርገን አናይም።(ዮሐ. 1፥1-14፣ ፊል. 2፥6-11፣ ዕብ. 4፥15)
3. ክርስቶስ ሰው ሆኖ እኛን ከማዳኑ የተነሣ ከዘላለማዊ አምላክነቱ እና ክብሩ ዝቅ ያለ አይደለም። ይልቁንም እርሱን (ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር) የምናመልክበት እና ለዘላለም የምናመሰግንበት እጅግ ከፍ ያለ ምክንያት ሰጠን እንጂ። ቀድሞ ስለፈጠረን እና ስለሚመግበን እናመሰግነው እና እናመልከው ነበር። አሁን ግን የእኛን ባሕርይ ለብሶ እና እስከሞት የሚደርስ መከራ ተቀብሎ በማዳኑ የማንከፍለውን ውለታ ውሎልናል፤ አምልኳችንን በማዳን ደስታ እና ምሥጋና ሞልቶታል።
4. እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው መሠረታዊ እና የመዳን ወንጌል ምሰሶዎች ናቸው። ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት (በአይሁድ ነገረ ሃይማኖታዊ ብያኔ - in the paradigm of Judaism) የተገለጸው በዚህ መልኩ ነው። ከዚያ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ከግሪክ የእውቀት ባሕል ጋር መስተጋብር ስታደርግ አስተምሮዋን በግሪክ ፍልስፍናዊ ብያኔ (Hellenistic paradigm) መግለጽ ነበረባት። ይህም ውስብስብ ነገሮችን ፈጠረ፤ ምሥጢረ ሥላሴን እና ነገረ ክርስቶስን በተወሳሰበ መንገድ መግለጽን አመጣ። ቤተ ክርስቲያን ለአሕዛብም ስለሆነች በግሪክ ፍልስፍና ተጽሕኖ ሥር የነበረውን ዓለም ለማምጣት ወደዚህ ተዋሥኦ መግባቷ ትክክል እና የግድ መሆን የነበረበት ነገር ነበር።
ግን ከላይ ያልናቸውን መሠረታዊ ነገረ ክርስቶሳዊ ጉዳዮች ተምሮ እስካመነ ድረስ ሁሉም ክርስቲያን ይህን ውስብስብ ተዋሥኦ የመመርመር እና የመረዳት ግዴታ የለበትም። (ይህ ቢሆንስ ክርስትና 'ተራው' ምእመን የማይረዳው የelite ሃይማኖት በሆነ ነበር)። ከሁሉም ክርስቲያን የሚጠበቀው መሠረተ እምነትን አውቆ በዚያ በተአምኖ መኖር ነው። መምህራን ሊይዙት እና ቤተ ክርስቲያንን ከስህተት ይጠብቁበት ዘንድ የሚማሩት ረቂቅ እና ሐተታዊ (speculative) ትምህርት አለ። ሁሉም ሄዶ ሄዶ የሚያርፈው ግን መሠረታዊው ትምህርት ላይ ነው። ሂደቱ simplicity ----> complexity -----> simplicity ነው።
ውስብስብ ጉዳዮችን ወደ ምእመናን አውርዶ በማኅበራዊ ሚዲያ መወዛገብ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል።
Bereket Azmeraw
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ኦርቶዶክስ መሆን በራሱ ኋላ ቀርነት እንደሆነ ተደርጎ ነው የተሰበከው"

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ክህነት_በሀዲስ_ኪዳን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ_.pdf
247.5 KB
ክህነት በሀዲስ ኪዳን

* የተለየ ክህነት
* አዲስ ክርስቲያን ካህን መሆን ይችላል?
* ሽማግሌ ወይስ ካህን ?

++++++++++~~~~~+++++++++

ኃጢአትን ይቅር የማለትን ሥልጣን ለራሱ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባ ሥልጣን ስለሆነ ይህን ለሌላ ለማንም አንሰጥም በማለት፣ እግዚአብሔርን ታላቅ በሆነ አክብሮት እናከብረዋለን ይላሉ። ሆኖም ግን እርሱ በግልጽ የተናገረውን ትእዛዙን እንደሚሽሩትና ለካህናት የሰጠውን ሥልጣን አንቀበልም እንደሚሉት እንደ እነርሱ አድርጎ የሚያቃልለው ሌላ ማንም የለም። ራሱ ጌታችን “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” ያላቸው ከሆነ፣ እግዚአብሔርን የሚያከብረው የእርሱን ትእዛዝ ተቀብሎ የሚታዘዘው ነው? ወይስ ትእዛዙን አልቀበልም የሚለው? .. " (ቅዱስ አምብሮስ በእንተ ንስሐ፣ መጽሐፍ 1፡6-7)

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Forwarded from Father Sergiy Baranov
A humble person takes everything calmly.
I will emphasize it at once, calmly does not mean indifferently.
Humility is not indifference.
An indifferent person is not God's person. He is like the one who was given a talent and buried it (see Mt. 25:14-30).
A humble person takes bad circumstances peacefully, and good situations do not make him euphoric, fanciful, or emotionally exultant.
#archpriestSergiyBaranov
Forwarded from A Monk In The World
Every hour expect your death and the coming of Christ, and say: "Now I will survive to work over my soul; in the evening I can die." When the evening comes, think, "will I not die in this very night? or death will suddenly come, my breath will suddenly stop, and as a flower falls I will fade. As the grass dries up, I shall die and then will be without a trace. God alone knows where I will then be, for He will judge each according to his deeds, saying 'I assign him to go there.'" Think then every day, and so not be concerned about anything, only about your own sins, and in this way your soul will enter into humility and lamentation and you will consider yourself as a frightful sinner and will ceaselessly gush forth founts of tears. but in necessities, in clothing, vessels, and things, observe simplicity, poverty, modesty, not because there is nothing to buy these things with, but because by this the soul is humbled and is not removed from God, and then everywhere it will be easy to find them.

- St. Paisios
በምሥጋና ዐረገ፤ ቤተ ክርስቲያኑንም ከፍ ከፍ አደረጋት።
***
እየታያቸው ከፍ ከፍ አለ፤ የባሕርይ ክብሩን የምታመለክት ደመና ተቀበለችው። በእርሱ ዕርገትም አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ሆና ከፍ ያለች እና በሰማያዊ ሥፍራ የተቀመጠች ሆነች።
የዚህ ዓለም ኃያላን የሚያናንቋት ሐረገ ወይን የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯ በምድር ቢሆን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ናቸው። ይህ ምን ይደንቅ!
አንዳንድ አገልጋዮቿ በሥርዓተ አምልኮዋ በዘፈቀደ እና በቸልተኝነት የምንመላለስባት ቤተ ክርስቲያን በመንቀጥቀጥ የሚያገለግሉ ሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት ያላት ናት። በላይ በበጉ ዙፋን የምትቀድስ ናት! ለዚህ ጸጋዋ አንክሮ ይገባል!
ይህ ሁሉ የሆነው ግን ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባቱ ያቀርበን ዘንድ በእኛ ሥጋ ከፍ ከፍ ብሎ በአብ ቀኝ በመቀመጡ የተሰጠን ጸጋ ነው።
***
"እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።"
***
(ሉቃ. 24፥50-53)
አንድ ወንድም ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደና “እድን ዘንድ የሚረዳኝን ምክር ምከረኝ" አለው፡፡ መቃርዮስም "ወደ መቃብር ቦታ ሒድና ሙታንን ስደባቸው" አለው፡፡ ያ ወንድምም ወደዚያ ሄዶ ሰድቧቸውና ድንጋይ ወርውሮባቸው ተመለሰና ይህንኑ ማድረጉን ነገረው፡፡ መቃርዮስም “ምን አሉህ?” ሲለው እርሱም “ምንም ነገር አላሉኝ" አለው። አረጋዊውም “ነገ ተመልሰህ ሒድና
አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ
ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን
አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡

++++++++~++++++


በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ
ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ
ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም
«ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ
ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው::

++++++++++++~~~~+++++++++

ነፍስህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ስትሰለች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና ሲያስጠላት፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሀት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደቅህ ተገንዘብ፤ ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት መጀመሪያው ይህ ነውና።

#ከበረሐውያን_አንደበት

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።”
(ያዕ. 4፥8)
***
የመልካም ነገር ጅማሮ ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰው? የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ ነው፦ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ያዕቆብ በመልእክቱ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፤" ብሎ ሲናገር መቅረብ ከሰው የሚጀምር ይመስል የእኛን ኃላፊነት ቀድሞ መናገሩ ለምንድር ነው? ብለን እንጠይቃለን። መልሱ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔርማ ሁሉን ፈጽሞ ትቀበለው ዘንድ እየጠበቀን ነው። ከሰው በኩል ግን መቀበል ይገባል። እንዴት ነው የምንቀበለው? በእምነት፣ በንስሐ፣ ከኃጢአት ጋር ተጋድሎ በማድረግ እና በክርስቶስ ትእዛዛት ለመኖር በመጣር ነው። እነዚህ ነገሮች የጸጋ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው እግዚአብሔር ለመቅረብ ጽኑ ፈቃዳችን በውስጥም በውጭም የምንገልጽባቸው ናቸው። እግዚአብሔር በእንዲህ ያለ ተግባር ውስጥ ሲያየን በእኛ ጥረት ሊገኝ የማይችለውን ዘላለማዊ ድኅነት ያጎናጽፈናል፤ የጸጋ አማልክት እስክንባል ደርሰን የእርሱ ጸጋ የሞላብን ያደርገናል። በእርሱ ዘንድ በባሕርዩ ያለ ቅድስናን ወደ እርሱ ቀርበን እናገኘው ዘንድ ይሰጠናል። ይህን ሁሉ የምናገኘው ከእኛ ብቃት ሳይሆን ከእሱ ጸጋ ነው፤ ነገር ግን በየጊዜው በምናደርገው የእምነት መታዘዝ እና ተጋድሎ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እና እርሱን ለመምሰል ያለነን በተግባር የተፈተነ ጽኑ ፈቃድ እንገልጣለን።
***
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ...
እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።”
***
(ያዕ. 4፥8-12)

Bereket Azmeraw
ቅዱስ ሚካኤል - መልአከ ምክሩ
***
በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ስለሚያደርገው የምክር ጉባኤ ተጽፏል። ይህ መለኮታዊ ምክር ( the devine council) እግዚአብሔር ስለሚያደርገው እና ስለፍርዱ ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ነው። ይህን የሚያደርገውም ከቅዱሳንም መርጦ ላከበራቸው ያለውን ክብር ያሳይ ዘንድ ከሥልጣኑ በጸጋ እያሳተፋቸው እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ምክር የሚጎድል ኖሮ እነርሱ ሊሞሉለት አይደለም።
የመጀመሪያው ይህን የተመረጡ ቅዱሳን ምክር የሚያሳይ ጥቅስ መዝ. 81/82 ነው፦ “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።"
ሌላኛው ደግሞ "እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፤" የሚለው ነው። (መዝ. 89፥6-7)
***
ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ምክሩ የሚባል የመላእክት አለቃ ሆኖ የዚህ መለኮታዊ ምክር አካል ስለሆነ ነው። 'ተሾመ' የሚለው ቃል ይህን መመረጥ ይገልጣል። ከሌሎች መላእክት በተለየ በዙፋን ላይ ተቀምጦ መሳሉም ለዚሁ ነው። ድንግል ማርያምም የዚህ ማኅበር አካል ነች። ቀድሞ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ሰሎሞን ለእናቱ ያለውን ክብር ይገልጥ በጎኑ ዙፋን አስቀምጦ ያማክራት ነበር። (1ኛ ነገ. 2፥19) ዳዊትም "ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ ተናግሮላታል። (መዝ. 44/45፥9)
ሐዋርያትም እንዲሁ ናቸው፤ ጌታ በ12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ላይ ሲፈርዱ በዙፋን እንደሚቀመጡ መናገሩ የመለኮታዊው ምክር አካላት እንዳደረጋቸው ያሳያልና። (ማቴ. 19፥28)
ይህንም ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ ተናግሮታል፦ “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” (ዳን. 7፥9) ነቢዩ 'ዙፋኖች' ያለው እግዚአብሔር ብዙ ዙፋኖች ኑረውት ሳይሆን የተመረጡ ቅዱሳን የሚሳተፉበትን ከእግዚአብሔር ፍርድ ሲወጣ ቀድመው የሚያውቁ እና በባለሟልነት የሚማልዱ የቅዱሳን ጉባኤ ክብራቸውን ለማመልከት ነው።
***
በዚህ ሁሉ ታላቁ መልአክ ሚካኤል አለ! ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል! ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ለጎስቋሎች ባሮችህ ለምንልን። አሜን።
#ሳታቋርጡ_ጸልዩ

"ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት  ነው፤   አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከሆነ ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።

    #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ