ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
17.3K subscribers
338 photos
84 videos
151 files
221 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤

ሰኞ

የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡

ማክሰኞ

ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡

ረቡዕ

ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡
ኀሙስ

ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡

ዐርብ

የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡

ቀዳሚት ሰንበት

በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡

እሑድ ሰንበት

በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡

ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡

እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡

ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
በቅርብ ቀን በዐበይት ወቅታዊ ጉዳዮች ይጠብቁን!

በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ብቻ!

* ከግንቦት እስከ ግንቦት

* የቅድስት ቤ/ክ ማእከላዊነት ላይ የተደቀኑ ፈተናዎች

* የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና መጠበቅ

* የመንግሥትና የሃይማኖት ድንበር

* ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት ለምን?

* ዛሬ ምእመናን ከአባቶች ምን ይጠብቃሉ?

* መልሶ ማልማትና የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት
ልደታ ለማርያም

በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡

ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡

ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና።

የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡

ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት
ወንድ ልጅ በገጽ፣ ሴት ልጅ በሕይወት ክርስቶስን ይመስሉታል። ወንድ በራስነቱ ሴት ልጅ ይክበር ይመስገንና ወልድ በፈቃዱ ለአብ እንደ ታዘዘ ለባሏ በመታዘዝ ክርስቶስን ትመስለዋለች። ወንድ እንደ ክርስቶስ ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ሚስቱን እንደሚወዳት እርሷም ለእርሱ ለውዷ በሕይወትና በሞት መካከል ሆና ጽኑ ሕማምን ተቀብላ የፍቅራቸው ፍሬ የሆነውን ልጅ በእቅፉ ታኖርለታለች። እርሱ ጌታችን ጽኑ ሕማምን በመቀበል ሕያው በሆነ ሞቱ እኛን ልጆቹን እንደወለደን።(ዮሐ 16:21)

Shimelis Mergia
ሁሉም_ክርስቲያን_ካህን_ነውን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
323.4 KB
ሁሉም ክርስቲያን ካህን ነውን?

* የ1ኛ ጴጥሮስ 2፥9 እንዲሁም የዮሀንስ ራዕይ 1፥6 ማብራሪያ እና ከ ዘጸአት 19፥6 አንፃር
* ክህነትን የተዳፈሩ ሰዎች
* ካህናት ትሆኑ ዘንድ ምን ማለት ነው?
* የክርስቲያኖች ሁሉ አጠቃላይ ክህነት

++++ ~~ +++++

እዚህ ላይ ጳውሎስ “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ” ሲል አሳሰበን። ሰውነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበው እንዴት ተደርጎ ነው? ብሎ የሚጠይቅ ይኖር ይሆናል። ዓይን ክፉ ነገርን አይመልከት፣ እንዲህ ካደረግህ ዓይንህ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል ማለት ነው፤ እጅህ ሕገ ወጥ የሆነ ተግባርን አያድርግ፣ ይህ ከሆነ የተቃጠለ መሥዋዕት ሆኗል ማለት ነው። ወይም ይህም ብቻውን በቂ አይደለም፣ በዚህ ላይ መልካም ሥራን መሥራትም ይገባናል እንጂ። እጅ ምጽዋትን ይስጥ፣ አንደበት የሚረግሙትን ይመርቅ፣ ጆሮም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት በመስማት ደስ ይሰኝ። መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነገር አንዳችም ነውርና ነቀፋ ያለው ሆኖ ሊቀርብ አይችልምና። መሥዋዕት የሌሎች ተግባራት ሁሉ ቀዳምያት ነውና። ስለዚህም ከእጃችንም፣ ከእግራችንም፣ ከአንደበታችንም፣ ከሌላውም አካላችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀዳምያትን እናቅርብ። ይህ ዓይነቱ መሥዋዕት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ጸሎተ ፍትሐት.pdf
172.3 KB
ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

👉እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለ ሆነ

👉የቤተ ክርስቲያን ባሕርይዋና ማንነቷ የሚገለጥበት ስለሆነ

👉ከዕረፍታቸው በኋላም ሕያዋንና አዋቂዎች ስለ ሆኑ

👉አስተምህሯችን፣ እምነታችን፣ ተስፋችን፣ ... የሚገለጥበት ስለ ሆነ

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
Forwarded from Father Sergiy Baranov
One of the main characteristics of love is self-sacrifice. If a person is ready to die for his beloved one, then he loves. If he is not ready to die, then this is something else. For a loving person, such sacrifice is not burdensome, but sweet. A loving person is ready to suffer voluntarily in order to please his beloved one and is even happy to suffer. After all, as far as gifts are concerned, it is more pleasant to give them then to receive. Thus, the point of human happiness is in love. However, people have committed some deeds that are contrary to love and let egotism into their hearts. I say it again, love is one's readiness to die for the beloved one, while egotism is readiness to kill the beloved one for one's own sake. This was the reason why paradise was lost. Egotism is the reason why we all suffer here on earth. God does not punish us. We ourselves came to this!
#archpriestSergiyBaranov
ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል

"ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)።
አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።
እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲትዋን ምዕራፍ ወይም ከሌላው የቅዱሳት መጻህፍት ክፍል ውስጥ ጥቂት በቃልህ ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም።
የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም። ከመንፈሳዊ ነገሮች አንፃር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያቢሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን ከእሳት በላይ ኀያላን ናችሁ። እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያቢሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ዜማዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ ከእናንተ መካከል እነዚህን የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሟቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል።

ነገር ግን"ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት?" ተብላችሁ ስትጠየቁ የምትመልሱትስ መልስ ምን የሚል ነው? "እኔ ከመነኮሳት አንዱ አይደለሁም። ሚስት አለቺኝ፣ልጆችም አሉኝ፣የቤተሰብ መሪ ነኝ" የሚል ምክንያት ታቀርባላችሁ። ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ከመነኮሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ እናንተ ኾናችሁ ሳለ ብዙዎች እንዲጠፉ ያደረገው "ቅዱሳት መፃህፍትን ማንበብ ለመነኮሳት ብቻ ነው" የሚለው አመለካከታችሁ ነው። ይበልጥ ብዙ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው በማእከለ ዓለም የሚኖሩትና ዕለት ዕለትም መንፈሳዊ ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና። ስለዚህም ከለማንበባችሁም በላይ" የእኛ ማንበብ ትረፍ ነገር ነው" ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው። ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ "ዝንቱ ኵሉ ተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ - ይህም ኹሉ እኛን ሊገስጸን ተፃፈ"(1ኛ ቆሮ 10:11) ያለውን አላዳመጣችሁምን?

ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
#ግንቦት_11

#ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ

ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።

ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።

ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።

ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።

በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።

ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።

ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።

ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።

የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።

ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።

ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
ከበረሐውያን አንደበት.pdf
16.4 MB
ከበረሐውያን ሕይወትና አንደበት

ጥበብ ወምክር ዘአበው ቀደምት

++++++~+++++

#ጸሎት_ከበረሓውያን_አበው


ሁሉም ነገር ለፈቃድህ የሚገዛልህና የሚታዘዝልህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ያደረግሁትን ነገር ሁሉ ይቅር በለኝ፣ ኃጢአተኛ
የሆንኩትን እኔን ከአሁን በኋላ እንዳልበድል አድርገኝ፡፡ ጌታ ሆይ፣ የማይገባኝ መሆኔን
ባውቅም ከኃጢአቴ ሁሉ ልታነጻኝ ትችላለህ። ጌታ ሆይ፣ ሰው ፊትን እንደሚያይ፣ አንተ ግን ልብን እንደምታይ አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መንፈስህን ወደ ውስጤ ጥልቅ ላክልኝ፣ ነፍሴንና ሥጋዬን ይኖርበትና ገንዘቡ ያደርገው ዘንድ፡፡ ያለ አንተ ልድን አልችልም፤ በምትጠብቀኝ በአንተ ግን ማዳንህን እናፍቃለሁ፡፡ እናም አሁን አንተን ማዳንህን እለምንሃለሁ፡፡ የአንተን ጥበብ እሻለሁ፣ የሚረዳኝንና የሚጠብቀኝን ታላቁን ደግነትህንና ቸርነትህን እማጸናለሁ፡፡ ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፡፡

+ አሜን +


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ