በኦሪቱ እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ የሚናረው ነገር ነበር፡፡ እርሱም «አንተ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ተጣበቅ የሚለው ነበር።እኛም ምንም ይሁን ምን ከእግዚአብሔር ጋር እንጣበቅ፡፡ ሐዋርያት በባሕር ላይ ስንጓዝ የገጠማቸውን ፈተና ያለፉት ከታንኳው በመውጣትና ከክርስቶስ በመለየት አይደለም፡፡ እዚያው በማዕበል ከሚጨነቀው ታንኳ ውስጥ ሆነው «ጌታ ሆይ አድነን ጠፋን» እያሉ ማዕበሉን በቃለ ኃይሉ በቅጽበት ጸጥ ሊያደርግ ወደሚችለው ወደ አምላካቸው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለዩ እንጂ፡፡ እርሱም ልመናውን ሰምቶ የነፋሱንና የባሐሩን ማዕበል በአምላክነቱ ገሠጸው ወዲያውኑም በቅጽበት ታላቅ ጸጥታ ሆነ፡፡ጭንቀታቸው ተወገደ፡፡ በፈተና ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን መውጣት ከክርስቶስ መለየት ነው፥ በፈተናው ድል መሆንና መሸነፍ ነው፡፡ ጌታችን «እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል» ያለው ለዚህ ነው፡፡ ማቴ ፳ ፬÷፲ ፫። እስከመጨረሻ መጽናት አስፈላጊ መሆኑን አስቀድሞ የነገረን ለፈተናዎች ራሳችንን እንድናዘጋጅ ነውና፡፡ የሌላውም ኃጢአት ለእኛ ኃጢአት ምክንያት ሊሆነን አይችልም፡፡ የሌላው ሰው ስንፍና ለእኛ ስንፍና ምክንያት ወይም ሽፋን ሊሆነን፣ በፍርድ ቀንም አስተያየት ሊያስደርግልን አይችልም፡፡ በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከኖኅ በስተቀር ሁሉም ኃጢአተኞች ሆነው ቢገኙ፤ ሁሉም በጥፋት ውኃ ጠፉ እንጂ ስለ ብዛታቸው ወይም ሁሉም ኃጢአተኞች በመሆናቸው የተደረገላቸው አስተያየት አልነበረም፡፡ ዛሬም ወደፊትም የሚሆነው ይኸው ነው፡፡ ስለዚህ በትንሹ የዚህ ዓለም የሕይወታችን ዘመን ፈተናዎችን ተቋቁመን ከክርስቶስ ጋር በቤተ ክርስቲያን ጸንተን ኖረን «በትንሹ ታምናችኋልና በብዙ እሾማችኋለሁ ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ»ለመባል ያብቃን፡፡
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (...typing)
መፃጒዕ
አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መፃጒዕ› ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ያለ ነው፡፡ መፃጒዕ ደዌ የጸናበት በሽተኛ፣ ሕመምተኛ ማለት ነው፡፡ መፃጒዕ ለ፴፰ ዓመት በአልጋው ላይ ሆኖ ምሕረትን ሲጠባበቅ የኖረ ሰው ነው። ስፍራዋም “ቤተ ሳይዳ” ትባላለች።ቤተ ሣህል (የምሕረት ቤት) ማለት ነው፤ መጠመቂያዋም በሰሎሞን ቤተ መቅደስ አጠገብ የምትገኝ ናት፡፡ (ዘሌ.፱፥፪) “ቤተ ሳይዳ” ዘይሁዳና “ቤተ ሳይዳ” ዘገሊላ የሚባሉ እንዳሉ በግልጽ በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጿል። “ወቦ ውስተ ኢየሩሳሌም ምጥማቃት ዘጵሩጳጥቄ ቅልንብትራ ዘውእቱ ቀላየ አባግዕ ብሂል ወይቤልዋ ስማ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወባቲ ኃምስቱ ሕዋራት” …በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት” ብሎ ሲገልጽ ነው። (ዮሐ.፭፥፪)

ቤተ ሳይዳ ዘኢየሩሳሌም ባለ አምስት በር፣ እርከን (መመላለሻ)፣ አምስት ዓይነት ድውያን ፈውስን ለማግኘት ጥምቀቱን ሲጠባበቁ የሚኖሩባት ናት። ውኃው የቤተ አይሁድ ምሳሌ፣ አምስት መመላለሻ የሕግጋተ ኦሪት እና የአምስቱ መጻሕፍተ ሙሴ ምሳሌ በእነዚያ ተጠብቀው ለመኖራቸው ምሳሌ ነው። ቀድሞ የገባባት አንዱ እንዲድን፣ እነርሱም አንድነት ቤተ እስራኤል ተሰኝተው ለመኖራቸው ምሳሌ ነው። አንድም አምስቱ እርከን (መመላለሻ) የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር በዚያ ሊያምኑ ያሉ ተስፈኞችና ያመኑባትም ልጅነትን ያገኙባታልና። አምስቱ ዓይነት ድውያንም የአምስቱ ጾታ ምእመናን ከእነ ፈተናቸው ምሳሌ ነው፡፡ እነርሱም አእሩግ በፍቅረ ነዋይ፣ ወራዙት በዝሙት፣ አንስት በትውዝፍት (በምንዝር ጌጥ)፣ ካህናት በትዕቢት አእምሯችን ረቂቅ መዓረጋችን ምጡቅ እያሉ፣ መነኮሳት በስስት ምግብን በፈለጉት ጊዜ ባያገኙት ይልቁንም በአት እየፈቱ በከንቱ የመፈተናቸው ምሳሌ ሆኖ ይነገራል።
መልአከ እግዚአብሔር ወርዶ ውኃውን ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ የሚነጻባት፣ ነገር ግን በዕለቱ ከአንድ ሕመምተኛ በቀር ለሌላው ፈውስ የማይደገምባት ቦታ ናት። ሐተታው የመጠመቂያ ውኀው የማየ ጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ውኃውን ያናውጥ (ይባርክ) የነበረው መልአክ የቀሳውስት (ካህናት) “ለቀድሶተ ማየ ጥምቀት” የመውረዳቸው ምሳሌ ነው፤ ፈውሱም የሚከናወነው በዕለተ ቀዳሚት ሲሆን የሚፈወሰው አንድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ የሚድነው አንድ ታማሚ ብቻ መሆኑ የአባቶቻቸው ምሕረት አለመቅረቱን ሲያሳይ፣ አለመደገሙ ደግሞ ፍጹም ድኅነት እንዳልነበረ ያሳያል፡፡
ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የኖረ መፃጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቦ ያንን በሽተኛ “ትፈቅድኑ ትሕየው? … ባድንህ ፈቃድህ ነውን?” አለው። ማእምረ ኅቡዓት ክርስቶስ፣” አዎን፥ እንዲለው እያወቀ”፤ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ “የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም” ብሎ የመሰከረለት ጌታችን ፈውስን በመጠባበቅ ከመዳን ውጪ ሌላ ዓላማ ያልነበረውን ይህን ሰው አይቶ ፈቃዱን እያወቀ ግን ፍቀድልኝና ላድንህ አለው። (ዕብ.፬፥፲፪) “ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው?“ እንዲል፤ (መክ.፮፥፲፪) የሚያስፈልገንን ሳንነግረው የሚያውቅ የሚሰጠንም ከእርሱ ከፈጣሪው ውጪ በእውነት ማን አለ?
መፃጉዕ በኋላ የሚክድ ነውና “ሳልፈቅድለት ነው ያዳነኝና አልጋ ያሸከመኝ” እንዳይል፣ በዕለተ ዓርብ የሚከስበትን ሲያሳጣውና ለኋላ ጥፋቱ የገዛ ኅሊናው እንዲቀጣው ፈቃዱን ጠየቀው። “ሰው የሌለኝ ሆኖ እንጂ ያንንማ ማን ይጠላል” በሚል ጉጉቱን ከወዳጅ አልባነቱ ጋር ድኅነትን ፈቅዶ ገለጠ። እስከ ውኃው መናወጥ ሳያቆየው “ተንሥእ ንሣእ ዓራተከ ወሑር …፤ ተነሥና አልጋህን አንሥተህ ሂድ” አለው፤ ወዲያው አፈፍ ብሎ በፍጥነት ያን ሁሉ ዘመን የተሸከመች አልጋ ተሸክሟት ሄደ።
ጌታችን መፃጉዕን ‹‹ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ያለው፦
• አንደኛው ቅዱስ ኤስድሮስ እንዳለው አልጋው ጠንካራ የብረት አልጋ ነበረና ጽንዓ ተአምራቱን ለማሳየት ነው፡፡
• ሁለተኛው ‹‹ታዲያ ቢያድነኝ በከንቱ መች ሆነና የገዛ አልጋዬን ትቼለት የመጣሁ ለመዳኔ ዋጋ የከፈልኩበት አይደለምን?›› እንዳይል “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎታል።
ያለ ተረፈ ደዌ አንሥቶት “ያለህን ይዘህ ሂድ፤ እኔ ከአንተ አንዳች አልሻም” ባሰኘ ቃል ሸኝቶታል። ታዲያ ይህ ምስኪን መፃጒዕ “ሰው የለኝም” ብሎ የደረሰለትን ረሳ፤ ማን እንደሆነ እንኳን አላወቀውም። ወንጌላዊውም “ዘሐይወ ኢያእመረ ዘአሕየዎ …፤የዳነው ያዳነውን አላወቀውም” ይለዋል። ( ዮሐ.፭፥፲፫) ይህን ሁሉ ያደረገው አምላክ ተዘነጋ። ዛሬም ከደዌው፣ ከማጣቱ፣ ከችግሩ፣ ከሥጋ ኑሮ ጉድለቱ እንደ መፃጒዕ አምላኩን ያልረሳ ማነው? ተአምራቱን አይቶ፣ ቃሉን ሰምቶ አምላኩን ያስታወሰስ ማነው? ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠስ ማን ነው?” (ኤር. ፳፫፥፲፰)። እኛም ብንሆን ከአዳም በደል ነጻ ያደረገንን አምላክ ውለታ ዘንግተን የምናፌዝ ሁላችንንም ወደ ልባችን እንድንመለስ ነቢዩ እንዲህ ሲል ይመክረናል “እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ፡፡” (ኢሳ.፳፰፥፳፪ )
መፃጉዕ ያዳነው ማን እንደሆነ ሲጠየቅ እንኳን አላወቀም። ወንጌላዊውም “የዳነው ያዳነውን አላወቀውም” ብሎ ገልጾታል። (ዮሐ.፭፥፲፫) በምኩራብ አግኝቶት ያዳነውን እንዳወቀውም ሄዶ ለአይሁድ “ያዳነኝ እርሱ ጌታ ኢየሱስ ነው” ብሎ ነገራቸው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቤተ መቅደስ ሳለ ያን ያዳነውን ሰው አገኘውና “ዑቅ ኢትአብስ ዳግመ እንከ ከመ ዘየአኪ ኢይርከብከ፤ ከዚህ የከፋ “ስለ ደዌ ሥጋ ፈንታ ደዌ ነፍስ” እንዳያገኝህ ሁለተኛ እንዳትበድል” (ቁ.፲፬) ያለውን ዘንግቶ ደዌ ዘኃጢአትን ጠርቶ ተወዳጃት፤ በዕለተ ዓርብ የጌታውን ጉንጮች የጸፉች እጁም ደርቃ
ሰላ
ቀርታለች።ዛሬም ቢሆን እንደ መፃጉዕ ሰዎች በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ፣ ሰውነታቸው የሰለለ፣ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ፣ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን በጠበል ቦታ፣ በገዳማት እና በአድባራት አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መፃጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ።
ስለዚህ ይህ ሳምንት ጌታችን ድውያንን ስለመፈወሱ የሚነገርበትና እኛም ባለን ዓቅም በነፍስ በሥጋ የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንዳለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን ማብላት፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ፣ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ምግባራት ናቸው፡፡
በዚህ ዕለት የእግዚአብሔር አምላካችን ፈዋሽነትና አዳኝነት እንዲሁም ታዳጊነትና የወደቁትን የማይረሳ እውነተኛ መድኃኒት መሆኑ የሚዘከርበትና ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ቅዱስ ዳዊትም "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፣ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ፣ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፤ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል፣ እኔም አቤቱ ማረኝ እልሃለሁ” በማለት የእግዚአብሔርን አዳኝነት በዝማሬው አረጋግጧል።
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፣ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና” ሲል ሲቀኝ፣ (መዝ.፸፪፥፲፪) ጻድቁ ኢዮብም እንዲሁ “ረዳት (ኃይል) የሌለውን ምንኛ ረዳኸው” በማለት የእግዚአብሔርን አዳኝነት መስክሯል፡፡ (ኢዮ.፳፮፥፪) ስለዚህ ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ ወገን፣ ረዳት የለኝም በማለት ተስፋ የቆረጥን ሰዎች እግዚአብሔር ከሰውም፣ ከሥልጣንም፣ ከገንዘብም በላይ ነውና እርሱን ተስፋ አድርገን ሁል ጊዜ በስሙ መጽናናት እና የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ መጣል እንደሚገባን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አቤቱ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ሐሤትም ያድርጉ፡፡ ሁል ጊዜ ማዳንህን የሚወዱ ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ” እንዳለው ሁል ጊዜም በአምላካችን እግዚአብሔር ደስተኞች
ጌታችን በተግባር እንዳስተማረን መንፈሳዊ ሕይወት በትንሹ ተጀምሮ ከዚያ ቀስ በቀስ እያደገና እየጠነከረ የሚሄድ እንጂ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ በቅጽበት ፍጹም የሚሆንበት አይደለም፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከተለያየ ሁኔታና ሕይወት ከጠራቸው በኋላ ወዲያውኑ ዕለቱን ወደ ፍፁምነት ደረጃ አልደረሱም፡፡ ብዙ ድክመቶች ነበሩቸው። እርሱ ስለ ሰማያዊ መንግስት ሲነግራቸው ስለ ምድራዊ መንግስት የሚጠይቁበት ጊዜ ነበር።የሚነገራቸውን ባለማስተዋላቸው፣ ለእርሱ የቀኑና የተቆረቆሩ ምስሎአቸው እሳት ከሰማይ ወርዶ እርሱን ያልተቀበሉትን ሰዎች እንዲያጠፋቸው በመጠየቃቸው፣ ስለ ሞቱና መከራው ሲነግራቸው “አትሙትብን” በማለታቸው ÷ ስለ እምነት ማነስ ሁሉ ብዙ ጊዜ ተገሥጸዋል፡፡ እነርሱም ከዚህ የተነሳ “ጌታ ሆይ እምነት ጨምርልን” እስከማለት ደርሰዋል ። ጌታችንም ብዙ ጊዜ ይገስጻቸውና ስሕተታቸውን እንዲያስተካክሉ በአባትነቱ ይመክራቸው ነበር፤ ሦስት ዓመት ከእርሱ ጋር ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ በቃልም በተግባርም ተምረው እንኳ ፍጹማን መሆን አልቻሉም ነበር። ጌታችን በሰጣቸው ተስፋ መሰረት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ነበር ፍጹማን የሆኑት። እንግዲህ ሐዋርያት በእንዲህ ዓይነት ሂደትና ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉ ከሆነ ወደ ፍጹምነት ደረጃ መድረስ በአንድ በኩል በራስ ጥረት በዋናነትም በእግዚአብሔር ቸርነት በሂደትና ቀስ በቀስ እንጂ በአንድ ጊዜ በቅጽበት የሚሆን ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ በክርስትና የሕይወት ጉዞ ውስጥ የሕይወትን አካሄድ÷ ስልትና ዘዴ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የጉዞውን ርዝመትና ጠባይ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ ያሉና ሊገጥሙ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ ሳያውቁ የሚጀመር ጉዞ መሰናሎች ሲገጥሙት የመውደቅ ዕድሉ የሠፋ ነው፡፡ ከዚህም አንዱ የአካሄድን ፍጥነት መወሰን ነው፡፡ አንዳንዶች ክርስትና በተወሰነ ጊዜ ተሰርቶ ማለቅ እንዳለበት የሥራ ዕቅድ (ፕሮጀክት) ወዲያውኑ እንደ ጀመሩ አካሄዳቸው የጥድፊያና የችኮላ ይሆናል፡፡ ሰውነቱ ጾምን በሚገባ ሳይለማመድ እስከ ማታ ድረስ በመጾም ይጀምራል። «የክርስቶስ ክቡር ደም በፈሰሰባት ምድር በጫማ አልሄድም» እስከ ማለት ይደርሳል፡፡ ይህን ዓለም በሙሉ የመጸየፍና የምናኔ ነገር ብቻ ይታሰበዋል። ሌሎች ሰዎች ኀጢአተኞችና ደካሞች ሆነው ይታዩታል። አንዳንዶች ሥራቸውን እስከ መተው ደርሰው በየገዳማት መዞርን ብቻ ስራዬ ብለው ይይዛሉ:፡ በአጠቃላይ ነገሮችን ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርገው ይይዟቸዋል፡፡ በየቦታው በመዞር ብቻ በረከትና ጽድቅ የሚገኝ ይመስለዋል። ከትምህርት ቤት ወደ ትምህርት ቤት እየተዘዋወረ መምህር ሲያማርጥና የተመቸ ሁኔታን ሲፈልግ አንድ ቁም ነገር ሳይማር ጊዜውን የሚያጠፋውን ተማሪ አበዉ ’እግረ ተማሪ’ ይሉታል፡፡ዛፍ እንኳን ፍሬ የሚያፈራው ከተተከለበት ቦታ ሲኖር ነው:: ነገር ግን በየጊዜው እየተነቀለ የሚተከል ከሆነ ወይ ይደርቃል፤ ባይደርቅ እንኳ ፍሬ ማፍራት አይችልም።ጊዜውን በዙረት ብቻ የሚጨርስ ሰውም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም፡፡ ቢያፈራም እንኳ በአንድ ቀን በቅላ በአንድ ቀን አብባ በአንድ ቀን ታፈራለች እንደምትባለው ዕፀ ከንቱ÷ ፍሬው ምትሐታዊ ይሆንና ከመታየቱ ወዲያውኑ ይረግፋል። በእንዲህ ያለ ሕይወት የሚጓዙ ሰዎች የማይመች አካሄድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ይህ ዓይነት ሕይወት ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል አስቸጋሪ አካሄድ ነው፡፡
....................
ክርስትና የክርስቶስ ፍቅር እንደ ተረዳውና እንዳከበረው መጠን ከውስጥ በሚመነጭ ፍቅር የሚመሠረት እንጂ በተጽዕኖ ከውጭ የሚጫን ሸክም አይደለም። ሐዋርያው «የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል» አለ እንጂ ሌላ ማንም ያስገድደናል አላለም። በሰዎች ላይ ከባድና እስቸጋሪ ሸክም የሚጭኑ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን ጌታችን እንዲህ በማለት ገሥጾአቸዋል « ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይወዱም»:: ማቴ 23÷4። እንዲህ በሌሎች ላይ መጫን ገድልና ትሩፋት መስሎ የሚታያቸው ሰዎች ሁሉን ከሚያውቅና ሁሉን በጊዜው ከሚያደርግ ጌታ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሐዋርያትን የግድ፥ እንዲጸሙ ለማደረግ ወደ ጌታችን ቀርበው: « እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጸሙት ስለ ምንድነው?» እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ለጾም ከራሱ ከባለቤቱ የበለጠ ተቆርቋሪዎች በመምሰል በሌሎች ላይ ለመወሰን ቀረቡ፡፡ ማቴ.9÷14። አባቶቻችን ሐዋርያትንም እንጀራ ሲበሉ፡ “እጃቸውን አይታጠቡም በሰንበት ቀን እሸት ቆርጠው በሉ» ወዘተርፈ እያሉ ይከሷቸውና ይነቅፏቸው ነበር:: ጌታችን ከሰው የሚፈልገው ግን ከባድና አስጨናቂ የሆኑ ነገሮችን አይደለም፤ « እናንተ ደካሞች፥ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፉችኀለሁ… ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና» በማለት የእርሱ ቀንበር ቀላልና የማይጎረብጥ መሆኑን ነገረን። የተለያዩ ሰዎች መጥተው ምን አናድርግ?» እያሉ በጠየቁት ጊዜ ዮሐንስ መጥምቅ የነገራቸዉ በዚያው በአቅማቸው ሊሠሩት የሚችሉትን እንጂ ከባድ የሆኑ ነገሮችን አላዘዛቸውም ሉቃ.3፥10-14:: ምክንያቱም ገና በመንፈስ ያላደጉ ስለነበሩ ከበድ ያለ ነገር ቢነግራቸው አይችሉትምና፡፡ ጌታችንም፦ «ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና በማለት ለሁሉም በሚቻልና በማይከብድ ሁኔታ አዘዘ ማቴ.7÷1። ሌሎች ለእኛ ሊያደርጉልን የምንወደውን ነገር እኛም ያንን ለሌሎች ማድረግ እንችላለንና። ሌሎች እንዲያደርጉልን ከምንፈልገው ነገር እኛ ለሌሎች ማድረግ የማንችለው ካለ ከሌሎች የምንፈልገው እኛ የማንችለውን ነው ማለት ነው። እኛ የማንችለውን ከሌሎች መጠበቅ ደግሞ ተገቢ አይደለም፡ እንዲሁም ራሳችን ከሌሎች የምንፈልገውን ጠንቅቀን እንደ ምናውቅ ሁሉ ሌሎች ከእኛ የሚፈልጉትንም በእኛው ፍላጎት አንጻር በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡ ስለዚህ ይህን ማወቅም ሆነ መፈጸም ከባድ አይደለም።
...................
ወደ ክርስትና የገቡት አይሁዶች እንኳ ኦሪታዊ ልማዳቸው አልተዋቸው ብሎ ከቤተ አሕዛብ እያመኑ ወደ ክርስትና የሚመጡትን አማንያን «ያንኑ የኦሪቱን ሕግና የሙሴን ትእዛዛት በሙሉ ሊጠብቁ ይገባል» እያሉ ስላስቸገሩ በዚህ ምክንያት የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተደርጓል። በዚህ ጉባኤም ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ «እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ?» በማለት የጉባኤ መግቢያ ሐሳብ ተናገረ። ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት ከተወያዩ በኋላ፦ ለጣዖት ከተሰዋ ከደምም ፥ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና ክዚህ ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ» ሲሉ በአንድነት ወሰኑ። የሐዋ. 15፥29።
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
#በየጥቂቱ_ማደግ
ሐመር መስከረም/ጥቅምት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም

Forwarded from አረቦን
ሕመም ፣ መከራና ስቃይ በዚህ ዓለም ውስጥ እስካለን ድረስ የማንገላገላቸው እውነታዎች ናቸው። እስከምንሞት ድረስ በልዩ ልዩ ስቃዮች ውስጥ እናልፋለን። ክርስቲያኖች ይህንን እንዴት ልንረዳውና በምን መልኩ ልንኖረው ይገባል የሚለውን ከዲያቆን ዶክተር አቤል ኃይሉ ጋር ተወያይተናል። አቤል በቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ የትምህርት እርከኖች ከማለፉ ባሻገር የህጻናት ካንሰር ስፔሺያሊስት ነው። በዚህም ምክንያት የተማረውንና ያነበበውን ብቻ ሳይሆን እለት እለት በስራ ገበታው የሚያጋጥሙት የተለያዩ ሁኔታዎች የልምድ እውቀት የሚጨምሩ ናቸውና ለዚህ ውይይት ተገቢው ሰው ያደርጉታል። ቤተክርስቲያናችን ደዌንና ድውያንን በሚወክል መልኩ ከአቢይ ጾም ሳምንቶቿ ውስጥ አንዱን መጻጉዕ ብላ ሰይማዋለች። ይህ ሳምንት ህመምንና ስቃይን ለመወያየት እጅግ ተገቢ ሳምንት ነው ብለን በማመናችን ይህን ዘለግ ያለ ውይይት አድርገናል። እንድትከታተሉን እንጋብዛለን። https://youtu.be/_RJvWe2E2hU
YouTube
ሕመም ፣ ስቃይና ክርስቲያናዊ ኑሮ - Illness, suffering and Christian life | ኤማሁስ ፖድካስት Ep13
ከዚህ ቀደም በኤማሁስ የተዘጋጁ መደመጥ ያለባቸው መርሐግብራት።
መጥምቁ ዮሐንስ - https://youtu.be/bYcwvyga3CA?si=izBWN8l7umktxkfb
https://youtu.be/ooKoq0Kc9hk?si=z5031eSfxYY87HAY
ደጉ ሳምራዊ - https://youtu.be/1YRXDDfNkcA?si=mbqIlUo3h_wgzTvE
ሑረ ወመሀሩ - የቤተክርስቲያን ተልእኮ ከየት ወዴት
https://…

Forwarded from Father Sergiy Baranov
Look, what kind of God we have!
He comes to meet His prodigal son who has lost everything, not only his inheritance, but also his conscience and human appearance. However, all of a sudden, his Father goes out to meet him.
He doesn't just go, but runs.
#archpriestSergiyBaranov

Forwarded from ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC
የዕለቱን ወንጌል እናንብብ!
መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም
የማቴዎስ ወንጌል ም 26 ቁ 1 - 7
መልካም ዕለተ ሠሉስ !
#ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል
#tewahedomediacenter #tuesday
መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም
የማቴዎስ ወንጌል ም 26 ቁ 1 - 7
መልካም ዕለተ ሠሉስ !
#ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል
#tewahedomediacenter #tuesday
Forwarded from Father Sergiy Baranov
We all have death ahead of us and no one promised it would be an easy one.
Even if we do not make it till the times of antichrist, look, here is a person dying in horrible pain from cancer. For him, this is already the day of doom. It is already dreadful and painful.
The end will come all the same.
#archpriestSergiyBsranov