ልሳን ዘየካቲት
የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሪፎርም እና የKPI/ Key Performance Indicator/ የአፈጻጸም ቁልፍ መለኪያ ወይም የሥራ አፈጻጸም ዋና መለኪያ ዕቅድ ውይይትና ማጽደቅ ተካሄደ
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
ነሐሴ 12/2019 ዓ.ም
በየካቲት 12 ሆስፒታል የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ማዕከል የኳሊቲ ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ግዛው እና የሚመለከታቸው የየክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በኬዝ ቲሙ ሥር የሚገኙ የሪፎርም ፣ የኢንፌክሽን መከላከልና ቁጥጥር (IPC)፣ የታካሚ ደኅንነት /Patient Safety/, CBHI/ Community Based Health Insurance ማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን፣
Physician Audit/ የሕክምና አገልግሎት ቁጥጥር / ግምገማ/ ፣ Health Literacy/የጤና ግንዛቤ ማስጨበጪያ/ እና Call Center/የጥሪ ማዕከል/ ክፍሎችን ያካተተ የሪፎርም እና የKPI ዕቅድ ዝርዝር ውይይት ተካሄደ
በውይይቱም የእያንዳንዱ ክፍል ዕቅድ፣ የሚጠበቀው ውጤት፣ የአፈጻጸም አቅጣጫ፣ የሚያስፈልጉ ድጋፎችና በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ተገምግመዋል
ከዚህ በተጨማሪም የቀደመውን ዓመት አፈጻጸም በመገምገም የተገኙ ስኬቶች፣ የታዩ ክፍተቶች እና በቀጣይ ዓመት ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች በጋራ ተዳስሰዋል
የውይይቱ ዋና ዓላማም የተቋሙን የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻል፣ የታካሚ ደኅንነትን ማረጋገጥ፣ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ባህል መገንባት እና የተቋሙን የጥራት ማሻሻያ ሥራዎች በተቀናጀና በተጠያቂነት፥በተመሠረተ መንገድ ማስፈጸም ነው
በመሆኑም በዛሬው ዕለት የቀረበው የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሪፎርም እና የKPI ዕቅድ ከተሳታፊዎች ጋር በስፋት ከተወያየበት በኋላ በጋራ አስተያየትና ምክረ ሐሳብ ተጠናክሮ ጸድቋል
በአሁኑ ወቅት የዕቅድ ዝግጅትና ማጠናቀቂያ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል
ይህም ያለፈውን የሥራ አፈጻጸም በመገምገም የተሻለውን ለማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ለቀጣዩ ዓመት ግልጽ፣ ተግባራዊና ውጤት ተኮር ዕቅድ ለማዘጋጀት ወሳኝ ወቅት ነው
ባሳለፍነው ዓመት በታቀደው መሠረት በተለያዩ የጥራት ማሻሻያ ሥራዎች ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡም ለቀጣዩ ዓመት ዕቅድ ጠንካራ መሠረት ሆኗል
ይህንን ውጤታማ አፈጻጸም በማስቀጠልና በበለጠ በማሻሻል፣ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የታካሚዎችን እርካታና ደኅንነት የሚያሳድጉ፣ የአገልግሎት ጥራትን የሚያጠናክሩ እና የተቋሙን አፈጻጸም ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ሥራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑ ተገልጿል
በመጨረሻም የኳሊቲ ዳይሬክቶሬቱና የየክፍሉ ኃላፊዎች በተቀናጀ መልኩ በመሥራት የተዘጋጀውን ዕቅድ በተግባር በማዋል እና አፈጻጸሙን በየወቅቱ በመከታተልና በመገምገም የማዕከሉን የጤና አገልግሎት ጥራት ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል
ሠናይ ቀን!
📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን
📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050
👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC
👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE

Facebook
Yekatit 12 Hospital Medical College | Addis Ababa
Yekatit 12 Hospital Medical College, Addis Ababa. 29,911 likes · 252 talking about this · 326 were here. Yekatit 12 Hospital was founded in 1923 and one of the 1st modern hospitals in the country....
❤2👍1
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር የላቀ ዕውቅና አገኘ
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተካሄደው የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ ተቋማዊ ምዘና መሠረት ከከተማዋ ሆስፒታሎች መካከል 3ኛ ደረጃን በማግኘት የክብር ዋንጫና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተሸልሟል።
የተቋሙ የምዘና ውጤት በጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋም ውስጥ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ታማኝነትና የሥነ ምግባር ባህልን ለማጠናከር የተወሰዱ ተቋማዊ እርምጃዎች ያስገኙትን ውጤት የሚያሳይ ነው። በተለይም ሙስናን መከላከል፣ የሥራ ሂደቶችን በተጠያቂነት መምራትና ለተገልጋዮች ፍትሃዊና ተደራሽ አገልግሎት ማቅረብ የመልካም አስተዳደር ዋና መርሆች እንደሆኑ ተቋሙ በተግባር አሳይቷል።
ይህ ዕውቅና የኮሌጁን የአስተዳደር አቅም ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ለሕዝብ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በታማኝነት፣ በፍትሃዊነትና በሙያዊ ሥነ ምግባር መርሆች ላይ እንዲመሠረት ያለውን ቁርጠኝነትም ያረጋግጣል። በጤና ተቋም ውስጥ መልካም አስተዳደር የአስተዳደር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከታካሚ እምነትና ከአገልግሎት ጥራት ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ፣ ውጤቱ ለተቋሙ ልዩ ትርጉም አለው።
የ3ኛ ደረጃ ዕውቅናው በኮሌጁ የተጀመረው የመልካም አስተዳደርና የፀረ ሙስና ሥራ መጨረሻ ሳይሆን የበለጠ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያበረታታ የአፈጻጸም መነሻ ነው። ተቋሙም በቀጣይ የግልጽነትና የተጠያቂነት ሥርዓቱን በማጠናከር፣ የፀረ ሙስና አሠራሮችን በማስፋትና የተገልጋዮችን እምነት በማጠናከር የበለጠ የላቀ ተቋማዊ ውጤት ለማስመዝገብ ይሰራል።
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ላስመዘገበው ውጤት የተቋሙን አመራርና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ይላል። ዕውቅናው የተቋሙን የላቀ አርአያነት በማጠናከር ለተሻለ አገልግሎት፣ ለጠንካራ ተቋማዊ ባህልና ለተገልጋዮች የበለጠ እምነት የሚያበረክት እርምጃ እንዲሆን ይጠበቃል።
📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
📅 ነሐሴ 15 /2018 ዓ.ም
📍
📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050
👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC
👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE
🔖 #Y12HMC 💛✨

የጃን ሜዳ ፖሊስ መምሪያ ለየካቲት 12 ሆስፒታል ታካሚዎች ያደረገው የርህራሄ ጉብኝት
አዲስ አበባ፦ ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጃን ሜዳ ፖሊስ መምሪያ የመምሪያው ኃላፊዎችና አባላት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት በሆስፒታሉ የሚገኙ ታካሚዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት የፖሊስ መምሪያው ለታካሚዎች የሚመገቡና የሚጠጡ ምግቦችንና መጠጦችን በስጦታ በማበርከት፣ በሆስፒታል ቆይታቸው በርትተው እንዲታከሙና ከህመማቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል። ይህም የፖሊስ ተቋሙ ከህግና ሰላም ማስከበር ባለፈ ለማህበረሰቡ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ያሳየበት ተግባር ሆኗል።
በጉብኝቱ ላይ የጃን ሜዳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ስጦታው ቡጤ ተገኝተዋል። ኢንስፔክተር ስጦታው ቡጤ በሰጡት አስተያየት፣ መምሪያው እንደዚህ ያሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በተለይም በችግር ውስጥ ያሉ የማህበረሰቡን አባላት መደገፍና ማገዝ የፖሊስ ተቋሙ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ትስስር የሚያጠናክር ተግባር መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከያና የመምሪያ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ተሬሳ ጋዲሳ በበኩላቸው፣ “የፖሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ህግን ማስከበር ብቻ ሳይሆን፣ ማህበራዊ ኃላፊነትንም መወጣት ነው” ብለዋል።
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በኩል የህንፃ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፊራፊስ አቡና ፖሊስ የማህበረሰቡ አካል በመሆኑ በችግር ላይ ያሉ ዜጎችን በመደገፍና በማገዝ የህዝብ አገልጋይነቱን በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል።
አቶ ፊራፊስ አክለውም፣ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅና የጃን ሜዳ ፖሊስ መምሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ በመኖሩ፣ በቀጣይም በጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የጃን ሜዳ ፖሊስ መምሪያ ያደረገው ይህ ጉብኝትና ድጋፍ፣ በህመም ላይ ለሚገኙ ዜጎች የሞራል ድጋፍ ከመሆን ባለፈ ተቋማት ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰብዓዊነትን፣ መረዳዳትንና የህዝብ አገልጋይነትን ለማጠናከር የሚያበረታታ ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል።

❤1
ከ18 ዓመታት የስቃይ ጥላ ወደ ደስታና ተስፋ
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተሳካ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ የ18 ዓመቷን ትዕግስት አበበን ህይወት ወደ አዲስ ምዕራፍ ቀይሯል።
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ነሃሴ 16/2018 ዓ.ም
አንዳንድ የህይወት አጋጣሚዎች ሰውን ለጥቂት ጊዜ ብቻ አይፈትኑም የሚቆዩት ለዓመታት ነው አንድ የልጅነት አደጋ የ18 ዓመቷን ትዕግስት አበበን ለዚህ ዓመታት የሚዘልቅ ፈተና ዳርጓት ነበር። ዛሬ ግን ያ ረጅም የስቃይ ጉዞ በተስፋ፣ በደስታና በአዲስ የህይወት እድል መቀየር ጀምሯል።
ትዕግስት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ አካባቢ ከ18 ዓመታት በፊት ተወለደች ገና የስድስት ወር ህፃን ሳለች የልጅነት ህይወቷን በአንድ አሳዛኝ አጋጣሚ ተለወጠ ከፍራሽ ላይ ተንከባላ በእሳት ላይ ወደቀች።
የቃጠሎው አደጋ በእጇ ላይ ከባድ ጠባሳና መጨማደድ አስከትሎ የእጅዋን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ገደበ በወቅቱ ወደ ህክምና ተቋም ብትወሰድም የተሟላ የህክምና እና የሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ እድል ሳታገኝ ቀረች።
ከዚያ በኋላ ዓመታት አለፉ። ትዕግስትም ከልጅነቷ ጀምሮ የእጇን እንቅስቃሴ በመገደብ እና በዕለት ተዕለት ኑሮዋ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር የቆየውን የቃጠሎ መጨማደድ ይዛ አደገች። እጇን ሙሉ በሙሉ መዘርጋትና መታጠፍ፣ የፈለገችውን ነገር በነፃነት መያዝ እና እንደሌሎች ሰዎች በእጇ ተጠቅማ የዕለት ተዕለት ተግባሯን ማከናወን ለእሷ በፍፁም አይታሰብም።
18 ዓመታት ከህፃንነት እስከ ወጣትነት እነዚህ ዓመታት ትዕግስት እጇን ብቻ ሳይሆን በልቧም የተሸከመችው የትዕግስት ጉዞ ነበሩ። በስሟ ያለውን “ትዕግስት” በእውነት እንድትኖረው ያደረገ ጉዞ።
ከዚያ ግን አንድ ቀን ተስፋ መጣ ለ18 ዓመታት የቆየውን ችግር በመቀየር ትዕግስት ወደ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለህክምና እንድትመጣ የሚያደርግ አጋጣሚ አገኘች።
በተቋሙ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ ባለሙያዎች ትዕግስትን በጥንቃቄ መርምረው፣ የቃጠሎው መጨማደድ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ በመሆኑ በእጇ ላይ ያስከተለውን ጉዳት በመገምገም ተስማሚ የህክምና እቅድ አዘጋጁ።
በዶ/ር ዳግማዊ ገረመዉ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ ሀኪምና ረዳት ፕሮፌሰር የተመራው የህክምና ቡድን የላቀ እና የተሳካ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ አከናወነላት።
የቀዶ ህክምናው ዓላማ የእጇን ገደብ ማስወገድና የእጅዋን እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን ማሻሻል ነበር ለትዕግስት ግን ይህ ከቀዶ ህክምና በላይ ነበር፤ ለ18 ዓመታት የተዘጋችበትን የነፃነት በር እንደገና የከፈተ እድል ነበር።
የህክምናው ውጤት ከተስፋ በላይ የሆነ ደስታን ይዞ መጣ ትዕግስት እጇን ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ መዘርጋትና መታጠፍ ጀመረች የፈለገችውን ነገር ጨብጣ መያዝ ቻለች ሰውን በእጅ መጨበጥ ቻለች ከሁሉም በላይ ግን በእጇ ላይ የነበረው ገደብ በህይወቷ ላይ ያሳደረው የመተማመን ማነስ በአዲስ ተስፋ መተካት ጀመረ።
ከዚህ በፊት ለእሷ ቀላል ያልነበሩ ነገሮች አሁን በተሻለ ሁኔታ ይቻላሉ እጇን በነፃነት ማንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ህይወቷንም በተስፋ ማየት ጀምራለች።
ከህመም ወደ ደስታ ከገደብ ወደ ነፃነት ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ ከ18 ዓመታት የቃጠሎ መጨማደድ ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ።
ህክምናውን ያከናወኑት ዶ/ር ዳግማዊ ገረመዉ እንደሚገልፁት የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ የአካል ገጽታን ለማስተካከል ብቻ የሚደረግ ህክምና አይደለም በተለይም እንደ ትዕግስት ያሉ ታካሚዎች ለዓመታት የተሸከሙትን የአካል ገደብ በማሻሻል ወደ የተሻለ የኑሮ ጥራት እንዲመለሱ የሚያስችል የህይወት ለውጥ ነው ያሉት።
የትዕግስት ጉዳይም ይህንኑ ያሳያል ለ18 ዓመታት ከእሷ ጋር የኖረው የቃጠሎ ጠባሳ ዛሬ የህይወቷ መጨረሻ ሳይሆን አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ሆኗል።
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ ቡድን የተሰራው ስራም አንድ ህክምና ተሳክቷል ከሚል በላይ የሚገልጽ ነው አንዲት ወጣት እንደገና በራሷ እንድትተማመን፣ እጇን በነፃነት እንድትጠቀም እና የወደፊት ህይወቷን በተስፋ እንድትመለከት እድል ሰጥቷል።
የትዕግስት ታሪክ በአንድ ቃል ሲጠቃለል “ተስፋ እስካለ ድረስ ለውጥ ይቻላል” የሚል ትልቅ መልዕክት ነው።
ዛሬ የ18 ዓመቷ ትዕግስት የትናንቱን ህመም ትታ የነገውን ህይወት በተስፋ ለመገንባት በአዲስ መንፈስ ወደፊት ትመለከታለች።
ይህ ተአምር ብቻ አይደለም የህክምና እውቀት የሙያ ትጋት የታካሚ ትዕግስት እና ተስፋ ተደምረው የፈጠሩት የህይወት ለውጥ ነው።
ማስታወሻ: የፎቶ እና ሕክምና ታሪክ ፈቃድ ከታካሚ ተወስዷል::
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ — ህይወትን በህክምና መለወጥ።

❤5👍1🙏1