Turullee Dhugatu Mo'ata
10.9K subscribers
508 photos
129 videos
110 files
413 links
Sobni miseensa guddaa qabaatuun yeroo dheerefatun ni malaa, garuu dhugaa hinjifatuu ammoo gonkumaa hin danda'u.
Download Telegram
በፍትሕ ሚንስትር የተዘጋጀው "የሀይማኖት ጉዳዮች አዋጅ" በተመለከተ ከዩኒቨርስቲ ተወካዮች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን ተቃውሞ ገጥሞታል!
(#ሀሩን_ሚዲያ፦ግንቦት 01/2016)
ከሰሞኑ በአወዛጋቢነቱ አጀንዳ ሁኖ የቆየው በፍትሕ ሚንስትር የተዘጋጀው "የሀይማኖት ጉዳዮች አዋጅ"ከዩንቨርሲቲ ተወካዮች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት ማድረጉ ተሰምቷል። ውይይቱ የተዘጋጀው በሰላም ሚኒስትር ሲሆን በውይይቱ ላይ ከዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትና አንድ መምህር በአጠቃላይ ከአንድ ዩኒቨርስቲ ሁለት (2)ተወካዮች ያካተተ መሆኑን ለሀሩን ሚዲያ ምንጮች ገልጸዋል።በውይይቱ ሁሉንም ሀይማኖቶች የሚመለከቱ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱት መካከል በተለይ ኢስላምን የተመለከቱ ህጎች "በቡድን ማምለክ"እና "ማንነትን የሚያሳይ አለበባስ"ብቻ መፍቀዱ በጋራ ሰላት መስገድን እና ኒቃብ መለበስ የሚከለክል በመሆኑ አንድ ሀይማኖት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ለአፈፃም የሚችግር መሆኑን ከምሁራኑ ተነስቷል።ከኦዲት ሪፖርት ከፋይናንስ ቁጥጥር መንግስት በሃይማኖት ያለውን ጣልቃ ገብነት በተመለከተ ፣የሀይማኖት ተቋማት ግንባታ ሊሎር የሚገባ እርቀት ፣የመቃብር ቦታዎች እና ሌሎችም ሰፊ ሀሳቦች መነሳታቸው ተገልጿል።በመጨረሻም ውይይት ሲመሩ የነበሩ አካላት የተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተለይ በቡድን አምልኮ እና ማንነት የተመለከተ አልባሳት ላይ በድጋሜ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉበት መናገራቸውን የሀሩን ሚዲያ ምንጮች ገልጸዋል። በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች በተጨማሪ ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም ቅሬታቸውን እያቀረቡ ሲሆን አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የህዝብ ቅሬታዎችን ባማከለ መልኩ እንዲስተካከል የተለያዩ ሀይማኖታዊ ተቋማት በየፊናቸው ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
https://t.me/Xaaliburidallah