✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ኅዳር 14 ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ ጾመ ነቢያት +"+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::
+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::
+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል::
+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን::
+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት: ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን::
+ጾመ ነቢያት ማለት ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው::
በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስና
ቅዱስ ዳንኤል በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን
ናቸው:: (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3)
+ቅዱስ ዳዊት "ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ" (መዝ.
68:10, 108:24) ብሎ ዘወትር ሰውነቱን በምን
ለእግዚአብሔር ያስገዛ እንደ ነበር ጠቅሷል:: ቅዱሳን
ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ
መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም
አብቅቶታል::
+በየዘመኑ ጻድቃነ ብሊት በጾማቸው ከመዓት ርቀዋል::
ጸጋ: ክብርና ሞገስንም አግኝተዋል:: ይህ ጾም ኅዳር 15
ቀን ጀምሮ ታሕሳስ 29 ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን በ4
ዓመት አንዴ 1 ቀን ወደ ሁዋላ ያሰግራል::
+ጾሙም የተለያዩ መጠሪያዎች ሲኖሩት እነዚህ
ይጠቀሳሉ:-
1.ጾመ ነቢያት
2.ጾመ ማርያም (ጌታን ጸንሳ ሳለ የአባቶቿን ጾም
ጾማለችና)
3.ጾመ ሐዋርያት (ሐዋርያትም በረከተ ነቢያትን ሲሹ
ይጾሙት ነበርና)
4.ጾመ ጌና ("ጌና - ልደተ እግዚእ ስቡሕ" ማለት ነው)
5.ጾመ ስብከት (ስብከተ ነቢያት ስለሚታሰብበት)
6.ኅዳር ጾም (በወሩ ምክንያት)
7.ጾመ ፊልዾስ (አርድእተ ፊልዾስ ሐዋርያ ለጉዳይ ስለ ጾሙት)
=>አምላከ አበው ነቢያት በጾሙ ከሚገኘው ጸጋ በረከት አይለየን::
=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 21-የተወደዳችሁ የክርስቶስ ወገኖች ሆይ! አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን ስም አጠራር የማዳኑን ኃይል እንነግራችሁ ዘንድ ስሙ፡፡ በቀናች ሃይማኖት ሆኖ ስሟን መጥራት ወድቆ የሚፍገመገመውን ያነሣል፣ ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋልና፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን የክብርት እመቤታችንን ስም የሚጠራ አንደበት ምንኛ የተባረከ ነው፡፡ እንደምን ያመልጥ! እንደምንስ ከመከራ ሁሉ ይድን ዘንድ ምንኛ ዕድለኛ ይሆን! እንደምን ከፍ ከፍ ይል! ይህ ስም ከሁሉ ይልቅ እንደምን የተከበረ ነው፡፡ በቃልኪዳን ውኃ ያነጻን ዘንድ ጻድቃንም ለመሆን ወደ እርሷ ለሚገቡ ኃጥአን አማላጅ ይሆን ይሆን ዘንድ በቃልኪዳን ቀለም በመንግሥተ ሰማያት በር የተጻፈ ነውና፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን ቃልኪዳን የተጀመረ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ አይደለም፡፡ አዳም ከገነት ከወጣና ከከብሩም ከተለየ ጀምሮ ነው እንጂ፡፡ ፈጽሞ ባለቀሰ ጊዜ ጌታችን አለኝታ ባለው ቃልኪዳን ‹ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ተሰቅዬ ሙቼ አድንሃለሁ› ብሎታልና፡፡ እመቤታችንን የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት አድርጎ እንደፈጠራት ልብ አድርጋችሁ እነሆ ዕወቁ፡፡ ሁለተኛም ከሁሉ ይልቅ ከቸር ፈጣሪያችን በተሰጧት ኪዳናት ሁሉ ለእስራኤል ደኅንነት ትሆን ዘንድ ለሙሴ የተሰጠው ሕጉ የተጻፈበት ጽላት ያለበት መጠጊያ ብሎ ስም እንዳወጣለት ዕወቁ፡፡
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ለነቢያት፣ ለሐዋርያት፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታትም ሁሉ እመቤታቸው ናት-የእርሷ ቃልኪዳን ፍጻሜያቸው ነውና፡፡ በእርሷ ሥጋ መስቀልን አሳስቦ ከመናገሩ የተነሣ ምንም ለእነዚህ ክቡራን ሁሉ ቃልኪዳን ቢሰጣቸው የቃልኪዳን መመኪያ አክሊል እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ይህን ቃልኪዳን በመስማት አምነው አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችንን ስም በመጥራት የዳኑትን ስንቱን እንነግራችኋለን፡፡ የተአምራቷ ኃይል ከሰማይ ከዋክብት ከባሕር አሸዋ እጅግ የበዛ ነውና፡፡ ልመናዋ ክብሯ ለዘለዓለሙ በዕውነት በሁላችን በተዋሕዶ ልጆች ላይ አድሮብን ይኑር››
+ + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ አናሲሞስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኽም ቅዱስ አስቀድሞ ከሮሜ ሰዎች ወገን ለሚሆን ስሙ ፊልሞና ለሚባል ለሮሜ ሰው አገልጋይ የነበረ ነው፡፡ ፊልሞናም በሮሜ አገር የከበረች ወንጌልን ቅዱስ ጳውሎስ ባስተማረ ጊዜ በጌታችን አመነ፡፡ ከዚያም ፊልሞና አገልጋዩን አናሲሞስን ይዞ ከሮሜ አገር ወደ አስባንያ ሄደ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን የአናሲሞስን ልብ ለወጠውና አሳተው፡፡ የጌታውንም ገንዘብ ሰርቆ በመሸሽ ወደ ሮሜ አገር ተመልሶ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ፡፡
አናሲሞስም በሮሜ አገር ተቀምጦ ሳለ ፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ወሰደው፡፡ አናሲሞስም የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርቱን በሰማ ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነና ለሐዋርያው ደቀ መዝሙሩ ሆነ፡፡ ነገር ግን የጌታውን ገንዘብ በመስረቁ በአናሲሞስ ልብ ውስጥ ጽኑ ሀዘን አደረ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስም የሠራውን ሁሉ ነገረው፡፡ ሐዋርያውም ‹‹አይዞህ አትፍራ፣ ልብህም አይዘን›› ብሎ አጽናናው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ፊልሞና መልእክት ላከለት፡፡ ይህችም ስለ አናሲሞስ የጻፋት ከመልእክቶቹ አንዲቱ ናት፡፡ ለፊልሞናም በመልእክቱ እንዲህ አለው፡- ‹‹እኔ በእስራቴ ጊዜ ስለወለድኩት ልጄ እማልሃለሁ ይኸውም አናሲሞስ ነው፤ የቀድሞ ሥራው አልጠቀመህም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ለአንተም ለእኔም እጅግ የሚጠቅም ሆኗል፡፡ አሁንም ወደአንተ ልኬዋለሁና ልጄ እንደመሆንህ ተቀበለው፡፡ የበደለህንም በደል ወይም የሚበድልህ ቢሆን በእኔ ላይ አድርገው፡፡››
ፊልሞናም አናሲሞስ ከእርሱ ዘንድ በደረሰ ጊዜ አገልጋዩ በጌታችን በማመኑና በመጸጸቱ ደስ አለው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳዘዘውም አደረገለት፡፡ እጅግም ወደደውና ብዙ ገንዘብ ሰጠው፣ አናሲሞስ ግን ‹‹እኔ በክርስትና ባለጸጋ ሆኛለሁና ምንም ገንዘብ አልወስድም›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ፊልሞና ሸኘውና ወደ ሮሜ አገር ተመለሰ፡፡ አናሲሞስም በሰማዕትነት እስከሚያርፍበት ጊዜ ድረስ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን የሚያገለግለው ሆነ፡፡ ቅዱስ አናሲሞስም ካህን ሆኖ ተሾመና የሚያገለግል ሆነ፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም በመጽሐፋቸው ቅዱስ አናሲሞስን ‹‹ታማኝ ካህን ነው›› ሲሉ አመስግነውታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ የንጉሡ የጭፍሮች አለቃ ቅዱስ አናሲሞስን ይዞ በግዞት ወደ አንዲት ደሴት ሰደደው፡፡ ቅዱስ አናሲሞስም በዚያች ደሴት የሚኖሩትን ሰዎች የከበረች ወንጌልን ሰበካለቸው፡፡ እነርሱንም ካሳመናቸው በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው፡፡ ከብዙ ቀናትም በኋላ የጭፍሮቹ አለቃ ወደዚያች ደሴት በደረሰ ጊዜ ቅዱስ አናሲሞስን የከበረች የጌታችንን ወንጌል ሲያስተምር አገኘው፡፡ ከያዘውም በኋላ ብዙ አሠቃየው፡፡ ጽኑ ግርፋትን ካስገረፈው በኋላ ጭኖቹን ሰበረው፡፡ ቅዱስ አናሲሞስም በዚሁ ምስክርነቱን ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡ የከበረች በረከቱ ትደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
(ምንጭ፡- ተአምረ ማርያም፣ ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት)

የካቲት 21
የዕለቱ ምንባባት፦
✅ሮሜ ፱፥፩ - ፲፯፤
✅፩ጴጥ ፪፥፳ - ፍ፤
✅ግብ ፲፩፥፩ - ፲፬፤
✅የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፬፥፩ - ፳፯፤
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ፤
@wwwyarede
የካቲት 21 ምስባክ፦
አግረረ ለነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ፤
ወኀረየነ ሎቱ ለርስቱ፤
ሥኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ።
መዝ፵፮፥፫
መልካም አዳር
@wwwyarede
የዕለቱ ምንባባት፦
✅ሮሜ ፱፥፩ - ፲፯፤
✅፩ጴጥ ፪፥፳ - ፍ፤
✅ግብ ፲፩፥፩ - ፲፬፤
✅የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፬፥፩ - ፳፯፤
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ፤
@wwwyarede
የካቲት 21 ምስባክ፦
አግረረ ለነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ፤
ወኀረየነ ሎቱ ለርስቱ፤
ሥኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ።
መዝ፵፮፥፫
መልካም አዳር
@wwwyarede
Forwarded from ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ (AkliluB B)
የዘወረደ መዝሙር
ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንህነሰ ህዝቡ።
ባዑ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ፡ ንህነሰ ህዝቡ።
ንፁም ፆመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ ፡እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ፤ ንህነሰ ህዝቡ።
አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፡ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንህነሰ ህዝቡ። ምሕረት ወፍትሐ አኀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንፁሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንህነሰ ህዝቡ አባግዓ መርዔቱ፡
ዓራራይ
መሐረነ
ንጉሠ ስብሐት፡ ተሣሃለነ እግዚአ ለሰንበት፡ ወአቡሃ ለምሕረት፡ ወሀበነ ጾመ ለንስሐ፡ በዘይሠረይ ኃጢአት።
ሰላም
አክብሩ ሰንበትየ፡ ወዕቀቡ ቃለ ሰላምየ፡ትርከቡ ሕይወተ ዘለዓለም።
ይቤ እግዚአብሔር
የቅዳሴ ምንባባት
ዕብ፡ ምዕ፡ 13፡ ቁ፡ 7 – 17።
ያዕ፡ ምዕ፡ 4፡ ቁ፡ 6 - ፍጻሜ ሐዋ፡ሥ፡ ምዕ፡ 20፡ ቁ፡ 13 - ፍጻሜ
ምስባክ መዝሙር፡ 2፡ ቁ፡11።
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት።
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ።
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመኢይትመአዕ እግዚአብሔር።
ትርጉም
፦
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።ጥበብን አጽኑአት ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ።
ወንጌል፡ ዮሐንስ፡ ምዕ፡ 3፡ ቁ፡ 10 – 21። ቅዳሴ ዘእግዚእነ (ነአኵተከ)፡፡

"ጾምን ቀድሱ፡ ምሕላንም ዐውጁ፡ ሸማግሌዎቹን ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ(ለምኑ)፤›› (ኢዩ.፩፥፲፩ – ፲፭)
ሰበር! አሳዛ-ኝ ዜና
በምሥራቅ ወለጋ ሆሮ-ጉዱ #ጃርቴ ወረዳ ተጨማሪ 29 ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸው ተሰማ።
********************************
በምሥራቅ ወለጋ ሆረ ጉዱ #ሻንቦ ዞን #ጃርቴ ወረዳ #ዴቢስ በተባለ ቀበሌ 29 ምዕመናን በኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለዋዜማ ሬዲዮ ዛሬ ተናግረዋል።
ባሳለፍነው ቅዳሜ የጃርቴ ወረዳ ዴቢስ ቀበሌ ነዋሪዎች የዓብይ ጾምን መያዛ ምክንያት በማድረግ ቤ/ክ ተሰብስበው በነበሩበት ወቅት ነው የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች ወደ ቤተ-ክርስትያኑ በመዝለቅ የቤተ-ክርስትያኒቱን አስተዳዳሪ ቄስ ወዲያውኑ እንደገደላቸው እና እንደዚሁም 28 የሚሆኑትን ምዕመናን ደግሞ #ገርጂ ወደ ተባለ ጫካ ይዟቸው በመሄድ በጥይት ደብድበው እንደገደሏቸው የተሰማው።
አስከሬናቸው በትላንትናው ዕለት (29/06/2013 ዓ/ም) ተጥሎ መገኘቱን እና ዛሬ በእዛው በቀበሌአቸው የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ መፈጸሙን የሟች ቤተሰቦች ለዋዜማ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ክስተቱ የሆነው በዕለቱ የቀበሌው ሚኒሻዎች ፣የወረዳው አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊሶች ጋር በመሆን በሌላ አካባቢ የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎችን ለመምታት ዘመቻ በማካሄዳቸው ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት መሆኑን የቀበሌ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የቀበሌው ሚኒሻዎች እና የልዩ ኃይል ፖሊሶች አሰሳ በሚል ከቀበሌው መውጣቸው መረጃው የደረሳቸው የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች ወደ ቀበሌው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአሁን ወቅት የቀበሌ ነዋሪ የኦነግ ሼኔን ጥቃት በመፍራት ቀዬውን ለቆ ወደ ተለያዩ ቀበሌዎች እና አጎራባች ወረዳዎች እየሸሹ መሆናቸው ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።
የኦሮማያ ክልል ፖሊስ ስለጉዳዩ ተጨማሪም መረጃ ተጠይቆ እስከአሁን ምላሽ አለመስጠቱን ነው የተሰማው።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬም በዚህ አሳዛኝ ክስተት ሕይወታቸው ላጡ እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸው በአፀደ ገነት ያኑርልን÷ ላዘኑትም መጽናናቱን ያድልልን።
(የመረጃ ምንጫችን:- ዋዜማ ሬዲዮ እና አደባባይ ሚዲያ )

† የካቲት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
(ታላቁ ነቢይና ካህን መጥምቁ ዮሐንስ ሔሮድስ በግፍ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ ቅድስት ራሱ ለ15 ዓመታት ዙራ አስተምራ አርፋለች:: በዚህ ዕለትም በልሑክት (በሸክላ ዕቃ) የተገኘችበት በዓል ይከበራል:: በዓሉም "ተረክቦተ ርዕሱ" በመባል ይታወቃል:: )
2.አባ ሚናስ ሊቀ ዻዻሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጃርቴ ወረዳ ዴቢስ በተባለ ቀበሌ አንድ ካህን እና 28 ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ !!!
መጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ.ም (ሻሸመኔ፤ኢትዮጵያ)
*************************************************
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጃርቴ ወረዳ ዴቢስ በተባለ ቀበሌ አንድ ካህን እና 28 ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ።
ባሳለፍነው ቅዳሜ የጃርቴ ወረዳ የዴቢስ ቀበሌ ነዋሪዎች የዐቢይ ጾም መያዣን ምክንያት በማድረግ በቅጽረ ቤተክርስቲያን ተሰባስበው በነበረበት ወቅት “የኦነግ ሸኔ” ታጣቂዎች ወደ ቤተክርስቲያኑ በመዝለቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳዳሪ ካህን ወዲያውኑ እንደገደሏቸው እና 28 የሚሆኑትን ደግሞ ገርጂ ወደተባለ ጫካ ይዘዋቸው በመሄድ በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል ሲሉ እማኞች ገልፀዋል።
አስከሬናቸው ጫካ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን እና ከትናንት በስቲያ በዚያው በቀበሌያቸው የቀብር ሥነ ስርዓቱ መፈጸሙን የሟች ቤተሰቦች ለዋዜማ ተናግረዋል።
በእለቱ እለት የቀበሌው ሚሊሻዎች የወረዳው አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል የልዩ ሃይል ፖሊስ ጋር በመሆን በሌላ አካባቢ “የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎችን” ለመምታት ዘመቻ በመሄዳቸው ምክኒያት በተፈጠረ ክፍተት መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች ተናገረዋል።
የቀበሌውን ሚሊሻ እና የልዩ ሃይል አሰሳ በሚል መውጣታቸውን መረጃ የደረሰው “ኦነግ ሸኔ” ወደ ቀበሌው በመግባት ጥቃት ማድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የቀበሌው ህዝብ “የኦነግ ሼኔን ታጣቂዎች” በመፍራት ቄያቸውን ለቀው ወደ ተለያዩ ቀበሌዎች እና ወደ አጎራባች ወረዳዎች እየሸሹ መሆኑን ለዋዜማ ተናግረዋል።
የኦሮምያ ክልል ፖሊስ ሰለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጠን ጠይቀን እስካሁን ምላሽ አላገኘንም ሲል ዋዜማ ራዲዮ ገልፃለች።
መረጃውን ከዋዜማ ራዲዮ አገኘን
#ኦርቶዶክሳዊ ሚዲያ ለኦርቶዶክሳውያን
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
የዩቲዩብ ቻናላችንን https://www.youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q
የኢንስታግራም አካውንታችንን
http://www.Instagram.com/eotcwestarsidiocese
የቲውተር አካውንታችንን
http:// www.twitter.com/eotcwestarsidiocese
እንዲሁም ድረገፃችን
http:// www.eotcwestarsidiocese.org
ይጎብኙ

Forwarded from ✥ማኅሌት ዘቅዱስ ያሬድ✥
ሥርዓተ ማኅሌት ዘመጋቢት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 'መጋቢት ፭'
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።
ዚቅ
ላህም መግዝዕ ተጠብሐ፤ ጽዋዓ መድኃኒት ተቶስሐ፤ አግብርት አግብርት አግብርት ይረፍቁ፤ ውስተ ሕፅኑ ለመርዓዊ፡፡
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።
ዚቅ
ወይሁቦ ጸሎቶ ለዘጸለየ፤ ወባረከ ዓመተ ጻድቃኑ፡፡
ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት፤ እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት።
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ማርያም ቤዛ ብዙኃን፤ ሕይወተ ኮነት ለኲሉ ዓለም፤ ፍሥሐነ ለእለ አመነ፡፡
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።
ዚቅ
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ ከመ አዕዋፍ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ጽሑፍ፡፡
ወረብ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ/፪/
'ኀበ ዓምደ ወርቅ'/፪/ ስሙ ጽሑፍ/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ሰላም፤ ዓቃቤ ሥርዓት ዘሤመ ወማዕፆ ሕግ ዘዓቅም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መነኮስ በምግባረ ሠናይ ፍጹም፤ እንበለ መብልዕ ወስቴ እንዘ ትትጋደል በጾም፤ ነጺራ ትዕግሥተከ አንከረት ገዳም፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ፤ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ፤ ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ።
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ/፪/
ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ/፬/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከርሥከ ዘተሴሰየ ኅብስተ፤ አኮ ኅብስተ ምድራዌ እንተ ያመጽዕ ሐኬተ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኲሉ ይንዕዱከ ከሡተ፤ ብርሃነ ለዕውራን ወለሐንካሣን ፍኖተ፤ ወለበሐማን ቃለ ዘኮንኮሙ አንተ፡፡
ዚቅ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይከ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበስለ፤ ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይከ፤ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድሐ።
ወረብ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዌ ኅብስተ/፪/
አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ እንተ ረሰየ ህላዌ፤ ኀበ ኢሰማዕ ቦቱ ዜና ሞት ወዝክረ ደዌ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንተ ዘገዳማውያን ሠርዌ፤ ወረዱ ጊዜ ሞትከ ዑፁፋነ ፅዱል ሥርጋዌ፤ ከመ ይትቀበሉ ኪያከ መርዓዌ፡፡
ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡
ወረብ
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለገብረ ሕይወት/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ብርሃነ ሰማይ ዘአገቶ፤ እለ ያዕቆብ ወዮሴፍ እስከነ ፈርሁ ቀሪበቶ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባዕል ለብዕለ ጸጋከ ዘያስተቶ፤ ኃያል ብእሲ ይንሣእ ሢመቶ፤ ወበዓለ ዕዳ ይበርብር ንዋዮ ወቤቶ፡፡
ዚቅ
ፀሐይ ፀሐይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ፤ ዘያበርህ ስኑ በውስተ ቀላይ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ዘባረኮ አግዚእ አዶናይ።
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ ክብር ወስብሐት ዘሎቱ፤ መጽሐፈ ገድልከሰ ኢይነግር ዜና ኩናቱ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሊተ ይመስለኒ ባሕቱ፤ ግንዘተ ሥጋከ በእደ መላእክት ውእቱ፤ እንዳኢ እግዚአብሔር የአምር ባሕቲቱ።
ዚቅ
ወረዱ መላእክት ምስለ አክሊላት ከመ ይግንዙ ሥጋሁ፤ ወቀበርዎ መልዕልተ ደብር ነዋኅ፡፡
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም መቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ፤ ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ፤ ዜና መቃብርከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ፤ ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም ዓፀድ፤ ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ፡፡
ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ፡፡
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘእግዚአብሔር ገብር በእደ መላእክት ቅቡር፤ በኢየሩሳሌም ሀገር፤ ኀበ ኢይበጽሕ ሰብእ በእግር፤ እንበለ ዳዕሙ ዖፍ ዘይሠርር።
አንገርጋሪ
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፪/
ወረብ
'ግሩማን መላእክት'/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፪/
እስመ ለዓለም
ይትፌሥሑ በኀበ አልቦቱ ሞት፤ ይነሥኡ እሴቶሙ፤ እስመ ትዕግስት ተውህበ ሎሙ ከመ ይንሥኡ፤ ብዙኅ ሕማሞሙ ለጻድቃን፤ ወእምኲሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር፤ ወየዓቅብ ነፍሳቲሆሙ፤ እስመ እንዘ ይነብሩ ውስተ ዓለም እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ፤ ከመ ይንሥኡ አስበ ስብሐቶሙ፤ አክሊል ንፁሕ ዲበ ርእሶሙ፡፡
ወረብ
ይትፌሥሑ በኀበ አልቦቱ ሞት ይነሥኡ እሴቶሙ/፪/
እስመ ትዕግሥት ተውህበ ሎሙ ከመ ይንሥኡ እሴቶሙ/፪/
✝ መልካም በዓል ✝
👉 @werebs👈

መዝሙር ዘቅድስት መጋቢት ፭ ፳፻፲፫ ዓ·ም
በ (፭/ር) ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ሀልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ።
ትርጉም፦
ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውን ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙ ምስጋናን ስጡ/አቅርቡ ሰንበትን አክብሩ ጽድቅን ሥሩ ሌባ በማያገኘው ብል በማያጠፋው በሰማያት መዝገብን አከማቹ ክርስቶስ ባለበት ለመሆን በላይ ያለውን እያሰባችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።
የዕለቱ ምንባባት፦
፩ተሰ ፬፥፩ - ፲፫፤
፩ጴጥ ፩፥፲፫ - ፍ፤
ግብ ፲፥፲፯ - ፴፤
የዕለቱወንጌል፦ ማቴ ፮፥፲፯ - ፳፭
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ፤
የዕለቱ ምስባክ፦
እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ፤
አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ፤
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ። መዝ ፺፭፥፭
ትርጉም፦
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ፤
እምነትና በጎነት በፊቱ ናቸው፤
ቅድስና እና የክብር ገናንነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።
ምሥጢር፦
እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ፈጠረ፤
ሃይማኖት ምግባር በፊቱ ነው አለ ምግባር ሃይማኖት የያዘ ሰውን ይወዳል፤
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ መመስገን ዓቢየ ስብሐት መባል ገንዘቡ ነው።
መልእክት፦
ሰማይ ማለት ሥዕለ ማይ - የውኃ ንድፍ ማለት ነው አንድም ልዑል ማለት ነው። ቀለሙ/መልኩ ሰማያዊ ነው እጅግ ብሩህ ቢሆን ዐይን ይበዘብዝ ነበርና እጅግም ጨለማ ቢሆን ለዐይን ይከብድ ነበርና። ይህንንም የፈጠረው የዐይን ማረፊያ ይሆን ዘንድ ነው ጠፈር/ሰማይ ባይኖር የሰው፣ የእንስሳና የአራዊት ዐይን ሁሉ ማረፊያ አጥቶ ወልቆ ወልቆ በወደቀ ነበርና።
ይህ ለሥጋዊ እንቅስቃሴአችን ሲሆን ለመንፈሳዊው እንቅስቃሴያችን ደግሞ በተለይ በጊዜ ቅዳሴ የዐይናችን ማረፊያ የሚሆነው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። አምላክችን ምግባር ከሃይማኖት አንድ አድርጎ የያዘ ሰውን ይወዳል ባልነው መሠረት አስቀድሳለሁ ብሎ ከቤቱ ተዘጋጅቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ሰው በዕለቱ የታወቀና ድንገተኛ ነገር ካላጋጠመው በስተቀር ሥጋ ወደሙን ይቀበል ዘንድ ወዶና ፈቅዶ የሚኖርበት ክርስቲያናዊው ሕግ ያስገድደዋል ይህን ካላደረገ ዐይኑ ማረፊያ ያጣ ሰው ሆኗል።
“እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ - እግዚአብሔርማ ሰማያትን ፈጠረ” ብሎ ለመዘመር አቅም የሚያንሰው ይሆናል። ዐይናችን ማረፊያ ሲያገኝ ልባችንም በተስፋ የተመላ ይሆናል እንዲህ ከሆነ ዐይን ያላያትን በሰው ልብ ያልታሰበችውን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያዘጋጃትን ዘለዓለማዊት መንግሥት በተስፋ እየጠበቀ የመኖር ዕድሉ ከቀን ወደቀን ያድጋል “ትምጻእ መንግሥትከ - መንግሥትህ ትምጣልን” እያለ ይጸልያልና።

አንኳን ለመስቀለ ኢየሱስ መጋቢት 10 በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡
#መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤
...መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤
...መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
...መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤
በአዲስ አበባ በብቸኝነት(እስከ ቅርብ ጌዜ ድረስ) ከቀድሞ ጀምሮ የመስቀለ ኢየሱስ በዓል በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ክብረ በዓሉ እንደሚከበር፡፡
በዚሁ ደብር በቀደሙት ዘመናት አገልጋዮች የመድኀኔ ዓለምና የመስቀል አገልጋዮች ተብለው በሁለት ምድብ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ነበሩ፤
የመስቀል አገልጋይ ካህናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደመወዛቸው ከቤተ መንግሥት ይይከፈላቸውም ጭምር ነበር፤ ….)
በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ
አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ
ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡
በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት
ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡
ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት
ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡
በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ #ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት
አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ
ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤
በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡
ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ
በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
*** እንደተለመደው ሥርዐተ ማኅሌቱንም አቅርበንላችኋል፡፡ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በዋይዜማ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታቱ በኪዳኑ፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በቅዳሴው እንገናኝ፡፡
(ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታሪክ የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት)
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እንኳን ለቅዱስ ዕፀ መስቀል፣ ለቅድስት ዕሌኒ ንግሥት፣ ለቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ እንዲኹም ለቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሣሌም ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"
ዳግመኛም ዛሬ መጋቢት 10 ቀን ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ፣ ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ፣ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ፣ አቡነ መልክዐ ክርስቶስ እንዲኹም ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼

መጋቢት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
" የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን::"
(1ቆሮ. 1:18-23)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@wwwyarede
1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
" የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን::"
(1ቆሮ. 1:18-23)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@wwwyarede
††† እንኳን ለጻድቁ አቡነ አሌፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† መጋቢት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አሌፍ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ቴዎቄጤኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ባስሊዖስ (ዻዻስና ሰማዕት)
4.አባ ኤፍሬም ሰማዕት
5.አባ ኤልያስ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
5.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
††† መጋቢት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አሌፍ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ቴዎቄጤኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ባስሊዖስ (ዻዻስና ሰማዕት)
4.አባ ኤፍሬም ሰማዕት
5.አባ ኤልያስ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
5.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ