የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለሚያስፈትኑ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ኦረንቴሽን ተሰጠ።
(ግንቦት 5/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ የ2017 ዓ.ም ከተማ አቀፉን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለማስፈጸም የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ከተማ አቀፉን የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ውይይት የተገኙና ፈተናው ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች የመጡ ርዕሳነ መምህራንም የሞዴል ፈተናውን በተያዘው መርሀ ግብር ከመስጠት ጀምሮ የተፈታኝ ተማሪዎችን መረጃ በአግባቡ በመመዝገብ ለፈተናው ዥግጁ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የ2017 ዓ.ም ክልላዊ ፈተናው በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን አምና የነበረውን አፈጻጸም በመገምገም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው ቢሮው ፈተናው ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።

ከተማ አቀፉ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 3 እና ሰኔ 4/2017 ዓ.ም እንዲሁም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 10፣11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በትላንትናው እለት መገለጹ ይታወቃል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ከመምህራን ጋር ውይይት መካሄድ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገለፀ።
(ግንቦት 6/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር ''ትውልድ በመምህር ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል'' በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ፣ ምልከታ የተካሄደባቸው ክፍለ ከተማዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና ሌሎች አመራሮችን ጨምሮ ውይይቱን በየካ ክፍለ ከተማ በኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኙት በእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ በበሻሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ በጋራ ጉሪ አንደኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ውይይቱን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር በየአመቱ መሰል ውይይቶች እንደሚካሄድ ገልፀው ውይይቶቹ ለስራ ውጤታማነት ትልቅ እገዛ እንደነበራቸው ያብራሩ ሲሆን እየተካሄደ የሚገኘውም ውይይት የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የትምህርት ልማት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል ያሉት ሀላፊው ትውልድን በመቅረፅ ስራ ውስጥ በቅንጅት ስራዎች ከተለያዩ አካላት ጋር እየተከናወኑ ይገኛሉም ብለዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መምህራን በዛሬው እለት እየተከናወነ ከሚገኘው ውይይት ባሻገር በደም ልገሳ፣ በከተማ ግብርና ፣ በማዕድ ማጋራትና በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል።
(ግንቦት 6/2017 ዓ.ም) መምህራን ተግባሩን ባከናወኑበት ወቅት በደም ልገሳ፣ በከተማ ግብርና ፣ በማዕድ ማጋራትና በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ መሳተፋችን ለሀገራዊ ለውጡ ያለንን አጋዥነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።