Addis Ababa Education Bureau
127K subscribers
14.9K photos
107 videos
2.31K files
4.65K links
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Download Telegram
ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተግባራት የተሻለ ስራ በሰሩ የትምህርት ተቋማት ልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

(ግንቦት 28/2017 ዓ.ም) የልምድ ልውውጡ በአጼ ነአኩቶ ለአብ 1ኛ ደረጃ እና በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዋና ርዕሳነ መምህራን እና የስርአተ ጾታ ክበብ ተጠሪዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማው እና የቢሮው የዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ በክፍለ ከተማው በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በተለይም በስርአተ ጾታ ክበባት በሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ተቋማት መካከል የአጼ ነአኩቶ ለአብ 1ኛ ደረጃ እና እንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚጠቀሱ መሆናቸውን ገልጸው ተቋማቱ በስርአተ ጾታ ክበባት ማቋቋሚያ መመሪያ በተቀመጠው መሰረት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡበት መንገድ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን በመሆኑ የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች ያገኙትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ በተቋማቸው ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በክበባቱ አማካይነት በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚስተዋሉ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ከወጣውን መመሪያ ጋር በተገናኘ የተሰጣቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ትምህርት ቤቶቻቸው ለሴት ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ቦታ እንዲሆኑ ያከናወኗቸው ተግባራት ልምድ የሚወሰድባቸው በመሆኑ የዛሬው የልምድ ልውውጥ መርሀግብር መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ቢሮው ቀደም ሲል በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚከሰትን ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ከህይወት ክህሎት ጋር በተገናኘ የወሰዱትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ተግባራዊ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ ጠቁመው በቀጣይ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የጾታ እክኩልነትን አረጋግጠው የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤት ማሻሻል እንዲችሉ ስራ ክፍሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ለ2018 የትምህርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለተማሪዎች ለማቅረብ እንዲቻል ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

(ግንቦት 28/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ለ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማቅረብ ጨረታ ያሸነፉ ድርጅቶች ወደ ምርት ከመግባታቸዉ በፊት ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለስ ለ2018 የትምህርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለተማሪዎች ለማቅረብ እንዲቻል በከተማ ደረጃ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊዎች መለየታቸዉን በመግለጽ ያሸነፉ ድርጅቶች ወደ ምርት ከመግባታቸዉ በፊት ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሳምሶን አክለዉም ኮሚቴው ጨረታዉን ባሸነፉ በ21 ዱም ጋርመንቶች በመሄድ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባውና በሚፈለገው ልክ ጥራቱ የተጠበቀ የተማሪዎች የደንብ ልብስ እንዲሰፋ ትልቅ ሀላፊነትና አደራ ጭምር የተጣለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ ዓል አድሃ/አረፋ/ በዓል አደረሳችሁ !


(ግንቦት 29/2017 ዓ.ም) 1446ኛውን ዓመት የኢድ ዓል አድሃ/አረፋ/ በዓልን ስናከብር የመረዳዳት ፣ የመተጋገዝና አብሮ የመቋደስ ልምዳችንን ይበልጥ በማጎልበት ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን ለ2017 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ምዕራፍ ውጤታማነት ተገቢዉን ትኩረትና ርብርብ በማድረግ እንዲሁም ተማሪዎች የተማሩትን ምን ያህል እንደተረዱ የሚመዘኑበት መምህራንና የትምህርት አመራሮች የለፋንበትን የምናጭድበት ምዕራፍ ላይ የምንገኝ በመሆኑ ለውጤታማነቱ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡


የሁላችንም ተሰናስሎ መስራት በትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት ላይ የሚኖረው ሚና ቀላል ባለመሆኑ ከምንጊዜው በላይ ትኩረት በመስጠት እንደድንሰራ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡


ኢድ ዓል አድሃ/አረፋ/ በዓል የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆን እመኛለሁ።


ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ



የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት

https://linktr.ee/aacaebc
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የ2018 የትምህርት ዘመንን መሪ እቅድ ገመገሙ።

(ግንቦት 29/2017) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የቢሮውን የ2018 የትምህርት ዘመንን ረቂቅ መሪ እቅድ የገመገሙ ሲሆን እቅድ በቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌታሁን ለማ ቀርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በ2017 ትምህርት ዘመን የተመዘገቡትን አበረታች ውጤቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን ለይቶ በማስተካከል በቀጣይ በ2018 ትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ አራት ስትራቴጂክ ትኩረት መስኮች ላይ መሰረት በማድረግ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅምን ፣ የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበትን ፤ የአጠቃላይ ትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥን ፤ ጥራትና ተገቢነት ያለው መማር ማስተማር እና የትምህርት ውስጣዊ ብቃት ማሳደግ በሚሉት ላይ በትኩረት በመስራት የትምህርት ሴክተሩን አጠቃላይ ትምህርት ተልዕኮ፣ ራዕይና ፣ ዕሴቶችን ለማሳካት ይሰራል ብለዋል፡፡

ሀላፊው አክለዉም የጸደቀው የ2018 የትምህርት ዘመን ሪቂቅ መሪ እቅድ በቀጣይ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግበተና በሚሰጡ ግብዓቶች ተካተው የሚዳብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ እቅድ ነባራዊ ሁኔታን ከሃገራዊ፣ ከተማ አቀፍና ተቋማዊ ሁኔታ ጋር በመዳሰስ ፤ ዋና ዋና የአፈጻጸም ስትራቴጅዎችና አቅጣጫዎችን በመለየት የ2018 ትምህርት ዘመን ግቦችና ፤ ዋና ዋና ተግባራትና የውጤት ዓመላካቾች ተለይተው በእቅዱ ውስጥ መካተታቸዉን ተናግረዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc