የሳይንስ ፣ ሂሳብና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ግምገማ ተካሄደ ::
(መጋቢት 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልፀግና ትግበራ እና የአፋን ኦሮሞ የስርአተ ትምህርት ማበልፀግና ትግበራ ዳይሬክቶሬቶች " የፈጠራ ስራን ከቃል ወደ ባህል!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን የ 2017 ዓ. ም የሳይንስ ፣ ሂሳብና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በውይይቱ ላይ እንዳሉት ውድድሩ ተማሪዎች ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎችን እንዲፈጥሩና ስርዓተ ትምህርቱ በአግባቡ እንዲተገበር የራሱ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል ::
አያይዘውም ውድድሩ ተማሪዎች የፈጠራ ስራቸውን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ አይነቶችን በአግባቡ መለየትና የቀረቡትን መስፈርቶች በወጥነት መተግበር ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል ::

የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ማበልፀግና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ አባይ ተስፋዬ በበኩላቸው ውድድሩ በተማሪዎችና መምህራን መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር የመማር ማስተማር ስራው ተግባር ተኮርና በፈጠራ የታገዘ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል :: አክለውም በውጤት አሰጣጥ ላይ ዳኞች ተናበው በመስራት ለውድድሩ ስኬታማነት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል ::
የቢሮው ኬሚስትሪ ስርዓተ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታሁን ጌታቸው የፈጠራ ሥራ አይነቶችና የማወዳደሪያ መስፈርቶች ላይ ማብራሪያ የያዘ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል ::
በውይይቱ የቢሮው ስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪዎችና የተፈጥሮ ሳይንስ ትግበራ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በሚገኘው መቅደላ ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው እና ከመጋቢት 24 ፍሬዎች መካከል አንዱ የሆነው ባለ 4 ወለል የመማሪያ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
(መጋቢት 23/2017 ዓ.ም) በመማሪያ ህንጻው የአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ፣የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አ ፈጻሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ እና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ አሰፋ ግርማን ጨምሮ የክፍለ ከተማውና የወረዳ 6 አመራሮች፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ እና የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በመቅደላ ቅድመ አንደኛ እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ ለአገልግሎት የበቃው ባለ 4 ወለል ህንጻ የኢትዮጵያ ትንሳኤ በተረጋገጠበትና ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስ እንደሚቻል በተረጋገጠበት መጋቢት 24 ዋዜማ ላይ መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ጠቁመው የመማሪያ ህንጻው በትምህርት ቤቱ ያለውን የተማሪ ክፍል ጥምርታ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ውጤታማ የሚያደርግ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አ ፈጻሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በከተማችን ባለፉት ሰባት አመታት በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልጸው በዛሬው እለት ከመጋቢት 24 ፍሬዎች መካከል አንዱ ሆኖ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት የተገነባው የመማሪያ ህንጻ ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
በተመሳሳይ አመራሮቹ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባውን የማስፋፊያ ሁለ ገብ ህንጻ ግንባታ አስጀምረዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አ ፈጻሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በከተማችን ባለፉት ሰባት አመታት በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልጸው በዛሬው እለት ከመጋቢት 24 ፍሬዎች መካከል አንዱ ሆኖ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት የተገነባው የመማሪያ ህንጻ ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
በተመሳሳይ አመራሮቹ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባውን የማስፋፊያ ሁለ ገብ ህንጻ ግንባታ አስጀምረዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ትምህርት በቴሌቭዥን ሥርጭት በAMN PLUS እና በትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ መስተጋብሮች
(መጋቢት 24/2017 ዓ.ም)
. ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 11፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00
. ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
https://youtu.be/2pDqW3LFSYc