Addis Ababa Education Bureau
127K subscribers
14.8K photos
107 videos
2.31K files
4.61K links
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Download Telegram
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም) በጥያቄና መልስ ውድድሩ የመንግሥትና የግል ት/ቤቶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ውድድሩም የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት አይነቶችን በማካተት ተካሂዷል።

የክ/ከተማው ት/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅግአየሁ አድማሱ እንደገለፁት የጥያቄና መልስ ውድድሩ የ2016 የትምህርት ዘመን 1ኛ መንፈቀ አመትን ምክንያት በማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸው ዓላማውም ተማሪዎች በዕውቀት ታንጸው የተሻለ የውድድር መንፈስ በመላበስ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ዕዉቀታቸው የላቀ በነገ ህይወታቸው የትኛውም ቦታ ገብተው በራስ መተማመን መስራት የሚችሉና ከእራሳቸው አልፈው ለሀገር እንዲተርፍ ለማስቻል የጥናት ባህላቸውን ማዳበር፣የማጠናከሪያ ት/ት መውሰድ ብሎም ባገኙት እድል ተጠቅመው ለሌሎች በውጤታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች ማስጠናት እውቀታቸውንም ማካፈል ይኖርባቸዋል ያሉት ወ/ሪት እጅጋየሁ መምህራንም የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች ብቃት እንዲኖሯቸው የበኩላችሁን ሚና ልትወጡ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም በጥያቄና መልስ ውድድር ደረጃ ለያዙ ተማሪዎችና ለዝግጅቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዋንጫ ሽልማት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአብዮት እርምጃ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም) "መቼም ፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!" በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካታት ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን ፣ የቂርቆስ ከፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የልዩ ፍላጎትና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ኤርሚያስ አካሉ ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር መ/ሪት ፋሲካ ወርቁ እንዲሁም መምህራን፣ተማሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካተት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚደረሱ ጾታን መሰረት የደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ብቁና የተሻለ ትውልድ መፍጠር የሁሉም ዜጋ ኃላፍነት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የጥያቀና
መልስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ለአሸናፉ ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመርሀ-ግብሩም ተማሪዎች የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ጭፈራዎችን ፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን በመነባንብ ፣ በስነ-ግጥምና በጭውውት አቅርበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የተማሪዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በጀሞ አንደኛ ደረጃ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ተካሄደ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 4/2016 ዓ.ም) የማለዳ ስፖርት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የተነቃቃ የትምህርት መንፈስ እንዲኖር የሚያስችል መርሀ ግብር መሆኑንና ፕሮግራሙ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተከታታይነት ተግባራዊ እንደሚሆን የክፍለ ከተማው የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በመርሃ-ግብሩ ወቅት ገልፀዋል።

ሃላፊው አክለውም በየትምህርት ቤቱ የጠዋት ጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተማሪዎች ልማድ እንዲያደርጉት መርሃ -ግብሩ ያግዛል ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የዕለተ አርብ የፅዳት ዘመቻ በመዝገበ ብርሃንና ሰላም ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሄደ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም) በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በመዝገበ ብርሃንና ሰላም ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የዕለተ አርብ የፅዳት ዘመቻ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተማሪዎች ፣ መምህራንና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በተገኙበት በመዝገበ ብርሃንና ሰላም ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሂዳል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የትምህርት ተቋማት የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ "ፅዳቱ የጠበቀ የመማሪያ ስፍራ፣ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል" በሚል መሪ ቃል የአምስት ወራት ሳምታዊ የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በወረዳ 04 በኡላዱላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

በዚህ የትምህርት ተቋማት የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን እንዲሁም የአካባቢያቸውን ፅዳት በመጠበቅ ጤነኛ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ሂደት የማሳካት ተግባር እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የስርዓተ ፆታ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ ፆታ ጥቃት/የነጭ ሪቫን ቀንን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር አከበር::

ቀኑን በማስመልከት መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በአሉን ስናከብር በሀገራችን እስካሁን ሲፈጠሩ የነበሩ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ያደረግነውን አስተዋፅኦ የምንገመግምበትና በቀጣይም ጥቃትን ለመከላከል ቃላችንን የምናድስበት ቀን ነው ብለዋል :: በአሉን ምክንያት በማድረግ በሚቀርበው ሰነድ የፆታ እኩልነት ግንዛቤን የምናሳድግበትና በሀገራችን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት የአስተሳሰብ ችግሮችን ለመቅረፍ እርስ በዕርስ ውይይት የምናደርግበት ይሆናል ያሉት ኃላፊው የፆታ ጥቃትን ዝም ባለማለት ከአቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ሲገጥመን በታማኝነት ለሕግ አካል በማሳወቅ ኃላፊነታችንን እንወጣ ብለዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ትእግስት በሪሁን የመወያያ ሰነድ አቅርበው በሰራተኞች ውይይት ተደርጓል ::
ቀኑን በማስመልከትም በቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም ከእንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጡ የስርአተ ፆታ ክበብ ተማሪዎች የተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ስራዎች ቀርበዋል ::