Addis Ababa Education Bureau
126K subscribers
14.7K photos
107 videos
2.31K files
4.59K links
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Download Telegram
በአራዳ ክ/ከተማ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የ2016 የትምህርት ዘመን አጀማማር በፎቶ

(አዲስ አበባ 7/1/2016 ዓ.ም)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በኮከበ ጽበሀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

(አዲስ አበባ 7/1/2016 ዓ.ም) በትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ፣ የየካ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆ እንዲሁም የከተማ ፣ ክፍለ ከተማ ፣ ወረዳ አመራሮችን ጨምሮ መምህራን ተማሪዎችና ወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የ2016 ዓ.ም የትምህርት አመትን በስኬት ለማስጀመር ቀደም ሲል ከሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸው ትምህርት ቤቶች ፍጹም ሰላማዊና ከማንኛውም የጸጥታ ስጋት ነጻ ሆነው የተማሪዎችን ውጤትም ሆነ ስነምግባር ማሻሻል እንዲችሉ መምህራን እና ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆ በበኩላቸው በ2015 ዓ.ም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ ወደ 2016 የትምህርት አመት መገባቱን ገልጸው ዘንድሮ በሁሉም የትምህርት እርከኖች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ የሚደረግበት እንደመሆኑ ክፍለከተማው በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል።
ኮከበ ጽበሀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2016ዓ.ም የትምህርት አመት በአግባቡ ለማስጀመር ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ ተገቢውን የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ደለለኝ አስማረ ገልጸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸውና ከጋደኞቻቸው ጋር በ2016 የትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ ሲገናኙ

(አዲስ አበባ 7/1/2016 ዓ.ም)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

(አዲስ አበባ 7/1/2016 ዓ.ም) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ2016 የትምሀርት ዘመን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አካላት ፣ተማሪዎች፣መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የተማሪዎች ወላጆች በተገኙበት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዶ የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እልት በይፋ ተጀምራል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድርባ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ ባደረጉት ንግግር መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳ አመራሮች የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ እንዲሁም ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት የሚካሄድባቸውና ከአዋኪ ነገሮች ነፃ የሆኑ ሰላማዊ አካባቢ እንዲሆኑ አጥብቀን እንሰራለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በክ/ከተማው የሚገኘው በገላን ቁጥር 2 አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በመማሪያ ክፍሎቻቸው በመገኘት የመማር ማስተማር ሂደቱ በት/ቤታቸው ህገ-ደንብ ላይ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
በክፍለ ከተማው በረጲ እና በዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ2016 ትምህርት የማስጀመሪ መርሀ ግብር ተከናውኗል፡፡

(መስከረም 6/2016 ዓ.ም) በኮልፌ ቀራኒዬ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ የክፍለ ከተማ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በረጲ እና በዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርት የማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ተከናውኗል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ለትምህርት ዘመኑ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል መምህራን እና የትምህርት ማህበረሰቡ በርካታ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልፀው ተማሪዎች በስነ-ምግባር ታንፃችሁ ትምህርታችሁ ላይ ትኩረት በማድረግ ጥሩ ውጤት ለማምጣት መትጋት አለባችሁ ብለዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው ተማሪዎች በስነ-ምግባር እና በጥሩ ውጤት ታጅባችሁ ትምህርታችሁን በመከታተል እና ተወዳዳሪ በመሆን የሀገራችሁን ፣ የቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም የመምህራኖቻችሁ ኩራት መሆን አለባችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱም የመማሪያ ቁሳቁስ እንዲሁም ዩኒፎርም ለተማሪዎች የመስጠት መርሀ ግብር ተከናውኗል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbueau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc