❄️ በእንተ ቅዱሳን መላእክት ❄️
" ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።" (ራእ 19:10)
ይህን በመጥቀስም ለመላእክት መስገድ ተገቢ አይደለም የሚሉ ክፍሎችም አሉ። ዳሩ ግን የመልአኩ አባባል ካለመረዳት እንጂ ለመላእክት መስገድ ከሃይማኖት ውጭ ሆኖ ዮሐንስ ባለማወቅ የሰገደለት ሆኖ አይደለም። ይህንንማ እንዳንል የሰጋጁ የዮሐንስ ማንነት ያግደናል። ዮሐንስ ድንግላዊና የጌታ ሐዋርያ ከመሆኑም ሌላ ጌታ የሚወደው በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ፤ ወንግጌልን መልእክታትን የጻፈ ፥ እንዲሁም የዓለምን ፍጻሜ በራእይ ያየ ነው ነው።
ይህን ያህል የጌታ ባለሟል የሆነ ቅዱስን ሰው ለትንሿ ለነገር ለመላእክት መስገድ ተገቢ አለመሆን አጥቶት በስሕተት ሰገደ ማለት የጻፋቸው ወንጌሎችም መልእክታትም ስሕተት አላቸው ማለት ነው።
ይህ ማለት ግን ሰው እንደ እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት አይደለም። እሱ በፍጹም እምነት ውስጥ ሳይሆን እሱ ማን መመለክ እንዳለበት ሳያውቅ ለእኛ ማሳወቅ አይችልምና። ስለዚህ በስሕተት ሰገደ ማለት ከፍተኛ ስህተት ነው።
ዮሐንስ ለመልአኩ የአክብሮት ስግደት ያቀረበው ለመላእክት መስገድ ተገቢ መሆኑን ስላወቀ ነው። መልአኩም ደግሞ #አትስገድልኝ ማለቱ የዮሐንስን ክብርና ማዕረግ መግለጡ ነው። ዮሐንስም በክብሩ ከመልአኩ እኩል ሆኖ ነበርና፥ እንድም በስልጣን በልጦት ነበር #ካህን ነውና ስልጣነ ክህነትህ ከእኔ ስልጣን ትበልጣለች ሲለው ነው..ስለ ስልጣነ ክህነት ታላቅነት " የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?" (1ኛ ቆሮ 6:3) ተብሎ ተጽፏልና።
ስግደት ደግሞ የበላይና የበታች መግለጫ ስለሆነ አንተ'ኮ በክብር ከእኔ እኩል ነህ። ስለዚህ ለእኔ ልትሰግድ አይገባም ቢለውም ዮሐንስ ግን ከመስጊድ ወደ ኋላ አላለም ትሁት ነውና። ይህን ማረጋገጥ ከፈለግን ራእይ 22:8-9 እንመልከት.. '' ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።'' (ራእ 22:8-9)
እንግዲህ ዮሐንስ ተሳስቶ ሰገደ ቢባል እንኳ ሁለት ጊዜ ይሳሳታል? የመጀመሪያው አንሶ? እንግዲህ አባባሉ የትሕትና አባባል መሆኑ ግልጽ ነው።
'' መላእክትም ከሰይጣናት የሚለያቸው አንዱ ይህ ነው። ሰይጣናት የማይገባቸውን ክብር ሁሉ በትዕቢት ይቀበላሉ ፤ መላእክት ግን የሚገባቸው እንኳን ቢሆን ስለ ትህትና ይተዋሉ። ክብርን ሁሉ ለጌታቸው ይሰጣሉ። '' ቅዱስ እንድርያስ ዘቂሳርያ
ይቆየን 🍋

❤3
እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ። አንዳንድ ሰዎች ኅሊናቸውን በመጣላቸው መርከብ በማዕበል እንደሚጠፋ እምነታቸውን አጥፍተዋል።
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:19
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:19
❤1
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ።
የበረከት የደስታ በዓል ይሁንልን።
ሐገራችንን ሰላም ያድርግል።
የበረከት የደስታ በዓል ይሁንልን።
ሐገራችንን ሰላም ያድርግል።
❤1👏1
የቅዱስ ገብርኤል አጋዥነት በግልጽ የሚያሳይ፣ ለተጨነቀች ነፍስ ትልቅ መጽናኛና እምነትን የሚያጽናና ታላቅ የእግዚአብሔር ቃል ነው 👉
የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ምልጃ፣ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እያሉጣ በረከት ሁልጊዜም በዙሪያችን ይስፈር፤ ከክፉ ሁሉ ያድነን 🌼
«የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ እዩ ጣሙም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።» — መዝሙረ ዳዊት 34:7-8
የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ምልጃ፣ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እያሉጣ በረከት ሁልጊዜም በዙሪያችን ይስፈር፤ ከክፉ ሁሉ ያድነን 🌼
❤3
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ስለ ነገረ መላእክት ባስተማረበት መጽሐፉ የመላእክት ተፈጥሮአቸው ልዩ ልዩ ነው። ምንም እንኳ መናፍስት ቢሆኑም የራሳቸው አካል አላቸው። ቁመታቸው ከምድር እስከ ጨረቃ የሚደርሱ አሉ ፣ ራሳቸው ብቻ የምድር ትልቁን ተራራ የሚያህል አሉ ፣ ሰውነታቸው በአይን የተሸፈኑ አሉ ፣ ልብሳቸው መብረቅ የሆነላቸው አሉ ወዘተ... እንግዲህ እነዚህን መላእክት ማክበርና መታዘዝ ተገቢ ነው።
"በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።" — ዘጸ 23:20
"በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።" — ዘጸ 23:21

🔥1
ቅዱስ ዑራኤል - የከበረው መልአክ
የህይወትን ጽዋ ለአበው የሚያጠጣቸው እርሱ ነው።
ጌታ አምላክ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በምድሪቱ የረጨ እርሱ ነው።
ጌታ አምላክ ኢየሱስ ሲወለድ በአብሪ ኮከብ ተመስሎ 3ቱን ነገስታት ወደ ቤተልሄም የመራቸው እርሱ ነው።
በሐዲስ ኪዳን እንደተጻፈው በመጠመቂያው ቦታ መልአኩ ሲገባ ውሃው ይነዋወጽ ነበረ ቀድሞ የገባውም የታመመ ሰው ከያዘው በሽታ ሁሉ ይድን ነበረ። ያ ውሀውን የሚቀድሰው መልአክ ዑራኤል እርሱ ነው።
ጌታ ኢየሱስ በዚህ በከበረ መልአክ ምልጃ ይማረን። አሜን።

❤2
‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡
መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።
ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡
ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።
ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡
‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡
‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡"
አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም

በሥዕሏም ፊት ሰገዱ ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክት ይደረግ ይሁን ይበሉ፡፡
🥰3
" ወቅድመ ሥዕላ ስግዱ ወኢሰገደሰ ላቲ ይደምሰስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝክረ ስሙ ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን ፥
በሥዕሏም ፊት ሰገዱ ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክት ይደረግ ይሁን ይበሉ፡፡"
1. የሰገዱበት ምክንያት (የሥዕላት ክብር)
በኦርቶዶክስ እምነት ለቅዱሳን ሥዕላት (በተለይም ለክርስቶስ፣ ለድንግል ማርያምና ለቅዱሳን ሥዕላት) የሚቀርበው ስግደት የአምልኮ ስግደት (Latria) ሳይሆን የጸጋ እና የክብር ስግደት (Dulia) ነው።
በሥዕሉ ላይ የሚታየውን አካል (ባለቤቱን) ለማክበርና ለመዘከር የሚደረግ መግለጫ ነው።
አማኙ በሥዕሉ ፊት ሲሰግድ ለቀለሙ ወይም ለጨርቁ/ለእንጨቱ ሳይሆን፣ በሥዕሉ ላይ ለተሳለው ቅዱስ አካል ያለውን ክብርና ፍቅር ይገልጻል።
2. "ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ..."
የሚለው ጠንካራ አገላለጽ
ይህ ዓይነቱ ጠንካራና የርግማን መልክ ያለው አገላለጽ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከተከሰቱት የአይኮኖክላስት (Iconoclasm - ሥዕላትን የማጥፋት/የመቃወም) ንቅናቄዎች እና ክርክሮች ጋር የተያያዘ ነው።
የታሪክ አውድ፡ በታሪክ ሥዕላትን አናከብርም የሚሉና ቅዱሳን ሥዕላትን የሚያረክሱ ወገኖች በተነሱበት ወቅት፣ የሥዕላትን ክብር ለመጠበቅና አማኙን ከክህደት ለመጠበቅ ሲባል እንዲህ ያሉ ጥብቅና የጠንካራ ቀኖና መግለጫዎች በድርሳናት ላይ ይጻፉ ነበር።
ፍርዱ፡ ይህ አገላለጽ እምነቱንና የሥዕላቱን መለኮታዊና መንፈሳዊ ክብር በአክራሪነት ለመጠበቅ የመጣ መንፈሳዊ ማስጠንቀቂያ (Anathema) ነው።
3. "በሰማይ ያሉ መላእክት ይደረግ ይሁን ይበሉ"
ይህ ደግሞ ምድራዊው ጸሎት፣ ውሳኔና ምስጋና ከሰማያዊው አምልኮ ጋር ያለውን አንድነት የሚያሳይ ነው። ቤተ ክርስቲያን በምድር የምትወስነውና የምታደርገው መንፈሳዊ ሥርዓት በሰማይ ባሉ መላእክት ዘንድ ተቀባይነትና ድጋፍ እንዳለው የሚገልጽ ቀመር ነው።

'' ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ''
'' ኢየሱስም፡— ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።''
- ማርቆስ 10:18 -
ይህንን ቃል የተናገረው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንዳንድ ወገኖች ይህንን ቃል በመጥቀስ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር አይደለም ፤ ቸር እግዚአብሔር ብቻ ነው ፥ ስለዚህ እርሱ እግዚአብሔር አይደለም ( ሎቱ ስብሐት) ይላሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር እግዚአብሔር እንደሆነ ምንም ጥርጥርም የለው። እንኳን ጌታችን፤ ብዙ ሰዎችም ሳይቀር ቸር ተብለዋል...እኛ ቸሮች እንድንሆንም ታዘናል።
🌿 '' ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤'' (መዝ 17:25)
🌿 '' ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።'' ( መዝ 110:5)
🙌 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው እንኳ ከሚሰራው ሥራ አንዱ የቸርነት ሥራ ነው።
'' የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣'' (ገላ 5:22)
እንዲህ ከሆነ የጌታችን ንግግር እንዴት ይታያል?
ጌታችን ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና በሰዎች ልቡና ያለውን ተንኮልና ቀናነት በራሱ ስለሚያውቅ ( ዮሐ 1፡49 ፣ ዮሐ 4፡18 ) የዚህንም ሰው የልቡን ሐሳብ አወቀ። ይህ ሰው በልቡ የኢየሱስን እግዚአብሔርነት ሳያምን እንዲሁ በአፉ #ቸር_መምህር-ሆይ ብሎ የተጠራው። ጌታችንም ከእግዚአብሔር በቀር ሰው በባሕርዩ ቸር ሊባል አይገባውም አለው ( ቅዱሳን ቸር ቢባሉ በጸጋ ነውና)
ጌታችንን ቸር ያለው ሰው እርሱ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ እንደሆነ ሳያውቅ - ሳያምን ነበርና እንዲሁ ቸር ብሎ የጠራው።
ስለዚህ አምላክነቴን እግዚአብሔርነቴን ሳታውቅ ሳትረዳ ስለምን ቸር ትለኛለህ? አምላክነቴን ተረድተህ ቸር በለኝ። ከእግዚአብሔር( ከእኔ) በቀር ቸር ማንም የለምና ማለቱ ነው።
👏 ኢየሱስ ቸር እንደሆነ ማስረጃዎች።
'' የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።'' (2 ቆሮ 8:9)
የኢየሱስን እግዚአብሔርነቱን አምነን ቸሩ አማኑኤል ሆይ እንበለው።
ይቆየን።

'' እግዚአብሔር ትንሽ ይናገራል ብዙ ያደርጋል፥ እኛ ግን ብዙ እንናገራለን ጥቂት እንሰራለን።'' ( ቅዱስ ሳዊሮስ )
በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከመጽሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ሌላ የተጻፉ ቅዱሳት መጽሐፍት አሉ። እነዚህ መጽሐፍት ሐሳባቸው ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተስማሚ ናቸው።
እነዚህ መጽሐፍት
ገድላት ፣ ድርሳናት ፣ የጸሎት መጽሐፍት እንዲሁም የምርምር (ስነ-ተፈጥሮ) መጽሐፍት ናቸው።

www.ethiopianorthodox.org የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን በpdf format ለማግኘት ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ
እግዚአብሔር ያቀደልህን ነገር ሳያሳካልህ ወደ እርሱ አይጠራኸም። ልክ እንደ ስምዖን አረጋዊ ከአልጋ ላይም ሆነ ማዳኑን ታያለህ።
በእግዚአብሔር ማመን
እርሱን መጠበቅ
በጎ ሥራን መሥራት
ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት ለነገይቷ ኢትዮጵያ
በእግዚአብሔር ማመን
እርሱን መጠበቅ
በጎ ሥራን መሥራት
ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት ለነገይቷ ኢትዮጵያ
🌸🌸🌸 “ወንድሞቼ! አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ አግኝቻታለሁ” (ቅዱስ ቶማስ) 🌸🌸🌸
◈ ቅዱስ ቶማስም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ የቅዱስ ጴጥሮስን ተግሳጽ ሲሰማ ቆየ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ተቈጥቶ የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ለቅዱስ ቶማስ ለማሳየት ሔዶ መቃብሯን ቢከፍት የእመቤታችንን ሥጋ ሊያገኘው አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ቆመ፡፡
✥ ቅዱስ ቶማስም ‹‹ወንድሞቼ! አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ አግኝቻታለሁ›› ብሎ እመቤታችን የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህ ሰበንም ሊቁ በመልክዓ ማርያም ድርሰቱ “ ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ፣ በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘአሣበ ሤጡ ዕፁብ …እመቤቴ ማርያም ሆይ ዋጋው እጅግ ብዙ በሆነና መዓዛው በሚጣፍጥ ሽቱ በሐዋርያት እጅ ለተገነዘው ንጹሕ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡” እንዳለው ቅዱሳን ሐዋርያት ሞገሳቸውን እመቤታችንን ለመቅበር የገነዙበት ነበር፡፡
◈ እነርሱም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤና ዕርገት እየተደሰቱ ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ በየሀገረ ስበከታቸውም ሕሙማንን ሲፈውሱበትና ገቢረ ተአምርሲያደርጉበት ኖረዋል፡፡ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤ እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን ልብስና በራሳቸው ላይ የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፤ቅዱሳን ሐዋርያት ለበረከት ተካፍለውታልና፡፡
🌸 እኔም ቅዱስ ቶማስ ነኝ እመቤታችን በክብር ስታርግ በመንፈሳዊ ዓይን ዛሬ ላይ ሆኜ አይቻለሁ።

ሕያውን አምላክ የተሸከመችው ታቦት፣ በምድራዊ መቃብር ውስጥ ታስራ ትቀር ዘንድ አይገባም፤ ልጇ ወደ ሰማያዊው ቅድስተ ቅዱሳን እንደገባ ሁሉ እንዲሁ፣ እርሷም የቃል ኪዳን ታቦት ሆና አብራ ገብታለች ።
ዘቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ።
ዘቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ።
❤3