The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
የጭራ መድኀኔዓለም ገዳም በ4ኛው መቶ ክፈለ ዘመን በአቡነ ሙሴ የተመሰረተ ገዳም ነው ።ገዳሙ 10 ቤተ መቅደሶች እዳሉትና 8 የተሰወሩ ቤተ መቅደሶችና 2 አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ቤተመቅደሶች ያሉት ሲሆን ይህገዳም በሰፊው አለም የሚታወቅበት 2 ፈዋሽ ፀበሎች ሲኖሩት በእምነቱም ከእምነቱም ውጭ ያሉ ሰወች በህክም መድሃኒት ያልተገኘላቸው በእነዚህ ፀበሎች እየተፈወሱ ምስክርነት የሰጡ ብዙወች ናቸው።
፨ሌላው ልዮ የሱባኤና የተመስጦ ቦታ ነው ፤መልክዐ ምድሩ እጅግ ሳቢና ማራኪ መንፈስን የሚያድስ ከመሆኑ ባሻገር ብርቅየ የዱር አራዊት ጭምር ያሉበት ቦታ ነው።
፨ታዲያ ይህቦታ መንገድ ባለመኖሩ ምክንያት መስጠት ያለበትን ጥቅም ሳይሰጥ ቆይቷል።በመሆኑም ይህን ቦታ የሚፈለገውን ጥቅም እንዲሰጥ ከማድረግ ባሻገር ቅርሱ ከአዳጋ ለመታደግ ጭምር ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለመስራት /ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት ቢደረግም የሚፈለገውን ያህል እርቀት መሄድ አልተቻለም ነበር ነገር ግን በ2017ዓ.ም በጀት አመት በቅርብ ቀናት ግብርና ፅ/ቤት እንዲሁም አጋሮቻቸው አስ/ ምቤቱን ጨምሮ በተደረገ ትብብር በኩል በተገኘ ድጋፋ ኮሚቴውን ማነሳሳትና ተጨማሪ በጀቶችን ለማፈላለግ በር የከፈተ በመሆኑ ወደስራ ተገብቶል።ስለሆነም ሁላችንም የበኩላችን በመወጣት ቅርሳችንን እንጠብቅ ታሪካችን እናስተዋውቅ እያልን መርዳት ለምትፈልጉ ፡
፨ከኮን የጭራ መድኃኔ ዓለም የጠጠር መንገድ ፕሮጀክት
1000336996647

የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት "የደብረ ሳህል የዶጊት ሚካኤል ወሀመረ ብርሃን ቤተ-ዮሐንስ አቡነ ተክለ ሀይማኖት የአረንጓዴ መስህብ ሀብት ልማት ፕሮጀክት ትውውቅ አደረገ።
ኮን፦ግንቦት 14/2017 ዓ.ም (ዋድላ ኮሙዩኒኬሽን)
በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት "የደብረ ሳህል የዶጊት ሚካኤል ወሃመረ ብርሃን ቤተ-ዮሐንስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የአረንጓዴ መስህብ ሀብት ልማት የፕሮጀክት ትውውቁን በዛሬው ዕለት የሀይማኖት አባቶች፣ የወረዳው አመራሮች እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት አካሂዷል።
ፕሮጀክቱ እውን የሚሆንበትን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም አገልግሎት ባለሙያ ዲ/ን ጌታዬ ፍቅር ፕሮጀክቱ ሊሟሉለት የሚገቡ መሰረተ ልማቶች፣ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ያሉ ምቹ ሁኔታዎች፣ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች በጥልቀት ያመላከቱ ሲሆን ፕሮጀክቱ አልቆ ወደስራ ሲገባ ማህበራዊ እሴትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስተሳስርና ለንግድና ለቱሪዝም መስህብነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተው ፕሮጀክቱ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑም በትውውቁ ተመላክቷል።
ውይይቱን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ወንድሜነው እና የዋድላ ወረዳ ቤተ-ክህነት ዋና ስራአስኪያጅ ሊቀ-ልሳናት እየበሩ ሀይሉ በጋራ በመሆን መርተውታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት በእጅጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመው ፕሮጀክቱ ስራ ላይ ከዋለ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይጠበቃል ያሉት ተሳታፊዎቹ ይህንን ፕሮጀክት ዳር ለማድረስ የመጀመሪያው ስራ መሬቱን ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ፣ አጠቃላይ የዲዛይን ስራ መስራትና ሌሎች የማስፈጸሚያ ስልቶችንና የሀብት ማፈላለግ ስራ በእጅጉ ይጠይቃል ብለው ወጭ የምንቆጥብበትን መንገድ በመፍጠር ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ።

በዋድላ ወረዳ የአሸንዳየ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።
ነሃሴ 7 /2017 ዓ.ም (ዋድላ ወረዳ ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት )
በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ወጣቶችና ልጃገረዶች ባህሉን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ ።
የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ወንድሜነው እንደገለፁት እንደዋድላ ወረዳ የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን ሳይበረዝና ሳይከለስ ባህሉን ፣ወጉን ፣ ልምዱንና አለባበሱን በጠበቀ መልኩ በአደባባይና በፓናል ውይይት የቅኔ ውድድር ጭምር ለማክበር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ። በተለይ ቅኔ ዋድላ ላይ የመጀመሪያ ምንጭ ሁኖ ታላቁ ፈላስፋ ዮሐንስ ገብላዊ የመሰረተው ስለሆነ በዓሉን በቅኔ ጭምር የምናከብረው ለሚቀጥለው ቅኔው በአለም ደረጃ የጥናትና ምርምር ማእከል አድርጐ ለማቆየት እንደ ወረዳ መንግስት እየሰራ ነው።
ሀላፊው አክለውም የአሸንዳየና ቡሄ ባህላዊ አጨዋወትን በትክክል የሚአሳዩ እንደወረዳ 40 ወጣቶችና 40 ልጃገረዶች ተመልምለው እስከ ነሀሴ 15 / 2017 ዓ.ም ድረስ በተግባር ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
አቶ ካሳሁን ወንድሜነው አያይዘውም የወረዳችን የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ባህል አስጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍና ለማስቀጠል ወጣቶቹና ልጃገረዶቹ የዋድላን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስና የፀጉር አሰራር በመሰራት ቱባ ባህሉን አጉልቶ ለማሳየት በሚያስችል መልኩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።
በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሌላ አካበቢን አለባበስና የፋሽን አለባበስን መልበስ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ጠቁመው የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ባህል መገለጫ አንዱ አለባበስ መሆኑን አቶ ካሳሁን ያሉ ሲሆን መላው የባዓሉ ባለቤት በሙሉ ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም የሚከበረውን የአሸንዳዬና ቡሄ በዓል የዋድላ ወረዳን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስ በመልበስ በዓሉን ማክበር ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።