WallagaUniversity_CCD
10.9K subscribers
18.3K photos
97 videos
20 files
110 links
This is Wallaga University Corporate Communications Directorate 's official Telegeam Channel.
Download Telegram
4👎1
ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት ሁለት ቢሊዮን አራት መቶ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺ ሁለት መቶ አርባ (2,406,195,240.00) ብር በጀት እንደተመደበለት ገለጸ።

ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት ለመደበኛ ሥራ፣ ለካፒታል ፕሮጄክት ማስፈጸሚያና ከመሥሪያ ቤቱ ገቢ ሁለት ቢሊዮን አራት መቶ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺ ሁለት መቶ አርባ (2,406,195,240.00) ብር በጀት መመደቡን የዩኒቨርሲቲዉ ፋይናንስና በጀት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዋቅጋሪ ጃራ ገለጹ።

ለበጀት ዓመቱ ከተመደበዉ:
#ለመደበኛ በጀት አንድ ቢሊየን አራት መቶ ሃምሳ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ (1,456,686,170.00) ብር፣
#ለካፒታል_ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ ስምንት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን (850,000,000.00) ብር እና ከመሥሪያ ቤቱ ገቢ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠኝ ሺ ሰባ ብር (99,509,070.00) ብር ጸድቋል ብለዋል።

ከጸደቀዉ ብር ሁለት ቢሊዮን አራት መቶ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ሁለት መቶ አርባ (2,406,195,240.00) ብር በጀት ዉስጥ ሁለት ቢሊዮን ሦስት መቶ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ አንድ መቶ ሰባ (2,306,686,170.00) #ከመንግሥት_ግምጃ_ቤት ወይም #ትሬዠሪ ሲሆን ብር ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠኝ ሺ ሰባ (99,509,070.00) ደግሞ #ከመሥሪያ_ቤቱ_ገቢ (#ዉስጥ_ገቢ) መሆኑን አቶ ዋቅጋሪ ገልጸዋል።

በመደበኛ በጀት ከተመደበዉ ዉስጥ #ለመማር_ማስተማር_ፕሮግራም ሥር ስምንት መቶ ዘጠና ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ አንድ መቶ ሰባ (892,385,170.00) ተመድቧል። ከዚህ ዉስጥ:
#ለተማሪዎች_ምግብ_አገልግሎት እና #መድሃኒት_አገልግሎት የሚዉል አራት መቶ አሥራ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺ (414,291,000.00)፣
#ለመማር ማስተማር ሥራ ማስፈጸሚያ፣ ለደመዝ እና ጥቅማጥቅም አራት መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን ዘጠና አራት ሺህ አንድ መቶ ሰባ (478,094,170.00) ተመድቧል።

#በጥናትና ምርምር ፕሮግራም ሥር ብር አርባ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ ሺህ (40,921,000.00)
#በማማከርና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሥር:
#የሥልጠናና_የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ብር ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አምሰት ሺህ (29,295,000.00)፤
#የህክምና_አገልግሎት ለመስጠት የሚዉል ደግሞ ብር አንድ መቶ ዘጠና ስምንት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ (198,377,000.00) ብር ተመድቧል።
#እንዲሁም #በሥራ_አመራርና_አስተዳደር ፕሮግራም ሥር:
ለድጋፍ አገልግሎት መስጠት የሚዉል ብር ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስምንት ሺ (292,708,000.00) ተመድቧል።

የተፈቀደዉ በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ በፋይናንስና አስተዳደር መመሪያ መሠረት ሥራ ላይ እንዲዉል ዘርፎችና የሥራ ክፍሎች አዉቀዉ እንደያስፈጽሙ ይጠበቃል በማለት የዩኒቨርሲቲዉ ፋይናንስና በጀት ሥራ አስፈጻሚ ገልጸዋል። በየዘርፉና በፕሮግራሞች ሥር የተደረገዉን ዝርዝር የበጀት ክፍፍል ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል።
6🔥1
👍72
የትምህርት ምዘና ጥራት እና ዝመናን ለማሻሻል ያለመው አህጉራዊ ጉባዔ በኢትዮጵያ!!

41ኛው የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ጉባዔ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

"የትምህርት ምዘናን ለማሸጋገር ጥራት ያለው ትምህርትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ " በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው 41ኛው የአፍሪካ ትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባዔ፤ ከነሀሴ 19 እስከ ነሀሴ 23 2017 ለአምስት ቀናት የሚደረግ ይሆናል።

ጉባዔው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዲሁም ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በርካታ እንግዶች በተገኙበት የመክፈቻ ፕሮግራሙ ተከናውኗል።

በጉባዔው ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፥ ዓለም በየዕለቱ በፍጥነት ስልጣኔን ተከትላ በለውጥ ጎዳና ላይ ባለችበት በአሁን ወቅት፤ አፍሪካ የወደፊቷን በጥንቃቄ መስራት ይኖርባታል ነው ያሉት።

ስለ አህጉራችን መሰረታዊ እና ዘላቂነት ያለው ለውጥ መስራት ያለብን ዛሬ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ግብርናው ዘርፍ፣ በመሰረተ ልማት እንዲሁም በትምህርት ተደራሽነት ባለፉት 5 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን ማከናወኗን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ አያይዘው እንደገለጹት በኢትዮጵያ በሁሉም አከባቢዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እኩል ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዚህ ጉባዔ በትምህርትና ምዘናና ሥርዓት ዙሪያ ያሉ እሳቤዎች፣ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ልምዶች የሚቀርቡበት መድረክ ነው ብለዋል።

በምዘናና ፈተና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ፤ ዘላቂ የሆነ ትብብርን በመፍጠር በጋራ መስራት የጉባዔው ዋና አላማ መሆኑን አንስተዋል።

#EBC እንደዘገበዉ
2
Dameelee garaagaraan hojiileen egeree Afrikaa murteessuu danda’an raawwachuun barbaachiisaadha- Pirofeesar Birhaanuu Naggaa

Finfinnee, Hagayya 19, 2017 (FMC) – Addunyaa jijjiiramaa jirtu keessatti hojiilee egeree Afrikaa murteessuu danda’an tumsan raawwachuun barbaachiisaadha jedhan Ministirri Ministeera Barnootaa Pirofeesar Birhaanuu Naggaan.

Gamtaan Madaallii Barnootaa Afrikaa Konfiraansii waggaa 41ffaa magaalaa Finfinneetti gaggeessaa jira.

Pirofeesar Birhaanuu Naggaan wayita kanatti, yeroo ammaa addunyaan qaroomina irra waan jirtuuf galmaa fi bakka gahuumsa egeree Afrikaa yaaduun murteessaadha jedhan.

Dameelee garaagaraan egeree Itiyoophiyaas ta’ee Afrikaa haala amansisaan ijaaruuf tumsaan hojjechuun barbaachisaa ta’uu dubbataniiru.

Fuulduratti jijjiirama Afrikaa hammatee egeree ishee murteessuu danda’an Qonna, Misooma Anniisaa, Bu'uuraalee Misoomaa fi damee Barnoootaa irratti hojjechuu gaafata jedhan.

Daayrektarri Olaanaa Tajaajila Madaallii Barnootaa fi Qormaataa Dooktar Isheetuu Kabbadaa gamasaaniin, Madaalliin barnootaa milkaa’ina barnootaa waliigalaaf barbaachiisaadha jedhan.

#FMC Afaan Oromootu gabaase
2