Werabe university muslim students union
1.51K subscribers
677 photos
164 videos
73 files
602 links
This is the official telegram channel of wrumsu.

Email: wrumsu12@gmail.com
twitter: http://twitter.com/wrumsu
Telegram: @wrumsu
Telegrambot:@wrumsu_feedback_bot
Download Telegram
​✨ ታላቅ የምስራች ለወራቤ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በሙሉ! ✨

​السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

👉​እነሆ የ2019 ዓ.ል የቂርዓት ፕሮግራማችንን ማስጀመርያን እና ለእናንተ ለውድ ወንድምና እህቶቻችን የተዘጋጀውን ልዩ Welcome Program ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው

👉​በፕሮግራማችን ላይ በተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን) የተዘጋጀ ልዩና መንፈስን የሚያድስ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል.
​ከጥዑም አንደበታቸው የሚወጡ ጠቃሚ ተግሳፆችንና ምክሮችን በመቅሰም የመንፈስ ምግብ እንድንሸምት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል.

🕌​ቦታ፦ ሰልማኑል ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ

🕧​ቀን እና ሰዓት፦ ዛሬ ጁመአ ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ

⭐​እጅግ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንዳያመልጥዎ.

​ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ.
⭐الدآل عل الخير كفاعله.⭐
❤24
🎙የዳዕዋ ፕሮግራም!

🔻በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=7b970bcacee9ec3de3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7❤1
Updated program
👍12❤3🤩1
Forwarded from Werabe University
#ማስታወቂያ

ቀን፡-29/01/2019

1ኛ) ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ1ኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ

2) በ2018 ትምህርት ዘመን የሪሜዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አጠናቃችሁ የማለፊያ ነጥብ ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በተራ ቁጥር 1) እና 2) የተገለጻችሁ ተማሪዎች የ1ኛ አመት 1ኛ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 16 እና 17/2019 መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
- ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሜድያል) ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ወደፊት በመገናኛ ብዙሃን የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን።

በተራ ቁጥር 1 የተገለጻችሁ ተማሪዎች:-
◆ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ክልላዊና በሔራዊ ፈተና ሰርተፍኬት እና ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና አንድ የማይመለስ ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል።
◆ ሁሉም ተማሪዎች የእስፖርት ትጥቅ፣አንሶላ፣ብርድ ልብስና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።
◆ በተለያየ ምክንያት በ1ኛ አመት 1ኛ መንፈቅ የመልሶ ቅበላ ሞልተው የወጡ የመጀመሪያ ዲግሪ የመደበኛ መርሐ ግብር ተማሪዎች ጥቅምት 19/2019 ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
◆ ጥቅምት 18/2019 የቅጣት ምዝገባና መማር ማስተማር የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
◆ ሌሎች መረጃዎችን በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ የሚገለጹ ስለሆነ የዩኒቨርሲቲውን ፌስቡክ ገጽ ይከታተሉ።

ዕውቀት ለልህቀት!
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
❤8😭1
​🌺 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 🌺


​🌸 ውድ እና የተከበራችሁ እህቶቻችን!

​እነሆ ያላወቅነውን የምናውቅበት፣ ያልተማርነውን የምንማርበት እና የመንፈስ እርካታን የምናገኝበት ልዩ የእህቶች ለእህቶች የሙሀደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል! 

​‼️ መች? የት? በምን ርዕስ? አትሉም?
​ባትሉም በለመድነው በታወቀው ስፍራችን ተገኝተን በአላህ ፈቃድ በሚከተሉት አስተማሪ ርዕሶች ላይ ልንተዋወስና ልንማማር ቀኑ እስኪደርስ በጉጉት እየጠበቅን ነው፦ 

​👉 ስለ እስልምና እና ተውሂድ (ልዩ ዳዕዋ)
👉 ስለ ሴት ሰሀብያት አርአያነት ያለው ታሪክ
👉 ልዩ ልዩ አነቃቂና ማራኪ ግጥሞች
👉 እና ሌሎች በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች 

​📅 ቀን፦ እሁድ (01/02/2019 ዓ.ል)
⏰ ሰዓት፦ ጠዋት 3:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ  ሰልማን አል-ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ

​🌸 ለኢልም እንደሚጓዙ እግሮች ጠንካራ፣
ለኢልም እንደሚከፈቱ አእምሮዎች ብሩህ፣
ኢልምን እንደሚናፍቁ ልቦች ቅን የሉም! 🌸

​✨ዉድ እህቶች  በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችዋል!

@wrumsu
❤14
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ለ2 ወራት የሚቆይ ልዩ ኮርስ፦

(ወጣ ያለ ሀሳብ ስለሆነ ሙሉ ብታነቡት።)
ይህ ኮርስ በአላህ ፍቃድ በተለያዩ ኢስላማዊ የዒልም ዘርፎች ላይ ያለንን እውቀት ከፍ ለማድረግ፣የንባብ ልምዳችንን ለማዳበር እና ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም አጋዥ ነው።በሂደቱ ላይ ፈተናዎች የሚኖሩ ሲሆን ተደምረው ከ300 በመያዝ ከፍተኛ ውጤት ለሚያስመዘግቡ 30 ሰዎች ተሸላሚ የሚያደርግ ይሆናል።ለሁሉም ተሳታፊዎች ደግሞ የውጤት ካርድ ይዘጋጃል።

የኮርሶቹ ይዘት እንደሚከተለው ሆኖ በአማርኛ ቋንቋ ለየብቻ በPDF ወይም በ PPT የሚቀርቡ ይሆናሉ።
1,ከዓቂዳ:ኹዝ ዐቂደተክ
2,ከፊቅሂ:ስለ ውርስ ህግጋት(መዋሪስ)
3,ከአዳብ:ሙንከራት
4,ከሲራ:ከረሱል(صلى الله عليه وسلم)ታሪክ በጥቂቱ።
ንባብ በራሳችሁ ሆኖ አንዳንዴ live ልንገናኝ እንችላለን።

ሽልማቱ የተዘጋጀው በስፖንሰር አማካኝነት ሲሆን በቅደም ተከተል፦

አንደኛ ለወጣ/ች:ኪታብ እና 60,000ብር
ሁለተኛ:ኪታብ እና 50,000ብር
ሶስተኛ:ኪታብ እና 25,000ብር
አራተኛ:ኪታብ እና 10,000ብር
አምስተኛ:ኪታብ እና 5000ብር

ስድስተኛ:ኪታብ እና 4000ብር
ሰባተኛ:ኪታብ እና 3000ብር
ስምንተኛ:ኪታብ እና 2000ብር
ዘጠነኛ:ኪታብ እና 1500ብር
አስረኛ:ኪታብ እና 1000ብር
ከ11 እስከ 30ኛ ለሚወጡ ደግሞ የኪታብ ሽልማት ይሆናል።

የመመዝገቢያ እና የሙሉ ሂደቱ ዋጋ:300 ብር ነው።
የኮርስ ግሩፑ link፦https://t.me/liyucourse
ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች እዚያው ግሩፑ ላይ ታገኛላቹ።

በዚሁ አጋጣሚ:fresh ተማሪዎች ካላችሁ የpsychology,logic & english ኮርሶች tutorial እና ppt ሊዘጋጅ ስለሚችል በ @zidni1 አሳውቁኝ።
❤12
🕌🕌السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🕌🕌

🗓በ2019 ዓ.ል አዲስ ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ል ወራቤ ዩኒቨርስቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ::

✏️በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለእዚህ  እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን !!

✏️የወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን እያሳወቀ  የናንተን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::

ማንኛውንም information ለማግኘት እነዚህን የተመደቡ የጀመአ አባላቶችን Contact ማድረግ ትችላላችሁ::

✅ አ/ሀሚድ ረሺድ  +251955354953

✅አ/ሀኪም ሙሰማ +251919289727

✅አባስ ኢድሪስ +251972984344 (ormomifa)


የእህቶችን ስልክ በ: +251919289727 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::
  
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ራሳችሁን እና ማህበረሳባችሁን የምትጠቅሙበትን እውቀት እና ልምድ ትቀስሙ ዘንድ ተመኘን::

https://t.me/wrumsu
❤14👍11
✨አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ✨

ዉድእና የተከበራችሁ senior ሙስሊም ተማሪዎች እንዴት ናችሁ?
እነሆ ምትክ እህቶች እና ወንድሞች(fresh ተማሪዎች) ሊመጡ ጥቂት ቀናቶች ናቸዉ የቀሩት እነሱንም ለመቀበል ከጀምዐዉ ጋር መስራት ምትፈልጉ senior እህቶች እና ወንድሞች በሙሉ የዚህ ኸይር ስራ ተካፋይ እንድትሆኑ እስከ ሀሙስ ቀን 12 ድረስ ይህንን @wrumsu_feedback_bot ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ትችላላችሁ።
من كان لأخيه كان الله له
Whoever is there for his brother, God will be there for him."

📢መስታወሻ: ስትመዘገቡ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር እንዳይረሳ
👉👉@wrumsu_feedback_bot
👍5
🌿 بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ 🌿
📚 ለወጣቶች በተለይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚያመሩ 📚
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ከወጣቶች ውስጥም በተለይ ወደ ትምህርት ተቋማት፣ ጥሩም መጥፎም ሰዎች ወደሚገኙበት ዩኒቨርሲቲ ያመራ ወጣት ይበልጥ ምክር ያስፈልገዋል።
🤲 ነፍሲያውን መታገል ይጠበቅበታል። ኸይርና ሸሩን፣ የሚገባውንና የማይገባውን፣ ኢስላም የሚፈቅደውንና የሚከለክለውን ማወቅ አለበት።
⚔️ ወደ ጦር ሜዳ የሚሄድ ሰው ባዶ እጁን አይሄድም፤ ስንቅ ይዞ፣ በቂ ትጥቅ ታጥቆ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።
📖 ትምህርት በራሱ የትጋትና የጂሃድ አይነት ነው። በተለይ እንደኛ ሀገር ሙስሊምና ካፊር፣ ጥሩ ፀባይ ያለውና መጥፎ ፀባይ ያለው አንድ ላይ ሆነው በሚማሩበት የትምህርት ተቋም ላይ ሲገኙ ይበልጥ ጠንቀቅ ማለት ያስፈልጋል።
⚠️ የዱንያ ትምህርት እውቀት ለመጨመር ብሎ ሄዶ፣ ስነምግባሩን አጥቶ፣ ዲኑን አጥቶ የሚመለስ ሰው አለ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤲 أَللَّهُمَّ احْفَظْنَا فِي دِينِنَا
🌿 አላህ ይጠብቀን! 🌿
📌 ለሌሎችም ይደርስ ዘንድ ሼር ያድርጉ!
❤11🔥4🎉1
የአንዳንድ ሰው ንግግር ግን እንዴት ነው ሚጣፍጠው በረቢ...
አላህ የኡስታዛችንን እድሜ ያርዝመው ኸይር ጀዛቸውንም እሱ ይክፈላቸው 🤲

የዛሬው ዳዕዋ ያመለጣቹ በጣም ነው ማዝነው ግን Record ለቅላቹሀለው በእርግጥ በአካል እንደመገኘት ባይሆንም ማዳመጡ በላጭ ነው

መጨረሻ ላይ የተነሱት ጥያቄዎች ለኛ በተለይ ለተማሪዎች አሪፍ ጥያቄዎች ናቸው ማገናዘብ ለሚችል ከግልፅም በላይ ግልፅ የሆነ መልስም ተሰቷቸዋል

@wrumsu
👍25❤9
🕌🕌السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🕌🕌

🗓በ2019 ዓ.ል አዲስ ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ል ወራቤ ዩኒቨርስቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ::

✏️በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለእዚህ  እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን !!

✏️የወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን እያሳወቀ  የናንተን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::

ማንኛውንም information ለማግኘት እነዚህን የተመደቡ የጀመአ አባላቶችን Contact ማድረግ ትችላላችሁ::

✅ አ/ሀሚድ ረሺድ  +251955354953

✅አ/ሀኪም ሙሰማ
+251919289727

✅አባስ ኢድሪስ
+251972984344 (ormomifa)


የእህቶችን ስልክ በ: +251919289727 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::
  
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ራሳችሁን እና ማህበረሳባችሁን የምትጠቅሙበትን እውቀት እና ልምድ ትቀስሙ ዘንድ ተመኘን::

https://t.me/wrumsu
👍13❤2
❤21
السلام عليكم ورحمت الله
የሙሀደራ ፕሮግራም
ለሁሉም አዲስ ገቢ ፍሬሽማን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ እንኳን አላህ በሰላም አገናኘን እያልን በዛሬዉ እለት ከመግሪብ ሰላት በሇላ ከጀመአ ጋር ትዉዉቅ የምታደርጉበት የሙሀደራ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ እራት በልታቹ ከካፌ መልስ እንድትታደሙ በአላህ ስም እንጠይቃለን::
የመስጂድ አድራሻ ጥቆማ:- አዲስ እየተሰራ ባለዉ በር በኩል ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሳትሉ ቀጥታ መንገዱን ይዛቹ ስትመጡ ታገኙታላቹ::
👍12🤩6👌2❤1🥰1
ውድ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ senior/fresh ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ማነኛውም ጥያቄ ወይም ሀሳብ አስተያት ካላቹ ይህንን ቦት 👉👉 @wrumsu_feedback_bot በመጠቀም በአላህ ፍቃድ የምትፈልጉትን ማግኘት ትችላላቹ።

ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመኣ
https://t.me/wrumsu
❤6
السلام عليكم ورحمت الله
     የሙሀደራ ፕሮግራም
ለሁሉም አዲስ ገቢ ፍሬሽማን ተማሪዎች በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን ዛሬ ማለትም በ ዕለተ ማክሰኞ ከመግሪብ ሰላት በሇላ ለሁለተኛ ጊዜ ሚደረግ የሙሀደራ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ እራት በልታቹ ከካፌ መልስ እንድትታደሙ በአላህ ስም እንጋብዛለን
የመስጂድ  አድራሻ ጥቆማ:- አዲስ እየተሰራ ባለዉ በር በኩል ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሳትሉ ቀጥታ መንገዱን ይዛቹ ስትመጡ ታገኙታላቹ::
❤4👍3👌1
ማስታወቂያ

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን በደህና መጣችሁ እያልን የሰልማነል ፋሪስ መስጂድ በኩል ጀመዓችንን ለማገዝ በተቋቋመዉ የሱቅ አገልግሎት እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናቀርባለን ።


{ባልዲ🪣፣ መዘፍዘፊያ፣,የበሶ መበጥበጪያ,መጥረጊያ,መወልወያ,ሳሙና, ደብተር📕✏️ ..ሌሎችም የሸቀጣሸቀጥ አቅርቦት አለን!!)


✍በይተልማል ስትራክቸር
    
የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን
ስልክ: +251969888602

ጀመኣው በሚያደርገው በማነኛውም እንቅስቃሴ ላይ ሀሳብ አስተያት ካለ ይህንን @wrumsu_feedback_bot በመጠቀም ያድርሱልን
❤5👍2👌1
ግጥም አይደለም

ርዕስ:- ሰልማነል ፋሪሴ

በግቢ ህይወትህ የመመራትህ ሚስጥር፣ ያለመዉደቅህ የልብህ መጠንከር ሚስጥር ምንድነዉ ቢሉኝ፣ እኔም አልኳቸዉ ሚስጥሩ አንድ ነዉ።
ከጀርባዬ አንድ ቤት አለ። ብርሀኑ የሚያፈካኝ፣ ጨለማዉ የሚያጨልመኝ፣ ከፍታዉ ከፍ የሚያደርገኝ፣ ዉድቀቱ የሚጥለኝ፣ መሙላቱ የሚሞላኝ፣ መጉደሉ ሚያጎድለኝ፣ የተበታተነ አልባሌ ማንነቴን ካልነበረበት ሰብስቦ ነፍስ ዘርቶ ሰዉ ያደረገኝ፣ ብደሰት ማመሰግንበት፣ ቢከፋኝ ምፅናናበት፣ ራሳቸዉን ጊዜያቸዉን አቅም ጉልበታቸዉን ሰዉተዉ ከኔ በላይ ለኡማዉ የሚሉ ጀግና እና ቆራጥ ወንድም እህቶችን ያገኘሁበት።

ስስቴዋ መስጂዴ ሰልማነል ፋሪስ
ምናልባትም እኮ የሰዎች ዘለፋ፣ ወቀሳ እና ስድብ፣ ዉሸት እና ቅጥፈት ግንብን የመናድ ሀይል ቢኖራቸዉ የሚናራህ ጨረቃ እንኳ ባልተረፈኝ ነበር። ግና ሀቅ ሁሌም ሀቅ ነዉ።
አብሽር ቅንጣት ታህል ስጋት እንዳይገባህ። መስጂዴዋ እዚ እኮ ደርሰናል። ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁን እና አንተን በመኻደም ፍቅር ቀልባቸዉን በጣሉ ወንድም እህቶች ዉለታ እዚ ደርሰናል።
በነዚያ በቀደምቶቹ የወቀሳን ቸነፈር፣ የዘለፋን በትር፣ የቅጥፈትን ህመም ዋጥ አድርገዉ ላንተ ሲሉ አንገታቸዉን ደፍተዉ ቀና ባደረጉህ ወንድሞች እዚ ደርሰናል።
እኔም የድርሻዬን የነሱን ባልደርስም አማናዬ ነህና እጠብቅሀለዉ። ያ ቀን እስኪመጣ ሀቁ ሁሉ ወጥቶ ቀጣፊ አንገት ደፍቶ አላህዬም ፈርዶ እዉነታዉ ተገልጦ፣ ልክ እንደ ጁመአ ሰላት ቤቶችህ ተጣበዉ በረንዳ እስክወጣ እጠብቅሀለዉ።
የአይኔ ማረፍያ ሰልማነል ፋሪሴ፣ እስከዝያዉ ድረስ ዉድቀትህን ለሚመኙ ግን እንዲህ በላቸዉ፦
ልጆቼ እኮ አሉ ለኔ ሚዋደቁ፣ ከክብራቸዉ ክብሬ የበለጠባቸዉ፣ ደምና ስጋቸዉን ጨርሰዉ አጥንታቸዉን ሊሰጡኝ የተዘጋጁ ልጆች አሉኝ በላቸዉ።
እነሱ ቢሄዱ እንኳ እነሱን የሚያስንቅ ግለቱ የሚፋጅ እሳት የሆነ ትዉልድ ተክተዉ እየሄዱ ነዉ በላቸዉ።
ለኔ መልፋት ሀሴትን እንጂ ድካምን የማይሰጣቸዉ ትዉልዶች እየመጡ ነዉ በላቸዉ።
አብሽር አለንልህ። እኛ ወድቀን አንተ ከፍ በል፣ እኛ ደክመን አንተ እረፍ፣ እኛ ጨልመን አንተ ብርሀን ሁን። ያንተን ከፍታ እስካለየን የመጣንበት ትምህርትስ መች ሊጥመን። ከቶ ብቻ ቆየም ዘገየም ሀቅህ ወጥቶ ያሳየኝ።
ስላንተ እንዲሁ በደረቁ ፅፎ ማቆም ቢያቅተኝ እቺን አጭር ግጥም ጀባ ብዬሀለዉ።

መስጂዴዋ የኔ መከበርያ የአኼራ ደሞዜ
እጠብቅሀለዉ አጥንቴ ተጣብቆ ግርጥት እስኪል ወዜ
ባንተ ከመጡብኝ አልሳሳም ለነፍሴ
ተረክቤሀለዉ ከነ ሙሉ ዝናህ
አስረክብሀለዉ ከኔ በላይ ለፍቶ ተግቶ ለሚያቀናህ
ሰልማነል ፋሪስ ስምህን በልቤ ፅፌ አኑሬዋለዉ
እስከለተ ሞቴ በጣጣጣም ወድሀለዉ::           
✍️ 🖋️:- አብዱልሀሚድ ነኝ የሰልማነል ፋሪስ ወዳጅ
❤36👍7🔥3👌3👏1
بسم الله الرحمن الرحيم

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

🌟​የ ዳዕዋ እና የ well come ፕሮግራም ጥሪ🌟

📚​ውድ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ  ሙስሊም ተማሪዎቻችን በሙሉ

👉ዩኒቨርሲቲ የዕውቀት አድማሳችሁን የምታሰፉበት ስብዕናችሁን የምትገነቡበት እና ለነገው መልካም ህይወታችሁ መሰረት የምትጥሉበት ታላቅ እድል ነው.

👉በዲኑ ጠንካራ እና በአካዳሚ የበለፀገ ትውልድን ማፍራት ዓላማው የሆነው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ኢማናችሁን ጠብቃችሁ በትምህርታችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ እናንተን ለመርዳት ዝግጁ ነው።

👉​በዚህ የአዲስ ምዕራፍ ጉዞ ላይ በመስጂዳችን ሰልማን-አልፋሪሲ ሞቅ ያለ አቀባበል ልናደርግላችሁ ልንተዋወቃችሁ እና በቆይታችሁ የሚያስፈልጓችሁን መረጃዎች ልናካፍላችሁ ዝግጅታችንን ጨርሰናል.

​📌 በፕሮግራማችን ላይ..

1.የ ቁርአን ቲላዋ

2.በተወዳጅ ኡስታዞቻችን ጥዑም እና አንደበትን የሚያርሱ ዳዕዋዎች.

3.ግጥም

4.ስነፅሁፍ

5.ከSenior ተማሪዎች ​ስለ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ልምድ ማካፈል እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚና አስፈላጊ ምክሮች.

🕌​ቦታ ሰልማን አል ፋሪሲይ የተማሪዎች መስጂድ
⏱️​ቀን እና ሰዓት ፦በቀን 20/02/19 ዕለተ ጁመአ አመሻሽ ከ(11:30) ቡሃላ
❤13🎉5👍2🔥2
ኢንሻ አላህ ፕሮግራሙን በማስመልከት ከመግሪብ በኋላ የ live ስርጭት ይኖረናል

@wrumsu
👍5👌2