።Word of God
474 subscribers
511 photos
1 video
54 links
A Christian's telegram channel got a daily verse plate,
Follow us on Instagram: @word_o.f_god
Like our page on Facebook: https://www.facebook.com/wordofGodk
Contact us: @Wordof_God_bot
Website: wordofGod.com
YouTube: https://youtube.com/c/KishaChristian
Download Telegram
“እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።”
— ቆላስይስ 3፥17

“And whatsoever ye do in word or deed, do all in the name of the Lord Jesus, giving thanks to God and the Father by him.”
— Colossians 3፥17 (KJV)
@wordof_God
1👍1
❝. . . .በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤❞
—ቆላስይስ 3:2-3

. . .So think about the good things that are there in heaven above. Do not think only about things that are on the earth. Remember that your old nature has died. God is keeping your new life safe with Christ. You have that new life because you belong to Christ. One day, Christ will show himself clearly to everyone. Then everyone will see that you are with him. They will see that you also are great, like he is.
—Colossians 3:2 - 4 EASY
@wordof_God
👍2🔥1
እህህ ዝምታ እኮ እንዴት ዝምታ

" .. ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።"
(ወደ ዕብራውያን 12:24)

— እርሱ ዝም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ዝምታ ብቻ፤ ቃል የለም መናገርም የለም ከሰቆቃው በቀር፥ ደሙ ግን በሃይል ይጮሃል። የአቤልስ ደም "የፍትህ ያለ" እያለ ወደ እግዜሩ ይጮሃል። የክርስቶስ ደም ግን "ተቀበላቸው" . . . . . .❝ልጅ አድርጋቸው❞ . . . .❝ይቅር በላቸው❞. . . . . . . . .❝ካህናት አርጋቸው❞(ራዕይ 5:9-10) እያለ ወደ ማደሪያው ወደ አርያም ያስተጋባል።

እያንዳንዱ ወንጀለኛ በአሰቃቂው የመስቀል ሞት ሲገደል የእያንዳንዷን ደቂቃ አየር ማስገባት እና ማስወጣት በስቃይ ሰቆቃ ያሳልፋል። የሰራውን አረመኔያዊ ክፋት እያወራረደ፣ ከታደለ ነፍሱ በጊዜ ከወጣች እፎይታን ታገኛለች። (መቼስ "ከመተንፈስ ትንሽ ልረፍ አሰኪ ሞቼ ልመለስ" አይባል እንግዴ!) . . . . . .ነውር የማያውቀው የኔ ትሁት ጌታ በመስቀል ሆኖ የሚያስታውሰው፤ የሚያወራርደው አንዳች ስኳ ሳይኖረው፤ የእኔኑ በደል መሆኑ ያሳብዳል እንጂ አያስታብይም ዝምም አያስብል . . . . .እህህ ዝምታ እኮ እንዴት ዝምታ

በሩቁ ከቆሙት ታዛቢያን ህዝብ አንስቶ አጠገቡ እስከተሰቀለው ድረስ ሁሉም "ለምን አይወርድም፣ ለምንስ እራሱን አያድንም??? አይችልም እንዳይባል ሙታን ሲያስነሳ በገሃድ ታይቷል። ሃሳቡ ምንድነው?" እያሉ ቢጎተጉቱትም . . . . . . . ሌላው ደረቱን እየደቃ ዋይ ዋይ ሲል። የገዛ እናቱ ዘጠኟን ወር በሆድ ተሸክማ በምጥ ወልዳ ጡቶቿን አጥብታ ያሳደገችው ልጇ በሐሠት ተወንጅሎ፣ በግፍ ሲገደል በነፍስ በውስጠቷ ሰይፍ አለፈ።

ይሄ ሁሉ ከእስራኤል መንግስት እርቄ አህዛብ፣ ከእግዚአብሔር ተለይቼ ያለ ክርስቶስ የሆንኩትን ምስኪን ተስፋ ቢስ ተላላ፣ የበረሀ ወይራ ልጅ አርጎ ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መሆኑ . . . . . .ደግሞ እሱን እንድመስለው መጥራቱ . . . . . . . ዝምም አያስብል . . . . .እህህ ዝምታ እኮ እንዴት ዝምታ . . . . .ታላቅ ሚስጥር ፤ ድንቅ ተዓምር. . . .!!!

" እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:6)

ዘመዴ ሰው ሆኖ ዝቅ ብሎ
ቤዛዬ ነው ሞቶ ሞቴን ገድሎ
በፍፁም እሽታው ሰውን ከአብ አስታርቆታል
ምስክር ነኝ እስከ ምድር ዳር

ዝም አልልም
ኢየሱሴን ልሸሽገው ዘንድ አልችልም፤

Blessings 🧡
https://youtu.be/_zPY6IBTTMU
ኢየሱስ በዕለተ ሐሙስ!
ከYeamlak Chernet

"ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው። እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር። ኢየሱስም፣ አብ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር እንዳደረገለት፣ ከእግዚአብሔር እንደ ተላከና ወደ እግዚአብሔርም እንደሚመለስ ዐውቆ፣ ከእራት ተነሣ፤ መጐናጸፊያውን አስቀመጠ፤ ወገቡንም በፎጣ ታጠቀ። ከዚያም በመታጠቢያው ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር እያጠበ በታጠቀው ፎጣ ያብስ ጀመር። … እግራቸውን አጥቦ ካበቃ በኋላም፣ ልብሱን ለብሶ ተመልሶ በቦታው ተቀመጠ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና። እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል። እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው፣ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ" (ዮሐንስ 13:1-6፣ 12-17)።

አንድ መጋቢ በአንድ ወቅት በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ ከላይ የተጠቀሰውን [የመጽሐፍ ቅዱስ] ጥቅስ ባብራሩበት ጽሑፍ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፤ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ኖሮኝ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ባስተምር ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ከትምህርት ቤቱ ሲመረቁ የምሰጣቸው ጥቁር ጋወን ሳይሆን ፎጣ እና ማስታጠቢያ ነበር። ምክንያቱም አገልጋይነት በሌላው ላይ መሠልጠን ሳይሆን ዝቅ ብሎ ማገልገል ነውና።

ኢየሱስ ስለ ኀጢአታችን በመስቀል ላይ ዋጋ ከመክፈሉ በፊት በነበሩት የመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብ ነበር።

ዝቅ ብሎ፣ በብዙ አቧራ ያደፈውን እግራቸውን ካጠበላቸው ከእነዚህ ደቀ መዛሙርቱ መካከል በጀርባ እርሱን ለመሸጥ የሚደራደር ሰው ነበር፤ ፈጽሞ እንደማያውቀው የሚክደው ሰው ነበር፤ እርሱን በመከተል የሚደርስባቸው መከራ ፈርተው በአንድ ምሽት ጥለውት የሚሸሹ ነበሩ።

እርሱ [ኢየሱስ] ግን እነዚህን ሁሉ በፍጹም ፍቅሩ ይወድዳቸው ነበር። [ሆኖም] የእርሱ ደቀ መዛሙርቱን መውደድ የድርጊታቸውን ትክክለኛነት አያሳይም፣ የእርሱን ፍቅር ወሰን አልባ ፍቅር እንጂ።
እርሱ [ኢየሱስ] ግን ዝቅ ብሎ የሁሉንም እግር በማጠብ ትህትናን ያስተምራቸው ነበር። ይሁን እንጂ፣ የእርሱ እግራቸውን ማጠብ የማናቸውንም የስህተት አካሄድ ልክ አያደርገውም።

ዮሐንስ በጻፈልን የወንጌሉ ዘገባ ላይ ስለ ኢየሱስ እግር ማጠብ ከመናገሩ በፊት እንዲህ ብሎ ይነግረናል "ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ" (13:1)። ኢየሱስ ራስ ወዳድ አልነበረም። ሁሉን ትቶ እንደመጣ ሁሉ ሁሉን ትቶ እንደሚሄድ ያውቅ ነበር። ክብርን የሚሻው ከአባቱ እንጂ ከሰዎች አድናቆትን ጭብጨባ አልነበረም።
በምድር ያለውን ነገር እንድንንቅ ፤ ራስ ወዳድነታችንን እንድንጥል ፣ የ'ego' ጥማታችንን እንድናስወግድ የሚያደርገን አንድ ቁልፍ ነገር ቢኖር ጌታን ፊት ለፊት ለማግኘት የሚኖረን ጉጉት ነው። ኢየሱስ የሚያከብረውን አባቱን ሲያይ ለሚያዋርዱትና ለሚክዱት ደቀ መዛሙርቱ አዘነላቸው እንጂ አልናቃቸውም። እነርሱን በመናቅ እንደማይከብር ያውቀዋልና።

መቼም ከዚህ ከኢየሱስ ተግባር ብዙ ልንማር እንደምንችል ባስብም፤ አንድ መርሳት የሌለብን ትእዛዙ ግን "እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል" (13:14) ያለውን ነው። እንደ የጌታ እራት እና ጥምቀት ሁሉ እግር መተጣጠብም ጌታችን አድርጉት ብሎ ያዘዘን ቅዱስ ስርዓት ነው።

የምንጠላቸውን ፣ የምንንቃቸውን ፣ ልናያቸው እንኳ የማንፈልጋቸውን ሰዎች ኢየሱስ እንደሚወዳቸው እና ዛሬ በምድር ቢኖር ዝቅ ብሎ እግራቸውን እንደሚያጥብ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። (ኢየሱስ ያስተማረውን የሚኖር ፤ ስብከቱና ምግባሩ የማይምታቱበት የእውነት መምህር ነበር)።

የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ፣ ባሕርያቸውና ንግግራቸው እንኳ የማይጥመንን ፣ በእኛ ላይ ክፋትን የሚሸርቡትን ፣ የሚጠሉንን ፣ በመከራችን ፊታቸውን የሚያዞሩብንን ሰዎች ሁሉ ደግሜ እላለሁ ኢየሱስ እንደሚወዳቸውና በምድር ቢኖር ዝቅ ብሎ እግራቸውን እንደሚያጥባቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

ይህ ሁሉ ግን የሰዎቹን ትክክለኛ ያልሆነ ምግባር እና ድርጊት ልክ አያደርገውም።

ትሁታን እንሁን! ሂዱ እግር እጠቡ! ሂዱ ጠላቶቻችሁ ውደዱ! ሂዱ ለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ! ሂዱ የሚረግሟችሁን መርቁ! ሂዱ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ ሌሎችን ከፍ አድርጉ። ሂዱ! ከመታወቅ የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ በርቱ።

ትህትና የሚገባንን እንኳ አለመፈለግ ሲሆን ትዕቢት ግን የማይገባንን እንኳ መፈለግ ነው። እርሱ [ኢየሱስ] ትሁት ነውና ትሁታን በመሆን ፈለጉን እንከተል ፤ እንደዚያ ካልሆነማ የእርሱ ተከታይ መሆናችን በምን ይታወቃል???

ትህትናን ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
ራሱን አዋርዶ!
@wordof_God
2👍1
❝ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤❞
—(ወደ ገላትያ ሰዎች 3:13)

Christ redeemed us from the curse of the law; being made sin, or a sin-offering, for us, he was made a curse for us; not separated from God, but laid for a time under the Divine punishment. The heavy sufferings of the Son of God, more loudly warn sinners to flee from the wrath to come, than all the curses of the law; for how can God spare any man who remains under sin, seeing that he spared not his own Son, when our sins were charged upon him? Yet at the same time, Christ, as from the cross, freely invites sinners to take refuge in him.
@wordof_God
👍1
—So, we have learned about many people who trusted God long ago. They are like a very big crowd all round us and we should copy their example. We must be like people who run in a race. We must throw away everything that stops us from running well. The sins that we do make us fall down very easily. We must not let those sins rule us. God has prepared the way that is in front of us. We must continue to be strong while we run along that way. We must choose to run that race well. As we run, we must always look towards Jesus. He is the one who trusted God completely. Our faith starts with him, and he will help us to trust God all the way to the end. Jesus accepted punishment on the cross. He chose to receive much pain. He did not think about being ashamed to die like that. He knew that God had prepared something very good for him that would make him happy. Now he has sat down at the right side of God to rule with him in heaven.
Hebrews 12:1 - 2 EASY

@wordof_God
👍1
ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
²⁷ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
@wordof_God
👍2
“ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።”
  — ዮናስ 2፥8
“When my soul fainted within me I remembered the LORD: and my prayer came in unto thee, into thine holy temple.”
  — Jonah 2፥7 (KJV)
@wordof_God
👍2
ሉቃስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
⁵ ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤
⁶ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦ የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።

So he told them this parable: “What man of you, having a hundred sheep, if he has lost one of them, does not leave the ninety-nine in the open country, and go after the one that is lost, until he finds it? And when he has found it, he lays it on his shoulders, rejoicing. And when he comes home, he calls together his friends and his neighbors, saying to them, ‘Rejoice with me, for I have found my sheep that was lost.’ Just so, I tell you, there will be more joy in heaven over one sinner who repents than over ninety-nine righteous persons who need no repentance.
Luke 15:3 - 7 ESV

@wordof_God
4👍1
እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።”
ሶፎንያስ 3:17 NASV

The LORD thy God in the midst of thee is mighty; he will save, he will rejoice over thee with joy; he will rest in his love, he will joy over thee with singing.
Zephaniah 3:17 KJV

@wordof_God
3👍2
“ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።”
  — 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥3

But the Lord is faithful. He will establish you and guard you against the evil one.
2 Thessalonians 3:3 ESV

@wordof_God
2🥰1
ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።
— መፅሐፈ ኢዮብ 13:15 NASV

Though he slay me, I will hope in him; yet I will argue my ways to his face.
Job 13:15 ESV
@wordof_God
5👍1
👍41