Wolkite University Students' Union
17K subscribers
3.11K photos
36 videos
261 files
877 links
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"Our Reward Is a Student's Happiness!!!"

TELEGRAM
@WkUSU

FACEBOOK_PAGE
www.fb.com/WKUStsU

EMAIL
student.union@wku.edu.et

WEBSITE
https://wkusu.com
Download Telegram
Remind!!

30 days
.........🕘
Happy Mother's Day  ❤️

ዕድሜ + ጤና + ፍቅር ለሁሉም እናቶቻችን
❤️‍🩹
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በጎ አድራጎት ዘርፍ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን  የሲኒማ ምሽት ነገ(08/09/2017 ዓ.ም) በእለተ  አርብ  አሰናድቶ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ።

      ትኬቱ በወ/ዩ/ተ/ህ መረጃና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ቢሮ (LTH-124 አጠገብ ) የሚሸጥ ሲሆን  የሚገኘው ገቢ በአጠቃላይ ለመቄዶንያ አረጋውያን እና የአይምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የሚውል መሆኑን በመረዳት ቀና ትብብራችሁን እንድታደርጉ እየጠየቅን በእለቱ ገብታችሁ ፊልሙን መመልከት የማትችሉ ተማሪዎችም የገቢ ማሰባሰብያውን አላማ በመረዳት ቲኬቱን እንድትገዙ እየጠየቅን። የተዘጋጀውን ፊልም በሰአቱ በመገኘት እንድትታደሙ በተጨማሪም የበጎ ተግባሩ ተካፋይ እንድትሆኑ በትህትና እንጠይቃለን።

=>ቀን:  አርብ 8 /09/2017 ዓ/ም
=>የሚጀምርበት ሰዓት: ከምሽቱ 01:15
=>የሚታይበት ቦታ፡ በLTH-126
=>መግቢያ : 30 ብር

ማሳሰቢያ፡- አርፍዶ የተገኘ ተማሪ ለሚደርስበት የቦታ ማጣት ተጠያቂ አንሆንም።


Links
የመቄዶንያ 👉  https://youtube.com/@mekedonia?si=kLvP7hGIBAoLEvzm

የሰይፉ ሾው  👉 https://youtube.com/@seifufantahun?si=BJglkVUzR4XY2f3f

ከላይ ባሉ ማስፈንጠሪያዎች ሰብስክራይብ በማድረግ screenshots ከስር ሀሳብ መስጫው ላይ ያጋሩን  🙏

<< ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው >>
ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ የመጀመሪያው ዙር ገቢ ማሰባሰቢያው ተጠናቀቀ፡፡

ከየካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመቄዶንያና እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል ላይ እየተደረገ በቆየው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ላይ የመጀመሪያው ዙር የገቢ ማሰባሰብ የቀጥታ ስርጭት ግቡን በማሳካት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በይፋ ተጠናቀቀ፡፡

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  በአዲስ አበባ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋውያን መኖሪያና ዘመናዊ ሆስፒታል አጠቃላይ የፊኒሺንግ ስራውን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ከየካቲት 01 ቀን 2017  ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 1 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ በመያዝ በ Mekedonia እና በ Seifu Show ዩቱብ ቻናል ላይ በመጀመር ላለፉት ሶስት ወራት (90 ቀናት) በቆየው ገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን እቅድ በማሳካት አጠቃላይ በገንዘብ እና በአይነት ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በሰይፉ ዩቱዩብ ቻናል የተደረገው የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰብ ግንቦት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል፡፡

ይህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄደበት Seifu on EBS እና Seifu Show ዩቱዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭትና በማስታወቂያ ገቢ የተገኘ ብር 4,032,585.63 ለመቄዶኒያ ገቢ የተደረገ ሲሆን በመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ላለፉት ሶስት ወራት ሲደረግ በቆየው ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ በማመስገን ለዚህ ዝግጅት ዋናውን ሚና ሃላፊነት በመውሰድ የ1 ቢሊየን ብር ግብ እንዲሳካ ላደረገው ለሰይፉ ፋንታሁን ምስጋና በማቅረብ የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን እንዲሁም በመቄዶኒያ በሚገኙ ተረጂዎች በእጅ ጥበብ የተሰራ ጋቢ ለሰይፉ ፋንታሁን እና ለአርቲስት ይገረም ደጀኔ ያለበሱ ሲሆን በአረጋውያኑ ምርቃት በመታጀብም በሰይፉ ፋንታሁን ምስል የተቀረፀ ምስለ ቅርፅ በስጦታ አበርክተዋል፡፡

በዚህ  በመቄዶንያ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ላለፉት ሶስት ወራት በዘለቀው እና ለተመካቾች በደረሰ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር  ፣ ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የመጡ መምህራን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ፤ ባንኮች እና የሚዲያ ባለሞያዎች መድረኩን በማድመቅ ልግስና በመስጠት እና ለጋሾችን በማበረታታት አብረውን ቆይተዋል። አሁንም በመቄዶንያ ዩቱዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ እንደቀጠለ ነው::................
Special NEWS for GC 🤗

🔴🔊Application 2025 is NOW Open!🔊🔴

👉ለመማመልከት
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdkbf1ksV8672iqGNV1qg32keCHeocR5I5xlul4S7A29yx9bg/viewform?usp=header
👉 ለበለጠ መረጃ
https://www.iteachforethiopia.org/
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት 
ፌስቡክ     👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
ድህረ-ገፅ   👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉
@WKU_SU_BOT

ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን
First year students revised academic calender!!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት 
ፌስቡክ     👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
ድህረ-ገፅ   👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርወልቂየጤተማሪዎች ህብረት

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉
@WKU_SU_BOT

ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን
ውድ የ 2017 ዓ.ም እጩ ተማራቂ ተማሪዎቻችን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
ለምን? ካሉ
በዩኒቨርስቲያችን የመጀመሪያ የሆነው እጩ ተመራቂ ተማሪዎቻችንን ከታላላቅ ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የምናገናኝበት (JOBFAIR/ CAREER EXPO) ፕሮግራም ግንቦት 25 እና 26 2017 ዓ.ም/ June 2-3, 2025 ይካሄዳል።
ምን ያህል ዝግጁ ነዎት?
ዝግጅቱ ላይ ለመካፈል እጩ ተመራቂ ተማሪዎቻችን ማሟላት የሚጠበቅባቸው፥
1. ብቁ የሆነ እና ቀጣሪ ድርጅቶችን የሚያሳምን Cover Letter, CV እና ለ Interview ላይ ዝግጁ መሆን፥
2. ለስራ ቅጥር የሚሆኑ የአለባበስ ስርዓት አሟልቶ መገኘት፥
3. ለፕሮግራሙ ስትመጡ Cove Letter, CV እና Interview Preparation ዝግጅታችሁን አጠናቃችሁ Cover Letter, CV ይዛችሁ እንድትገኙ ይህን ይዞ ያላመጣና ያልታየለት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ አይሆንም።
ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እያሳሰብን በቀጣይ ሳምንት በአንዱ ቀን አጠቃላይ በ JOB-FAIR/ CAREER EXPO ዙሪያ ገለጻ እና ከዚህ በፊት ለወሰዳችኋቸው ስልጠናዎች የስልጠና ሰርተፊኬት የመስጠት ፕሮግራም እንደሚኖረን ከወዲሁ ለመግለጽ እወዳለን!!

Students Career Improvement Office

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት 
ፌስቡክ     👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
ድህረ-ገፅ   👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርወልቂየጤተማሪዎች ህብረት

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉
@WKU_SU_BOT

ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን
ማስታወቂያ
ለተከበራችሁ የ2017 ዓ.ም የዩንቨርስቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ (GC 2025)


culture day የሚከበረው የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 16/9/2017 መሆኑን ከዚህ በፊት ባሳወቅናቹ መሰረት ስለሚከበር በዚህም ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ለፕሮግራሙ እንድትዘጋጁ እና ለ culture day የሚያስፈልጉትን አልባሳት  committew ስለሚያዘጋጅ አልባሳቱን መከራየት የምትፈልጉ ተማሪዎች ምዝገባውንም ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ 2:00 ሰዓት ብቻ በGC PRESIDENT ቢሮ( Registrar ህንጻ G+1) በአካል በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን መፅሔት እና ባይንደር ማሰራት የምትፈልጉ ተማሪዎች ምዝገባም መጀመሩን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:
1, በግል አልባሳትን የተከራያችሁ ተማሪዎች ላይ ህብረቱም ሆነ ኮሚቴው ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን።
2, ያለን ጊዜ አጭር ስለሆነ ማሰራት የምትፈልጉ ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ ምትፈልጉትን አልባሳትም ሆነ መፅሔት እና ባይንደር እንድትመዘገቡ እንገልጻለን ።
3 የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች አልባሳት ዋጋቸው 700 ብር (ከአዲስ አበባ የሚመጡ) ሲሆን የጉራጌ ማህበረሰብ ልብስ ግን እዚሁ ወልቂጤ ከተማ ላይ ስለሚገኝ 350 ብር መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
+251904133665 ጽናት
+251963288469 አቤል
+251942590129 ሃኒ
+251912273504 ዝምቤ
+251963381693 ነቢል

የ2017 ዓ.ም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ኮሚቴ
ማስታወቂያ
ለሪሜዲያል ተማሪዎች በሙሉ
:-

በ2017 ዓ.ም በግቢያችን ደረጃ የሚሰጠዉ ፈተና ማክሰኞ (19/09/2017ዓ.ም) የሚጀመር መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በ19 እና በ20 የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science )ተማሪዎች እንዲሁም በ21 እና 22 ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ(Social Science )ተማሪዎች የሚፈተኑ ይሆናል፡፡

ፈተናዉ የሚሰጠዉ በተለያየ ዙር ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናዉን በቀን ዉስጥ በ 4 ዙር የምትፈትኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ 2ዙር ይፈተናሉ፡፡  ስለሆነም  ተፈታኞች በየትኛዉ ቀን፤ ስዓት እንዲሁም በየትኛው ቦታ እንደሚፈተኑ ቀድመዉ እንዲያውቁ እናሳስባለን።

ማስታወቂያ  
(R &G Talks program)
‎ለግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ ፦ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እያልን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት  በሪፎርም እና ጋይዳንስ ዘርፍ ውስጥ ከሚዘጋጁ  አስተማሪ፣አዝናኝና ድንቅ ከሆኑ ፕሮግራሞች መሃከል ቀዳሚው እና ዋንኛ የሆነው  (R &G Talks program ) መሆኑ ይታወቃል፡፡  በመሆኑም በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ዙር ባማረ እና በደመቀ  መልኩ  ለማቅረብ  ሙሉ ዝግጅታችንን የጨረስን ሲሆን የፊታችን አርብ ማለትም በቀን 22/09/17 ዓ.ም በ LTH 121 ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ ለታዳሚዎች ይቀርባል። በፕሮግራሙ ላይም ክርክር ፣ንግግር፣ ጥያቄና መልስ በተጨማሪም አዝናኝ ፣አስተማሪ እና የተለየ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች፣ የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ይኖሩናል በመሆኑም ዉድ የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ በዚህ ትልቅ ፕሮግራም ላይ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

ማሳሰቢያ:-  ከዚህም በተጨማሪ የፍሬሽ ማን እና የሪሜዲያል  ተማሪዎችን ዓላማችሁን እንድታሳኩ እና በአጠቃላይ እስከ ዲፖርትመንት ምርጫችሁ እንዴት ዉጤታማ መሆን ይቻላል በሚል ዕርስ ለእናንተ ለየት ያለ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

ቀን: ‎አርብ  ግንቦት 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት: ምሽት 12:30
ቦታ : ‎LTH 121
‎ለበለጠ መረጃ፡ +251927336744
                        +251982305128

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የሪፎርም እና ጋይዳንስ ዘርፍ