በብዕር
837 subscribers
160 photos
1 video
1 file
71 links
በብዕር
ስለሁሉ ለሁሉ
:
በቤታችን የራሳችንን የእጅ ስራ ውጤቶች እንዲሁም የወደድናቸውን እናጋራለን
የቤታችን ቁልፍ👇
@with_apen
Download Telegram
ሀቅ አንተ ታውቃለህ🥰
🥰10😭32👏1💯1
ጭንቅላት ለሚያስፈልገው ሰው ልብ አትስጥ¡ አሉ

እውነታቸውን ነው አ ☀️
👏13💯32😁2
ከአላህ ለአላህ ወደ አላህ

❤️❤️❤️☀️☀️
15
#ቀን_አለ

መሄዳችሁ ሄድኩበት ላላችሁት ሰው እረፍት የሚሆንበት ፣ የታባቱስና ማን እንዳለው አያለሁ ያላችሁት ልክ ስትርቁት የሚጠነክርበት፣ በጣም ጠቃሚ ነኝ ብላችሁ የምታስቡበት ቦታ ላይ ሰላም እያናጋችሁ እንደነበር የምትረዱበት ፣ ጠውልጎ ያያችሁት ፊት ከእናንተ ገሸሽ ሲል መጎምራት እንደሚጀምር የማድያቱ ሰበብ እናንተ እንደነበራችሁ የምታዩበት #ቀን_አለ

Glamour
:
@with_apen
@with_apen
😢8👏2💔2
አሁን ቅድም አይደል ከእናንተጋ
የዋልኩት
አሁን ትናንት አይደል አንተን ያገኘሁት
አሁን ዛሬ አይደለም ከሰዎች መካከል ይህንን የፃፍኩት
ታድያ ለምንድን ነው? ሰው እንደሌለው ሰው ሰውን የተራብኩት ?

Glamor
:
@with_apen
@with_apen
🤔4😢2🤗2🔥1
የቄስ ትምህርት ቤት የመጨረሻ ትውልድ ሳልሆን አልቀርም ከኔ ቡሀላ ያሉት ልጆች ሁሉ መዋለ ሕፃናት ነው የተማሩት...
በርግጥ እኔም ቄስ ትምህርት ቤት ተማርኩም ለማለት ይከብደኛል አስተማሪያችን ቄስ የነበረ አይመስለኝም  ። አስተማሪያችን ቄስ ቦጋለ እየተባሉ የሚጠሩ የነበረ ቢሆንም.....ከሆነ ግዜ ቡሀላ ቄስ አደለሁም ቲቸር ቦጋለ በሉኝ ይሉን ነበር...ለካ ጴንጤ ሆነው ነው። አባትችን ሆይም ብዬም አላውቅ ፀሎት የአመቱ ድግስ ምናምን የሚባልም ነገር አልነበረም።ስለዚህ ስም ያልወጣለት መዋለ ሕፃናት ብለው ይቀለኛል።

አንድ የሰፈር ልቅሶ ላይ ከረዥም አመት ቡሀላ አብረን ያደግን የሰፈር ልጆች ተገናኘን። በተገናኘንበት ቦታ ላይ  በልጅነታችን በእቃቃ ሚስቶች እንጠራራ የነበረውን አስታውሶ ስለ ጠራኝ አበሳጨኝ እና ጉዱን ልነግራቹ ነው እንግዲ። ይሄ ወንጀለኛ..ይቅርታ ይሄ ስሙን የማልጠራላቹ አብሮ አደጌ ..(ባያድግ ምኞቴ ነበር ግን አደገ ...🙄) እሱ ባሉት ብዙ የሰፈር የእውነተኛ ሚስቶች ሙድ እንይዝበት እና ጨዋታ ስናጣ ጨዋታ መፍጠሪያችን የነበረ ልጅ ነው።
ድብር ሲለን ከእንትናጋ ምንድን ነው ያደረጋቹት እያሉን....እያፋጠጥነው...... እኔ በዚ እድሜዬ አድርጌ የማላቃቸውን እሱ በዛ እድሜው ከተለያዩ...ቱ..🤭
ስላደረጋቸው ነገሮች እንደበርበት ነበር።
የሱን ጉድ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ስለሆነ የሰፈር ዱርዬዎች በያዙት እና ባስፈራሩት ቁጥር በየግዜው  ስለሚያደርጋቸው ድርጊቶች እንሰማ እና መደበርያችን ነበሩ።
እጅ ከፍንጅ በተለያየ ግዜ የተያዘ እና ከሀጢያቱ ያልተማረ የሰፈራችን ልጅ ነው።ሀይማኖት እና ዕድሜ ሳይለይ በአግባቡ የተበላሸ እና ያበላሸ ልጅ ነበር...😥😁

ይሄ ልጅ ነው እንግዲ ለቅሶ ላይ ማዘን ሲገባን ፌበን እንዴት ናት ብሎ ያሳቀበኝ....
🤣81
ፌበን እኮ እዛ ቄስ ት/ቤት ውስጥ የእቃቃ ብቻ ነበረች እኔ ኮ በሷ ስሜ መጥፋቱ አደለም ያናደደኝ ከዚ ሁላ ግዜ ቡሀላም መወራቱም አደለም ....እኔ በሷ ስም ስሜ ለመጥፋት የሚያበቃ ..ምንም ድርጊት ስላልነበረኝ ነው።
እናንተ ታምኑኛላቹ አደል🙄? እንዳታምኑት

✍️Mewla

@with_apen
@with_apen
😁9🤣2


..... አሁን የሆ'ነውን የሆነው በእሱ ጥረት ነው። አንድአንዴ እንዴት አድርጎ እንዳገኘኝ ከዛ ደግሞ እንዴት አድርጌ እንደገባሁት ግራ ይገባኛል።

‎ለመወደድ የሚሰጠው ትክክለኛ ምላሽ አይገባኝም ነበር። ሰው እወድሻለው ሲል መልሶ ምን እንደሚባል ስለማላውቅ እንደ ፍቅር ቃል በላብ የሚያሰምጠኝ አልነበረም።

በዙሪያዬ ካሉት ‎መውደድ አለመቻል ሳይሆን ተገቢው ምላሽ ምን እንደሆን እንደማላውቅ የገባው እሱ ብቻ ነበር።

‎ከፍቅር ገለፃው በኋላ ምላሽ ስለማይጠብቅ እንደሌሎች ሰዎች ቅሬታውን ስለማያሰማኝ እኔን መውደድሽን አታቁሚ እንጂ ለመናገሩ እኔ እበቃለው ብሎ ህይወትን ቀለል ስላደረገልኝ ይመስለኛል ለላግዝሽ የተዘረጋውን እጁን በእሺታ ጠበቅ ያደረኩት።

‎ መወ'ደድ እንደሚገባኝ መውደድን መንገር እንደማይገል ብዙሺኛ ቀናቶችን እየነገረ ፤ አድርጎ እያሳየ  አለማመደኝ።

እያመሻሸ የደራው ጎጇችን ፣ እያደር የሞቀው ቤታችን  የመረዳት አቅሙና የትዕግስቱ ፍሬ ውጤቶች ናቸው።



©Glamour
:
@with_apen
@with_apen
🥰72❤‍🔥1👍1🔥1
"People are not drawn to you because you like them — they are drawn to you because they like themselves when they are with you."

📚The Like Switch
:
@with_apen
@with_apen
😭4👍3💯1
ሕልም

መቼ ነው ሕልም ማለት የጀመርኩት ?
መቼስ ሳይንስ እናትሕ ሆድ ውስጥም ሆነህ ማለም ጀምረሀል ማለቱ አይቀርም።
ግን ከተወለድክ ቡሀላ የመጀመርያ ሕልምህ ምን ነበር?
በራሱ ጥያቄ ፈገግ አለ ?።
መቼስ አስፈራሪ ነው የሚሆነው።ሕፃን ሆኜ ጭራቅ፣ አያ ጅቡ ጆሮ ቆራጭ መጣልህ እየተባለ ላደኩኝ  ልጅ ሕልሜ አስፈራሪ አስጨናቂ አስለቃሽ እንደነበረ መገመት አይከብደኝም።
በቃ በዘመኑ ቋንቋ የሆነ የተወጋ ሕልም እንደነበረኝ ገመትኩ።የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ልጆች ህልም የተረበሸ እና ሳቅ የራቀው እንደነበረ አሰብኩ።

የእንቅልፍ ሕልሜን ብቻ ሳይሆን የኑሮዬንም ሕልም የቀጩ ብዙ ናቸው። አሁን የራሴን ማስተዳደር ጀምሬ እንኳን የሂወቴን ካርታ አላገኘሁትም በጣም ተዛብቶብኛል ህልሜን ነው መከተል ያለብኝ ወይስ መንገዱ የመራኝን ወይስ ሰው ሲያደርግ ያየሁትን ..........
የቱን ?
ያለ ሕልም መኖር አይቻልም ......በቃ ዝም ብሎ መኖር ? ......እራሱን ይጠይቃል።

አይቻልም..........! ይለዋል እራሱ አብዛኛውን ቀኑን ብቻውን ስለሚያሳልፍ ከራሱ ጋር ሲሟገት ሲታገል ሲጨቃጨቅ ይውላል የዛሬ ሕልሙ ደሞ ህልም ተኮር ነው።
አይቻልም እንዴት ይቻላል ህልም እኮ ማለም ነው መመኘት መፈለግ ነው እንዴት ሳልመኝ ሳያምረኝ መኖር እችላለሁ። አይ አይ አልችልም።

✍️Mewla

@with_apen
@with_apen
🔥53
💯5
👍51
ዝቅ ለጊዜው ከፍ በጊዜው!!!


☀️
🥰235
እንደኔ በግራ እና በቀኝ ሳንቡሳ ከምረው በሚሸጡ ሰዎች መንገድ ሳትገዙ አንገታችሁን ደፍታችሁ ስታልፉ "አላህ ስሜቱን በሚቆጣጠር ወጣት ይገረማል" የሚል ሀዲስ ትዝ የሚላችሁ ሰዎች እረፉ

:
@with_apen
@with_apen
😁16🤣5
አማር
አየሩ የፈረሱን ፀጎር ወደ ኋላ እያንሳፈፈ አየር ላይ አድርጓቸዋል። የፈረሱን ፀጉር ንፋሱ ወደ ኋላ ባያንሳፋቸው ኖሮ በጥሩ ቀሪፂ የተቀረፀ ሀውልት እንጂ ከስጋ እና ከደም የተሰራ ሂወት ያለው አካል አይመስልም ነበር። ግርማ ሞገስ ያለው የጦር ፈረስ ነው የጥቁረቱ ድምቀት ብቻውን አንድ ክፍለ ጦር ነው። ፈረሱ ከጥቁረቱ ጋር ያንፀባርቃል ። እግሮቹ በፀጉር ተሸፍኖ ከመሬቱ ጋር የተጣበቀ ይመስል ቀጥ ብሎ ቆሟል።ኮርቻው ሳይቀር ጥቁር በመሆኑ አንዳች ሀይል ያለው አንፀባራቂ ፍጥረት አስመስሎታል።
ልጓሙ አይኖቹን አስቀርቶ ወደ አፍንጫው እየጠበበ በሚሄድ ጭንብል ጋር አብሮ ተሰራቷል።

ከፈረሱ ጎን ጭንቅላቱ ላይ ጠበቅ ተደርጎ በነጭ ጨርቅ እንደ አረቦች የጦር አጠቃለል ተጠቅልሎ ከበስተኋላው የጥምጣሙ ጫፍ የንፋሱን አቅጣጫ ይዞ የሚርገበገብ ወጣት ቆሟል። በቆዳ የተሰራ የጦር ልብስ ለብሷል።በግራ ጎን ወርቃማ አንፀባራቂ ሰይፍ ታጥቋል ፀሀይ ሲያርፍባቸው መስታወት ይመስል ከሩቅ ያንፀባርቃሉ ። የግራ እጆቹ  መዳፍ የሰይፉን እጀታ ሙልት አድርገው ይዘውታል። ከላይ ሰፋ ብሎ ወደ እግሮ እየጠበበ ሚሄድ ነጭ ሰፊ ሱሪ  ታጥቋል። ገመዶቹ ጉልበቶቹ ድረስ እየተሳሰረ የሚሄድ በቆዳ የተሰራ ጫማ ተጫምቷል። ከኋላው ሻጥ ተደርጎ የተለጠፈ ክብ ባለ ጌጥ ሰይፉን የሚመስል ወርቃማ ጋሻ ይዟል።

ፊቱን ሲመለከት ጠቆርቆር ያለ የራሱ ምስል ነው።
<<አማር>>
ተብሎ የተጠራ ይመስለው እና ድምፁ ግን አቅጣጫ ስለሌው ማድመጥ ብቻ ነው የቻለው።

ድምፁ ተጣርቶ  አላቆመም

<< ሰራዊትህን ይዘህ ታገላቸው ድል የአማኞች ነው >>

የሚል ድምፅ ይሰማል።ሰራዊት የተባለውን ወደ ኋላ ለማየት ሲሞክር ቁጥራተው (200) ሁለት መቶ የሚሞሉ የፊት ገፅታቸው የማይታይ ሰውነታቸው  ነጭ ብርሀን ያላቸው ሰዎች እንደ ራሱ የታጠቁ ከፈረሶቻቸው ላይ እንደተቀመጡ የሱን ትዕዛዝ የሚጠብቁ የጦር ሰራዊቶች ይመለከታል።

ወደ ፊቱ መለስ ብሎ ሲመለከት መጀመርያ ያልታየው ሌላ የጠላት ጦር የሚመስሉ ሰዎች ይመለከታል።
ብዛታቸው  ቁጥራቸው የማይገመት ፣ መጨረሻቸው የማይታይ ሰዎችን ያያል።
በብዛታቸው ልቡ የደንገጠ ይመስለዋል....።
ድል የአማኞች ነው ......
ድል የአማኞች ነው ......
ድል የአማኞች ነው.......
(አትፍራ :አትዘን : አብሽር)

የሚል ድምፅ አብሮ እየደጋገመ እያለ ከእንቅልፉ ነቃ በላብ ጥምቅ ብሎ  ይሄንኑ ህልም ለሶስተኛ ግዜ እያየው እንደሆነ ታሰበው።

ይቀጥላል እንዴ..?

✍️Mewla

@with_apen
@with_apen
🔥4👏32👍2
የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ሆኖ በጊዜ አባት የሞተበት ሰው መሆን እንዴት እንደሆነ አታውቅም። የቁስም የስሜትም ጥገኝነት የሚፈልጉ ታናናሽ እህቶች ታላቅ ወንድም መሆን ምን እንደሆነ አትረዳም። እንዳላስጨንቀው ብላ አንጀቷን የምታስር እናት ልጅ መሆንን ከነጭራሹ በህልሟ እንኳ አይመጣባትም። ታድያ እንዴት ትረዳኛለች?

‎አባቷ የአይኔ ማረፊያ እያሉ አሳድገዋት.... ወንድሞቿ ትከሻቸውን እያቀበሉ ደህንነቷን ሰጥተዋት....እናቷ ተደብቃ ስታለቅስ ሳታይ አድጋ

‎የሆነ ቀን እናቴ ደውላ ለሆነ ነገር የተወሰነ ብር እንደምትፈልግ ስትነግረኝ ብሩ በጣም አስፈልጎኝ ቢሆንም ከእሱ ቀንሼ ስልክላት ስታይ.....ስሜቴ በወረደበት እና አዝኛለው ባልኩበት ጊዜ እህቶቼ ደውለው ስለድብርታቸው ሲያወሩ የራሴን ረስቼ ሳፅናናቸው ስለሁኔታዬ ስደብቃቸው ስትመለከት....በጣም አሞኛል ብለው እንኳን ፍቃድ የማይሰጥ ለሰው ክብር የሌለው አለቃዬ ጋር ክፍያው በጣም ጥሩ ስለሆነ ብቻ ችዬው ስቀመጥ ስታስተውል

‎ለራስህ ቅድሚያ ስጥ....አሞህ አትደብቅ....ድካም ሲሰማህ ገንዘብ ሲያጥርህ ስራው ሲያሰለችህ አለቃህ ሲያመናጭቅህ ዝም አትበል....የማትወደውን ስራ ትተህ ህልምህን ተከተል ብላ መወትወት ጀመረች።

‎እውነት ነው
‎ .......እወዳት ነበር....ሽማግሌ ልልክ ነበር...እንጋባለን ብዬም አስብ ነበር።


‎ለራሴ ማሰብ ስላልቻልኩ....ታላቅ ወንድምም አባትም ሆኖ የማደግን ሀላፊነት ስለማትረዳ.....እድገታችን ስለሚለያይ....ተለያየን።

©Glamor
:
@with_apen
@with_apen
🤝6😢43❤‍🔥2💔1
9🔥2
እናንተ ለሷ ብለን ነው የምንሰዳደበው ብላችሁ የምትፋለሙላትን ጀነት
ቀልቡ ንፁህ የሆነ፣ በምላሱም አንድም ቀን ሰውን ያላስቸገረ፣ የጥሩ ስብእና ባለቤት የሆነ ሰው ብዙም ሳያደክም በአቋራጭ ሊገባት ይችላል።

አቤት በዚህ ዘመን ለአላህ ብዬ የሚለው መብዛቱ ።

Muhammad Seid (ABX)
😢10👏4💯4
ቢሆንማ እንደነሱ
ማን ይኖራል ከመቅደሱ
ደግነቱ !
በፍቅር የወደቅነው ከእምነቱ።

©Glamour
:
@with_apen
@with_apen
🔥82
አንዳንዴ....

አንዳንዴ ጌታችሁን ልትለምኑት እጃችሁን አንስታችሁ ያረብ ከማለታችሁ ቃላት ጠፍተውባችሁ አያውቅም ? በሀጃችሁ መብዛት፣ በፍላጎታችሁ ጥናት፣በስብራታችሁ ብርታት የልባችሁን መተንፈስ ሳትችሉ ቀርታችሁ አታውቁም ?....እኮ !ግና አብሽሩ ረሱልን የፊታቸውን ወደስማይ ማንጋጠጥ አይቶ የምላሳቸውን ንግግር ሳይሻ የልባቸውን መሻት አውቆ ወደሚወዷት ቂብላ ያዞራቸው ጌታ ፊት ቆማችሁ ባንደበታችሁ መታሰር ፣በምላሳችሁ ዝምታ ባዶን አትመለሱም የልባችሁን ያውቃልና ሀጃችሁን ሞልቶ ከህመማችሁ ያሽራችዃል ።አብሽሩ 🤍

Vis

@with_apen
@with_apen
🥰164