የጥበብ - መንገድ ™
5.85K subscribers
1.05K photos
21 videos
42 files
58 links
❝ Art is a step from nature toward the Infinite ~ Kahlil Gibran ™🌸📚

@abawassie ✉️
Download Telegram
የማይነጋ ህልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ኑሮ ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።

— ገጣሚ፣ ጸሐፌ ተውኔት፣ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን 📖
❤17
ሀገሬ ውበት ነው

ለምለም እና ነነፋስ ሚጫወቱበት
ሀገሬ ቆላ ነው ደጋ ወይናደጋ
እዚያ ብርሀን አለ ለሊቱ ሲነጋ
ሀገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
ሀገሬ ጅረት ነው ገደል እና ሜዳ
ውሸት ነው በበጋ ጸሀይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም
አይበርድም አይበርድም

....

ለምለም ነው ሀገሬ
ውበት ነው ሀገሬ
ገነት ነው ሀገሬ

(ሰዓሊ ወገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)


መልካም ልደት ገብርዬ 🖤
❤11🥰5
__

« ለማንም ፡ ምንም ፡ ነኝ ፥ ያ ፡ ነው ፡ ትልቁ ፡ ነፃነቴ ...! »

—F Kafka
❤25
“ ግጥም ነበረኝ ”

የምጽፍልሽ..

እሳት የበላቸው ፊደላት

ቀለም ያቀረሻቸው

ትኩስ ናፍቆት..

እውቀት ያሻገታቸው መባተቶ ች
፡
የዓለም ህመም የተከመረባቸው

ጉራንጉሮች..

ጽሐይ ወገግታ ያልጎበኛቸው ፡፡

ደንጋዛ ንጋቶ ች..

‹ሁሉም ቀረ! ›

አልሆን ብሎኝ ።

ተሳንፌ

ግጥሙን ሰረዝኩት፡ ስምሽን ፅፌ፡፡

©የአባ ልጅ
❤7🥰3
ነገረ-ተረክ እንደገና

(ያዕቆብ ብርሃኑ)


ኢውጅን አዮኒስኮ (Eugene Ionesco) የቤኬት፣ ሳርትር፣ ካሙ ዘመነኛ የታወቀ የተውኔት የአብዘርድ ድራማ ጸሐፊ ነው፡፡ የበለጠ Rhinoceros በተሰኘው አብዘርድ ድራማው ይታወቃል፡፡ ይህ ሰው ‹The Paris Review› ከተሰኘ Prestigious መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ በተረኮቻችን ስለምንፈጥራቸው ገጸባህሪያት ሥነፍጥረት ፈጽሞ የማልስማማበትን ሀሳብ ሰንዝሮ አየሁ፡፡ ልቀንጭብ...

‹‹They (characters) have no metaphysics, no order, no law. They are miserable and they don’t know why. They are puppets, undone. In short, they represent modern man. Their situation is not tragic, since it has no relation to a higher order. Instead, it’s ridiculous, laughable, and derisory.››

እንደ ኢውጅን አዮኒስኮ አረዳድ የተውኔት፣ የልብወለድ፣ የተረክ፣ የአፈታሪክ ገጸባህሪያት በሙሉ የሰው ልጆች ምናብ ለመጫወቻነትና ጊዜ ማሳለፊነት ብቻ የተፈጠሩ አቅመቢስ ናቸው፡፡ በዚህም በእኛ ሀገር፣ በአማረልኝ የፍልስፍና ስሜት ተረክን ኩሸት ለማለት የሚዳዳቸው ጥቂት ወጣቶች ተደጋጋሚ ልፈፋ እሰማለሁ፡፡ የሚናገሩትን አያውቁትምና ምን እንላለን?!

እኔ ግን ከኢውጅን እለያለሁ፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ተረክ እውነታን ይበልጠዋል እላለሁ፡፡ የተረክ ፍጡራን ክታብ፣ ምልክት፤ ኅሊናዎቻችን ናቸው! ተረክ በስነተፈጥሮው ውስጥ መቸንከር የለውም፡፡ ለምሳሌ ከግለሰቦቹ አዳም ረታ እና ሀዲስ ዓለማየሁ ይልቅ የተረኮቻቸው ውጤት የሆኑት መዝገቡ ዱባለና ጉዱ ካሳ ለምናባችን ይቀርባሉ፤ ለአንደበታችን ይቀላሉ፤ ለመመሰል ይመቻሉ፡፡ ‹ጉዱ ካሳ› ሀዲስ ከመፈጠሩ በፊት ነበር፤ ሀዲስ ጉዱ ካሳ ወደ የጋራ ምናባችን ለመንቃቱ ሰበብ ብቻ ነበር፡፡ የሥንዝሮ ተረክ ዕድሜ እንደ ግዮን ወንዝ የረዘመ ቢሆንስ ስንኳ ለሚሰማው ሁሉ ዘወትር ትኩስ፣ ለእያንዳንዱ ዘመንና ትውልድ ምንጊዜም አዲስ ነው፡፡ የላሜ ቦራ፣ ብልጮና መሰል ተረኮችም እውነታ የተለየ አይደለም፡፡ የተረክ ፍጡራን ለጋራ ኅሊናችን (Collective consciousness) የሚያዋጡት ተምሳሌትነት(symbolism) ግን ግዝፈቱ ለጉድ ነው፡፡

ኅብረተሰብ ሁለተናውን የሚያበለጽጉ የባህል ወካዮችን ከተጨባጩ ዓለም እንዲህ ይመለምልና ወደ ተረት፣ ተረክ ፍጡርነት (Mythic figure) ያሳድጋቸዋል፡፡ የሆነ ነገር ወካዮች ያደርጋቸዋል፡፡ ወይ የጀግንነት፣ አሊያም የመንፈሳዊ ብቃት፣ የፈጠራ፣ የአመጽ፣ የፌዝ ወይ ሌላ... ኮንፊሸስና ላኦ ዙ የቻይናን ጥንታዊ ስልጣኔ ሁለት የተራራቁ ዓለማት (መንፈሳዊና እና ቁሳዊ) ጽንፎች ወካይ ናቸው ብለናል፡፡ ንግስት ፉራ ለዘመናት የሲዳማ ሴቶች የጭቆናን ቀንበር የመስበር ምልክት ነበረች፡፡ የቃቄ ወርድውት የጉራጌ ሴቶች ሁሉ የእምቢባይነት ልሳን በመሆን ትታወቃለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነገረ ወጉ ይበልጡኑ በቤተክነት ቅጥር ውስጥ የተወሰነ ቢሆንስ ስንኳ ትርክቱን ከትል እስከ አዕዋፍትና መናፍስት የሚያጣቅስ ሺህ ዘማነትን የተራመደ የፈጠራ ምልክት ነው፡፡ አለቃ ገብረሃና ‹በጨዋታ ፈላስፋነታቸው› ኢትዮጵያዊው ሙላ ናስረዲንን ቢባሉ ያንስባቸዋል፡፡ ነገር ላለማርዘም እንጂ ሌሎች ከአጼ እስከ ደጃዝማች በገቢር ኖረው ያለፉ ግን በጀግንነታቸው የተረክ ፍጡርነት የተላበሱ በርካቶችን መጥራት እንችላለን፡፡

እንግሊዛዊያን ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የራሳቸው የተረክ ዓለም ‹አበጀ በለው› ነበራቸው፡፡ ሮቪንሁድ ይባላል፡፡ ድሆች ሲበደሉ አይወድም፡፡ ከሀብታሞች እየዘረፈ ለድሆች ይናኛል፡፡ ሮቪንሁድ ራሳቸው የጠነሰሱት የካፒታሊዝም ልክየለሽ የሀብት ክምችት ጠራርጎ ሳይወስዳቸው በፊት የሚቃወሙበት፣ የሚሟገቱበት ኅሊናቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምናልባት ጠፍተው ያልጠፉትም መሰል ተረኮቻቸው ባስታጠቋቸው ኅሊና ስለተመሩ ይሆናል፡፡ ዳኒሾች፣ ሴልቲኮች፣ ጀርመኖች፣ ብራዚላዊያን፣ የማሌዢያ ሰዎች ይሄን መሰል የተረት ዓለም ፍጡራን በተረኮቻቸው ውስጥ እንዳላቸው አንብቤለሁ፡፡ ሮቢንሁድ፣ ሌላው ቀርቶ ኦቴሎ እንኳን ለምናብ ባላቸው ቅርበትና ተለጣጭነት ሰውየውን ሸክስፒርን ይበልጡታል፡፡
.
.
.

ነገረ ሃቲታችን የሚያራምድ የሚያሰፉ አንድ ተረክ ከምሥራቅ እንምዘዝ...

የኮንፊሸስና ላኦ ዙ የመጀመሪያ ግንኙነት ለየት ያለ ታሪክ አለው ይባላል፡፡ ሁለቱ ሰዎች በአስተምኅሮታቸው ፍጹም የተራራቁ ሀሳቦችን ያራምዳሉ፡፡ ኮንፊሸስ በዘመኑ ገናና ነበር፡፡ የአደባባይ ሰው ነው፡፡ በተጨባጩ ዓለም ውስጥ እንደምን ስምሙ ሆኖ በምግባር መመላለስ እንደሚቻል የሚያስተምር ሰው ነበር፡፡ በርካታ ደቀመዛሙርት አፍቷል፡፡
በአንጻሩ ላኦ ዙ የጽሞናው አሳሽ ነው፡፡ የታኦይዝም (ዳኦይዝም) መስራች እሱ ነው ይባላል፡፡ ነጠል ብሎ ማሰላሰልን ይመርጣል፡፡ አንድ ቀን ከኮንፊሸስ ተማሪዎች አንዱ ኮንፊሸስን ጠየቀ፡፡
‹‹መምህር ስለ ላኦ ዙ ሳትሰማ አትቀርም መቼስ... በውስጣችን ስላለ ፍጹም ስክነት ስላረበበት ሰፊ ዓለም(ስለታኦ መሆኑ ነው) ያስተምራል ይባላል፡፡ ስለዚያ ነገር ልታስተምረን ትችላለህን?››
ኮንፊሸስ ሲመልስ...

‹በዓለም ሳለህ በጨዋነት ኑር፤ ምግባርን ሰልጥንባት፣ ጸጋን ተጎናጸፍ፤ የኅብረተሰብን ስሪትና ሕግጋት አክብር፤ ዘለዓለማዊነትን ስትሞት ትደርስበታለህ፡፡ ምን ያስቸኩልሃል? ሌላውን እንቶፈንቶ ግን ተወው፡፡››

ሆኖም ራሱ ኮንፊሸስ እንኳን በዚህ መልስ አልረካም፡፡ የላኦ ዙ በጽሞና መግነን ከንከኖታል፡፡ ደቀመዛሙርቱን አስከትሎ ላኦ ይገኝበታል ወደ ተባለው ዋሻ ሄደ፡፡ በዘመኑ ላኦ ዙም ምሥጢራዊ ነገሮች ያደርጋል በሚል ዝናው የናኘ ሰው ነበር፡፡ ፊቱን ወደ ኋላ አዙሮ ጎሽን ሽምጥ ይጋልባል እየተባለ ይወራለታል፡፡ ኮንፊሸስ ምን እንደሚገጥመው ስላላወቀ ፈርቷል፡፡ ደቀመዛሙርቱን ወደ ኋላ አስቀርቶ ብቻውን ወደ ዋሻው ዘለቀ፡፡

ላኦ ዙ መምጣቱን ቢያውቀም በዋሻው ውስጥ በጸጥታ ተቀምጦ ማሰለሰሉን ቀጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ በኮንፊሼሳያዊ አስተምህሮ...
‹‹ይገርማል! እንግዳ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ ተቀመጥ ማለት እኮ ጨዋነት ነው›› አለ፡፡
ወዲያውኑ ላኦ ከመቀመጫው ተነስቶ ሰይፉን ከአፎቱ እየመዘዘና እና በቀጥታ ዓይኖቹ ላይ እያነጣጠረ...

‹‹ወደ ተጠለልኩባት ዋሻዬ ለመግባት ስለምን ይሄን ያህል ፈራህ? በአጭሩ እዚህ የጨዋነትና የሥነምግባር ትምህርቶች አይሰጡም፡፡ እዚህ የምናስተምረው በጸጥታ ስለመሞትና ከሞት ስለመነሳት (ስለዘለዓለማዊነት) ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ዝግጁ ነህን?››
ኮንፊሸስ በፍርሃት ይቅርታ ጠይቆ ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለሰ፡፡
.
.
.
ልክ ሲያፈልግ ኢየሱስ ጅራፍ እንደመዘዘው ሁሉ፣ የጥንታዊ ቻይና መንፈሳዊው ዓለም ወካይ ሆኖ የቀረበው ላኦ ዙም ሰይፍ ስለመታጠቁ ቢነገረን ሊገርመን አይገባም፡፡ አንዳንዴ እውነት በሰይፍ፣ በጅራፍ ሊገለጥ ይችላል፡፡ ሁሉም ጥበብ ማባበል፣ ማጫወት አይጠበቅበትም፡፡ ሁሉም እውነት መቀባባት አይሻም፡፡ ሥለሞት ማውራት ለአፈጮሌዎቹ ቃል ነው፡፡ በተረክ እየተመላለሱ በኅልውና እያሉ ሞትን መለማመድ ግን በነፍስ መፍገምገምን የሚጠይቅ ሌላ ፍጹም ሌላ ተዓምር... ደግሞም እውነታ (Reality) ግልብ እና ጠጣር(fixed) ነው፤ ተረክ ግን ጥልቅ፣ ረቂቅ እና ሩቅ!
❤5
ኮንፊሸስና ላኦ ዙ በሕይወት የነበሩ ሰዎች ስለመሆናቸው እንኳን ማስረጃ ማግኘት ያዳግታል፡፡ ነገርግን ማስረጃ ምን ይፈይዳል? ይህ ተረክ እውነት ጠቀስ መሆኑም አለመሆኑም ልዩነት የለውም፡፡ አውነታነቱን የሚጠይቅ ራሱ ነገር ያልገባው ሰው ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ የክርስቶስ በመስቀል ላይ የማዳን ትርክት ዋናው ቁምነገሩ ተጨባጭነቱ (እውነታነቱ) ላይ አይደለም፡፡ ተምሳሌትነቱ እንጂ! ዋናው ቁምነገር ተምሳሌትነቱ ነው፡፡ ተምሳሌትነቱ ዘለዓለማዊ ነዋ፡፡ እናስ በሁለት የጥንታዊ ቻይና ሰዎች ዙሪያ የሚነገሩ ተረኮች ለሺህ ዘመናት ለቢሊዮኖች ፍኖት እንደነበሩ ማወቅ ነፍስን ያጠግብ የለምን?

ተረኩ ኩሸት ቢሆን እንኳን ተረኩን የጥንታዊ ቻይና ሰዎች የቁሳዊና መንፈሳዊ ዓለም ፍትጊያ ወካይ አድርጎ መፈከር ይቻላል፡፡ ታሪክም እንደሚዘክረው የኮንፊሼስ አስተምህሮ እና ታኦይዝምም ለሺህ ዘመናት የሰለጠነ ፍትጊያ ሲያካሂዱ ዘልቀዋል፡፡ዘወትር አሸናፊ መስሎ የሚቀርበው ቁሳዊው ዓለም፣ ጊዜው ሲደርስ ግን (When it matters most) ምንጊዜም አሸናፊው መንፈሳዊው ዓለም ሲሆን ይታያል፡፡ ሆኖም ኅብረተሰብ የተረጋጋ ሕልውና ይኖረው ዘንድ ካስፈለገ ሁለቱን ዓለማት ማስታረቅ፣ ቢቻል ማዋሀድ ያስፈልጋል፡፡

የአውሮፓዊያን ስልጣኔ ትልቁ ድክመቱም ይሄው ይመስለኛል፡፡ እነፍሮይድና ካርል ዩንግ እስከ ደቀመዛሙርታቸው ተነስተው ቀልብ እስኪያስታጥቁት በነኒቼ ልሳን አረፋ እየደፈቀ፣ በነካሙ ብዕር ተስፋ ማጣትን እየሞዘቀ ዘለቀ፡፡ እንዲያውም ሁለቱ የዓለም ጦርነቶችም የአንድ ዘመን ሞገሱ የተገፈፈ የጋራ ቀልብያ (Collective consciousness) ትርምስ ውጤት ስለመሆኑ የሚሰብኩ ሙህራን ተነስተዋል፡፡
.
.
.

እኔ ግን እላለሁ... አንድን ኅብረተሰብ ልታውቁት ስትሹ ተረኮቹን መርምሩ፡፡ ተረኮቹ ልጆቹን እንደምን እንደሚገራ ይነግሯቸኋል፤ ስለሴቶቹ ያለውን እሳቤ ያሳውቋችኋል፤ ስለፍትህ ያለውን አረዳድ ያመሰጥሩላችኋል፡፡ በየትኛው እንሰለጠነ፣ በየትኛው እንደሰየጠነ፣ በየቱ ደግሞ ኋላ እንደቀረ ይገልጡላችኋል፡፡ ተረክ ይፈውሳል፤ ያድሳል፤ ያነሳሳል፡፡ ምክንያቱም ተረክ ያለው ምናብ (imagination) አለው፡፡ ምናብ ያለው ኅሊና አለው፡፡ ኅሊና ያለው መለኮትን ያውቃል፡፡ ተረኮች - የመንፈስ ልምሻ ፈውሶች፣ መጽናኛዎች፣ ቃልኪዳኖች ናቸው፡፡

በእርግጥም ተረክ ያለው ምናብ አለው፡፡ ተረክ ያለው ታሪክ፣ ቀለም፣ ማንነት ይኖረዋል፡፡
በበኩሌ ሥልጣኔ ራሱ የታሪክ ነገረ ሥልት እና ጭብጥ ለውጥ ውጤት ይመስለኛል፡፡ A shift in storytelling is a shift in civilization. የግሪክና የመካከለኛው ዘመን የኤሮፓ ሕዳሴ ጉዞ ለዚህ ጉልህ ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ በአሥራ አራተኛው ክፍለዘመን የኤሮፓ ሕዳሴ ሲጀመር እኛም እነሱም እኩል የክርስትና ሚቶሎጂ ተከተዮች ነበርን፡፡ እንዲያውም በሮም ካቶሊካዊከት ቤክርስቲያን ከእኛ ሀገር የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሢሶ መንግሥትነት አልፋ የሙሉ መንግሥት ሥልጣን ባለቤት ነበረች፡፡

እነሱ ለውጡን ከመሰዊያው ከቤተክርስቲያን ጀመሩት፡፡ ሚቶሎጂውን በድርሰት፣ በግጥም፣ በፊልም ጥበብ፣ በድራማ፣ በተውኔት ለወጡት፡፡ ቤተክርስቲያናቱ ወደ ተውኔት መድረክነት ተቀየሩ፡፡ ሲያልቅ ሁለታችንም ከስረናል፡፡ የእነሱ ስልጣኔ ከተፈጥሮ የተነጠለ ኃሪሶት የሌለው በድን ሆነ፤ የእኛ ደግሞ የተቸነከረ፣ መታደስ ያቃተው ቆሞ ቀር...
❤8
I have an old soul,
art makes me happy,
my metaphor defines me.

I have fascination in poetry,
rhymes make me feel the world.

I love to read,
books comfort me.

I am a man of philosophy,
to seek wisdom is my purpose.

I write
to make me feel alive.

I express my soul
through art.

[Weirdo ]
❤14
Forwarded from Seblework Old Books ™
“ Pain and suffering are always inevitable for a large intelligence and a deep heart. The really great men must, I think, have great sadness on earth. You see I so love humanity that would you believe it? I often dreamed of forsaking all that I have and going to become a Sister of Mercy. I close my eyes and think and dream, and at that moment I feel full of strength to overcome all obstacles; no wounds no festering sores could frighten me then. I would bind them up and wash them with my own hands, I would nurse the afflicted, I would be ready to kiss such wounds.”

— Fyodor Dostoevsky

Crime and Punishment 📚
❤6
Forwarded from Selenophile
🎨 𝗛𝗮𝗽𝗽𝘆 𝗜𝗻𝘁𝗲𝗿𝗻𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻𝗮𝗹 𝗔𝗿𝘁𝗶𝘀𝘁 𝗗𝗮𝘆! 🎨
꧁⎝ 𓆩༺✧༻𓆪 ⎠꧂

"𝑾𝒉𝒂𝒕 𝒘𝒐𝒖𝒍𝒅 𝒍𝒊𝒇𝒆 𝒃𝒆 𝒊𝒇 𝒘𝒆 𝒉𝒂𝒅 𝒏𝒐 𝒄𝒐𝒖𝒓𝒂𝒈𝒆 𝒕𝒐 𝒂𝒕𝒕𝒆𝒎𝒑𝒕 𝒂𝒏𝒚𝒕𝒉𝒊𝒏𝒈?"
- 𝐕𝐚𝐧 𝐆𝐨𝐠𝐡

🎬 You know, life would probably 𝐬𝐭𝐢𝐜𝐤 and 𝐬𝐭𝐨𝐧𝐞𝐬 if we never had courage to attempt anything. 𝐉𝐮𝐬𝐭 𝐥𝐢𝐤𝐞 𝐢𝐧 𝐚𝐫𝐭, if you have no courage how will you create your 𝐦𝐚𝐬𝐭𝐞𝐫𝐩𝐢𝐞𝐜𝐞? Because 𝐛𝐞𝐡𝐢𝐧𝐝 𝐞𝐯𝐞𝐫𝐲 𝐦𝐚𝐬𝐭𝐞𝐫𝐩𝐢𝐞𝐜𝐞 is an 𝐚𝐫𝐭𝐢𝐬𝐭 with the 𝐠𝐫𝐞𝐚𝐭𝐞𝐬𝐭 𝐦𝐢𝐧𝐝 to 𝐜𝐫𝐞𝐚𝐭𝐞 what your 𝐡𝐞𝐚𝐫𝐭 is telling you. 𓂃✍︎

🎭 𝑨𝒓𝒕 is more than just 𝐜𝐨𝐥𝐨𝐫𝐬 on a canvas or 𝐰𝐨𝐫𝐝𝐬 on a page — it is the 𝒗𝒐𝒊𝒄𝒆 𝒐𝒇 𝒐𝒖𝒓 𝒉𝒆𝒂𝒓𝒕𝒔, the 𝐬𝐭𝐨𝐫𝐲 of our 𝐬𝐨𝐮𝐥𝐬, and the 𝐦𝐢𝐫𝐫𝐨𝐫 of our 𝐬𝐨𝐜𝐢𝐞𝐭𝐲. To every 𝒑𝒂𝒊𝒏𝒕𝒆𝒓, 𝒘𝒓𝒊𝒕𝒆𝒓, 𝒎𝒖𝒔𝒊𝒄𝒊𝒂𝒏, 𝒅𝒂𝒏𝒄𝒆𝒓, 𝒑𝒉𝒐𝒕𝒐𝒈𝒓𝒂𝒑𝒉𝒆𝒓, 𝒄𝒓𝒆𝒂𝒕𝒐𝒓, 𝒂𝒏𝒅 𝒅𝒓𝒆𝒂𝒎𝒆𝒓 out there: your gift 𝐦𝐚𝐭𝐭𝐞𝐫𝐬. You turn ordinary moments, steps, shots, design, and letters into something 𝐛𝐞𝐚𝐮𝐭𝐢𝐟𝐮𝐥. ִ་༘࿐𝄞𝄢℘

𝙒𝙚 𝙖𝙧𝙚 𝙖𝙡𝙡 𝙖𝙧𝙩𝙞𝙨𝙩𝙨, 𝙥𝙖𝙞𝙣𝙩𝙞𝙣𝙜 𝙤𝙪𝙧 𝙤𝙬𝙣 𝙨𝙩𝙤𝙧𝙮 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮𝙙𝙖𝙮.

So with that, may your imagination never run dry our dearest 𝘼𝙧𝙩𝙞𝙨𝙩𝙨! ˙✧˖°📷 ༘ ⋆。˚
❤8
The poetry of a sun- flower💛
እንደ አፍሪካ የደነቆረ አህጉር ያለ አይመስለኝም ።

በጣም የሚገርመኝ ነገር አህጉሩ ምን ያክል የደነቆረ እንደሆነ ለመመልከት አንዲት ትንሽ የኢሮፕ ሀገር ከአፍሪካ ጋር forum ታደርጋለች ለምሳሌ የጣሊያን አፍሪካ ፎረም የፈረንሳይ አፍሪካ ፎረም ነገ የሚጀመረዉ ሩሲያ አፍሪካ ፎረም ተመልከቱልኝ እንግዲህ 54 ሀገራት የያዘችዉ አፍሪካ በአንዲት ሚጢጢ ኢሮፕ ሀገር ጋር forum ስናደርግ በጣም አስቂኝ ነዉ ።

ለምን ጣሊያን እስያ ፎረም ለምን ጣሊያን ደቡብ አሜሪካ ፎረም ለምን አንዴት የአፍሪካ ሀገር ( ለምሳሌ ኢትዮጵያ ) ከኢሮፕ ጋር ፎረም አታደርግም ? እነሱም ይጫወቱብናል እኛም የእነሱ መጫወቻ አሸንጉሊት እንድንሆን ፈቅደናል ።
😢12🔥8
ባሻዬ! በአርሲ ወገኖቻችን ላይ በተደጋጋሚ ለደረሰው ግድያ እንዲሁም አገራችን አሁን ላለችበት ምስቅልቅል መንግሥታችንን ለምን ተጠያቂ ታደርጋለህ? መንግሥታችን ምን ያድርግህ?

ቆይ ቆይ! ጄሊፊሽ ስለተባለው የባህር እንሰሳ ተፈጥሮ አንድ ነገር ልንገርህ፣

ጄሊፊሽ አጥንት የለውም፣ አንጎል የለውም፣ ልብ የለውም፣ ዓይን የለውም እንዲሁ በደመነፍስ ይኖራል። ታዲያ ጄሊፊሽ የሆነውን መንግሥት ምን አድርግ ነው የምትለው?ባሻዬ! በአርሲ ወገኖቻችን ላይ በተደጋጋሚ ለደረሰው ግድያ እንዲሁም አገራችን አሁን ላለችበት ምስቅልቅል መንግሥታችንን ለምን ተጠያቂ ታደርጋለህ? መንግሥታችን ምን ያድርግህ?

ቆይ ቆይ! ጄሊፊሽ ስለተባለው የባህር እንሰሳ ተፈጥሮ አንድ ነገር ልንገርህ፣

ጄሊፊሽ አጥንት የለውም፣ አንጎል የለውም፣ ልብ የለውም፣ ዓይን የለውም እንዲሁ በደመነፍስ ይኖራል። ታዲያ ጄሊፊሽ የሆነውን መንግሥት ምን አድርግ ነው የምትለው?
😢13❤7
❤3
የጥበብ - መንገድ ™
Photo
ጠቢባን ሰብሰብ ብለዉ ስለ ፍቅር እያወሩ ነዉ ። ከጠቢባኑ መካከል የባለቅኔዉ አጋቶን የሚያወራበት ተራ ሲደርስ ፍቅርን እንደሚከተለዉ ገልፆታል ፦

በርግጥ ፍቅር ባለ ቅኔ ብቻ ሳይሆን የባለቅኔነትም ምንጭ ነዉ ። የፍቅር እጅ የዳበሰዉ ማንኛዉም ሰዉ ከዉስጡ ቅላፄ ኖሮ ባያዉቅ እንኳ በቅኔ ይሞላል ። በርግጥ የዝናን ብርሀን ለማየት የሚታደለዉ በፍቅር የተቃኘዉ አርቲስት መሆኑን ጥበብን የሚያዉቅ ሁሉ ያዉቀዋል ። ይህም ፍቅር በራሱ ቅኔና ጥበብ አዋቂ መሆኑን ያሳያል ። ደግሞስ ለነፍሳት ሁሉ መፈጠር መንስኤዉ ፍቅር ስለ መሆኑ የሚክድ አለ ? ፍጥረት ሁሉ ከፍቅር ጠቢብነት የሚመነጭ አይደለምን ?

አፖሎ የቀስት ዉርወራ የህክምናና የምትሀትን ጥበብ የፈጠረዉ በፍላጎትና በፍቅር መሪነት አልነበረም ። በርግጥ አፖሎም የፍቅር ደቀ መዝሙር ነበር ። ለአቴን የሽመና ጥበብ ፣ ለሚዩሰስ የዜማ ርቀት ለዜዩስ ግዛት ዉበት ምንጩ ምን ነበር ? ሁሉም ከፍቅር መንጭቶ ስለ ፍቅር የተፈጠረ አይደለምን ?

በጥንቱ ዘመን አማልክት የሚገዙት በአሰገዳጅ ህግጋት ስለ ነበር በመካከላቸዉ አስከፊ ግብር ይከሰት ነበር ። ሆኖም ፍቅር ከተወለደ ጊዜ አንስቶ በምድርና በሰማየ ሰማያት ያለዉ ሁሉ በሰላምና በአፍቅሮት ተሞላ ።

ጥንታዊ ንግርት እንደሚያሳየን በሄሶይድና ፓራሜንዲስ ይካሄዱ የነበሩ ከአስገዳጅነት የሚመነጩ እስርና ግርፋቶች የፍቅር አምላክ ባለመኖሩ የተከሰቱ ነበሩ ። የፍቅር አምላክ ከተፈጠረ በኋላ ግን በመንግስተ ሰማያት ዉስጥ ከሰላምና ደስታ በቀር ምንም ግጭትና ጥላቻ ተከስቶ አያዉቅም ። ምክንያቱም የፍቅር አምላክ የፍቅርን አገዛዝ አስፍኗል ።

ስለሆነም ፍቅር ፍፁም መልካምና ፍፁም ፍትሀዊ ነዉ ። ለመልካሙና ለፍትሀዊዉ ሁሉ ምንጭም ፍቅር ነዉ እላለሁ ።

ነጎድጓዳማዉን ወጀብ አስክኖ ምድርን ሰላም የሚያዉላት አዉሎ ንፋሱን ፀጥ አድርጎ ለምስኪኑ ፍጡራን ሰላማዊ እንቅልፍ የሚቸረዉ ፍቅር ነዉ ። ሁለት ጥንዶችን ወደ አንድ ጥልቅ ደስታ የሚያመጠዉ ፍቅር ነዉ ። ሰዉን ከምሬትና ጥላቻ ፈዉሶ ልበ ብሩህነትን የሚያሰርፀዉ ፍቅር እንጂ ሌላ አይደለም ።

እናም ሁላችን የሰዉንም ሆነ የአማልክትን ቀልብ የሚሰልበዉን ጥዑም ዜማዉን አርአያ አድርገን ዉብ የክብርና የመወድስ ዜማ እያዜምን ቅኔም እየዘረፍን የፍቅርን ዳና እንከተል ።

<< Symposium >> Plato

የስዕሉ ባለቤት አርቲስት ፍራንቼስኮ ሃየዝ በ1859 The Kiss የተሰኘ የስዕል ስራ ነዉ ።
❤11🥰2
Forwarded from Seblework Old Books ™
#እንደ ማስታወቂያ 🙏📖

@sebleold inbox 📥

0946523397
❤7
❤1
የጥበብ - መንገድ ™
Photo
ከቡዳፔስት እስከ ኮተቤ ተራራ

አንድ ወቅት ነበር… በሶሻሊስት ኢትዮጵያ ዘመን አገሪቱ ከምሥራቁ ጎራ ጋር በነበራት ጠንካራ ወዳጅነት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ለትምህርት ወደ ቡልጋሪያ፣ ምሥራቅ ጀርመን፣ ሩማንያ እና ሀንጋሪ ይላኩ ነበር። ከእነዚህም ወጣቶች መካከል አንዱ፣ የኮከበጽባህ ተማሪ የነበረው .. ከራሺያ ኤምባሲ ጀርባ ይኖር የነበረው (ስሙ ይቆየን) ሕክምና ለመማር ወደ ሀንጋሪ ያመራው ልጅ ታሪክ ሁሌም ይገርመኛል ። እኔ አራት አመት ታላቁ ነኝ፡፡

ትምህርቱን አጠናቆ፣ የሕክምና ልብሱን ለብሶ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ በ እጣ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል በሐኪምነት ተመደበ። ነገር ግን የዚህ ባለሙያ ፍላጎት ከመደበኛው ዘመናዊ ሕክምና ወሰን አልፎ የራቀ ነበር። ... ጸጉሩን እና ጢሙን አሳድጎ ላየው ባህታዊ እንጂ ሃኪም አይመስልም ነበር፡፡ እሚገርመው እጅግ ትሁት እና በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ነበር .. ከ 1975 እስከ 82 ምኒሊክ ሆስፒታልን እሚያስታውሱ ይህን ሰው ልብ ይሉታል፡፡ ባላቃልቻው ዶክተር እሚሉትም ነበሩ፡፡

ከቢሮው ጠረጴዛ ሁልጊዜ የማይለያት አንዲት ግዙፍ መጽሐፍ ነበረች። የሕክምና መጽሐፍ የምትመስል፣ ነገር ግን ... ካወቃችሁት የቱባው መንፈሳዊ ጸሐፊ ሎብሳንግ ራምፓ ( በ እውነተኛ ስሙ Cyril Henry Hoskin - his image is placed here) የፍልስፍና እና የትምህርት ኢንሳይክሎፒዲያ የነበረች።

ይህ ዶክተር ታዲያ በ ራምፓ ተለክፎ ይሁን ተመስጦ ... ስለ ተፈጥሮአዊው የሰው ልጅ የመንፈስ ብርሃን (ኦራ የሚባለው Aura) እና በሰው ዓይን ስለማይታዩት ረቂቅ ኃይሎች በጥብቅ ያምን ነበር። ታካሚዎች ወደ እርሱ በሚመጡበት ጊዜ፣ ራጂ ወይ ኤክስሬ ከማዘዝ 3 በ 4 ጉርድ ፎቶ እንዲያመጡለት ይጠይቅ ነበር "የበሽተኛው ፎቶግራፍ ከተነሳ፣ በሰው ዓይን የማይታዩት መንፈሳዊ ምስሎች እና የሕመም ምልክቶች በፎቶው ላይ ስለሚታዩ ፎቶ አምጡልኝ ... ከሰው አይን ያመለጡ በ ካሜራ ሌንስ ይይዛሉ " በማለት ያስረዳ ነበር። .. ያኔ ቀበና አካባቢ ያሉት እነ ፎቶ አሰፋ እነ ፎቶ ይልማ ... ኝብ ሰፈር የነበረው የእትዬ ገበያነሽ ፎቶ ቤት ገበያቸው ደርቶ ነበር፡፡

በጊዜ ሂደት፣ ይህ ፍልስፍናው በሕክምና ሙያው ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመረ። ታካሚዎቹን በመድኃኒትና በዘመናዊ መሣሪያዎች ብቻ ከመመርመር ይልቅ በራምፓ መንፈሳዊ ዕይታ መነፅር መመርመርን አበዛ። ይህ አቀራረቡ ግን ከሆስፒታሉ የሕክምና ሥነ-ምግባር (Medical Ethics) እና ከሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ጋር ከፍተኛ ውዝግብና ጭቅጭቅ ፈጠረ። በመጨረሻም ከደከመበት የሆስፒታል ሥራው ለመልቀቅ ወሰነ። አክችዋሊ "አብዷል" ብለው ነው ያባረሩት፡፡ ... ከደርግ እስርም የጠበቀው አብዷል መባሉ ሳይሆን አልቀረም፡፡

ከሆስፒታሉ ከተሰናበተ በኋላ፣ በዚያን ዘመን የአዲስ አበባ ዳርቻና ይመስል ወደነበረው ኮተቤ ብረታብረት አካባቢ አመራ .. ከፍተኛ 16 ቀበሌ 01 የነበረውን የ እናቱን ቤት ሽጦ ኮተቤ 1000 ካሬ ቦታ በ 1500 ብር ገዛ (ተመራ) ... (በደርግ ግዜ ቦታ በሳንቲም ደረጀ ነበር እምትመራው ) ። በዚያም ላይ ቤቱን ሰርቶ፣ የካበተውን የሕክምና ዕውቀቱን ከመንፈሳዊው የራምፓ ፍልስፍና ጋር በማዋሃድ ሰዎችን መፈወስ ጀመረ።

ዛሬም ቢሆን በኮተቤ ኮረብታው ላይ የሚገኘውን ይህን ሰው፣ አብዛኛው ሕዝብ እንደ መደበኛ "ጠንቋይ" አድርጎ ይመለከተዋል። ነገር ግን እርሱ የሚያካሂደው ጥበብ የራምፓን የረቂቅ ዓለም ዕውቀት መሠረት ያደረገ ነው። አሁንም ቢሆን ሰዎች ወደሱ ይሄዳሉ፡፡

ሰዎች የሕመምተኞቻቸውን ፎቶግራፍ ይዘው ወደ እርሱ ይሄዳሉ። እርሱም ፎቶውን በመመልከት የሕመሙን መንስኤ ይናገራል፤ ሕመምተኛው ይድናል ወይስ ይሞታል? የሚለውን ይተነብያል፤ እንዲሁም ምን ዓይነት የሕክምና እንክብካቤ ወይም የዕፅዋትና የመንፈስ ሕክምና እንደሚያስፈልገው ይወስናል።

ዘመናዊውን የሳይንስ ትምህርት ከምሥራቅ አውሮፓ ቀስሞ፣ የሰው ልጅ ረቂቅ አካልን ደግሞ ከራምፓ መጻሕፍት ተማርኮ፣ በሳይንስና በመንፈሳዊነት መካከል የተወጠረው የዚህን ሰው ቤት ጎብኝቻለሁ ፣ በህመሜ ግዜ ... ነጭ ሳሪያን ኮት እና ክሬም ካኪ ሱሪ ለብሷል በጣም ንጹህ ሰው ነው የግል ንጽህናው ማለቴ ነው .. ቤቱ ስትገቡ መልካም መአዛ አለው ... ምንም ጭሳ ጭስ የለም ... ሰፋፊ መስኮቶች ብሩህ ብርሃን እና መስኮቶቹ ወደ የካ ተራራ ያሳያሉ ... ሶፋዎቹ የቀርክሃ እና የ እንጨት ናቸው ... ብዙ መጽሃፍት አንዱን የግድግዳ ክፍል ሞልተውታል ፡፡
ድምጹ ጎርናና ... በጣም ቀጭን ጢሙም ጸጉሩም ድሬድ የሆነ ጎራዳ አፍንጨው ላይ ክብ መነጽሮች ያስቀመጠው ይህ ሰው .. ከቤቱ አይወጣም ... ይህ ታሪክ የሰው ልጅ ዕውቀትን፣ እምነትን እና የሕክምናን ወሰን እንዴት አጣጥሞ ለመኖር እንደሚሞክር የሚያሳይ ሰው ነው ።

© Siendu Gebre
❤15
Forwarded from Seblework Old Books ™
« የታሪክ »

« የልቦለድ »

« እንዲሁም የተለያዩ
መንፈሳዊ መጽሐፍት»  
    
ካሉበት መጥተን እንገዛለን ።
ይደውሉልን ።
ስልክ 
0946523397
           0967594409

@sebleold inbox 📖
❤4
'' ሕግ የሰው ልጅ የመጨረሻው መጠጊያ ካልሆነ፣ ኅብረተሰቡ ወደ ጫካ ሥርዓት መመለሱ አይቀሬ ነው። ''

ዳኝነቱ ለእውነት ሳይሆን ለሥልጣን ያደላ ይመስላል።

“ ወንጀለኛው ዳኛ ማለት እውነትን እያወቀ በውሸት የሚፈርድ ሳይሆን፣ እውነትን ለመከላከል አቅም አጥቶ የሚጸጸት ነው።

-"እውነተኛው ወንጀለኛ ሕጉን የሚያስፈጽመው ሳይሆን ሕጉ ራሱ ሊሆን ይችላል።

-"ፍትሕ የኃያላን መጫወቻ እስከሆነች ድረስ ሰላም አይኖርም።

ወንጀለኛ ው ዳኛ 📖

© ሀዲስ ዓለማየሁ

@sebleworkbooks inbox
🔥5❤4