ፍልስፍና
623 subscribers
491 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
Forwarded from አርምሞ🧘🏽‍♂ (ሞገስ ዘአምድ Gυrυ🪽)
ሶስቱ ነብያት
|
|
1. ኒቼ 2. ካርል ዩንግ 3. ዶስቶቪስኪ
|
የነብይነት ጸጋ ነበራቸው። የኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጸሀፎቻቸውን ደፍራ ከቅዱሳት መጸሀፍቷ ብትቀላቅል ብዙ ትጠቀማለች።
|
|
1. ኒቼ
በተቋማዊው ክርስትና ላይ የበረታ ሒስ በመሰንዘር ይታወቃል። " የመጨረሻው ክርስትያን መስቀል ላይ ሞቷል" እስከማለት የደረሰ ጭፍለቃው ስነጽሁፋዊ ግነት እንጂ literall(አማናዊ) ትርጉም አይደለም። የdetail አቅሙን ያየ ሌጣውን ትርጉም አይወስድም። ኒቼ cult ተሰርቶበታል። ፈጣሪን በአኗኗራቸው ክደውት በአንደበታቸው እግዜር አለ የሚሉት ቅዘናሞች አፍ ማስቲካ ሆኗል።
|
" እግዜር ሙቷል" የምትል ሀረጉን መዘው ፍዳውን ያሳዩታል።
እስቲ ሙሉውን.....
|
" እግዜር ሙቷል። አዎ ሞቶ ይቀራል። ደሞ እኛ ነን የገደልነው። ከግድያም ታላቁን ግድያ የፈጸምን እኛ ሰዎች ሊመቸን ኖሯል? ምድሪቱ ያላትን ቅዱስ እና ታላቁን ሀይል በቢላችን ደሙ አፍስሰናል! ይሔን ደም ከእጃችን የሚያጥብልን ማነው? የቱ ፌሽታ ካሳ ሊሆን? የቱ አስደንጋጭ ጫወታ ሊያረሳሳን? እውነት? ኤግዜር ለእኛ ካደረገልን በላይ ለራሳችን ማድረግ እንችላለን? ይሔን ለራሳችን በማድረግ አማልክት መሆን ምን ሊረባን?"
|
|
ቃል በቃል አልተረጎምኩም። ፍረዱኝስቲ ይሔ ወንጌል አይደለም ወይ? ስነጽሁፋዊ ውበቱ ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዘኛ ሲሔድ ከእንግሊዘኛም ወደ አማርኛ ስመልሰው ተዳክሟል። "በራሳችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፣ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፣ ደሙ በልጅ ልጆቻችን ይሁን" የሚሉ የመጸሀፍ ቅዱስ ንግግሮች ከላይ ባለው የኒቼ ሀተታ ካልተፈቱ ግራ ናቸው። በተሰቀለው ኢየሱስ ላይ ሰው ሁሉ አንድ ነው ባይ ነው። መሲሁ የትኛውም ዘመን ላይ ቢመጣ አገዳደሉ ይለያይ እንጂ ሟች ነው።
"እኔ ይሔን አላደርግም" ያለ ምእመን እንደ ጴጥሮስ ሊክድ የተዘጋጀ ነው።
📍 የተነሳውን ኢየሱስ በማመን/በመሆን ግን ልዩነት አለ ይላል።
ኒቸ በስልጣን እንጂ በጨዋነት አያምንም። ትንሳኤ ስልጣን ነው ይላል the will to power መጸሀፉ ላይ። እንደ መጀመሪያው ሟች አቤል ትሁት ሆኖ ሞቶ መቅረት ወይስ እንደ መጨረሻዉ ሟች ኢየሱስ እውነት ተናግሮ ሞቶ መነሳት?
|
|
2. ካርል ዩንግ
|
የሲግመን ፍሮይድ ተማሪ ነበር። ከፍሩይድ ይበረታል ይሉታል። አባቱ ፓስተር ነው። በሙሉ ስሙ ካርል ጉስታቭ ጁንግ(ዩንግ) ይባላል። ይሔም እንደ ኒቼ ጀርመናዊ ሲሆን psychiatrist, psychoanalys እና ሳይንቲስት ነው። ድርሳኖቹን ያነበበ ከ 149 አመት በፊት አለም እንዲህ አይነት ደፋር ነበራት ወይ ማለቱ አይቀርም!
|
ታዋቂ መጸሀፉ the red book ይሰኛል። ከዲያቢሎስ ጋር በመንፈሱ ተገናኝቶ የጻፈው ነው። ከዚህ ገጠመኙ ተነስቶ የግል ሰይጣናችንን መገናኘት አለብን ይላል። በባህል እና ሀይማኖት የተወገዘ ድብቅ ፍላጎታች የሚፈጥረው Shadow አለ። ስንቆጣ ልጆቻችንን እስከመግደል የደረሰ ቅጣት የሚቀጣቸው በዚህ Shadow ውስጥ የሚገለጠው ሰይጣን ነው።
" ተቆጡ በቁጣችሁ ላይ ጸሀይ አይግባ" ካለ በሗላ "ለዲያቢሎስም እድል ፈንታ አትሰጡት" ይላል። አጅሬ ሹልክ ትላለች ሲለን ነው።
|
ሴጦ እየተገለጠ ልጆቻችንን ይቆጋል፣ ወዳጆች bully ያደርጋል፤ ስራችሁን ብታጡስ እያለ ያቦካል። ለኛ አይታይም! ባለቤቱ ፍሬውን እያየ የራሴ ጠላት እራሴ ነኝ ብሎ የታገለ አንድ ቀን እንደ ዩንግ ይገናኘዋል። ክስተቱ shadow encounter ይባላል።
የኛ ሰይጣን ከዋናው ሰይጣን ይለይልናል። በውጣችን ሆኖ ማስጠቃቱን ያቆማል።
" እባብም እርግብም ሁኑ የሚለው ትዕዛዝ ይፈጸማል" ነው መደምደሚያው!
|
ኒቸ እግዜርን የገደለ ሰው እረፍት የለውም ሲል ዩንግ ተቀብሎ እግዜር በውስጡ የተነሳለትን ያሳያል። ሰው ሰይጣንን ፊት ለፊት ካገኘው በሗላ 3 stage አለው ይላል።( በቀጣይ ጽሁፍመጣበታለሁ)
|
|
3. ዶስቶቪስኪ

ሩስያዊ ነው። ከ105 አመት በፊት የተገኘ ደራሲና ጋዜጠኛ። የኒቸ literatural prophecy ደርሶበታል። ተቋማት ደግፈው ያቆሙት የስነምግባር ሰው የፈረሱበት እለት ሊሆን የሚችለውን ዶቶቪስኪ ሆኖት ጻፈው።
|
ኒቼን አምኖ በዩንግ መንገድ ያልሔደ ሰው ዶቶቪስኪን ይመስላል። የስርቻውን ሰው ይሆናል። the underground man ይለዋል።
ፍርፋሪ እና ልጆች መኖር ያስቀጥሉት የነበረው የተለመደው ሰው ከ existential (ህልውናዊ) ጥያቄዎቹ ፊት ስላልቆመ የስነ-ምግባር ሰው ይመስላል ባይ ነው።
|
ዶቶቪስኪ በስሜት ሆኖት ያሳየናል። ከ Red bookም በላይ እጅግ የምፈራው መጸሀፍ ነው። ፍርሀት እንደ አይጥ ስርቻ ለስርቻ የሚያርመጠምጠኝ ነበርኩና የሚለውን ሳነብ ያ ቦታዬ ያልዳነ ያህል ያመኛል። ልቤን ስውር እያደረገኝ ስንቴ አስቀመጥኩት?
|
በስራ እና በልጅ ላመልጣት የነበረች ክፉ ጥረት ነበረች። በሁለቱም የተሳካልኝ ሰው አይደለሁምና ህልውናዊ ጥያቄዎቼ ፈጠው አላላውስ አሉኝ። ዛሬ የተወለድኩ ያህል "ከየት መጣሁ? ወዴት ልሒድ? ማነኝ?" ምናምን አልኩ። ሰውነቴ እስር ቤት ሆኖብኝ መተንፈስ ተቸግሬአለሁ። በየአመቱ ይሔን መጸሀፍ ጀምሮ ያለመጨረስ እቅድ አለኝ። ዘንድሮም እሱ ላይ ነኝ። በጨዋታ፣ በፌ.ቡ፣ በበርጫ፣ በጨብሲ፣ በኢየሱስ፣ በወንጌል፣ በታማልዳለች አታማልድም፣ በጨላ አጫብለን የረሳነውን አማናዊ ጥያቄ እና ፍላጎታችንን ያፈጣል።
|
ሶስቱ ተባብረው የሚሉት ይሔን ነው።
" በስነ-ምግባር አታመልጡም! ለጊዜው የጸጥታ ተቋማት ከሌቦች ጋር ስላልሰሩ አትሰርቁም፤ አማኝ የመሰላችሁት የሀይማኖት ተቋማት ብሔር ስላልገባቸው ነው"

.
ባጠቃላይ
#የሰላም_ዘመን_አልፎ_የጽድቅ_ዘመን_ይመጣል እያሉን ነበር።



፦ Behailu_mulugeta


@rasnflega