ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞
439 subscribers
354 photos
8 videos
43 links
ስለ ሌላ ስለምንም አናወራም...ግን " በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" ስለተባለለት ስለ እርሱ.......እናውጃለን!!!!
Download Telegram
“ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አልረሳንህም፥ ኪዳንህንም አልወነጀልንም።”
— መዝሙር 44፥17

እስከ ዛሬ ድረስ፥ እግዚአብሔር በነፍሳችን ላይ፥ አንድም ቀን ራሱን በምንም ሁኔታ ነቅንቆ አያዉቅም፥ ቡቃያዉንም በሚታረመዉ ዘር አይቀጣዉም፥ ደግሞም አይለዉጠዉም። ስለዚህ "ክስተቶች" እኛን እንጂ እርሱን በታሪክ መካከል አስገርመዉት አያዉቁም፤ እናም የቀየረን የሚቀየረዉ የመከራዉ ክስተት ሳይሆን ያ "ማለዳ ማለዳ" የተባለለት የጉልጎታዉ አዛኝ ብርቃችን ነዉ።
ለዚህም ክስተቶች በባህሪያቸዉ ወይ ያስደንቃሉ ካልሆነም አስንቀዉ ያበቃሉ፤ ይህም ቢሆን በክርስቶስ ፊት የብርታት ቀለባችን ነዉ፤ እያለፈ ያለዉ ወንዝ ካለማቋረጡ የተነሳ እየተመለሰ ያለ ቢመስለን እንኳን፥ እግዚአብሔር በሂደት ላይ ስለሚገኝና ራሱም በነገሩ መካከል ስለሚታይ የማቋረጫዉን መንገድ መረዳታችን እንደሚበልጥ ምነዉ ቀድመን ባወቅን!!!፥ እነሆ ወንዙ ዳር ያለን እኛ፥ ብዙ ነገሮች ከወንዙ ላይና ዉጭ በዙሪያችን ሲያልፉ፥ እማኞች ነበርን፤ ይሄም ቢሆን በእኛ ላይ የደረሰዉ የብዙ ክስተቶች ስብጥር ነዉ ብለን ዝም አልን እንጂ፥ በየትኛዉም እዉቀት ከኪዳኑ ዘወር ልንል የሚያበቃን ነገር አላገኘንም!!
ክርስቶስ ያሳየን ኪዳን እኮ፥ ነፍሳችን ዉስጥ የልጁን ሞት ዘወትር የሚመለከት፥ ብርቱና የሚጣራ ህያዉ ደም ነዉ፤ እንግዲህ ከክስተቶቻችን በላይ የምንፅናናበት፥ የከበረ የነፍሳችን ሰረገላ ይሄዉ ኪዳን ነዉ!
ስለዚህ እኛም እንዲህ እንላለን “ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አልረሳንህም፥ ኪዳንህንም አልወነጀልንም።”

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
7
“በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።”
— ኢያሱ 10፥21
እነሆ እግዚአብሔር ልክ ነገር እያደረገ ነዉና አላዋቂም ሆነ አዋቂ በፊቱ ዝም ይበል፤ ገደቦቻችን ከእኛ ትንታኔ ዉጭ ሲሆኑ ልክ የሚል መልስ ይኖራቸዋል!፥ እንዴት መሰላችሁ!፥ ሰዉ በኤደን ገነት ለመኖር ልክ መሆን ሳይጠበቅበት፥ ልክ ያልሆነዉን በልክነት ዉስጥ ይለይ ዘንድ ፥ እንደሚጠበቅበት ማሳሰቢያ ተነገረዉ፤ ይሀዉላችሁ ልክኛነት፥ እንዲሁም ከምህረት የመነጨ የበዛ ርህራሄን መግለጥ፥ ከክርስቶስ መገለጥ በፊት የእኛ ገደብ ነበሩ፥ ሰዉ እኮ ማመን የከበደዉ የታማኙ ልጅ ነበር።
ይሄዉ ሰዉ፥ ሁሉ ተሰቶት ሁሉን ከመጠቀም ራሱን የሚገዛበት መንፈስ፥ እንዲያዉ በፀጋ መልሶ ተሰቶታል፥
እንዲያዉም በዉጊያ መካከል የነበሩት የእስራኤል ልጆች ከጠላት ጋር ጉልበት ለጉልበት እየተፈታተሹ፥ አንገት ለአንገት እየተናነቁ እንኳን እግዚአብሔር ግን ሕዝቡ እንደሚሰማዉ አይሰማዉም፥ ይልቅስ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ስለመኖሩ ይቆጣጠራል፥ ይህ ማለት ያለ አብ ፍቃድ የሆነ አንድስ እንኳን በእኛ ላይ አልሆነም፥ ለዚህም ነዉ እግዚአብሔር ከጀብድ ይልቅ ምሳሌዉን ወዶ የምታገኙት!
እየታገሉን ቢመስለንም እየተሸነፈ ያለን የጠላት መንጋ ለማየት፥ የክርስቶስ አሸናፊነት ዘላለማዊ ብቃታችን ነዉ።
#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
7👍5
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች!
መልካምነትን ከቅርበት ዉስጥ የምንወስደዉ በረከት ነዉ፥ እግዚአብሔር መልካም ነዉ ስንል ደግሞ፦ ከነገሮች የመጉዳት አቅም በላይ፥ የዉጤቱ ሚዛን እርሱ ጋር ብቻ ይኖራል ብለን፥ መደምደም የሚያስችለንን ዉጤት ቀድመን አዉቀናል እያልን ነዉ። መልካምነት እንዲህ ከሆነ፥ ቅርበታችሁ ደግሞ በማይፋቅ አዲስነት ዉስጥ የተቀመጠ የዋጋ ጣሪያ በመሆኑ፥ ደግሞ በዘመን መጨረሻ በእናንተ ላይ ለመወሰን፥ ከክርስቶስ ዉጭ የደሙን ዋጋ አወራርዶ፥ እንዲህና እንዲያ የሚል ከቶ አይኖርም። እንኪያስ እኛ ሁላችን ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ታዋቂዎች ነን ማለት ነዉ!! ወዳጆቼ ከመከራችሁ ቁልላት በላይና በበለጠ፥ የመታመናችሁ ቅንጣት ሰናፍጭ በፊቱ እጅግ በጣም ትልቅ ናት!፥ ምክንያቱም መከራዉ ይመክርባችኋል እንጂ፥ መጨረሻችሁን የመወሰን መብት አልተሰጠዉም፥ ታዲያ ቅንጣቷ እምነታችሁ የምድርን መንግስታት ድል ትነሳ ዘንድ!፥ ፍፃሜያችሁ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ለመከረባችሁ መከራ ንገሩት!!!

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                           @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
                   
#ተባረኩ
10👎2
“ ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።”
— ማርቆስ 5፥30

ወደ እግዚአብሔር መንግስት የተጠራችሁና የርስቱ ተካፋዬች የሆናችሁ ቅዱሳን!
አንዳንዴ እንዲህም አለ፥ ከብዙ ድካምና ቆይታ በኋላ፥ ተስፋ በሌለዉ ረጅም ሰልፍ ወደተከበበዉ መፍትሄ ለመድረስ እየጓጓን ያለን ሰዉዎች፥ እባካችሁ ክብሩን ዳሱ፥ የመከራዉ ጎርፍ ከበታቹ የሚያለፈዉ በዳሰሳችሁት ክብር ነዉ፥ ዉርንጭላዋ እስኪ ምን ነበራት?፥ ያዉም እኮ እስረኛ፥ ነገር ግን በለበሰችዉ ክብር ከበረች፥ ስትዳስሱት ትዳሰሳላችሁ ማለት።
እግዚአብሔር ዛሬም ይሄንን ጥያቄ የሚጠይቀን አይመስላችሁም?፥ "ማን ነዉ የተቀባዉን መሲህ ከብዙ መድሃኒቶች መካከል ወስዶ የቀረ?"
ከዚህ ቀጥሎ የምታቀርቡት ጥያቄ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተቀደሰ ነዉ!

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
2
ነፍሴ ሆይ ከሁካታዉና ከጫጫታዉ፥ ከምኞቱም መለስ በይና፥ እስኪ በእግዚአብሔር ቃል ልምከርሽ፥ እንዲያዉ የተለየ ነገር የሸተተሽ ጊዜዉ አዲስ ዓመት ስለሆነ ነዉን?
ደግሞስ አሁን ለዉጥ ትዝ ያለሽ በእርግጥ ከስጋ በላይ ሆነሽ ዓመቱን ጨርሰሽ ነዉን?
እንኪያስ በክርስቶስ ኢየሱስ የሞላብሽን በረከት መሰብሰብ የምትችይዉ አሁን እንደሆነ ያሰብሽዉ ዘመንን አይተሽ ነዉን?
ነፍሴ ሆይ በእርያዎች ፊት የምትጥይዉ እንቁ ማለት ዘመንን ያለ አዘማኙ በምኞት የወጠርሽዉ ቀን ነዉና፥ ከምትፈልጊዉ ሁሉ በላይ ቀኖቹን ያንቺ እንዲሆኑ በመጀመሪያ ፈልጊ፥ አሮጌዉ ከአዲሱ ዓመት የሚለየዉ እነሆ ከተዋጀ ብቻ ነዉ
ይቺን መልዕክት እርሶም ለነፍሶት ይጋብዟት!
እንኳን አደረሳችሁ!!!

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
👍41
ተግሣጹ ወደ አስተዉሎት የሚመራ ታላቅ ፍቅር ቢሆንም፥ በቁጣዉ ዉስጥም ወደር አልባ ቅድስናዉን በቅነት ዉስጥ እመለከታለሁ፥ ለእኔ ግን በእግዚአብሔር አባትነት ዉስጥ ማስፈራቱ ህልዉናዬ እንደሆነ አጥብቄ እረዳለሁ።

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረll
3
“በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።”
— ኢሳይያስ 27፥6

ይህ ተስፋ፥ ያዕቆብን ለፊተኛዉ ዘመን ያጨ፥ እስራኤልን ደግሞ ለፈጠነ እዉነት ያቀረበ፥ የተናጋሪዉን ልክ የለሽ ሹመት፥ ወደ ምድር የሳበ ማስታወሻ ነዉ።
መጪዉ ዘመን እንዴት ያለ ይሆን ለሚል ያዕቆብ፥ በግምቱ ፍርስራሽ ስር፥ እግዚአብሔር ርህራሄዉን እንዴት ባለ እጁ ቸረዉ!፥ እንደ ያዕቆብ እዉቀት ከሆነ ምቾት፥ እንደ እግዚአብሔር ያለን የሙላት ሕይወት ወደሚያጭድበት መገፋት ቢንደረደርም እንኳን፥ እስራኤል በያዕቆብ ዉስጥ ያለ የተመረጠ ማንነት ሆነ
ወዳጆቼ የመረዳት ባለጠግነትን የሚጠይቅ የእዉቀት ወሰንጋ ከደረሳችሁ፥ ከክርስቶስ ፊት መገኘታችሁን ለፍጥረት ገለጣችሁ ማለት ነዉ!

ከታጋይ ያዕቆብ እስከ አሸናፊዉ እስራኤል ድረስ፥ አንዱ በአንደኛዉ ዉስጥ ያለፈ የማንነት መሞረጃ ሆኖ ትርጉም የሚሰጥ ሆነ፤ ደስታ እንደ ያዕቆብ ብኩርናን ከይሳቅ ማግኘት ሲሆን፥ ደስታ እንደ እስራኤል ግን ብኩርናን ከእግዚአብሔር መዉሰድ ማለት ሆነ።

የምታልፉበት ሕይወት የመሞረጃዎቻችሁን ቀናት የፈጠሩ በሚመስላችሁና፥ አንዱ ቀን ከሌላዉ የማይሻል ሆኖ እንኳን፥ እናንተ ግን በሚወድቅ የዘር ምሳሌ፥ ራስን ወደ መካድ የመረዳት አቀበት ትወጣላችሁ፥ ምክንያቱም
የወደቀ ዘር ይሆናል!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
2
“ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።”
  — ዘጸአት 2፥15

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ጉዳይ እንዳለዉ በሚያሳዉቅ ሁኔታ መርቶ የት እንደከለላችሁ ከግምታችሁ ዉጭ ሲሆን፥ በተለይ ሰዎችና ድርጊቶች ግን ዛሬን ያለማቋረጥ እንድታዩ እንደ ጺጢፋራ አለቅም ይሏችኋል፥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደቆመ የምታዉቁት ፈርዖን ስለራራላችሁ ከመሰላችሁ፥ ተንኮል በልቡ ያኖረ ጊዜ ለጠላት እድል ፋንታ እንዳመቻቻችሁለት ቀድማችሁ አስተዉሉ። እዛጋ የጠላት አፍ ሲከፈት ስለእናንተ መገኘት በሌለበት ቦታ እንኳን ቢሆን ምንጩን ከመነደል ሚድያም አያግደዉም፥ መንግስትና ግዛት፥ ፍትህና ርስት፥ ዓላማና ኑሮ ያልሰጠዉን እረፍት ሙሴ ጉድጓዱጋ አገኘዉ፥ ዛሬ ወዴት እየተሸሸጋችሁ ነዉ?

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

                 #ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

@wisdom3in1
                    @wisdom3in1
                   
#ተባረኩ
6
“እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤”
— ዘፍጥረት 26፥28-29
ሁሌ "ምን ትኩረትህን ይስበዋል?" ካላችሁኝ ከቶ በዉን ሊገጣጠሙ የማይችሉ ነገሮች "እሺ!" ብለዉ ሲታዘዙ ይገርመኛ፥ ከነዚያም መካከል ይህ አንዱ ነዉ፥ “ይስሐቅም፦ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው።”
— ዘፍጥረት 26፥27
መገፋትና መፈለግ፥ መነጠልና መወደድ፥ መሰደድና መሰብሰብ፥ ተቃርነዉ እንጂ ተጣምረዉ የሚያዉቁት እዚህ ምዕራፍ ላይ ብቻ ነዉ።
ይስሐቅ ከጀርባዉ ምን እንዳለ ግን አላወቀም፥ እንዲሁ ከመጠላት ኋላ ምን አለ?፥ እንዲሁ ከመዘለፍ ኋላ፥ መጨረሻዉስ ምን ሊሆን ይችላል?፥ ብሎ ለሚሞግት ሰዉ፥ ይህ መልስ ነዉ፥ እግዚአብሔር ለሚጠሏችሁ እያሳየ ያለዉ በተጨባጭ ማንነቱን ነዉ። በእርግጥ እንደክማለን እንፈተንማለን፥ ነገር ግን ዉጤቱ በእግዚአብሔር ፊት ለእኛ የተለወጠ ነዉ። ስለዚህ በእኛ ድክመት እንኳን ጌታ ይሰበካል!

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ-ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ
@wisdom3in1
                  @wisdom3in1
             
#ተባረኩ
3
ሰዉ መሆን ለክርስቶስ ዝቅታ ነዉ፥ ከዝቅታም በታች እኔና እናንተጋ መምጣቱ ደግሞ ያዉም ክብሩን መጣሉ ነዉ፤ እናም የሆነልን ከገባን በላይ ነዉ፤ ወዳጆቼ እነዚህ ቃላት የትህትና መግለጫ ብቻ ሳይሆኑ የምስክርነት መንደርደሪያዎች ቢሆኑ ብለን እንዲህ እንድናስበዉ ወደድን፥ እናም ከኔ ዳግም መወለድ ይልቅ የክርስቶስ እኔን መስሎ መወለድ እጅግ ሲበዛ ያስደነግጣል!። ጌታዬ እኔን ብሎ መቷልና መልኬን ወስዶ መልኩን ሰጠኝ።

እንግዲያዉስ የእምነታችን ራስ የሆነዉ እርሱ ሁሉን የምንገዛበት አቅማችን ነዉ፥ የክርስቶስ መወለድ የእኛን አለመኖር የምናበስርበት መኖሪያችን ሆነ!
ከእርሱ ተካፍለናል።

እንኳን አደረሳችሁ!

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
7
በእኛ ዉስጥ የተሳለዉን፥ በዚች ምድር ላይ እንስል ዘንድ አብዝተን ብንተጋ፥ የብላቴንነት ወራታችንን በማወቅ እየሻርን፥ ኋላም ለእግዚአብሔር የተሰጠ አይምሮ እናቀርብለታለን እንጂ፥ ጥላ ወደሚሆን መረዳት አንዞርም፤ ምክንያቱም አካል አለና።

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።”
— ማቴዎስ 6፥7

በእርግጥ "ጌታዬን እንዴት ላዉራዉ?" ብላችሁ አስባችሁ የምታዉቁ ከሆነ፥ እንኪያስ በመጀመሪያ እርሱ የሚላችሁን ብቻ በትህትና ስሙና አድርጉት፥ ይህ ፊተኛይቱ የፍቅር መታዘዝ ናት፥ ምክንያቱ ደግሞ እግዚአብሔርን ካወቃችሁት በላይ ለማወቅ፥ የእናንተ ቃል ሳይሆን፥ ቃል ሆኖ የመጣዉን ለመስማት፥ ከወጣችሁበት ምኩራብ፥ ወደ ሰገነታችሁ ዉጡ፥ ምኩራብ የጠቢባን መኖሪያ ቢሆንም፥ ሰገነት ግን የጥበብ መገኛ ነዉ፤ ጥበብ ደግሞ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ።

ከእግዚአብሔር የተማሩት እነሱ፥ እግዚአብሔርን በእግዚአብሔርነቱ በግላቸዉ ያወቁት ናቸዉ፥ ይህ ማለት እዉቀታቸዉ ነፍሳቸዉን ዘልቆ ይቆጣጠራታል፤ እናም ሰዉ የተፈወሰና የማያቋርጥ ግንኙነት ይኖረዋል ማለት ነዉ።

እንግዲያዉስ ለተጠየቃችሁት መጠራት፥ በምትሰጡት መሰጠት መካከልና፥ የሕፃንነትን ወራት በሚያስታዉስ የአፍ መደጋገም መሃል እንድትቆዩ ከቶ አልተፈቀደም፥ ይልቅስ እግዚአብሔር ከተሰጠ አፍ በላይ፥ የተሰጠ ልብ እንደሚፈልግ፥ እናንተንም አይጠፋችሁም፤ በዚህ ሁሉ ግን እርሱ የቅርብ አምላክ ነዉ፥ እንደ ቅርበቱ እናንተስ ምን እያወጋችሁት ይሆን

#እንወዳችኋለን
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
1
የተፈጠራችሁለት፥ ከተቀጣጠራችሁት ጉዳይ ጋር፥ ምንም እንኳን ባይናበብ፥ የተሸከማችሁት መስቀል፥ የራቃችሁን ፅድቅ ወራሽ ከማድረግም በላይ ክርስቶስን ካየንበት፥ እንኪያስ የዛሬዉ ስማችሁ የሚቀደድ የመርገም ጨርቅ ዋጋ ያለዉ ነዉ፤ ይሄ ማለት አብረሃም ዘንድ ሎሌ ሆኖ ቢቆይም፥ የሄደበት መንገድና የተላከበት ዓላማ፥ ከኖረለት እዉነት በብዙ በለጠና፥ ያለስምም እንኳን ቢሆን በብዙ ምርቃት ወደ እረፍቱ ገባ።

እግዚአብሔር መስሎት ስለማይሰራ፥ የሚመሳሰል ነገር እንደሚሰራ አናስብም፥ ቢሆንም ግን፥ ከዉጭ ወደ ዉስጥ፥ ከዉድቀት ወደ መነሳት፥ እንዲሁም ካለመታዘዝ ወደ ፀጋዉ፥ በማይጠቅም የፅድቅ ጎናችን፥ የመዳንን ጥሩር አለበሰን፥ ደግሞም በቤቱ ያለን ልጆች ሆንን!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
👍1
ወዳጆቼ መዳረሻችን የተዋጀንበት ስፍራ ሳይሆን፥ የዋጀን ጌታ ዘንድ ነዉ፥ እንኪያስ ትኩረታችሁ ወደ መረጣችሁ ቢሆን፥ የተሰጣችሁን አደራ ከሰጣችሁ ጋር የማገናኘት ሕይወት፥ ዕለት ዕለት እየበዛላችሁ፥ ራስንም በማሸነፍ የሚዘጋ ክርስቶሳዊ ምዕራፍ ሆኖ እንደሚቆጠር አትርሱ።

ዛሬስ? ዛሬማ "ጌታ ኢየሱስን ለመከተል ጫንቃችሁ ላይ ምን ተሸክማችኋል?" ብሎ ለሚጠይቃችሁ፥ መልሳችሁ ምን ይሆን?፥ ክርስቶስን ለመዉደድና ለመከተል አቅም የምታገኙት፥ ልባችሁ በሞላዉ ልክ እንደሆነ አታዉቁምን?፥ መስቀል የዳናችሁበትን እዉነት የምትኖሩበት፥ እግዚአብሔር ደግሞ ከእናንተ የሚጠብቀዉ ኑሮ ነዉ!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

#ሰማያዊ_ጥበብ                   
                  
#ተባረኩ
2👍2
“ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤”
— ዕብራውያን 1፥2

ሁሉን ወራሽ ባደረገዉ?
መንገዱን ስቶ አቅጣጫዉን ያወቀ የመሰለዉ፥ ያለመንገዱ እንደማይደረስ ያላወቀ ሞኝ ብቻ ነዉ፥ በዚህም መሰረት የጎደለ እዉቀት ማለት የክርስቶስ ጠላትነት መገለጫ እዉነት ነዉ፤ ስለዚህ ሐዋርያዉ ጳዉሎስ "ዓለማት የተፈጠሩት በልጁ ነዉ" አለን፥ እናም መፍጠር የሕይወት ልኬት ሆኖ ተቀመጠ፤ ሕይወት ዉስጥ ደግሞ ዉርስ ተሰወረ።
ምን ማለት ነዉ?
ዓለማት በክርስቶስ ካለመኖር ወደ መኖር ሲመጡ፥ የጎደለም ሆነ የጎደለዉ አልነበረም፤ እነሆ ክርስቶስ የሁሉ ሙላት ሆኖ በሰማያት ታይቶ ነበር፤ ነገርግን እንዲህም እንኳን ቢሆን ዉርስ መኖር ነበረበትና፥ ሳይጎድለዉ፥ ፀጋን ከሕግ በላይ ያደረገ ዉርስ ሊወርስ፥ ወደ ሞላት ዓለም፥ ግን ደግሞ፥ እርሱ ወደ ጎደላቸዉና፥ ወደጠፉት አሕዛብ ዘንድ ወረደ፤ የተሰጠዉን ያልተቀበለ፥ የሰጠዉን አያዉቅምና፥ ክርስቶስን ለማወቅ
ሁሉን ይወርስ ዘንድ፥ አንዱ ስለ ሁሉ ነፍሱን ሰጠ፥ ቅድሚያ እርሱ ኖሮን የጎደለን ዓለማት ነበሩ፥ ኋላ ግን እርሱ ርቆን የሞላን ዓለማት ሆነዉ ተገኙ የወረሰን ሌላ ነበር፥ ያንን ዉርስ የሰረዘ ድምፅ ከዘመን በዉሃላ ለእኛ ደረሰን፥ እነሆ እኛም ሰማን!!!
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

#Share እንዲሁም #Subscribe ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ
                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
3👍1
“ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።”
  — ዕብራውያን 1፥6

መርህ ይለወጣል? ወይስ?
መርህ በየሁናቴዉና በየሰበቡ የሚቀየር ከሆነ ለጥላዉ አካል አያስፈልገዉም እንደማለት ነዉ፥ መርህ የማይለወጠዉ ያጸደቀዉ ዋና አካል ይሁንታ ሲያገኝ ነዉ፥ ደግሞ መርህ የሚሻረዉ ያዉ አካል ሲገድበዉ ነዉ፥ እንኪያስ አንዳች አትጠራጠሩ እግዚአብሔር ቃሉ ከሚያልፍ፥ ሰማይን ማሳለፍ ቀላል እንደሆነ በሚገባን ቃል፥ ትልቅ እዉነት ተናገረን፤ ስለዚህ ሁለተኛዉን ኪዳን የጀመርነዉ በፊተኛዉ በኩር በኩል ነዉ፥ ፉክክር ዉስጥ ብልጫ ሲኖር ብልጫ ዉስጥ ግን ፉክክር አይኖርም፥ ስለዚህ ብኩርና "የተገባዉና" የብልጫ ጉዳይ ነዉ፥ የበለጠዉ ሁሉን ጠቅሎ የያዘዉና የሚገባዉ ሲገለጥ፥ ሁሉም ይዘዉት የመሰላቸዉን ብኩርና አስቀመጡ፤
እዚህጋ መርህ ተገለጠ ስግደት ለበኩሩ ብቻ የሚል ተፃፈ። እንኪያስ ስላፀደቀዉ መርህ እንደንደራደርበት ዘንድ እኛ ማን ነን?
#ሰማያዊ_ጥበብ

                 #ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

#Share እንዲሁም #Subscribe ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ
   
#ተባረኩ!
7