Forwarded from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
#በሙከራ_የተረጋገጡ_ቴክኖሎጂዎችን_ወደ_ቴክኒክ_ሙያና_ትምህርትና_ስልጠና_ማሸጋገር_የሚያስችል_ስምምነት_ተፈረመ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሙከራ የደገፈውን የተቀናጀ የዐሳ እርባታ እና የሽቅብ ግብርና ቴክኖሎጂ ፕሮጀክትን በቴክኒክ ሙያና ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች፣ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች በኩል ወደ ሕብረተሰብ ለማድረስ የሚያስችል ስምምነት ከጀኔራል ዊንጌት ፓሊቴክኒክ ኮሎጅ ጋር ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ያኒያ ሰኢድመክይ (ዶ.ር) እና የጀነራል ዊንጌት ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ፈርመውታል።
እንደ ዶክተር ያኒያ የስምምነቱ ዓላማ በሙከራ የተረጋገጡ መሰል ቴክኖሎጂዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ የስራ ዕድል እና ሀብት በመፍጠር፣ የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻል ወደሚያስችል ደረጃ ማሸጋገር ነው።
የሙከራ ፕሮጀክቱ በውስን ቦታ መተግበር የሚችል፣ ቴክኖሎጂው በአካባቢ አቅምና ግብዓት የሚሰራና ለዐቅም ማጎልበቻ የሚያገለግል በመሆኑ ለሽግግሩ የቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ተቋማት በተለይም የአኳ ካልቸር እና ግብርና ዲፓርትመንት ካላቸው ተቋማት የሚጣጣም በመሆኑ ጀኔራል ዊንጌት ተመራጭ ሆኖ ተገኝቷል።
ዶክተር ያኒያ አክለውም ኮሌጁ ፕሮጀክቱን በማስቀጠል፣ ለሠልጣኞች አቅም በማዋልና የገቢ ማመንጨት አቅሙን በተግባር እያሳየ ለተጠቃሚዎች እንዲያስተላልፍ እና እንዲያባዛው ሲሉ በአጽንኦት አሳስበዋል።
የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ በቀለ በበኩላቸው የአኳ ፓኒክ ዲፓርትመንት እና መሰል የግብርና ቴክኖሎጂን የሚመለከቱ እና ግብርናን የሚደግፉ ዲፓርትመንቶች በተቋሙ ቢኖሩም ለተግባር ስልጠና ከአዲስአበባ ውጭ ለመሄድ እንገደድ ነበር ብለዋል።
ይህን መሰል ቴክኖሎጂ የተሞከረበት ፕሮጀክት በቅርብ ማግኘታችን የስልጠና ፕሮግራሞቻችንን ከማገዙ በላይ ሠልጣኞች በተግባር የተፈተሸ ልምድ ይዘው ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ብሎም የስራ እድልና የገቢ አማራጮችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል በመሆኑ ለተፈጠረው እድል ማመስገናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡//@FTA

Forwarded from admasu Ye Abiye Lij
General Wingate Polytechnic College signs technology transfer agreement with Ministry of Innovation and Technology .
The Ministry of Innovation and Technology has signed an agreement with General Wingate Polytechnic College to bring the pilot project to the public through technical and vocational education and training colleges, trainers and trainees. The agreement was signed by State Minister for Innovation and Technology, Yania Seidmeki (Dr.) and Admasu Bekele, Deputy Dean of General Wingate Polytechnic College.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በ2013 ትምህርትና ስልጠና ዘመን የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት የእውቅናና ሽልማት እንዲሁም የ11ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት ማጠቃለያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ በ11ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት በቴክኖሎጂና በክህሎት ውድድር አሸናፊ ለሆኑ፤በ2013 በኤጀንሲ እና በኮሌጅ ደረጃ የላቀ አፈፃፀም ላመጡ የስልጠና አመራሮች፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች፤ከ25 አመት በላይ በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላገለገሉ 78 አሰልጣኞች፣ የስልጠና አመራሮች፣ እና ሌሎች ሰራተኞች እንዲሁም 11ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትና ተሳትፎ ላደረጉ ኮሌጆችና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

Forwarded from Boo
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች አብሮ ለመስራት እና አገልግሎቱን ለማዘመን ከ4 ግዙፍ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
ግንቦት 21/ 2013 አዲስ አበባ። ከተመሰረተ 78 ዓመታትን ያስቆጠረው አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከሚሠጠው መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ ድርጅቱንና ማኅበረሰቡን የሚያገለግሉ የፈጠራ ሥራችን በተቋሙ የቴክኒክ ሠራተኞች እየሠራ ይገኛል፡፡ድርጅቱ እነዚህን የፈጠራ ሥራዎቸው ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግና በሰፊው አምርቶ ወደ ገበያ ለተጠቃሚው ለማድረስ ከተለያዩ ግብዓቶች የሚደገፍ ተቋማት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲዩት ፣ የኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት፣ጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሰላም ኮሌጅ ምሳሌ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በወቅቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ ነጋሽ ባጫ በጉብኝቱ ወቅት ያዩት ነገር ሚዛን የሚደፋና መደገፍ ያለበት እንደሆነ ገልጸው ከተማ መስተዳደሩ በቀጣይ ትኩረትና ድጋፍ ሰጥቶ በድርጅቱ ላይ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፕሪሚየር ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ህብረት ፕሬዝዳንት አቶ ሰብል አለሙ ከረጅም ዓመታት ከውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙበት ኤግዜብሽን ላይ ከተቋሙ ጋር አብሮ ለመስራትና የተለያዩ የቴክኖሎጅ ሥራዎችን እንዲሁም የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፎችን ለተቋሙ እንደሚያቀርቡ ቃል ገብተዋል፡፡
#Anbessabus
#አንበሳአውቶብስ

Forwarded from Dame Mersha
General Winget polytechnic collage got trophy from Kolfe subcity for its best performance of industry extension service and provision of short-term trainings for more than 8950 trainees and 1502 enterprise
Forwarded from Anbessa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ድርጅታን አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋት ከ 4 ግዙፍ ተቋማት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት የሚያስችል የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ዘገባውን ናሁ ቴሌቪዥን በዝርዝር ሰርቶታል፡፡
በኮሌጆች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአሰልጣኞች የእግር ኳስ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሸናፊነት ተጠናቀቀ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ የምስረታ በዓልን ምክኒያት በማድረግ በኮሌጆች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአሰልጣኞች የእግር ኳስ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ በምድብ የተደለደሉ 10 ኮሌጆች ሲሆኑ በጨዋታው ላይ የተሳተፉት ግን 8 ኮሌጆች መሆናቸው ታውቋል። በውድድሩም ምድብ አንድ ላይ የነበሩት አዘጋጁ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሳትፉ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ደግሞ ከተሳትፎ ውጪ ሆኗል።
በሌላ በኩል ምድብ ሁለት ላይ ከተደለደሉት ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ አዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ፣ ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ውድድሩን ሲቀላቀሉ የካ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ግን ራሱን ከጨዋታ አግሏል።
በጨዋታው መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት 8ቱ ኮሌጆች ለዋንጫና ለደረጃ 16 ጨዋታዎችን ያደረጉ ሲሆን ለዋንጫ ለማለፍ በተደረገው ውድድር አራቱ ቡድኖች ውስጥ የገቡት ኮሌጆች ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ አዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ፣ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ናቸው።
ለዋንጫ ለማለፍ በተደረገው ውድድር ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ደግሞ አዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን በማሸነፍ ለዋንጫ ውድድር የቀረቡ ሲሆን ግንቦት 24 ቀን 2013 ዓ/ም በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን 3ለ2 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ሲሆን በነበራቸው 90 ደቂቃና በተጨማሪ የባከኑ ደቂቃዎች ጎል ሳይቆጠር 0ለ0 በመውጣታቸው መጨረሻ ላይ በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማሸነፍ ችሏል።
በተያያዘ ዜና የኮሌጁን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ የምስረታ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ሰልጣኞች በየዲፓርትመንቶቻቸው የሚያደርጉት የእግር ኳስ የውስጥ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ዲፓርትመንታቸውን ወክለው የሚደረጉ የመረብ ኳስ ጨዋታ ውድድሮችም በአጓጊነት የሚጠበቁ ናቸው።