Forwarded from Amhara Education Bureau
#የትምህርት #ተቋማት #የህዝብ #ግንኙነት #የማህበራዊ_ሚዲያ
#የትምህርት ተቋማት የህዝብ ግንኙነት (Public Relations) ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያ ማለት ምንድነው?
#በትም/ት ተቋማት #የማህበራዊ_ሚዲያ ማለት የትምህርት ተቋማት ከህዝብ፣ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች እና ከሌሎች ተያያዥ አካላት ጋር ለመገናኘት የሚጠቀሟቸዉ ዲጂታል መድረኮች ማለት ናቸው።
ለምሳሌ፦ Facebook፣ Telegram፣ YouTube፣ Twitter ወዘተ።
#ዋና_ጥቅሞቹ
#1. ፈጣን መረጃ ስርጭት
#ተቋማት ዜና፣ ማስታወቂያ፣ የፈተና ቀን እና ሌሎች መረጃዎችን በፍጥነት ለህዝብ ማድረስ ይችላሉ።
#ቀጥታ ግንኙነት (Interaction)
2ተማሪዎችና ወላጆች ከተቋሙ ጋር በቀጥታ ጥያቄ ማቅረብ እና መልስ መቀበል ይችላሉ።
3.ስም እና ምርጥ ገጽታ (Image Building)
#ተቋማት ስኬቶቻቸውን፣ ፕሮግራሞቻቸውን እና እንቅስቃሴዎቻቸውን በማሳየት ጥሩ ስምና ገጽታ ይገነባሉ።
4. ዝቅተኛ ወጪ (Cost-effective)
#ከመደበኛ ሚዲያ (ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ወዘተ) ጋር ሲነጻጸር ነጻጸር በጣም ዝቅተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው።
5. ተማሪዎችን ማሳተፍ (Engagement)
#ውይይቶች፣ ግጥሞች፣ ፎቶ እና ቪዲዮ በመጋራት ተማሪዎች በተቋሙ ጉዳይ በቀጥታ መሳተፍ ይችላሉ።
6. አስተያየት መሰብሰብ (Feedback)
#ተቋማት ከህዝብ እና ከተማሪዎች አስተያየት በቀላሉ ሊሰበስቡና በግብዓትነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
#በአጠቃላይ
👉የማህበራዊ ሚዲያ በትምህርት ተቋማት ውስጥ የህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር፣ መረጃ ለማስፋፋት እና ከህዝብ ጋር ቀላል እና ቀጥተኛ ግንኙነት ለመፍጠር በጣም ጠቃሚ መሣሪያ ነው።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069440360748

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ከምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በዲጂታል አማራጮች ይገናኙ!
ወቅታዊ፣ ታማኝና ፈጣን የትምህርት መረጃዎችን ለማግኘት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ። በዞናችን የሚከናወኑ የትምህርት ልማት ስራዎችን እና ሌሎች ትኩስ ዜናዎችን እናደርሳችኋለን።
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ፦
🔹 በቴሌግራም፦ https://t.me/westedu
🔹 በፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100069440360748

Telegram
West Gojjam Zone Education Department/ምዕራብ ጎጃም ዞን ትም/መምሪያ
Education
ማስታወቂያ ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
መጪ ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች ተለቋል።
ስለሆነም፡-
1.እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የተፈታኝ ተማሪው ትምህርት ቤት ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ ይጠበቅበታል።
2.በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ፣ የጾታ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
3.እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከልም ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ መያስ ይገበዋል።
4.ተፈታኞች በፈተና ወቅት ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ልማት ተግዳሮቶችን በጽናት በመጋፈጥ፦ የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው
የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ10 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ከወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ከሁለተኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራን እና ከሱፐርቫይዘሮች ጋር በፍኖተ ሰላም ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተመላከተው፣ ዞኑ በትምህርት ልማት ረገድ ከተደቀኑበት በርካታ ውስብስብና ፈታኝ ተግዳሮቶች ለመውጣት ባለፉት ወራት ሰፊና ተከታታይነት ያላቸው ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።
በተለይም፦
የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ማሻሻል፦ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈጠሩ አገራዊና አካባቢያዊ ጫናዎችን በመቋቋም፣ የመማር-ማስተማር ሂደቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥልና ተማሪዎች ወደ ገበታቸው እንዲመለሱ የተደረገው ጥረት፣
የመረጃ አያያዝና ቴክኖሎጂ ትግበራ፦ የትምህርት አስተዳደር መረጃ ሥርዓትን (EMIS) ለማዘመንና መረጃዎችን በጥራት ለማደራጀት የተሰሩ ውጤታማ ሥራዎች፣
የተማሪዎች ምዝገባና ፈተና ዝግጅት፦ የወረዳና የትምህርት ቤት አመራሮች ተቀናጅተው በመስራታቸው ለ6ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ክልላዊና አገራዊ ፈተናዎች ተማሪዎችን ብቁ የማድረግና የኦንላይን ምዝገባዎችን የማሳካት ተግባር፣
የሀብት ማሰባሰብና የውስጥ ገቢ ማሳደግ፦ ከተደቀኑበት የበጀትና የግብዓት እጥረት ለመውጣት የውስጥ ገቢን በማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ለመደገፍ የተሄደባቸው ርቀቶች በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።
እነዚህን ተግዳሮቶች ለመሻገር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ቢሆኑም፣ አሁንም በየደረጃው ያሉ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።
ይህ የ10 ወራት ግምገማ ያጋጠሙ ማነቆዎችን በዝርዝር በመለየት፣ በቀሪው ጊዜ ውስጥ መፍትሔ በማስቀመጥ የዞኑን የትምህርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ እንዳለው ታምኖበታል። መድረኩ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባቢያ በመያዝ ሥራውን ይቀጥላል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ

የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ኮምፒዩተሮችን ተረከበ
የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያግዙ፣ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ 100 ዘመናዊ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት (አብክመ) ትምህርት ቢሮ ተረክቧል::
የመምሪያው ኃላፊ አቶ የስጋት ደሴ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የአብክመ ትምህርት ቢሮ የዞኑን ነባራዊ ችግሮች እና ፍላጎቶች በመረዳት ቀደም ሲልም ጭምር የተለያዩ ተከታታይ ድጋፎችን ሲያበረክት መቆየቱን አስታውሰዋል።
📌 "ይህንን የኮምፒዩተር ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ማግኘታችን፣ በተለይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሀገር አቀፍ ፈተና በብቃትና በስኬት ለማስፈተን ለምናደርገው ዝግጅት እጅግ ጉልህ ሚና አለው"
ኃላፊው አክለውም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለዞኑ ትምህርት ጥራት መሻሻልና ለቴክኖሎጂ ተደራሽነት ለሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ በዞኑ ትምህርት ማህበረሰብ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ የተደረገው የኮምፒዩተር ድጋፍ በዞኑ የሚገኘውን የዲጂታል ትምህርት መሠረተ ልማት ከማጠናከሩም በላይ፣ ተማሪዎች ለፈተና የሚኖራቸውን ዝግጁነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
አቶ የስጋት ደሴ (የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ)