WERABE COMPREHENSIVE SECONDARY SCHOOL
604 subscribers
648 photos
18 videos
68 files
36 links
"Education is the most powerful weapon which you can use to change the world."Nelson Mandela

DM: @seifusultan
Download Telegram
የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት በከተማዋ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲካሄዱ የቆዩ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እንዲሁም ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን የተመለከተ የግምገማ መድረክ አካሄደ።
​በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች ፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ተገኝተዋል።
​በግምገማ መድረኩ ከተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-
​የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች፡ በክረምቱ ወራት የተካሄዱ የትምህርት ቤት እድሳቶች፣ የጠረጴዛ እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ጥገና፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እና ለተማሪዎች የተሰጡ የማጠናከሪያ (Tutorial) ትምህርቶች ውጤታማነት ተገምግሟል።
​የትምህርት ቤት ጥራት እና መሰረተ ልማት፡ የመማሪያ ክፍሎች፣ የላቦራቶሪ እና የቤተ-መጻህፍት ዝግጅት እንዲሁም የተማሪዎች የመማሪያ መጻህፍት ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሟል።
​የመምህራን እና ሰራተኞች ዝግጅት፡ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን መምህራንን በስነ-ልቦና እና በክህሎት ለማዘጋጀት የተሰጡ ስልጠናዎች እና የመደብ ክፍፍሎች መጠናቀቃቸው ተገልጿል።
​የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሙያው አቶ አ/ሃዲ ናስር በግምገማው ወቅት እንደገለፁት፣ በክረምቱ ወቅት የተከናወኑት ስራዎች አዲሱን የትምህርት ዘመን በሙሉ ዝግጅት ለመጀመር የሚያስችሉ ናቸው። አክለውም ትምህርት ቤት በወቅቱ ተከፍቶ የመማር ማስተማር ስራው ያለ ምንም መስተጓጎል እንዲጀምር ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
​በመጨረሻም የቀሩ የመሰረተ ልማት እና የማዘጋጀት ስራዎች ትምህርት ከመከፈቱ በፊት ሙሉ በሙሉ እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል።
👍5🥰2❤1
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከላይ የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም
❤3👍2🥰2
ቀን 04/01/2019
ወራቤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 ትምህርት ዘመን በታላቅ ዝግጅት ተጀመረ

​ወራቤ — በዛሬው ዕለት በወራቤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን የመማር ማስተማር ሂደት በይፋ ተጀምሯል።
​በትምህርት ቤቱ አወቃቀር መሠረት የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ትምህርት በወቅቱ የተጀመረ ሲሆን፣ ተማሪዎችም በታላቅ ተስፋና መንፈስ ወደ ክፍሎቻቸው ገብተው ትምህርታቸውን መከታተል ጀምረዋል።
​በዛሬው ዕለት የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በትምህርት ቤቱ በአካል በመገኘት የመጀመሪያውን ቀን የመማር ማስተማር ሂደትና የዝግጅት ደረጃ ምልከታ አድርገዋል። አመራሮቹ በትምህርት ቤቱ የታየውን ዝግጁነትና የተቀላጠፈ ጅምር በማድነቅ፣ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ስኬት አስፈላጊው ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል።
​በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሰይፉ ሱልጣን አዲስ ወደ ትምህርት ቤቱ ለተቀላቀሉት ተማሪዎች አቀባበል በማድረግ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አስተላልፈዋል። ርዕሰ መምህሩ በንግግራቸው፤ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ለከፍተኛ ውጤት እንዲበቁና የትምህርት ቤቱን ደንብና ስርዓት አክብረው እንዲንቀሳቀሱ አሳስበዋል።
​የእለቱን ውሎ በተመለከተ በትምህርት ቤቱ የተገኙ ተማሪዎች የስም ቁጥጥር (ጥሪ) በተደራጀ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን፣ የመማር ማስተማር ሂደቱም ሙሉ በሙሉ በተረጋጋና ስነ-ስርዓት ባለው መልኩ መጀመሩ ታውቋል።
❤3🥰3👍1
ማስታወቂያ
የወራቤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ገቢ የሆናችሁ ተማሪዎች ዩኒፎርም 11 እና 12ኛ ክፍሎች የሚለብሱትን ዩኒፎርም አሰፉ። ከዚህ በፊት ሰመያዊ ያሰፋችሁ ተማሪዎች ራሱንም ልበሱ።
🥰4👍2💔1