Weird News
7 subscribers
2 photos
Download Telegram
Channel created
" ለግድያ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ጥል ሳይኖር የመኖሪያ ቤቱን በር ከውስጥ በመቆለፍ ወላጅ እናቱንና እህቱን በሳንጃ ነው በጭካኔ የገደለው " - ኢንስፔክተር ደሣለኝ ዳመና

ወላጅ እናቱንና እህቱን በዘግናኝ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ።

አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ገርቦ ቀበሌ ነው።

በዚሁ ቀበሌ ወላጅ እናቱንና እህቱን በዘግናኝ ሁኔታ በገደለ ግለሰብ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግና የምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

የምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ፖሊስ የወንጀልና ታክቲክ ጉዳዮች ምርመራ ዘርፍ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ደሣለኝ ዳመና ምን አሉ ?

" ተከሳሹ ወጣት ሰንበቶ መንገሻ ይባላል።

ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ለግድያ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ጥል ሳይኖር የመኖሪያ ቤቱን በር ከውስጥ በመቆለፍ ወላጅ እናቱንና እህቱን በሳንጃ በጭካኔ ገድሏል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት፣ ወንጀል ፈጻሚው ወላጅ እናቱን በሳንጃ አንገታቸውን፣ ሆዳቸውንና ጀርባቸውን በመውጋት፣ እንዲሁም ጡታቸውን በመቁረጥ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል።

ይህን ድርጊት አይታ የጮኸችውን ታናሽ እህቱንም በአንገቷ አካባቢ ደጋግሞ በመውጋት ለሞት ዳርጓክ።

ተከሳሹ ቀደም ሲል የመከላከያ አባል ነበር በሕገ-ወጥ መንገድ ከድቶ (ኮብልሎ) የወጣ ነው። " ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ሾኔ ምድብ ችሎት ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ አቶ ግዛቸው ታደሴ በበኩላቸው፤ ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመበትን አኳኋን ከፖሊስ ጋር በመሆን በምርመራ ማጣራታቸውን ገልጸዋል።

ለፍርድ ቤቱም የአስከሬን ምርመራ ማስረጃ፣ ተከሳሹ ለወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠው የእምነት ክህደት ቃል እና የሰው ምስክሮችን በማቅረብ ክስ ተመስርቷል።

የክስ መዝገቡን የተመለከተው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሾኔ ምድብ ችሎት የድርጊቱን አሰቃቂነትና የተከሳሹን የጭካኔ ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቡ በሞት እንዲቀጣ በሙሉ ድምፅ ወስኖበታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Channel photo updated