ወግ ብቻ
19.3K subscribers
506 photos
11 videos
20 files
49 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

Creator @leul_mekonnen1
Download Telegram
የአይነስውሩ ገጠመኝ
_

ሰላም  ስሜ ግሩም ሲሆን ጀሞ በሚገኝ አንድ የመንግስት መስሪያቤት ውስጥ ከሰበታ እየተመላለስኩ እሰራለሁ. ሰበታ በተለያየ የኢንዱስትሪ ምርቶች በሚታወቁ ፋብሪካዎች እራሷን ያጠረች መለስተኛ የኢንዱስትሪ ከተማ ስትሆን ልክ እንደ ዳርዊኒያን ቲዮሪ እድገቷ ዘገምተኛ ነው. ሰበታ ላይ አይነስውር ሆኖ የቤት ኪራይ ከመፈለግ ሗይት ሀውስ ውስጥ ቁንጫ መፈለግ ይቀላል. አንዳንድ አከራዮችማ ገና የጊቢውን በር አንኳክተህ #የቤት ኪራይ አለ? ስትል አለ ይሉህና በር ከፍተው ገና እንዳዩህ መብረቅ የወረደባቸው ይመስል ያማትቡና ውይ ለናንተ አይሆንም ሽንትቤቱ እንዲህ ነው, ውሻው ምንትስ ነው እያሉ መልስ ሳይጠብቁ በሩን ይከረችሙብሀል. እኔም በሰው በሰው ባገኘሁት የቤት ኪራይ ውስጥ መኖር ከጀመርኩ ሁለት አመት ሞላኝ. ሁሌም ጠዋት አስራአንድ ሰኣት የመነሳት ልምድ ቢኖረኝም ቢሮ የምገባው ግን አርፍጄ ነው. በአንደኛው ማለዳ ተነስቼ በጣም የምወደውን የህንድ ክላሲካል ከፍቼ ለስራ መዘጋጀት ጀመርኩ: ቁርሴን በልቼ ጫማዬን ለማድረግ ማታ ያጠብኩት ካልሲዬን ካሰጣሁበት የጠረጴዛ እግር ላይ ሳነሳ ከውስጤ እስከዛሬ የማይጠፋው አንድ ተከስተ የሚባል ልጅ ያደረገው ነገር ታወሰኝ. ነገሩ እንዲህ ነው: የሆነ ቀን ተከስተ ደወለልኝ: ተከስተ ምላሱን ያዝ ስለሚያረገው ረ ከማለት ዘ ማለት ይቀናዋል. ገና ስልኩን ከማንሳቴ #ስማ ግዙሜ: ብቻዬን ስለሆንኩ እስኪ ቲሸዝትና ሹዛብ አጋዛኝ. ሲለኝ የዛሬን አያርገውና ያኔ ትንሽ ትንሽ አይ ስለነበረ ወድያው እሺታዬን ገለፅኩለትና ተገናኝተን ወደ ገበያ አመራን: የምንፈልገውን ነገር እንዳገኘን ዋጋ ከተስማማን በሗላ #በቃ ተከስተ ክፈልና እንሂድ: ስለው ተከስተ ጎንበስ አለና ጫማውን መነካካት ሲጀምር ነጋዴው ፈጠን ብሎ አ አይዞህ የጫማህ ማሰሪያ አልተፈታም: አለው. ተከስተ ሰውዬውን ችላ ብሎ ይባሱኑ እጁን ወደካልሲው ሰዶ የሆነ ነገር አውጥቶ ዘረጋውና ኢሄ ስንት ነው? ሲለኝ በሀፍረትና በመጠራጠር ዝም አልኩኝ: ይህን ያስተዋለው ነጋዴ እጁን ወደአፍንጫው እያስጠጋ አስር ብርነው .ሲለው ተከስተ በድጋሜ ከተአምረኛ ካልሲው ውስጥ የመቶ ብር ኖት አውጥቶ ይኸው መቶ ብዙን አገኘሁት ሲል ላየው ሰው የደቡብ አፍሪካን ዳይመንድ ያገኘ አትሌት ይመስል ነበር. ነጋዴው እንዳይተወው ብር ሆኖበት በመፀየፍ ሲቀበለው እኔ በበኩሌ የሀገሬን የብድር እዳ ብቻዬን የተሸከምኩት በሚመስል ሁኔታ አንገቴን ደፍቼ በልቤ ሁለተኛ ተከስተ የሚሉት ጓደኛ እያልኩ ተከስተን በወጉ መንገድ ሳልመራው የተመለስኩበት አሳፋሪ ገጠመኝ ነበር. ይህን እያሰላሰልኩ ጫማዬን ተጫማሁና ከቤት ወጥቼ ወደታክሲ ተራ መጣደፍ ጀመርኩ: የሰበታ እግረኛ መንገድ ለአይነስውራን አስቸጋሪ ነው በተለይ ዝናብ ከዘነበ ውሀ ስለሚቋጥር ከሱ ይልቅ የኮሪደሩን ጫፍ በመያዝ አስፓልት ላይ መሄድ ተመራጭ ነው. አንድ ወዳጄ ሲያጫውተኝ ይህ መንገድ እንዲስተካከልልን ለከተማው አስተዳደር ብናመለክትም #ይሄ እኔን አይመለከትም የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣንን አናግሩ ብሎ መልሶናል ብሎኝ ነበር. በዚህ አይነት የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣንን ብናናግር #መንገዱ የተሰራው በጣሊያን ወረራ ጊዜ ስለሆነ እስኪ ለጣሊያን ኢምባሲ አመልክቱ. ማለቱ አይቀርም እያልኩ የአስፓልቱን ጫፍ ይዤ ስጓዝ  አንዱ ሀብታም ካቆመው ሲኖትራክ ጋር በግንባሬ ተላተምኩ: ወድያው የሆነ መስታወት እጄ ላይ ሲወድቅ ታወቀኝና እንዴ የመኪናው መስታወት ተሰበረ ብዬ ሳስብ #አይዞህ ዋናው አንተ መትረፍህ ነው መነፅሩ ይገዛል. ብለው አንድ እናት ሲያፅናኑኝ የተሰበረው የኔ መነፅር እንጂ የመኪናው መስታወት አለመሆኑ ገባኝ. ማዘርም ቆይ ልጄ አብረን እንሻገር ሲሉኝ ከመቅፅበት ድምጿ የግንባሬን ህመም ያስረሳኝ ሽቶዋ ከሩቅ የሚጣራ ወጣት መጣችና ቆይ እኔ ላሻግረው ብላ በለስላሳ እጇ ይዛኝ እያሻገረቺኝ ወንድሜ ይቅር በለኝ ገና ከመኪናውጋር ሳትጋጭ እያየሁክ ነበረ ጥፋቱ የኔ ነው ብላ ማልቀስ ስትጀምር በድርጊቷ ብናደድም ድምጿ በፈጠረልኝ ቆንጆ ምስል ውብ አይኖቿ ሲደፈርሱ በውስጤ እየታየኝ አለቃቀሷ ሆዴን አላወሰው: እቅፍ አርገህ አባብላትና ስታለቅሺ ደሳልሺኝ የሚለውን የአብነት አጎናፍርን ዘፈን ዝፈንላት የሚል ስሜት እየወረረኝ አታስቢ ደናነኝ አልኳት: ከተሻገርን በሗላም እንባዋን እየጠረገች በናትክ ይቅር በለኝ ስትለኝ #አይዞሽ ተርፊያለሁ ለወደፊቱ ግን እንደዚህ አይነት ነገር ሲገጥምሽ ዝም ከማለት ይልቅ በቻልሽው መጠን ሰውን መርዳት ይልመድብሽ ስላት ሳግ ባፈነው ድምጿ እኔኮ ሳያችሁ ስለምታስፈሩኝ ነው ደሞም ሁለተኛ አይለምደኝም ስትል ሳቄን እየተቆጣጠርኩ እኛ አናስፈራም አንቺም እንደዚህ ያሰብሽው ባለማወቅ ይመስለኛል: እኛን ቀርበሽ በማየት ለኛ ያለሽን አመለካከት መቀየር ይኖርብሻል. ስላት ልክነክ ጓደኛዬ እናንተን እንዳልፈራና ለናንተ የልቦለድ መጽሃፍት በድምፅ አንብባላችሁ እንደምታውቅ ነግራኝ ነበረ: እኔም ካሁን በሗላ መጥፎ አመለካከቴን ለማስተካከል እጥራለሁ: እባክህን: ይቅር ካልከኝ ጓደኛሞች እንሁን? እያለችኝ ታክሲ ተራ ስለደረስን ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን. እኔም ዛሬ ላጋጠመኝ ነገር ጥፋተኛው ማንይሆን እያልኩና የወጣቷን ግልፅ መሆን እያደነኩ ወደስራ ገባሁ.

By ጫላ መኮንን

@wegoch
@wegoch
@paappii