ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ፣ ጥር 27/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ የትግራይ ሕዝብ በጦርነት ስጋት ውስጥ መኖር ሊበቃው ይገባል ሲሉ ትናንት በጽሁፍ በትግሬኛ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል። ዐቢይ በዚሁ መልዕክታቸው፣ የትግራይ ልሂቃን ልዩነቶቻቸውን በመግባባትና የትግራይን ሕዝብ አንድነት በሚያስጠብቅ መንገድ እንዲፈቱት ጥሪ አድርገዋል። ትግራይ ከፌደራል መንግሥቱና ከሌሎች ኃይሎች ጋር ያላት ልዩነትም፣ በሕገመንግሥታዊና ዲሞክራሲያዊ አግባብ እንዲፈታ ዐቢይ አሳስበዋል። ዐቢይ፣ ትግራይ ለበርካታ አስርት ዓመታት የገባችባቸው ጦርነቶች ለሕዝቡ ምን ጥቅም አስገኙ? ብሎ መጠየቅ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
2፤ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በአገር ውስጥ ገንዘብ መገበያየት እንድትችል ፍቃድ ማግኘቷን ቢዝነስ ኢንሳይደር ድረገጽ ዘግቧል። ሩሲያ፣ ከአፍሪካ አሕጉር ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ናይጄሪያና ቱኒዚያ ጭምር በገንዘባቸው እንዲገበያዩ ፈቅዳለች። አገራቱ ይህን ዕድል ማግኘታቸው፣ ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት ግብይት የሚያጋጥማቸውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችላቸው ዘገባው አመልክቷል። ከሩሲያ ጋር በአገር ውስጥ ገንዘብ የሚገበያዩ አገራት ብዛት 40 ደርሷል ተብሏል፡፡
3፤ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሹ ኃይል በኦምዱርማን ከተማ ባንድ የገበያ ቦታ ላይ ፈጽሞታል ላለው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትና ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ ማስገባቱን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሱዳን ባለሥልጣናት፣ ቡድኑ በዚህ ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ዓለማቀፍ ሕግጋትን ኹሉ ጥሷል በማለት መክሰሳቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የሱዳን መንግሥት በዚኹ አቤቱታው፣ ቡድኑ በእዚህና መሰል ጥሰቶች፣ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ ሊፈረጅ የሚያስችሉትን መስፈርቶች አሟልቷል ብሏል ተብሏል።
4፤ የአሜሪካ ዓለማቀፍ የልማትና ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ በተጠባባቂነት እንዲመሩት እንደተሾሙለት ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ድርጅቱን መልሶ የማዋቀር ዓላማን ታሳቢ በማድረግ በድርጅቱ አጠቃላይ የውጭ ዕርዳታ ሥራዎቹ ላይ ፍተሻ እየተካሄደ መኾኑን ሩቢዮ ለኮንግሬሱ ማሳወቃቸውን ድርጅቱ ገልጧል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸው ድርጅቱን በተጠባባቂነት እንዲመሩ የሾሟቸው፣ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ፕሬዝዳንቱ ተስማምተዋል በማለት አማካሪያቸው ኤለን መስክ ከተናገሩ በኋላ ነው። ባኹኑ ወቅት ድርጅቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ አብዛኛዎቹን የዕርዳታ ሥራዎቹን አቋርጧል።
5፤ አሜሪካ፣ መቀመጫውን ጀኔቫ ካደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ልትወጣ እንደኾነ ተሠምቷል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት፣ ምክር ቤቱ በእስራኤል ላይ ከመጠን በላይ ትኩረት ያደርጋል፤ ለሌሎች ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈጻሚ መንግሥታት ሸፋን ይሠጣል በማለት እንደኾነ ፖለቲኮ ጋዜጣ ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካን ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አስወጥተዋት የነበር ቢኾንም፣ ተተኪያቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካን ወደ ምክር ቤቱ እንደመለሷት ይታወሳል። ምክር ቤቱ፣ በዓለም ዙሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመከታተል የጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ያደርጋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ፣ ጥር 27/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት በኹለቱ አገራት የጋራ ድንበር አካባቢ በሚንቀሳቀሱ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መውሰድ እንደጀመሩ ማስታወቁን የመንግሥት የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኃይል ርምጃው፣ ለኹለቱ አገራት ብሄራዊ ደኅንነት ስጋት የኾኑትን ሽብርተኝነትን፣ የኮንትሮባንድ ንግድን፣ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል ያለመ እንደኾነ ተገልጧል። የኬንያ ፖሊስ ሠራዊትም፣ በሰሜናዊ ኬንያ በመርሳቢት እና ኢሲዮሎ አውራጃዎች የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር፣ ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ሥራ፣ የሰዎች እገታና የጎሳ ግጭቶችን መቀስቀስን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል በቡድኑ ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኬንያን ፖሊስ መግለጫ ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ ከሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ጋር ግንኙነት የለኝም በማለት አስተባብሏል። የኬንያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ሙሉ በሙሉ እንደሚያከብር የገለጠው ቡድኑ፣ "ድንበር ዘለል የወንጀል መረቦች" መኖራቸውን ግን ጠቅሷል። ቡድኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮችና የደኅንነት ተቋሙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የድንበር ዘለል ሕገወጥ ተግባራትን ያመቻቻሉ በማለትም ከሷል። አባላቱ በድንበር ዘለል የወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፈው ወይም ተባባሪ ኾነው ከተገኙ ግን ርምጃ እንደሚወስድ ቡድኑ አስታውቋል።
2፤ ከአሜሪካ ዓለማቀፍ የልማትና ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ዕርዳታ ማቆሙን ተከትሎ፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ፍቃድ ውጭ ንብረት ማስተላለፍ፣ ማስወገድ ወይም መሸጥ ወይም ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ እንደማይችሉ ክልከላ ተጥሎባቸዋል። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ይህንኑ ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተገቢውን ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በኹሉም አገራት የገንዘብ ዕርዳታዎችንና የልማት ድጋፎችን መስጠት ያቆመ ሲኾን፣ የድርጅቱ የነፍስ አድንና የአስቸኳይ ዕርዳታዎች ግን ለጊዜው እገዳው አይመለከታቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የገንዘብ ዕርዳታ ተቀብለው፣ በአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ፣ በምግብ ዋስትና፣ በሥርዓተ ምግብ፣ በመጠጥ ውሃ፣ በስነ ጾታ፣ በትምህርት፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና የወባ በሽታን ጨምሮ በጤና እንዲኹም በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሚሠሩ በርካታ አገር በቀልና የውጭ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል።
3፤ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰበቦሩ ወረዳ ቀንጢቻ በተባለ ቀበሌ ትናንት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች፡፡ በመሬት መንሸራተት አደጋው ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች፣ በማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ተሠናርተው የነበሩ መኾናቸውንም ዋዜማ ተረድታለች፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ፣ ሌሎች በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ሕይወት ለማዳን የማፈላለጉ ሥራ እንደቀጠለ መኾኑንና ምናልባትም በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ ምናልባትም የአፈሩ ለምነትና የመሬቱ አቀማመጥ ሊኾን ይችላል ተብሏል፡፡
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች ቢሮ፣ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ከፋዮች ግብር ያለ ቅጣትና ወለድ መክፍል የሚችሉበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መኾኑን ተረድተው ግብሩን በቶሎ እንዲከፍሉ አሳስቧል፡፡ ቢሮው 429 ሺሕ 829 ግብር ከፋዮች በተያዘው በጀት ዓመት የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ ይከፍላሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጧል፡፡ ኾኖም እስከ ትናንት ባለው ጊዜ ግብር የከፈሉት፣ 228 ሺሕ 222 ግብር ከፋዮች እንደኾኑና በዚህም የከተማዋ አስተዳደር 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ቢሮው አመልክቷል። የጣሪያና ግድግዳ ግብር ማክፈያ ቀነ ገደብ የካቲት 30 እንደኾነም ቢሮው ጠቅሷል። ቢሮው ይህን ይበል እንጅ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቃዋሚው እናት ፓርቲ በመሠረተው ክስ መሠረት የከተማዋ አስተዳደር ተግባራዊ እያደረገው የሚገኘው የጣሪያና ግድግዳ ግብር ሕጋዊነት እንደሌለውና ይህንኑ ለማስፈጸም ያወጣው መመሪያም ተፈጻሚ እንዳይሆን ከ15 ቀናት በፊት መወሰኑ ይታወሳል።
5፤ ሳልሳዊ ወያነ ፓርቲ፣ የአሜሪካው ዓለማቀፍ የተራድዖና ልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቆም መወሰኑ ለትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች ከባድ መርዶ መኾኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ የማቆም ዜና፣ በተፈናቃዮች ላይ ብቻ ሳይኾን ለጉዳት ተጋላጭ በኾኑ የክልሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል መጠነ ሰፊ ስጋት እንደፈጠረ ፓርቲው ገልጧል። ፓርቲው፣ የትግራይ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ሰቆቃ እንዲያበቃ ዘላቂውና አዋጭ የኾነው መፍትሄ፣ ተፈናቃዮችንና ስደተኞችን ወደ ቀያቸው ባስቸኳይ መመለስ ነው ብሎ እንደሚያምን ጠቅሷል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትና ዓለማቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ይህን ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያስቀሩ የጠየቀው ፓርቲው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይ ግዛቶችን በኃይል የያዙ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ባስቸኳይና ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲወጡ እንዲያደርግ፣ ተፈናቃዮች ደኅንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ኹኔታዎችን እንዲያመቻችና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶችን እንዲጨምር ግፊት እንዲያደርጉም ጠይቋል።
6፤ የአውሮፓ ኅብረት የዓለማቀፍ አጋርነት ተቋም፣ በተለያዩ አገራት ያሉትን 100 ቢሮዎች ወደ 18 ሊቀንስ እንደኾነና ከአፍሪካ ቢሮዎቹ የኢትዮጵያውን፣ የሴኔጋሉንና የጋናውን ግን ላለመዝጋት መወሰኑን መረዳታቸውን በመጥቀስ የኅብረቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ተቋሙ የኢትዮጵያውን ጨምሮ በሦስቱ አገራት ቢሮዎቹን ላለመዝጋት የወሰነው፣ ቢሮዎቹ በዋናነት በፍልሰት ዙሪያ ስለሚሠሩ እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ወደ አውሮፓ በሕገወጥ መንገድ ከሚገቡ ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ፣ የሴኔጋልና የጋና ዜጎች መኾናቸው፣ ቢሮዎቹ እንዳይዘጉ ምክንያት ነው ተብሏል። ኅብረቱ የቢሮዎቹን ቁጥር የሚቀንሰው፣ በዓለም ላይ በተከሰቱ ጅዖፖለቲካዊ ለውጦችና በበጀት እጥረት ሳቢያ የውሳኔ አሠጣጡን ብራስልስ ላይ ለማማከል እንደኾነም ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ተቋሙ፣ የኅብረቱን ዓለማቀፍ አጋርነትና የልማት ፖሊሲዎች የመንደፍ ሥልጣን ያለው ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ፣ ረቡዕ ጥር 28/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከ50 በመቶ በላይ የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች ከተቋማዊ መዋቅር ጋር በተያያዘ መዘጋታቸውን ዋዜማ ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ሰምታለች። ባኹኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች 565 ገደማ ሲኾኑ፣ ከ540 በላይ የሚኾኑት ግን እንደተዘጉ መረዳት ተችሏል። በአዲስ አበባ ከ116 የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች 33ቱ ብቻ እንደቀሩ ምንጮች ተናግረዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ነባር የተቋሙ ሠራተኞችም ተቀንሰዋል ተብሏል። ኾኖም ድርጅቱ ያሠራው መዋቅር እስካኹን ለሠራተኞች ይፋ እንዳተደረገ ምንጮች ገልጸዋል።
2፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ የደኅንነት ስጋት ትፈጥራላችኹ በሚል ጠርጥሬያቸዋለኹ ያላቸውን ነዋሪዎች በዘፈቀደ ካሠረ በኋላ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር እየተቀበለ እንደሚለቅ ዋዜማ ታስረው ከተፈቱ ሰዎች ሰምታለች። ባለፈው ቅዳሜ ገርጂ አካባቢ ከታሠሩ 50 ወጣቶች መካከል፣ ስድስቱ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር ከፍለው መለቀቃቸውንም ዋዜማ ተረድታለች። ገንዘቡን መክፈል አንችልም ያሉ ወጣቶች፣ ለአራት ቀናት ከታሠሩ በኋላ ፖሊስ ጣቢያውን የሚጎበኙ ዓቃቢያነ ሕግ እንደሚመጡ ሲታወቅ እንደተለቀቁ ተናግረዋል። ገንዘቡ የሚከፈለው በደረሰኝ ሳይኾን፣ ለተረኛ ፖሊሶች በጉቦ መልክ የሚከፈል ነው ተብሏል። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ የከተማዋን ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሠ ምላሽ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
3፤ ጤና ሚንስቴር፣ በአሜሪካው ዓለማቀፍ የልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) እና በአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያ ድርጅት (ሲ ዲ ሲ) የገንዘብ ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺሕ በላይ ሠራተኞች የቅጥር ውላቸው እንዲቋረጥ ለክልሎችና ለኹለቱ የከተማ አስተዳደሮች መመሪያ አስተላልፏል። ሚንስቴሩ፣ በኹለቱ ተቋማት የገንዘብ ዕርዳታ የሚከናወኑ ሥራዎችም ኾኑ ክፍያዎች እንዲቋረጡ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ለክልሎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል። ሚንስቴሩ መመሪያውን ያስተላለፈው፣ በአሜሪካ የገንዘብ ዕርዳታ የሚካሄዱ ሥራዎች በዓለም ዙሪያ ለ90 ቀናት እንዲቆሙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ባዘዙት መሠረት ነው።
4፤ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ብሩህተስፋ ሙሉጌታ፣ ትናንት የኔዘርላንድ የፍልሰት ልዩ ልዐክ ፒተር ሹማን ከመሩት ልዐካን ቡድን ጋር በኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ዙሪያ አዲስ አበባ ውስጥ መወያየታቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል። ውይይቱ ያተኮረው፣ ኹለቱ አገራት ፍልሰተኞችን በመመለስና ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ በመቀላቀል ዙሪያ በሚያደርጉት ትብብር ላይ እንደኾነ አገልግሎቱ ገልጧል። ኔዘርላንድ አባል የኾነችበት አውሮፓ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አውሮፓ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ፍላጎት አላሳየም በማለት፣ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያዊያን ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉ አይዘነጋም።
5፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ ከ50 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሏቸውና
በሕዝብ ባለቤትነት የተያዙ ኩባንያዎች መረጃዎቻቸውን እስከ መጋቢት 1 ድረስ እንዲያቀርቡ ትናንት ማሳሰቢያ ሠጥቷል። ባለሥልጣኑ፣ ኩባንያዎች እንዲያቀርቡለት የጠየቃቸው መረጃዎች፣ የአክሲዮኖችን ብዛት፣ የባለአክሲዮኖችን አድራሻ፣ የአክሲዮኖች ዋጋ እና የአክሲዮን አወጣጥ ዝርዝሮችንና ተዛማጅ መረጃዎችን ነው። መረጃዎቹ ግልጽነትን ለማስፈንና ጠንካራ የካፒታል ገበያ ሥነ ምኅዳር ለመፍጠር አስፈላጊ መኾናቸውን የጠቀሰው ባለሥልጣኑ፣ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ መረጃዎቹን አለማቅረብ ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።
6፤ የኬንያ የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል፣ በሰሜናዊ ኬንያ በመርሳቢትና ኢሲዮሎ አውራጃዎች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት "የወንጀል መረብ" ላይ እየተወሰደ ያለው ዘመቻ ውጤት ማስገኘቱን ትናንት ማምሻውን ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። የኬንያ ጸጥታ ኃይሎች በኹለቱ ግዛቶች ሶሎሎ እና መርቲ በተባሉ አካባቢዎች በወሰዷቸው ርምጃዎች፣ የቡድኑ የተቀጣጣይ ፈንጂ መስሪያ ቁሳቁሶች፣ ዘመናዊ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ መገናኛ ሬዲዮዎች፣ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ ጥይቶችና ጀኔሬተሮች እንደተያዙ ግብረ ኃይሉ ገልጧል። ግብረ ኃይሉ፣ ቡድኑ ሽብርተኝነትን መደገፍንና የጎሳ ግጭት መቀስቀስን ጨምሮ በኬንያ ላይ ከፍተኛ "የብሄራዊ ደኅንነት ስጋት ደቅኗል" ብሏል። የአገሪቱ ጸጥታ ኃይሎች በቡድኑ ላይ ለከፈቱት ዘመቻ፣ ከኢትዮጵያ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር ምን ዓይነት ትብብር እያደረጉ እንደኾነ ግብረ ኃይሉ አልገለጠም።
7፤ አሜሪካ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እንድትወጣ የሚያስችለውን ትዕዛዝ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፈርመዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካን ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አስወጥተዋት የነበር ቢኾንም፣ ተተኪያቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካን ወደ ምክር ቤቱ እንደመለሷት ይታወሳል። ምክር ቤቱ፣ በዓለም ዙሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመከታተል የጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ያደርጋል። ፕሬዝዳንቱ፣ አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጋር ያላትን ግንኙነት በድጋሚ እንደምትፈትሽም አስታውቀዋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ፣ ጥር 28/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኙ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት ጥናት እያደረገ መኾኑን አስታውቋል። ተቋሙ፣ የፍጥነት መንገዶቹ የሚገነቡት፣ ከአዲስ አበባ እስከ ደሴ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ደብረማርቆስ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ጅማ እና ከአዲስ አበባ እስከ ነቀምት እንደኾነ ገልጧል። መንገዶቹ የሚዘረጉበት መልክዓ ምድር ባብዛኛው ተራራማ ቦታዎችን የሚሸፍን መኾኑን የጠቀሰው ተቋሙ፣ ግንባታዎቹ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃሉ ብሏል። ባኹኑ ወቅት የፕሮጀክቶቹ የአዋጭነትና የመሠረታዊ የዲዛይንና የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መኾኑንና የአራቱን የፍጥነት መንገዶች ግንባታ ወጪ የሚሸፈነው በመንግሥትና በግል አጋርነት ትብብር እንደኾነም ተቋሙ ጠቅሷል፡፡ ከአዲስ እስከ ጅማ እንዲሁም ከአዲስ እስከ ደብረ ማርቆስ ለሚገነቡት መንገዶች የተነደፉ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚንስቴር እንደቀረቡ ተገልጧል።
2፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከ11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ተመላሽ ማድረጉን ሪፖርተር ዘግቧል። ባንኩ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያስመለሰው ብድር ከዕቅዱ በአንድ ቢሊዮን ብር እንደሚልቅ ባንኩ መናገሩን የጠቀሰው ዘገባው፣ በዚኹ ጊዜ ውስጥ ከ13 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱንም አመልክቷል። ኾኖም ባንኩ በጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመስተካከልና ባንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ሳቢያ፣ የተበላሹ ብድሮችን በማስመለስ ረገድ ችግሮች እንደገጠሙት ትናንት ጉዳዩ ከሚመለከተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ጋር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ተናግሯል ተብሏል። ባንኩ፣ ለግብርውና ዘርፍ አበድሮ ያልተመለሰለትን 4 ነጥብ 97 ቢሊዮን ብር የተበላሸ ብድር ለመሠረዝ መወሰኑን ባለፈው ዓመት ግንቦት ላይ አስታውቆ ነበር።
3፤ ፍትሕ ሚንስቴር፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ከአቅም በላይ በመኾኑ ከውጭ አገራት ጋር የጋራ የወንጀል የምርመራ ቡድን ለማወቅር መገደዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የ6 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ተናግሯል። በምሥራቅና ደቡብ የአገሪ አካባቢዎች ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መበራከቱንና የወንጀሉን ሰንሰለት በማጥናት ዋና አስተባባሪዎችን የመለየት ሥራ መጀመሩን የሚንስቴሩ ሃላፊዎች ገልጸዋል። ሚንስቴሩ፣ ለዓለማቀፍ የግልግል ዳኝነት ተቋማት በውጭ ምንዛሬ የሚከፈሉ ክፍያዎች መዘግየትና አንዳንድ የፖሊስ አባላት የሚያሳዩት የስነምግባር ጉድለት ለሥራው ተግዳሮት እንደኾኑበትም ሃላፊዎቹ ጠቅሰዋል። በወንጀል የተገኘ ሃብትን በማስመለስ ረገድ፣ ባኹኑ ወቅት በሚንስቴሩ ሥር 292 የሃብት ምርመራ መዛግብት ይገኛሉ ተብሏል።
4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአገር ውስጥ የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻ ለጊዜው ተዘግቶ መዋሉን አስታውቋል። የአገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻ ለጊዜው የተዘጋው፣ ዛሬ ከቀኑ 6:30 ገደማ ከመንገደኞች የሚሰበሰቡ የሲጋራ መለኮሻዎች ወይም ላይተሮች ከሚቀመጡበት ሥፍራ ጭስ በመከሰቱ እንደኾነ አየር መንገዱ ገልጧል። ይህንኑ ተከትሎ፣ ዛሬ ወደ አገር ውስጥ የአየር መንገዱ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለማቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ሲሳፈሩ ውለዋል። እየር መንገዱ የአገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻ ከነገ ጥር ጀምሮ እንደገና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብሏል።
5፤ የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ)፣ በዓለም ዙሪያ በእርዳታ ሥራ ተሠማርተው የሚገኙ አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ሠራተኞቹ በሙሉ ከቀጣዩ ዓርብ ጀምሮ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የአሜሪካ መንግሥት አዟል። የድርጅቱን ቁልፍ ሥራዎች የመምራት ሃላፊነት ያለባቸው የተወሰኑ ሠራተኞችና አመራሮች ግን በተመደቡባቸው አገራት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆዩ መንግሥት ፈቅዷል። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዩ ኤስ ኤ አይ ዲን ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ጋር ለመቀላቀል የወሰነ ሲኾን፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማርኮ ሩቢዮም የተቋሙ ጊዜያዊ ሃላፊ ኾነው ተሹመዋል። ድርጅቱ በኢትዮጵያ በስብዓዊ ዕርዳታ፣ በምግብ ዋስትና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በሥርዓተ ምግብና ሌሎች በርካታ ዘርፎች ድጋፎችን በማድረግ ይታወቃል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ እንዲቋረጥ ያስተላለፉት ትዕዛዝ የነፍስ አድንና አስቸኳይ ዕርዳታዎችን አይመለከትም ቢባልም፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ግን የትኞቹ ፕሮግራሞቹ ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እስካኹን ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ፣ ጥር 29/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ አሜሪካ፣ ግብጽ የጋዛ ነዋሪዎችን ተቀብላ እንድታሠፍር ለማግባባት የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመችበት መኾኑን ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ኒው ዓረብ ድረገጽ ዘግቧል። የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑካን ሰሞኑን ወደ ካይሮ ባቀኑበት ወቅት፣ ከግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደር አብደላቲና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋር በዚኹ ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። የሕዳሴው ግድብ ውዝግብን ለመፍታት አሜሪካ ገንቢ ሚና እንድትጫወት ከተፈለገ፣ ግብጽ የጋዛ ነዋሪዎችን ተቀብላ ማስፈር እንዳለባት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለግብጽ አቻዎቻቸው ነግረዋቸዋል ተብሏል። ግብጽ ግን ከፊል የጋዛ ነዋሪዎችን እንድታሠፍር ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው ዙር የሥልጣን ዘመናቸው፣ የግድቡን ውዝግብ ለመፍታት ያቀረቡትን አስገዳጅ የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓ አይዘነጋም።
2. በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በጅማ ከተማ ቤታቸው ለኮሪደር ልማት የፈረሠባቸው ነዋሪዎች መንግሥት በተከራየላቸው የሆቴል አልጋዎች፣ በግለሰብ መኖሪያዎችና በቀበሌ ቤቶች ውስጥ እየተንገላቱ መኾኑን ለዋዜማ ተናግረዋል። በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ግራና ቀኝ ያሉ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ለኮሪደር ልማቱ መፍረሳቸውን ምንጮች ተናግረዋል። ከፈረሱት ቤቶች መካከል፣ አብዛኞቹ ሕጋዊ ካርታ ያላቸውና ግብር ከፋይ እንደነበሩ የጠቀሱት ምንጮች፣ ለፈረሱት ቤቶች ባለቤቶች መንግሥት የገንዘብ ካሳም ይኹን ተለዋጭ ቦታ አልሠጣቸውም ብለዋል። በኮሪደር ልማቱ የፈረሱት ቤቶች 15 ሺሕ ገደማ እንደኾኑ ዋዜማ ተረድታለች።
3፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት፣ በአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ገንዘብ የሚደገፉ ፕሮጀክቶች ሥራ ማቆማቸው በእጅጉ እንዳሳሰበው ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የገንዘብ እርዳታውን በድንገት ማቆሙ፣ በድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ድርጅቶቹ ድጋፍ በሚያደርጉላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ምክር ቤቱ ገልጧል። ምክር ቤቱ፣ በገንዘብ እርዳታው መቋረጥ የተጎዱ ድርጅቶች አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን የሚያገኙበትንና ችግሩን የሚቋቋሙበትን መንገድ የሚያፈላልግ አንድ ቡድን እንዳቋቋመ ጠቅሷል። ይህንኑ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አንድ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት ማቀዱንም ምክር ቤቱ ገልጧል።
4፤ የኬንያ ፖሊስ፣ በሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ባንድ ቤት ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 58 ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ኪቲንጌላ አውራጃ ውስጥ ትናንት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ካልያዙት ኢትዮጵያዊያኑ ጋር በተያያዘ፣ ኹለት ኬንያዊያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑን ሲያገኛቸው፣ በምግብ እጥረት ተጎድተውና ደክመው ነበር ተብሏል። ኢትዮጵያዊያኑ በሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ሲጠባበቁ እንደነበርም ፖሊስ መናገሩን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሐሙስ፣ ጥር 29/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የተመድ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮግራም (ዩ ኤን ኤድስ)፣ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ዕርዳታ ማቋረጡ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአዲስ አበባ እንዲኹም በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች በሚገኙ 270 ሺሕ ያህል የኤች አይ ቪ ታማሚዎች ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል በማለት አስጠንቅቋል።.በአገሪቱ ባኹኑ ወቅት መድሃኒት የሚወስዱ ታማሚዎች ብዛት 503 ሺሕ እንኾነ ድርጅቱ ጠቅሷል። ድርጅቱ፣ የእርዳታው መቆም፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ለበሽታው ተጋላጭ የኾኑ ሰዎች የኤች አይ ቪ ምርመራ፣ ለመድሃኒት አቅርቦት፣ ለበሽታው መከላከያ፣ ለሳምባ ምርመራ፣ በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ተደራሽ እንዳይኾኑ ያደርጋቸዋል ብሏል። ከእነዚህ ውስጥ 235 ሺሕ 560 ሰዎች ለበሽታው በድጋሚ ላለመጋለጥ የሚጠቀሙትን የኮንዶም አቅርቦት እንደሚያጡና 18 ሺህ ያህል ታማሚዎች የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶች እንደሚቋረጥባቸው ተገልጧል። የታማሚዎችን መረጃ ወደ ጤና ሥርዓቱ በየጊዜው የሚያስገቡ 10 ሺሕ የመረጃ ሠራተኞችም ሥራ እንደሚያቆሙ ድርጅቱ ጠቅሷል።
2፤ ዛሬ በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ የሕወሓት አመራሮች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱና በትግራይ ዘላቂ ሰላም እንዲሠፍን ጠይቀዋል። በተያያዘ፣ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የትግራይ ሕዝብ ባለፉት መቶ ዓመታት ያደረጋቸው ጦርነቶች “ሕልውናውን ለማረጋገጥ" እና ለጭቆና አጅ ላለመሰጠት" የተደረጉ መኾናቸውን ጠቅሶ፣ የትግራይ ሕዝብ ባደረጋቸው የትጥቅ ትግሎች እንደማይቆጭ ገልጧል። ቡድኑ ይህን ያለው፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትግራይ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ያደረጋቸው ጦርነቶች እንደጎዱት ጠቅሰው መልዕክት ባስተላለፉ ማግስት ነው። የትግራይ ሕዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች እንደ ሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ሕልውናውን የሚወስኑ ነበሩ ያለው ቡድኑ፣ ቁጭት ውስጥ መግባት ያለባቸው በትግራይ ሕዝብ ላይ ባዕዳን ኃይሎችን ያዘመቱ አካላት ናቸው ብሏል። ቡድኑ፣ አኹንም በትግራይ ዘላቂ ሰላም እንዲሠፍን ቁርጠኛ አቋም እንዳለው አረጋግጧል።
3፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በሕጋዊ የንግድ ተቋማት ሺሻ የማስጨስና ጫት የማስቃም ድርጊቶችን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ አገኘኋቸው ያላቸውን ግለሰቦች 2 ሺሕ ብር እየቀጣ መልቀቁን አስታውቋል። በተለይ በበቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ አዋኪ ድርጊቶች በሚፈጸምባቸው ቤቶች ውስጥ የተገኙ ግለሰቦችን በጊዜያዊነት ፖሊስ ጣቢያ ካቆየ በኋላ፣ ግለሰቦቹ ለፈጸሙት የደንብ መተላለፍ ጥፋት የከተማዋ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት በደረሰኝ እያስከፈለ በማስጠንቀቂያ መልቀቁን ገልጧል። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፖሊስ አባላት ግለሰቦችን የደኅንነት ስጋት ትፈጥራላችሁ በማለት የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች እያሠሩ በነፍስ ወከፍ እስከ 2 ሺሕ ብር ያለ ደረሰኝ እንደሚቀበሉ በመጥቀስ ዋዜማ ትናንት የዘገበችው ዘገባ እውነትን መሠረት ያላደረገ ነው በማለትም አስተባብሏል። ደንብ ከሚተላለፉ ግለሰቦች የገንዘብ ቅጣት የመሰብሰብ ሥልጣን እንደሌለው የገጠቀሰው ፖሊስ፣ ቅጣቱን ያስፈጸሙት የከተማዋ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ሠራተኞች ናቸው ብሏል።
4፤ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሐንስ ቧያለው ዓቃቤ ሕግ የከሰሰኝ በወከልኩት ሕዝብ ላይ የደረሰውን "በደል እና ግፍ" በመቃወሜ" ነው በማለት ዛሬ ለፍርድ ቤት የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለም፣ ክስ ቀረበብኝ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሳለኹ "የመንግሥትን ብልሹ አሠራር በማጋለጤ ነው" በማለት ክሱን መካዳቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ከዮሃንስ ጋር ወንጀል "አልፈጸምንም" በማለት ቃላቸውን መስጠታቸውን ጠበቃዎች ተናግረዋል ተብሏል። ፍርድ ቤቱ፣ 21 የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከመጋቢት 5 እስከ 12 እንደሚያዳምጥ አስታውቋል።
5፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት አዋጅን ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ አጽድቋል። የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት አዋጅ የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍና የዜጎችን የወሳኝ ኩነቶች መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ እንደሚያስችል ተናግሯል። አዋጁ ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የውጭ አገር ዜጎች ጭምር እንዲመዘገቡና የተሻለ የደኅንነት ጥበቃ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።
6፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ፣ ደንበኞቹ ከውጭ አገራት በቀጥታ ወደ አገር ውስጥ በኤምፔሳ ገንዘብ መላክ የሚያስችላቸውን ስምምነት ከዳሽን ባንክ እና ከካሽ ጎ ጋር ዛሬ መፈራረሙን አስታውቋል። ስምምነቱ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቀጥታ በካሽ ጎ ሞባይል መተግበሪያ አማካይነት ወደ ኤምፔሳ ገንዘብ የሚልኩበትና አገር ውስጥ የሚኖሩ ደንበኞችም መቀበል የሚችሉበትን ዕድል የሚፈጥር እንደኾነ ኩባንያው ገልጧል። በስምምነቱ ውስጥ ዳሸን ባንክ የሐዋላ ገንዘብ ልውውጡን አስተማማኝ ለማድረግ የራሱን ሚና ይጫወታል ተብሏል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ዓርብ፣ ጥር 30/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል የዘንድሮው የጤና መድኅን ክፍያ ካለፈው ዓመት አንጻር ከእጥፍ በላይ መጨመሩን ዋዜማ ተረድታለች። ባለፈው ዓመት ከፍተኛው የጤና መድኅን ክፍያ 1 ሺሕ 100 ብር ገደማ ሲሆን፣ ዘንድሮ ክፍያው ወደ 2 ሺሕ 800 ብር ማድጉን ዋዜማ ሰምታለች።
ለገጠር ነዋሪዎች እስከ 900 ብር የነበረው ከፍተኛው ክፍያ፣ ዘንድሮ ወደ 2 ሺሕ ብር ከፍ ብሏል። የክልሉ ጤና መድህን አስተዳደር በከተሞች የቤተሰብ ቁጥርን መሠረት ያደረገውን ክፍያ፣ ዘንድሮ የነዋሪዎችን ገቢ መሠረት ወደሚያደርግ ሥርዓት ቀይሮታል። አርሶ አደሮች የዘንድሮው የጤና መድኅን ክፍያ ከፍተኛ ነው በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ሲኾን፣ በብዙ ቦታዎች አልከፍልም ያሉ አርሶ አደሮች በግድ እንዲከፍሉ ጫና እየተደረገባቸው እንደኾነ ምንጮች ተናግረዋል።
2፤ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን፣ ከኅዳር ወር ወዲህ በትግራይ፣ አፋር፣ ኦሮሚያና አማራ ክልሎች ከ17 ሺሕ 400 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ከኅብረተሰቡ ጋር መልሶ ማዋሃዱን ትናንት በሥራ ክንውኑ ዙሪያ ከለጋሽ አገራትና ተቋማት ተወካዮች ጋር በተወያየበት ወቅት አስታውቋል። ኾኖም ኮሚሽኑ የቀድሞ ተዋጊዎችንና ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈትቶ መልሶ የማዋሃዱ መርሃ ግብር ከፍተኛ ሀብት እንደሚጠይቅ በመግለጽ፣ ለጋሾች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቋል። ለጋሾችም ለመርሃ ግብሩ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ኮሚሽኑ ገልጧል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ፣ የአጋር አገራት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የጀመረውን የመጀመሪያ ዙር ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ የማዋሃድ ሂደት ላንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ለምን እንዳቋረጠው እስካኹን በይፋ አልገለጠም።
3፤ ገንዘብ ሚንስቴር፣ ዕድሜያቸው ከኹለት ዓመት በታች የኾኑ ህጻናት የመቀንጨር ምጣኔን ለመቀነስ ለሚረዳው የሰቆጣ ቃልኪዳን መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ አዲስ መመሪያ አዘጋጅቷል። መመሪያው፣ ከመንግስት የሚመደበውን በጀት ወጥ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር ያለመ መኾኑን ዋዜማ ከመመሪያው ሰነድ ተመልክታለች። ቃልኪዳኑ በ15 ዓመት ውስጥ ስለሚተገበር፣ የወረዳዎች ቁጥርም እየጨመረ ስለሚሄድና የፋይናንስ አስተዳዳሩ የመንግስትን የፋይናንስ ሥርዓት እንዲከተል ማድረግ በማስፈለጉ መመሪያው እንደተዘጋጀ ሰነዱ ያስረዳል። በኹለተኛው የማስፋፊያ ምዕራፍ፣ መርሃግብሩ በ334 ወረዳዎች ውስጥ በመተግበር ላይ ሲኾን፣ መርሃ ግብሩ በማጠናቀቂያው በ2019 ዓ፣ም 700 ወረዳዎችን እንዲሽፍን ታቅዷል።
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አንዳንድ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በሦስተኛ ወገኖች በውል ሠጥቶ ለማሠራት የሚያስችለውን ደንብ ትናንት ምሽት አጽድቋል። ደንቡ፣ በሦሶተኛ ወገኖች አማካኝነት እንዲሠሩ የዘረዘራቸውን መንግሥታዊ አገልግሎቶች አስተዳደሩ ለጊዜው አልጠቀሰም። የከተማ አስተዳደሩ፣ በከተማዋ በጀት መድቦላቸዉ የተገነቡና በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎች በዘመናዊ ሕክምና መሳሪያ ለማሟላትና ዓለማቀፍ ደረጃን ያሟሉ አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካካበቱ የግል ዘርፍ ተቋማት ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉንም ገልጧል።
5፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት ባለፈው ዓመት በሦስት እጥፍ መጨመሩን የኬንያው ቢዝነስ ደይሊ ጋዜጣ አስነብቧል። ባለፈው ዓመት ታኅሳስ ወር የኩባንያው የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን የነበረ ሲኾን፣ በዘንድሮው ታኅሳስ ግን ቁጥሩ ወደ 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል። የኩባንያው የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ የጨመረው፣ የአየር ሰዓት እና ዳታ በኤምፔሳ አማካኝነት የሚገዙ ተጠቃሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንዲሁም ኩባንያው በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ድንበር ዘለል የገንዘብ የኤምፔሳ አገልግሎት በመጀመሩ እንደኾነ ከኩባንያው ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ ጋዜጣው ዘግቧል።
6፤ አሜሪካና እስራኤል፣ የጋዛ ነዋሪዎችን በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝና ሞሮኮ ውስጥ ለማስፈር እያሰቡ መኾኑን ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘግቧል። ሌሎች የዜና ምንጮች ደሞ፣ ለጋዛ ነዋሪዎች መስፈሪያነት ሶማሌላንድ ጭምር እንደታጨች ዘግበዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በፑንትላንድ ከመሸገው የአይ ኤስ ነውጠኛ ቡድን ላይ ከቀናት በፊት አሜሪካ የአየር ላይ ጥቃት እንድትፈጽም ማድረጋቸው ይታወሳል። የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር፣ ለሶማሌላንድ የአገርነት እውቅና ሊሰጥ ይችላል የሚሉ ዘገባዎችም መውጣታቸውና የሶማሌላንድ ዜጎችም ይሄው ተስፋ እንዳላቸው ሲገልጹ መሰንበታቸው አይዘነጋም። ሞሮኮን በተመለከተም፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው ዙር የሥልጣን ዘመናቸው፣ ሞሮኮ የምዕራብ ሰሃራ ግዛት ሉዓላዊ ግዛቴ ናት ለሚለው አቋሟ በይፋ እውቅና መስጠታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ፑንትላንድ፣ ሶማሌላንድና ሞሮኮ ለፍልስጤማዊያን መስፈሪያ እንዲኾኑ ታስበዋል የተባለው፣ ግብጽና ዮርዳኖስ ፍልስጤማዊያኑን ተቀብለው እንዲያሠፍሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን በገለጹ ማግስት ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ዓርብ፣ ጥር 30/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በቅርቡ የተሾሙት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የማያሠራ ጫና ከገጠማቸው ሥራቸውን እንደሚለቁ መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ብርሃኑ የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር የጀመሯቸውን ሥራዎች በማስቀጠል እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ዋና ኮሚሽነሩ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ የትምሕርትና ግንዛቤ ሥራዎችን ማስፋፋት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በገለልተኛነት መመርመርና አጥፊዎች እንዲታረሙና ተጎጂዎች እንዲካሱ ማድረግ ቅድሚያ ትኩረት የሚሠጧቸው ሥራዎች እንደኾኑ ተናግረዋል ተብሏል። ጠንካራ የሰብዓዊ መብት ትምህርትና ሥልጠና የሚሰጥ የሰብዓዊ መብቶች ኢንስቲትዩት የማቋቋም ሃሳብም እንዳላቸው ዋና ኮሚሽነሩ እንደገለጡ ዘገባው አመልክቷል።
2፤ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት፣ ለአገራዊ ምክክሩ የመረጣቸውን አጀንዳዎቹን ትናንት ለአገራዊ ምክክሩ ኮሚሽን አስረክቧል። ምክር ቤቱ፣ ከሕዝብ በሚሰብሰብ ግብር የሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ምክንያት የዲሞክራሲ ተቋምነት ኅልውናቸው አደጋ ላይ ወድቋል ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። በመንግሥት ሥር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን አገራዊ የጋራ መግባባት እንዳይፈጠር እንቅፋት ኾነዋል በማለት የከሰሰው ምክር ቤቱ፣ የሕዝብ መገናኛ ብዙኀን አስተዳደር ጉዳይ በአገራዊ ምክክሩ አጀንዳ እንዲኾን መጠየቁን ዘገባው ጠቅሷል። በመንግሥት የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኀን የሕዝብን ሃብት በብቸኝነት በመያዝ፣ የግል መገናኛ ብዙኀንን ከተሳትፎ ውጪ አድርገዋል በማለትም ምክር ቤቱ ችግሩን አብራርቷል ተብሏል። መረጃን በነጻነት የማግኘት መብትና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙ አፈናዎችና እንግልቶችን የሚመለከቱ አጀንዳዎችም ለኮሚሽኑ እንደቀረቡ ተገልጧል።
3፤ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የዎላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲዊ ግንባር እና የዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ወላይታ ሶዶን ጨምሮ የሪጅዮፖሊ ከተሞችን ለማደራጀት ባወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተቃውሞ አቅርበዋል። ፓርቲዎቹ፣ የወላይታ ዞን መቀመጫ የኾነችው ሶዶ የአስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ተጠሪነቷ ለክልሉ መንግሥት እንዲኾን ረቂቅ አዋጁ መደንገጉና የከተማው ምክር ቤት አባላትና በሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች የከተማዋ ተወካዮች ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ይመረጣሉ ተብሎ በአዋጁ ላይ መጠቀሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርገውታል። የከተሞች የፈርጅ ለውጥ የከተማ የዕድገት መለኪያ እንጂ ከፖለቲካዊ ተጠሪነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ያሉት ፓርቲዎቹ፣ የአስተዳደራዊ ተጠሪነት ለውጡ የወላይታን ሕዝብ ከከተማዋ ባለቤትነቱ ለመነጠልና የከተማዋን ተቋማት ከዎላይታ ዞን አስተዳደር ለማስወጣት ያለመ ሴራ ነው በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ፣ ከወላይታ ሶዶ በተጨማሪ አርባምንጭና ዲላ ከተሞችን ወደ ሪጂዮፖሊ ከተማ አስተዳደርነት ያሳደገ ነው። ፓርቲዎቹ ይህንኑ መግለጫ ካወጡ በኋላ፣ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሶዶ የሪጂዮፖሊ ከተማ እንድትኾን መወሰኑን ገልጧል።
4፤ የኬንያ የጸረ ሽብር ፖሊስ፣ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያው አማጺ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መሪ ነው ያለው ሳዳም ቡኬ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ መናገሩን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሳዳም ቡኬ፣ በሰሜናዊ ኬንያ በመርሳቢት እና ኢሲዮሎ አውራጃዎች የቡድኑ መሪ እንደኾነ ፖሊስ መግለጡን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የቡድኑ መሪ በቁጥጥር ሥር የዋለው፣ የአገሪቱ ጸጥታ ኃይሎች በኹለቱ አውራጃዎች የወንጀል መረብ በመዘርጋት በአገሪቱ ብሄራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ ደቅኗል ባሉት በቡድኑ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ በጀመሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው። የኬንያ የጸረ ሽብር ፖሊስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኹለቱ አውራጃዎች የሱማሊያውን አልሸባብን በሽብር ድርጊቶች በመርዳት፣ የአደንዛዥ እጽ፣ የሰዎችና ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በማካሄድ፣ የማስለቀቂያ ገንዘብ ማካበትን ዒላማ ያደረገ የሰዎች እገታ በመፈጸም፣ ሕገወጥ የማዕድን ቁፋሮ በማካሄድ እና የጎሳ ግጭቶችን በመቀስቀስ ወንጀሎች ተሠማርቷል በማለት ይከሳል።
5፤ የአውሮፓ ኅብረት የአስቸኳይ አደጋዎች መከላከያ ቢሮ፣ በአማራ ክልል እንደገና ባገረሸው የኮሌራ በሽታ የሦስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ቢሮው፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን 122 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙና በቋራ እና በገንዳ ውሃ ወረዳዎች ብቻ ኹለት ሰዎች በበሽታው እንደሞቱ ማረጋገጡን ገልጧል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደሞ አንድ ሰው በበሽታው እንደሞተና በባሕርዳር ከተማ 33 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙም የቢሮው መረጃ አመልክቷል። የበሽታው መነሻ፣ ቋራ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ በርሜል ጊዮርጊስ የሚባል የጸበል ቦታ እንደኾነ የጠቀሰው ቢሮው፣ ጸበሉን ለመጠቀም ከሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ስለሚሄዱ በሽታው የመስፋፋት ዕድሉ ከፍተኛ ነው ብሏል። በክልሉ የሚካሄደው ግጭት ለረድኤት ድርጅቶች እንቅስቃሴ እክል እንደሆነ መቀጠሉንም ማዕከሉ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ፣ የካቲት 1/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ አካባቢ ሐሙስ'ለት በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ይጓዙ በነበሩ መንገደኞች ላይ በተፈጸመ እገታ አንድ ሰው መገደሉን መስማቱን ዴይቸቨለ ዘግቧል። አራት ሰዎች ደሞ በእገታው ወቅት እንደቆሰሉ የዓይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ አካላት እገታውን የፈጸሙት፣ ከገንዳ ውሃ ከተማ ወደ ጎንደር ሲጓዙ በነበሩ የሕዝብ መጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ላይ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ታጣቂዎቹ ተኩስ የከፈቱት፣ መንገደኞች ዝርፊያውን ለመከላከል በሞከሩበት ወቅት ነው ተብሏል። ባለፈው እሑድም ማዕከላዊ ጎንደር ከአዘዞ ከተማ ወደ መተማ 18 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይም ጭልጋ ወረዳ «ናረው ዳርዳ» ከተባለ ቦታ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እገታ ተፈጽሟል።
2፤ በውጭ አገራት የተመሠረተው 'ብርጌድ ንሐመዱ' የተሠኘው የኤርትራ ተቃዋሚዎች ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ቢሮ ሊከፍት መኾኑን መስማቱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘግቧል። 'ብርጌድ ንሐመዱ' ወይም 'የሰማያዊ አብዮት ንቅናቄ' የተሰኘው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ስብስብ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ማካሄዱ ይታወሳል። በዚኹ ስብሰባ ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወከሉ የንቅናቄው አባላት እንደተሳተፉ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። ንቅናቄው በውጭ አገር የተመሠረተው ከኹለት ዓመት በፊት ሲኾን፣ በተለያዩ የምዕራቡ ዓለም አገራት የኤርትራ ኢምባሲዎችና የመንግሥት ደጋፊዎች ያካሄዷቸውን የባሕል ፌስቲቫሎች በማወክና በማስተጓጎል ይታወቃል።
3፤ ኤርትራ፣ በኅዳር ወር ያገተቻቸውን ሦስት የአዘርባጃን አሳ አጥማጅ ጀልባዎችንና የአዘርባጃን ዜጎች የኾኑትን ሠራተኞች ለመልቀቅ ዝግጅት እያደረገች መኾኗን ባለሥልጣናቷ እንደገለጡ የአዘርባጃን የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኤርትራ ባለሥልጣናት ጀልባዎቹን ለሦስት ወራት ያህል ያገቱት፣ እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም ሰፊ ምርመራ ለማድረግ የአገሪቱ ሕግ ስለሚፈቅድ እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በሦስቱ ጀልባዎች ውስጥ ታግተው የሚገኙት 18 የአዘርባጃን ዜጎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። ጀልባዎቹ ቀይ ባሕር ላይ የታገቱት፣ በአየር ጸባይ ለውጣ ሳቢያ አቅጣጫ ቀይረው ወደ ኤርትራ የባሕር ግዛት በገቡበት ወቅት ነበር።
4፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ በተለያዩ አገራት የሚሠጣቸውን ዕርዳታዎች እንዲያቆም ትዕዛዝ እንደደረሰው ሮይተርስ ዘግቧል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርክ ሩቢዮ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያስተላለፉት የ90 ቀናት የዕርዳታ እገዳ ትዕዛዝ አሜሪካ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በኩል በምትሠጣቸው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታዎችና የነፍስ አድን ዕርዳታዎች ላይ እንዳይተገበር መመሪያ አስተላልፈው ነበር። ኾኖም ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የደረሰው የእገዳ ትዕዛዝ 507 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የምግብ አቅርቦትን እንደሚያስተጓጉል ድርጅቱ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ከዚህ ምግብ ውስጥ አብዛኛው በ23 አገራት መጋዘኖች እንደሚገኝና ከፊሉ ወደተለያዩ አገራት በመጓጓዝ ላይ መኾኑን ጠቅሶ ማብራሪያ እንደጠየቀም ዘገባው አመልክቷል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛው የአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ፣ የካቲት 1/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኢትዮጵያ የኹለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዛሬ ከገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ ከብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱና ከፕላንና ልማት ሚንስትር ፍጹም አሠፋ ጋር በኦአገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር አተገባበር ዙሪያ ተወያይተዋል። ጆርጄዬቫ፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል እና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትንም ጎብኝተዋል። ጆርጂዬቫ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ጭምር እንደሚነጋገሩ፣ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩም ገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል። ጆርጂዬቫ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፣ ድርጅቱ ባለፈው ሐምሌ ለኢትዮጵያ ባጸደቀው የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ዙሪያ ኹለተኛውን ዙር ግምገማ በማጽደቅ ከብድሩ ውስጥ 248 ሚሊዮን ዶላር በለቀቀ ማግስት ነው።
2፤ እናት ፓርቲ፣ መኢአድና ኢሕአፓ፣ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ራሱን "የስኬት ማማ" ላይ እንዳለ አድርጎ በመንግሥታዊ መገናኛ ብዙኀን አስነግሯል በማለት ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተችተዋል። ገዥው ፓርቲ "አገራዊ ምስቅልቅሎሽ" ያመጣና "የሕዝብን አደራና ተስፋ ያስጨነገፈ" ፓርቲ ነው በማለት የወቀሱት ፓርቲዎቹ፣ ፓርቲው ራሱን በጥልቀት ገምግሞ በጋራ አገርን ለማዳን እንዲሠራ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል። ፓርቲው ጦር መሣሪያ ካነሱ ከኹሉም ሃይሎች ጋር በአፋጣኝ ሠላማዊ ድርድር እንዲጀመርም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ፣ ገዥው ፓርቲ የሚመራው መንግሥት በአገሪቱ በሰላምና ጸጥታ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማኅበራዊ መስኮች ላይ ፈጥሮታል ያሉትን ምስቅልቅል በመግለጫቸው ዘርዝረዋል።
3፤ ካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች፣ ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር የተቃረበው የሱዳን ጦር ሠራዊት "የበቀል ጥቃት" ይፈጽምብናል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ሪፖርተር ዘግቧል። በከተማዋ የሚኖሩ 70 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስጋት ያደረባቸው፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ከተማዋን ሲቆጣጠር እዚያው በመቆየታቸው እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኢትዮጵያዊያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ እንዲረዳቸው ተማጽኖ ማቅረባቸውንም ዘገባው ጠቅሷል። ጦር ሠራዊቱ በቅርቡ የአልጀዚራ ግዛትን መልሶ ሲቆጣጠር፣ በግዛቲቷ የሚኖሩ በርካታ ደቡብ ሱዳናዊያን ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል ድጋፍ አድርገዋል በሚል ጥርጣሬ በበቀል ስሜት እንደተገደሉ አይዘነጋም።
4፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ የሚካሄዱ ወርቅና መዳብን ጨምሮ ማናቸውም የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ከየካቲት 1 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን መመሪያ ያስተላለፈው፣ የክልሉ የማዕድን ሃብት በሕገወጥ መረቦች አማካኝነት እየተመዘበረ መኾኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በክልሉ የሚካሄደዱ መጠነ ሰፊ ሕገወጥ የማዕድን ቁፋሮዎችን የሚመረምር ግብረ ኃይል ማቋቋሙንም ቀደም ሲል ገልጦ ነበር። በሕገወጥ የማዕድን ቁፋሮው የታጠቁ ቡድኖች በዋናነት እንደሚሳተፉና በተለይ የወርቅ የኮንትሮባንድ ንግድ መረብ እስከ አዲስ አበባ፣ አሥመራ፣ ካምፓላና ዱባይ ድረስ የተዘረጋ ስለመኾኑ በተደጋጋሚ እንደተዘገበ አይዘነጋም።
5፤ አሜሪካ በዓለም ዙሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የምትሠጠው ድጋፍ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት እንደገና ካልቀጠለና ሌሎች ድጋፎች ካልተገኙ፣ በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ400 ፐርሰንት እንደሚጨምርና 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሞቱ የተመድ የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት (ዩ ኤን ኤድስ) ትናንት አስጠንቅቋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ እንዲቆም ካዘዙ በኋላ፣ እገዳው የኤች አይ ቪ በሽታን ጨምሮ ለነፍስ አድን የሚውሉ ድጋፎችን እንደማይመለከት መመርያ ተላልፎ ነበር። ኾኖም ይህ መመሪያ ኤች አይ ቪ ኤድስን በማኅበረሰብ ደረጃ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ላይ እንዴት እንደሚተገበር አኹንም ብዥታ እንዳለ ድርጅቱ አስታውቋል። የፕሬዝዳንቱ ትዕዛዝ ነፍስ አድንን አመለከትም ቢባልም፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት በአሜሪካ ድጋፍ በኤች አይ ቪና ሌሎች የነፍስ አድን ሥራዎች ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ሥራቸውን እንዳቆሙ ናቸው።
6፤ የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለደቡብ አፍሪካ የምትሠጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለማቋረጥ ያቀረቡት ምክንያት "በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ" እና "ደቡብ አፍሪካ ለዘመናት ላለፈችበት የቅኝ ግዛትና የአፓርታይድ ታሪክ እውቅና ያልሠጠ" ነው በማለት ተችቷል። ሚንስቴሩ ይህን ያለው፣ ፕሬዝዳንቱ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የነጮችን መሬት ያለ ካሳ በመውረስ ላይ ነው በማለት የገንዘብ ድጋፍ ማቋረጣቸውንና ከአገራቸው መውጣት ለሚፈልጉ ነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ጥገኝነት እንደሚሠጡ መግለጣቸውን ተከትሎ ነው። በደቡብ አፍሪካ ላይ "የሐሰተኛ መረጃና ፕሮፓጋንዳ በተቀናጀ መንገድ የተከፈተ ይመስላል" ያለው ሚንስቴሩ፣ ይሄ ትርክት በአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ተቀባይነት ማግኘቱ አሳዛኝ ነው ብሏል። የበርካታ አገራት ጥገኝነት ጠያቂዎች ከአሜሪካ እየተባረሩ ባሉበት ወቅት፣ "አሜሪካ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላላቸው ደቡብ አፍሪካዊያን የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥገኝነት እሠጣለኹ ማለቷም ምጸታዊ ነው" በማለት ሚንስቴሩ ተችቷል። አገሪቱ ከአሜሪካ የምታገኘው ብቸኛው ድጋፍ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከመደበችው በጀት 17 በመቶውን ብቻ ነው።
7፤ አንድ የአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ 2 ሺሕ 200 የአሜሪካ ዓለማቀፍ የተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ሠራተኞች ሥራ እንዲያቆሙ ያስተላለፉት ትዕዛዝ እስከ የካቲት 7 ተፈጻሚ እንዳይኾን አግዷል። ፍርድ ቤቱ እግዱን ያስተላለፈው፣ ኹለት የአሜሪካ የሠራተኛ ማኅበራት ፕሬዝዳንቱ ሕገመንግሥቱን እየጣሱና የድርጅቱ ሠራተኞች በፕሬዝዳንቱ ትዕዛዝ ሳቢያ ለጉዳት እየተጋለጡ መኾኑን በመጥቀስ ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል ነው። ፍርድ ቤቱ ደመወዛቸው እየተከፈላቸው በግዳጅ ዕረፍት እንዲወጡ የተደረጉ 500 የድርጅቱ ሠራተኞችም ለጊዜው ወደ ሥራ እንዲመለሱ አዟል። ፍርድ ቤቱ፣ የድርጅቱ ሠራተኞች በግዳጅ ዕረፍት እንዲወጡ የተላለፈው ትዕዛዝ ለረጅም ጊዜ ታግዶ እንዲቆይ የቀረበለትን አቤቱታም በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ይሰማል። የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ድርጅቱን ሙሉ ለሙሉ የማፍረስ ዕቅድ እንዳለው ይነገራል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ፣ የካቲት 3/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ ኢትዮጵያ በቡድን-20 ማዕቀፍ ሥር ከአበዳሪዎቿ ጋር የምታደርገው የዕዳ ሽግሽግ የመጨረሻው ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተናግረዋል። ትናንት ከሚንስትሩ ጋር መግለጫ የሠጡት የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጄዬቫም፣ አገሪቱ የብድር ሽግሽግ እንዲደረግላት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ ጠቁመዋል። አገሪቱ እስካለፈው የሰኔ ወር መጨረሻ የነበረባት የውጭ ዕዳ 28 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ እንደነበርና ከብድሩ ውስጥ ግማሹ አይ ኤም ኤፍ፣ ዓለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ የመሳሰሉ የባለብዙ ወገን አበዳሪዎች ያበደሩት ዕዳ መኾኑን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል። ፈታኝ ሲሉ የጠሩት የአገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃግብር አስደናቂ ውጤቶችን እንደሚያመጣ የገለጡት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ኢትዮጵያዊያን ውጤቱን በትዕግሥት እንዲጠብቁም አሳስበዋል። ጆርጄዬቫ፣ በጉብኝታቸው ወቅት የአገሪቱ የግል ዘርፍ መር የኾነ የገበያ ኢኮኖሚ መመልከታቸውንም ጠቁመዋል። መንግሥት በቅርቡ የወሰዳቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የኢንቨስትመንት ኹኔታውን አሻሽለውታል ያሉ ሲኾን፣ መንግሥትም የሚተነበይ የታክስና የቁጥጥር ሥርዓት መከተሉን እንዲቀጥል መክረዋል።
2፤ በግዢ ሂደት ላይ ከሚገኙ 6 የጭነት መርከቦች መካከል ኹለቱ በተያዘው ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ለዋዜማ ተናግሯል። አዳዲሶቹ መረከቦች ኮንቴነሮችንና ብትን ጭነቶችን ጨምሮ ለኹሉን የጭነት ዓይነቶች አገልግሎት የሚሰጡ እንደኾኑና የመጫን አቅማቸውም ከ63 ሺሕ ቶን በላይ እንደኾነ አገልግሎቱ ገልጧል። ኢትዮጵያ ባኹኑ ወቅት 10 የጭነት መርከቦች ያሏት ሲኾን፣ "ዓባይ ኹለት” የተሰኘችው ትልቋ መርከብ ከ63 ሺሕ ቶን በላይ ጭነት የመሸከም አቅም እንዳላትና ሌሎቹ ግን ከፍተኛው የጭነት አቅማቸው 27 ሺሕ ቶን እንደኾነ የአገልግሎቱ የኮምኒኬሽን መምሪያ ለዋዜማ ተናግሯል። አስሩ መርከቦች ከጠቅላላው የአገሪቱ ገቢና የወጭ ንግድ ውስጥ ማጓጓዝ የሚችሉት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚደርሰውን ጭነት ብቻ ሲኾን፣ ቀሪው ጭነት የሚጓጓዘው በኪራይ መርከቦች አማካኝነት ነው።
3፤ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ "ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጋር ትስስር አላችሁ" በሚል የሃሰት ክስ ግለሰቦችን በመወንጀልና በማሠር በተጠረጠሩ አንድ የወረዳ ፖሊስ አዛዥ ላይ የ14 ዓመት ጽኑ እስራትና የ10 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ መበየኑን የዞኑ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ያስተላለፈባቸው የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኮማንደር ብርሃኑ ሌንጮ ሲኾኑ፣ በሃሰት ወንጅለው ካሳሰሯቸው ግለሰቦች ላይ ከእያንዳንቸው ከ20 እስከ 100 ሺሕ ብር ጉቦ በመቀበል ከእስር ሲለቋቸው እንደነበርም የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ጠቁሟል። ፍርድ ቤቱ ከፖሊስ አዛዡ ጋር በመመሳጠር ይህን ጉዳይ ሲያስፈጽምና ገንዘቡን ሲያቀባብል በነበረው ጋዲሳ ቶለሳ የተባለ አንድ ግለሰብ ለይም፣ የ2 ዓመት እስራትና የ10 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ እንደበየነበት ዋዜማ ከዞኑ ፖሊስ መመሪያ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
4፤ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የስነ ምግባር ረቂቅ አዋጅ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፓርቲ አባልነት መዋጮ ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እንዳይቆርጡ እንደሚከለክል ቢቢሲ ዘግቧል። እስካሁን ባለው አሠራር፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የገዥው ፓርቲ አባላት ከኾኑ ሠራተኞች ደመወዝ ላይ የፓርቲ አባልነት መዋጮ እንደሚቆርጡ ይታወቃል። የጾታ ተዋጽዖን በተመለከተም፣ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ቢያንስ 30 በመቶ አመራሮች ሴቶች እንደሚኾኑ የሚገልጽ ድንጋጌ በፓርቲዎች መተዳደሪያ ደንብ ላይ መካተት እንዳለበትም ረቂቅ አዋጁ ያስገድዳል ተብሏል። በነባሩ አዋጅ ላይ ለፓርቲ ኃላፊነት የሚደረጉ ምርጫዎች የጾታ ተዋጽዖን ያገናዘቡ እንዲኾኑ ብቻ ነው በደምሳሳው የተደነገገው። ፓርቲዎች ለምርጫ ከሚያቀርቧቸው ዕጩዎች መካከልም 20 በመቶዎቹ ሴቶች እንዲኾኑ ረቂቅ አዋጁ እንደደነገገ የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።
5፤ የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን፣ ለኹለተኛው የውጭ የቴሌኮም ኩባንያ ከ2018 ዓ፣ም አጋማሽ በፊት ወይም ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ጥቂት ወራት የአገልግሎት ፍቃድ ሊሠጥ እንደሚችል መናገሩን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። ባለሥልጣኑ ተጨማሪ የቴሌኮም ፍቃድ ከመስጠቱ በፊት፣ የቴሌኮም ገበያውን ኹኔታና ብቃት ያላቸውን ዓለማቀፍ ኩባንያዎች ለመሳብ የሚያስችሉ ኹኔታዎችን እያጠና እና ለገበያው የዘረጋውን የቁጥጥር ሥርዓት እየገመገመ መኾኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ባለሥልጣኑ ኹለተኛውን የውጭ የቴሌኮም ኩባንያ ፍቃድ ለመስጠት ካኹን ቀደም ዓለማቀፍ ጨረታ አውጥቶ እንደነበር አይዘነጋም። ኾኖም ዓለማቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ባለማሳየታቸው፣ ባለሥልጣኑ ባለፈው ዓመት ኅዳር ገደማ ጨረታውን ለማቋረጥ እንደተገደደ ይታወሳል።
6፤ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ "የትኛውንም መስዋዕትነት ያስከፍለን ይኾናል እንጂ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ገበርን ያገኘነውን ድል ለማንም አሳልፈን አንሰጥም" ሲሉ ትላንት ለክልሉ ምክር ቤት ባደረጉት ገልጻ ላይ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት አንዱ ተልዕኮ ሥርዓቱን መጠበቅና የተገኘውን ድል ማስቀጠል ነው ያሉት ሽመልስ፣ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በደሎችን ሲፈጽሙ የነበሩ አካላት ተመልሰው ሊመጡ የሚችሉበትና በኦሮሞ ሕዝብ ዕጣ ፈንታ የመወሰን ዕድል ሊኖራቸው የሚችልበት ዕድል አክትሟል በማለትም ተናግረዋል። ሽመልስ "ጠላት" ያሉትን አካል በስም ባይጠቅሱም፣ የኦሮሞ ሕዝብ "ጨቋኝ" እና "ጠላት" የተባለውን ሥርዓት ለመገርሰስ ከከፈለው ዋጋ በላይ አኹን ያገኘውን ድል ለመጠበቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል በማለትም አክለዋል።
7፤ የአሜሪካ መንግሥት፣ የወባ በሽታን ለመከላከል፣ የጨቅላ ሕጻናትንና የእናቶችን ሞት ለመቀነስና በምግብ ዕጥረት የሚደርሱ ከባድ ጉዳቶችን ለመከላከል ሲያደርጋቸው የነበሩ ድጋፎች እንዲቀጥሉ መወሰኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ወባን ጨምሮ የሕይወት አድን ተደርገው በሚቆጠሩ ዕርዳታዎች መቋረጥ ሳቢያ ሰዎች እንዳይሞቱ ለመከላከል፣ ዕርዳታዎቹ በ30 ቀናት ውስጥ እንደገና እንዲጀምሩ እንደተወሰነ ከአንድ የመንግሥት ማስታዎሻ ላይ መመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) እንደገና እንዲቀጥላቸው ከተፈቀዱለት የዕርዳታ ዓይነቶች መካከል የሳንባ ነቀርሳ ወይም ቲቢ እና ሌሎች ሞት የሚያስከትሉ በሽታዎችና የጤና እክሎች እንደሚገኙበትም ዘገባው አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ ኤምፖክስ፣ አቪያን ፍሉ እና ኢቦላን የመሳሰሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር አሜሪካ የምትሠጣቸው ዕርዳታዎችም እንዲቀጥሉ ታዟል ተብሏል። ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የወባ በሽታን ለመከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም የሕጻናትንና እናቶችን ሞት ለመቀነስ ከፍተኛ ዕርዳታ ሲያደርግ እንደቆየ ይታወቃል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ፣ የካቲት 4/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን፣ ሰበ ቦሩ ወረዳ የሚገኘው የቀንጢቻ ሊቲዬም ማዕድን 40 ሠራተኞች ለስድስት ወራት ደሞዝ አልተከፈለንም ሲሉ በቀንጢቻ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ላይ በፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸውን ዋዜማ ከፍርድ ቤቱ ሰነዶች ላይ ተመልክታለች። ሠራተኞቹ፣ የኩባንያው ሃላፊዎች ስለ ቀንጢቻ ኹኔታና ዕጣፈንታ ምንም ዓይነት መረጃና አቅጣጫ ሳይሰጡ ጠፍተዋል በማለት ከሰዋል። የሠራተኞቹ ጠበቆች፣ ኩባንያው ሕጋዊ የማዕድን ማውጣት ፍቃድ ስለመያዙ እንዲረጋገጥላቸው ጭምር ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ ኩባንያው ሊቲየምና ታንታለም ለማውጣት ፍቃድ ያገኘው የብቃት መስፈርቶችን ሳያሟላ እንደኾነ ገልጦ፣ በምን አግባብ ፍቃዱን እንዳገኘ ምርመራ እያደረገ መኾኑን ቀደም ሲል መግለጡ ይታወሳል።
2፤ ሳልሳዊ ወያነ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተግባራዊ እንዲኾን ትኩረት ባለመስጠቱ የሚሊዮኖች ሕይወት አደጋ ላይ ወድቋል በማለት አዲስ ባወጣው መግለጫ ወቅሷል። ፓርቲው፣ ፌደራል መንግሥቱና ሕወሓት በርስበርስ ፕሮፓጋንዳ ተጠምደው፣ የሕዝቡን ሰቆቃ ረስተውታል በማለትም ከሷል። ስደተኞችና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ የሚያደርጉ ኹኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ ሂደዋል ያለው ፓርቲው፣ በትግራይ ክልል ለብሄር ማጽዳት ተጠያቂ የኾኑ አካላትን የማሠልጠንና የማስታጠቅ እንቅስቃሴዎችም ቀጥለዋል በማለት ከሷል። የግጭት ማቆም ስምምነቱ ፈራሚዎችና ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ ዙሪያ ዝምታቸውን እንዲሠብሩም ፓርቲው ጠይቋል።
3፤ ተቀዋሚው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው፣ ትናንት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳገደባቸው አስታውቀዋል። ልደቱ ጉዟቸው የታገደው፣ የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የኢትዮጵያ ፓስፖርትና የተረጋገጠ የጉዞ ቲኬት ይዘው ከገቡ በኋላ እንደኾነ በመግለጽ አየር መንገዱን ከሰዋል። አትላንታ የሚገኘው የአየር መንገዱ ቢሮ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመብረር በመጀመሪያ አሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተለየ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው እንደገለጠላቸው ልደቱ ጠቅሰዋል።
የአገሩን የጉዞ ሰነድ የያዘ ዜጋ ወደ አገሩ እንዳይገባ ለመከልከል የሕግ ማዕቀፍ የለም ያሉት ልደቱ፣ በሌላ አየር መንገድ ወደ አገራቸው ለመመለስ መወሰናቸውን ጠቅሰዋል። መንግሥት፣ ልደቱን በመንግሥት ግልበጣ ሴራና በአሸባሪነት እንደጠረጠራቸው ካኹን ቀደም መግለጡ ይታወሳል።
4፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሴት ተራራ ላይ በሚገኘው ጫካና ባካባቢው መንደሮች ላይ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰደድ እሳት ለቀውበታል በማለት ትናንት ምሽት ባሠራጨው መግለጫ ከሷል። ቡድኑ፣ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት ሙከራ ባደረጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብሏል። የመንግሥት ኃይሎች በጫካው ላይ ኾነ ብለው ሰደድ እሳት የለቀቁት ተዋጊዎቹን ለማጥቃት እንደኾነ የገለጠው ቡድኑ፣ የመንግሥት ኃይሎች በቄለም ወለጋ ዞን በተመሳሳይ ጫካዎችንና መንደሮችን በእሳት አያይዘዋል በማለት ወቅሷል።
5፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለጥገና በቆመ አንድ አውሮፕላኑ ላይ አንዲት ግለሰብ ሰሞኑን በምን ኹኔታ የልደት ስነ ሥርዓቷን ልታካሂድበት እንደቻለች ምርመራ እያደረገ መኾኑን ትናንት ማምሻውን ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። አየር መንገዱ፣ ግለሰቧ ድርጊቱን የፈጸመችው ከአመራሮቹ ፍቃድ ውጭ መኾኑን ገልጧል። ክስተቱ የሚፈጥረው ችግር ወይም አሉታዊ ግንዛቤ እንዳሳዘነው የጠቀሰው አየር መንገዱ፣ ያለ ፍቃድ ይህንኑ ዝግጅት ባዘጋጁ አካላት ላይ የእርምት ርምጃ እንደሚወስድ ገልጧል። ለልደት በዓል ዝግጅቱ ከግለሰቧ ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳልጠየቀና የውል ስምምነትም እንደሌለው ኩባንያው አስታውቋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ፣ የካቲት 5/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሕገወጥ ገቢና ወጪ እቃዎችን በተመለከተ መረጃ ለሚሰጡ አካላት ወሮታ መክፈል የሚያስችለውን "ሕገወጥ ዕቃዎችን የሚመለከት መረጃ አሰጣጥ፣ አመዘጋገብ፣ አያያዝና የወሮታ ክፍያን ለመወሰን" በሚል ርዕስ አዲስ መመሪያ ማዘጋጀቱን ዋዜማ ተረድታለች። የኮንትሮባንድ፣ የንግድ ማጭበርበር፣ የከበሩ ማዕድናትና የሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መበራከታቸውና መወሳሰባቸው በመንግሥት ገቢ ላይ አደጋ ማስከተሉ፣ ለመመሪያው መውጣት መነሻ መኾኑን ሚንስቴሩ ጠቅሷል። በጠቋሚ መረጃ የተያዘ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተወርሶ በሚሸጥበት ጊዜ፣ ለጠቋሚ 25 በመቶና ለዕቃው ያዥ ሕግ አስከባሪ አካላት 20 በመቶ እንደሚከፈል መመሪያው ያዛል። ሕገወጡን ዕቃ የያዙት ሚሊሺያዎች ወይም ብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኾነ 10 በመቶ የወሮታ ክፍያ እንደሚፈጸምላቸው በመመሪያው ላይ ተደንግጓል።
2፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ ትናንት መቀሌን የጎበኙ የምዕራብ አገራት አምባሳደሮች የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ፈራሚዎችና አስማሚ አካላት ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው የመመለሱን ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጡት መጠየቃቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል የተቻላቸውን ኹሉ ጥረት ለማድረግ ቃል እንደገቡም ጌታቸው ገልጸዋል። በትግራይ የተፈጠረው ውስጣዊ ፖለቲካዊ ችግር፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፌደራል መንግሥቱና ሌሎች ባለድርሻዎች ተፈናቃዮችን በጊዜ ወደቀያቸው አለመመለሳቸው የፈጠረው እንደኾነ ከአምባሳደሮቹ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ መግባባት ላይ እንደተደረሰበትም ጌታቸው ጠቅሰዋል። አምባሳደሮቹ፣ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች የሥልጣን ሽኩቻቸውን ወደ ጎን ብለው፣ ተፈናቃዮችን በመመለስ ላይ እንዲያተኩሩም አሳስበዋል ተብሏል።
3፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ሕወሓት በእንዳሥላሴ ከተማ በሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያዎች በግዳጅ መዋጮ እየሰበሰበ መኾኑን በመግለጽ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ቅሬታ አቅርቧል። የሕወሓት ባለሥልጣናት ከተፈናቃዮች በነፍስ ወከፍ 200 ብር በግዳጅ የሚሰበስቡት፣ ፓርቲውን ለማዳንና ለፓርቲው 50ኛ ዓመት በዓል ማክበሪያ በሚል ምክንያት እንደኾነ ተገልጧል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕወሓት አስገዳጅ መዋጮ መጣል እንደማይችል ገልጦ፣ የአካባቢው መንግሥታዊ አካላት ድርጊቱን እንዲከታተሉ አሳስቧል። ሕወሓት በግዳጅ መዋጮ መሰብሰቡን አስተባብሎ፣ ኾኖም ማንም ሰው ለፓርቲው በፍላጎቱ መዋጮ ማዋጣት ይችላል በማለት ምላሽ ሰጥቷል።
4፤ ኢትዮ ቴሌኮም፣ በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ መሙያ ጣቢያን ገንብቶ ሥራ አስጀምሯል። ዘመናዊው የመኪና ኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ በአንድ ሰኮንድ ውስጥ አንድ ኪሎ ሜትር ለመጓዝና በአማካይ በ15 ደቂቃ ውስጥ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ለማድረግ እንደሚያስችል ኩባንያው ገልጧል።
የመሙያ ጣቢያው እስከ 600 ኪሎ ዋት ድረስ ባትሪ የመሙላት አቅም ያላቸው ስምንት በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎችን፣ እስከ 500 ኪሎ ዋት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያላቸው 12 ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎችን እና የድንገተኛ ባትሪ መሙያ ስማርት ምሰሶ ቻርጀሮችን በተለያየ ቦታ ያካተተ እንደሆነም ኩባንያው ጠቅሷል፡፡
5፤ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን አብዱላሂ፣ አሜሪካ ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠቷ የማይቀር እንደኾነ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ አሜሪካ ለሶማሌላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ትኾናለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ይህን ፍንጭ የሠጡት ትናንት ዱባይ ውስጥ በተካሄደ የዓለም መንግሥታት ውይይት ላይ ነው። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሶማሌላንድ እውቅና ሊሠጥ እንደሚችል አንዳንድ ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ሲዘግቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ፣ እስካሁን ወደ አሜሪካ አላቀኑም። [ዋዜማ]

#NewsAlert
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሱሉልታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ የሆኑት አበበ ወርቁ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።
ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ መሆኑን የገለጹት የዋዜማ ምንጮች፣ ከወረዳ አሥተዳዳሪው ጋር የነበረ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በቡድኑ ታፍኖ መወሰዱን አስረድተዋል።
ዋና አሥተዳዳሪው፣ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው እና በርካታ የጸጥታ ኃይሎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀስበታል ወደተባለው "ሞዬ ጋጆ" በተባለው ስፍራ ሲደርሱ አማጺ ቡድኑ ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ እንደከፈተባቸው ተጠቁሟል።
በዚህም ዋዜማ ለጊዜው ቁጥራቸውን ማጣራት ያልቻለችው የጸጥታ ኃይሎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
ከጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው በተጨማሪ በርካታ የጸጥታ ኃይሎች በቡድኑ ታፍነው መወሰዳቸውንም ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት መረዳት ችላለች።
ከወራት በፊትም በተመሳሳይ በዚሁ ታጣቂ ቡድን ጥቃት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ለገሰ ሥዩም መገደላቸውን ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል።
ሟቹ አበበ ከሁለት ዓመት በፊት የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እንደነበሩ ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመለክታል። [ዋዜማ]