ለቸኮለ! ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኢትዮጵያ፣ በግጭቶችና ጦርነት ከደረሰው ጉዳት መልሶ ለማገገም 44 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከሌሎች የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው አዲስ ጥናት ማመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል። አገሪቱ በግጭቶችና ጦርነቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከአጠቃላይ ምርቷ 7 ነጥብ 5 በመቶ የሚኾነውን እንዳጣች ጥናቱ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቅሷል። ኢትዮጵያ ጦርነትና ግጭቶች ካደረሱባት ጉዳት ለማገገም፣ የሰሜኑ ጦርነት ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመታት ሊወስድባት እንደሚችልም ጥናቱ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ገንዘብ ሚንስቴር ባለፈው ዓመት ባካሄደው ጥናት፣ ለመልሶ ግንባታ 29 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስታውቆ ነበር። አዲሱ ጥናት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ባለፉት ኹለት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች የደረሱ ጉዳቶችን አያክትትም ተብሏል።
2፤ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ በአገር ዓቀፍ ደረጃ ኹሉም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበትን የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በተገኙበት በአዲስ አበባ አስጀምሯል። የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና ሕግ ተርጓሚ አካላት፣ የተለያዩ ማኅበራት ተወካዮች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል። ኮሚሽኑ ትናንት በአዲስ አበባ የአጀንዳ ማሰብሰብ ሥራ ማካሄዱ ይታወሳል። ኮሚሽኑ እስካኹን አጀንዳ በማሰባሰብ የምክክር ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን ያስመረጠው፣ በ10 ክልሎችና በኹለቱ የከተማ አስተዳደሮች ነው። በአማራና ትግራይ ክልሎች ግን ገና የተሳታፊዎች ልየታ እና መረጣ ሂደቶችን አልጀመረም።
3፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ፣ በትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የክልሉ ቴሌቪዥን ዛሬ ዘግቧል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በክልሉ የጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት፣ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም እንዲኹም ከሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የስልክ ጥሪዎችን እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን ማድረግ እንደሚያስችል ዘገባው አመልክቷል። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት፣ ኩባንያው የአራተኛው ትውልድ የቴሌኮም ኔትወርክ አገልግሎቶችን በክልሉ 16 ከተሞች እንደሚዘረጋ ተናግረዋል ተብሏል።
4፤ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ያልተካሄዱ ምርጫዎችን ለማካሄድ ለሰኔ 9 የያዘውን ቀጠሮ ባንድ ሳምንት በማራዘም ሰኔ 16 ለማካሄድ መወሰኑን አስታውቋል። ቦርዱ ምርጫውን ባንድ ሳምንት ያራዘመው፣ ቀኑ ከኃይማኖታዊ በዓል ጋር በመገጣጠሙ እንደኾነ ገልጧል። ቦርዱ ቀሪ ምርጫዎችን በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በአፋር ክልሎች የሚያካሂድ ሲኾን፣ ድጋሚ ምርጫ የሚያካሂደው ደሞ በሱማሌ ክልል በጅግጅጋ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች ነው።
5፤ የሱማሊያ መንግሥት፣ ከአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች መውጣት በኋላ በአገሪቱ የሚሠማራው አዲስ ኅብረ ብሄራዊ የሰላም ተልዕኮ 12 ሺህ ያህል ወታደሮችንና ፖሊሶችን እንደሚያካትት አስታውቋል። የፕሬዝዳንቱ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሑሴን ዓሊ፣ የአዲሱ ኅብረ ብሄራዊ ተልዕኮ ኃላፊነት አውሮፕላን ማረፊያውን፣ ቤተመንግሥቱንና የሞቃዲሾ ወደብን ጨምሮ 23 ቁልፍ ተቋማትን መጠበቅ እንደሚኾን ትናንት ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ወታደሮች በስተቀር፣ አብዛኞቹ በአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ሥር ተሳታፊ የኾኑ አገራት ወታደሮች በአዲሱ ተልዕኮ እንደሚካተቱ ዓሊ ጠቁመዋል። ዓሊ፣ የኅብረቱ ጦር በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ጠቅልሎ ሲወጣ፣ አልሸባብ አገሪቱን መልሶ ሊቆጣጠር ይችላል የሚለውን ስጋት ውድቅ አድርገውታል። ሱማሊያ አዲሱ ተልዕኮ እንዲሠማራላት ከተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ገና ፍቃድ አልጠየቀችም።
6፤ የደቡብ አፍሪካ ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግሬስ (ኤ ኤን ሲ) ባለፈው ረቡዕ በተካሄደው ምርጫ የፓርላማ አብላጫ መቀመጫውን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አጥቷል። ኤ ኤን ሲ 40 በመቶ ገደማ ድምጽ ያገኘ ሲኾን፣ የነጮች ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ጥምረት ደሞ 21 በመቶ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በቅርቡ ያቋቋሙት ፓርቲ 14 በመቶ እንዲኹም የኢኮኖሚ ነጻነት ተፋላሚዎች ፓርቲ 9 በመቶ ገደማ ድምጽ አግኝተዋል። በውጤቱ መሠረት፣ ኤ ኤን ሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግሥት ይመሠርታል ተብሎ ይጠበቃል። [ዋዜማ]

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አንቶኒ ብሊንከን ቅዳሜ ዕለት የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድን በስልክ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል እየተካረረ ያለው ውዝግብ መርገብ እንዳለበት አሜሪካ ፍላጎቷ መሆኑን ገልፀዋል። የውይይቱን ዝርዝር መረጃ ያንብቡት- https://tinyurl.com/mrxmmfum
ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ግንቦት 26/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በደቡብ ኮሪያና አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትናንት ሴዑል ገብተዋል። ትናንት በኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ልዑካን ቡድኖች መካከል በተደረገ ውይይት፣ ኢትዮጵያ በአራት ዓመታት ውስጥ ለምትተገብራቸው ፕሮጀክቶች ደቡብ ኮሪያ የ1 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ የምትሰጥበት ስምምነት እንደተፈረመ የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ አስታውቋል። በገንዘብ ድጋፉ የሚተገበሩት ፕሮጀክቶች ዓይነት ግን አልተገለጠም። ማክሰኞ የሚጀመረው የደቡብ ኮሪያና አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ዓላማ፣ በጋራ እድገትና አጋርነት ዙሪያ መወያየት ነው። በጉባዔው ላይ፣ የኤርትራና ኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጭምር ይሳተፋሉ።
2፤ ከኃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ፣ ማንኛውም የኃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚያገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል እንዲያሳውቅ የሚያዘው ድንጋጌ ከተሻሻለው ረቂቅ መውጣቱን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ በአዋጁ ላይ ስጋት ያላቸው የኃይማኖት ተቋማት ጉዳዩን የሚመለከት ቡድን እንዳቋቋሙ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የኃይማኖት መሪዎች፣ ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የኹሉንም ኃይማኖቶች መብት መጠበቁ እንዲረጋገጥ መጠየቃቸውንና በኃይማኖት ነጻነት ላይ ገደብ እንዳይጣል ሥጋት እንዳላቸው መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። የሙስሊም መሪዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች መስገድ እንደማይፈቀድ ረቂቅ አዋጁ መከልከሉን ተችተዋል ተብሏል። የወንጌል አማኞች ካውንስል በበኩሉ፣ ረቂቅ አዋጁ በኃይማኖታችን ላይ ያነጣጠረ ነው የሚል ቅሬታ እንዳለው ተገልጧል።
3፤ ከኢዜማ የለቀቁት የቀድሞው የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋስ አሠፋ ባለፈው ሳምንት ዓርብ እንደታሠሩ ቪኦኤ ዘግቧል። የሺዋስን ይዘዋቸው የሄዱት፣ የአዲስ አበባ ከተማ የደኅንነት አባላት መኾናቸውን የገለጡ ሲቪል የለበሱ ሰዎች እንደኾኑ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። የሺዋስ የተወሰዱት ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ነው ተብሏል። ትናንት ደሞ ፖሊሶች የየሺዋስን መኖሪያ ቤት እንደፈተሹና ለምርመራ ይፈለጋሉ ያሏቸውን ቁሳቁሶች ሰነዶች እንደወሰዱ ዜና ምንጩ አመልክቷል። የሺዋስ ባለፈው ኅዳር ጦርነት እንዲቆም ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ከተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
4፤ አዲሷ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት መለሠ፣ ኃላፊነቱን በተረከቡ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ሦስት ምክትሎቻቸውን ጨምሮ 10 የባንኩን ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሃላፊነት እንዳነሱ ፎርቹን አስነብቧል። አዲሱ የባንኩ አመራር፣ የባንኩን የቦነስ ክፍያዎችና ብድሮች አሰጣጥና ባንኩ ከውጭ አካላት ጋር የገባቸውን ኮንትራቶች እየፈተሸ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። ባንኩ ለደንበኞቹ የሚሰጠው ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞት የቆየ ሲኾን፣ ችግሩን ለመፍታት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ከብሄራዊ ባንክ እንደተበደረ ዘገባው ጠቅሷል። ባንኩ በተለይ ለግንባታው ዘርፍ ያበደረው ከፍተኛ ብድር በባንኩ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ተብሏል።
5፤ የኢትዮጵያ አጎራባች የኾነችው የሱማሊያዋ ሳውዝ ዌስት የፌደራል ግዛት፣ የሱማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ በኋላ በሱማሊያ ይሠማራል ተብሎ በሚጠበቀው ኅብረ ብሄራዊ ተልዕኮ እንዳይካተቱ መወሰኑን ውድቅ እንዳደረገች የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የግዛቲቷ አስተዳደር፣ ውሳኔው "ጊዜውን ያልጠበቀ" እና "አድሏዊ" ነው በማለት መቃወሙን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በተለይ በሳውዝ ዌስት ግዛት ከአልሸባብ ጋር በተደረጉ ውጊያዎች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በሱማሊያ ውሳኔ ዙሪያ በይፋ የሰጠው አስተያየት የለም።
6፤ የአሜሪካ ፍትህ ሚንስቴር፣ ኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ውስጥ ለደረሱት የቦይንግ ማክስ 8 የመንገደኞች አውሮፕላን አደጋዎች በቦይንግ ላይ ክስ ላይመሠርት እንደሚችል ባለሥልጣናቱ ለተጎጂ ቤተሰቦች እንደነገሩ ሮይተርስ ዘግቧል። ኩባንያው የወንጀል ክስ ላይቀርብበት እንደሚችል የተገለጠው፣ የፌደራል የወንጀል ክስ መመስረቻ ቀነ ገደብ የኾነው አምስት ዓመት በማለፉ እንደኾነ ባለሥልጣናቱ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ቦይንግ፣ የወንጀል ክስ እንዳይመሠረትበት በማክስ አውሮፕላኖቹ ሥሪት ላይ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ከሚንስቴሩ ጋር ከሦስት ዓመት በፊት ውል የገባ ቢኾንም፣ በቅርቡ በአንዳንድ አውሮፕላኖች ላይ በተከሰቱ ክስተቶች ሳቢያ ኩባንያው ስምምነቱን ጥሷል የሚል ውንጀላ ቀርቦበታል። ኩባንያው ስምምነቱን ጥሷል በመባሉ ላይ እስከ ሰኔ 6 ምላሽ እንዲሰጥ ቀነ ገደብ ተሰጥቶታል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች ኩባንያው የወንጀል ክስ እንዲመሠረትበት ሲወተውቱ መቆየታቸው አይዘነጋም። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ ግንቦት 26/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያና ሶማሊያ ውዝግብ እንዲረግብ አሜሪካ እንደምትፈልግ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ሐሰን መሐመድን ቅዳሜ'ለት በስልክ ባነጋገሩበት ወቅት አስታውቀዋል። ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በቀጣዩ ዓመት በግዛቷ እንደሚሠማራ በሚጠበቀው ኅብረብሄራዊ ተልዕኮ እንዳይካተት መወሰኗን አሜሪካ በበጎ እንዳልተመለከተችው ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። ብሊንከን፣ የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ መውጣቱም ኾነ የኹለቱ አገራት ውዝግብ መካረሩ ቀጠናውን ወደከፋ አለመረጋጋት ይወስደዋል የሚል ስጋት አላቸው። ብሊንከን፣ ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙበት የባሕር በር የመግባባቢያ ስምምነት ያለሞቃዲሾ ፍቃድ ተግባራዊ እንዳይኾን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ወይም ለማግባባት እንደምትሞክር በስልክ ውይይቱ ወቅት መናገራቸውን ዋዜማ ተረድታለች።
2፤ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አልብስ አደፍራሽ እንደተገደሉ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል። የወረዳው አስተዳደር ኮምንኬሽን ቢሮ በወረዳ አስተዳዳሪው ላይ ከትናንት ወዲያ ግድያውን የፈጸሙት፣ "ጽንፈኛ" ሲል የጠራቸው ኃይሎች እንደኾኑ ገልጧል። የወረዳው አስተዳደር፣ "ጽንፈኛ" ያላቸው ኃይሎች ግድያውን የፈጸሙት በምሽት ተሹልክልከው በመግባት ነው ብሏል። ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር፣ ኹለት የሸዋሮቢት ከተማ ጸጥታ ኃላፊዎች በተመሳሳይ ኹኔታ እንደተገደሉ አይዘነጋም።
3፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሚሳተፉበት የደቡብ ኮሪያ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ነገ ሴዑል ውስጥ ይጀመራል። ዐቢይ የመሩት ልዑካን ቡድን ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ትናንት ውይይት ካደረገ በኋላ፣ ደቡብ ኮሪያ ለመሠረተ ልማት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ጤና እና ከተማ ልማት የሚውል የ1 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ተስማምታለች። የደቡብ ኮሪያና አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ዓላማ፣ በጋራ እድገትና አጋርነት ዙሪያ የሚመክር ሲኾን፣ በጉባዔው ላይ የኤርትራና ኬንያ ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የ30 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ይሳተፋሉ።
4፤ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦራ ዞን መቱ ከተማ ዕሁድ'ለት ለኃይማኖታዊ መርሃ ግብር ለማካሄድ ወደ አደባባይ በወጡ የሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን አማኞች ላይ በፈጸሙት ድብደባ ከ20 በላይ በሚኾኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። የከተማዋ አስተዳደር በበኩሉ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ያካሄዱት የጎዳና ላይ የስብከት መርሃ ግብር ከአስተዳደሩ ቀድሞ ፍቃድ ያላገኘ እንደነበር መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ጸጥታ ኃይሎች ከሦስት ሰዓታት በኋላ ጣልቃ ገብተው መርሃግብሩን በማስቆም በርካታ ሰዎችን ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዱና ኾኖም ቀሪዎቹ አማኞች ፖሊስ ጣቢያ ሂደው የመርሃግብሩን ዓላማ በማስረዳት እንዳስለቀቋቸው የመርሃግብሩ አዘጋጆች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ ከንቲባ ግን፣ ጸጥታ ኃይሎች በቤተክርስቲያኗ አማኞች ላይ አደረሱት ስለተባለው ጉዳት መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል ተብሏል።
5፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ በአገራዊ የምክክር ሂደቱ በግጭቶች ተሳታፊ የኾኑ አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤታማ ሊኾን አይችልም ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የጋራ ምክር ቤቱ፣ ግጭቶች በሙሉ ቆመው ኹሉም አካላት ወደ ሰላማዊ ንግግር እንዲመጡ በድጋሚ መጠየቁንና መንግሥትም አማጺ ኃይሎች በአገራዊ ምክክሩ አንዲሳተፉ ኹኔታዎችን እንዲያመቻች በድጋሚ ጥሪ ማድረጉንም ዘገባው ጠቅሷል። ምክር ቤቱ የምክክር ኮሚሽኑ ግጭቶች እንዲቆሙ የማድረግ ሥልጣን እንዳልተሰጠው በመግለጽ፣ ግጭቶች ባልቆሙበት ኹኔታ አገራዊ ምክክር ማድረግ ውጤት ላያመጣ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ገልጧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ጫካ የገቡ ኃይሎች በምክክሩ የሚሳተፉ ከኾነ፣ ከለላ ለመስጠት መንግሥትን እንደሚጠይቅ መናገሩን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
6፤ የጃፓን መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ከኅብረተሰቡ ጋር የመቀላቀልና መልሶ የማቋቋም መርሃ ግብር የሚውል 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል። የጃፓን የገንዘብ ድጋፍ፣ ለመርሃ ግብሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመግዛት፣ ለሥልጠና እንዲኹም በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለወደሙ ጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል ነው። ጃፓን የምትለግሰውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያስተዳድረው፣ ለመርሃ ግብሩ ኹለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርገው በኢትዮጵያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እንደኾነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ተሃድሶ ኮሚሽን በመላ አገሪቱ 371 ሺህ 971 የቀድሞ ተዋጊዎችን ለማቋቋም ማቀዱንና ኾኖም በቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዳላገኘ ይገልጣል።
7፤ የሱዳን መንግሥት፣ ሩሲያ በሱዳን የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር እንድታቋቁም አኹንም ቁርጠኛ አቋም እንዳለው አረጋግጧል። በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሃመድ ሲራጅ፣ የባሕር ኃይል ጣቢያው የሎጅስቲክስ ማዕከል እንዲኾን ኹለቱ አገሮች እንደተስማሙ ለሩሲያ ዜና ምንጮች ተናግረዋል። ሱዳን፣ ሩሲያ የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ማዕከሉን እንድትገነባ የገባችላትን ቃል እንደማታጥፍ አምባሳደሩ ገልጸዋል። ኹለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ከአምስት ዓመታት በፊት ቢኾንም፣ እስካኹን ግን ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም።
8፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ0675 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ2089 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረ ገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ2852 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ6709 ሳንቲም ኾኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ9297 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ63 ብር ከ1683 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ግንቦት 27/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን ዛሬ አጽድቋል። ምክር ቤቱ በ2011 ዓ፣ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለውን አዋጅ ያጸደቀው፣ በኹለት ተቃውሞና ባንድ ድምጸ ተዓቅቦ ነው። የተሻሻለው አዋጅ፣ “በአመጽና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎች “በልዩ ኹኔታ” በድጋሚ እንዲመዘገቡ እንደሚችሉ ደንግጓል። ኃይልን መሠረት ባደረገ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፈ የፖለቲካ ቡድን በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለመቀጠል ስለመስማማቱ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ካረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ኾኖ እንደሚመዘገብ የማሻሻያ አዋጁ ይገልጣል። የተሻሻለው አዋጅ፣ በምርጫ ቦርድ ሕጋዊነቱን የተነጠቀው ሕወሃት በድጋሚ ሕጋዊ ሰውነቱን መልሶ እንዲያገኝ በር የሚከፍት ነው።
2፤ አሜሪካ የሚገኝ ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት የተባለ ተቋም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በትግራይ ፈጽመዋቸዋል ላላቸው ዓለማቀፍ ወንጀሎች የአገሪቱ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዳኝነት ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሠረትበት አዲስ ባወጣው ሪፖርት ጠይቋል። ተቋሙ፣ የመንግሥት ኃይሎች ከኤርትራ ወታደሮችና ከአማራ ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ ብሏል። ተቋሙ፣ በክልሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈጸመ በቂ ማስረጃዎች አሉ ያለው፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ጥቃቶች እንደተፈጸሙና ርሃብ የጦርነት መሳሪያ ኾኖ እንዳገለገለ በመጥቀስ ነው። የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ካኹን ቀደም ባወጣው የምርመራ ሪፖርት፣ በጦርነቱ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና የጦር ወንጀሎች እንደተፈጸሙ መግለጡ ይታወሳል።
3፤ 79 አባላትን የያዘ የሳዑዲ ዓረቢያ የኢንቨስትመንትና የንግድ ልዑካን ቡድን ለምክክር ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ጧት ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ልዑካን ቡድኑ በሦስት ቀናት ቆይታው፣ ከኢትዮጵያ የንግድ ዘርፍ ተወካዮች ጋር የኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። ልዑካን ቡድኑ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በኃይል፣ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት እድሎችንም ያጠናል ተብሏል። የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑካን ቡድን፣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ጋር የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረምም ተገልጧል።
4፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመኾን ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 60 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው መናገሩን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 25 ቢሊዮኑን ብር ከመንግሥትና ራሱ ከተቋሙ ምንጮች ለማግኘት እንዳቀደና በእስካኹኑ የሽግግር ሂደት የገንዘብ አቅርቦት ውስንነት ትልቅ ችግር እንደኾነበት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገው ሽግግር ኹለት ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተገልጧል። ዩኒቨርሲቲው የሽግግር ሂደቱን እያከናወነ ያለው በአሜሪካዊያን የከፍተኛ ትምህርት ባለሙያዎች እገዛ ሲኾን፣ የሽግግር ሂደቱም ጥሩ ደረጄ ላይ እንደሚገኝ ትናንት በተካሄድ ምክክር ላይ እንደተገለጠ የአሜሪካ ኢምባሲ ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።
5፤ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አጀንዳዎች ላይ የመከሩ ባለድርሻ አካላት የከተማዋን ሕዝብ አጀንዳዎች አደራጅተው ዛሬ እንዳስረከቡት አስታውቋል። ለኮሚሽኑ አጀንዳዎችን አደራጅተው ለማቅረብ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲመክሩ የቆዩት ባለድርሻ አካላት፣ ከከተማዋ 119 ወረዳዎች የተወጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ የፖለታካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የሕግ አውጪ፣ የሕግ ተርጓሚ እና የሕግ አስፈጻሚ አካላት እንዲኹም የማህበራት ተወካዮች ናቸው። ኮሚሽኑ፣ ከኹሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አጀንዳዎችን ካሰባሰበ በኋላ ተጠባቂው አገራዊ የምክክር ጉባዔ ይጀምራል ብሏል።
6፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 200 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችንና ስደተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ብሄራዊ ኮሚቴው፣ እስካኹን 1 ሺህ 579 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከባሕረ ሰላጤዋ አገር እንደመለሰ ገልጧል። ብሄራዊ ኮሚቴው ዜጎችን ከኦማን የመመለሱን መርሃ ግብር እያካሄደ የሚገኘው ከሚያዝያ 29 ጀምሮ ነው። በሳዑዲ ዓረቢያ በተለያዩ ማቆያዎች ከሚገኙ 70 ሺህ ፍልሰተኛ ዜጎች መካከልም፣ እስካኹን ከግማሽ በላይ የሚኾኑት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ0789 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ2205 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረ ገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ3862 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ7739 ሳንቲም ኾኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ8792 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ63 ብር ከ1168 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

አልፋሽጋ ከሶስት ክረምት በኋላ ?
የፌደራሉ መንግስት ከትግራይ አማፅያን ጋር ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት የሱዳን ወታደሮች ድንበር ተሻግረው የኣኢትዮጵያ ይዞታ የነበሩ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸው ይታወቃል። ከሶስት ዓመት ተኩል በኋላ ዋዜማ የድንበሩ አካባቢ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት ሞክራለች። አንብቡት- https://tinyurl.com/33c5yx37

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ግንቦት 28/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና የንግድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። 79 አባላትን ያካተተው ልዑካን ቡድን፣ ከተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ ታዋቂ ኩባንያዎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የአገሪቱን ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ያቀፈ እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። ልዑካን ቡድኑ በሦስት ቀናት ቆይታው፣ በአዲስ አበባ በሚካሄድ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ይሳተፋል፤ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛል ተብሏል። ሚንስቴሩ፣ የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በኹለቱ አገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋትና የኹለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ ገልጧል።
2፤ መንግሥት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ አስሮ ያቆያቸውን 19 ግለሰቦች ባለፈው ቅዳሜ መልቀቁን ምንጮችን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ሌሎች 20 ታሳሪዎች ደሞ ከአዋሽ አርባ ወደ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደተዛወሩ ዘገባው አመልክቷል። የኢዜማ የቀድሞ አባል ናትናኤል መኮንን እና ጋዜጠኛ አብነት ታምራት ከአዋሽ አርባ ከተለቀቁት መካከል እንደሚገኙበት ኢሰመኮ አረጋግጫለኹ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።
3፤ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የአከራይና ተከራይ ሕጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 እንደሚጀምር ማስታወቁን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ቢሮው፣ በከተማዋ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ሕጋዊ ሰነዶቻቸውን በመያዝ መመዝገብ እንደሚችሉ መግለጡን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ይህንኑ ምዝገባ የሚያደርገው፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ ነው። የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ ኪራይ እንደይጨምሩና ተከራዮችን በግዳጅ እንዳያስወጡ የሚያግደው አዋጅ፣ አከራዮች ኪራይ መጨመር የሚችሉት የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል በዓመት አንድ ጊዜ የሚያወጣውን ስሌት መሠረት በማድረግ ብቻ እንደኾነ ይደነግጋል።
4፤ ንግድ ሚንስቴር፣ የሰኔ ወር የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ትናንት ማምሻውን አስታውቋል። ላለፈው አንድ ወር በሥራ ላይ ባለው የችርቻሮ ዋጋ መሠረት፣ የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 78 ብር ከ67 ሳንቲም ነው። በተመሳሳይ፣ የአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ዋጋ 79 ብር ከ75 ሳንቲም፣ ኬሮሲን 79 ብር ከ75 ሳንቲም፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 70 ብር 83 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 62 ብር ከ36 ሳንቲም እንዲኹም ከባድ ጥቁር ናፍጣ 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።
5፤ ሳዑዲ ዓረቢያ ጅቡቲ ወደብ ላይ የሎጅስቲክ ቀጠና ለማቋቋም የሚያስችላትን ስምምነት ከጅቡቲ ጋር ተፈራርማለች። የኹለቱ አገራት የሎጅስቲክ ቀጠና የሊዝ ስምምነት ለ92 ዓመታት የሚቆይ ነው። አዲሱ የሎጅስቲክ ቀጠና፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ለውጭ ገበያ ለምታቀርባቸው ምርቶቿ አዳዲስ ገበያዎች እንድታገኝ እንደሚያስችላት ተገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ግንቦት 28/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሱዳን ወታደሮች፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ እና መተማ ወረዳዎች አኹንም አንዳንድ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠሩ መኾኑን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር አንዳንዶቹን አካባቢዎች የተቆጣጠረው፣ የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እንደኾነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። የሱዳን ወታደሮች፣ ቋራ ወረዳን ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ሽንፋ ወንዝ ላይ መስራታቸውን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ወንዙ የኹለቱ አገራት ድንበር እንደነበር ጠቅሰዋል። ነዋሪዎቹ፣ ባካባቢው የሠፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሱዳን ጦር ወደያዛቸው አካባቢዎች እንድንጠጋ አይፈቅድልንም ብለዋል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንድ የዞኑ ኃላፊ፣ የሱዳን ወታደሮች የተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፣ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ግን ፍቃደኛ ሳይኾኑ ቀርተዋል። ቋራ እና መተማ ከፍተኛ የሰሊጥ፣ ጥጥ እና አኩሪ አተር ምርት የሚመረትባቸው ናቸው።
2፤ ኢሰመኮ፣ በአማራ ክልል ታውጆ ከነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ መንግሥት አስሮ ያቆያቸውን ሰዎች የመልቀቁን ሂደት እንዲቀጥል ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ አሳስቧል። ኢሰመኮ፣ "ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ"፣ በአዋጁ በአንዳንድ የክልል አካባቢዎች ተጣሉ "የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ" እና "ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች" ወደነበሩበት እንዲመለሱ ጠይቋል። ኢሰመኮ ይህንኑ ጥሪውን ያስተላለፈው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ጥር 24 ለአራት ወራት ያራዘመው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቆይታ ጊዜ ግንቦት 24 ቀን መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
3፤ የኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የጋራ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። 79 አባላት ያሉት የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና የንግድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በፎረሙ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገባው ትናንት ነበር። ልዑካን ቡድኑ ከተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ ታዋቂ ኩባንያዎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የአገሪቱን ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ያቀፈ እንደኾነ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። የልዑካን ቡድኑ የሦስት ቀናት ቆይታ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በኹለቱ አገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋትና የኹለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ ገልጧል። መንግሥት፣ የሳዑዲ ባለሃብቶች በማምረቻ፣ ታዳሽ ኃይል፣ ቱሪዝም እና በሌሎች ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ጠይቋል።
4፤ የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ እና በሕገ መንግሥቱ ያላት አስተዳደራዊ ደረጃ በአገራዊ ምክክር አጀንዳ እንዲኾን መቅረቡን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የአዲስ አበባ ከተማን የባለቤትነት እና አስተዳደራዊ ወሰን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ያቀረቡት፣ ከተማዋን ወከለው በምክክሩ የተሳተፉ ተወካዮች እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል። ከአዲስ አበባ የባለቤትነት እና አስተዳደራዊ ወሰን ጥያቄ በተጨማሪ፣ የከተማዋ ተወካዮች የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ፣ የሕግ መንግስት፣ የሰንደቅ ዓላማ፣ የኃይማኖት፣ የቋንቋ እና የተቋማት ገለልተኛነት፣ የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ፣ የምርጫና የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓት እንዲኹም ብሄራዊ ምልክት፣ በአጀንዳነት ማቅረባቸውን መስማቱን ዜና ምንጩ ጠቅሷል።
5፤ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ በመንግሥትና ፓርቲ ኃላፊዎችና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ያነጣጠሩ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች በተያዘው ሳምንት እንደተፈጸሙ መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። አንደኛው የቦምብ ጥቃት የዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ላይ የተፈጸመ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። ሌሎቹ ኹለቱ ጥቃቶች፣ በዞኑ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲኹም በከተማዋ ምክትል ከንቲባ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተፈጽመው በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኾኖም በቦምብ ጥቃቶቹ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
6፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በተያዘው ሳምንት 172 ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል። ኢምባሲው፣ ኢትዮጵያዊያኑን ወደ አገራቸው የመለሰው፣ ከዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት ወይም አይ ኦ ኤም ጋር በመተባበር እንደኾነ ገልጧል። "የምሥራቁ መስመር" ተብሎ የሚታወቀው በጅቡቲ በኩል ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት የሚያስወጣው መስመር፣ በፍልሰተኞች ሕይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀነ እንደኾነ ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት በተደጋጋሚ አስታውቋል። በቅርቡ፣ ኢትዮጵያዊያን የሚበዙባቸውን ፍልሰተኞች የጫኑ ጀልባዎች ከየመን ወደ ጅቡቲ በመመለስ ላይ ሳሉ በመስጠማቸው፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሕይወታቸው ማለፉ አይዘነጋም።
7፤ የተለያዩ የሱዳን ድርጅቶች በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙ 6 ሺህ ያህል ሱዳናዊያን ስደተኞችን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከችግር እንዲታደጓቸው በጋራ መጠየቃቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ጋዜጣ ዘግቧል። ድርጅቶቹ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ለስደተኞቹ አስፈላጊውን ኹሉ እንዲያደርግ መማጸናቸውንም ጠቅሷል። የደኅንነት ስጋት እንዳደረባቸውና የአገልግሎት አቅርቦት ችግሮች እንደገጠሟቸው በመግለጽ ከኩመር እና አውላላ መጠለያ ጣቢያዎች ከሦስት ሳምንት በፊት ከወጡት ሱዳናዊያን ስደተኞች መካከል፣ ከ2 ሺህ 100 በላይ የሚኾኑት ሕጽናት እንደኾኑ ድርጅቶቹ ገልጸዋል ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን መንገድ ዳር የከተሙት ስደተኞች በቅርብ ርቀት ካለው አውላላ የስደተኞች መጠለያ አንዳንድ መሠረታዊ አቅርቦቶችን እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጦ፣ ኾኖም አካባቢው ለረድዔት ሠራተኞች ደኅንነት አኹንም አስጊ እንደኾነ ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ግንቦት 29/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ቀውስ የሰጡት ምላሽ በቂ እንዳልነበር ድርጅቶቹ ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት የግምገማ ሪፖርት አስታውቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ እስካለፈው ዓመት ታኅሳስ ድረስ፣ “የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራ አመራሩ በዋናነት የተበታተነ" እንደነበርና ይህም የዕርዳታ አሰጣጡ ውጤታማ እንዳይኾን እንዳደረገው ሪፖርቱ ገልጧል። ሪፖርቱ፣ በግጭት ወቅት ወሳኝ የኾነው "በመርህ ላይ ያተኮረ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራ" በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች "በበቂ ኹኔታ" ተግባራዊ አልሆነም ብሏል። ኾኖም ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በጦርነቱ ለተጎዱት ሦስት ክልሎች አስፈላጊውን ዕርዳታ በማድረስ ረገድ በርካታ መሰናክሎችን ማለፍ እንደቻሉ ሪፖርቱ ጠቅሷል።
2፤ የከባድ መኪና ሹፌሮች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መስራት አስቸጋሪ ኾኖብናል ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የከባድ መኪና ሹፌሮች፣ "የኮቴ" በሚል በእያንዳንዱ ኬላ ላይ በሕገወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፍሉ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ባንድ ኬላ ላይ የተሰጠ ደረሰኝ ሕጋዊ ይኹን አይኹን እንደማይታወቅና ቀጣዩ ኬላ ላይ ደረሰኙን አሳይቶ ገንዘብ ሳይከፍሉ ማለፍ እንደማይቻልም አሽከርካሪዎች መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። አሽከርካሪዎች ለኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ማጠናከሪያ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱም ገልጠዋል ተብሏል።
3፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ከሳዑዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 188 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። ከተመላሾቹ መካከል፣16ቱ ጨቅላ ሕጻናትና 20ዎቹ ደሞ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ አስታውቋል። ብሄራዊ ኮሚቴው ከሚያዚያ 04 ጀምሮ እስከ ትናንት በጠቅላላው ከ37 ሺህ 500 በላይ ዜጎችን መልሷል ተብሏል።
4፤ ኬንያ፣ የተቃዋሚ መሪውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው እንዲመረጡ በሰኔ መጨረሻ ማመልከቻ ሰነዱን ለኅብረቱ እንደምታስገባ አስታውቃለች። የአገሪቱ መንግሥት ኦዲንጋ እንዲመረጡ በአሕጉር ደረጃ የሚያስተባብር ቢሮ ከፍቷል። ከኦዲንጋ ሌላ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲና ሲሸልስ ለኮሚሽኑ ሊቀመንበርነት ዕጩዎቻቸውን አቅርበዋል። የኅብረቱ መሪዎች ቀጣዩን የኮሚሽኑን ሊቀመንበር የሚመርጡት በቀጣዩ ዓመት የካቲት ወር ላይ ነው።
5፤ ደቡብ ኮሪያ፣ በተመድ ውስጥ ሰሜን ኮሪያን በሚመለከቱ ጉዳዮች የአፍሪካ አገራትን የፖለቲካ ድጋፍ እንደምትፈልግ ይፋ አድርጋለች። የደቡብ ኮሪያና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ምሽት ሲጠናቀቅ ባወጣው መግለጫ፣ በቁልፍ ማዕድናት አጠቃቀም ላይ የሚመክር የኮሪያ-አፍሪካ የምክክር መድረክ እንዲቋቋም እንደተወሰነ ገልጧል። አገሪቱ፣ እስከ አውሮፓዊያኑ 2030 ለአፍሪካ አገራት 10 ቢሊዮን ዴላር እርዳታ ለመስጠት ቃል የገባች ሲኾን፣ ኩባንያዎቿም በኢንቨስትመንት ዘርፍ በአፍሪካ እንዲሠማሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጣለች። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሐሙስ ግንቦት 29/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቆማቸውን ዋዜማ ሰምታለች። ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል። ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል። አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል። ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።
2፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ቤተክርስቲያኗ በምክክሩ ሂደት ተሳትፎ እንድታደርግ ጥሪ ሳያደርግ የምክክር ተሳታፊዎችና የአጀንዳ ልየታ ማካሄዱ ቅር እንዳሰኛት ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች። ሲኖዶሱ፣ በአገራዊ ምክክር ሂደቱ ቤተ የቤተክርስቲያኗ መብት እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር የሚነጋገር ኮሚቴ መሰየሙን ገልጧል። ሲኖዶሱ፣ መንግሥት ባዘጋጀው ረቂቅ የኃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ ላይ የማሻሻያ ሃሳቦች ማዘጋጀቱና ገልጦ፣ ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴም አቋቁሜያለኹ ብሏል። በቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ መሰየሙንም ሲኖዶሱ አስታውቋል። በአገሪቱ በሚካሄዱ ግጭቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መቀጠሉ እንዳሳዘነው የገለጠው ሲኖዶሱ፣ ኹሉም አካላት ግጭቶችን በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በመግለጫው ጥሪ አድርጓል።
3፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ደዔታ ታዬ ደንደዓ ላይ የቀረቡ ምስክሮችን ቃል ዛሬ እንደተቀበለ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ዛሬ የሰማው የኹለት ምስክሮችን ቃል ሲኾን፣ ምስክሮች የሰጡትን ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችም መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 18 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ ዘገባው አመልክቷል። የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ በታዬ ላይ ክስ የመሠረተው፣ ታጣቂ ቡድኖችን የሚደግፉ የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አሠራጭተዋል፤ ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል በማለት ነበር።
4፤ ሱማሊያ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ መጨረሻ ከአገሪቱ እንዲወጡ ያሳለፈችውን ውሳኔ አጥፋለች ተብሎ የተሠራጨውን መረጃ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል። ሚንስቴሩ፣ ሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር የኾነችው ታንዛኒያ በጉዳዩ ዙሪያ የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ ከኢትዮጵያ ጋር እንድታሸማግላት ጠይቃለች መባሉንም "ሐሰት ነው" ብላለች። ሚንስቴሩ ማስተባበያውን ያወጣው፣ የአገሪቱ አንዳንድ ዜና ምንጮች እና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ለታንዛኒያ አቻው የጻፈው ደብዳቤ አግኝተናል በማለት መረጃውን ማሠራጨታቸውን ተከትሎ ነው። የሱማሊያ መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች እስከ ቀጣዩ ታኅሳስ መጨረሻ ከአገሪቱ እንዲወጡ እና የአፍሪካ ኅብረትን ጦር ይተካል ተብሎ በሚጠበቀው ኅብረብሄራዊ ተልዕኮ ሥር እንዳይካተቱ መወሰኑን ባለሥልጣናቱ ሰሞኑን መናገራቸው ይታወሳል።
5፤ ሱማሊያ ለቀጣዮቹ ኹለት ዓመታት የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ኾና ዛሬ በከፍተኛ ድምጽ ተመርጣለች። የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ፣ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሱማሊያን ጨምሮ አምስት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባላትን መርጧል። ሱማሊያ ባለፈው ኅዳር ወር ነበር አፍሪካን በመወከል የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል ለመኾን ራሷን ዕጩ አድርጋ ያቀረበችው። ባኹኑ ወቅት በጸጥታው ምክር ቤት አፍሪካን በመወከል ተለዋጭ መቀመጫ ያላቸው፣ ሞዛምቢክ፣ አልጀሪያ እና ሴራሊዮን ናቸው። ሱማሊያ በአባልነት የተመረጠችው፣ የኹለት ዓመት ቆይታዋን በቀጣዩ ዓመት ጥር ወር የምታጠናቅቀውን ሞዛምቢክን በመተካት ነው። ሱማሊያ በታሪኳ አንድ ጊዜ ብቻ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የኾነችው ከ50 ዓመታት በፊት ነበር።
6፤ አውሮፓ ኅብረት በስድስት የሱዳኑ ጦርነት ተፋላሚ የጦር መኮንኖች ላይ ማዕቀብ ሊጥል እንደኾነ መስማቱን ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን ዘግቧል። ኅብረቱ ማዕቀብ የሚጥለው፣ በሦስት የፈጥኖ ደራሹ ኃይል እና በሦስት የሱዳን ጦር ሠራዊት መኮንኖች ላይ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። አውሮፓ ኅብረት ባለፈው ጥር ወር ከኹለቱ ተፋላሚ ወገኖች ጋር ግንኙነት ባላቸው ስድስት ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉ አይዘነጋም። ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና አፍሪካ ኅብረት ሲቪሎችን ከጥቃት የሚከላከል ዓላማቀፍ ተልዕኮ በአገሪቱ እንዲሠማራ አውሮፓ ኅብረት ድጋፉን እንዲሠጥ በቅርቡ ጠይቆ የነበረ ሲኾን፣ ኅብረቱ ግን ማዕቀብ ከመጣል ውጭ ሌላ ዕቅድ እንደሌለው ዲፕሎማቶች ተናግረዋል ተብሏል።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ1069 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ2490 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረ ገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ7038 ሳንቲም እና መሸጫው 71 ብር ከ0979 ሳንቲም ኾኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ62 ከ1038 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ63 ብር ከ3459 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ዓርብ ግንቦት 30/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ለቀጣዩ 2017 በጀት ዓመት 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን አስታውቋል። ምክር ቡቱ፣ የ2017 ዓ፣ም በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል በኾነው ከ2016 እስከ 2018 በሚቆየው የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና ከ2017 እስከ 2021 ዓ፣ም የሚቆየውን የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍ ለማስፈጸም እንዲቻል ኾኖ የተዘጋጀ መኾኑን ገልጧል። በጀቱ፣ የመንግሥት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ተልኳቸውንና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸውን ወጪ ግምት ውስጥ በማስገባት መዘጋጀቱንም ምክር ቤቱ ጠቅሷል። በጀቱ በዋናነት፣ ለፌዴራል መንግሥት መደበኛና የካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች ድጎማ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያና ለተጠባባቂ ወጪ የሚውል ነው ተብሏል።
2፤ ከትግራይ ክልል የሄዱ ናቸው የተባሉ የታጠቁ ኃይሎች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ ማክሰኞ'ለት በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 15 ሰዎች እንደተገደሉና በርካታ ንብረት እንደተቃጠለ ከነዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። አሊጣራ በተባለ ቀበሌ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት የቡድን መሳሪያ የታጠቁ እንደኾኑ፣ ከተገደሉት መካከል ኹለቱ የሚሊሻ አባላት እንደኾኑ፣ የጥቃቱ አድራሾች በርካታ መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውንና ከብቶችን መዝረፋቸውን የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ነዋሪዎችም፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ 500 ያህል ከብቶችን ዘርፈውና ሦስት ሰዎችን አፍነው እንደሄዱ ተናግረዋል ተብሏል። የወረዳው አስተዳደር የሕወሃት ታጣቂዎችን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ የትግራይ ኃይሎች ወደ ወረዳው አልገቡም በማለት ውንጀላውን አስተባብሏል ተብሏል።
3፤ የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትናንት ያቀረበችበትን ቅሬታ ተከትሎ ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዱስ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መኾኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ፣ የአካታችነት መርሁ ከኹሉም የኃይማኖት ተቋማት ጋር "በእኩልነት የሚተገበር" መኾኑን ገልጧል። ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ቤተክርስቲያኗ በምክክር ተሳታፊዎች እና አጀንዳ ልየታ ሂደቱ እንድትሳተፍ ጥሪ ሳያደርግ መቅረቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጦ ነበር። ኮሚሽኑ ግን፣ ከጅምሩ በምክክር ሂደቱ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እንደኾነ ጠቅሷል፡፡ ጉባዔው፣ በተሳታፊዎች ልየታ እና በአዲስ አበባ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት "ከፍተኛ አስተዋጽኦ" ማድረጉንም ኮሚሽኑ ጠቅሷል።
4፤ የፌደራሉ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት እና አለመረጋጋት ከሕዝብ የሚቀበለውን ቅሬታ ከ80 በመቶ በላይ እንደቀነሰበት መግለጡን ሸገር ዘግቧል። በባሕርዳር የሚገኘው የተቋሙ ቅርንጫፍ፣ በክልሉ የሚታየው አለመረጋጋት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንቅፋት ስለኾነብኝ በውስን የክልሉ አካባቢዎች ላይ ብቻ ለመስራት መገደዱንና 50 በመቶ የሚኾነውን የክልሉን አካባቢ መሸፈን እንዳልቻለ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። ባለፈው ዓመት ከ1 ሺህ 300 በላይ አቤቱታዎችን የተቀበለው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ፣ በዘንድሮው ዓመት ግን ከ200 አቤቱታዎች በላይ እንዳልተቀበለ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ፣ በክልሉ የሚካሄደው ግጭት በባሕርዳር ዙሪያ፣ ጎንደር ከተማ እና በሌሎች የተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ብቻ እንድንቀሳቀስ አስገድዶኛል ብሏል ተብሏል። የፌደራሉ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በኦሮሚያ ክልል ያለው አለመረጋጋት ከአዲስ አበባ ከ200 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ እንዳይሠራ እንቅፋት እንደፈጠሩበት መናገሩንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።
5፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በሕግ ከተቀመጠው መጠን በላይ የካርበን ልቀት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በከተማዋ መንገዶች ላይ እንዳይሽከረከሩ የሚያግድ መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ እንደኾነ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መመሪያው፣ በተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ ወይም ካርበን ልቀት ሳቢያ በከተማዋ የሚፈጠረውን የአየር ብክለት ለመቆጣጠር የሚያስችል እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በከተማዋ የሚከሰተው 27 በመቶው የአየር ብክለት ምክንያት ተሽከርካሪዎች እንደኾነና በመመሪያው መሠረት ባንድ ኪሎ ሜትር ከ0 ነጥብ 5 በላይ የካርበን ልቀት ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ከአገልግሎት እንደሚታገዱ ተገልጧል፡፡
6፤ የጀርመን ፓርላማ፣ ጀርመን በአፍሪካ ቀንድና በኤደን ባሕረሰላጤ ሊኖራት የሚገባትን ሚና የሚመለከት ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ሰነድ ማዘጋጀቱን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ረቂቁ ሰነድ፣ የጀርመን ባሕር ኃይል በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያሉ ጅኦፖለቲካዊ ቀውሶችን በማረጋጋት ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚጠይቅ ነው። ጀርመን በአውሮፓ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ብትኾንም፣ እስካሁን አውሮፓ ኅብረት ጅቡቲ ውስጥ ባቋቋመው ወታደራዊ ጦር ሠፈር፣ ኅብረቱ ለሱማሊያ በሚሰጠው የወታደራዊ ሥልጠና ድጋፍም ኾነ በተናጥል በቀጠናው አገራት ውስጥ ይህ ነው የሚባል ወታደራዊ ሚና የላትም።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ1246 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ2671 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረ ገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ6545 ሳንቲም እና መሸጫው 71 ብር ከ0476 ሳንቲም ኾኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ62 ከ0773 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ63 ብር ከ3188 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ከአማራ ክልል ከአውላላና ኩመር መጠለያዎች የወጡ 8 ሺህ ሱዳናዊያን ስደተኞች አኹንም አካላዊ ጥቃትና እገታ እንደሚፈጸምባቸው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። 6 ሺህ ስደተኞች ከመጠለያዎቹ ወጥተው ጫካ ውስጥ የከተሙት፣ ለተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ጎንደር በእግር ሲጓዙ ፖሊስ ካስቆማቸው በኋላ መኾኑን መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። ዘገባው፣ ኩመር መጠለያ ውስጥ ኮሌራ እንደተስፋፋና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በመጠለያዎቹ ውስጥ ለቀሩ ስደተኞች ላንድ ወር የሚያቀርበው ምግብ ለኹለት ሳምንት እንኳ እንደማይበቃ መስማቱንም ጠቅሷል። ተመድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ሱዳናዊያን ስደተኞች ከጠየቀው 175 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ እስካኹን ያገኘው ልገሳ 400 ሺህ ዶላር ብቻ ነው።
2፤ ኢሰመጉ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጊዜ ገደቡ ያበቃውን በአማራ ክልል ተጥሎ የነበረውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያራዝም ጠይቋል። ኢሰመጉ፣ በአዋጁ ወቅት ይፈጸሙ የነበሩ ጥሰቶች ከአዋጁ ማብቃት በኋላም "ያለምንም የሕግ መሠረት" መቀጠላቸውን ገልጧል። መንግሥት ከአዋጁ ጋር በተያያዘ "በተለያዩ መደበኛ እና ኢመደበኛ" ማቆያዎች የታሠሩ ሰዎችን እንዲፈታ፣ በመደበኛው ሕጋዊ አሠራር ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ወይም ወደ መደበኛ ማቆያዎች እንዲያዘዋውርም ድርጅቱ ጠይቋል። ኢሰመጉ፣ የአዋጁ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድም፣ በአዋጁ ወቅት የተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን መርምሮ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ ጭምር ጥሪ አድርጓል።
3፤ "ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ለኢትዮጵያ" መንግሥት በጋዜጠኞች፣ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ በኾኑ ሰዎች እና ፖለቲከኞች ላይ የሚፈጽመው “የዘፈቀደ እስር” እንዳሳሰበው ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጅቱ፣ የመንግሥት ርምጃዎች የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የማፈን አዝማሚያን ያመለክታሉ ብሏል። መንግሥት “በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈጽማቸውን ጥሰቶች” እንዲያቆም እና የዜጎችን የመናገርና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲያከብር ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል። ድርጅቱ፣ መንግሥት ሀሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ያሠራቸውን ግለሰቦች ባስቸኳይ እንዲፈታም ጠይቋል።
4፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከሱማሊያ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ወይም ከተመድ በሱማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮችን የሚመለከት አዲስ ውሳኔ እንዳልደረሰው በቃል አቀባዩ ነቢዩ ተድላ በኩል ትናንት አስታውቋል። የሱማሊያ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የደረሰችበትን የባሕር በር ስምምነት እስከ ሰኔ መጨረሻ ካለፈረሰች ወታደሮቿን ከሱማሊያ እናስወጣለን በማለት ሰሞኑን አስጠንቅቀው ነበር። ቃል አቀባዩ፣ ሱማሊያ ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች የያዙት ተልዕኮ ከሶማሊላንድ ጋር ከተፈረመዉ የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
5፤ የኬንያ ፖሊስ፣ በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በሞያሌ በኩል በሕገወጥ መንገድ የገቡ 17 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ባለፈው ረቡዕ እንደታደገ ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል። ኢትዮጵያዊያኑ ፍልሰተኞች ሞምባሳ ውስጥ የተያዙት፣ ሰው አዘዋዋሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያጓጉዟቸው ሲሉ እንደኾነ ፖሊስ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑን በተሽከርካሪ ሲያጓጉዝ የነበረው ሹፌር በቁጥጥር ሥር አውሎ፣ ሰው አዘዋዋሪዎቹን እያደነ ነው ተብሏል። ከሞያሌ እስከ ናይሮቢ በርካታ የፍተሻ ኬላዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያዊያኑ በቡድን እንዴት በዋና ከተማዋ በኩል አልፈው ሞምባሳ እንደደረሱ ለጊዜው እንዳልታወቀ ተገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚባባስና የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋ እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን ከአንድ የድርጅቱ ሰነድ ላይ መመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነትና ላኪነት እና በችርቻሮና ጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የፈቀደው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት ሲል ሊኾን እንደሚችል ሰነዱ ማመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለቱ ተቋማት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም እንደሚፈልጉና የእስካኹኑን የዋጋ ንረት ከአለመረጋጋትና ከዓለማቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ጋር እንደሚያያይዙት ሰነዱ ያብራራል ተብሏል። ብሄራዊ ባንክ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ማብቂያ የመደበኛውንና የጥቁር ገበያውን የምንዛሬ ልዩነት ልዩነት ለማጥበብና ለ25 ቀናት የሚበቃውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ አንድ ወር ለማሳደግ ማቀዱን ሰነዱ ይጠቅሳል ያለው ዘገባው፣ ባንኩ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን ወደ ኹለት ወር ለማሳደግ ማሰቡንም እንደጠቆመ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ከእያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት።
2፤ ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል። በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል። ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል። በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው።
3፤ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ኩመር እና አውላላ ከተባሉ የተመድ የስደተኞች መጠለያዎች ለቀው የወጡ ሱዳናዊያን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር እንቅስቃሴ እያደረኩ ነው ማለቱን ቪኦኤ ዘግቧል። የተቋሙ ሃላፊዎች፣ ሱዳናዊያኑን ስደተኞች በዞኑ ውስጥ ወደሚገኝ አፍጥጥ የተባለ ቦታ የማዛወሩ ሂደት እንደተጀመረ መግለጣቸውን እንደገለጡ ዘገባው አመልክቷል። ተቋሙ፣ በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ኹኔታ ለማሻሻል እየሠራ እንደኾነም ገልጧል ተብሏል። በሺዎች የሚቆጠሩት ስደተኞች ከመጠለያዎቹ አቅራቢያ መንገድ ዳር የከተሙት፣ ታጣቂዎች በመጠለያዎቹ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ስላደርሱ፣ ተደጋጋሚ እገታዎችን ስለፈጸሙና አገልግሎቶች በማሽቆልቆላቸው እንደኾነ መናገራቸውን የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን መግለጡ ይታወሳል። ስደተኞቹ በበኩላቸው፣ ተመድ በሦስተኛ አገር እንዲያሠፍራቸው ይፈልጋሉ ተብሏል። መንገድ ዳር የከተሙት ስደተኞች አኹንም የጥቃት ሰለባ እየኾኑ እንደሚገኙ መናገራቸውን ሮይተርስ ትናንት ዘግቦ ነበር።
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል። የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው። አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው። አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።
5፤ ዓለም ባንክ፣ በአውሮፓዊያኑ 2023 የዓለም የወደቦች የብቃት መለኪያ ለሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ወደቦች ቀዳሚውን ደረጃ ሰጥቶታል። በድርጅቱ የደረጃ ምደባ መሠረት፣ በርበራ የካርጎ መርከቦችን በማስተናገድ አቅሙ ከዓለም 348 ወደቦች 106ኛ ደረጃ አግኝቷል። ጅቡቲ ወደብ በዓለም 379ኛ ደረጃ የተሰጠው ሲኾን፣ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ደሞ 328ኛ ደረጃ አግኝቷል። የጅቡቲ መንግሥት፣ ለጅቡቲ ወደብ የተሰጠውን ደረጃ "አድሏዊ" በማለት ውድቅ አድርጎታል። ዓለም ባንክ፣ የዓለም ወደቦችን ለማወዳደር የተጠቀመው መስፈርት፣ ካርጎ ጫኝ መርከቦች ወደቦች ላይ ጭነታቸውን ለማራገፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ነው። [ዋዜማ]

በራያ አላማጣ በትግራይ ታጣቂዎችና ነዋሪዎች መካከል ውጥረት ተባብሷል፤ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል- ዝርዝሩን ያንብቡት- https://tinyurl.com/mx53fjyu
ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ሰኔ 3/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያ ለሌሎች አገራት አየር መንገዶች የትኬት ሽያጭ ገቢ በውጭ ምንዛሬ ያልከፈለችው 149 ሚሊዮን ዶላር የተከማቸ ገንዘብ እንዳለባት ዓለማቀፉ የሲቪል አቬሽን ማኅበር አስታውቋል። ኤርትራ 75 ሚሊዮን ዶላር ያልከፈለችው ገንዘብ ያለባት ሲኾን፣ አልጀሪያ ደሞ 286 ሚሊዮን ዶላር እንዳለባት ማኅበሩ ገልጧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ለበርካታ አየር መንገዶች ያልከፈሉት ከፍተኛ የገንዘብ ክምችት የነበረባቸው ናይጀሪያና ግብጽ ግን በቅርቡ አብዛኛውን ገንዘብ ከፍለዋል ተብሏል። ኾኖም በርካታ አየር መንገዶች፣ በናይጀሪያና ግብጽ የገንዘብ ምንዛሬ ዋጋ መውረድ ሳቢያ ማግኘት ይገባቸው የነበረው ገቢያቸው በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆሉን ማኅበሩ ጠቅሷል።
2፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ወደ አክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ እንደገና በረራ ጀምሯል። አየር መንገዱ ለጊዜው ወደ አክሱም በቀን አንድ በረራ እንደሚያደርግ ገልጧል። አውሮፕላን ማረፊያው እንደገና በረራ ማስተናገድ የጀመረው፣ በሰሜኑ ጦርነት ከደረሰባት ጉዳት ላይ ሲደረግ የቆየው የጥገና ሥራ ባለፈው መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በአውሮፕላን ማረፊያው በረራ ማስጀመሪያ ስነ ሥርዓት ላይ፣ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳና ሌሎች ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
3፤ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የነበሩ ያልተሳካው የኅዳሩ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች ዓርብ'ለት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደተዛወሩ መስማቱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ ከተዛወሩት የሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል፣ የኢሕአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ፣ የሕግ ጠበቃ አበራ ንጉስ፣ ዮሴፍ ተሻገር እና እዮብ ገብረ ሥላሴ እንደሚገኙበት ዘገባው አመልክቷል። መንግሥት ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ ያዛወራቸው እስረኞች፣ በጠቅላላው 17 እንደኾኑ ዜና ምንጩ ጠቅሷል። ላንድ ሳምንት ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ አስሯቸው የነበሩት ሌላኛው የኅዳሩ ሰልፍ አስተባባሪና የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሠፋ ደሞ ቅዳሜ'ለት ከእስር ተፈተዋል።
4፤ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ያፒ መርከዝ የተባለው የቱርክ ተቋራጭ ኩባንያ ለንደን በሚገኘው ዓለማቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ባቀረበበት የካሳ ክፍያ ክስ ላይ መቃወሚያ ማቅረቡን እንደገለጠ ካፒታል ዘግቧል። ኩባንያው በኮርፕሬሽኑ ላይ የካሳ ጥያቄ ክስ የመሠረተው፣ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ የአዋሽ - ወልዲያ - ሃራ ገበያ የባቡር ሐዲድ ግንባታ ፕሮጀክቱን ለማቋረጥ መገደዱን ተከትሎ ነበር። ኮርፖሬሽኑ፣ ተቋራጩ ኩባንያ ያቀረበበት የጉዳትና ሌሎች የካሳ ጥያቄዎች የተጋነኑ እንደኾኑ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። የካሳ ክስ ሂደቱ መሰማት የጀመረው ባለፈው ዓመት ግንቦት ገደማ ነበር። ተቋራጩ ኩባንያ ባቡር ሐዲዱን ለመገንባት ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተዋዋለው፣ በ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ነበር። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ ግንቦት 3/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የትግራይ ታጣቂዎች በራያ አላማጣ ከተማ በኹለት ሳምንት ውስጥ ሦስት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው አምስቱን እንዳቆሰሉ ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች። የትግራይ ኃይሎች ባለፈው ሳምንት ባንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ቦምብ ጥለው ኹለት ሰዎችን በመግደል አራቱን እንዳቆሰሉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ቅዳሜ'ለት ደሞ አንድን ወጣት መግደላቸውን ተከትሎ፣ የአላማጣ ከተማና አካባቢው ሕዝብ የትግራይ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡ ትናንት ባደረገው የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠይቋል። የትግራይ ኃይሎች ፈጽመዋቸዋል የተባሉትን ግድያዎች፣ በቅርቡ የፈረሰው የቀድሞው አስተዳደር የአላማጣ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ኃይሉ አበራ ጭምር ለዋዜማ አረጋግጠዋል። በርካታ የትግራይ ኃይሎች፣ አላማጣ አከባቢ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደከተሙ ይነገራል። Link- https://tinyurl.com/mx53fjyu
2፤ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው አማጺ ቡድን ትናንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ሙከጡሪ ከተማ መግቢያ ላይ 29 ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን ዋዜማ በሥፍራው ከሚገኙ ምንጮቿ ሰምታለች። አማጺ ቡድኑ፣ እገታውን የፈጸመው፣ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ከከተማዋ መግቢያ ልዩ ስሙ ጃቴ ከተባለ ቦታ ላይ እንደኾነ ምንጮች ጠቁመዋል። ታፍነው የተወሰዱት ሰዎች፣ መነሻቸውን አዲስ አበባ ባደረጉ ኹለት በተለምዶ "አባዱላ" ተብለው በሚጠሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንዲኹም በሦስት ሲኖትራኮች፣ ባንድ ኤፍ ኤስ አር እና ባንድ የቤት አውቶሞቢል ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ እንደኾኑና አማጺዎቹ ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ትተዋቸው እንደሄዱ ዋዜማ ተረድታለች። ከተሳፋሪዎቹና ተጓዦቹ መካከል ኹለት ሰዎች ማምለጣቸውን የገለጡት የዓይን እማኞች፣ ቀሪዎቹ ግን ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በቡድኑ እገታ ሥር እንደሚገኙ ገልጸዋል።
3፤ ፍትሕ ሚንስቴር፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን ለመተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ አጠናቆ ለውይይት ዝግጁ ማድረጉን አስታውቋል። ፍኖተ ካርታው በፖሊሲው የትግበራ ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የያዘ እንደኾነ የገለጠው ሚንስቴሩ፣ ሰነዱ ሲቪል ማኅበራት በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የኾነ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ኹኔታ እና የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን አተገባበር ቅደም ተከተል እንዳካተተም ገልጧል። ሰነዱ፣ በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደት፣ የክልሎችን፣ የባሕላዊ ፍትሕ ሥርዓቶችን፣ የተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሚና፣ ተሳትፎና ኃላፊነት እንዲኹም የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን በተመለከተ የሚተገበሩ ተጨማሪ ርምጃዎችን ይዟል ተብሏል። ሚንስትሮች ምክር ቤት፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን ያጸደቀው ባለፈው ሚያዝያ ወር ነበር። መንግሥት የሽግግር ፖሊሲውን ያዘጋጀው፣ በወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነት በማፈላለግ፣ ይፋ ማውጣት እና ዕርቅ ማውረድ፣ በቅድመ ኹኔታ ላይ የተመሰረተ ምሕረት በማድረግ፣ በተቋማዊ ማሻሻያ እና በማካካሻ ስልቶች መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ነው።
4፤ ገንዘብ ሚንስቴር፣ በቀጣዩ በጀት ዓመት መንግሥት ለመሰብሰብ ባቀደውና በወጪው መካከል የ358 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት እንደሚኖር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ የበጀት መግለጫ ላይ ተገልጦ መመልከቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። መንግሥት በአዲሱ በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ጠቅላላ ገቢ የውጭ ድጋፍን ጨምሮ 612 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ይሆናል ብሎ እንደሚገምትን ይህም ከተያዘው በጀት ዓመት የ23 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ እንዳለው የበጀት መግለጫው እንደሚያመለክት ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት 502 ቢሊዮን ብሩን ለመሰብሰብ ያቀደው ከታክስ ሲኾን፣ 61 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብሩ ታክስ ነክ ካልኾኑ ገቢዎች፣ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብሩ ከአጋሮች የሚገኝ ድጋፍ እንደኾነ ተገልጧል ተብሏል። በበጀት ዓመቱ የፌደራል መንግሥቱ ጠቅላላ ወጪ 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እንደሚኾንም ከሰነዱ ላይ መመልከቱን ዜና ምንጩ ገልጧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ይህንኑ ዝርዝር የቀጣይ ዓመት በጀት ገና አላጸደቀም።
5፤ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በክልሉ ምሥራቅ ጎጃም ዞን በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በዞኑ ከሚገኙ 996 የአንደኛና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ባኹኑ ወቅት የመማር ማስተማር ሥራቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ እንደኾኑ አስታውቋል። በተያዘው የትምህርት ዘመን ከ539 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎች በአንደኛና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገብተው እንደሚማሩ ተጠብቆ የነበረ ቢኾንም፣ በግጭቱና በሰላም እጦት የተነሳ ባኹኑ ወቅት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ግን ከ13 ሺህ 000 እንደማበልጡ ቢሮው ገልጧል። 791 ትምህርት ቤቶች ከ41 ሺህ 940 በላይ ተማሪዎችን በተያዘው ወር የ6ኛ ክፍል ክልል ዓቀፍ ፈተና እንደሚያስፈትኑ ተጠብቆ እንደነበር የጠቀሰው ቢሮው፣ 12 ትምህርት ቤቶች ብቻ በኹለት ዙር 506 ተማሪዎችን ያስፈትናሉ ተብሏል።
6፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ1366 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ2793 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ8875 ሳንቲም እና መሸጫው 71 ብር ከ2853 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ62 ከ2618 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ63 ብር ከ5070 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በጎ ፍቃደኛ የአካባቢ ብክለት ተሟጋች የሕግ ባለሙያዎች አንዳንድ የመንግሥት ሃላፊዎች እያስፈራሯቸውና እየዛቱባቸው መኾኑን በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሠራው "ቁም ለአካባቢ" የተባለው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅት መናገሩን ሸገር ዘግቧል። የሕግ ባለሙያዎቹ የሕዝብን ጥቅም በፍቃዳቸው ወክለው በፍርድ ቤቶች የሚከራከሩት፣ የአካባቢ ብክለት ያደረሱ የመንግሥት ተቋማትንና ፋብሪካዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። የአካባቢ ጥበቃ መብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ ከባለሥልጣናት ማስፈራሪያና ዛቻ በተጨማሪ የገንዘብ እጥረት ችግር እንዳለበት መናገሩንም ዘገባው ጠቅሷል።
3፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ከሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 167 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡ ከተመላሾቹ ፍልሰተኛ ዜጎች መካከል፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 16 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል። ኮሚቴው ሚያዝያ 4 በጀመረው ፍልሰተኞችን የማጓጓዝ እንቅስቃሴ፣ ከ70 ሺህ ፍልሰተኞች መካከል፣ እስካኹን ወደ 40 ሺህ የሚጠጉትን ወደ አገራቸው መመለስ ችሏል።
3፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ኤርትራ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የኢንቨስትመንት አጋርነት ለመፍጠር ከ8-10 ሳምንታት ውስጥ የኢንዱስትሪ መረጃዎቿንና የልማት እቅዶቿን አዘጋጅታ ለአገሪቱ እንደምትልክ ቃል እንደገቡ የደቡብ ኮሪያው ሄራልድ ጋዜጣ ዘግቧል። ደቡብ ኮሪያ ጥቅም ላይ ያልዋሉ የአፍሪካ የማዕድን ሃብቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል ቁልፍ ሚና መጫወት ትችላለች ያሉት ኢሳያስ፣ አፍሪካና ደቡብ ኮሪያ በማዕድን ላይ በአጋርነት ለመስራት ዝርዝር እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ያ ካልኾነ ግን የአፍሪካን ማዕድን ጥቅም ላይ ለማዋል ብዙ ውስብስብ ችግሮች እንዳሉ ኢሳያስ መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ይህን ለጋዜጣው የተናገሩት፣ ባለፈው ሳምንት ደቡብ ኮሪያ ባስተናገደችው የደቡብ ኮሪያና አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ከተሳተፉ በኋላ ነው።
4፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ አሜሪካ ለጋዛው ጦርነት ያቀረበችውን የተኩስ አቁም የውሳኔ ሃሳብ ትናንት ምሽት አጽድቋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ፣ በመጀመሪያው መርሃ ግብር የስድስት ሳምንት ተኩስ አቁም ማድረግንና እስረኞችንና ታጋቾችን መልቀቅን፣ በኹለተኛው ምዕራፍ ዘላቂ ተኩስ አቁም ማድረግን እንዲኹም በሦስተኛው ምዕራፍ ጋዛ ሰርጥን መልሶ መገንባትን ያካተተ ነው። እስራኤል የውሳኔ ሃሳቡን ቀደም ብላ እንደተቀበለችው አሜሪካ ገልጣ ነበር። ጸጥታው ምክር ውሳኔውን ማጽደቁን ተከትሎ፣ ሐማስ ውሳኔው ተፈጻሚ እንዲኾን እተባበራለኹ ብሏል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ መንግሥት በመጭው 2017 በጀት ዓመት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አጠቃላይ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። የቀጣዩ ዓመት በጀት ከዘንድሮው በጀት ጋር ሲነጳጸር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሺዴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። 451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚኾነው በጀት ለመደበኛ በጀት 283 ነጥብ 2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲኹም 236 ነጥብ 7 ቢሊየኑ ለክልሎች የበጀት ድጎማ እንደተያዘ ተገልጧል። ለመደበኛ ወጪ ከተያዘው በጀት ውስጥ፣ 128 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለመደወዝ፣ ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያዎች እንደተመደበም አሕመድ አብራርተዋል።
2፤ መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለአዲሶቹ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ለሲዳማ ክልሎች የሚመደብላቸው የፌደራል በጀት ድጎማ በቀድሞው የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፌደራል በጀት ድጎማ ቀመር መሠረት እንደሚቀጥል አስታውቋል። የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ ቆጠራ እስክታካሂድ ድረስ የፌደራል በጀት ድጎማ ቀመሩ በነበረበት እንደሚቀጥል የቀጣዩን ዓመት በጀት አስመልክተው ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል። በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ በርካታ ዞኖች ዘንድሮ ገጥሞናል ባሉት የበጀት እጥረት ሳቢያ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ለመክፈል ተቸግረው እንደከረሙ ሲገልጡ ነበር።
3፤ መንግሥት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችንና ደብዳቤዎችን እንዲጠልፍ ሥልጣን የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ረቂቅ አዋጁ፣ የወንጀል መርማሪ አካል አስቸኳይ ኹኔታ ካጋጠመው በአካባቢው ያገኘውን የዐቃቤ ሕግ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛ ዘዴዎችን እንዲጠልፍ የሚፈቅድ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ያለ ፍርድ ቤት መገናኛ ዘዴዎችን የመጥለፍ ሥልጣን አልተሰጠውም። ረቂቅ አዋጁ፣ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ በማስመሰል በፍርድ ቤት ጥፋተኛነት የተላለፈበት ግለሰብ ይከፍል የነበረውን የገንዘብ የቅጣት ጣሪያም ከ100 ሺህ ብር ወደ 500 ሺህ ከፍ አድርጎታል ተብሏል።
4፤ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ብቻ ለውጭ ገበያ ካቀረበችው ቡና 209 ነጥብ 54 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውቋል። በግንቦት ወር ብቻ 43 ሺህ 481 ቶን ቡና ወደ ውጭ መላክ ታቅዶ እንደነበር የገለጠው ባለሥልጣኑ፣ የእቅዱ 105 በመቶ እንደተመዘገበ አመልክቷል። በወሩ የተገኘው ገቢ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛው እንደኾነ ተገልጧል። ባለሥልጣኑ አገሪቱ በበጀት ዓመቱ በ11 ወራት ውስጥ ከ252 ሺህ 466 ቶን በላይ የቡና ምርት በመላክ፣ 1 ቢሊዮን 208 ሚሊዮን 73 ሺህ ዶላር አግኝታለች ብሏል። አገሪቱ ከቡና የወጪ ንግድ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችው፣ በቀይ ባሕር ላይ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ እክል በገጠመው ወቅት ላይ ነው።
5፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት በኢትዮጵያ በምግብ እጥረት ለተጎዱ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕጻናትና ሴቶች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ 276 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ዛሬ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። ኾኖም እስካኹን የተገኘው የገንዘብ ልገሳ 30 በመቶው ብቻ እንደኾነ ቢሮው ገልጧል። ቢሮው፣ በአገሪቱ ከግንቦት ወር ወዲህ በተለያዩ ወረዳዎች 46 ሺህ 800 የኮሌራ በሽተኞች እንደተመዘገቡና በ78 ወረዳዎች የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ገና እንዳልቀነሰ ጠቅሷል። በሌላ በኩል፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከኩመር እና አውላላ የስደተኞች መጠለያዎች የወጡት ሱዳናዊያን ስደተኞች፣ 1 ሺህ 300 ያህል እንደኾኑ የቢሮው መረጃ አመልክቷል።
6፤ ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት አይ ኦ ኤም፣ ፍልሰተኞችን የጫነች አንዲት ጀልባ ትናንት ከየመን ባሕር ጠረፍ አቅራቢያ ሰጥማ 49 ፍልሰተኞች እንደሞቱ አስታውቋል። ከሟቾቹ መካከል፣ 31ዱ ሴቶችና ስድስቱ ሕጻናት እንደኾኑ ድርጅቱ ገልጧል። ከ140 በላይ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች የደረሱበት ገና ያልታወቀ ሲኾን፣ 71 ሰዎች ግን በሕይወት ተረፈዋል ተብሏል። ከሱማሊያው ቦሳሶ ወደብ ከተነሳችው ጀልባ ተሳፋሪዎች መካከል፣ 145ቱ ኢትዮጵያዊያን እንዲኹም 115ቱ ሱማሊያዊያን እንደኾኑ ተገልጧል። ባለፈው ሚያዚያ ወር በኹለት ሳምንት ልዩነት ኹለት ተመሳሳይ አደጋዎች ደርሰው፣ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች የሚበዙባቸው ከ60 በላይ ፍልሰተኞች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ሰኔ 5/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቅዳሜ'ለት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት የማረቆ ብሄረሰብ ተወላጆች እንደተገደሉ ቪኦኤ ዘግቧል። በተሽከርካሪ ከገበያ በመመለስ ላይ በነበሩ መንገደኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት፣ ሌሎች ስድስት ሰዎች እንደቆሰሉ ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በዞኑ እና ልዩ ወረዳው መካከል ዘጠኝ ቀበሌዎችን ማዕከል ያደረገው የይገባኛልና የወሰን ውዝግብ፣ ካኹን ቀደምም ደም አፋሳሽ ግጭት ማስከተሉ አይዘነጋም።
2፤ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የዓለም ሥራ ድርጅት የበላይ አስተዳደር አካል አባል ኾነው ትናንት ጀኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው የድርጅቱ ጉባኤ እንደተመረጡ ኢሠማኮ አስታውቋል። የዓለም ሥራ ድርጅት ለሦስት ዓመታት በበላይነት የሚቆጣጠሩትንና የሚያስተዳድሩትን አካላት የመረጠው፣ ከአባል አገራት ሠራተኞች፣ ከመንግሥታትና ከአሠሪዎች ነው። አስተዳዳሪው አካል፣ የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተር መምረጥን ጨምሮ በድርጅቱ ፖሊሲዎችና በጀት ላይ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሥልጣን አለው። የኢሠማኮ ልዑካን ቡድን የዓለም ሥራ ድርጅት ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። ኢሠማኮ፣ የዓለም ሥራ ድርጅት በሠራተኞች መብት ዙሪያ ያወጣቸውን ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ እንድታጸድቅ ሲወተውት መክረሙ አይዘነጋም።
3፤ የአሜሪካ ደኅንነት መስሪያ ቤት ባለሥልጣናት የየመን ኹቲ ኃይሎች ለአልሸባብ ጦር መሳሪያ ለማቀበል ከቡድኑ ጋር መወያየታቸውን እንደደረሱበት ሲኤኤን ዘግቧል። አሜሪካ፣ ኹቲዎች ጦር መሳሪያ ለአልሸባብ ሰጥተው እንደኾነና ኢራን ከኹለቱ ቡድኖች ስምምነት ጀርባ እጇ ይኖርበት እንደኾነ እየመረመሩ መኾኑን መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። በተለይ ኹቲዎች ለአልሸባብ ወታደራዊ ድሮኖችንና ሚሳይሎችን ሊያስታጥቁ ይችላሉ የሚለው ስጋት የአሜሪካ ባለሥልጣናትን በከፍተኛ ደረጃ አሳስቧል ተብሏል። የኹቲ ኃይሎችና አልሸባብ አሜሪካን የጋራ ጠላታቸው ቢያደርጉም፣ በመካከላቸው ግን የርዕዮተ ዓለም ልዩነት አላቸው።
4፤ የዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ አል-ፋሽር "የጦር ወንጀል" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች" ተፈጽመው እንደኾነ አስቸኳይ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል። በከተማዋና አካባቢዋ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ በሆስፒታሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና መጠነ ሰፊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ምልክቶች እንደሚታዩ የፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ተናግረዋል። ከተማዋ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የጦርነት ተፈናቃዮችና ነዋሪዎች የሚገኙባት ስትኾን፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከተማዋን ከሱዳን ጦር ሠራዊት ለማስለቀቅ ውጊያ ከፍተዋል። ከዳርፉር ግዛቶች ፈጥኖ ደራሹ ኃይል እስካኹን ያልተቆጣጠራት፣ ሰሜን ዳርፉር ብቻ ናት። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ሰኔ 5/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተወያየበት የሚገኘው የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሠራተኞችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች ይጥሳል የሚል ትችት እንደቀረበበት ሪፖርተር ዘግቧል። የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ አዋጁ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አለመወሰኑ፣ በደመወዝ ቦርድ ውስጥ የመንግሥት ሠራተኞች ተወካዮች በአባልነት አለመካተታቸው፣ የመንግሥት መስሪያ ቤት የበላይ ሃላፊዎች ሠራተኞችን ወደ ሌላ ቦታ አዛውሮ የማሠራት ሥልጣን መያዛቸውና የወሊድ ፍቃድ በሦስት ወራት ብቻ መገደቡ ተገቢ አለመኾኑን ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሚንስቴር ሃላፊዎች መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሥራ አመራር ጉባዔ የዲስፕሊን ጥሰት የፈጸሙ ሠራተኞችን የማባረር ሥልጣን መያዙንና፣ ሠራተኞች የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት እንዳያቀርቡ የሚከለክል እንደኾነ በመግለጽ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተችተዋል ተብሏል።
2፤ የአገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር ዓቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በወረቀትና በበይነ መረብ እንደሚፈተኑ አስታውቋል። ፈተናው በበይነ መረብ የሚሰጠው፣ በተወሰኑ የተመረጡ ከተሞች ብቻ እንደኾነና ተማሪዎችም ቴክኖሎጂውን ሲለማመዱት እንደቆዩ ተቋሙ ገልጧል። አገር ዓቀፉ የ12ኛ ክፍል ፈተና በአገሪቱ የሚሰጠው፣ ከሐምሌ 3 ጀምሮ ነው። ተቋሙ፣ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለፈተናው የማይቀመጡ ተማሪዎች ይኑሩ አይኑሩ ለጊዜው አልገለጠም። በተለይ በአማራ ክልል ግጭት ባለባቸው የምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ለዘንድሮው የስድስተኛና ስምንተኛ ክፍል ክልል ዓቀፍ ፈተና ማስፈተን እንዳልቻሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በቅርቡ መግለጡ አይዘነጋም።
3፤ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር ዶይቸቨለ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ፣ የኅዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ በነበሩት የኢሕአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ፣ አበራ ንጉስ እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደሰጠ ዘገባው አመልክቷል። ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት፣ ባለፈው ሰኞ ዓቃቤ ሕግ በጠየቀባቸው የተጨማሪ የምርመራ ቀን ጥያቄ ላይ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመስማት ነበር። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ኹከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ሙከራ አድርገዋል ተብለው ነበር።
4፤ እስር ላይ የሚገኙ ሦስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንዳቀረቡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ዛሬ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ባለፈው ሳምንት የጊዜ ገደቡ ከተጠናቀቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ነበር። ጋዜጠኞቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፣ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደተያዙ፣ በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ እና ፌደራል ፖሊስ በእስር ላይ በማቆየት ሕገመንግሥታዊ መብታቸውን እንደጣሰባቸው በመግለጽ እንደኾነ ጠበቆቻቸው መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።
5፤ አሜሪካ፣ በኢትዮጵያ ከተሞች የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል የአምስት ዓመት እቅድ መንደፏን ገልጣለች። የአሜሪካው ዓለማቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም ዩኤስአይዲ አማካኝነት ለሚተገብረው ፕሮጀክት፣ አሜሪካ 8 ሚሊዮን ዶላር እንደመደበችለት የአሜሪካ ኢምባሲ ባሠራጨው መረጃ ላይ ገልጧል። ፕሮጀክቱ የሚተገበረው፣ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ በሸገር ከተማ እና በሐረሬ ብሄራዊ ክልል 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደኾነ ኢምባሲው ጠቅሷል። የፕሮጀክቱ ዓላማ፣ ኢትዮጵያ ቢያንስ 95 በመቶዎቹን በበሽታው የተያዙ ሰዎች መመርመርና ማከም እንድትችል እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግብ መሠረት ቲቢ በሽታን በአውሮፓዊያኑ 2030 እንድታስወግድ ማገዝ እንደኾነ ተገልጧል። ፕሮጀክቱ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞችን፣ እስረኞችን፣ በመጠለያዎች የሚኖሩ ሰዎችን፣ አረጋዊያንና፣ የኤችአይቪ ሕመምተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
6፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ1651 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ3084 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ5675 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ9589 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ3553 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ5824 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]