ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ታኅሳስ 8/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ሥጋት አሠራርን ከለጋሾች ጥገኝነት የሚያላቅቅ ጥናት አርቅቆ ለመንግሥት ውሳኔ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም ጉዳዩ ለሚመለከተው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ኮሚሽኑ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሸንኮራ አገዳ ምርት ተይዞ የነበረ 250 ሺህ ሄክታር መሬት ለምግብ እህል ማምረቻ ማግኘቱን ሺፈራው መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሺፈራው፣ ከዕርዳታ ሥርጭት ሥርቆት ጋር በተያያዘ፣ በኮሚሽኑ ውስጥ 375 ተጠርጣሪዎች እንደተለዩና የተወሰኑት ከሃላፊነት እንደተባረሩ ወይም ክስ እንደተመሠረተባቸው ተናግረዋል ተብሏል።
2፤ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሩሲያ መንግሥት ንብረት ከኾነው አቭቶቫዝ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ጋር መኪና ለመገጣጠም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኩባንያው ጋር የፈረመው ስምምነት፣ ላዳ ተሽከርካሪዎችን ለመጣጠምና ለማምረት የሚያስችል ነው። የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከሩሲያው ኩባንያ ጋር በመተባበር ላዳ ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም እንደሚጀምር የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚው አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ፣ ኩባንያው በሂደት ላዳዎችን በማምረት ለአፍሪካ ገበያ የማቅረብ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል።
3፤ በትግራይ ክልል በሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ መምህራን ለ17 ወራት ያለተፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ትናንት በሰላምዊ ሰልፍ መጠየቃቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። መምህራኑ፣ ውዝፍ ደመወዝ ያልተከፈላቸው፣ በ2014 እና የ2015 ዓ፣ም እንደኾነ በሰልፉ ላይ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሰልፈኞቹ፣ የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ቀደም ሲል ላበደራቸው ብድር ወለዱን እንዲሰረዝላቸው መጠየቃቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
4፤ የአፍሪካ ኅብረት ጦር የሱማሊያን ፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግሥትና ፓርላማ ጥበቃ ትናንት ሙሉ በሙሉ ለአገሪቱ ወታደሮች አስረክቧል። የሱማሊያ ጦር የኹለቱን ቁልፍ ተቋማት ጥበቃ የተረከበው፣ ለ16 ዓመታት ይጠብቁ ከነበሩት የኡጋንዳ ወታደሮች ነው። የትናንቱ የጸጥታ ጥበቃ ርክክብ፣ ኹለተኛው ዙር የኅብረቱን ወታደሮች ከአገሪቱ የማስወጣት መርሃ ግብር መጀመሪያ መኾኑን የኅብረቱ ተልዕኮ አስታውቋል። ኅብረቱ በኹለተኛው ዙር እስከ ታኅሳስ መጨረሻ ሦስት ሺህ ወታደሮቹን ለማስወጣት አቅዷል።
5፤ ቻድ አራት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ72 ሰዓታት ውስጥ እንዲወጡ ቅዳሜ'ለት አዛለች። ቻድ የሱዳን ዲፕሎማቶች እንዲወጡ ያዘዘችው፣ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ቻድ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የምትልከውን ጦር መሳሪያ ታስተላልፋለች በማለት መወንጀላቸውን ተከትሎ ነው። ሱዳንም፣ በቻድ ላይ የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ መዛቷን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሱዳን ቀደም ሲል 15 የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ዲፕሎማቶችን ማባረሯ ይታወሳል።
6፤ ኬንያ ከዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ጋር ዲፕሎማሲያዊ እሰጣገባ ውስጥ ገብታለች። ኮንጎ፣ "ኤም-23"ን ጨምሮ የተወሰኑ አማጺያን ሰሞኑን ናይሮቢ ውስጥ ተሰብስበው አዲስ ጥምረት ፈጥረዋል በማለት አምባሳደሯን ከናይሮቢ ጠርታለች። ኬንያ በበኩሏ፣ በኮንጎ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳልገባች ገልጣ፣ ናይሮቢ ውስጥ ጥምረት መስርተው መግለጫ ሰጡ የተባሉትን የኮንጎ አማጺያን ማንነት አጣራለኹ ብላለች። ኬንያና ኮንጎ የምሥራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል ሲኾኑ፣ ኬንያን ጨምሮ የቀጠናው አባል አራት የኮንጎ አማጺያንን ግስጋሴ ለመግታት በምሥራቅ ኮንጎ ያሠማሩትን ጦር በአገሪቱ መንግሥት ጥያቄ በቅርቡ አስወጥተዋል። [ዋዜማ]

በስብዕናቸውና በፖለቲካዊ አስተዳደራቸው አንድ አይነት መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ብዙ ድርሳን ተፅፎላቸዋል። የሚከተሉት ሁለት መፅሀፍት ግን ንጉሱን በቅርበት ለመረዳት የተሻሉ አስረጂዎች ናቸው። ዋዜማ ሁለቱን መፅሀፍት መሳ ለመሳ ወርዳቸዋለች። አንብቡት- tinyurl.com/3a8c995z #bookreview
Wazemaradio
ግርማዊነታቸው….በኹለት ድርሳናት በኩል - Wazemaradio
ዘመናዊት ኢትዮጵያን በኹሉም መልኳ ከቀረፇት መሪዎች መካከል አፄ ኅይለ ሥላሴ ቀዳሚ መሆናቸው ላይ፣ የዘመናዊ ታሪኮቻችን ፀሐፍት ብዙም ሙግት ውስጥ አይገቡም። የጣሊያንን የአምሥት ዓመት ወረራን ቀንሰን፣ ከ1909 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1923 ድረስ በአልጋ ወራሽነት፤ ከ1923 ዓ.ም. እስከ 1967 መግቢያ ያሉትን ዓመታት ስንቆጥር፣ በጥቅሉ ለአምሣ ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያን በጠንካራው መዳፋቸው ሥር አቆይተዋታል።…
ለቸኮለ! ሰኞ ታኅሳስ 8/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሦስት ወረዳዎች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን በተመሳሳይ ሰዓት ጥቃቶችን ማድረሱን ዋዜማ በየሥፍራው ካሉ ምንጮቿ መረዳት ችላለች። የቡድኑ ታጣቂዎች ካለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ጥቃቶቹን የተፈጸሙት፣ በዋጫሌ ወረዳ ሙከጡሪ ከተማ፣ በደብረ ሊባኖስ ወረዳ ደብረጽጌ ከተማ እንዲኹም በያያ ጉለሌ ወረዳ ፊታል ከተማ እንደኾነ ምንጮች ተናግረዋል። የጥቃቱ ዓላማ በዋናነት በየማረሚያ ቤቱ ያሉ የታጣቂ ቡድኑን አባላት ለማስፈታት ያለመ እንደነበር ዋዜማ ሰምታለች። ኾኖም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከቡድኑ ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ፣ የቡድኑ አባላት እስረኞቹን ማስፈታት ሳይችሉ እንደቀሩ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ በደብረጽጌ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍን በኃይል ሰብረው በመግባት ኮምፒውተሮችንና ሌሎች ንብረቶችን ማውደማቸውን የገለጡት ምንጮች፣ ኹለት የአዋሽ ባንክ የጥበቃ ሠራተኞችን ደሞ አፍነው መሠወራቸውን ጠቅሰዋል። በተኩስ ልውውጡ፣ በርካታ የታጣቂ ቡድኑ አባላት እንደተገደሉ ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች።
2፤ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ አራተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ በሚንስቴሮች ደረጃ አዲስ አበባ ውስጥ መጀመራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። አራተኛው ዙር ድርድር የተጀመረው፣ የኢትዮጵያ እና ግብጽ መሪዎች ባለፈው ሐምሌ በግድቡ ውሃ ሙሌትና አስተዳደር ዙሪያ ስምምነት ባልተደርሰባቸው ነጥቦች ላይ በአራት ወራት ውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ የተስማሙትን ስምምነት መሠረት በማድረግ እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። ዛሬ ከተጀመረው የሚንስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ቀደም ብሎ፣ የሦስቱ አገራት የቴክኒክ ባለሙያዎች የአንድ ቀን ውይይት ማድረጋቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ሚንስቴሩ፣ ዛሬ የተጀመረው ድርድር ካኹን ቀደም የተካሄዱ ድርድሮችን በማጎልበት እንደሚካሄድም ጠቅሷል። ሚንስቴሩ፣ ኢትዮጵያ ከድርድሩ ፍትሃዊና ምክንያታዊ በኾነ የውሃ አጠቃቀም መርኾ መሠረት በሙሉ መግባባት ላይ የተመሠረተ ውጤት ትጠብቃለች ብሏል።
3፤ የባሕርዳር ከተማ ምክር ቤት በግል የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ ላልተወሰነ ጊዜ ጭማሪ እንዳይደረግ የሚከለክል ጊዜያዊ ደንብ አጽድቋል። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ትልቅ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮት ኾኗል ያለው ምክር ቤቱ፣ የኪራይ ጭማሪ እገዳውን የጣለው መንግሥት በጥናት ላይ የተመሠረተ ቋሚ የኾነ ሕግና ደንብ እስኪያዘጋጅ እንደኾነ ገልጧል። ይህንኑ ደንብ ተከትሎ፣ በከተማዋ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ የሚያከራየውን ቤት ብዛት ጉዳዩ ለሚመለከተው አስተዳደር ማሳወቅ እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል። ደንቡን ተላልፈው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ በሚያደርጉ አከራዮች ላይ፣ በአንድ ክፍል መኖሪያ ቤት 10 ሺህ ብር እንዲኹም በሙሉ ግቢ ቤት 25 ሺህ ብር መቀጮ እጥላለኹ በማለት ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል።
4፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት በአማራ ክልል ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በሰሜን ምስራቅ ማዕከላዊ የጸጥታ ዕዝ በቁጥጥር ሥር የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ አያያዝ እና ከዚህ ቀደም የሰጣቸውን ግብረ መልሶች አፈጻጸም ለመገምገም ኹለተኛ ዙር ምልከታ ማድረጉን አስታውቋል። የቦርዱ አባላት፣ ጮሪሳ የማቆያ ማዕከል ተገኝተው ከተጠርጣሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን አጣርቶ ለፍርድ ከማቅረብና የወንጀል ተሳትፎ የሌላቸውን ደሞ በማሰናበት ረገድ መጓተቶች አሉ በማለት ቅሬታ ማቅረባቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል። ተጠሪጣሪዎቹ የምርመራ ሂደቱ እንዲፋጥንላቸው በአጽንዖት መጠየቃቸውን ምክር ቤቱ ጠቅሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አዝመራ አንዴሞ፣ ተጠርጣሪ የወንጀል ተሳታፊዎችን ፍርድ ቤት የማቅረብ ጉዳይ ባስቸኳይ እንዲፋጠን ለጸጥታ ዕዙ ማሳሰባቸው ተመላክቷል። በተጠቀሰው ማቆያ ስንት ተጠርጣሪዎቹ እንደሚገኙ ግን ምክር ቤቱ አልገለጠም።
5፤ ዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውሱ እንደቀጠለ ነው ሲሉ ባለፈው ዓርብ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ በክልሉ አስገድዶ መድፈርና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች አኹንም መቀጠላቸው እንዳስደነገጣቸው ገልጸዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ በትግራይ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚኾኑ ሴቶች እንደተደፈሩ የሚያሳይ መረጃ መኖሩን ገልጸዋል። ከጾታዊ ጥቃት ከተረፉት ሴቶች መካከል፣ 80 በመቶዎቹ ተገደው ስለመደፈራቸው እንደተናገሩና ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶዎቹ የተደፈሩት በታጣቁ ቡድኖች መኾኑን ሪፖርት ማድረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ በትግራይ የተፈጸመውን ዓይነት ጾታዊ ጥቃት ከዚህ ቀደም ዓይቼ አላውቅም ብለዋል። በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት የጤና ተቋማት ጉዳትና ውድመት እንደደረሰባቸውና ከኹለት ሳምንት በፊት በአንድ አንቡላንስ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አምስተ ሰዎች መገደላቸውንም ዶክተር ቴዎድሮስ ገልጸዋል።
6፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለኹለት ፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ እውቅና መስጠቱን አስታውቋል። ቦርዱ ሕጋዊ ማረጋገጫ የሰጠው፣ ለትንሳዔ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ እና ለዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ነው። ቦርዱ ለዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ሕጋዊ የአገር ዓቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለፈው ታኅሣሥ 4 ቀን መስጠቱን ጠቅሷል። ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ በበኩሉ፣ በትግራይ ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለው ሕጋዊ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከቦርዱ ተሰጥቶታል።
7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ8610 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ9783 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ9910 ሳንቲምና መሸጫው 69 ብር ከ3508 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ1119 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ3341 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ታኅሳስ 9/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ንግግር ላይ መኾኗን ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። የአገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ትንበያዎች፣ የውጭ ፋይናንስ ፍላጎት ማለትም አይ ኤም ኤፍ እና ሌሎች የልማት አጋሮች ሊሰጡ የሚችሉት ብድርና ድጋፍ ገና ውይይት እየተደረገባቸው መኾኑን ድርጅቱ መናገሩን ዜና ምንጩ አመልክቷል። አገሪቱ፣ ከዓለም ባንክ ሌላ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ማግኘት እንደምትፈልግም ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት ባለፈው ሳምንት ከዓለማቀፍ ቦንድ ገዢዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ፣ ከጥር እስከ መጋቢት ከአይ ኤም ኤፍ ጋር የብድር ስምምነት ላይ እደርሳለኹ ብሎ እንደሚያስብ ገልጧል ተብሏል። ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ እስከ 2027/28 ዓ፣ም ድረስ 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ክፍተት እንደሚኖርበት መስማቱንም ሮይተርስ ጠቅሷል።
2፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሚያቀርቡለትን የምርጫ ቦርድ ዕጩ ሰብሳቢ ሹመት እንደሚያጸድቅ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ፣ ኹለት እጩዎችን መርጦ ከሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ማቅረቡ ይታወሳል። ምክር ቤቱ በዕለቱ፣ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሹመት ጭምር እንደሚያጸድቅ ገልጧል።
3፤ የኢትዮ ቻይና የወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ከ10 የቻይና ኩባንያዎች የተውጣጡ 22 አባላትን ያካተተ መኾኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ልዑካን ቡድኑ፣ የኢትዮጵያን የእንስሳት እና ግብርና ውጤቶች በቻይና ገበያ የማስተዋወቅ ዓላማ እንዳለው መናገሩን ሚንስቴሩ ጠቅሷል።
4፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት አራዝሟል። የክልሉ መንግሥት ቀነ ገደቡን ያራዘመው፣ በሕዝቡ ጥያቄ መሠረት መኾኑን ገልጧል። ባለፈው ሳምንት በቀረበው የሰላም ጥሪ መሠረት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወደ ጊዜያዊ ማዕከላት እየገቡ መኾኑና የገለጠው የክልሉ መንግሥት፣ በፍቃደኝነት ወደ ማዕከላት የገቡትን ታጣቂዎች ብዛት ወደፊት እገልጣለኹ ብሏል።
5፤ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ የነበሩ 118 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ከእስር ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል። ፍልሰተኞቹ፣ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው መኾናቸውን ኢምባሲው ጠቅሷል። ኢምባሲው ካለፈው ኅዳር ወዲህ በጠቅላላው 448 ፍልሰተኞችን ከታንዛኒያ ወደ አገራቸው መልሷል። ፍልሰተኞቹ በወህኒ ቤት ቆይታቸው፣ ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ችግሮች ተጋልጠው እንደቆዩ ኢምባሲው ጠቅሷል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ታኅሳስ 9/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የመንግሥት የጸጥታና ደኅንነት ግብረ ኃይል በሱማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ፣ ፊቅ፣ ዋርዴርና ቢኬ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 14 የአልሸባብ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት፣ ከጦር መሳሪያዎች፣ ቦንቦች፣ ሌሎች ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ሰነዶች ጋር መኾኑን ግብረ ኃይሉ ገልጧል። በሱማሌ ክልል ውስጥ የሽብር ቡድን አባላትን ሲመለምል፣ ሲያደራጅና ሲያስተባብር ነበር የተባለው ዓሊ አብዲ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው፣ በሞያሌ በኩል ሊወጣ ሲል እንደኾነ ተገልጧል።
2፤ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ኾነው ተሹመዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለቦርዱ ሰብሳቢነት በዕጩነት ያቀረቧቸውን ሜላተወርቅን ሹመት ያጸደቀው ባንድ ድምጸ ተዓቅቦ ነው። አዲሷ ተሿሚ፣ ከየካቲት 2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 2015 ዓ.ም ድረስ የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኾነው አገልግለዋል። ሜላተወርቅ፣ የቦርዱ ዕጩ ሰብሳቢዎች መልማይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ካቀረባቸው የመጨረሻዎቹ ኹለት ዕጩዎች መካከል አንዷ ነበሩ። ምክር ቤቱ በተጨማሪም፣ ጌትነት ታደሠ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲኹም መሳፍንት ተፈራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኾነው እንዲሾሙ የቀረቡለትን የውሳኔ ሃሳቦችም አጽድቋል።
3፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአምስት አዳዲስ ቦይንግ አውሮፕላኖች መግዣ ከአሜሪካው ሲቲ ባንክ የ450 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራርሟል። አየር መንገዱ ከግዙፉ ሲቲ ባንክ በሚያገኘው ብድር፣ ሦስት ቦይንግ 737-8 ማክስ የመንገደኞች አውሮፕላኖችንና ኹለት 777F ቦይንግ ካርጎ አውሮፕላኖችን እንደሚገዛ ተገልጧል። አየር መንገዱ አምስቱን አውሮፕላኖች በተያዘው ወር ይረከባል ተብሏል። አየር መንገዱ በባንኩ ብድር አምስቱን አውሮፕላኖች መግዛቱ፣ የጠቅላላ አውሮፕላኖቹን ብዛት 150 ያደርሰዋል። አየር መንገዱ፣ 67 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ለመግዛት በቅርቡ ከኩባንያው ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
4፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ የምክር ቤቱ አባል የኾኑትን ታረቀኝ ደግፌን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። ምክር ቤቱ የታረቀኝን ያለመከሰስ መብት ያነሳው፣ በ7 ተቃውሞ እና በ5 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው። ታረቀኝ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ ወንጀል፣ ኹከትና ግጭት በማስነሳት የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ በማድረግ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስ፣ ንብረት እንዲወድምና ሰዎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ወንጀሎች በመጠርጠራቸው እንደኾነ ተገልጧል።
5፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎችና ጠበቃዎች ኮሚቴ አባልና የሕግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ ትናንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመንገድ ተወስደው መታሠራቸውን የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል። ቤተክርስቲያኗ፣ የሕግ ባለሙያው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ያቋቋመውን የቤተክርስቲያኗ የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ በመምራት፣ ቤተክርስቲያኗን ወክለው የሕግ አገልግሎት ሲያበረክቱ መቆየታቸውን ገልጣለች። ጠበቃ አያሌው፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከ"ሕገወጥ የጳጳሳት ሹመት" ጋር በተያያዘ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራቸው ለተፈናቀሉ ምዕመናን፣ ነጻ የሕግ ጥብቅናና የሕግ ምክር አገልግሎት መስጠታቸውንም ቤተክርስቲያኗ ጨምራ ጠቅሳለች።
6፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሰሜን ምሥራቅ ሱዳን የኤል ጀዚራ ግዛት ዋና ከተማና የአገሪቱ ጦር ሠራዊት አንደኛው ክፍለ ጦር ዋና ማዕከል የነበረችውን ዋድ ማዳኒ ከተማን ትናንት ተቆጣጥሯል። የአገሪቱ ኹለተኛዋ ትልቋ ከተማ ዋድ ማዳኒ፣ አብዛኞቹ ከካርቱም የተፈናቀሉ ከ186 ሺህ በላይ የጦርነቱ ተፈናቃዮች የተጠለሉባት ናት። ኾኖም የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ተዋጊዎች በሦስት ቀናት ከባድ ውጊያ ወደ ከተማዋ መጠጋታቸውን ተከትሎ፣ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከከተማዋ ሸሽተዋል። ጦርነቱ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ከተጀመረ ጀምሮ ከውጊያ ነጻ የነበረችው ዋድ ማዳኒ፣ የዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች የሰብዓዊ ዕርዳታ ማዕከል አድርገዋት ቆይተዋል። ገዚራ ግዛት፣ በእርሻ ምርት በአገሪቱ ቀዳሚ ናት።
7፤ በቀይ ባሕር ላይ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከ10 አገራት የተወጣጣ ጥምር የጸጥታ ኃይል መቋቋሙን ፔንታጎን አስታውቋል። ጥምር ኃይሉን ያቋቋሙት፣ አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ባሕሬን፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሆላንድ፣ ኖርዌይ፣ ስፔንና ሲሸልስ ናቸው። ጥምር የጸጥታ ኃይሉ የተቋቋመው፣ የየመን ኹቲ ኃይሎች በቀይ ባሕር ላይ በሚንቀሳቀሱ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው በሚሏቸው የንግድ መርከቦች ላይ ተደጋጋሚ የድሮንና ሚሳይል ጥቃቶች ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ጥምር ኃይሉ፣ በኤደን ባሕረ ሰላጤ ለሚያልፉ የንግድ መርከቦች የደኅንነት ከለላ እንደሚሰጥ ፔንታጎን ገልጧል።
8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ8795 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ9971 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ5653 ሳንቲምና መሸጫው 68 ብር ከ9166 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ60 ከ9534 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ1725 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]
https://youtu.be/wYNkpxSUG5I?si=3lgLx5_8hwiUaPW7

YouTube
ኢትዮጵያ ለ3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ድርድር ላይ ናት (ለቸኮለ! ታኅሳስ 9)
1-ኢትዮጵያ ለ3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ድርድር ላይ ናት
2-ዛሬ የተሰሙት ሹመቶች
3-የአየር መንገዱ ብድር
4-የምክር ቤት አባሉ መብት መነሳት
5-የቤተ ክርስቲያኗ ጠበቃ ታሰሩ
6-ለቀይ ባሕር የተቋቋመው ጥምር ጦር
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ…

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ታኅሳስ 10/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ግብጽ አራተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ ድርድር መጠናቀቅ አስመልክታ ያወጣችው መግለጫ "የተመድና አፍሪካ ኅብረት ቻርተሮችን የጣሰ" እና "የኢትዮጵያን አቋም አዛብቶ ያቀረበ ነው" በማለት ከሷል። ሚንስቴሩ፣ በግድቡ ላይ እስካኹን በተደረጉት ድርድሮች የግብጽ "የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ" ከስምምነት ላይ እንዳይደረስ እንቅፋት ኾኗል ብሏል። ድርድሮቹ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝን ውሃ እንዳትጠቀም ለማገድ ያለሙ አይደሉም ያለው ሚንስቴሩ፣ ኢትዮጵያ ወደፊትም "የእኩልነትና ምክንያታዊነት" መርኾዎችን ባከበሩ አኳኋን የወንዙን ውሃ መጠቀሟን ትቀጥላለች በማለት የመንግሥትን አቋም ገልጧል።
2፤ ግብጽ በአዲስ አበባ የተካሄደው አራተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ያለ ውጤት መጠናቀቁን አስታውቃለች። ግብጽ፣ ድርድሩ የከሸፈው፣ ኢትዮጵያ "ቴክኒካዊና ሕጋዊ መፍትሄዎችን በተደጋጋሚ ውድቅ በማድረጓ ነው" ብላለች። ግብጽ፣ ኢትዮጵያ ድርድሩን መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ኹኔታ እስኪቀየር ጊዜ ለመግዛት እየተጠቀመችበት ነው በማለትም ከሳለች። የግድቡን ውሃ አሞላልና አስተዳደር በቅርበት እንደምትከታተል የገለጠችው ግብጽ፣ በግድቡ ምክንያት አንዳች ጉዳት ከደረሰባት የውሃና ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ወደኋላ እንደማትል አስታውቃለች።
3፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ የውጭ ዜጎች ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ መኾኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ባንኩ የውጭ ሠራተኞቹን ከአገሪቱ ለማስወጣት የወሰነው፣ ባለፈው ጥቅምት የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በኹለት ባልደረቦቹ ላይ አካላዊ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ እንደኾነ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ባንኩ ሠራተኞቹን ከአገሪቱ መቼ እንደሚያስወጣ ግን ምንጮቹ ቁርጥ ያለ ጊዜ እንዳልጠቀሱ ዘገባው አመልክቷል። ባንኩ፣ በክስተቱ ዙሪያ ለመንግሥት ቅሬታውን ማቅረቡንና መንግሥትም ድርጊቱን እንደሚያጣራ ባለፈው ጥቅምት ገልጦ ነበር። ባንኩ፣ በአገሪቱ በ308 ሚሊዮን ዶላር የሚተገበሩ ስምንት ፕሮጀክቶች አሉት።
4፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ያጋጠሙትን ውጣ ውረዶች ተከትሎ ሌሎች የቴሌኮም ኩባንያዎች በዘርፉ ለመሠማራት ያላቸው ፍላጎት መቀዛቀዙን ሮይተርስ ዘግቧል። የውጭ ኩባንያዎች በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ ፍላጎታቸው የቀነሰው፣ በጸጥታ ችግሮች፣ መንግሥት ለዘርፉ ባወጣቸው የሕግ ማዕቀፎች ላይ ለውጦችን በማድረጉና መንግሥት የቴሌኮም ዘርፉን ለእውነተኛ ውድድር ለመክፈት ያለው ቁርጠኝነት አጠያያቂ በመኾኑ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። መንግሥት ለኹለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ የጀመረውን ሂደት ማቋረጡ ይታወሳል። መንግሥት ዘርፉን ለውድድር ሲከፍት፣ ለቴሌኮም ኩባንያዎች ከቀረጥ ነጻ ዕድልና ለተወሰነ ጊዜ የገቢ ግብር እፎይታ ሰጥቶ የነበረ ቢኾንም፣ በተሻሻለው ሕግ ላይ ግን ማበረታቻዎቹ እንዳልተጠቀሱ ዜና ምንጩ አውስቷል።
5፤ ትናንት በመቀሌ ጉብኝት ያደረገው የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት የኤርትራ ጦር እንዲወጣ መጠየቁን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጌታቸው፣ ኅብረቱ የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲኾን ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የልዑካን ቡድኑ መሪ ኢዛቤል ዋይዝለር፣ አውሮፓ ኅብረት በጦርነቱ ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቀዋል ተብሏል።
6፤ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ትናንት ከቀትር በኋላ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር ዶይቸቨለ ዘግቧል። በእሳት አደጋው ሳቢያ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እንዲኹም ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎች እንደተስተጓጎሉ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። የእሳት አደጋው የተከሰተው፣ በአውሮፕላን መንደርደርያው ሜዳ አካባቢ መኾኑን ከዓይን እማኞች መስማቱን ዜና ምንጩ ጨምሮ አመልክቷል። ኾኖም የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽንም ኾነ የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን፣ በአውሮፕላን ማረፊያው ተከስቶ ነበር ስለተባለው የእሳት አደጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያሉት ነገር የለም። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ታኅሳስ 10/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣ ግብጽ በሕዳሴ ግድብ ድርድር "ተቀባይነት የሌላቸውን የቅኝ ግዛት ውሎች" የሙጥኝ ብላ ይዛለች በማለት ከሰዋል። ኢትዮጵያ ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ለመድረስ ዝግጁ መኾኗን ዛሬ አራተኛውን ዙር የግድቡን ድርድር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ የገለጡት አምባሳደር ስለሺ፣ ግብጽ ግን ትናንት ባወጣችው መግለጫ በድርድሩ ላለመቀጠል ወስናለች በማለት ወቅሰዋል። አምባሳደር ስለሺ፣ ኢትዮጵያ የወንዙን ውሃ በፍትሃዊነትና በዕኩልነት መርህ፣ መጠቀም በሚያስችል አኳኋን የመጠቀም ፍላጎቷንና አቋሟን ማንጸባረቋንም ገልጸዋል። አምባሳደር ስለሺ አያይዘውም፣ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 94 በመቶ መድረሱንና የኮንክሪት ግንባታውም በቀጣዩ ዓመት መስከረም እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
2፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለማቀፍ ሠራተኞቹን ባስቸኳይ ከኢትዮጵያ ለማስወጣት መወሰኑ በኢትዮጵያ ባሉት ፕሮጀክቶቹ ላይ መስተጓጎል ሊፈጥር እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። ባንኩ በኢትዮጵያ በገንዘብ የሚደጉማቸው 22 የልማት ፕሮጀክቶች 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ናቸው። ባንኩ ዓለማቀፍ ሠራተኞቹን ለማስወጣት የወሰነው፣ ከአንድ ወር በፊት የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በኹለት ዓለማቀፍ ሠራተኞቹ ላይ ዲፕሎማቲክ መብቶችን በጣሰ መልኩ "ያላግባብ እስር" እና "አካላዊ ጥቃት" መፈጸማቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት በክስተቱ ዙሪያ የምርመራ ውጤቱን ስላላሳወቀው እንደኾነ ገልጧል። ዓለማቀፍ ሠራተኞቹ ወደ ሌላ አገር ተዛውረው እንደሚቆዩ የጠቆመው ባንኩ፣ መንግሥት የምርመራ ውጤቱን ይፋ ካደረገ ግን ሠራተኞቹ እንደሚመለሱ ገልጧል። ባንኩ ከኢትዮጵያ የሚወጡትን ሠራተኞቹን ብዛት አልጠቀሰም። መንግሥት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በባንኩ ውሳኔ ላይ በይፋ የሰጠው አስተያየት የለም።
3፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሳያማክሩኝ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስሾማቸው "የሕግ ጥሰት" ነው ማለቱን ሪፖርተር ዘግቧል። በ2011 ዓ፣ም የወጣው የምርጫ ቦርድ ማሻሻያ አዋጅ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ዕጩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ስም ዝርዝር ከመልማይ ኮሚቴ፣ ከተቀበለ በኋላ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በዕጩዎች ዙሪያ እንዲመካከር መደንገጉን የጋራ ምክር ቤቱ ገልጧል ተብሏል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሜላተወርቅ ኃይሉ የቦርዱ ሰብሳቢ ኾነው እንዲሾሙ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ፣ ሰኞ'ለት ማጽደቁ ይታወሳል።
4፤ የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የብሄራዊ ሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል። ሚንስትሮች ምክር ቤት፣ ረቂቅ አዋጁ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የላቀ ተግባር ለሚያከናውኑ ዜጎችና ሌሎች ግለሰቦች እውቅና ለመስጠትና የሥራ ፈጠራ እንዲጎለብት ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጧል። ረቂቅ አዋጁ፣ በሕገመንግሥቱ የተደነገገውን የሜዳይ፣ ኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ እንደሚዘረጋ ሚንስትሮች ምክር ቤት ጨምሮ ገልጧል። ምክር ቤቱ፣ የዕረፍት ቀናትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅም አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡
5፤ የትግራዩ ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት የአልጀርስ ስምምነትን አስመልክቶ ያወጡትን መግለጫ አውግዟል። የአልጀርሱ ስምምነት ዋጋ ቢስ ነው ያለው ፓርቲው፣ ኤርትራ ከፈረንጆች 2021 ጀምሮ ትግራይን በመውረር የአልጀርሱን ስምምነት በግልጽ ጥሳለች ብሏል። ፓርቲው፣ የአልጀርሱ ስምምነት በሰሜናዊ ትግራይ የሚገኘውን የኢሮብ ብሄረሰብ ከኹለት የከፈለና ዓለማቀፍ ሕጎችን የጣሰ ነው በማለት የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን አመልክቷል። ፓርቲው የኤርትራ ኃይሎች በፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት፣ በአፋጣኝ ከትግራይ ለቀው እንዲወጡም ጠይቋል። አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የአልጀርሱን ስምምነት ማክበራቸው ከምንጊዜውም በላይ አኹን አስፈላጊ ነው በማለት አገራቱ ለስምምነቱ ተገዢ እንዲኾኑ መጠየቁ ይታወሳል።
6፤ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ሽግግር ተልዕኮ ዛሬበሒርሸበሌ ግዛት የሚገኝ አንድ የጦር ሠፈሩን ለሱማሊያ ጦር ሠራዊት አስረክቧል። ኅብረቱ ለአገሪቱ ጦር ሠራዊት ያስረከበው ጦር ሠፈር፣ በኅብረቱ ተልዕኮ ሥር የቡሩንዲ ወታደሮች ይዞታ የነበረ ነው። የኅብረቱ ተልዕኮ ኹለተኛውን ዙር ወታደሮቹን ከሱማሊያ የማስወጣት መርሃ ግብር ባለፈው ዕኹድ የጀመረው፣ የአገሪቱን ቤተመንግሥትና ፓርላማ ጥበቃ ከኡጋንዳ ወታደሮች ወደ ሱማሊያ ጦር በማስተላለፍ ነበር። ኅብረቱ በኹለተኛው ዙር መርሃ ግብር፣ ሦስት ሺህ ወታደሮቹን እስከተያዘው ወር መጨረሻ ከአገሪቱ ለማስወጣት አቅዷል።
7፤ የአሜሪካው ፔንታጎን ከሦስት ዓመት በፊት ኬንያ በሚገኘው የአሜሪካው "ማንዳ ቤይ" ወታደራዊ ጦር ሠፈር ላይ አልሸባብ የፈጸመውን የሽብር ጥቃት አቀነባብሯል ያለውን ሞዓሊም አይማን በድሮን ጥቃት መግደሉ ተገልጧል። አሜሪካ በምሥራቃዊ ኬንያ በጦር ሠፈሯ ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት፣.አንድ ውፕታደርና ኹለት ሲቪል ኮንትራክተሮች ተገድለውባታል። አሜሪካ አይማን ያለበትን አድራሻ ለጠቆመኝ፣ 10 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እሰጣለኹ ብላ ቃል ገብታ ነበር። አይማን የተገደለው፣ በደቡባዊ ሱማሊያ "ጂሊብ" በተባለ ቦታ እንደኾነ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ8901 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 57 ብር ከ0079 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ8770 ሳንቲምና መሸጫው 69 ብር ከ2345 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ1438 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ3667 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]
https://youtu.be/Y45qa07tJhc?si=en0q2fNLhCO4Av7_

የአፍሪካ ልማት ባንክ ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው (ለቸኮለ! ታኅሳስ 10)
1-የአፍሪካ ልማት ባንክ ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው
2-ኢትዮጵያ ግብፅን ወቀሰች
3-ስለ አዲሲቷ ተሿሚ የተሰማው
4-የሚንስትሮች ምክር ቤት አዲስ ረቂቅ
5-ፓርቲው ስለ አሜሪካ እና ኅብረቱ መግለጫ
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ ስርጭት…

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ታኅሳስ 11/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ በፈረስ ቤት ከተማ ዙሪያ ከማክሰኞ ጧት ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል። የፋኖ ታጣቂዎች ማክሰኞ እኩለ ቀን ላይ የወረዳውን ዋና ከተማ ፈረስ ቤትን በቁጥጥር ስር አውለው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። መከላከያ ሠራዊት ከትናንት ጧት ጀምሮ ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር ማጥቃት መክፈቱንና ከከተማዋ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መዋሉን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በምዕራብ ጎጃም ዞን በኹለቱ ወገኖች መካከል የተኩስ ልውውጡ የቀጠለው፣ የክልሉ መንግሥት ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ተጨማሪ ሰባት ቀናት መስጠቱን በገለጠ ማግስት ነው።
2፤ የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ታጣቂዎች በሰላም ጥሪው መሠረት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እየተመለሱ መኾኑን አስታውቋል። ቢሮው እስከ ትናንት ድረስ 5 ሺህ 216 ታጣቂዎች ወደ ጊዜያዊ መቀበያ ማዕከላት ገብተዋል ብሏል። የክልሉ መንግሥት በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ በሳምንቱ መግቢያ ላይ ተጨማሪ ሰባት ቀናት መስጠቱ ይታወሳል።
3፤ በአፋር ክልል ሰሜኑን በኢሳ ሱማሌ እና አፋር ጎሳዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ዋዜማ ሰምታለች። ግጭቱ የተቀሰቀሰው፣ በዞን 6 ገራኒ በተባለ ወረዳ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ግጭቱን ተከትሎ፣ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውጥረቶች እንዳሉ ምንጮች ገልጸዋል። የግጭቱ መነሻ ምን እንደኾነ ወይም በግጭቱ ስለደረሰው ጉዳት ዋዜማ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻለችም። የኹለቱ ጎሳዎች ግጭት ለዓመታት የቀጠለ ሲኾን፣ በተለያዩ ጊዜያትም ለበርካቶች ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት ኾኗል።
4፤ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ የአገሪቱን ቀሪ ቁልፍ ቦታዎች ማለትም የሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያንና የሞቃዲሾ ወደብን መጠበቅ እንደሚቀጥል የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኅብረቱ ወታደሮች የኹለቱን ቦታዎች ጥበቃ ለሱማሊያ መንግሥት የሚያስተላልፉት፣ ኅብረቱ በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ወታደሮቹን ጠቅልሎ ሲያስወጣ እንደኾነ የመንግሥት ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የኅብረቱ ተልዕኮ ባለፈው ዕሁድ በጀመረው ኹለተኛው ዙር ወታደሮችን የማስወጣት መርሃ ግብር፣ የፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግሥቱንና ፓርላማውን ጥበቃ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ማስረከቡ ይታወሳል።
5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ወታደሮቹ የአገሪቷን ኹለተኛ ትልቅ ከተማ ዋድ ማዳኒን እንዴት ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል አስረክበው ሊወጡ እንደቻሉ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከተማዋን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ በሱዳን ጦር ሠራዊት ላይ ትችቶች በርትተዋል። በግጭቱ ሳቢያ፣ 250 ሺህ ሰዎች ከከተማዋ እንደተፈናቀሉ ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ዋድ ማዳኒ የምትገኝበት አል ጀዚራ ግዛት፣ የአገሪቱ ዋና የግብርና ምርት ማዕከል ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሐሙስ ታኅሳስ 11/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የብቃት መመዘኛ ፈተና ነገ እንደሚጀመር ዋዜማ ፈተናውን ከሚወስዱ ሠራተኞች ሰምታለች። ዋዜማ ባገኘችው መረጃ ሠራተኛ፣ የብቃት መመዘኛው ፈተናውን ነገ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እንዲኹም አራት ኪሎ አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ፈተናውን ይወስዳሉ። ሠራተኞች እስከ ጧቱ 1:00 ሰዓት የመፈተኛ ቦታቸውን እንደሚያውቁና 5:00 ሰዓት ላይ በአውቶብሶች ወደ ፈተና ጣቢያዎች እንደሚወሰዱ ተነግሯቸዋል። ለመሬት ልማት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል የተባለው የብቃት መመዘኛ ግን፣ ግልጽ ባልኾነ ምክንያት ተራዝሟል መባሉን ሠራተኞቹ ለዋዜማ ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ፣ የብቃት መመዘኛ ፈተናውን የሚሰጠው አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ባደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ነው።
2፤ ተቃዋሚው እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች እየሰጠው የሚገኘው ምዘና እንዲኹም በምዘናው የሚሰጠው የሠራተኞች ምደባ ባስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል። ፓርቲው፣ ፈተናና ምዘናው መንግሥት የማይፈልጋቸውን ሠራተኞች በማስወገድ የሚፈልጋቸውን ለመተካት ኾን ብሎ ያዘጋጀው ስልት መኾኑን ለመገመት አያዳግትም ብሏል። ከፈተናው በፊት የፈተናው መልስ በየትምህርት ቤቶች አስቀድሞ ተለጥፎ መገኘቱን ከመረጃ ምንጮቹ መረዳቱን የጠቀሰው ፓርቲው፣ ይህን ተከትሎ ፈተናው ለጊዜው መቋረጡን እንደደረሰበት ገልጧል። ፓርቲው፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እየሠሩ የሚገኙ ሠራተኞች የብሄር ማንነታቸውን እንዲሞሉ የሚያስገድደው ቅጽ ባስቸኳይ እንዲቆምም ፓርቲው ጠይቋል።
ፓርቲው በዚኹ መግለጫው፣ የከተማዋ አስተዳደር ሠራተኞች የፈተና አሰጣጡን፣ ምደባውንና "ብሄር" የሚጠይቀውን ቅጽ በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወሙ ጥሪ አድርጓል።
3፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ አማኑኤል ከተማ ዙሪያ ከትናንት ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንድ ነዋሪ፣ ከኹለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ጠቁመው፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ግን ለጊዜው ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጠዋል። ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በከተማዋ ተኩስ መኖሩንና ኹሉም የመንግሥትና የግል ተቋማት ዝግ መኾናቸውን ዋዜማ ተረድታለች። በተኩስ ልውውጡ ሳቢያ፣ ከደብረማርቆስ ወደ ባሕርዳር የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከተቋረጠ ሳምንታት እንዳስቆጠረ ምንጮች ጠቁመዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማና አካባቢዋም፣ ላለፉት ሦስት ቀናት በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ መካሄዱን ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች። ነዋሪዎቹ በግጭቱ በውል ባልታወቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል።
4፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደበረት ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ካቺሲ ከተማ የተጠለሉ 10 ሺህ 590 ተፈናቃዮች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮች ሰምታለች። ተፈናቃዮቹ የመንግሥት ኃይሎችና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን ከሚያደርጉት ውጊያ በመሸሽ ከዘመድና ከኪራይ ቤቶች እንደተጠለሉ ምንጮች ጠቁመዋል። ተፈናቃዮቹ ከወረዳው 22 ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ሲኾኑ፣ መንግሥትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚያደርጉላቸው ሰብዓዊ ዕርዳታ በመቋረጡ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ዋዜማ ተረድታለች። ባኹኑ ወቅት ሦስቱን የከተማ ቀበሌዎች ጨምሮ በወረዳው ስር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ከሚገኙት 12 ቀበሌዎች በስተቀር፣ ሌሎቹ የከፋ የሰላም ችግር እንዳለባቸውና አርሶ አደሮችም የደረሱ ሰብሎቻቸውን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ምንጮች ተናግርዋል። ዋዜማም ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጌቱ ታደሠ በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ብትደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ሃሳባቸውን ማካተት አልቻለችም።
5፤ አውሮፓ ኅብረት በቀይ ባሕር ላይ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከ10 አገራት የተወጣጣውን ጥምር የጸጥታ ኃይል እንደሚቀላቀል አስታውቋል። የኅብረቱ የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል፣ የኅብረቱ የፖለቲካና ደኅንነት ኮሚቴ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ጥምር የጸጥታ ኃይሉ የየመን ኹቲ ኃይሎች በቀይ ባሕር በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ የሚፈጸሙትን ጥቃት በጋራ ለመከላከል መወሰኑን አስታውቀዋል። አውሮፓ ኅብረት ጥምር ኃይሉን ለመቀላቀል መወሰኑ፣ ሌሎች አገራትም በአሜሪካ የሚመራውን የጋራ የጸጥታ ኃይል እንዲቀላቀሉ ሊያግዝ ይችላል ተብሏል። ብሪታንያ ጥምር ኃይሉን የተቀላቀለች ሲኾን፣ ፈረንሳይም ጥምር ኃይሉን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ ተገልጧል።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ9091 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 57 ብር ከ0273 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ5745 ሳንቲምና መሸጫው 68 ብር ከ9260 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ1646 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ3879 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።[ዋዜማ]
https://youtu.be/GtufiI_N57Q?si=L-99oYNoImxM1P_y

የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ውጊያ (ለቸኮለ! ታኅሳስ 11)
1-የአ.አ. ሠራተኞች ፈተና ነገ ይጀመራል
2-“ምዘናው በአስቸኳይ እንዲቆም. . .” እናት ፓርቲ
3-የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ውጊያ
4-የምዕራብ ሸዋ ዞን ተፈናቃዮች ሮሮ
5-ኅብረቱ የጸጥታ ኅይሉን ሊቀላቀል ነው
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ…
2-“ምዘናው በአስቸኳይ እንዲቆም. . .” እናት ፓርቲ
3-የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ውጊያ
4-የምዕራብ ሸዋ ዞን ተፈናቃዮች ሮሮ
5-ኅብረቱ የጸጥታ ኅይሉን ሊቀላቀል ነው
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ…
ለቸኮለ ማለዳ! ዓርብ ታኅሳስ 12/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የፌደራል አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም፣ ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ዕርዳታ ሥርጭት እንደገና የጀመሩት በ20 በመቶ አቅማቸው ብቻ መኾኑን ለፋና ብሮድካስት ተናግረዋል። ዓለማቀፍ ረድኤት ድርጅቶች፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭትን የሚቆጣጠር ሦስተኛ አካል እንዲኖር ማድረጋቸውንም ሺፈራው ገልጸዋል። ረድኤት ድርጅቶች የተረጂዎች ልየታና የተለዩትን ተረጂዎች ዝርዝር የማጽደቁን ሥራ ለብቻቸው ለማከናወናወን ፈልገው እንደነበር የጠቀሱት ሺፈራው፣ በኋላ ግን በድርድር ከመንግሥት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ብለዋል።
2፤ የትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ኮሚቴ መንግሥትና ዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች በክልሉ በድርቅና ጦርነት ሳቢያ ለምግብ እጥረት ለታዳረጉ ዜጎች የነፍስ አድን ጥረት እንዲያደርጉ ትናንት በሰጠው መግለጫ ጥሪ አድርጓል። በክልሉ ላይ ያንዣበበው የርሃብ አደጋ ባስቸኳይ ካልተቀለበሰ፣ የከፋ የርሃብ አደጋ ይከሰታል በማለት ኮሚቴው ማስጠንቀቁን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በቅርቡ ባቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ኮሚቴ፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮችን አካቷል።
3፤ ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) 39 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሱማሊያዋ ወደብ ቦሳሶ ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል። ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች፣ በቦሳሶ ወደብ በኩል በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ የመን የሚያደርጉት ጉዞ እጅግ አደገኛው የፍልሰት መስመር እንደኾነ አይ ኦ ኤም በተደጋጋሚ ይገልጣል። አይ ኦ ኤም፣ በየመን በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሦስት ወራት የበረራ መቋረጥ በኋላ ሰሞኑን ማጓጓዝ መጀመሩን ሰሞኑን መግለጡ ይታወሳል።
4፤ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳኑ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን የሚያጣሩ ሦስት ገለልተኛ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎችን ሹሟል። ለኢትዮጵያው ጦርነት የተመድ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አጣሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር የነበሩት ታንዛኒያዊው ሞሃመድ ቻንዴ ኦትማን፣ የሱዳኑ.አጣሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነዋል። ሌሎቹ ኹለቱ የአጣሪ ኮሚሽኑ አባላት፣ ናይጀሪያዊቷ ጆይ ኢዚሎ እና የዮርዳኖስና ስዊዘርላንድ ዜግነት ያላቸው ሞና ሪሽማዊ ናቸው። አጣሪ ኮሚሽኑ ባለፈው ጥቅምት ሲቋቋም ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪ ግለሰቦችንና አካላትን መለየት፣ የጥሰት ማስረጃዎችን መሰነድና ምክረ ሃሳብ ማቅረብ ይገኙበታል።
5፤ አንጎላ ከዓለም ነዳጅ አምራች አገራት ድርጅት (ኦፔክ) ራሷን አግልላለች። አንጎላ ከድርጅቱ አባልነቷ የወጣችው፣ ድርጅቱ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ለምታመርተው ነዳጅ የወሰነላትን ኮታ በመቃወም ነው። ድርጅቱ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨመር፣ አባል አገራቱ ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን የነዳጅ መጠን እንዲቀንሱ ይፈልጋል። አንጎላ ባኹኑ ወቅት በቀን የምታመርተው የነዳጅ መጠን 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በርሜል ነው። [ዋዜማ]

#DEVELOPINGnews
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ ዛሬ ሊሰጠው አቅዶ የነበረው አወዛጋቢው የመጀመሪያ ዙር የብቃት መመዘኛ ፈተና ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙን ዋዜማ ሰምታለች።
ለፈተና የተመረጡት ሠራተኞቹ በአውቶቡስ ወደ ፈተና ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ሲጠባበቁ እንደነበር ለዋዜማ ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ፣ የብቃት መመዘኛ ፈተናውን የሚሰጠው አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ባደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እንደሆነ ገልፆ ነበር። ዝርዝር መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ያገኛሉ- http://tinyurl.com/b2hy24me

ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ - Wazemaradio
ዋዜማ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ ዛሬ ሊሰጠው አቅዶ የነበረው አወዛጋቢው የመጀመሪያ ዙር የብቃት መመዘኛ ፈተና መሰረዙን ዋዜማ ሰምታለች። ለፈተና የተመረጡት ሠራተኞቹ በአውቶቡስ ወደ ፈተና ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ሲጠባበቁ እንደነበር ለዋዜማ ተናግረዋል። ዳግማዊ ሚኒልክ ት/ቤት የፈተና ጣቢያ ሊፈተኑ የነበሩ አንድ ሰራተኛ የተወሰኑ ሰራተኞች ስም ዝርዝር ብቻ በመፈተኛ…
ለቸኮለ! ሐሙስ ታኅሳስ 12/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ምርጫ ቦርድ፣ የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ከአባልነት የወጡ ግለሰቦችን በመጠቀም ፓርቲውን የመከፋፈል ሥራ እየሠራና የፓርቲውን አመራሮች በማሰር ፓርቲውን የማጥፋት ርምጃ እየወሰደ ነው በማለት ላቀረበው አቤቱታ ብልጽግና ፓርቲ እስከ ታኅሣሥ 15 ድረስ ምላሽ እንዲሰጥ አዟል። ዋዜማ፣ ብልጽግና ፓርቲ በቀረበበት አቤቱታ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ፣ ቦርዱ ታኅሳሥ 10 ላይ ደብዳቤ መጻፉን ከምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ አረጋግጣለች። የቤሕነን ሊቀመንበር አብዱሰላም ሸንገል በበኩላቸው፣ ደብዳቤውን ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሲዘዋወር ማየታቸውን ገልጸው፣ እርሳቸው ግን ለቦርዱ አቤቱታ እንዳላቀረቡ ለዋዜማ ተናግረዋል። ደብዳቤው ከደረሰን በኋላ ቅሬታችን ለቦርድ እንገልጻለን ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አንድ ግለሰብ ቅሬታ አቅርቦ ሊኾን እንደሚችልና ቦርዱ ግን ከግለሰብ የቀረበለትን ቅሬታ እንደ ድርጅት አድርጎ መውሰዱ ተገቢ እንዳልኾነ ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ፣ ፓርቲያቸው ከክልሉ መንግሥትና ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጋር በልማትና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ባለፈው ሐምሌ ስምምነት ተፈራርሞ በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝም ለዋዜማ ተናግረዋል።
2፤ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን የትምህርት ቤቶቹን እውቅና መሰረዙ ተቀባይነት የሌለው ትግባር ነው ሲል ለዋዜማ ተናግሯልል። የትምህርት ቤቶቹ መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሶሎሞን ገሠሠ ለዋዜማ እንደነገሯት ከሆነ፣ ባለሥልጣኑ ከክፍያ ጋር ተያይዞ በትምህርት ቤቶቹ ላይ ላቀረበው ክስ ትምህርት ቤቶቹ ለአንድ ተማሪ በወር 2 ሺህ 500 ብር ብቻ እያስከፈለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህም ከሌሎች ትምህርት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር ፍጹም ተመጣጣኝ ዋጋ መሆኑን ተናግረዋል። ከአፋን ኦሮሞ ትምህርት ጋር ተያይዞ ለቀረበባቸው ክስም ትምህርት ቤቶቹ የአፋን ኦሮሞ ትምህርትን መመሪያው ሳይወጣ ጭምር ለተማሪዎቻችን እናስተምር ነበር ያሉ ሲሆን፣ መመሪያው ከወጣ በኋላ ትምህርቱን ለተማሪዎች እየሰጠን እንገኛለን ሲሉ ለዋዜማ አስረድተዋል። ባለሥልጣኑ ከስርዓተ ትምህርት ጥሰት ጋር በተገናኘ ለአጸደ ህጻናት ተማሪዎች መጽሐፍ አትማችሁ አሰራጭታችኋል ያለ ሲሆን፣ ሥራ አስኪያጁ ግን አገሪቷ ለአጸደ ሕጻናት ተማሪዎች የሚሆን ስርዓተ ትምህርት እንዳላዘጋጀች ጠቁመዋል። ስለሆነም ትምህርት ቤታቸው ለአጸደ ሕጻናት ተማሪዎች ያሰራጨው መጽሐፍ ስህተት ካለው የሚመለከተው አካል አይቶ የራሱን ውሳኔ መወሰን ይችላል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ 20 ዓመታትን ማስቆጠሩን፣ በስሩም ከ 4 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንዳሉትና ለኪራይ ቀድሞ በወር ከሚከፍለው 200 ሺህ ብር ባሁኑ ወቅት ከ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ እየከፈለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
3፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ከአማራና ትግራይ ክልሎች በስተቀር በኹሉም አካባቢዎች በ700 ወረዳዎች የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ እና ወኪሎችን የመምረጥ ሂደት ማከናወኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ፣ በአማራ ክልል ካለው የጸጥታ ችግርና በትግራይ በተከሰተው ርሃብ፣ ድርቅ እና ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የተሳታፊ ልየታ ማድረግ አልቻልኹም ብሏል፡፡ ኾኖም በኹለቱ ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መኾኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። በአገሪቱ በ327 ወረዳዎች የምክክር አጀንዳዎችን የሚለዩ ተወካዮች እንደተመረጡም ኮሚሽኑ ገልጧል። ኮሚሽኑ፣ በእስር ላይ በሚገኙ በፖለቲካ ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች በአገራዊ ምክክሩ ላይ ሃሳብና አጀንዳ እንዲሰጡ ለማስቻል ወደፊት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥበትም ጠቁሟል።
4፤ ኢዜማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፓርቲው ተመራጭ አማንያስ ጉሹና ባስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ አዲስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አማንያስ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ሳይያዙና ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከታኅሣሥ 9 ጀምሮ በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ፓርቲው ገልጧል። ግለሰቡ እስከ ትናንት ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ኢዜማ ጠቅሷል። በክልሉ በጋሞ ዞን ዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል በሚገኙ አባላቱ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተባባሱ መጥተዋል ያለው ኢዜማ፣ በአባላቱ ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶች የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት መፍትሄ እንዲበጅላቸው አሳስቧል። አማንያስ፣ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል ፓርቲውን ወክለው የክልሉ ምክር ቤት አባል እንደኾኑ ፓርቲው ገልጧል።
5፤ አስር የአሜሪካ ሕግ አውጭ ምክር ቤት አባላት የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል። ሕግ አውጪዎቹ ለተባበሩት ዓረብ ኢሜሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በጻፉት ደብዳቤ፣ አገሪቱ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ደጋፍ እያደረገች ነው በሚሉ መረጃዎች ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው መግለጣቸውን የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሕግ አውጭዎቹ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፈረንጆች 2005 በዳርፉር ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መጣሷን በመግለጽ፣ በሱዳን የምትከተለውን ፖሊሲ እንደገና እንድታጤን መጠየቃቸውን ዜና ምንጮች ገልጸዋል። ዓረብ ኢሚሬቶች ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ጦርነቱን እንደሚያባባስና የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ እንደሚከት መግለጻቸውን በዘገባው አመልክቷል። የምክር ቤቱ አባላት፣ ዓረብ ኢሜሬቶች ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ይልቅ የሱዳን ጦርነት እንዲያበቃ በሚያግዙ መፍትሄዎች ላይ ከአሜሪካ እና ከዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመኾን እንድትሰራ ጠይቀዋል ተብሏል።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ9214 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 57 ብር ከ0398 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ4558 ሳንቲምና መሸጫው 68 ብር ከ8049 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ2004 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ4244 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ ታኅሳስ 13/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትናንት ለሠራተኞቹና ባለሙያዎቹ ሊሰጠው የነበረው የብቃት ምዘና ፈተና ተሰርዟል። ተፈታኝ ሠራተኞች በፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ሲጠባበቁ እንደነበር ለዋዜማ ተናግረዋል። የምዘና ፈተናውን ለመስጠት የተመረጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ኮተቤ ዩኒቨርስቲ፣ የብቃት ምዘናውን ያልሰጠነው የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመን ነው ማለታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። አስተዳደሩ የብቃትና ባሕሪ ምዘና ፈተናውን ሊሰጥ ያሰበው፣ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ላደረጉ ተቋማት ሠራተኞችና ባለሙያዎች ነበር።
2፤ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የቅዱስ ሚካዔል ትምህርት ቤቶች የከተማዋ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን የትምህርት ቤቶቹን እውቅና መሰረዙ ተቀባይነት የለውም ሲል ለዋዜማ ተናግሯል። የትምህርት ቤቶቹ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሶሎሞን ገሠሠ፣ ባለሥልጣኑ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ላቀረበው ክስ ለአንድ ተማሪ በወር 2 ሺህ 500 ብር ብቻ እያስከፈሉ እንደኾነና ከሌሎች ትምህርት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር ፍጹም ተመጣጣኝ ክፍያ እንደኾነ ተናግረዋል። በአፋን ኦሮሞ ትምህርት ጋር ዙሪያ ለቀረበባቸው ክስም፣ ትምህርት ቤቶቹ የአፋን ኦሮሞ ትምህርትን አስተዳደሩ የቋንቋ መመሪያው ሳይወጣ ጭምር ያስተምሩ እንደነበር ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ ትምህርት ቤቶቹን ለአጸደ ሕጻናት መጽሐፍ አትማችኹ አሰራጭታችኋል ያለ ሲኾን፣ ትምህርት ቤቶቹ ግን መጽሃፉ ስህተት ካለው ባለ ጉዳዩ አካል ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል ብለዋል። ትምህርት ቤቱ 20 ዓመታትን ማስቆጠሩንና ከ 4 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንዳሉት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
3፤ ትናንት በባሕርዳር ከተማ ላንድ ሰዓት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። የተኩስ ልውውጡ የተካሄደው፣ በከተማዋ ቀበሌ 14 ውስጥ ቦንብ መፈንዳቱን ተከትሎ እንደኾነ ምንጮች ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡ በየትኞቹ ወገኖች መካከል እንደኾነ ግን ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ምንጮች ተናግረዋል። በቦንብ ፍንዳታውና በተኩስ ልውውጡ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
4፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በስሜ በ"ኤክስ" (በቀድሞው ትዊተር) ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ላይ ተሠራጭቷል ያለውን "ሐሰተኛ መግለጫ" አውግዟል። ሚንስቴሩ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማና አርማ እንዲኹም የሚንስቴሩን ስም በሕገወጥ መንገድ በመጠቀም ትናንት በተሠራጨው "ሐሰተኛ" መረጃ ላይ ርምጃ እወስዳለኹ ብሏል። ሚንስቴሩ "ሐሰተኛ" ያለውን መግለጫ ይዘት ባይጠቅስም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ቱርክ-ሠራሽ ድሮኖች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ባለው ውጊያ እያደረጉት ስላለው አስተዋጽኦ የሚገልጽና ቀልዶች ጭምር የተካተቱበት አንድ በእንግሊዝኛ የተጻፈ መግለጫ በሚንስቴሩ ስምና አርማ በ"ኤክስ" ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ትናንት ሲዘዋወር ዋዜማ ተመልክታ ነበር።
5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የአገሪቱ ኹለተኛ ትልቅ ከተማ ዋድ ማዳኒ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሥር እንድትወድቅ ያደረጉ የሠራዊቱ አዛዦች ተጠያቂ ይኾናሉ በማለት ዝተዋል። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል፣ ከተማዋ የምትገኝበትን አል ጀዚራ ግዛት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሬያለኹ ብሏል። የዋድ ማዳኒ ነዋሪዎችና በከተማዋ ተጠልለው የነበሩ የካርቱም ተፈናቃዮች፣ የኢትዮጵያ አጎራባች ወደኾኑት ገዳሪፍና ሴናር ግዛቶች ተፈናቅለዋል። [ዋዜማ

ለቸኮለ! ቅዳሜ ታኅሳስ 13/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢሰመኮ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን መንግሥት ደመወዝ ላልተከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንዲከፍልና ከሠራተኞች ደመወዝ ጋር በተያያዘ የተቋረጡ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ እንዲያደርግ ጠይቋል። በዞኑ የአብዛኞቹ የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች ከነሐሴ 2015 ዓ፣ም ጀምሮ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጠው ኢሰመኮ፣ በተለይ በሾኔ ከተማና በሰባት ወረዳዎች የትምህርትና ጤና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል ብሏል። በየወረዳው በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውንም ኢሰመኮ አመልክቷል። በዞኑ ከደመወዝ ክፍያ ጋር የተያያዘ ቅሬታና ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች "ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ ድብደባና እስራት" እንደደረሰባቸው መረዳቱንም ኢሰመኮ ጠቅሷል።
2፤ ቢጂአይ ኩባንያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ከዲያጎ ኩባንያ የገዛው ለእያንዳንዱ የአክሲዮን ድርሻ 60 ብር ብቻ በመክፈል መኾኑን ይፋ ካልኾኑ ሰነዶች ተመልክቻለኹ ሲል ሪፖርተር ዘግቧል። ዲያጎ ሜታ አቦ ፋብሪካን ሲሸጥ፣ እያንዳንዳቸው 1 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው 11 ሚሊዮን 500 ሺህ የአክሲዮን ድርሻዎች እንደነበሩት ዘገባው አስታውሷል። የቢጂአይ ሥራ አስኪያጅ ሜታ አቦን በዝቅተኛ ዋጋ የገዛነው፣ በከፍተኛ ዕዳና ኪሳራ ተዘፍቆና ባብዛኛው ምርት አቁሞ በነበረበት ወቅት ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ዘገባው፣ ሜታ አቦ ፋብሪካ ባንድ ዓመት ውስጥ ሕልውናው ሙሉ በሙሉ አክትሞ ከቢጂአይ ጋር እንደሚዋሃድም ሥራ አስኪያጁ ገልጸውልኛል ብሏል። ሜታ አቦ ባንድ አክሲዮን 60 ብር ለቢጂአይ በተሸጠበት ወቅት፣ ፋብሪካው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ዋጋ እንደነበረው ዘገባው ጠቅሷል።
3፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከባላንጣቸው የፈጥኖ ደራሹ ኃይል አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር መስማማታቸውን የሳዑዲ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኹለቱ ባላንጣዎች ንግግር የሚያተኩረው፣ ተኩስ አቁም በማድረግ ዙሪያ እንደኾነ ተገልጧል። ጀኔራል ቡርሃን፣ ከጄኔራል ደጋሎ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ያላቸውን ፍላጎት ለኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ጌሌ እና ለኢጋድ ዋና ዳይሬክተር ወርቅነህ ገበየኹ በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ጀኔራል ቡርሃን ከባላንጣቸው ጋር ለመነጋገር ተስማምተዋል የተባለው፣ የጄኔራል ደጋሎ ኃይሎች የአገሪቱን ኹለተኛ ትልቅ ከተማ ዋድ ማዳኒን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ነው።
4፤ ፔንታጎን በዚህ ሳምንት ለኹለተኛ ጊዜ ሱማሊያ ውስጥ ረቡዕ'ለት በፈጸመው የድሮን ጥቃት አንድ የአልሸባብ መሪን ጨምሮ 10 የቡድኑን አባላት መግደሉን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፔንታጎን ስብሰባ ላይ የነበሩ የአልሸባብ አባላትን የገደለው፣ በመካከለኛውና ታችኛው ጁባ ድንበር ላይ እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፔንታጎን፣ በድሮን ጥቃቱ ተገድሏል የተባለውን የአልሸባብ መሪ ማንነት ገና ይፋ አላደረገም። ፔንታጎን ማክሰኞ'ለት በተመሳሳይ አከባቢ በፈጸመው የድሮን ጥቃት፣ አልሸባብ ከሦስት ዓመት በፊት በምሥራቃዊ ኬንያ በአሜሪካ ጦር ሠፈር ላይ የፈጸመውን ከባድ ጥቃት በማቀነባበር የሚጠረጠረውን ሙዓሊም አይማን የተባለ የቡድኑን መሪ መግደሉን አስታውቆ ነበር።
5፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ኅብረት-መራሽ ለኾኑ የሰላም ማስከበርና ማስፈን ተልዕኮዎች ከተመድ በጀት ለመመደብ የሚያስችለውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል። ተመድ ለኅብረቱ በቋሚነት የሚመድበው በጀት፣ የኅብረቱ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን፣ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሚያዋጡ የአፍሪካ አገራትን ወጪዎችና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍን እንደሚኾን ተገልጧል። አፍሪካ ኅብረት በሱማሊያ ያሠማራውን ግዙፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጨምሮ በአሕጉሪቱ ለሚያሠማራቸው የተለያዩ ተልዕኮዎች እስካኹን ቋሚና አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭ አልነበረውም። የውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት፣ በምክር ቤቱ ተለዋጭ መቀመጫ ያላቸው አፍሪካዊያኑ ጋቦን፣ ሞዛምቢክና ጋና ናቸው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ታኅሳስ 15/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሃላፊ አብዱል ካማራ ላይ በምሽት ከቢሯቸው ውጭ አካላዊ ድብደባና እስር የፈጸሙት የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንስትር ጠባቂዎች መኾናቸውን ሰምቻለሁ ሲል ደይሊ ኔሽን ዘግቧል። የድብደባውና እስሩ ምክንያት፣ መንግሥት ለባንኩ መክፈል ያለበት 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ መዋጮ ለባንኩ እንዳልደረሰ የባንኩ ሃላፊዎች በመግለጣቸው እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። ሌላኛው ታስረው የተደበደቡት፣ የባንኩ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ሃላፊ ቦስኮ ቡከንያ ናቸው ተብሏል። ኾኖም ገንዘብ ሚንስቴር አቢጃን ለሚገኘው የባንኩ አካውንት ሳይኾን፣ በባንኩ ኢሜል ስም በተላከለት ሌላ ሜክሲኮ ወይም ፓናማ ለሚገኝ የባንክ ሒሳብ 6 ሚሊዮን ዶላር ስለመክፈሉና መንግሥትም በጉዳዩ ላይ ምርመራ ስለመጀመሩ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። ቡከንያ ወደ ቤታቸው ተወስደው ቤታቸው እንደተፈተሸና ላፕቶፖችና ደረሰኞች እንደተወሰዱባቸው ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
2፤ እንባ ጠባቂ ተቋም ከግል ድርጅቶች የአስተዳደር በደል ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን መቀበል ጀምሬያለኹ ማለቱን ሪፖርተር ዘግቧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ባሻሻለው አዋጅ፣ እንባ ጠባቂ ተቋም የግል እርሻዎችንና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ድርጅቶች አቤቱታዎችን እንዲቀበልና እንዲመረምር ሥልጣን ተሰጥቶታል። የተሻሻለው አዋጅ፣ የተቋሙ ሠራተኞች ያለመከሰስ መብት እንዳላቸው ጭምር ደንግጓል። ኾኖም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እንዳለ ኃይሌ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በሚታሠሩበት ኹኔታ የተቋሙ ሠራተኞች ያገኙት መብት በቂ ዋስትና አይኾንም በማለት ስጋታቸውን መግለጣቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
3፤ የቀድሞው የኢዜማ ከፍተኛ አመራር አባል ዳንዔል ሺበሺ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ቅዳሜ'ለት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ መኖሪያ ቤቴ በኃይል ገብተው ፍተሻ አካሂደዋል በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት መልዕክት ከሰዋል። ዳንኤል፣ ጸጥታ ኃይሎቹ በቤተሰባቸው ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ መፈጸማቸው ገልጸዋል። ጸጥታ ኃይሎች ድርጊቱን በፈጸሙበት ወቅት፣ እሳቸው ራቅ ወዳለ ቦታ ተጉዘው እንደነበር ዳንኤል ጠቅሰዋል። ዳንኤል፣ የኢዜማን አካሄድ በመቃወም ከፓርቲው አባልነታቸው የለቀቁት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ገደማ ነበር።
3፤ ሱዳናዊያን ሲቪሎች በጦር ሠራዊቱና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የሚካሄደውን ጦርነት በብዛት መቀላቀል መጀመራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ወጣቶች ከጦር ሠራዊቱ ወግነው፣ ጦርነቱን እንዲቀላቀሉ የጦር ሠራዊቱ አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ጥሪ ያደረጉት ባለፈው ዓመት ሰኔ ነበር። ጦር ሠራዊቱ፣ የአገሪቱ ኹለተኛ ትልቅ ከተማ ዋድ ማዳኒ በባላንጣው ቁጥጥር ስር መውደቋን ተከትሎ፣ በዋይት ናይል ግዛት በርካታ ወጣቶችን እየመለመለ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል በቅርቡ የኢትዮጵያ አጎራባች በኾነችው ዋይት ናይል ግዛት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ይከፍታል የሚል ስጋት አንዣቧል። ዋይት ናይል፣ ላለፉት 30 ዓመታት የአገሪቱ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ወታደራዊ ልሂቃን የወጡባት ግዛት ናት። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ምሽት! ሰኞ ታኅሣሥ 15/2016 ዓ.ም. የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1-በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ በሮ ቀበሌ ውስጥ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት፣ በዚኹ ቀበሌ የምትገኘው የበሮ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መገደላቸውን ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮቿ ሰምታለች። ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ 30 ደቂቃ አካባቢ እንደሆነ የገለፁት ምንጮች፣ በጥቃቱም በቁጥር ስምንት የሚደርሱ የቤተ ክርስቲያኒቷን የበቆሎ ምርት በመሰብሰብ ላይ የነበሩት አገልጋዮች ሕይወት ወዲያው ማለፉን ገልፀዋል። ከእነርሱ በተጨማሪም፣ ቁጥራቸው በውል ባልታወቁ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የበቆሎው ምርት እና አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኗ ንብረቶችም በድሮን ጥቃቱ ምክንያት መቃጠላቸውን ምንጮች አክለው ለዋዜማ ተናግረዋል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በወረዳው ሥር ባሉ አብዛኞቹ ቀበሌዎች፣ ድሮኖች በተደጋጋሚ ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበርም ዋዜማ ከምንጮቿ መገንዘብ ችላለች።
2-የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ የመጀመሪያ ያለውን የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የተመለከተ ሪፖርቱን ዛሬ አመሻሹን አውጥቷል።
ከ2014 ዓ.ም. እስከ 2015 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ድረስ ያለውን የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው በዚኽ ባለ 47 ገጽ ሪፖርቱ፣ በአራት ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ከ650 ሺህ በላይ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን የሚያስጠልሉ 17 መጠለያዎች ላይ ምርመራዎችን በማካሄድ ሪፖርቱን ማጠናቀሩን ገልጿል። ኮሚሽኑ እንደገለጠው ይኽ ሪፖርት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ እና ሰነድ የማግኘት መብት፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ የመንቀሳቀስ መብት፣ የሰብአዊ ድጋፍ የማግኘት መብት እንዲሁም ለሕፃናት፣ ለሴቶች፣ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች የሚደረግ ልዩ ድጋፍ እና በአጠቃላይ የዘላቂ መፍትሔዎች አተገባበር ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ መንግሥት ከተለያዩ ጎረቤት አገራት ግጭቶችን በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞችን ተቀብሎ እያስተናገደ መሆኑ፤ ስደተኞች ወደ መጠለያቸው እንዲመለሱ መደረጉ፤ የትምህርትና የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎች ለስደተኞች የሚደረጉ መሆኑ ዋና ዋና ቁልፍ እመርታዎች ናቸው ሲልም በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
3--ግብፅ፣ ኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድቡን የምትገነባው፣ አመነጫለኹ ካለችው የኤሌክትሪክ ኅይል ባለፈ በናይል ወንዝ ላይ የበላይነቷን ለማስፈን ነው ስትል ወቀሳዋን አሰማች። ይኽን የተናገሩት የአገሪቷ የመስኖ እና ውኀ ሃብት ሚንስትር ሓኒ ሰዊላም፣ ባለፉት ዐሥራ ኹለት ዓመታት በነበሩት ድርድሮች፣ ግድቡ ያመነጫል የተባለውን የኤሌክትሪክ ኀይል ለማመንጨት ከሚያስፈልገው ውኀ በላይ የሚይዝ እጅግ ግዙፍ የውኀ ማጠራቀሚያ እንዳለው መጥቀሳቸውን የአገሪቷ ጋዜጦች አስነብበዋል። “በድርድሮቹ ጊዜያት ኢትዮጵያ ከተከተለቻቸው ሂደቶች፣ ግድቡን አስመልክቶ ካላት አተያይ እና ከተጋነነው ውኀ ማከማቻ አኳያ ሌሎች ስውር አጀንዳዎች ይናጠቃሉ” ያሉት ሚንስትሩ፣ “ግድቡ የፖለቲካ ፋይዳ አለውና፣ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝን እንድትቆጣጠር ግብፅ አትፈቅድም” ማለታቸውም ተዘግቧል። ኢትዮጵያ ግብፅን ስለምትወቅስበት “የቅኝ-ግዛት ስምምነት” የተጠየቁት ሚንስትሩ፣ ኢትዮጵያ ይኽን ደጋግማ የምታነሳው ሉላዊ አተያዩን ለማሳት ነው ሲሉ ክሱን አስተባብለዋል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በኅዳሴ ግድቡ ዙሪያ ባለፈው ሳምንት ያካሄዱት አራተኛው ዙር ድርድር፣ ያለውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።
4--የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ ከሚሰጠው የብቃት መመዘኛ ፈተና ጋር ተያይዞ ያሳስበኛል ሲል ረፋድ ላይ መግለጫ አውጥቷል። በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ዳይሬክተሮችን እና የቡድን መሪዎችን የብሄር ስብጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ብሄር የሚመጡት ከ40 በመቶ በላይ ሊበልጡ እንደማይገባ መገለፁ፣ ለምዘና መሠረታዊ የሆነውን ከትምህርት ዝግጅትና ከሥራ ልምድ የሚመነጭ የችሎታና ብቃት ጉዳይ አሳንሶ እንዳይመለከት ጥብቅ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲልም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። ኢዜማ፣ የከተማ መስተዳደሩ ስለ ፈተናው እና ለማኅበረሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት ከመስጠት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለውን የብሄር ኮታ ምደባን አስመልክቶ፣ ለከተማዋ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጥም ጠይቋል።
ከዚኹ ጋር ተያይዞ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የብቃት መመዘኛ ፈተና፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 20 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ከተማ አስተዳደሩ አዲስ የመዋቅር አደረጃጀት ጥናት ባደረጉ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙት ከ14 ሺ በላይ ለሚሆኑት ሠራተኞቹ፣ ታኅሣሥ 12 ሊሰጠው የነበረው የብቃት መመዘኛ ፈተና፣ “ቴክኒካዊ” በተባለ ምክንያት ሳይሰጥ መቅረቱ ይታወሳል።
5-ለ24 ዓመታት በቀላል ምግቦች አቅርቦት ውስጥ ሰፋ ያለ የገበያ ድርሻ የነበረው እና ቴስቲስ እና ጆሊ ጁስ የተሰኙ ምርቶችን በማምረት የሚታወቀው ቴስቲ ፉድስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር፣ በውጭ ምንዛሬ ዕጥረት የተነሳ ሥራ ማቆሙን ፎርቹን አስነብቧል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በውጭ ምንዛሬ ችግር የተነሳ ወሳኝ የሆኑት የምርት ግብዓቶችን ከውጪ ማስገባት ባለመቻሉ ፋብሪካው ሥራ ለማቆም እንደተገደደ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የድርጅቱ ሠራተኞችም ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚያገኙ ድረስ የዕረፍት ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ዘገባው አመልክቷል። ድርጅቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ማለፉን እና የምርት መጠኑም በከፍተኛ መጠን መቀነሱን የገለፀው ዘገባው፣ ከሦስት ዓመታት ወዲኽ የጆሊ ጁስ ምርቱ በአምስት እጥፍ፣ እንዲኹም የቴስቲስ ምርቱ በ10 ዕጥፍ መቀነሱን ጠቁሟል። የምግብ፣ መጠጥ እና ትምባሆ ማኅበራት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ደረጄ ዋቅቶላ፣ የድርጅቱ ፈተናዎች እንደ አገር ያለውን የውጭ ምንዛሬ ችግር ያሳያል ማለታቸውንም ዘገባው ገልፇል።
6- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ አንድ የዶላር መግዣ ዋጋ 55.9393፣ መሸጫው ደግሞ 57.0581 ሆኖ እንደዋለ በድረ ገፁ ገልጧል። አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ የመግዣ ዋጋ ደግሞ 67.9368 ሆኖ ሲውል፣ መሸጫው ደግሞ 69.2955 ሳንቲም ሆኖ ውሏል። አንድ ዩሮ መግዣ ዋጋ ደግሞ 61.6283 ሲሆን፣ መሸጫው ደግሞ 62.8609 ሳንቲም እንደነበረ ባንኩ በድረ-ገፁ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ታኅሳስ 16/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያ የ33 ሚሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ ብድር ወለድ ትናንት በቀነ ገደቡ ሳትከፍል መቅረቷን ብሉምበርግ ዘግቧል። የወለዱ መክፈያ ዋናው ቀነ ገደብ ያለፈው ከኹለት ሳምንት በፊት ሲኾን፣ ቀነ ገደቡ የ14 ተጨማሪ የእፎይታ ቀናት ነበረው። መንግሥት የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ብድር ወለዱን ከኹለት ሳምንት በፊት ያልከፈለው፣ ኹሉንም አበዳሪዎች በእኩል ለማስተናገድ እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል። የወለድ መክፈያው የእፎይታ ጊዜ ትናንት ማብቃቱን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋን መክፈል ያልቻለች አገር ኾናለች።
2፤ ኢሰመኮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞንና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል ባለፈው ጥቅምት የተፈጠረው ግጭት ያስከተለውን ጉዳት የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡና ተጎጂዎች እንዲካሱ ጠይቋል፡፡ ኢሰመኮ፣ ግጭቱ ባስከተለው ጉዳት ላይ ባካባቢው ተገኝቶ ምርመራ ማድረጉን ገልጧል። የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፣ በክልሉ እስካኹንም ዘላቂ መፍትሄ ያልተሰጣቸው "የመዋቅርና የአስተዳደር ጥያቄዎች" ለሰላምና ደኅንነት እጦትና ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት እየኾኑ መቀጠላቸው "እጅግ አሳሳቢ" እንደኾነ ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ለችግሩ ሕዝቡን ተዓማኒ በኾነና ተቀባይነት ባለው ሂደት በማሳተፍ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልጉ መጠየቃቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
3፤ ኢሰመኮ ትናንት ይፋ ባደረገው የመጀመሪያው የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብዓዊ መብቶች ኹኔታ ሪፖርት ከግንቦት 2015 ዓ.ም ወዲህ ሰብዓዊ ዕርዳታ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ስደተኞች ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ መጋለጣቸውንና በስደተኛ ጣቢያዎች የመድኃኒት፣ የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩን ገልጧል። የኢሰመኮ ሪፖርት፣ ለሦስት ዓመታት የተቋረጠው የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ አገልግሎትም ባፋጣኝ እንዲጀምር ጠይቋል። የሰብዓዊ መብት ምርመራው የተደረገው፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በጋምቤላና ሱማሌ ክልሎች በሚገኙ 17 የስደተኞች መጠለያና መቀበያ ጣቢያዎችና በአዲስ አበባ በሚገኙ ስደተኞች ላይ እንደኾነ ኢሰመኮ ጠቅሷል። ሪፖርቱ፣ የስደተኞች ምዝገባና ሰነድ የማግኘት ሥርዓት ክፍተት እንዳለበትና ይህም በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መሠረታዊ መብቶች ላይ ችግር መፍጠሩን አመልክቷል።
4፤ አራት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትናንት "ኪዳን ለሥር ነቀል ለውጥ" የተባለ ጥምረት መስርተዋል። አዲሱን ጥምረት ያቋቋሙት፣ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ አረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ብሄራዊ ሸንጎ (ባይቶና) ናቸው። የጥምረቱ አመራሮች፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት በብረታ ብረትና የምግብ ዕርዳታ ዝርፊያ፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በቡድናዊ የሥልጣን ሽኩቻ ላይ ተሠማርተዋል በማለት ከሰዋል። ፓርቲዎቹ፣ የክልሉን ኹለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት ኹሉን ዓቀፍ ሽግግር መንግሥት እንዲመሠረት ጠይቀዋል። [ዋዜማ]

በእጅጉ የፖለቲካ መዳፍ ያረፈበት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ሊጠገን የማይችል የሚመስል ስብራት ገጥሞታል። ይህ ስብራት በተማሪዎችና በወላጆች ላይ ከሚያደርሰው ብርቱ ተፅዕኖ ጎን ለጎን ለሀገራዊ ድባቴም ዳርጎናል። ዋዜማ በ "ከስምንተኛው ወለል" የስቱዲዮ ውይይት በዘርፉ አንቱ የተባሉ ባለሙያዎችን ጋብዛ አወያይታለች። ተከታተሉት- https://youtu.be/KF7uJB175U4?si=pCuV-9ZbhjG3OGbY
YouTube
የትምሕርት ስርዓቱ ስብራት
በእጅጉ የፖለቲካ መዳፍ ያረፈበት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ሊጠገን የማይችል የሚመስል ስብራት ገጥሞታል። ይህ ስብራት በተማሪዎችና በወላጆች ላይ ከሚያደርሰው ብርቱ ተፅዕኖ ጎን ለጎን ለሀገራዊ ድባቴም ዳርጎናል። የዚህ የትምህርት ስርዓታችን ችግር ምንጩ ምንድነው? ከችግሩ ለመውጣት የሚረዳ የመፍትሄ አማራጭስ ይኖር ይሆን? ዋዜማ በ "ከስምንተኛው ወለል" የስቱዲዮ ውይይት በዘርፉ አንቱ የተባሉ ባለሙያዎችን…
ለቸኮለ! ማክሰኞ ታኅሳስ 16/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ከደመወዝ ክፍያ መዘግየት እና ከተቋማት መዘጋት ጋር ተያይዞ ጥያቄ የሚያነሱ ባለሙያዎች እየታሠሩ መኾኑን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። ከታሠሩት የመንግሥት ሠራተኞች መካከል፣ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሎጂ መምህር የኾኑት መለሠ አብርሃም ይገኙበታል። ጥያቄ ባነሱ የመንግሥት ሠራተኞች ላይ እስሩን እየፈጸመ ያለው የክልሉ ፖሊስ እንደኾነ የገለጹት ምንጮች፣ ታሳሪዎቹን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሚያስሯቸው እና ካሰሯቸው በኋል ለፍርድ እንደማያቀርቧቸው ለዋዜማ አስረድተዋል። እስረኞቹም በቢሾፍቱ እና በሆሳዕና ከተማ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ዋዜማ ከምንጮቿ መገንዘብ ችላለች። ዋዜማ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስንት የመንግሥት ሠራተኞች እንደታሠሩ ማረጋገጥ አልቻለችም።
2፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በክልሉ በተከሰተው የሠላም እጦት ሳቢያ ጣና ሐይቅ የኅልውና አደጋ ውስጥ መግባቱን አስታውቋል። የክልሉ ኮምንኬሽን ባወጣው መግለጫ፣ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት የተነሳ በሐይቂ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ሲደረግ የቆየው ጥረት እንደተስተጓጎለ ገልጧል። ቀደም ሲል መንግሥት የገዛቸውና በተለያዩ ድጋፎች አማካኝነት ጥቅም ላይ ሲውሉ የቆዩት የአረም ማስወገጃ መሳሪያዎች፣ ዝገት እያጋጠማቸውና በብልሽት ከጥቅም ውጭ እየኾኑ መኾኑን ቢሮው ጠቅሷል፡፡ እምቦጭ አረምን የማጥፋት ሥራውን የሚያከናውነው ኤጀንሲም፣ በሠላም ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ መሥራት እንዳልቻለና አረሙን የማስወገድ ጥረቶች መስተጓጎላቸው ተገልጧል።
3፤ ኢትዮጵያ ትናንት መክፈል የነበረባትን 33 ሚሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ብድር ወለድ ባለመክፈሏ ዕዳዋን ባለመክፈል በአፍሪካ ከዛምቢያና ጋና ቀጥላ ሦስተኛዋ የአፍሪካ አገር መኾኗን ሮይተርስ ዘግቧል። የገንዘብ ሚንስትር አህመድ ሽዴ ከጥቂት ቀናት በፊት በመንግሥታዊ ቴሌቪዥን ላይ በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ የወለድ ዕዳዋን የማትከፍለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳለልባት ሳይኾን ኹሉንም አበዳሪዎቿን በእኩል ለማስተናገድ በመወሰኗ እንደኾነ መግለጣቸው ይታወሳል። የገንዘብ ሚንስቴር ከፍተኛ አማካሪ የኾኑት ሂንዣት ሻሚልም፣ ኢትዮጵያ የወለድ ክፍያውን እንዳልፈጸመች ማረጋገጣቸውን የዘገበው ደሞ ብሉምበርግ ነው። ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት በፊት በታኅሣሥ 2007 ዓ.ም የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሽጣ ላገኘችው ብድር፣ የ33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ መክፈያ ጊዜው ታኅሣሥ 1 ቀን ላይ መጠናቀቁ ይታወሳል። የወለዱ መክፈያ ጊዜ 14 ተጨማሪ የእፎይታ ቀናት የነበሩት ሲኾን፣ የእፎይታ ጊዜውም ክፍያው ሳይፈጸም ትናንት አብቅቷል።
4፤ ዓለማቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የናይጀሪያ መንግሥት ባልከፈለው የውጭ አየር መንገዶች የትኬት ሽያጭ ገቢ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሪቱ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ እንደሚችል መናገሩን የናይጀሪያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ፣ የብሪታኒያና ቱርክ አየር መንገዶች ወደ ናይጀሪያ በረራ ማድረግ ሊያቆሙ ይችላሉ በማለት ማኅበሩ ማስጠንቀቁን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የናይጀሪያ አውሮፕላን ማረፊያዎች የአገልግሎት ጥራታቸው ዝቅተኛ ቢኾንም፣ የሚያስከፍሉት ክፍያ ግን በአፍሪካ እጅግ ውድ እንደኾነ ማኅበሩ ገልጧል ተብሏል። እስካለፈው ዓመት ሐምሌ ድረስ የናይጀሪያ መንግሥት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልከፈለው 180 ሚሊዮን ዶላር ነበረበት። ኾኖም ሐምሌ ላይ የናይጀሪያ መንግሥት 100 ሚሊዮን ዶላሩን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በያዘው የናይጀሪያው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ገንዘብ ለመለዋወጥ መስማማታቸው ይታወሳል።
5፤ ተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ አምባገነን መንግሥት ባለባት ኢትዮጵያ ዜጎች በየዕለቱ እነደቅጠል እየረገፉ ይገኛሉ በማለት መንግሥትን ተችቷል። ፖለቲካዊ ሥልጣንን ለማስጠበቅ ሲባል በንጹሃን እና ባልታጠቁ ዜጎች ላይ በብልጽግና ፓርቲ መራሹ መንግሥት በየዕለቱ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ ድርጊት የተስፋ መቁረጥ እና የአጥፍቶ መጥፋት አካሄድ ነው ሲል ፓርቲው ከሷል። ኦነግ፣ መንግሥት በሕዝቡ ዘንድ ቅቡልነትና ተዓማኒነት ስላጣ በዚህም ምክንያት በመሳሪያ ኃይል ሥልጣኑን ለማስጠበቅ በንጹሃን ደም እየቆመረ ነው ብሏል። ኾኖም የመንግሥት ድርጊት የጀመረውን ትግል ፈጽሞ ወደ ኋላ ሊመልሰው እንደማይችል ገልጧል። ፓርቲው፣ በትላንትናው ዕለት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ በሮ ቀበሌ ሰብል በመሰብሰብ በነበሩ ንጹሃን ላይ የድሮን ድብደባ መፈጸሙን የገለጸ ሲኾን፣ በዚህም 8 ሰዎች ሕይወታቸው ወዲያውኑ ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጫለኹ ብሏል። ኦነግ፣ መንግሥት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት መላው የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች፣ ዐለማቀፉ ማኅበረሰብ እንዲኹም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲያወግዙ እና ድርጊቱን እንዲያስቆሙት ፓርቲው ጠይቋል።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ9499 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 57 ብር ከ0689 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 67 ብር ከ9069 ሳንቲምና መሸጫው 69 ብር ከ2650 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ61 ከ6680 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ9014 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]
https://youtu.be/6clxr1UZVA4?si=kEWcuJa5R8bSVvBU

የኢትዮጵያ ወለድ መክፈያ ቀን አበቃ (ለቸኮለ! ታኅሳስ 16)
1-ሆሳዕና እስሩ በርክቷል
2-ጣና ሐይቅ አደጋ ውስጥ ገብቷል
3-የኢትዮጵያ ወለድ መክፈያ ቀን አበቃ
4-አየር መንገዱ የናይጄሪያ በረራውን ሊያቋርጥ ይችላል
5-“መንግሥት በንጹሃን ደም እየቆመረ ነው” ኦነግ
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ ስርጭት…
2-ጣና ሐይቅ አደጋ ውስጥ ገብቷል
3-የኢትዮጵያ ወለድ መክፈያ ቀን አበቃ
4-አየር መንገዱ የናይጄሪያ በረራውን ሊያቋርጥ ይችላል
5-“መንግሥት በንጹሃን ደም እየቆመረ ነው” ኦነግ
#wazemaradio #Lechekole #EthiopianNews #Amharicnews
ስለ ዋዜማ ራዲዮ
"ዋዜማ ሬዲዮ" በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የፖድካስት ሬዲዮ ስርጭት…
#NewsAlert
የሕወሓት አጋር የሆነውና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ዋዜማ ስምታለች። በምስጢር የተያዘው ስምምነት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ያንብቡት- http://tinyurl.com/49jmnfhy