ኢሰመኮ በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች “እጅግ አሳሳቢ” ኾነዋል ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዝርዝሩን አንብቡት- https://tinyurl.com/bdcmh6p3
Wazemaradio
“በአማራ ክልል ከህግና ፍርድ ውጪ የሚፈፀመው ግድያ እና እስራት አሳሳቢ ሆኗል” ኢሰመኮ - Wazemaradio
ዋዜማ- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች "እጅግ አሳሳቢ" ኾነዋል ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢሰመኮ፣ "የትጥቅ ግጭቱ ወደ ክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች መስፋፋቱን" ካሰባሰበው መረጃ መረዳቱን ገልጧል። ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 30 2015 ዓ፣ም…
#NewsAlert
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከመንግሥት ጋር እየተፋለሙ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችን ለማነጋገር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለዋዜማ ገልጿል። ዝርዝሩን ያንብቡት https://tinyurl.com/58auad55

የምክክር ኮሚሽኑ ታጣቂ ኃይሎችን ለማነጋገር እየተዘጋጀ ነው - Wazemaradio
ዋዜማ- የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከመንግሥት ጋር እየተፋለሙ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችን ለማነጋገር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለዋዜማ ገልጿል። ኮሚሽኑ በአማራ ክልሉ በፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያ መቀስቀሱን ተከትሎ፣ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው እንዲነጋገሩ መጠየቁ የሚታወስ ነው። ኮሚሽኑ ባቀረበው የሰላም ጥሪ ላይ ታጣቂ ኃይሎችን እና…
ለቸኮለ! ቅዳሜ መስከረም 5/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመንግሥት ጋር የሚፋለሙ ታጣቂ ቡድኖችን ለማነጋገር ዝግጅት ላይ መኾኑን የኮሚሽኑ አባል ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ለዋዜማ ተናግረዋል። ኮሚሽነር ዮናስ ኮሚሽኑ በተለይ ጥረት የጀመረው፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ነፍጥ ያነሱ ታጣቂ ቡድኖችን በአካል ለማነጋገር እንደኾነ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ የመንግሥት አካላትን አነጋግሮ መንግሥት ከታጣቂዎቹ ቡድኖች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መኾኑን ከገለጠ በኋላ እንደኾነ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። ኮሚሽኑ እስካኹን የአማራ ክልል ምሁራንና የክልሉን አመራሮች እንዲኹም በኦሮሚያ ክልል ግጭት ዙሪያ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ማነጋገሩን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል። የኮሚሽኑ ጥረት ውጤት ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
2፤ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ 10 ሺህ ሱዳናዊያን ስደተኞች በተጠለሉበት ኩመር መጠለያ ጣቢያ ዘጠኝ ሱዳናዊያን ስደተኞች በኮሌራ በሽታ እንደሞቱና 395 ሰዎች በበሽታው እንደታመሙ መናገሩን ቪኦኤ ዘግቧል። የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በሐምሌ መግቢያ ወረርሽኙ በክልሉ ከተከሰተ ወዲህ 70 ሰዎች እንደሞቱና ከ3 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ለሕመም እንደተዳረጉ አስታውቋል። ኢንስቲትዩቱ፣ በሽታው በተስፋፋባቸው ዘጠኝ ወረዳዎች ዛሬ የክትባት ዘመቻ ጀምሯል።
3፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን አንዳንድ ሲቪል ማኅበራት የሕግ ዕውቅና የሌላቸው የባንክ አካውንቶችን እየተጠቀሙና የውጭ ምንዛሬ እየደበቁ መኾኑን ደርሸበታለኹ ሲል ባሰራጨው የማሳሰቢያ ደብዳቤ አስታውቋል። ባለሥልጣኑ፣ አንዳንድ ሲቪል ማኅበራት ገንዘባቸውን በውጭ አገራት ባንኮች በሦስተኛ ወገኖች የባንክ አካውንቶች እያስቀመጡ እንደኾነ መረጃ እንዳለው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። በሲቪል ማኅበራት አዋጅ መሠረት፣ ሲቪል ማኅበራት ከባለሥልጣኑ ዕውቅና ውጭ የባንክ አካውንት መክፈት አይችሉም፤ በባለሥልጣኑ ዕውቅና የባንክ አካውንት መክፈት የሚችሉትም በራሳቸው ስም ብቻ ነው። ባለሥልጣኑ፣ አዋጁን በሚተላለፉ ሲቪል ማኅበራት ላይ ርምጃ እንደሚወስድ ከቀናት በፊት ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር።
4፤ የአጼ ቴዎድሮስ ልጅ የልዑል አለማየሁን ጸጉር ያስቀመጡ ብርታኒያዊያን ጸጉሩን በቀጣዩ ሳምንት ለኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ሊመልሱ መኾኑን ቴሌግራፍ ጋዜጣ አስነብቧል። ጸጉሩን በግል ንብረትነት ለዓመታት ያስቀመጡት፣ ልዑል አለማየሁን ከመቅደላ የወሰደውና በኋላም የግል ተንከባካቢው የነበረው የብሪታኒያዊው አሳሽ ወታደር ሻምበል ትሪስትራም ስፒዲ ቤተሰቦች ናቸው። የልዑሉ ጸጉር ለኢትዮጵያ የሚመለሰው፣ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ከብሪታንያ ሙዚዬም ከሚገኝ አንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታቦት ጋር እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል።
5፤ የአልሸባብ መሪ ማሃድ ካራቴ ሰሜኑን በቪዲዮ ባስተላለፈው መልዕክት አሜሪካን ማስጠንቅቀቁን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ካራቴ፣ "አሜሪካ በድሮን ጥቃት ሲቪሎችን ዒላማ ታደርጋለች፤ ለሱማሊያ መረጋጋትም እንቅፋት ኾናለች" በማለት መክሰሱን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ካራቴ ይህንኑ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፈው፣ ከሳምንት በፊት አሜሪካ ያሰለጠነቻቸው የሱማሊያ ልዩ ኃይሎች ሦስት የቡድኑን አዛዦች መግደላቸውን ተከትሎ ነው። አሜሪካ ከዓመታት በፊት የካራቴን አድራሻ ለሚጠቁማት የ10 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ቃል መግባቷ ይታወሳል።
6፤ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ወደ ኡጋንዳ አቅንተዋል። ጀኔራል ቡርሃን ከፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በኹለትዮሽ ጉዳዮችና የሱዳኑን ጦርነት በሰላም መፍታት በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ ይመክራሉ። ጀኔራል ቡርሃን ከካርቱም ከወጡ ወዲህ በውጭ አገራት ጉብኝት ሲያደረጉ፣ የኡጋንዳ ጉብኝታቸው ስድስተኛቸው ነው። ኢጋድ ለሱዳኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ አፈላላጊ ቡድን አድርጎ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ጅቡቲ መሪዎችን ቀደም ሲል የሰየመ ሲኾን፣ ጀኔራል ቡርሃን እስካኹን የጎበኙት ግን ደቡብ ሱዳንን ብቻ ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ መስከረም 7/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከ1 ሺህ በላይ መታሠራቸውን ለተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። ተርክ፣ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል ካሏቸው ጥቂት አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መኾኗን የጠቀሱ ሲኾን፣ በአገሪቱ የመብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባም አሳስበዋል። በተያያዘ፣ ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ያቋቋመው ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን ዛሬ ወይም ነገ በተልዕኮው ዙሪያ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ፣ በቅርቡ የተጠናቀቀውን የኮሚሽኑን የጊዜ ቆይታ በድጋሚ እንዲያራዝም በርካታ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መጠየቃቸው ይታወሳል።
2፤ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል በአሉቶ ላንጋኖ በከርሰ ምድር እንፋሎት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በስድስት ጉድጓዶች ላይ ባደረኩት ሙከራ 25 ሜጋ ዋት እንደሚያመነጭ አረጋግጫለኹ ብሏል። በቀሪዎቹ አራት ጉድጓዶች ላይ እስከ ታህሳስ ኃይል የማመንጨት ሙከራ እንደሚደረግ ተቋሙ ገልጧል። ፕሮጀክቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሜጋ ዋት እንዲኹም በኹለተኛው ምዕራፍ ሌላ 35 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታቅዷል። የፕሮጀክቱ ወጪ፣ ከዓለም ባንክ በብድርና ድጋፍ በተገኘ 143 ሚሊዮን ዶላር የሚሸፈን ነው። ተቋሙ፣ አራት ተጨማሪ ጉድጓዶችን ለመቆፈር ከዓለም ባንክ ጋር ስምምነት እንደደረሰ ገልጧል።
3፤ የደቡባዊ ትግራይ ዞን ጸጥታ ቢሮ የዞኑን ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ሳምሶን ተፈሪን በመግደል የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሳምሶን ማይጨው ውስጥ በድንገት በጥይት የተገደሉት፣ መስከረም 1 ቀን ምሽት ላይ ነበር። ሟቹ ሳምሶን ቀደም ሲል የዞኑ ዋና ከተማ ማይጨው ከንቲባ ኾነው አገልግለዋል።
4፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ትናንት ጧት ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር በምዕራብ ሱማሊያ ባኮል አውራጃ ራብ ዱሬ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ ማካሄዳቸውን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ፣ አልሸባብ በኹለት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ካሚዮኖች ላይ ሦስት የከባድ መሳሪያ ፍንዳታዎችን እንዳደረሰና ለሰዓታት የዘለቀ ከባድ የተኩስ ልውውጥ እንደተደረገ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ነጻ ምንጮች ባያረጋግጡትም፣ አልሸባብ በጥቃቱ 167 ወታደሮችን ገድያለኹ ብሏል። በካሚዮኖቹ ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጦር ሠፈሮች ወደሚገኙባቸው "ዋጂድ" እና "ሁዱር" ሲጓዙ ነው ተብሏል።
5፤ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች ቅዳሜ'ለት በጀርመኗ ስቱትጋርት ከተማ በፈጠሩት ግጭት ፖሊስ 228 የመንግሥት ተቃዋሚ ስደተኞችን አስሯል። ግጭቱን ለመቆጣጠር ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲኾን፣ 26 ፖሊሶች ቆስለው ሆስፒታል እንደገቡና ስድስት ኤርትራዊያን እንደቆሰሉ ተገልጧል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው፣ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ለተቃውሞ የተወሰነላቸውን ቦታ ጥሰው የመንግሥት ደጋፊዎች ፌስቲቫል ወዳዘጋጁበት ቦታ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።
6፤ የሱማሌላንድ ራስ ገዝ መንግሥት የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት ልዑካን ቡድን የራስ ገዟ የጎሳ ሚሊሻዎች በቅርቡ የተቆጣጠሯትን ላስ አኖድ ከተማ መጎብኘቱን ክፉኛ አውግዟል። ፑንትላንድ የይገባኛል ጥያቄ የምታነሳበትን የሱል አውራጃ ዋና ከተማ ላስ አኖድን ከወራት ውጊያ በኋላ ከሱማሌላንድ መንግሥት ኃይሎች ያስለቀቁት፣ አውራጃው በሱማሊያ ስር እንዲተዳደር እንፈልጋለን የሚሉ የጎሳ ታጣቂዎች ናቸው። ሱል አውራጃ ሉዓላዊ ግዛቷ እንደኾነች የጠቀሰችው ሱማሌላንድ፣ የሱማሊያ ባለሥልጣናት ጉብኝት የግዛት አንድነቴን ይጥሳል በማለት አስፈላጊውን አጸፋዊ ርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ መስከረም 7/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ "የመብት ጥሰቶች"፣ "የጦር ወንጀሎች" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ቀጥለዋል" ብሏል። ኮሚሽኑ፣ በትግራይ "የጅምላ ግድያ"፣ "አስገድዶ መድፈር"፣ "የግዳጅ ማፈናቀል" እና "የዘፈቀደ እስር" መቀጠሉን የኤርትራንና አማራ ክልል ኃይሎች "የአስገድዶ መድፈር" እና ሌሎች የጾታ ጥቃቶችን መፈጰም እንደቀጠሉ ገልጧል። የኤርትራ ወታደሮች አኹንም በትግራይ መኖራቸው፣ ፌደራል መንግሥቱ "ለመብት ጥሰቶች ድጋፍ ለመስጠቱ" ወይም "ታጋሽነት ለማሳየቱ ማሳያ ነው" በማለትም ኮሚሽኑ ከሷል። የአማራ ክልል የጸጥታ ኹኔታ ማሽቆልቆሉ "እጅግ እንዳስደነገጠው" የገለጠው ኮሚሽኑ፣ ኹኔታው ወደከባድ የመብት ጥሰት ሊይመራ እንደሚችል በመጥቀስ "የገለልተኛ ምርመራና ክትትል" አስፈላጊ መኾኑን አውስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሞሐመድ ቻንዴ በኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ "እጅግ አሳሳቢ" መኾኑን ጠቅሰው፣ ግጭቶች "አገር ዓቀፍ ወደመኾን ደረጃ ደርሰዋል" በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። የመንግሥት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲንም፣ "ጉድለት ያለበት"፣ "የተጎጂዎችን ሃሳብ ያላካተተ"፣ "ተጎጂዎች አመኔታ ያልጣሉበት" እና "ዓለማቀፍ ጫናን ለመቀነስ ወይም ምርመራን ለማስቀረት ያለመ ነው" በማለት ኮሚሽኑ አጣጥሎታል።
2፤ የፌደራሉ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእንባ ጠባቂ ተቋምን ምክረ ሃሳቦች ለመቀበል እምቢተኝነት ያሳያሉ ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ በሰጡት ቃል ከሰዋል። እንዳለ፣ ኹለቱ የፖሊስ ኮሚሽኖች ተባባሪ ባለመኾናቸው ተቋሙ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመምራት ተገዷል ብለዋል። የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽንም፣ ተመሳሳይ ችግር እንደሚታይበት ዋና እንባ ጠባቂው ጠቅሰዋል። አንዳንድ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ እንደ ባሕርዳር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ የመሳሰሉ የክልል ከተማ አስተዳደሮችና የክልል ቢሮዎች፣ የሕዝቡን የአስተዳደር በደሎች ለመስማትና የተቋሙን የመፍትሄ ሃሳቦች ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የማይኾኑት፣ "ማን ይነካናል?" በሚል አስተሳሰብ እንደኾነም እንዳለ ለጣቢያው ገልጸዋል።
3፤ የፌደራል የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል ብሄራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከመስከረም 29 ጀምሮ በሦስት ዙር መስጠት እንደሚጀምር ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ እንደሚሰጥ አገልግሎቱ ገልጧል። አገልግሎቱ፣ ለፈተናው የሚቀመጡ ተፈታኞች ምዝገባ ከነገ ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ድረስ ይካሄዳል ብሏል። በትግራይ ክልል በጸጥታ ችግር ሳቢያ፣ ከ2012 ዓ፣ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና አልተሰጠም።
4፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዛሬ የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን የዓለም የተፈጥሮ ቅርስ አድርጎ መዝግቧል። የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በ1962 ዓ.ም የተቋቋመ ሲኾን፣ ቀይ ቀበሮን ጨምሮ የተለያዩ ብርቅዬ የዱር አራዊትና ልዩ ልዩ የእጽዕዋት ዝርያዎች ይገኙበታል። በሳዑዲ ዓረቢያ ጉባዔውን እያካሄደ የሚገኘው የዩኔስኮ ቅርስ መዝጋቢ ኮሚቴ፣ የጌዲዖ ዞን ባሕላዊ መልክዓ ምድርንም ትናንት የዓለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል። የኹለቱ ቅርሶች መመዝገብ፣ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸውን ቅርሶች ብዛት 11 አድርሶታል።
5፤ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ኹለተኛውን ዙር ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹን የማስወጣት ሂደት ትናንት ጀምሯል። የኅብረቱ የሰላም ተልዕኮ ትናንት ለሱማሊያ ጦር ያስረከበው፣ በመካከለኛው ሸበሌ ግዛት የሚገኘውን የቡሩንዲ ወታደሮች ጦር ሠፈር ነው። የኅብረቱ ተልዕኮ በኹለተኛው ዙር እስከ መስከረም መገባደጃ ድረስ፣ ሦስት ሺህ ወታደሮቹን ከአገሪቱ የማስወጣት ዕቅድ አለው። ባለፈው ሰኔ በመጀመሪያው ዙር፣ ኹለት ሺህ የኅብረቱ ወታደሮች ከሱማሊያ መውጣታቸው ይታወሳል። ኅብረቱ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በታኅሳስ 2024 ዓ፣ም ወታደሮቹን ሙሉ በሙሉ ከሱማሊያ ጠቅልሎ ለማስወጣት አቅዷል።
6፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 78ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በኒውዮርክ ተጀምሯል። ላንድ ሳምንት የሚቆየው ጠቅላላ ጉባዔው፣ የዘላቂ ልማት ግቦችና የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። በጉባዔው ከሚሳተፉት የአፍሪካ መሪዎች መካከል የኬንያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የሩዋንዳ፣ የደቡብ አፍሪካና የናይጀሪያ መሪዎች የሚገኙበት ሲኾን፣ አፍሪካዊያን መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት የደረሰባት አፍሪካ ከበለጸጉ አገራት ፍትሃዊ የኾነ የማካካሻ የገንዘብ ድጋፍ እንድታገኝና ዓለማቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲሻሻል ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ መስከረም 8/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ከተማ ዕሁድ'ለት የድሮን እንደኾነ በተገመተ ጥቃት 16 ወጣቶች እንደተገደሉ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል። በጥቃቱ ሌሎች ሦስት ሰዎች ቆስለዋል መባሉን ዘገባው ገልጧል። የዓይን ምስክሮች፣ ሟቾቹ የፋኖ ታጣቂዎች ደጋፊ የኾኑ ያልታጠቁ ወጣቶች እንደኾኑ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በአከባቢው ከቅዳሜ ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቱ ቀጥሎ ሰንብቷል ተብሏል።
2፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማዕከላዊ ዕዝ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ከመስከረም 7 ቀን ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በባለኹለት እግር የሞተር ሳይክል ተሸከርካሪዎች ላይ እገዳ ጥሏል። ማዕከላዊ ዕዙ በከተማዋ በባለኹለት እግር ሞተር ሳይክሎች ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ የጣለው፣ ባለኹለት እግር ሳይክሎች ለሕግ ማስከበር ሥራ ስጋት ናቸው በማለት ነው።
3፤ የኢትዮጵያ የመርከብና ሎጅስቲክስ ድርጅት አጠቃላይ የሃብቱን መጠን በአራት እጥፍ ለማሳደግ ጥያቄ ማቅረቡን ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል። ድርጅቱ ያቀረበው ጥያቄ፣ የካፒታል መጠኑን አኹን በመንግሥት ከተፈቀደለት 20 ቢሊዮን ብር ወደ 90 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ እንደኾነ ከምንጮቹ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። ድርጅቱ የካፒታሉን መጠን እንዲያሳድግ ፍቃድ የሚፈቅደው፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ነው። ከዓመት በፊት በነበረው የፋይናንስ ሪፖርት፣ የድርጅቲ አጠቃላይ ካፒታል 65 ቢሊዮን ብር ደርሶ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል።
4፤ ከኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሐዲድ በቅርብ ርቀት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሱሞኑን ግጭቶች እንደተካሄዱ ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮች ሰምታለች። በኹለቱ ወገኖች መካከል ግጭቶች የተካሄዱት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ከተማና አካባቢዋ እንደኾነ ተሰምቷል። የግጭቱ አካባቢ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ጋር የሚዋሰን ነው። በግጭቱ ዋናው አውራ ጎዳና ለአጭር ጊዜ ተዘግቶ ነበር ተብሏል።
5፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜን አሜሪካ በሚያደርገው በረራ የአየርላንዷን ደብሊን ከተማ ጊዜያዊ ማረፊያው ማድረግ ለማቆም መወሰኑን የአቬሽን ድረገጾች ዘግበዋል። አየር መንገዱ በደብሊን ፋንታ፣ በጣሊያኗ ሮም ከተማ አጭር ቆይታ ያድርጋል ተብሏል። አየር መንገዱ እስካኹን በነበረው የበረራ መስመሩ፣ ደብሊን ላይ አውሮፕላን ሳይቀይር በትንሹ የ50 ደቂቃ ቆይታ ያደርግ ነበር። አየር መንገዱ፣ ወደ አሜሪካ እና ካናዳ ከተሞች በሳምንት ከ21 በላይ በረራዎችን ያደርጋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ መስከረም 8/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ሰሞኑን በሱማሌ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ግጭት እንደተከሰተ ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮቿ ተረድታለች። ግጭቱ የተካሄደው፣ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ወደ ሱማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጅግጅጋ ከተማ በሚወስደው መስመር በባቢሌ ከተማ አቅራቢያ እንደነበር ታውቋል። ግጭቱ በትክክል በየትኞቹ አካላት መካከል እንደተካሄደ ግን ለጊዜው ማረጋገጥ አልተቻለም። በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ላይ ኹለቱ ክልሎች ቀደም በይገባኛል ጥያቄ ሲወዛገቡ የነበረ ሲኾን፣ ከጥቂት ዓመታት በፊትም ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የኾነ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። የሰሞኑን ግጭትና ውጥረት ተከትሎ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው እንደተሠማራ ተሰምቷል።
2፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪት ወረዳ ዕሁድ'ለት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ከነዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
በወረዳው በኹለት ቦታዎች ላይ የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙና 30 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት የተፈጸመው ከውጊያ ቀጠና ውጭ ሰላማዊ ሰዎች በብዛት ይንቀሳቀሱበት በነበረው ባንዱ ቦታ ላይ ብቻ እንደኾነ ነዋሪዎች እንደተናገሩ ዘገባው ጠቅሷል። ሌላኛው የድሮን ጥቃት ጫካ ላይ በማረፉ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እንዳላደረሰ መረዳቱን ዘገባው አመልክቷል። በተመሳሳይ ቀን በደምበጫ ከተማ ባንድ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት ደሞ፣ በትንሹ 18 ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል ተብሏል።
3፤ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በአማራ ክልል መተማ ወረዳ በኩመር የሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 400 የሚጠጉ ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው ሕክምና ላይ እንደሚገኙ ዛሬ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። በኩመር ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በኮሌራ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ቢሮው ገልጧል። በኮሌራ ወረርሽኙ መስፋፋት ሳቢያ፣ አዲስ የሚገቡ ሱዳናዊያን ስደተኞችን ከመተማ የስደተኞች መቀበያ ጣቢያ ወደ ኩመር መጠለያ ማዕከል የማጓጓዝ ሥራ ለጊዜው መቆሙን ቢሮው አመልክቷል። የሱዳኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞችና ተመላሾች ብዛት 80 ሺህ 500 ደርሷል ተብሏል።
4፤ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በታላላቅ ወንዞች መሙላት በተፈጠረው ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መንግሥታዊና የረድዔት ድርጅቶች አስቸኳይ ዕርዳታ እንዲያደርጉለት ጠይቋል። የጎርፍ መጥለቅለቁ የተከሰተው፣ ባሮ፣ አኮቦ፣ አልዌሮ እና ጊሎ የተባሉት ወንዞች ከልክ በላይ በመሙላታቸው እንደኾነ የክልሉ መንግሥት ገልጧል። በተለይ በኑዌር ዞን በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ እና ጆር ወረዳዎች በርካታ ሕዝብ ከቀየው ተፈናቅሏል ተብሏል። በአደጋው የጠፋ የሰው ሕይወት ይኑር አይኑር ግን የክልሉ መንግሥት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያወጣው መረጃ የለም።
5፤ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ኒውዮርክ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ነው። ደመቀ ከጉባዔው በተጓዳኝ፣ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ እና የሌሎች አገራት ልዑካንና ባለሥልጣናት ጋር በኹለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። ትናንት የአገራት መሪዎች የተሳተፉበት ጉባዔ በተመድ የዘላቂ ልማት ግቦች ላይ የተወያየ ሲኾን፣ ቀደም ሲል አገራት የደረሱበትን የአዲስ አበባውን የድርጊት መርሃ ግብር መተግበር እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ተሰጥቶበታል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ዓለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ባስቸኳይ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
6፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት እና የምሥራቃዊ ሱዳን የጎሳ ታጣቂዎች ትናንት በሰሜናዊቷ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ተጋጭተዋል። ግጭቱ የተከሰተው፣ "የምሥራቃዊ ሱዳን ተቃዋሚ ቡድኖች ኅብረት" አጋር የኾኑ የጎሳ ታጣቂዎች በከተማዋ መንገዶች ላይ ኬላዎችን ማቆማቸውን ተከትሎ እንደኾነ ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። ፖርት ሱዳን ላይ በሱዳን ጦር ሠራዊትና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል በሚያዝያ ወር ለጥቂት ቀናት ግጭት ከመካሄዱ በስተቀር፣ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በጦር ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ኾና ነው የቆየችው። ከካርቱም የሸሹ የአገሪቱ አንዳንድ መስሪያ ቤቶችና ዓለማቀፍ ድርጅቶችም መቀመጫቸውን ያደረጉት ፖርት ሱዳን ላይ ነው።
7፤ አውሮፓ ኅብረት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሱማሊያ የድርቅ ተጎጂዎች ለሚሰጠው የምግብ ዕርዳታ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ለጊዜው ማቋረጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ኅብረቱ የገንዘብ ድጋፉን ለጊዜው ያቋረጠው፣ ለድርቅ ተጎጂዎች በተለገሰው ዓለማቀፍ የምግብ ዕርዳታ ላይ "መጠነ ሰፊ ሥርቆት" እና "ምዝበራ" እንደተፈጸመ ተመድ በምርመራ ማረጋገጡን ተከትሎ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ዓመት ለሱማሊያ ከመደበው 1 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ውስጥ፣ አውሮፓ ኅብረት የለገሰው 7 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። በምግብ ዕርዳታ ላይ በተፈጸመው "መጠነ ሰፊ ዝርፊያ" እና "ምዝበራ" የተሳተፉ አካላትን ማንነት ዘገባው አልጠቀሰም።
8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ1793 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ2829 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 65 ብር ከ2853 ሳንቲምና መሸጫው 66 ብር ከ5910 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ8432 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ0201 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ መስከረም 9/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1. በኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንዲሁም አሁን ድረስ በዘለቀው የአማራና የኦሮምያ ክልሎች በቀጠለው ጦርነት ተፈፅመዋል የተባሉ ብርቱ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበውን ክስ ለመከላከል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ካውንስል ዛሬ አልያም ነገ ቀርበው እንደሚከላከሉ ይጠበቃል። ካውንስሉ ያቋቋመው አጣሪ የባለሙያዎች ቡድን የምርመራ ግኝቱን ሰኞ ዕለት ለህዝብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ካውንስሉ በሪፖርቱ ላይ ነገ ይወያያል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ “የጦር ወንጀል” ፣ “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል” ና ግፍ መፈፀሙን የሚያመላክት መረጃ አግኝቻለሁ ብሏል። ጉዳዩ በአለማቀፍ መርማሪ እንዲጣራም መክሯል። የኢትዮጵያ መንግስት የአጣሪ ባለሙያዎቹ ቡድን እንዲበተን ይፈልጋል።
2፤ ኢሰመኮ በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ በተቀሰቀሰ “የተስቦ በሽታ” ሦስት ሰዎች እንደሞቱ አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢሰመኮ፣ በጊዜያዊ ማቆያ ማዕከሉ የሚገኙት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከጎዳና የታፈሱ እንደኾኑ ገልጧል። ኢሰመኮ ክትትል ባደረገበት ወቅት 190 ሰዎች ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እንዳገኙና ሦስቱ በጽኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ እንደነበሩ ማረጋገጡን ኢሰመኮ ጠቅሷል። የሰዎቹን ሰብዓዊ ክብርና አያያዝ የሚያረጋግጥ በቂ የምግብ፣ የውሃ፣ የመኝታ፣ የንጽሕናና የሕክምና አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲሟሉ ያሳሰበው ተቋሙ፣ ሰዎችን በግዳጅ በማቆያ ማዕከል የማስገባት አስገዳጅ አሠራር "ባስቸኳይ እንዲቆምም" ጠይቋል።
3፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሰሜኑ ጦርነቱ የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ለቤተሰቦቻቸው ሊያረዳ መኾኑን አስታውቋል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ አዲስ የጦር ጉዳተኞች ማዕከል ባስመረቁበት ወቅት "በሺዎች" የሚቆጠሩ የትግራይ ተዋጊዎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን እንዳጡ ተናግረዋል። የመርዶ ማርዳቱ መርሃ ግብር በትክክል መቼ እንደሚካሄድ ግን ጌታቸው አልገለጡም። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የሟች ተዋጊዎችን ቤተሰቦች እንደሚደግፍም ጌታቸው ተናግረዋል።
4፤ በትግራይ ክልል ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በክልሉ "መሠረታዊ ለውጥ" ለማምጣት ሰላማዊ ትግላችን እንቀጥላለን ሲሉ ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ፓርቲዎቹ፣ ባለፈው ጳጉሜ በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በሞከርንበት ወቅት የክልሉ ጸጥታ ኃይሎች የመብት ጥሰት አድርሰውብናል በማለት ከሰዋል። በክልሉ ሰላማዊ ትግላቸውን እንደሚገፉበት ያረጋገጡት፣ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ ሳልሳዊ ወያነ እና የታላቋ ትግራይ ኮንግሬስ ፓርቲ (ባይቶና) ናቸው። የፓርቲዎቹን መግለጫ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቦታል።
5፤ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ቆርኬ ከተማ ባለፈው ዕሁድ በተከሰተው ግጭት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች እንደተገደሉና ከኹለት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ ዶይቸቨለና ቪኦኤ የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሰው ዘግበዋል። በቆርኬ ከተማ ላይ ጥቃት የከፈቱት፣ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ናቸው ሲሉ ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች ግን፣ ግጭቱ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እንደተካሄደ ተናግረዋል ተብሏል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ መስከረም 9/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በረቂቅ የሽግግር ፖሊሲው ዙሪያ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር የኹለትዮሽ ውይይት ለማድረግ ኹኔታዎች እንዲመቻቹለት ለፍትሕ ሚንስቴር በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በፍትሕ ሚንስቴር ሥር የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን ባዘጋጀው ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲና በፖሊሲው ሂደት ላይ ልዩነቶች እንዳሉትና ለልዩነቶቹ መፍትሄ ለመፈለግ የኹለትዮሽ መድረክ አስፈላጊ መኾኑን እንደገለጠ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። ፍትሕ ሚንስቴር ነሃሴ 26 ቀን 2015 ዓ፣ም "በሽግግር ፖሊሲ አማራጮች" ዙሪያ ባዘጋጀው አገር ዓቀፍ ውይይት ላይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲሳተፍ ተጠይቆ፣ በጊዜው በውይይቱ መገኘት እንደማይችል እንዳሳወቀ መረዳቱንም ዘገባው አመልክቷል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀኔራል ጻድቃን ገ/ተንሳይ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ያነሱት አንዱ ልዩነት፣ ረቂቅ ፖሊሲው የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መሠረት አላደረገም የሚል ነው ተብሏል።
2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሰሜኑ ጦርነቱ የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ለቤተሰቦቻቸው ሊያረዳ መኾኑን አስታውቋል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ አዲስ የጦር ጉዳተኞች ማዕከል ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ "በሺዎች የሚቆጠሩ" የትግራይ ተዋጊዎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን እንዳጡ ተናግረዋል። ለሟች ቤተሰቦች መርዶ የማርዳቱ መርሃ ግብር በትክክል መቼ እንደሚካሄድ ግን ጌታቸው አልገለጡም። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የሟች ተዋጊዎችን ቤተሰቦች እንደሚደግፍ ጌታቸው ቃል ገብተዋል።
3፤ በኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንዲኹም አኹን ድረስ በቀጠለው የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች ግጭት ተፈጽመዋል የተባሉ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበውን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ዛሬ ወይም ነገ ቀርበው እንደሚከላከሉ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ ያቋቋመው የባለሙያዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን የምርመራ ግኝቱን ሰኞ'ለት ለሕዝብ ይፋ ያደረገ ሲኾን፣ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም በሪፖርቱ ላይ ነገ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ “የጦር ወንጀል”፣ “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል” እና ግፎች እንደተፈጸሙ የሚያመለክት መረጃ አግኝቻለኹ ብሏል። ኮሚሽኑ፣ የመብት ጥሰቶቹ በዓለማቀፍ መርማሪ እንዲጣሩም ጥሪ ማቅረብ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት መርማሪ ኮሚሽኑ እንዲበተን ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል።
4፤ መከላከያ ሠራዊት በሱማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በምዕራባዊ ሱማሊያ "ሮብ ድሬ" በተባለ ቦታ ላይ በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሸባብ ላይ ከባድ የአጸፋ ርምጃ የወሰዱት፣ የቡድኑ ታጣቂዎች የደፈጣ ጥቃት ለማድረስ መሞከራቸውን ተከትሎ እንደኾነ ሠራዊቱ ገልጧል። አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የደፈጣ ጥቃቱን የፈጸመው፣ ሦስት ፈንጂ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን፣ 12 ፈንጂ የታጠቁ ታጣቂዎቹን እና ሌሎች ከ450 በላይ የሚኾኑ ታጣቂዎቹን በማሰለፍ እንደኾነ ሠራዊቱ አስታውቋል። በምዕራብ ሱማሊያ ባኮል ግዛት ከኢትዮጵያ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች በኹለት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ካሚዮኖች ላይ የደፈጣ ጥቃቶችን ባለፈው ዕሁድ ጧት እንደፈጸሙና ይህንኑ ተከትሎ ለሰዓታት የዘለቀ ውጊያ እንደተካሄደ ተዘግቦ ነበር። ከነጻ ምንጭ ባይረጋገጥም፣ አልሸባብም በውጊያው 167 ወታደሮችን ገድያለኹ ማለቱ ይታወሳል።
5፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ 125 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በኹለት ዙር ከጎረቤት ጅቡቲ ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል። ፍልሰተኞቹ ወደ አገራቸው በባቡርና በአውሮፕላን ወደ አገራቸው የተመለሱት፣ ከዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው። በነገው ዕለት ደሞ 95 ተጨማሪ ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው እንደሚጓጓዙ ኢምባሲው ዛሬ ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ የመን እና ሳዑዲ ዓረቢያ ለመግባት መሸጋገሪያ አድርገው የሚጠቀሙት ጅቡቲን ነው።
6፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ እና የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ እል ቡርሃን ወደ ኒውዮርክ አቅንተዋል። ጀኔራል ቡርሃን ወደ ኒውዮርክ የተጓዙት፣ በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው። ጀኔራል ቡርሃን በመጭው ዓርብ ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠብቅ ሲኾን፣ ከጉባዔው በተጓዳኝ ከተለያዩ አገራት መሪዎችና የዓለማቀፍ ድርጅቶች ባለሥልጣናት ጋር ጭምር ለሱዳኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ማስገኘት በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። ጀኔራል ቡርሃን ከሰሜናዊቷ ፖርት ሱዳን ከተማ የተነሱት፣ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር የኾኑትን ማሊክ አጋርን እና ሚንስትሮቻቸውን አስከትለው ነው።
7፤ ከሱዳኗ ካርቱም አቅራቢያ በሩሲያው የግል የጸጥታ ኩባንያ ዋግነር ይታገዛል በሚባልለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ላይ ከተፈጸሙት ተከታታይ የድሮንና የምድር ላይ ወታደራዊ ጥቃቶች ጀርባ የዩክሬን ልዩ ጦር እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር በምርመራዬ ደርሼበታለኹ ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል። በትንሹ ካርቱም አካባቢ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ጥቅም ላይ የዋሉት ኹለት ድሮኖች፣ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት የምትጠቀምባቸው ድሮኖች እንደኾኑ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቅሷል። ከጥቃቶቹ ጀርባ የዩክሬን ልዩ ጦር እጃ ሊኖርበት ይችላል የሚል መረጃ ከአንድ ስሙን ካልጠቀሰው የዩክሬን ወታደራዊ ምንጭ መስማቱን የጠቀሰው ዜና ምንጩ፣ የዩክሬን መከላከያ ሚንስቴር ግን መረጃውን ለማረጋገጥም ኾነ ለማስተባበል አልፈልግም ማለቱን ገልጧል። ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ከምታደርገው ጦርነት ጋር በተያያዘ፣ ከሩሲያ ውጭ በሌላ አገር ዒላማ ላይ ጥቃት ሳትፈጽም እንዳልቀረች ሲዘገብ የአኹኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ1843 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ2880 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 65 ብር ከ3387 ሳንቲምና መሸጫው 66 ብር ከ6455 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ከ0472 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ2281 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ መስከረም 10/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የስደተኞችና ተፈናቃዮች ኹኔታ ማሽቆልቆሉ "በእጅጉ እንዳሳሰበው" አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በስደተኞችና የተፈናቃዮች መጠለያዎች አሳሳቢ የምግብ አቅርቦት እጥረት መኖሩን የጠቀሰው ኢሰመኮ፣ በተለይ በጋምቤላ ክልል በስደተኞች መጠለያዎች ከሦስት ወራት በላይ የምግብ ዕርዳታ እንዳልቀረበ ገልጧል። የስደተኞችና ስደት ተመላሾች አገልግሎትም፣ በክልሉ በምግብ እጥረት 30 ስደተኞች በርሃብ ሳቢያና ከመጠለያ ውጭ ምግብ ፍለጋ ላይ ሳሉ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሞታቸውን ገልጦልኛል ብሏል። ኢሰመኮ፣ ችግሩን ለመፍታት፣ ዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያቋረጡትን የምግብ ዕርዳታ ባስቸኳይ እንዲጀምሩ ጥሪ አድርጓል።
2፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሚገኘው የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ አንድ አምቡላንስ ማክሰኞ'ለት "ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች" በግዳጅ እንደተወሰደበት አስታውቋል። ማኅበሩ፣ ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለማቀፉን የጄኔቫ ስምምነት እንደሚጻረርና ከማኅበሩ ዓላማ ውጭ እንደኾነ ገልጧል። ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት አምቡላንሱን እንዲመልሱና አምቡላንሱ ሰብዓዊ አገልግሎቱን እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ማኅበሩ ተማጽኗል። የማኅበሩ ሠራተኞች፣ በጎ ፍቃደኞች፣ አምቡላንሶችና ሌሎች የማኅበሩ ተሽከርካሪዎች ደኅንነታቸው ተረጋግጦ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ፣ በአገሪቱ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ማኅበሩ ጠይቋል።
3፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአማራ ክልል ከታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በክልሉ ምንም ዓይነት ጊዜያዊ ማቆያ የለም ሲል ትናንት በድጋሚ ማስተባበሉን ዶይቸቨለ ዘግቧል። የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ለጣቢያው በሰጠው ቃል፣ በሸገርም ኾነ በፍቼ ከተሞች አንዳችም የሰዎች ማቆያ ማዕከል እንደሌለ በመግለጽ አስተባብሏል። ኢሰመኮ ግን፣ በክልሉ ሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ በኋላ ጭምር በአዲስ አበባ ከጎዳና ተዳዳሪነት የታፈሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገኙበት ማቆያ ማዕከል እንዳለ ትናንትም ኾነ ቀደም ሲል ባወጣቸው መግለጫዎች መግለጡ ይታወሳል።
4፤ ዩክሬን በኬንያው ሞምባሳ ወደብ የምግብ እህል ማከማቻ መጋዘን ለማቋቋም ከኬንያ ጋር ስምምንነት ላይ ደርሳለች። ኹለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፣ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በተጓዳኝ ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። የኹለትዮሽ ስምምነቱ፣ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚታየውን የምግብ እጥረት ለማቃለል ያለመ እንደኾነ ተገልጧል። ስምምነቱ መቼ ተግባራዊ እንደሚኾን ግን መሪዎቹ አልጠቀሱም።
ምሽት በአዳዲስ መረጃዎች እንጠብቃችኃለን [ዋዜማ]

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ውጥረት ነግሷል።
ግጭቱ እንዴት እንደተቀሰቀሰ ዋዜማ ያሰባሰበችውን መረጃ አንብቡት-- https://tinyurl.com/yckpxt9t

በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት የከረረ ብሔር ተኮር ውጥረት አስከትሏል - Wazemaradio
ዋዜማ- ከሰሞኑ በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ባቢሌ አካባቢ በጫት ቀረጥ ሰበብ የተቀሰቀሰው ግጭት ውጥረት መፍጠሩን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርበት ካለቸው ምንጮች ተረድታለች፡፡ ግጭቱ የብሔር መልክ የያዘው ከኦሮሚያ በኩል የተነሱ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ዩኒፎርም የለበሱ የታጠቁ ኃይሎች፣ በቆሎጂ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በሰፈሩ የሶማሌ ተፈናቃዮች ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነው። የኦሮሚያ ክልል ኃይሎች በተፈናቃዮቹ…
ለቸኮለ! ዓርብ መስከረም 11/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያ ጀኔቫ ላይ እየተካሄደ ባለው የተመድ ሰብዓዊ ምክር ቤት 54ኛ ስብሰባ ምክክር ላይ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ባለሙያዎች ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግሥት "የጦር ወንጀሎችን" እና "በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን" ፈጽሟል በማለት በቅርቡ ያቀረባቸውን ክሶች ውድቅ አድርጋለች። የመንግሥትን ምላሽ የሰጡት በጀኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋዓብ ክበበው፣ የመርማሪ ኮሚሽኑን ሪፖርት "ከደረጃ በታች የኾነ"፣ "በጥቂት ስደተኞች ቃል" እና "በማኅበራዊ ትስስር ዘዴዎች ላይ በወጡ መረጃዎች ላይ የተመሠረተ" እና "ፖለቲካዊ ዓላማ ያዘለ" በማለት አጣጥለውታል። አምባሳደር ጸጋዓብ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ተከትሎ ለወሰዳቸው አዎንታዊ ርምጃዎች መርማሪ ኮሚሽኑ ዕውቅና አለመስጠቱ ኢትዮጵያን እንዳሳዘናትም ገልጸዋል። ኮሚሽኑ "በግጭት አባባሽ ድርጊት ተጠምዷል" በማለትም ጸጋዓብ ከሰዋል።
2፤ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘው ላሊበላ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ተኩስ ረቡዕ'ለት ሌሊት ስትናጥ እንዳደረች መስማቱን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። የመንግሥት ኃይሎች ከከተማዋ መሃል ከባድ መሳሪያ ይተኩሱ የነበረው፣ የፋኖ ታጣቂዎች መሽገውበታል ወደተባለ ገጠራማ ቦታ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። የመንግሥት ኃይሎች የፋኖ ደጋፊዎች ያሏቸውን ወጣቶች ለመያዝ በከተማዋ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ እንዳሠሩ የዓይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል። ኾኖም ትናንት በከተማዋ መጠነኛ መረጋጋት እንደሰፈነ ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል።
3፤ ሰሞኑን በሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ባቢሌ ከተማ አካባቢ በጫት ቀረጥ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ግጭት የብሄር መልክ እንደያዘ ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርበት ካለቸው ምንጮች ተረድታለች። ግጭቱ የብሄር መልክ የያዘው፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች በቆሎጂ በተባለ ቦታ ላይ በሠፈሩ የሱማሌ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነው። በጥቃቱ ኹለት ሕጻናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች ለዋዜማ ተናግረዋል። የግጭቱ መነሻ ከኦሮሚያ አወዳይ ተነስቶ በጅግጅጋ በኩል ወደ ጎረቤት ሱማሊያ በሚወጣው የጫት ምርት ላይ በኹለቱ ክልሎች መካከል የተነሳ "የቀረጥ ውዝግብ" ነው። የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው፣ የሱማሌ ኃይሎች ካራማራ አካባቢ የነበራቸውን የቀረጥ መቅረጫ ጣቢያ ወደ ባቢሌ ማዛወራቸውና የኦሮሚያዎቹም ወደ ወሰን ተጠግተው ኹለቱም ወገኖች አማካይ ቦታ ላይ የቀረጥ ኬላ ከዘረጉ በኋላ እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
4፤ የአሜሪካ ዓቃቤ ሕግ "ጥብቅ ሚስጢራዊ መረጃዎችን" ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ብሎ በጠረጠረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አብርሃም ተክሉ ላይ ክስ መመስረቱን ሲኤንኤን ዘግቧል። አብርሃም ክስ የተመሠረተበት፣ የአሜሪካ የመከላከያ ሚስጢራዊ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ መረጃዎቹን በግሉ የመያዝ መብት ሳይኖረው ይዞ በመገኘት እና ለሌላ አገር ድጋፍ ለማድረግ ሲል መረጃዎቹን አሳልፎ በመስጠት ወንጀሎች እንደኾነ ተገልጧል። ተጠርጣሪው ከአንድ የውጭ አገር መንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ ከነበረ አማጺ ቡድን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በትንሹ 83 የስለላ መረጃዎችን እንዳስተላለፈ፣ በዚኹ ወቅት ወደዚያችው አገር በተደጋጋሚ እንደተመላለሰና ከዚያች አገር የደኅንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ካንድ ሰው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበረውዘገባው ጠቅሷል። ተጠርጣሪው የሠራባቸው፣ የአሜሪካ ፍትህ እና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች በየፊናቸው በግለሰቡ ላይ ምርመራ ጀምረዋል ተብሏል። በክሱ ላይ የኢትዮጵያ ስም በቀጥታ ባይጠቀስም፣ ዜና ምንጩ ግን በክሱ ሰነድ ላይ "ሌላ የውጭ አገር" ተብላ የተጠቀሰችው አገር ኢትዮጵያ መኾኗን ከምንጮቹ ማረጋገጡን ገልጧል።
5፤ በብሪታንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአጼ ቴዎድሮስ ልጅ የልዑል ዓለማየኹን የጸጉር ዘለላ እና በመቅደላው ጦርነት ወቅት ከመቅደላ የተዘረፈውን የመድሃኒያለም ታቦት ትናንት እንደተረከበ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ኢምባሲው፣ ከልዑል ዓለማየሁ የጸጉር ዘለላ እና ከታቦቱ በተጨማሪ፣ ከብር የተሠሩ ኹለት ዋንጫዎችንና በወቅቱ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ የዋለ አንድ የጦር ጋሻ ተረክቤያለኹ ብሏል። በቅርሶቹ ርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ፣ በብሪታንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለስ፣ የኢትዮጵያ የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንና የብሪታንያ ፓርላማ አባላት እንደተገኙ ኢምባሲው ገልጧል።
6፤ ባሕርዳር ላይ በጥቅምት ወር እንዲካሄድ ታስቦ የነበረው የጣና ፎረም ዓመታዊ የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ወደ ሚያዝያ ወር መተላለፉን ጣና ፎረም አስታውቋል። ፎረሙ፣ "ቀደም ብለው ባልተገመቱ ኹኔታዎች" ሳቢያ የዘንድሮው 11ኛው የፎረሙ የመሪዎች ከፍተኛ ጉባዔ ወደ ሚያዝያ ተላልፏል ብሏል። የጣና ፎረም ከፍተኛ የአፍሪካ መሪዎች፣ የጸጥታ ባለሙያዎችና ምሁራን ከፍተኛጉባዔ ባሕርዳር ላይ መካሄድ የጀመረው፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የሥልጣን ዘመን ነበር። የጣና ፎረምን ጉባዔ የሚያስተባብረው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የሰላምና ጸጥታ ጥናት ኢንስቲትዩት ነው።
7፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥና የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሱዳኑ ጦርነት ወደ ሌሎች የቀጠናው አገራት ሊዘመት ይችላል ሲሉ ትናንት በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር አስጠንቅቀዋል። ጀኔራል ቡርሃን፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በባላንጣቸው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግና ቡድኑንና ከሱዳን ውጭ የሚገኙ ለቡድኑ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን "አሸባሪ" ብሎ እንዱፈርጅ ጠይቀዋል። ጀኔራል ቡርሃን፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሱዳን ውጭ ከተለያዩ "አሸባሪ" እና "ሕገወጥ" ቡድኖች ድጋፍ መጠየቁ፣ ለቀጠናዊና ዓለማቀፍ ሰላምና ጸጥታ ስጋት የደቀነ ኃይል እንዲኾን አድርጎታል ብለዋል። የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ በበኩላቸው ከቡርሃን ንግግር ትንሽ ቀደም ብለው ባሠራጩት መልዕክት፣ "ለተኩስ አቁም" እና "ለኹሉን ዓቀፍ ፖለቲካዊ ንግግር" ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።
8፤ የካናዳዋ ካልጋሪ ከተማ ፖሊስ ባለፈው ነሃሴ መገባደጃ ገደማ በኤርትራዊያን መካከል ተፈጥሮ በነበረው የቡድን ጸብና ብጥብጥ ተሳትፈዋል ያላቸውን 16 ኤርትራዊያን ፎቶ በድረገጹ ይፋ አድርጓል። የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ጎራ ላይተው በፈጠሩት በዚኹ ግጭት፣ አብዛኞቹ ጦር መሳሪያ የያዙ 150 ያህል ኤርትራዊያን እንደተሳተፉ ፖሊስ ገልጧል። ቀሪዎቹን በግጭቱና ኹከቱ የተሳተፉ ኤርትራዊያን ሕዝቡ ለይቶ እንዲጠቁም ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
9፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ1992 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ3032 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ5656 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ8569 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ6712 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ8446 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ መስከረም 12/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ አብን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚፈጽሟቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች "በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ" ጠይቋል። አብን፣ ባስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን "አንድን ሕዝብ በማንነቱ ምክንያት ላልተገባ እንግልትና ሞት" የዳረጉ የመንግሥት አመራሮችና የጸጥታ አካላት በሕግ እንዲጠየቁም አሳስቧል። ጸጥታ ኃይሎች "አካላዊ ድብደባ"፣ "ውድ ንብረቶችን መቀማት"፣ "ማንገላታትና የማዋከብ ድርጊቶች" በስፋት እየፈጸሙ እንደኾነና በአዲስ አበባ ዙሪያ "ጅምር የፋብሪካ መጋዘኖች" የታሳሪዎች ማጎሪያ መኾናቸውን አብን ገልጧል። አብን፣ በብሄራቸው ብቻ ተመርጠው የታሠሩ፣ በግል ቂም፣ በፖለቲካ ልዩነትና ለጥቅም ማስፈጸሚያነት ሲባል በየቦታው የታሠሩ ዜጎች ጉዳያቸው ተመርምሮ በፍጥነት መለቅቅ አለባቸው ብሏል። በበሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ቀበሌ የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነትና ንብረት የመጠበቅ ሃላፊነታቸውን ባለመወጣት ለደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ተጠያቂነት እንዲሰፍንም ፓርቲው ጠይቋል።
2፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአልጀሪያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ወደ ቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የቀጥታ በረራ መጀመሩን አስታውቋል። አየር መንገዱ ከአልጀርስ ወደ አዲስ አበባ ባደረገው የመጀመሪያ በረራው፣ የአገሪቱ የትራንስፖርት ሚንስትር ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እንደተወያዩ ተገልጧል። የኹለቱ አገራት ልዑካን በጥቅምት ወር መጨረሻ በኹለቱ አገራት መካከል በሚደረጉ የቀጥታ መደበኛ የአውሮፕላን በረራዎች ዙሪያ ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል ተብሏል።
3፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም፣ ደጀን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደምበጫ፣ አማኑዔልና ሌሎች ከተሞች የሞባይል ስልክ የመልዕክትና የድምጽ አገልግሎቶች ሰሞኑን ተቋርጠዋል። በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞንም በተመሳሳይ፣ የስልክ አገልግሎቶች መቋረጣቸው ታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በክልሉ በርካታ ከተሞች በተቋረጡ የስልክ አግልግሎቶች ዝዙሪያ ያወጣው መረጃ የለም።
4፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ) ባለፈው ነሃሴ በመቀሌ ከተማ የተቃዋሚዎችን ሰልፍ ሊዘግቡ በወጡት ተሻገር ጽጋብ፣ መሃሪ ካህሳይና መሃሪ ሰለሞን በተባሉ የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ላይ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ የትግራይ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ተጠያቂ እንዲኾኑ ጠይቋል። መሃሪ ሰለሞንና መሃሪ ካህሳይ፣ "በሕገወጥ ሰልፍ ላይ ተሳትፋችኋል" ተብለው ከታሠሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ በዋስትና እንደተለቀቁ ሲፒጄ ገልጧል። ጋዜጠኛ ተሻገርም፣ የታሠረበት ምክንያት ሳይነገረው በዋስትና መፈታቱን ቡድኑ ጠቅሷል። በምሥራቅ አፍሪካ የሲፒጄ ሃላፊ ሙቶኪ ሙሞ፣ የክልሉ አስተዳደር በጋዜጠኞቹ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንዲያጣራ ጠይቀዋል። ሲፒጄ፣ የክልሉ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በጉዳዩ ዙሪያ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡኝም ብሏል።
5፤ ጅቡቲ እና ኢራን ከሰባት ዓመታት በኋላ በድጋሚ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ተስማምተዋል። ኹለቱ አገራት በተለያዩ መስኮች ለመተባበር ጭምር ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ጅቡቲ ከሰባት ዓመታት በፊት ከኢራን ጋር የነባራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠችው፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ተመሳሳይ ርምጃ መውሰዷን ተከትሎ ከሳዑዲ ጋር በመወገን ነበር። ሳዑዲ ዓረቢያና ኢራን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ባለፈው መጋቢት በቻይና አደራዳሪነት እንደገና ማደሳቸው ይታወሳል።
6፤ ሱማሊያ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ኹለተኛውን ዙር የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች የመውጫ ጊዜ ለሦስት ወራት እንዲያዘገይላት ጠይቃለች። ሱማሊያ ለጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ፣ በማዕከላዊ የአገሪቱ ግዛቶች በአልሸባብ ላይ የጀመርኳቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች "ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ እክል ገጥሟቸዋል" ብላለች። አፍሪካ ኅብረት ሦስት ሺህ ወታደሮቹን እስከተያዘው ወር መጨረሻ ለማስወጣት ባለፈው ዕሁድ በጀመረው ኹለተኛው ዙር መርሃ ግብር፣ አንድ የቡሩንዲ ጦር ሠፈር ለሱማሊያ ጦር አስረክቧል። ሱማሊያ ይህንኑ ጥያቄ ያቀረበችው፣ በነሃሴ አጋማሽ አልሸባብ መጠነ ሰፊ ማጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ጦር ሠራዊቷ በቅርቡ ከተቆጣጠራቸው በርካታ አካባቢዎች መሸሹን ተከትሎ ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ መስከረም 12/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኹለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተጀምሯል። ውይይቱ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ እንደኾነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣ አገራቱ በጉዳዮቹ ዙሪያ መግባባት ላይ ለመድረስ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ የሚል ዕምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ስለሺ፣ በመርኾዎች መግለጫ መሠረት በአባይ ወንዝ ውሃ አጠቃቀም ፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህን ማስፈን ብቸኛው አማራጭ መኾኑንም ተናግረዋል። በድርድሩ ላይ፣ የግብጽ የውሃና መስኖ ሚንስትር ፕሮፌሰር ሐኒ ሴዊላም እና የሱዳን ተጠባባቂ የውሃ ሚንስትር ዳውልበይት ተገኝተዋል።
2፤ አዲሱ የንብረት ግብር ረቂቅ አዋጅ አነስተኛ መኖሪያ ቤቶችንና አንዳንድ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ከንብረት ግብር ነጻ አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ ተፈላጊ በኾኑ አከባቢዎች ላይ ከ15 ስኩዌር ሜትር ባነሰ መሬት ላይ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ከንብረት ግብር ነጻ እንዲኾኑ ያደረገ ሲኾን፣ ተፈላጊ ባልኾኑ አካባቢዎች ከ30 ስኩዌር ሜትር ባነሰ ቦታ ላይ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችም በተመሳሳይ ከግብር ነጻ ይኾናሉ ተብሏል። ሌሎች ተቋማትንም ከንብረት ግብር ነጻ ለማድረግ፣ የተቋማቱ የአገልግሎት ዓይነት በመስፈርትነት ታይቷል።
3፤ ኢሰመጉ የፌደራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ የሚፈጽሙትን "ሕግን ያልተከተለ የጅምላ እስር እንዲያቆሙ" እና "ሥልጣናቸውን ያላግባብ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ" ጠይቋል። መንግሥት በአማራ ክልል የሚወስዳቸው የኃይል ርምጃዎች፣ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች በመለየት እንዲፈጸና ከሕግ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግም ኢሰመጉ ጠይቋል። ኢሰመጉ፣ በፌደራል መንግሥቱ እና የአማራ ክልል ታጣቂ ኃይሎች መካከል ውይይት ተደርጎ ግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሰጠውም ጥሪ አድርጓል። ኢሰመጉ አያይዞም፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ካሳ ተሻገር ፍርድ ቤት እንዲቀርቡና የአካል ነጻነት መብታቸው እንዲከበር አሳስቧል።
4፤ የሱማሊያ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች ከአገሪቱ መውጣታቸው እንዲዘገይ ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረቡ ኅብረቱን እንዳላስደሰተ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኅብረቱ ባለሥልጣን መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። ሱማሊያ ጥያቄውን ማቅረብ የነበረባት ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ሳይኾን፣ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ምክር ቤት ሊኾን ይገባ ነበር በማለት ቅራታቸውን መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሱማሊያ እንዲዘገይ የጠየቀችው፣ ባለፈው ሳምንት ዕሁድ የተጀመረውን ኹለተኛውን ዙር ወታደሮችን የማስወጣት ሂደት ነው። ኅብረቱ፣ በመስከረም መጨረሻ በሚጠናቀቀው ኹለተኛው ዙር ሦስት ሺህ ወታደሮቹን ከአገሪቱ ለማስወጣት አቅዷል።
5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት አዛዥ እና የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል ቡርሃን በቅርቡ ከጎበኟቸው አገራት ወታደራዊ ድጋፍ እንዳልጠየቁ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ቡርሃን ጦርነቱን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ እንደኾኑም ገልጸዋል። የጦር ሠራዊቱ ባላንጣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ተኩስ አቁም እንዲደረግና ኹሉን ዓቀፍ ንግግር እንዲደረግ ከቀናት በፊት ጥሪ አድርገው ነበር። [ዋዜማ]

ዋዜማ – በግብፅና በኢትዮጵያን ግንኙነት ላይ አዲስ አቅጣጫ ሊፈጥር የሚችል የህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር ድርድር እየተካሄደ ነው። የዚህ ድርድር ስኬትም ሆነ መፋረስ በግብፅ መንግስት ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶታል። ዝርዝሩን ያንብቡት-https://tinyurl.com/3ft292w2
Wazemaradio
አስገዳጅ ስምምነት ማለት ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? - Wazemaradio
ዋዜማ - በግብፅና በኢትዮጵያን ግንኙነት ላይ አዲስ አቅጣጫ ሊፈጥር የሚችል የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር ድርድር እየተካሄደ ነው። የዚህ ድርድር ስኬትም ሆነ መፋረስ በግብፅ መንግስት ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶታል። ግብፅ በዚህ ድርድር ህጋዊ አስገዳጅነት ያለው ስምምነት እንዲደረስ በእጅጉ አሰላስላ የተዘጋጀችበትን አቋም ይዛ መጥታለች። ግብፅ ባለፉት ስምንት ዓመታት ድርድር ማሳካት የፈለገቻቸውን ጥቅሞቿን ማሳካት…
ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ መስከረም 14/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ትናንት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በተለይ በቀበሌ 17 እና 18 በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተካሂዷል። የከተማዋ ማዕከላዊ የጸጥታ ዕዝ ሠራዊቱ በ"ጽንፈኛ" የፋኖ ታጣቂዎች ላይ በወሰደው ርምጃ የቡድኑን አመራሮች ጨምሮ ከ50 በላይ ታጣቂዎችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉን አስታውቋል። ታጣቂው ኃይል በከተማዋ ዙሪያ ያደረገው የጥቃት ሙከራ "ሙሉ በሙሉ" ከሽፏል ያለው የጸጥታ ዕዙ፣ የቡድኑ ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጥረናል በማለት ያሠራጩት መረጃ "ሃሰት" ነው በማለት አስተባብሏል። ሠራዊቱ በቡድኑ ላይ ርምጃ የወሰደው፣ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ወደ ከተማዋ ሰርጎ የገባው ታጣቂ ኃይል ባንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ እንደኾነ ተገልጧል።
2፤ መከላከያ ሠራዊት "ጽንፈኞች" ሲል በጠራቸው የጎንደር አከባቢ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ ትናንት በጎንደር ከተማ በወሰደው ርምጃ "በርካታ የጽንፈኛ ቡድኑን አመራርና አባላት ሙትና ቁስለኛ" ማድረጉን ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሠራዊቱ፣ "ጽንፈኛው ኃይል" በከተማዋ ቀበሌ 18 አካባቢ የክፍለ ከተማው ቢሮ የማቃጠልና ከሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበር ስኳር፣ ዘይትና ሌሎች ፍጆታዎችን ዘርፏል ብሏል። ሠራዊቱ፣ በተኩስ ልውውጡ ወቅት ተገድለዋል ያላቸውን የተወሰኑ ቡድኑ አመራሮችን ስም ጭምር ጠቅሷል።
3፤ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተደረገው ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ። የግብፅ የውሀና መስኖ ሚኒስቴር ድርድሩ ኢትዮጵያ ቀድሞ ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ዳግም ለውይይት በማቅረቧና አዳዲስ አቋሞች በመያዟ ድርድሩ ውጤታማ አልነበረም ብሏል። የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው ድርድሩ ገንቢ ውይይት የተደረገበት ነበር፣ በትብብር መንፈስ ድርድሩን ወደፊት ለመቀጠል ዝግጁ ነን ብለዋል።
4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ49 በመቶ ድርሻ እንደገና እያቋቋመው የሚገኘውን የናይጀሪያ አየር መንገድ የአገሪቱ መንግሥት ለጊዜው እንዳገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማረጋገጡን ሪፖርተር አስነብቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያን አየር መንገድ በአዲስ መልክ የማቋቋም ሃላፊነት የተረከበው፣ በቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሞሐመዱ ቡሃሪ የሥልጣን ዘመን ነበር። አዲሱ የናይጀሪያ መንግሥት ግን የናይጀሪያ አየር መንገዱ በረራ እንዳይጀምር ያገደው፣ ስምምነቱን ከተግባራዊነት በፊት መገምገም ስለፈለገ እንደኾነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። የአዲሱ አየር መንገድ የአክሲዮን ባለድርሻዎች ገና የአክሲዮን ክፍያቸውን አልፈጸሙም ተብሏል። የናይጀሪያ መንግሥት በአዲሱ አየር መንገድ የያዘው ድርሻ አምስት በመቶ ብቻ ነው።
5፤ የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ትናንት ጅቡቲ ውስጥ ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ጋር ተወያይተዋል። የፕሬዝዳንት ሞሐመድ እና የኦስቲን ውይይት፣ ሱማሊያ ከአልሸባብ ጋር እያደረገች ባለችው ውጊያ፣ ሱማሊያና አሜሪካ በጸጥታ መስክ ባላቸው ትብብር እና የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱማሊያ ላይ በጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ዙሪያ እንደኾነ ተገልጧል። ኦስቲን ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል ጌሌ ጋር ጭምር በኹለትዮሽ የጸጥታ ትብብር ዙሪያ የሚወያዩ ሲኾን፣ ከጅቡቲ ቀጥሎ ወደ ኬንያና አንጎላ ያቀናሉ።
6፤ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ሱማሊያ እና ራስ ገዟ ሱማሌላንድ እንዲዋሃዱ የማሸማገል ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ይህን ያስታወቁት፣ የሱማሌላንዱን ልዩ መልዕክተኛ ጃማ ሙሴ ጃማን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ ነው። ሙሴቪኒ፣ ኡጋንዳ መገንጠልን አትደግፍም በማለት ለሱማሌላንዱ ልዩ መልዕክተኛ እንደነገሯቸው ጽሕፈት ቤታቸው አመልክቷል።
7. ፈረንሳይ በቅርቡ መፈንቅለ መንግስት ከተደረገባት ኒጀር ወታደሮቿን ሙሉ በሙሉ ለማስወጣትና አምባሳደሯንም ወደ ሀገርቤት ለመመለስ መወሰኗን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቀዋል። የፈረንሳይ ወታደሮች በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ ከኒጀር ለቀው ይወጣሉ። ፈረንሳይ በኒጀር አንድ ሺህ አምስት መቶ ወታደሮች ያህል ያሏት ሲሆን የፀረ ሽብር ወታደራዊ ተልዕኮ የነበራቸው ናቸው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ መስከረም 14/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢዜማ ሊቀመንበሩ ጫኔ ከበደ ትናንት በመንግሥት ጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዛሬ ቀትር ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የጸጥታ አካላቱ ጫኔን በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው፣ "ታርጋ ቁጥር በሌለው መኪና" እና "ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ኹኔታ" እንደኾነ ፓርቲው ገልጧል፡፡ ፓርቲው፣ መግለጫውን እስካወጣበት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ጫኔ በምን ምክንያት እንደተያዙ አለማወቁንም አመልክቷል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ኮሚቴ ማቋቋሙን የገለጠው ኢዜማ፣ ይህን መሰል "ሕግና ሥርዓት ያልተከተለ" እርምጃ በጽኑ አወግዛለኹ ብሏል።
2፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ሦስተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ ድርድር በቀጣዩ ወር ካይሮ ውስጥ ለመቀጠል መስማማታቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በኹለተኛው ዙር ድርድር ሦስቱ አገራት የጋራ መግባባት ላይ ሊደርሱባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እመርታ እንዳሳዩ ሚንስቴሩ ገልጧል። ኢትዮጵያ በኹለተኛው ዙር ድርድር "በቅን መንፈስ" መደራደሯን የገለጠው ሚንስቴሩ፣ የግብጽ ተደራዳሪ ቡድን ግን እኤአ በ2015 ዓ፣ም ስምምነት ላይ የተደረሰበትን የመርኾዎች መግለጫ የሚጻረር አቋም ይዞ ቀርቧል ብሏል። ሚንስቴሩ፣ ግብጽ "አግላይ የኾኑ የቅኝ ግዛት ውሎችን የሙጥኝ ብላ መያዟ"፣ "በናይል ወንዝ ላይ በብቸኛነት የመጠቀም ፍላጎቷ" እና "ለራሷ የውሃ ድርሻ መወሰኗ" በድርድሩ ሂደት መሠረታዊ ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ኾኗል በማለትም ወቅሷል። የኢትዮጵያ አቋም፣ የሦስትዮሽ ድርድሩ ዓላማ የሦስቱን አገራት ፍላጎት በሚያስጠብቅ መልኩ በግድቡ ሙሌትና ውሃ አለቃቀቅ ዙሪያ የተጀመረውን ድርድር መቋጨት እንደኾነ ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በተጀምረው የድርድር ሂደት ኹሉንም አሸናፊ ከሚያደርግ ስምምነት ለመድረስ ጥረቷን እንደምትቀጥል ሚንስቴሩ አረጋግጧል።
3፤ በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማዕከላዊ ዕዝ መስከረም 16 እና 17 ለሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት በአማራ ክልል በአደባባይ በሚደረጉ መሰብሰቦች ላይ የጣለውን እገዳ ለጊዜው ማነሳቱን አስታውቋል። ማዕከላዊ ዕዙ፣ በመሰብሰብ መብት ላይ የተጣለውን እገዳ ማንሳት ያስፈለገው፣ ለሃይማኖታዊ በዓላቱ እና የበዓላቱ ስነ ሥርዓት ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ብቻ መኾኑን ገልጧል።
4፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግር እና ባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን ጧት 12:00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ መጣሉን አስታውቋል። እገዳው የጸጥታና የትራፊክ ተቆጣጣሪ አካላትን እንደማይመለከት የገለጠው ቢሮው፣ እገዳውን በሚተላለፉ ሌሎች አካላት ላይ ግን ጥብቅ ርምጃ እወስዳለኹ በማለት አስጠንቅቋል። የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ በተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ላይ የእንቅስቃሴና የትራንስፖርት አገልግሎት እገዳ የጣለበትን ምክንያት ግን አላብራራም። ባለፈው ከሐምሌ እስከ ነሃሴ በሞተር ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተመሳሳይ እገዳ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።
5፤ ራስ ገዝ ሱማሌላንድ ከሱማሊያ ጋር የሚደረግ ድርድር በመገንጠል ዙሪያ ብቻ እንጅ በውህደት ዙሪያ ሊኾን አይችልም በማለት ዛሬ አቋሟን አስታውቃለች። ሱማሌላንድ ይህን አቋሟን በድጋሚ የገለጠችው፣ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ሱማሌላንድ ሱማሊያ እንዲዋሃዱ የማሸማገል ጥረት ሊያደርጉ መኾኑን የሱማሌላንዱን ልዩ መልዕክተኛ ጃማ ሙሴ ጃማን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ መግለጣቸውን ተከትሎ ነው። ሙሴቪኒ፣ "ኡጋንዳ መገንጠል ስትራቴጂካዊ ስህተት ስለኾነ አትደግፈውም" በማለት ለሱማሌላንዱ ልዩ መልዕክተኛ እንደነገሯቸው ጽሕፈት ቤታቸው ገልጦ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሱማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካይድ የመሩት ልዑካን ቡድን ትናንት ወደ ጅቡቲ አቅንቶ ከፕሬዝዳንት እስማዔል ጌሌ ጋር ተወያይቷል።
6፤ የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ከቀትር በኋላ ናይሮቢ ገብተዋል። ኦስቲን፣ በኬንያ ጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በኹለትዮሽ የጸጥታና የጸረ-ሽብር ትብብሮችና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ። ኦስቲን፣ ትናንት ጅቡቲን በጎበኙበት ወቅት ከፕሬዝዳንት እስማዔል ጌሌ ጋር በኹለትዮሽ የመከላከያና የጸጥታ ትብብሮች እንዲኹም በቀጠናዊ ጸጥታ ዙሪያ የመከሩ ሲኾን፣ በጅቡቲ የሠፈረውን የአሜሪካውን የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ መጎብኘታቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል። መከላከያ ሚንስትር ኦስቲን፣ ከኬንያ ቀጥሎ ወደ አንጎላ ያቀናሉ።
7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ2080 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ3122 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ6128 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ9051 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ8131 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ9894 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።[ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ መስከረም 15/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ በአስተዳደራዊ "ውስጣዊ ድክመት" ሳቢያ አሽቆልቁሏል ብሏል። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመኾኑን ገልጦ፣ የትግራይ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበት እንደሚገኝም ገልጧል። ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በቅርበት ስለመስራትና ተጨማሪ ፖለቲካዊ ውይይት በማድረግ አስፈላጊነት ዙሪያ ውይይት ማድረጉንም ጠቅሷል። በሰላማዊ ትግል፣ በፓርቲው ውስጣዊ ድክመትና በቀጣይ የፓርቲውና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይ ፕሮግራሞች ላይ ጭምር መወያየቱን ፓርቲው አመልክቷል።
2፤ ዕሁድ'ለት በጎንደር ከተማ በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ሚሊሻዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች እንደተገደሉ ወይም እንደቆሰሉ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ነዋሪዎች ቆስለው ሆስፒታል የገቡ ሰዎችን ወታደሮች ወዳልታወቀ ሥፍራ እንደወሰዷቸው መናገራቸውን የዘገበው ደሞ ቢቢሲ አማርኛ ነው። የፋኖ ታጣቂዎች ከከተማዋ ኹለት ፖሊስ ጣቢያዎች አባሎቻቸውን ጨምሮ "በመቶዎች የሚቆጠሩ" እስረኞችን አስፈትተናል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ትናንት እንደተቋረጠ መኾኑንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዝግ መኾናቸውን ዘገባው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
3፤ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ መንግሥትና ረድዔት ድርጅቶች በአማራ ክልል መተማ ወረዳ "አውላላ" በተባለ መንደር 16 ሺህ ስደተኞችን የሚያስተናግድ አዲስ የስደተኞች መጠለያ ለመገንባት ዝግጅት እያደረጉ መኾኑን አስታውቋል። ቢሮው፣ በኩመር የስደተኞች ጣቢያ በኮሌራ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መቀነሱንም ገልጧል። ባለፈው ሳምንት ወደ ኮሌራ ሕክምና ማዕከል የገቡት ተማሚዎች በቀደመው ሳምንት ከገቡት በሦስት እጥፍ ቀንሶ 54 ታማሚዎች ብቻ ለሕክምና መግባታቸውን ቢሮው ጠቅሷል። በጠቅላላው ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ነሃሴ ጀምሮ፣ 447 ሰዎች ለኮሌራ ሕክምና እንደገቡ የገለጠው ቢሮው፣ 90 በመቶዎቹ እንዳገገሙና ዘጠኝ ታማሚዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ አመልክቷል።
4፤ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳለህ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ኒውዮርክ ውስጥ ተገናኝተው መወያየታቸውን የኤርትራ ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው ገልጠዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ እንዲኹም በኤርትራና በተመድ መካከል በሚኖረው ትብብርና አጋርነት ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር የማነ አስታውቀዋል።
5፤ ኬንያና አሜሪካ ትናንት ናይሮቢ ውስጥ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የመከላከያ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ፣ ኹለቱ አገራት በመከላከያ ቴክኖሎጂ፣ በጸረ-ሽብር፣ በጸረ-ጽንፈኝነት፣ በጋራ ወታደራዊ ልምምድና በባሕር ላይ ደኅንነት መስኮች እንዲተባበሩ ያስችላቸዋል። የአሜሪካው መከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ኬንያ በሃይቲ ለምታሠማራው የፖሊስ ኃይል አሜሪካ የገንዘብና ሎጅስቲክስ ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብተዋል። አሜሪካ በኬንያ ያሠፈረቻቸው ወታደሮች አሏት። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ መስከረም 15/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢሰመጉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ቀበት ከተማ በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ መስከረም 10 ባወጣው መግለጫ ስለደረሰው ሞትና የአካል ጉዳት በዝርዝር ባለመግለጡ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ዘንድ ለተፈጠረው "ቅሬታ" ዛሬ ባወጣው ሌላ መግለጫ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ኢሰመጉ፣ በቀበት ከተማ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ በተፈጸመው ዝርፊያ፣ የንብረት ማውደምና የማፈናቀል ድርጊቶች እንዲኹም ለግጭቱ መነሻ ናቸው የተባሉ ምክንያቶችን በመስከረም 10 ሪፖርቱ ያካተትኩት፣ በክልሉ ሃላባ፣ ሃዲያና ስልጤ ዞንኖች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥራ አስኪያጅ ከኾኑት መልዓከ ሕይወት ንጉሴ ባወቀ ያገኘኹትን መረጃ ብቻ መሠረት አድርጌ ነበር በማለት አብራርቷል። ኾኖም በዕለቱ በጸጥታ ኃይሎች ርምጃ በከተማዋ የአንድ ሙስሊም ሕይወት ማለፉንና በ19 ሙስሊሞች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን በቅርቡ ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መረዳቱን ኢሰመጉ አመልክቷል። ኢሰመጉ፣ ባካባቢው ወደፊት በአካል ጥልቅ ምርመራ አድርጎ ሌላ የተደራጀ ሪፖርት እንደሚያወጣም ቃል ገብቷል።
2፤ በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት የሞቱ ተዋጊዎችን ለቤተሰቦቻቸው የማርዳት ሂደት ተጀምሯል። መርዶው ለቤተሰብ ከተነገረ በኋላ በማኅበረሰቡ ባህል መሠረት ለሟቾች እየተለቀሰና በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት ጸሎት እየተደረገ እንደኾነ ተሰምቷል። ሕዝቡ መርዶው ይነገራል ተብሎ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ከተገለጠበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደቆየ ነዋሪዎችን አነጋግሬ ተረድቻለኹ ሲል ቢቢሲ ኦሮምኛ ዘግቧል። በመርዶው ስነ ሥርዓት ላይ ምን ያህል ተዋጊዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ አልተገለጸም፡፡ በክልሉ ለኹለት ዓመታት ሲደረግ በነበረው ጦርነት ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በፊት የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ 600 ሺህ ገደማ ሰዎች ሞተዋል ማለታቸው ይታወሳል።
3፤ በትግራይ ክልል የክልሉ ጤና ባለሙያዎች እና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በጋራ ባካሄዱት ጥናት ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ወዲህ 1 ሺህ 329 ሰዎች በርሃብ መሞታቸው ተገልጧል። በጥናቱ መሠረት፣ በክልሉ ባኹኑ ወቅት ርሃብ "ዋነኛ የሞት መንስዔ" ኾኗል ተብሏል። ከስምምነቱ በኋላ ጥናት በተደረገባቸው ቦታዎች ከሞቱት ሰዎች መካከል፣ 68 በመቶ ያህሉ የሞቱት ከርሃብ ጋር በተያያዘ እንደኾነ ጥናቱ አመልክቷል። የጥናት ቡድኑ ይህን ያረጋገጠው፣ ባለፈው ነሐሴ ወር በዘጠኝ የተለያዩ አካባቢዎች እና በ53 የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ባደረገው ጥናት መኾኑን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። ዓለማቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ተቋማት በክልሉ በምግብ ዕርዳታ ላይ ሥርቆት ተፈጽሟል በማለት የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ካቋረጡ ወዲህ፣ በርሃብ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ ሲነገር ቆይቷል።
4፤ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም በመንግሥታዊ አገልግሎቶች የብልሹ አሠራር መንስዔ በኾኑ ጉዳዮች ላይ አገራዊ ጥናት ሊያካሂድ መኾኑን ዛሬ አስታውቋል። በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት ወደ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሚመጡ አቤቱታዎች እየጨመሩ መኾኑን የገለጠው ተቋሙ፣ በአስፈጻሚ አካላት አገልግሎት አሰጣጥ የብልሹ አሠራር መንስዔ የኾኑ ጉዳዮች ምን እንደኾኑ ለመለየት አገራዊ ጥናት ማድረግ እንዳስፈለገ ነው የገለጸው። ብዙ ጊዜ የመንግሥትን አመራር አካላትና የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን ጨምሮ የሪፎርምና የለውጥ ሥራዎች ቢሠሩም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት ወደተቋሙ የሚመጡ አቤቱታዎች መጨመራቸው መንስዔው ብልሹ አሠራር ነው ብሎ እንደሚያምን ተቋሙ ጠቁሟል። በ2016 በጀት ዓመት በተጀመረው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደር ልኬታ ላይ ጥናት እንደሚደረገም ተቋሙ ገልጧል።
5፤ በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞንና ደሴ ከተማ ማዕከላዊ የጸጥታ ዕዝ በቀጣዩ ሳምንት ሰኞ የሚከበረውን የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ንግስ ክብረ በዓልን ጨምሮ የመውሊድ፣ ደመራና መስቀል ሃይማኖታዊ በዓላትን የየዕምነቱ ተከታዮች ያለምንም የጸጥታ ስጋት ማክበር እንደሚችሉ አስታውቋል። የጸጥታ ዕዙ በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ወደ ቀድሞ ሰላሙ የተመለሰ መኾኑን ጠቅሶ፣ የየዕምነቱ ተከታዮች በዓላቱን ማክበር የሚችሉበት ኹኔታ ተፈጥሯል ብሏል። የግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን ይከበራል።
6፤ ሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች መውጣት እንዲዘገይ ብትጠይቅም ኅብረቱ ግን ዕቅዴን አልቀይርም ብሏል። አፍሪካ ኅብረት ይህን አቋሙን የገለጠው፣ ሱማሊያ ባለፈው ስምንት የተጀመረው ኹለተኛው ዙር የኅብረቱን ወታደሮች የማስወጣት ሂደት ለሦስት ወራት እንዲዘገይላት ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረቧን ተከትሎ ነው። በሱማሊያ ልዩ ኮማንዶዎች ያሠማራችው አሜሪካ ግን የሱማሊያን ጥያቄ እንደምትደግፍ በሞቃዲሾ የሱማሊያ ኢምባሲ መናገሩን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አፍሪካ ኅብረት በተያያዘው ወር መጨረሻ ከሱማሊያ ሦስት ሺህ ወታደሮቹን ለማስወጣት ዕቅድ የያዘ ሲኾን፣ በአውሮፓዊያኑ ታኅሳስ 2024 ዓ፣ም ደሞ ወታደሮቹን ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት አቅዷል።
7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 55 ብር ከ2124 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 56 ብር ከ3166 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ4967 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ7866 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ7184 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ8928 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ መስከረም 16/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢዜማ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች የሊቀመንበሩን ጫኔ ከበደን መኖሪያ ቤትና ቢሮ እንደፈተሹ መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ዘገባው፣ ፓርቲው በሊቀመንበሩ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንደ "አፈና" እንጂ በሕግ ቁጥጥር ስር እንደማዋል እንደማያየው የፓርቲው የሕግ ክፍል ሃላፊ ሥዩም መንገሻ ነግረውኛል ብሏል። ዕሁድ'ለት የተያዙት ጫኔ፣ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ውስጥ ተይዘው እንደሚገኙና ገና ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ተገልጧል።
2፤ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በአዳማ ከተማ ከመስከረም 03 2016 ዓ፣ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ማጠናቀቁን አስታውቋል። ፓርቲው፣ በስልጠናው ማብቂያ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርቲው ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሥራ መመሪያና ስምሪት መስጠታቸውን ገልጧል። የአመራር አባላቱ ሥልጠና፣ በአገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ፈጥሯል ተብሏል በሥልጠናው ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ኹለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች መሳተፋቸው ተመላክቷል። ፓርቲው፣ ተመሳሳይ ሥልጠና በየደረጃው ለሚገኙ የፓርቲው አመራሮች በቀጣይነት እንደሚሰጥም ገልጧል።
3፤ የእስራኤል መንግሥት በቴላቪቭ ለሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ ከኹለት ዓመት በፊት በ10 ሺዎች የሚገመት ዶላር መክፈሉን እንደደረሰበት ሐርቴዝ ጋዜጣ ዘግቧል። ዜና ምንጩ፣ እስራኤል ገንዘቡን የሰጠችው፣ ለአስተዳደራዊ ወጪዎች መኾኑን ተረድቻለኹ ብሏል። የእስራኤል የኢምግሬሽን ባለሥልጣናት ግን፣ ገንዘቡ ወደ ኤርትራ በፍቃዳቸው ለሚመለሱ ስደተኞች የጉዞ ሰነዶች ማተሚያ የሚውል መኾኑን እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ዘገባው፣ እስራኤል በጥቂት ዓመታት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞችን መመለሷን ገልጧል።
4፤ የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ አዋሳኝ በምሥራቅ ሱዳን ገዳሪፍ ግዛትና ሌሎች አካባቢዎች በኮሌራ ወረርሽኝ 10 ሰዎች ሞተው 162 ሰዎች ወደ ሕክምና ማዕከላት እንደገቡ አስታውቋል። በወባ ትንኝ የሚተላለፈው ደንግ ትኩሳት ወረርሽኝ ጭምር በገዳሪፍ መከሰቱን ድርጅቱ ገልጧል። የአገሪቱ ሐኪሞች ማኅበር በበኩሉ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በምሥራቅ ሱዳን በበሽታው እንደሞቱ ገልጦ፣ ወረርሽኙ "የጤና ቀውስ" ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የገዳሪፍ አዋሳኝ በኾነችው መተማ በሱዳናዊያን ስደተኞች ጣቢያ በነሃሴ በተከሰተ ኮሌራ ወረርሽኝ ከተያዙት 447 ሰዎች መካከል፣ ዘጠኙ መሞታቸውን ተመድ ሰሞኑን አስታውቋል።
5፤ የሱዳን የቀድሞው ሲቪል የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ: የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር ጀኔራል ቡርሃን በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን አውግዘዋል። ሐምዶክና የቀድሞ ባለሥልጣኖቻቸው ለተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጻፉት ደብዳቤ፣ ተመድ ጀኔራል ቡርሃንን መጋበዙ በአፍሪካ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትን የማብረታታት ያህል ነው ብለዋል። የደብዳቤው ፈራሚዎችና ትልቁ የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ የነጻነትና ለውጥ ንቅናቄም፣ ቡርሃን በጠቅላላ ጉባዔው ባደረጉት ንግግር የአገሪቱ ጦርነት የሚፈታበትን ፍኖተ ካርታ አለማመላከታቸውን ክፉኛ ተችተዋል።
ለእስልምናና ለክርስትና እምነት ተከታዮች መላው የዋዜማ ባልደረቦች መልካም በዓል እንመኛለን [ዋዜማ]