ለቸኮለ! ሰኞ ነሐሴ 16/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያና ሱማሊያ ግንኙነት መሻከር ጀምሯል ሲል ደይሊ ኔሽን አስነብቧል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ የቀድሞው የአልሸባብ ምክትል አዛዥ ሙክታር ሮቦውን በሚንስትርነት ማስሾማቸው ኢትዮጵያን አስቆጥቷል ያለው ዘገባው፣ ይህንኑ ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሱማሊያ ፌደራል ክልሎች ጋር የተናጥል ግንኙነት መጀመሯን ጠቅሷል። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ አዚዝ ጋሪን በቅርቡ በሚስጢር አዲስ አበባ ሂደው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን መስማቱን ዘገባው ጠቁሟል። የኢትዮጵያ ጦር መኮንኖች ልዑካን ቡድን ሰሞኑን በደቡብ ምዕራብ፣ ሒርሸበሌ፣ ጁባላንድ ራስ ገዞች ባደረገው ጉብኝት፣ በጸጥታና ሽብርተኝነትን በጋራ በመዋጋት ዙሪያ ተወያይቷል።
2፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ መቀመጫውን ፍኖተ ሰላም ከተማ ላይ ያደረገው ምዕራብ ጎጃም ዞን ከሁለት እንዲከፈል የክልሉ ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ለዞኑ ደብዳቤ መጻፋቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ዞኑ ከሁለት የሚከፈለው፣ ከአገልግሎት አሰጣጥና የልማት ተደራሽነት አንጻር ተጎጅ የሆኑ የአስተዳደር መዋቅሮች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ነበር። አዲሱን ዞን የሚያዋቅሩት፣ የባሕርዳር ዙሪያ፣ ሰሜን ሜጫ፣ ደቡብ ሜጫ፣ ሰሜን አቸፈር፣ ደቡብ አቸፈር፣ ጎንጅ ቆላ እና ይልማና ዴንሳ ወረዳዎች ከመርዓዊ፣ ዱርቤቴ እና አዴት የከተማ አስተዳደሮች ጋር በመሆን ነው። አዲሱ ዞን በ2016 ዓ፣ም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
3፤ ኢሰመኮ በአዲስ አበባ ለሚቀርቡለት የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎች ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት አመርቂ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችለውን የቅንጅት፣ የትብብርና የቅብብሎሽ ማዕቀፍ መዘርጋቱን አስታውቋል። አዲሱ ማዕቀፍ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጸምባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ነጻ የሕግ፣ የጤና፣ የመጠለያና የስነ ልቦና ድጋፎችን አሟልቶ መስጠት ያስችላል ተብሏል። ኮሚሽኑ አዲሱን ሥርዓት የዘረጋሁት፣ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎችናጊዜያዊ ማቆያዎች የተጠቀሱት አገልግሎቶች አሰጣጥ ክፍተት በመኖሩ ነው ብሏል።
4፤ የኬንያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተሸናፊ ራይላ ኦዲንጋ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫውን ውጤት ውድቅ እንዲያደርግ የሚጠይቅ አቤቱታ ዛሬ በበርካታ ማስረጃዎች አስደግፈው ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። ኦዲንጋ አቤቱታውን ያቀረቡት፣ የምርጫ ኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶን የምርጫው አሸናፊ ያደረጋቸው በተጭበረበረ የምርጫ ውጤት ነው በማለት ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባአቤቱታው ላይ በ14 ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
5፤ በኬንያ የብሪታኒያ አምባሳደር ጄን ማሪዮት በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብተዋል የሚሉ ክሶችን አስተባብለዋል። አምባሳደሯ በምርጫው ጣልቃ ገብተዋል የሚሉ ትችት የቀረበባቸው፣ ከምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዋፉላ ቸቡካቲ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ የሚያሳይ ፎቶ በኬንያ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተለቀቀ በኋላ ነው። ብሪታኒያ በኬንያ ምርጫ ለይታ የምትደግፈው ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ የለም ያሉት አምባሳደሯ፣ ብሪታኒያ ከኬንያ ጋር ያላትን አጋርነት ለመስረዳት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነት እናደርጋለን ብለዋል።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ3637 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4110 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ1737 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ3572 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ2324 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ2770 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ነሐሴ 17/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለሁለት ዓመት ያዘገየውን የዞን አደረጃጀት በተያዘውሳምንት እንደሚያጸድቅ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። አዲሶቹ አራት ዞኖች፣ ሰሜን ሲዳማ፣ ምሥራቅ ሲዳማ፣ ማዕከላዊ ሲዳማ እና ደቡብ ሲዳማ ተብለው ተከፍለዋል። ሀዋሳ፣ አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም እና ዳዬ ከተሞች ደሞ የዞኖቹ ማዕከሎች ሲሆኑ፣ ሀዋሳ የከተማ አስተዳደር ትሆናለች። የክልሉ መንግሥት የዞን አደረጃጀት ጥያቄውን እስካሁን ያቆየው፣ ክልሉ በሁለት እግሩ እስኪቆም ድረስ እንደሆነ የክልሉ ምክር ቤት ምንጮች ተናግረዋል።
2፤ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዴ አፍሪካ ኅብረት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሰላም ሊያመጣ አይችልም ሲሉ በአፍሪካ ሪፖርት መጽሄት ላይ ጽፈዋል። የኅብረቱ ልዩ ልዑክ ኦባሳንጆ መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ተነጥለዋል በማለት የተቹት ጌታቸው፣ አሁን ድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም ለማድረግ ካለው ዕድል ይልቅ ኦባሳንጆ በተሾሙበት ወቅት የነበረው ዕድል ይሻል ነበር ብለዋል። ኦባሳንጆ የኤርትራ መንግሥትን ለሰላም ድርድሩ እንደሚጋብዙ ፍንጭ መስጠታቸው ትክክል እንዳልሆነ ጌታቸው አክለው ጠቁመዋል።
3፤ የሱማሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ አልሸባብ በሞቃዲሾው አያት ሆቴል ለፈጸመው እገታና ጥቃት መንግሥታቸው ሃላፊነት እንደሚወስድ መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ባሬ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተጠያቂነት አይቀርላቸውም ብለዋል። ጸጥታ ኃይሎች 21 ሰዎች የተገደሉበትንና 117 ሰዎች የቆሰሉበትን ጥቃት ለመመከት ቅንጅት እንዳልነበራቸው ታዛቢዎች ተናግረዋል።
4፤ ሱዳን በጎርፍ በተጠቁ ስድስት ግዛቶቿ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው፣ በሪቨር ናይል፣ ገዚራ፣ ዋይት ናይል፣ ዌስት ኮርዶፋን፣ ሳውዝ ዳርፉር እና ከሰላ ግዛቶች ነው። መንግሥት ለጎርፉ ተጎጅዎች የአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶችን ማስተባበር ጀምሯል። በጎርፉ እስካሁን 80 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች ደሞ ለጉዳት ተዳርገዋል። ክከፍተኛ ዝናብ መጣሉና የጎርፍ አደጋው እስከ ጥቅምት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
5፤ የናይል ተፋሰስ አገሮች የሆኑት ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ በጋራ ያስገነቡት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ 95 በመቶ መጠናቀቁን የታንዛኒያው ሲትዝን ጋዜጣ ዘግቧል። በታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ድንበር ላይ የተገነባው የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 80 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። ግንባታው የተከናወነው፣ ከዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና ከሌሎች ምንጮች በተገኘ 468 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ ነው። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ነሐሴ 17/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) በሚል ስያሜ ለሚቋቋም ፓርቲ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለመስጠት ሕጉ እንደማይፈቅድለት ዛሬ ባበራጨው ደብዳቤ አስታውቋል። ቦርዱ ግንቦት 24 የቀረበለትን የምዝገባ ጥያቄ ያልተቀበለው፣ ኢሠፓ "ጸረ-ዲሞክራሲያዊና ወንጀለኛ ፓርቲ" ተብሎ ተፈርጆ እስካሁን ባልተሻረ አዋጅ የፈረሰ ፓርቲ በመሆኑ እንደሆነ ጠቅሷል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅም፣ ካሁን ቀደም ሕጋዊ ከነበረ ፓርቲ ስያሜ ጋር የሚመሳሰል ስያሜ ላለው አዲስ ፓርቲ ፍቃድ መስጠት እንደማይችል መደንገጉን ገልጧል።
2፤ መከላከያ ሠራዊት በሠራዊቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያልተረጋገጡ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ድርጊታቸውን ባስቸኳይ እንዲያቆሙ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። ያለ በቂ መረጃ ስለ ሕወሃት እንቅስቃሴ የሚያስተጋቡና ጦርነት የተጀመረ አስመስለው የሚዘግቡ መገናኛ ብዙኀን፣ ጸጥታ ኃይሎችን እየተጋፉ መሆኑን የጠቆመው ሠራዊቱ፣ በግዴለሽነት በዚህ ተግባራቸው የሚቀጥሉ አካላትን በሕግ እንደሚጠይቅ ገልጧል። ሠራዊቱ ጨምሮም፣ ሕወሃት ሠራዊቱ ጥቃት ሰነዘረብኝ በማለት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው ሲል ከሷል።
3፤ ኢዜማ ፌደራል መንግሥቱ በአፋር እና ሱማሌ ክልሎች መካከል ላለው "የርስበርስ ግጭት" ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው በአስተዳደር ወሰን ዙሪያ የሚነሳው ግጭት፣ ከሁለቱ ክልሎች አልፎ ለአገሪቱ ስጋት መሆኑን እና ለውጭ ኃይሎች መግቢያ ቀዳዳ እንደሚፈጥር መረዳት እንደሚያስፈልግ ገልጧል። ኢዜማ መንግሥት የሁለቱን ክልሎች ጎሳ መሪዎች እና የሐይማኖት አባቶች አስተባብሮ የሰላም ችግሩን እንዲፈታው አሳስቧል።
4፤ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፓስፖርት እያላቸው የመኖሪያ ፍቃድ ስለሌላቸው ብቻ እየታሠሩ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ሕጋዊ እና የታደሠ ፓስፖርት እያላቸው የገንዘብ ቅጣት እየተቀጡ ያሉ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን ኢምባሲው ጨምሮ ገልጧል። ለኢትዮጵያዊያን ሱዳን ውስጥ ለመኖር ፓስፖርት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የጠቀሰው ኢምባሲው፣ ዜጎች ሕጋዊ የመምሪያ ፍቃድ እንዲያወጡ አሳስቧል።
5፤ ኬንያ 200 ፈጥኖ ደራሽ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ትናንት ወደ ምሥራቃዊ ኮንጎ ልካለች። የኬንያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሚሠማሩት፣ በተመድ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር ነው። ሰላም አስከባሪ ኃይሉ የሰላማዊውን ሕዝብ ደኅንነት የማስጠበቅና ታጣቂ ሚሊሻዎችን የማዳከም ሃላፊነት አለበት። ኬንያ የመጀመሪያዎቹን 200 ሰላም አስከባሪዎች ወደ ምሥራቅ ኮንጎ ያሰማራችው ባለፈው ነሐሴ ነበር። ቡሩንዲ ደሞ የምሥራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ስር መንግሥትን የሚያግዙ ተዋጊ ወታደሮች ሰሞኑን አሠማርታለች።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ3810 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4286 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ0682 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ2496 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ4281 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ4767 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የጉራጌ ዞንን ክልልነት ጥያቄ የደገፉ የዞኑ ነዋሪዎችና አመራሮች እየታሠሩ እንደሆነ ቪኦኤ ዘግቧል። ሰሞኑን የዞኑን አመራሮች ጨምሮ 13 ሰዎች እንደታሠሩ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል። የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ፣ ከክልልነት ጥያቄ ላይ በተያያዘ በዞኑ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨትና ግጭት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ ግለሰቦችንና የመንግሥት ሥራ ሃላፊዎችን ማሠሩን አረጋግጧል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ስንት የዞኑ አስተዳደር ሃላፊዎችን እንዳሠረ ግን አልገለጸም።
2፤ የተመድ ሕጻናት ድርጅት ዩኒሴፍ ኢትዮጵያን እና ሱማሊያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ እና ሳህል አገሮች 10 ሚሊዮን ሕጻናት በድርቅ ሳቢያ ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ገልጧል። ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከባድ አደጋ ላይ ያሉ ሕጻናት ቁጥር በ40 በመቶ ጨምሯል ያለው ድርጅቱ፣ የምግብ እጥረትና የውሃ ወለድ በሽታዎች አደጋ አባባሽ ሆነዋል ብሏል። በኢትዮጵያ፣ ሱማሊያና ኬንያ በድርቅ ሳቢያ ጥራቱ ለተጠበቀ መጠጥ ውሃ እጥረት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 16.2 ሚሊዮን እንደደረሰና ሕጻናት ለኮሌራ በሽታ ያላቸው ተጋላጭነት እንደጨመረ ድርጅቱ ጠቁሟል።
3፤ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በአልሸባብ ላይ ለሚያውጁት አጠቃላይ ጦርነት የአገሪቱ ሕዝብ እንዲዘጋጅ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ጥሪ አድርገዋል። አልሸባብ ሰሞኑን በሞቃዲሾው አያት ሆቴል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ያወገዙት ፕሬዝዳንቱ፣ መንግሥታቸው ቡድኑን ለማዳከም ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የአልሸባብ ታጣቂዎች በሆቴሉ ላይ በፈጸሙት ጥቃት 21 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ፕሬዝዳንቱ መግለጫ ሲሰጡ የትናንቱ የመጀመሪያቸው ነው።
4፤ የእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች ከመሬታቸው ያፈናቀሏቸውና ግድያ የፈጸሙባቸው ኬንያዊያን ቤተሰቦች በአውሮፓ ኅብረት ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ትትናንት ክስ መመስረታቸውን ደይሊ ኔሽን አስነብቧል። ከሳሾቹ ወደ አውሮፓ ፍርድ ቤት የሄዱት፣ በደላቸውን የእንግሊዝ መንግሥት ችላ በማለቱ እንደሆነ ገልጸዋል። 100 ሺህ ያህሉ ከሳሾች እንግሊዝ ይቅርታ እንድትጠይቃቸው እና ካሳ እንድትከፍላቸው ነው በክሳቸው የጠየቁት። ከሳሾች ከሁለት ዓመት በፊት አቤቱታቸውን ለተመድ አቅርበው፣ የተመድ ልዩ አጣሪ ቡድን እንግሊዝ ለበደሎቿ ኃላፊነት አለመውሰዷ አሳሳቢ ነው ብሎ ነበር።
5፤ በደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ግዛት በባላንጣ ታጣቂ ቡድኖች መካከል በቅርቡ የተቀሰቀሰው ግጭት ከ15 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን እንዳፈናቀለ በአገሪቱ የተመድ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ አስታውቋል። ቶንጋ በተባለች ከተማና አቅራቢያዋ ከሳምንት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት፣ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የደቀነው አደጋ አሳሳቢ መሆኑን የሰላም ተልዕኮው ገልጧል። ተፋላሚ ኃይሎች ባስቸኳይ ተኩስ አቁመው፣ ለአገሪቱ ሰላም ስምምነት ተገዥ እንዲሆኑ ተልዕኮው አሳስቧል።
6፤ በኮሮና በሽታ የተያዙ ሰዎች እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ጭንቀትንና ድብታን ጨምሮ ከአዕምሮ ሕመም ጋር ተያያዥ በሆኑ የጤና ችግሮች የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑን የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በጥናት ደርሰንበታል ብለዋል። ጥናቱ የተደረገው፣ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በነበሩ 1 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ነው። ችግሩ ሊከሰት የሚችለው ግን፣ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በሁለት ወር ውስጥ ነው። ሕጻናት ከአዋቂዎች በተለየ ይየችግሩ ተጠቂ እንደማይሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሱዳን አልፎ ለሕወሃት የጦር መሳሪያ በመጫን የኢትዮጵያ አየር ክልልን ጥሶ የገባ አንድ አውሮፕላን መትቶ መጣሉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የዘመቻዎች ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜ/ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል። አውሮፕላኑ ተመትቶ የወደቀው፣ ትናንት ምሽት አራት ሰዓት ገደማ በሑመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሲያልፍ እንደሆነ ሜ/ጀኔራል ተስፋዬ ገልጸዋል። ሜ/ጀኔራል ተስፋዬ አውሮፕላኑ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ ይታመናል" ብለዋል። ሕወሃት በቆቦ ግራና ቀኝ ዞብል ተራራ፣ ቢሶብርና ወትወት በተባሉ አካባቢዎች ንጋት ላይ ውጊያ መክፈቱን ሜ/ጀኔራሉ ጨምረው ገልጸዋል።
2፤ ሕወሃት የተኩስ አቁሙን ውሳኔ በመጣስ ዛሬ ንጋት ላይ በምሥራቅ ግንባር ቢሶብር፣ ዞብልና ተኩለሽ በተባሉ አካባቢዎች ጥቃት መክፈቱን የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የመንግሥት ኃይሎች ጥቃቱን በተቀናጀ መንገድ እየመከቱ መሆኑን መግለጫው አውስቷል። ሕወሃት በበኩሉ፣ የመንግሥት ኃይሎች በጩቤበር፣ ጃኖራ፣ ጉባጋል፣ አላማጣና ሌሎች ግንባሮች ጥቃት ከፍተውብኛል ሲል ከሷል። ፌደራል መንግሥቱ በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጥል ተኩስ አቁም ያወጀው ባለፈው መጋቢት ነበር።
3፤ መንግሥት በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አገሪቱን ለመበተን የቆረጠው "የሕወሃት የጥፋት ኃይል" የከፈተውን አዲስ ወታደራዊ ጥቃት በአንድነት እንዲመክቱ በቃል አቀባይ ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል። ሕወሃትን በግድም ይሁን በውድ ወደ ሰላም ለማምጣት ሁሉንም ርምጃዎች እንደሚወስድ የገለጸው መንግሥት፣ ባሁን ወቅት መንግሥትና ጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመቀልበስ ሙሉ አቅማቸውንና ኃይላቸውን አንቀሳቅሰዋል ብሏል። መግለጫው ሕወሃት ላለፉት ስድስት ወራት በምዕራባዊና ደቡባዊ ግንባሮች ያደርጋቸውን ተደጋጋሚ የጥቃት ሙከራዎች መከላከያ ሠራዊት አክሽፎ ግጭቱ እንዳይባባስ ማድረግ ችሎ እንደነበር ጠቅሷል።
4፤ ምርጫ ቦርድ በስድስት የደቡብ ክልል ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የክልልነት ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂድበትን የጊዜ መርሃ ግብር በሕገ መንግሥቱ ገደብ ውስጥ መወሰን የራሱ ሥልጣን መሆኑን ለፌደሬሽን ምክር ቤቱ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል። ቦርዱ ይህን ያለው፣ ሕዝበ ውሳኔውን በሦስት ወር ውስጥ እንዲያካሂድ ፌደሬሽን ምክር ቤት ለጻፈለት ደብዳቤ በሰጠው ምላሽ ነው። የሕዝበ ውሳኔውን ማካሄጃ ጊዜ ወደፊት እንደሚገልጽ የገለጠው ቦርዱ፣ ፌደሬሽን ምክር ቤት የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዖና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም የደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ባስኬቶና አሌ ልዩ ወረዳዎች አንድ አዲስ ክልል ለማዋቀር ውሳኔ ያሳለፉባቸውን ሰነዶች እንዲልክለት ጠይቋል።
5፤ ንግድ ሚንስቴር ግለሰቦች ብቻቸውን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ንግድ ኩባንያ እንዲያቋቁም የሚፈቅድ ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን ሪፖርተር አስነብቧል። ሆኖም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሚያቋቁሙ ግለሰብ ባለሃብቶች፣ አንድ ሕጋዊ የንብረት አደራ ተቀባይ ማስመዝገብ እንደሚኖርባቸው ረቂቅ መመሪያው ያዛል። ከዓመት ከመንፈቅ በፊት በጸደቀው አዲሱ የንግድ ሕግ መሠረት የተረቀቀው መመሪያ፣ አሁን ሥራ ላይ ያለውን የንግድ ኩባንያዎች የምዝገባ፣ ፍቃድ አሰጣጥና የቁጥጥር መመሪያ የሚተካ ነው። ለ60 ዓመታት የቆየው የንግድ ሕግ፣ ኃ/የተ/ የግል ኩባንያ እንዲያቋቁሙ የሚፈቅደው ለሁለትና ከሁለት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ነበር።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ3909 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4387 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 58 ብር ከ7641 ሳንቲም፣ መሸጫው 59 ብር ከ9394 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ51 ብር ከ9718 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ0112 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ነሐሴ 19/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የኡጋንዳ ምድር ጦር አዛዥና የፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ልጅ ጀኔራል ሙሆዚ ኪያነሩጋባ ትናንት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ጀኔራል ሙሆዚ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀኔራል ሙሆዚና ልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው፣ ሕዳሴ ግድብን፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የደኅንነትና ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቶችን ጎብኝተዋል። ጀኔራል ሙሆዚ፣ የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ኦሪየም ኦኬሎ እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ለኦፊሴላዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ከትናንት ወዲያ ነበር።
2፤ የሕወሃት ታጣቂዎች በመቀሌ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሰብዓዊ አገልግሎት መጋዘን ያስቀመጠውን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ትናንት ማለዳ ላይ ዘርፈዋል ሲል የተመድ ዋና ጸሃፊ ቃል አቀባይ ስቲፋን ዱጃሪች ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባልደረቦች ዝርፊያውን ለመከላከል ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ዱጃሪክ ገልጸዋል። ዱጃሪክ የነዳጁ መዘረፍ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል ብለዋል።
3፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሊ የትግራይ ባለሥልጣናት በመቀሌ የድርጅቱ ንብረት የሆነ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ዘርፈዋል ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ከሰዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ድርጊቱን"አሳፋሪ" እና "አስቀያሚ" በማለት ገልጸውታል። የነዳጅ አቅርቦት ከሌለ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዕርዳታ ፈላጊዎች ለርሃብ ይጋለጣሉ በማለት ያስጠነቀቁት ዴቪድ ቢስሊ፣ የተዘረፈው ነዳጅ ባስቸኳይ ለድርጅቱ እንዲመለስ አሳስበዋል።
4፤ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ እና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጥሪ አድርገዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ግጭቱ ዳግም ማገርሸቱ እንዳሳዘናቸው ይገለጹት ጉተሬዝ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ዋስትና እንዲያገኝና መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል። የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ እና የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬልም ተመሳሳይ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
5፤ የኬንያው ምርጫ ኮሚሽን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተሸንፈዋል ያላቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫው አሸናፊ መሆናቸውን እንዲያውጅላቸው ጠይቀዋል። ኦዲንጋ ይህን ያሉት፣ የምርጫ ኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አሸንፈውበታል ያለውን የምርጫ ውጤት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲሰርዘው አቤቱታ ካስገቡ በኋላ ነው። ኦዲንጋ የምርጫ ኮሚሽኑን የከሰሱት፣ ሩቶ በተጭበረበረ ምርጫ አሸንፈዋል ብሎ አውጇል በማለት ነው። ፍርድ ቤቱ በ12 ቀናት ውስጥ በኦዲንጋ አቤቱታ ላይ ብይኑን ይሰጣል።
6፤ የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ካሪም ካኻን ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል ክሶችና ምርመራ ዙሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትብብሯን መቀነሷን ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አስታውቀዋል። ዓቃቤ ሕጉ ጸጥታው ምክር ቤት ሱዳን ከፍርድ ቤቱና ዓቃቤ ሕግ ጋር እንድትተባበር ግፊት እንዲያደርግና ዳርፉር ላይ ለተፈጸሙት ዓለማቀፍ ወንጀሎች ፍትህ እንዲያስገኝ ጠይቀዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ በዳርፉር በጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች በቀድሞው የጃንጃዊድ ሚሊሽያ መሪ ዓሊ ራህማን ላይ በሚያዝያ የእስር ቅጣት መጣሉ የፍትህ ተስፋ እንደፈነጠቀ ዓቃቤ ሕጉ ገልጸዋል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ሐሙስ ነሐሴ 19/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ የሥራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ እንደተመታ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በከተማዋ የንግድ መደብሮች እና ባንኮች ተዘግተው እና የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጦ መዋሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የከተማዋ ሕዝብ አድማ የመታበት ምክንያት፣ የጉራጌ ዞን የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር የተያይዘ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። የደቡብ ክልል ጸጥታ ዕዝ የንግድ መደብሮችንና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ማቋረጥ ክልክል መሆኑን ትናንት አስጠንቅቆ ነበር።
2፤ መንግሥት ሕወሃት ትናንት በመቀሌ የዘረፈውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ነዳጅ እንዲመልስ ዛሬ በቃል አቀባይ ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። መንግሥት ዓለማቀፍ ድርጅቶች ለነዳጅ ዝርፊያው ቡድኑን ተጠያቂ እንዲያደርጉና ሕወሃትም ሰብዓዊ ዕርዳታ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንደሚውል ማስተማመኛ እንዲሰጥ ጠይቋል። የነዳጅ ዝርፊያው የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን የጠቀሰው መንግሥት፣ ሕወሃት ዝርፊያውን ለማስቆም የሞከሩ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞችን አስሯል በማለት ከሷል። ዝርፊያው ሕወሃት ዕርዳታን ለጦርነት ዓላማ ሲጠቀም እንደቆየ ማረጋገጫ መሆኑን መንግሥት ገልጧል።
3፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ ሲገባ መትቼ ጣልኩ ካለችው ክስተት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ሲል በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው ቃል ማስተባበሉን ብሉምበርግ ዘግቧል። ዜና ምንጩ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የጸጥታ ሹም፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ የገባ አውሮፕላን መትቶ ጥሏል በማለት እንደነገሩት ጠቅሷል። የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፣ የመንግሥት መረጃ "ሐሰት ነው" ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። መንግሥት መትቼ ጥያለሁ ስላለው አውሮፕላን ከትናንት ወዲህ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጠም።
4፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራዩ ሕወሃት መካከል ድጋሚ ግጭት ማገርሸቱ አሳስቦናል ሲሉ አሜሪካ እና ቱርክ በየፊናቸው ስጋታቸውን ገልጸዋል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ መንግሥትና ሕወሃት ለሰላም መስፈን ከፍተኛ ጥረቶችን እንዲያደርጉ በትዊተር ገጻቸው አሳስበዋል። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ደሞ፣ መንግሥት እና ሕወሃት ወደ ሰላማዊ ንግግር እንዲመለሱና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጠይቋል።
5፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ሰነዶች መርምሮና የተከሳሹን ጠበቆች አስተያየት ምርምሮ ብይን ለመስጠት ለነሐሴ 27 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ጋዜጠኛው ማኔጅንግ ኤዲተርና ባለቤት በሆነባት "ፍትህ" መጽሄት ላይ የታተሙ 17 ጽሁፎችን ነው። ፍርድ ቤቱ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረው ለዛሬ ሲሆን፣ ሆኖም ሰነዶቹ ብዙ በመሆናቸው ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት እንደተገደደ ገልጧል።
6፤ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን አግተው ለኦነግ ሸኔ አሳልፈው ሰጥተዋል በተባሉ አምስት ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማሳለፍ ለነሐሴ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን አዲስ ማለዳ ዘግቧል። ዛሬ የጥፋተኛነት ውሳኔ የተላለፈባቸው፣ ጋዲሳ ገለቱ፣ ናስር መሐመድ፣ ነብዩ በባክር፣ ከሊፋ አብዱራህማንና ዮሴፍ ጃረታ ናቸው። ጥፋተኞቹ የኦነግ ሸኔን ዓላማ ለማራመድና የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ለማገት ከቡድኑ ጋር ተስማምተው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል። ተማሪዎቹ ኅዳር 24፣ 2012 ዓ፣ም የታገቱት፣ ከደምቢዶሎ ወደ አማራ ክልል በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሲጓዙ ነበር።
7፤ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን መሐመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ፑንትላንድ ራስ ገዝ ማቅናታቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸው አብሺር ሁርሴ ጋር ብቻ ፑንትላንድ የገቡት ፕሬዝዳንቱ፣ ከፑንትላንዱ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ ጋር ተወያይተዋል ተብሏል። ደኒ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የፕሬዝዳንት ሞሐመድ ተቀናቃኝ ነበሩ። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፑንትላንድ የሄዱት፣ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በራስ ገዟ ጉብኝት ባደረገና ከፕሬዝዳንት ደኒ ጋር በተወያየ ማግስት ነው።
8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4077 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4559 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ0182 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ1986 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ1142 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ1565 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ዓርብ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ መቀሌ ላይ ሕወሃት የዘረፈው 570 ሺህ ሊትር ወይም 12 ቦቴ ነዳጅ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ወደ ክልሉ ያስገባው ነዳጅ እንደሆነ ድርጅቱ ትናንት ባወጣው ዝርዝር ማብራሪያ ገልጧል። ታጣቂ ኃይሎች ወደ መጋዘን ገብተው በኃይል ዘርፈውታል ያለው ድርጅቱ፣ ነዳጁ ካልተመለሰለት በክልሉ የመድኻኒት፣ ምግብ እና ማዳበሪያ አቅርቦቶችን ለማዳረስ እንዲሁም ጀነሬተሮችንና ተሽከርካሪዎችን ለማንቀሳቀስ አልችልም ብሏል። የክልሉ ባለሥልጣናት ነዳጁን ባስቸኳይ እንዲመልሱለት ድርጅቱ በድጋሚ ጠይቋል።
2፤ ሕወሃት-መራሹ የትግራይ ክልል መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሊ የትግራይ ባለሥልጣናት የድርጅቱን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ዘርፈዋል በማለት ያቀረቡትን ክስ ነቅፏል። የክልሉ መንግሥት ትናንት መልሶ የወሰደው ነዳጅ ከወራት በፊት ለድርጅቱ ያበደረውን ነዳጅ መሆኑን ገልጦ፣ ዝርፊያ ፈጽሟል መባሉን አስተባብሏል። የዋና ዳይሬክተሩ ውንጀላ በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል ያለው የክልሉ መንግሥት፣ ነዳጁን የፈለኩት የጤና ተቋማትን ለማንቀሳቀስ ነው ብሏል።
3፤ የአሜሪካው ዓለማቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና ሃላፊ ሳማንታ ፓዎር ሕወሃት ከመቀሌው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የዘረፈውን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ እንዲመልስ በትዊተር ገጻቸው ጠይቀዋል። ፓዎር ዝርፊያ በመፈጸም ለተረጅዎች ምግብ የሚቀርብ ሰብዓዊ ዕርዳታን ማስተጓጎል የጭካኔ ተግባር ነው ብለዋል። ሃላፊዋ ሕወሃት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎችን እንዲያከብር በመልዕክታቸው አሳስበዋል።
4፤ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አለምጸሃይ መሠረት ትናንት ከኡጋንዳ መከላከያ ሚንስትር ጋር የሁለቱን አገራት የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን ኢምባሲው በትዊተር ገጹ አስታውቋል። በዚሁ ውይይት ሁለቱ አገሮች ያቋቋሙት የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ በየጊዜው እንዲሰበሰብ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጧል። በውይይቱ ላይ የኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ዊልሰን ማባዲ ተገኝተዋል። ውይይቱና ስምምነቱ የተደረገው፣ የኡጋንዳ ምድር ጦር ዋና አዛዥና የፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ልጅ ጀኔራል ሙሆዚ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በተመለሱ ማግስት ነው።
5፤ የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ውስጥ የተመረተው የወባ በሽታ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅዷል። መድኃኒቱ በበሽታው ለተያዙ ነፍሰ ጡር እናቶች እና ሕጻናት የሚሰጥ ነው። "ሱልፋዶክሲን/ፒሪሚታሚን" የተባለውን መድኃኒት ያመረተው፣ ዩኒቨርሳል ኮርፖሬሽን የተባለ የኬንያ መድሃኒት አምራች ኩባንያ ነው። አፍሪካ እስካሁን የወባ መድኃኒት የምታስገባው ከውጭ ነው። በአፍሪካ በወባ በሽታ ከሚሞቱት 80 በመቶዎቹ ነፍሰ ጡሮችና ሕጻናት ናቸው።
6፤ አሜሪካ ከ25 ዓመታት በኋላ ለሱዳን የሾመቻቸው ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ካርቱም ገብተዋል። አዲሱ በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ ሲሆኑ፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አምባሳደሩን የሾሟቸው ባለፈው ኅዳር ነበር። አሜሪካ የካርቱም ኢምባሲዋን የዘጋችው፣ ሱዳን የአልቃይዳውን መሪ ኦሳማ ቢን ላደንን ያስጠለለች "የሽብር አስተባባሪ አገር ናት" ብላ በፈረጀቻት ወቅት ነበር። ሱዳንም ከ20 ዓመታት በኋላ ባለፈው ዓመት ለአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መሾሟ ይታወሳል።
7፤ ቻይና ዘንድሮ ብድር ከምትሰርዝላቸው 17 የአፍሪካ አገራት ዝርዝር ውስጥ ጉረቤት ኬንያን እንዳስወጣች የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል። ቻይና ኬንያን በዝርዝሩ ያስወጣቻት፣ ኬንያ መካከለኛ ገቢ ላይ የደረሰች መሆኗን በመጥቀስ ነው። ቻይና ዘንድሮ ለአፍሪካዊያኑ አገራት ከወለድ ነጻ የሆኑ 23 ብድሮችን ለመሰረዝ ወስናለች። ሆኖም ቻይና ይህን ውሳኔ የወሰነችው፣ ኬንያ የዩክሬኑ ጦርነት በፈጠረባት ጫና ሳቢያ ቻይና የብድር መክፈያ ጊዜዋን እንድታራዝምላት በጠየቀች ማግስት ነው። ቻይና ከዓለም ባንክ ቀጥሎ ትልቋ የኬንያ አበዳሪ ናት። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ዓርብ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ መንግሥት በትግራይ ክልል የሕወሃት ወታደራዊ አቅሞችን ዒላማ ያደረጉ ርምጃዎችን እንደሚወስድ በቃል አቀባይ ቢሮው በኩል ወጣው መግለጫ አስታውቋል። የትግራይ ሰላማዊ ነዋሪዎች የሕወሃት ወታደራዊ ቁሳቁሶችና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ከሚገኙባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ መንግሥት አሳስቧል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ሕወሃት ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ የማያደርግ ከሆነ፣ የሰላም ዝግጁነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ማናቸውንም ርምጃ እንደሚወስድም መንግሥት ጨምሮ ገልጧል። ሕወሃት በበኩሉ ዛሬ መንግሥት በመቀሌ የአየር ድብደባ ፈጽሟል ሲል ከሷል።
2፤ በኦጋዴን ሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋግጧል ሲሉ የማዕድን ሚንስትር ታከለ ኡማ ተናግረዋል። የነዳጅ ክምችቱ የተረጋገጠው፣ ከ2014 ዓ፣ም ጀምሮ የማዕድን ሚንስቴር ጋር በገባው ውል መሠረት የአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሲየት ኩባንያ ባደረገው ጥናት እንደሆነ የጥናቱ ውጤት ይፋ በተደረገበት ስነ ሥርዓት ላይ ተገልጧል። ከጥናቱ በፊት የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱ ከሁለት እስከ ሦስት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ ይገመት ነበር። መንግሥት የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱን በውጭ ኩባንያ ሲያስጠና የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጧል።
3፤ የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል አስተዳደራዊ ወሰን ማካለል ሂደት ይቁም ሲሉ እናት ፓርቲ፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ የወሰን ማካለሉ፣"ሕግን ያልተከተለ፣ ሂደቱን ያልጠበቀ፣ የከተማዋን ሕዝብ መብት የሚጥስና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውክ" ነው ብለዋል። የከተማዋና የክልሉ አስተዳደር ወሰን መፈታት ያለበት በአገራዊ ምክክር ሂደቱ ሊሆን እንደሚገባም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደር ወሰኑ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ተካልሎ ተጠናቋል በማለት ባለፈው ሳምንት መግለጻቸው ይታወሳል።
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት አከራዮች በተከራዮች ላይ ኪራይ እንዳይጨምሩ እና ተከራዮችን እንዳያስወጡ የሚከለክለውን ደንብ ለተጨማሪ ስድስት ወራት ማራዘሙን አስታውቋል። የከተማዋ አስተዳደር ይህንኑ ደንብ በየጊዜው እያሻሻለ ለአንድ ዓመት ያህል ሲተገብር የቆየው፣ የኑሮ ውድነቱ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ይናገራል።
5፤ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ትግራይ ለሚገኙ እና ርሃብ ላይ ላሉ ዘመዶቻቸው ገንዘብ መላክ እንዳልቻሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ከዘመዶቼ ማን በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ብለዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ በተሉይ ከአንድ ዓመት ወዲህ ስለ ትግራይ ተደጋጋሚ አስተያየቶችንና መግለጫዎችን ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ደሞ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ለትግራይ ሰቆቃ ትኩረት ያልሰጠው በዘረኝነት ምክንያት ሊሆን ይችላል በማለት ተናግረው ነበር።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4171 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4654 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ2040 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ3881 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ2913 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ3371 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። አንድ የቻይና ዩዋን ደሞ በ6 ብር ከ9222 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ7 ብር ከ0606 ሳንቲም ተሽጧል [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይል " ከሱዳን በኩል የጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ሲገባ መትቶ የጣለው አንቶኖቭ አውሮፕላን ፍቃድ ያልተሰጠው እና በተከለከለ የበረራ መስመር በኩል የገባ" እንደነበር በመንግሥታዊው ቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫቸው አስታውቀዋል። አውሮፕላኑ በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ ተመትቶ የወደቀው ማክሰኞ ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ መሆኑን እና የወደቀበትን አካባቢ ማረጋገጥ እንደተቻለ ዋና አዛዡ በካርታ አስደግፈው አብራርተዋል። አውሮፕላኑ ሲቪዬት ኅብረት ሰራሽ የሆነ አንቶኖቭ-26 አውሮፕላን መሆኑንና 40 ወታደሮችን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የመጫን አቅም እንዳለው የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ አመልክቷል።
2፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የአየር ድብደባ ዒላማ የማደርገው የሕወሃት ወታደራዊ ዒላማዎችን ብቻ ነው በማለት መናገሩን የውጭ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል። መንግሥት ሕወሃት ሰላማዊ ሰዎች የሞቱ አስመስሎ ባዶ የአስከሬን ጆንያዎችን በሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ በማስቀመጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድብደባ ፈጸመ በማለት ለመወንጀል ይሞክራል ማለቱን የተለያዩ የውጭ ዜና ምንጮች ዘገባዎች አመልክተዋል። መንግሥት ይህን ማስተባበያ የሰጠው፣ ትናንት በመቀሌ ተፈጸመ በተባለ የአየር ድብደባ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። በመቀሌ ባንድ ሙዓለ ሕጻናት አካባቢ ተፈጸመ በተባለ ድብደባ ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ አራት ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ የሆስፒታል ምንጮችንና የዓይን እማኞችን በመጥቀስ የተለያዩ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል።
3፤ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሚሸል ባቸሌት በመንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ድጋሚ ግጭት ማገርሸቱ የዕርዳታ ፈላጊዎችን ሰቆቃ ያባብሳል ሲሉ ትናንት ባወጡት መግለጫ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ባቸሌት በዚሁ መግለጫቸው የግጭቱ ማገርሸት እንዳሳሰባቸው ገልጸው፣ መንግሥት እና ሕወሃት አሁን የተቀሰቀሰውን ውጊያ ለማርገብ ጥረት እንዲያደርጉ እና ግጭቱን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።
4፤ የተመድ የአየር ንብረት ተቋም በአፍሪካ ቀንድ ያለው ዝናብ አልባ የአየር ሁኔታ እየተባባሰ እንደሚሄድ መግለጡን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። ተቋሙ በቀጣይ ወራት በቀጠናው ድርቅ መባባሱ፣ ቀጠናውን ታይቶ ለማይታወቅ ሰብዓዊ ቀውስ ይዳርገዋል ብሏል። ከጥቅምት እስከ ታኅሳስ ያለው የዝናብ ወቅት ለአምስተኛ ጊዜ በአብዛኛው ደረቅ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጧል። በተጠቀሱት ወራት ውስጥ የኢትዮጵያ፣ ሱማሊያ እና ኬንያ ደረቃማ አካባቢዎች ከመደበኛው የዝናብ መጠን በእጅጉ ያነሰ ዝናብ ያገኛሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ድርጅቱ ተናግሯል። ከጥቅምት እስከ ታኅሳስ ባሉት ወራት የሚጥለው ዝናብ የቀጠናው አገራት ከሚያገኙት ዓመታዊ የዝናብ መጠን 70 በመቶውን ይሸፍናል።
5፤ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ሰሞኑን በከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የሥልጣን ሽግሽግ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ጀኔራል ቡርሃን የሥልጣን ሽግሽግ ያደረጉት፣ በምድር ጦር፣ በወታደራዊ ዘመቻዎች፣ በወታደራዊ አቅርቦቶች እንዲሁም በሠራዊቱ ቁጥጥር ዘርፎች ላይ እንደሆነ የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የተደርገው የሥልጣን ሽግሽግ ወታደሩ በሲቪሉ መንግሥት ላይ ባለፈው ጥቅምት የሥልጣን ግልበጣ ካደረገ ወዲህ የመጀመሪያው ትልቁ ሽግሽግ ነው።
6፤ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ከጥር ወር ውዲህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ዝቅተኛ የኮሮና በሽታ ክትባት መድኃኒት ተደራሽነት ያላቸው አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ወረርሽኙ የሚያስከትለውን ሞት በመቀነስ ረገድ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ በመግለጫው ጠቁመዋል። ከአፍሪካ አሕጉር ጠቅላላ ሕዝብ ውስጥ፣ እስካሁን ክትባቱን የወሰደው አንድ ሦስተኛው ሕዝብ ብቻ ነው። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
ማምሻውን ዘግይቶ በወጣ ዜና- መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከምትገኘው ቆቦ መውጣቱን የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሠራዊቱ ከከተማዋ የወጣው፣ በጦርነቱ ሳቢያ "የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ" ሲባል እንደሆነ መግለጫው አመልክቷል። ሕወሃት "የሰው ኃይል ማዕበልን" በመጠቀም ቆቦ ከተማን በብዙ አቅጣጫዎች ከቦ እያጠቃ ነው ያለው መግለጫው፣ መከላከያ ሠራዊት ወደኋላ ተመልሶ ከከተማዋ ውጪ ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ መወሰኑን ገልጧል። መንግሥት በዚሁ መግለጫው፣ ሕወሃት በሰርጎ ገቦቹ አማካኝነት በከተማዋ ውስጥ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለመጀመር ሁኔታዎችን እያመቻቸ ይገኛል በማለት ከሷል።
1፤ ሕወሃት "በማዕበል የውጊያ ስልት" በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹን አሰልፎ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃቱን እያስፋፋ ይገኛል ሲል መንግሥት በቃል አቀባይ ቢሮው በኩል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሕወሃት ባሁኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ እያደረገ፣ እየገደለ፣ እያፈናቀለ እና የልማት መሠረተ ልማቶችን እያወደመ ነው በማለት የከሰሰው መንግሥት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት ግን አሁንም የሕወሃትን ጥቃት በመመከት ላይ ይገኛል ብሏል።
2፤ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉ መንግሥት ዞኖችን ለማዋቀር ያረቀቀውን አዋጅ ዛሬ ማጽደቁን የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። በጸደቀው አዋጅ መሠረት፣ ክልሉ አራት ዞኖች፣ 11 ወረዳዎችና አንድ የከተማ አስተዳደር ይኖሩታል። ሲዳማ ክልል ከተመሠረተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዋቀሩት ዞኖች፣ ሰሜን ሲዳማ ዞን፣ ደቡብ ሲዳማ ዞን፣ ምሥራቅ ሲዳማ ዞን እና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ተብለው ተሰይመዋል። ምክር ቤቱ ለ2015 ዓ፣ም በጀት ዛሬ ካጸደቀው 19 ቢሊዮን 900 ሚሊዮን ብር ውስጥ 150 ሚሊዮኑ ዞኖቹን ለማዋቀር እንዲውል ወስኗል።
3፤ በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ኦልቾ ውሪሮ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ሐሙስ'ለት ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸሙት የእሩምታ ተኩስ አንድ አሽከርካሪ እንደተገደሉ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ታጣቂዎቹ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪን ጨምሮ አራት ተሽከርካሪዎች እንዳቃጠሉ ምንጮቹ ትተናግረዋል። ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙበት አካባቢ፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ እና ሌመን በተባሉ ከተሞች መካከል ላይ የሚገኝ መሆኑን የኦልቻ ውሪሮ ወረዳ ኮምንኬሽን ቢሮ ለዜና ምንጩ ገልጧል። ጥቃቱን ተከትሎ፣ ተሽከርካሪዎች በጸጥታ ኃይሎች እጀባ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ ተገልጧል።
4፤ ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች ትግራይ ውስጥ ያላቸውን ያልተመለሱ ብድሮች ከሒሳብ መዝገባቸው ላይ ሊያነሳላቸው እንደሆነ ሪፖርተር ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ብሄራዊ ባንክ ከባንኮች ማኅበር ጋር በመሆን ንግድ ባንኮች ትግራይ ውስጥ ያልተመለሱላቸውን ብድሮችና ፕሮጀክቶች እየለየ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል። ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ትግራይ ክልል ተበዳሪዎች ከፍተኛ ብድሮችን አበድረው ብድራቸውን ማስመለስ ካልቻሉ ባንኮች መካከል፣ ንግድ ባንክ፣ ልማት ባንክና ወጋገን ባንክ ቀዳሚዎች ናቸው። ልማት ባንክ ብቻ ትግራይ ውስጥ አበድሮ ያልተመለሰለት 10 ቢሊዮን ብር ከሒሳብ መዝገቡ እንዲነሳለት ጠይቋል።
5፤ ከሦስት ቀናት በፊት ወደ ሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝ ፌደራል ክልል ያቀኑት የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ለሦስተኛ ቀን ከራስ ገዟ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ ጋር ውይይት ላይ እንደሆኑ የፑንትላንዱ ዜና ምንጭ ጋሮዌ ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ እና ፕሬዝዳንት ደኒ በምን ጉዳዮች ዙሪያ እየተነጋገሩ እንደሆነ ሁለቱም ወገኖች የገለጹት ነገር የለም። ታዛቢዎች በፌደራል መንግሥቱ እና በፑንትላንድ ራስ ገዝ መንግሥት መካከል አንዳንድ አለመግባባቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፑንትላንድ የገቡት፣ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ወደ ራስ ገዟ አቅንቶ ከፕሬዝዳንት ደኒ ጋር በጋራ ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያየ ማግስት ነበር።
6፤ የተመድ አባል አገራት በውቂያኖሶች የብዝኀ ሕይወት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ ዓለማቀፍ አሳሪ ስምምነት ላይ ለመድረስ ኒውዮርክ ላይ ለሁለት ሳምንታት ያደረጉት ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቋል። ድርድሩ ውቂያኖሶች ላይ የሚደርሰውን የብዝኀ ሕይወት ውድመት ለመከላከልና ውድመቱ የሚያስከትለውን ከባቢያዊይና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ ነበር። ከድርድሩ አወዛጋቢ ጉዳዮች መካከል፣ ኩባንያዎች በዓለማቀፍ ውቂያኖሶች የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን ተጠቅመው ከሚያመርቷቸው መድሃኒቶችንና የኬሚካል ውጤቶች የሚገኘውን ትርፍ አገራት በምን ቀመር ይከፋፈሉት? የሚለው ዋነኛው ነው። የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ወደፊት አምስተኛውን ዙር ድርድር ያዘጋጃል።[ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትናንት አልጀሪያ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት እንደገቡ ጽሕፈት ቤታቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አልጀርስ የገቡት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን አስከትለው ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአልጀሪያ የስንት ቀናት የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ጽሕፈት ቤታቸው አልገለጸም።
2፤ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት የከተማዋ ነዋሪዎች እና ታክሲዎች ከትናንት ጀምሮ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ እንዲሁም ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱን የከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። የከተማዋ ምግብ ቤቶች እና የምሽት መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል። የጸጥታ ምክር ቤቱ ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ውጭ ማንኛውም ሰው በከተማዋ ጦር መሳሪያ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ከልክሏል። በከተማዋ ገደቦች የተጣሉት፣ ለሕዝብ ደኅንነት ሲል እንደሆነ ተገልጧል።
3፤ በአማራ ክልል የሚገኘው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለደኅንነታቸው በመስጋት ከግቢ እየወጡ መሆኑን ዶይቸቨለ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። የከተማዋ ነዋሪዎች የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ባለመኖሩ፣ ተማሪዎች በእግራቸው ሲጓዙ ማየታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም እስከ ትናንት ድረስ በከተማዋ አቅራቢያ በመንግሥት ኃይሎች እና በሕወሃት ተዋጊዎች መካከል የተኩስ ድምጽ እንዳልተሰማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ከግቢያቸው መውጣት ጀመሩ የተባለው፣ መከላከያ ሠራዊት በቅርብ ርቀት ከምትገኘው ቆቦ ከተማ ትናንት መውጣቱን ተከትሎ ነው።
4፤ ድርጅቶች ጦር መሳሪያ የመያዝ ፍቃድ የሚሰጣቸው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ካላቸው እንደሆነ በሕግ እንደተደነገገ ሪፖርተር አስነብቧል። ሆኖም ከ50 ሚሊዮን ብር በታች ካፒታል ያላቸው ድርጅቶች፣ ያሉበት አካባቢ የጸጥታ ችግር ያለበት መሆኑ ከተረጋገጠ የጦር መሳሪያ ፍቃድ ሊሰጣቸው እንደሚችል ፌደራል ፖሊስ ባወጣው መመሪያ ላይ ተጠቅሷል። በመመሪያው መሠረት፣ ድርጅቶች ማስፈቀድ የሚችሉትን መሳሪያ ብዛት የሚወስነው፣ የድርጅቱ የስጋት ተጋላጭነት፣ ከመንግሥት ጸጥታ ተቋማት ያለው ርቀት፣ የአገልግሎት ዓይነቱ እና የካፒታል መጠኑ ናቸው ተብሏል። ፌደራል ፖሊስ በጦር መሳሪያ አዋጁ ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀው መመሪያ፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደር፣ አጠቃቀምና ቁጥጥር መመሪያ የተሰኘ ነው።
5፤ የሱማሊያው ነውጠኛ አልሸባብ በኬንያ ላይ ጥቃት እሰነዝራለሁ ሲል የዛቻ መግለጫ ማውጣቱን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አልሸባብ ቀጣዩ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኬንያ በሱማሊያ ያሠማራቻቸውን ወታደሮች ካላስወጡ እና ኬንያ ሱማሊያ ላይ ያላትን የውጭ ፖሊሲ ካልቀየሩ፣ በኬንያ ላይ ጥቃት አደርሳለሁ በማለት ነው የዛተው። ኬንያ በአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር በርካታ ወታደሮች አሏት። አልሸባብ ባለፉት ዓመታት በናይሮቢ እና ሌሎች አካባቢዎች የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን አድርሷል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ሰኞ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት እና ሕወሃት ግጭት አቁመው የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል። ኮሚሽኑ አፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ሲቪክና የሐይማኖት ተቋማትና መገናኛ ብዙኀን ግጭቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ ንግግር እንዲጀመርና በጦርነቱ ገፈት ቀማሽ ክልሎች የሰላማዊ ሰዎች ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ሁሉም ወገኖች የግጭቱ ተጎጅ የሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት፣ ደኅንነት፣ አካላዊ እና ሞራላዊ ሁኔታ እና የሰውነት ክብር እንዲያከብሩ ተማጽኗል።
2፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተመድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን መንግሥት እና ሕወሃት አዲስ ያገረሸውን ግጭት ባስቸኳይ አቁመው ንግግር እንዲጀምሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ረድዔት ድርጅቶች ለትግራይ የሚያቀርቡት ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲቀጥል መንግሥትና ሕወሃት ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኗል። በቅርቡ በመቀሌ በሙዓለ ሕጻናት ማዕከል ላይ ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ስለመጎዳታቸው የወጡ ሪፖርቶችና ሰሞኑን በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ በተካሄደ ማጥቃት ላማዊ ሰዎች ዒላማ ሆነዋል መባሉ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጧል።
3፤ ትናንት ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አልጀሪያ የገቡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቡኔ ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአልጀሪያው ፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙሪያ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። ዐቢይ ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ የሚችሉባቸው በርካታ ዘርፎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
4፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኀንና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ በማለት ማስጠንቀቁን ኢዜአ ዘግቧል። መገናኛ ብዙኀን በጦርነት ጊዜ ለአገሪቱ ብሄራዊ ጥቅሞ፣ ለሰላምና ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ያሳሰቡት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ፣ "ለጠላት ፕሮፓጋንዳ ግብዓት የሚውሉ መረጃዎችን" ከማሰራጨት መቆጠብ እንደሚያስፈልግም መክረዋል።
5፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ የሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩን በድረገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። የሙከራ አገልግሎቱ ደንበኞች በሚገዟቸው የኩባንያው የስልክ ሲም ካርዶች የድምጽ፣ የጽሁፍና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን መስጠት ነው። ኩባንያው አንድን የሳፋሪኮም የሞባይል ስልክ ሲም ካርድ የሚሸጠው በ30 ብር ነው።
6፤ በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ አፍሪኮም ዋና አዛዥ ጀኔራል ማይክል ላንግሌይ ዛሬ ሞቃዲሾ መግባታቸውን በሞቃዲሾ የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ጀኔራል ላንግሌይ ነውጠኛውን አልሸባብ በጋራ መዋጋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከሱማሊያው መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር ጋር መነጋገራቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ጀኔራል ላንግሌይ የአፍሪኮም አዲሱ ዋና አዛዥ ሆነው የተሾሙት በወሩ መጀመሪያ ነበር።
7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4344 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4831 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ2586 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ4438 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ5078 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ5580 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረጥ ነጻ ገበያ (አጎዋ) ከታገደች ወዲህ ከሥራ የተቀነሱ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች ከ5 ሺህ 700 በላይ መሻገሩን ሪፖርተር አስነብቧል። ሠራተኞቹ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቀነሱ ናቸው። አገሪቱ ከአጎዋ ከታገደች በኋላ፣ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አምስት የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ሠራተኞችን የቀነሱ ሲሆን፣ ሁለት ፋብሪካዎች ደሞ ሠራተኞቻቸውን አሰናብተው ሥራ አቁመዋል። የአጎዋ እገዳ ካልተነሳ ወይም ፋብሪካዎች አማራጭ ገበያ ካላገኙ፣ ተጨማሪ ሠራተኞች ሊቀነሱ ይችላሉ ተብሏል።
2፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለደንበኞቹ የሚያቀርበው 300 ሚሊዮን ዶላር ብሄራዊ ባንክ እንዲመድብለት መጠየቁን ካፒታል ዘግቧል። ባንኩ በተያዘው በጀት ዓመት ለደንበኞቹ ሚሰጠው ብድር 30 ቢሊዮን ብር እንዲጸድቅለት ማቅረቡንም ዘገባው አመልክቷል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 10.9 ቢሊዮን ብር ብድር ማስመለሱን የገለጸው ባንኩ፣ ለትግራይ ክልል ተበዳሪዎች የሰጠውን ብድር ሳይጨምር አጠቃላይ ያልተመለሰለትን የብድር መጠን ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ጠቁሟል።
3፤ በሲዳማ ክልል አዲስ የተቋቋመው ክልላዊው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት ማካሄዱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ጠቅላላ ጉባዔው የፓርቲውን አመራሮች ጭምር የመረጠ ሲሆን፣ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብም ማጽደቁን ዘገባው አመልክቷል። ፓርቲው 320 አባላት የተገኙበትን ጠቅላላ ጉባዔ ያካሄደው፣ ከሦስት ወር በፊት ከምርጫ ቦርድ ባገኘው ጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ መሠረት ነው።
4፤ የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሑመራ ዞን አስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት በዞኑ በሁሉ አካባቢዎች የሰዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 3:00 ብቻ እንዲሆን መወሰኑን የአማራ ክልል ብዙኀን መገናኛ ዘግቧል። የዞኑ ጸጥታ ምክር ቤት የግል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በሙሉ ከማለዳ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ገደብ መጣሉን ዘገባው አመልክቷል። መኖሪያ ቤት እና ንግድ ቤት አከራዮች ጸጉረ ልውጦችን ይዘው ለጸጥታ አካላት እንዲያቀርቡም ታዘዋል።
5፤ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ከምሽቱ 2:00 በኋላ ከጸጥታ ኃይሎች ውጭ ማናቸውንም የሰዎች እንቅስቃሴ ማገዱን አስታውቋል። አስተዳደሩ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስንም ከልክሏል። ባጃጅ እና አነስተኛ እና መለስተኛ ተሽከርካሪዎች ደሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንዳይንቀሳቀሱ ታግደዋል። አስተዳደሩ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የሚገኙ መጠጥ እና ምግብ ቤቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ ማገዱንም ጨምሮ ገልጧል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከዩክሬን ወደቦች ያስጫነው 23 ሺህ ቶን የምግብ ስንዴ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን አስታውቋል። የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ ከዩክሬን ወደቦች የምግብ እህል ወደ አፍሪካ ሲጓጓዝ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው። ስንዴውን የጫነችው መርከብ ከዩክሬን ወደብ መንቀሳቀስ የቻለችው፣ ሩሲያ በተመድ እና ቱርክ አደራዳሪነት በዩክሬን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ለማንሳት መስማማቷን ተከትሎ ነው።
2፤ በአማራ ክልል የተለያዩ የከተማ አስተዳደሮች በሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲሁም በአገልግሎት መስጫዎች ላይ የሰዓት ገደቦችን መጣል ቀጥለዋል። የኮምቦልቻ፣ ደሴ እና ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ደብረ ብርሃን ከተሞች እንዲሁም የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የእንቅስቃሴ ገደቦች እና ሌሎች ክልከላዎች ከተጣሉባቸው መካከል ይገኙበታል። በሰሜን ጎንደር ዞን ደሞ የደምቢያ እና ደባርቅ ከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ደንግገዋል።
3፤ መንግሥት የማኅበረሰብ ጤና መድኅን አባልነትን ግዴታ ሊያደርግ መሆኑንን ሪፖርተር ዘግቧል። የማኅበረሰብ ጤና መድኅን አባልነትን ግዴታ የሚያደርገው ምክር ቤት በፌደራል ደረጃ ይመሠረታል ተብሏል። ዜጎች አባል ለመሆን የአባልነት መዋጮ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በገጠር አካባቢዎች የአባልነት ክፍያው 375 ብር ሲሆን፣ በትላልቅ ከተሞች ደሞ 665 ብር ነው። የአባልነት መዋጮ የመክፈል አቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች መንግሥት ይከፍላል። እስካሁን በነበረው በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አባልነት መንግሥት መክፈል ከሚችሉት በዓመት 3.1 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል።
4፤ የኢትዮጵያው ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከጥር 2013 ዓ፣ም እስከ ታኅሳስ 2014 ድረስ ባለው አንድ ዓመት 226 ሺህ 417 ቶን ካርጎ በማስተናገድ በካርጎ ጭነት በአፍሪካ አራተኛ ደረጃ መያዙን ዘ ኢስት አፍሪካ አስነብቧል። የኬንያው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ ደሞ ከ363 ሺህ ቶን በላይ ካርጎ በማስተናገድ በአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል። የግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ አውሮፕላኖች ደሞ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በተጠቀሰው ዓመት የአፍሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች በድምሩ ያስተናገዱት 2.15 ሚሊዮን ቶን ካርጎ ነው።
5፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4454 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4943 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 58 ብር ከ6099 ሳንቲም፣ መሸጫው 59 ብር ከ7821 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ3982 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ4462 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በመቀሌ ከተማ የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲሉ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። በጥቃቱ ሦስት ቦምቦች እንደተጣሉ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። ጌታቸው በከተማዋ ላይ ተፈጽሟል ባሉት የአየር ጥቃት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ግን ያሉት ነገር የለም። በመንግሥት ኃይሎች እና በሕወሃት መካከል ግጭት በድጋሚ ካገረሸ ወዲህ፣ በመቀሌ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ሕወሃት ሲገልጽ የአሁኑ ሁለተኛው ነው።
2፤ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ጦርነት በመስጋት ወደ መርሳ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች ጉዞ ጀምረው የነበሩ አንዳንድ የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመራቸውን ለዶይቸቨለ ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልድያ እስከ ትናንት ምሽት መብራት፣ ስልክ እና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳልተቋረጠ እና በከተማዋ ቅርስ ርቀት ተኩስ እንደማይሰማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
3፤ የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል አዲስ ባገረሸው ጦርነት ሳቢያ ካለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ ክልል ተረጅዎች ማቅረብ ማቋረጡን አስታውቋል። ቢሮው ያቋረጠው በየብስ ብቻ ሳይሆን በአየር ጭምር ሲያጓጉዝ የቆየውን ዕርዳታ እንደሆነ ገልጧል። ቢሮው በአማራ እና አፋር ክልሎች ነዋሪዎች ጦርነቱን በመስጋት ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ስለመሆኑ ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች ደርሰውኛል ብሏል።
4፤ ሳፋሪኮም ኩባንያ በድሬዳዋ ለጀመረው የሞባይል አገልግሎት ለድምጽ በደቂቃ 50 ሳንቲም እንደሚያስከፍል ለአል ዓይን ኔትዎርክ በሰጠው ቃል ተናግሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት ደሞ 120 ሜጋ ባይት በ10 ብር፣ 900 ሜጋ ባይት በ50 ብር እና ሁለት ጌጋ ባይት በ100 ብር ለደንበኞቹ እየሸጠ እንደሚገኝ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው እስከ ቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ ወር ድረስ የቴሌኮም አገልግሎቱን በ25 ከተሞች እጀምራለሁ ብሏል።
5፤ በደቡብ ሱዳን ሰላም ስምምነት መሠረት የአማጺዎች ተዋጊዎች ከመንግሥት ጦር ሠራዊት ጋር መቀላቀል መጀመራቸውን ዘግበዋል። ሰሞኑን ከ50 ሺህ በላይ የአማጺ ተዋጊዎች ከመንግሥት ጦር ሠራዊት ጋር ተቀላቅለዋል። አማጺያን በሰላም ትጥቅ ፈተው ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በመዋሃድ አንድ ብሄራዊ ጦር ሠራዊት እንዲቋቋም ማድረግ ከአራት ዓመት በፊት የተፈረመው የሰላም ስምምነቱ ዋነኛ ግብ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር አብርሃም በላይ በስነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
6፤ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያሸነፉበት የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተጭበርብሯል በማለት ተሸናፊው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትሩ ራይላ ኦዲንጋ ያቀረቡትን አቤቱታ ትናንት መስማት ጀምሯል። ሰባት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት፣ የኦዲንጋ ጠበቆችን ከምርጫ ኮሚሽኑ እና ከዊሊያም ሩቶ ጠበቆች ያከራክራል። ችሎቱ በኦዲንጋ አቤቱታ ላይ በመጭው ሰኞ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ መንግሥት የሕወሃት ኃይሎች በወልቃይት፣ ዋግኽምራ ዞን እና ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ አዲስ ጥቃት ከፍተዋል ሲል ዛሬ በቃል አቀባይ ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ከሷል። የመንግሥት ኃይሎች አሁንም የሕወሃትን ጥቃት እየተከላከሉ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ሕወሃት ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ጠይቋል።
2፤ በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ባገረሸው አዲስ ውጊያ ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተመድ ዋና ጸሃፊ ቃል አቀባይ ስቲፈን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በአፋር ክልል እና ትግራይ ክልል አዋሳኞች አካባቢዎች በያሎ እና ገሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ተመድ ሪፖርት እንደደረሰው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። በአፋር እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ጭፍራ ወረዳ ጭምር ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል።
3፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮን ጠርቶ ማነጋገሩን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሱዳን መንግሥት አምባሳደር ይበልጣልን ጠርቶ ያነጋገረው፣ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሱዳን በኩል ጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ የገባ አንድ አውሮፕላን መትቶ ጥሏል በማለት ሰኞ'ለት በካርቱም ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጋር በተያያዘ ነው። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ የአምባሳደሩ መግለጫ ከአስተናጋጇ አገር ጋር ቀድሞ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር የሚጠይቀውን የዲፕሎማቲክ ደንብ የጣሰ ነው ብሏል።
4፤ ትናንት እኩለ ሌሊት በመቀሌ ተፈጸመ የተባለው የአየር ድብደባ የተፈጸመው በአይደር ሆስፒታል አካባቢ ነው ሲል ሮይተርስ የሆስፒታሉን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል። ትናንት ተፈጸመ በተባለው የአየር ድብደባ ምን ጉዳት እንደደረሰ ግን የሮይተርስ ዘገባም ሆነ ሕወሃት አልጠቀሱም። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሕወሃት ውንጀላ ላይ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም። የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲሉ ሌሊት ላይ በትዊተር ገጻቸው የገለጡት የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ነበሩ።
5፤ ኦፌኮ በሰሜን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሱት ግጭቶች ሊፈቱ የሚችሉት ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ እውነተኛና ሁሉን ዓቀፍ ድርድር ብቻ ነው ብሎ እንደሚያምን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመንግሥት እና ሕወሃት መካከል ጦርነቱ በድጋሚ ማገርሸቱ በጦርነቱ አካባቢ ያሉ ሕዝቦችን ለዳግም ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ እንደሆነ ኦፌኮ ገልጧል። ኦፌኮ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ግጭቱን አብርደው ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አድርጓል። ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልል በግጭትና ድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሰብዓዊ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑንም ጠቅሷል።
6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4617 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ5109 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 58 ብር ከ7334 ሳንቲም፣ መሸጫው 59 ብር ከ9081 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ6401 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ6929 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ ራዲዮ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ማክሰኞ'ለት በትንሹ 55 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ የዓይን ምስክሮች መናገራቸውን ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል። ታጣቂዎች ጥቃቱን ፈጸሙ የተባለው በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ፣ አገምሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ነው። ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች ከከተማዋ ዕሁድ'ለት መነሳታቸውን ተከትሎ ነው ሲሉ እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎች ተፈጸመ ስላሉት ግድያ የአስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊዎች ያሉት ነገር የለም።
2፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ያገረሸው ጦርነት ለመምህራን ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት እንቅፋት እንደፈጠረበት ትናንት በሰጠው መግለጫ መናገሩን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መምህራንና ተማሪዎች በጦርነቱ መፈናቀላቸውንና ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን የጠቀሰው ማኅበሩ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ንግግር እንዲጀምር ጠይቋል። ለትግራይ ዕርዳታ ፈላጊዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ እንዲቀጥልም ማኅበሩ ጥሪ አድርጓል።
3፤ የኢትዮጵያ መርከብ እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በሰኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 3.6 ሚሊዮን ካርጎ በማጓጓዝ 3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥራ አስኪያጅ ማሞ ምኅረቱ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። የድርጅቱ ትርፍ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ121 በመቶ ብልጫ እንዳለው ማሞ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ90 በመቶ እድገት እንዳለው ማሞ ጠቁመዋል።
4፤ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎዛ በአገራቸው በውጭ ዜጎች ላይ የተቃጣውን ተቃውሞ መንግሥታቸው እንደማይታገስ ለፓርላማው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። በፕሪቶሪያ "ዳዱላ" የተባለ በውጭ ፍልሰተኞች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ንቅናቄ፣ ፍልሰተኞች እና የውጭ ዜጎች ሕክምና እንዳያገኙ ማገድ መጀመሩን መንግሥት ገልጧል። ንቅናቄው ዜጎች በሆስፒታሎች ለሚጠብቁት ረጅም ወረፋና ጥራት የለው ላሉት የሕክምና አገልግሎት ፍልሰተኞችን ተጠያቂ ያደርጋል። በአገሪቱ አራት ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። [ዋዜማ ራዲዮ]