ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሱማሊያዋ ፑንትላንድ አስተዳደር ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች እንዲወጡለት ማዘዙን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የግዛቲቷ ዋና ከተማ ጋሮዌ ከንቲባ ሕጋዊ ያልኾኑ ስደተኞች ራሳቸው ባስቸኳይ ካልወጡ የማባረር ርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቃቸውን ዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ አስተዳደር ኢትዮጵያዊያኑን ፍልሰተኞች ለማስወጣት የወሰነው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ እንደኾነ ተገልጧል። ሞቃዲሾ፣ ከሳምንታት በፊት ፑንትላንድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ለመዝጋት ወስኛለኹ ማለቷ አይዘነጋም።
2፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት 50 ያህል የረድዔት ሠራተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ሕይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል። የረድዔት ሠራተኞች ኾን ተብሎ ዒላማ ባይደረጉም፣ የአገሪቱ የጸጥታ ኹኔታ ግን ለአደጋ እንዳጋለጣቸው ድርጅቱ ጠቅሷል። የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ከአውሮፓዊያኑ 2019 ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ 46 የረድዔት ሠራተኞች እንደተገደሉና 36ቱ የተገደሉት ከግጭት ጋር በተያያዘ እንደኾነ ባለፈው የካቲት ተናግሮ ነበር።
3፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ በሳዑዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 172 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው እንደመለሰ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከተመላሾቹ ስደተኞች መካከል፣ ኹለት ጨቅላ ሕጻናት እና ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኾኑ 29 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል። ብሄራዊ ኮሚቴው ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለስ ችሏል።
4፤ የአሜሪካ ፌደራል አቬሽን ባለሥልጣን አንድ የሳውዝዌስት አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 የመንገደኞች አውሮፕላን ባለፈው ወር በረራ ላይ ከፍታው በድንገት በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ አዲስ ምርመራ ከፍቷል። አውሮፕላኑን ያጋጠመው ክስተት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰከሰው ማክስ 8 አውሮፕላን ካጋጠመው ክስተት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቦይንግ ኩባንያ ላለፉት ኹለት ተከታታይ ወራት የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኑ አንድም አዲስ ትዕዛዝ እንዳልደረሰው የአሜሪካ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኩባንያው ለማክስ 8 አውሮፕላኖቹ አዲስ ትዕዛዝ ያልደረሰው፣ ማክስ 8 አውሮፕላኖቹ በቅርብ ወራት በረራ ላይ በተከታታይ ችግሮች ያጋጠሟቸው መኾኑን ተከትሎ እንደኾነ ተገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በስድስት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ የተከሰተው ርሃብ በበርካታ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉን ዋዜማ ተረድታለች። ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት ረጅም ርቀት እንደሚጓዙ ዋዜማ ሰምታለች። ጭናቅሰን፣ መልካ በሎ፣ ሚደጋ፣ ፈዲስ፣ መዩ ሙሉኬ እና ቁምቢ በተባሉ ወረዳዎች ለተከሰተው ድርቅና ርሃብ፣ መንግሥት እስካኹን ድጋፍ እንዳላደረገ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በቀደሙት ጊዜያት ይደረግ ከነበረው በተቃራኒ የአኹኑ መንግሥት ለርሃብ የቅድመ መከላከል ሥራ ባለመስራቱ ችግሩ እንደተባባሰ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የወረዳዎቹ ነዋሪዎቹ ርሃቡን በመሸሽ ወደ ሐረር ከተማና ወደ መሃል አገር በመፍለስ ላይ እንደኾኑ ተገልጧል። ዋዜማ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤትን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ጠይቃ የነበረ ቢኾንም፣ ጽሕፈት ቤቱ ግን ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይኾን ቀርቷል።
2፤ በአማራ ክልል ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ባለፈው ሳምንት በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ20 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ነዋሪዎችን እና የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ግድያዎቹ ሰኔ 7 እና 9 በቀራኒዮ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ጂጋ ከተማ የተፈጸሙት፣ የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ ካደረጉ በኋላ እንደኾነ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። በጂጋ ከተማ፣ የመንግሥት ኃይሎች መምህራንና የባንክ ሠራተኞችን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል ተብሏል። በምሥራቅ ጎጃም ዞን ኸለት እጁ እነሴ ወረዳ ደሞ፣ ሰኔ 7 ቀን የመንግሥት ወታደሮች ሰባት ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ግድያዎቹ "የበቀል ርምጃ" እንደሚመስሉ የዓይን ምስክሮች መግለጣቸውንም በዘገባው አመልክቷል።
3፤ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች ሦስት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርጉትን አፈና እንዲያቆሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ድርጅቶቹ፣ በአገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ የሚፈጸመው ማስፈራሪያና ዛቻ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ ሥራቸውን ባግባቡ እንዳይሠሩ አድርጓል ብለዋል። የመንግሥት የጸጥታና ደኅንነት ኃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ካውንስል (ኢሰመጉ) እና ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጽሙት ማስፈራሪያ እና ዛቻ መጨመሩን ድርጅቶቹ በመግለጫቸው አውስተዋል። የኢትዮጵያ ዓለማቀፍና አሕጉራዊ አጋሮች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን፣ የጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን መብት እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም ክትትል እንዲያደርጉ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።
4፤ የፌደራሉ ዋና ኦዲተር፣ 16 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ከሥራ ለተሰናበቱ ሠራተኞች ደመወዝ ሲከፍሉ እንደቆዩ ማረጋገጡን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል። መስሪያ ቤቶቹ ለሌሉ ወይም ለተሰናበቱ ሠራተኞች 485 ሚሊዮን 183 ሺህ ብር በላይ እንደተከፈሉ ተቋሙ ገልጧል። 73 መስሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ደሞ፣ ከመንግሥት የግዢ አዋጅና መመሪያ ውጭ የ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ግዢ እንደፈጸሙ ተቋሙ ጠቅሷል። የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ያለ ጨረታ በቀጥታ የ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ግዢ እንደፈጸሙ የገለጠው የተቋሙ ሪፖርት፣ ከደንብና መመሪያ ውጪ ከፍተኛ ግዢ ከፈጸሙት የ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ግዢ ፈጽሞ የተገኘው የገቢዎች ሚንስቴር ነው ብሏል።
5፤ የፌደራሉ ዋና ኦዲተር የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የፓስፖርት መመዝገቢያ ቀን ካሳለፉ ግለሰቦች የሚሰበስበውን የቅጣት ገንዘብ በግለሰቦች ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ሲያስቀምጥ እንደኖረ አጋልጧል። ተቋሙ፣ በአዋጅ ባልተሠጠው ሥልጣን ነሃሴ 2015 ዓ፣ም የቅጣት ገንዘብ መሰብሰቢያ ዝርዝር መመሪያ በማውጣት ተግባራዊ ማድረጉንና ከሰበሰበው ገንዘብ ከግማሽ በላይ የሚኾነውን ለሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ክፍያና ለሠራተኞች የበዓል ስጦታ እንዳዋለው ተገልጧል። ተቋሙ፣ በአምስት ወራት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በግለሰቦች ስም በከፈተው የባንክ ሒሳብ 7 ነጥብ ከ9 ሚሊዮን ብር እንዳስገባና ለትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ለበዓል ስጦታ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮኑን ብር አውሎታል ተብሏል። በሕጉ መሠረት፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በተሰጣቸው ሥልጣን ከአገልግሎቶቻቸው የሚሰበስቡትን ገቢ በቀጥታ ፈሰስ ማድረግ ያለባቸው ለገንዘብ ሚንስቴር ነው።
6፤ የማላዊ መንግሥት 238 ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው ሊመልስ መኾኑን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ማላዊ በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች የምትመልሰው፣ ከዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ጋር በመተባበር እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የአገሪቱ ኢምግሬሽን ባለሥልጣናት ለኢትዮጵያዊያኑ መመለሻ የጉዞ ሰነዶችን አዘጋጅተዋል ተብሏል። ከጥር ወር ወዲህ ብቻ የማላዊ ጸጥታ ኃይሎች ወደ አገሪቱ በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል ያሏቸውን 142 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን እንደያዙ ተገልጧል። ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ማላዊ ግዛት ውስጥ የሚያዙት፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቋረጥ ሲሞክሩ ነው። ባለፈው ዓመት በሰሜናዊ ማላዊ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች የጅምላ መቃብር መገኘቱ ይታወሳል።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ2229 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ3674 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ2170 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ6013 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ3029 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ5290 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

በኦሮሚያ የማዳበሪያ ስርጭት መደነቃቀፍ ገጥሞታል፣ የማዳበሪያ ስርቆት በስፋት ተስተውሏል
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ በአርሲና ባሌ አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮችም በተመሳሳይ ማዳበሪያ ለማግኘት ተቸግረናል ሲሉ አቤቱታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት በበኩሉ፣ ብልሹ አሰራርና ስርቆት የማዳበሪያ ስርጭቱ ላይ እንቅፋት እንደፈጠረ አምኖ ከፍተኛ መጠን ያለው ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ማከፋፈሉን ነግሮናል። ዝርዝሩን ያንብቡት- https://tinyurl.com/3b2crwrn

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ሰኔ 12/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኦነግ፣ የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ቆንዶላ ቀበሌ ሰኔ 7 ቀን በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል በማለት ከሷል። ኦነግ፣ የፋኖ ታጣቂዎች በሠርገኞች ላይ ቦምብ ጥለው 20 ሰዎችን እንደገደሉና አራት ሰዎችን ደሞ በጥይት እንደገደሉ አረጋግጫለኹ ብሏል። ኦነግ፣ በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ወሊሶ ከተማ ሆስፒታል እየታከሙ መኾኑን ገልጧል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የፋኖ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት እንዲያወግዙ ኦነግ በመግለጫው ጠይቋል።
2፤ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ፣ በክልሉ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን መናገሩን ቪኦኤ ዘግቧል። ባለፉት 10 ወራት ብቻ በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ500 ሺሕ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ የጤና ቢሮው ሃላፊዎች መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በዞኑ የቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዎችም፣ በበሽታው ሕጻናት እንደሞቱ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የክልሉ ጤና ቢሮ በበኩሉ፣ በሽታውን ለመቆጣጠር በመድሃኒት አቅርቦት ላይ እየሠራኹ ነው ብሏል ተብሏል።
3፤ የሱማሊያ መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሃመድ ኑር፣ የኢትዮጵያንና ሶማሊላንድ ራስ ገዝን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት "የቀን ሕልም" በማለት ማጣጣላቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሚንስትር ኑር፣ ኢትዮጵያ የሱማሊያን "አንድ ስንዝር መሬት ልትወስድ እንደማትችል ታውቀዋለች" በማለት በማለት መናገራቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ሚንስትሩ፣ ሱማሊያ በዚህ ስምምነት የግዛት አንድነቷ ከተጣሰ፣ "ወታደራዊ ስልቶችን ልትጠቀም ትችላለች" በማለት ጭምር እንደዛቱ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
4፤ የአሜሪካ መከላከያ ባለሥልጣናት፣ የኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት አልሸባብ በርካታ ተዋጊዎችን እንዲመለምል አስችሎታል በማለት መናገራቸውን የአሜሪካ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ባለሥልጣናቱ፣ የሱማሊያ ጦር ባለፉት ኹለት ዓመታት በማዕከላዊ የአገሪቱ ክፍሎች ያገኛቸውን ኹሉንም ድሎች አልሸባብ ባለፉት ጥቂት ወራት ቀልብሷቸዋል ማለታቸውንም ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የየመን ኹቲ ኃይሎች ለአልሸባብ ዘመናዊ ጦር መሳሪያዎችን የሚሠሩ ሦስቱ ባለሙያዎችን መላካቸው እንደታወቀም የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጠቁመዋል ተብሏል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ሰኔ 12/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ባሌ ዞኖች እና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ አለማግኘታቸው እንዳሳሰባቸው ለዋዜማ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት በበኩሉ፣ የማዳበሪያ ሥርጭቱ ለብልሹ አሠራርና ሥርቆት የተጋለጠ እንደነበር ለዋዜማ ተናግሯል። የክልሉ መንግሥት የማዳበሪያ ሥርጭቱን ከግብርና ቢሮው ወደ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አዙሮታል። በምዕራብ ሸዋ ዞን ጉደር ከተማ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ መንግሥት ከተመነው ዋጋ በላይ በኩንታል ከ500 እስከ 700 ብር ጭማሪ ተደርጎበት እንደሚሸጥላቸው ጠቁመዋል። ባኹኑ ወቅት በመንግሥት የዋጋ ተመን መሠረት የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ 3 ሺህ 800 ብር ነው። አርሶ አደሮች የጤና ኢንሹራንስ፣ የመንገድ፣ የስፖርት፣ የሴቶች ሊግ እና የሰላምና ጸጥታ የመሳሰሉ ክፍያዎችን የከፈሉበትን ደረሰኝ ካላሳዩ ድረስ ማዳበሪያ መውሰድ እንደማይችሉም አስረድተዋል።
2፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በአውላላ የሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያ የተጠለለች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ኹለት ኢትዮጵያዊያን ሰኞ'ለት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት እንደተገደሉ መስማቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ስደተኛዋና ኢትዮጵያዊያኑ የተገደሉት፣ ከገንዳውሃ ከተማ ወደ ሌላ ቦታ በሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ሲጓዙ፣ ታጣቂዎች ተሽከርካሪው ውስጥ ከነበረ የመንግሥት ጸጥታ ባልደረባ ጋር የተኩስ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። በተኩስ ልውውጡ ሌሎች ኹለት ኢትዮጵያዊያን ቆስለዋል ተብሏል። የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ ግድያው ስደተኛዋን ዒለማ ያደረገ እንዳልነበር ማረጋገጡን የዜና ምንጩ ጠቅሷል።
3፤ ብሄራዊ ባንክ፣ ከ30 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለሚያቀርቡለት አቅራቢዎች ከዓለም ገበያ ዋጋ ላይ 72 በመቶ ማበረታቻ ጭማሪ እያደረገ ለመግዛት ዝግጁ መኾኑን መናገሩን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። ባንኩ፣ 3 ኪሎ ግራም እስከ 30 ኪሎ ግራም ወርቅ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎች ደሞ በዓለም የገበያ ዋጋ ላይ 67 በመቶ ማበረታቻ ተጨማሪ እንደሚያደርግ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ባንኩ፣ ይኼን ማሻሻያ ከሰኔ 10 ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል። ባንኩ ማሻሻያውን ያደረገው፣ በኮንትሮባንድ ንግድ ሳቢያ መስፋፋት አገሪቱ ከወርቅ ሽያጭ ማግኘት የሚገባት ገቢ እያሽቆለቆለ መሄዱን ተከትሎ ነው። የወርቅ ማዕድን የሚገኝባቸው አንዳንድ አካባቢዎች በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር እንደኾኑ ካኹን ቀደም ተዘግቦ ነበር።
4፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሰኔ 16 በሚያካሂደው የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ 1 ሚሊዮን ድምጽ ሰጪዎች እንደሚሳተፉ አስታውቋል። ቦርዱ በ29 የምርጫ ክልሎች ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫዎችን የሚያደርገው፣ በሱማሌ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በአፋር ክልሎች ነው። ለምርጫው ከ1258 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን እንዲኹም ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች 380 ዕጩዎች መመዝገባቸውን ቦርዱ ገልጧል።
5፤ ግብርና ሚንስቴር፣ መንግሥት ለግል ባለሃብቶች ካስተላለፈው 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሔክታር የእርሻ መሬት ባኹኑ ወቅት በመልማት ላይ የሚገኘው 41 በመቶው ብቻ እንደኾነ በዘርፉ ላይ በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ መናገሩን ሪፖርተር ዘግቧል። የእርሻ መሬት ከወሰዱት 5 ሺህ 700 ባለሃብቶች መካከል 98 ነጥብ 6 በመቶ የሚኾኑት የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እንደኾኑ ሚንስቴሩ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። ባለሃብቶች በሚገጥሟቸው የፋይናንስ እጥረትና ሌሎች ውስንነቶች የተነሳ፣ ያለሙት መሬት ምርታመነቱ ዝቅተኛ መኾኑም ተገልጧል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክም፣ ለግብርናው ዘርፍ ከሰጠው 10 ቢሊዮን ብር ብድር ግማሹ የተበላሸ ብድር እንደኾነበት ተናግሯል ተብሏል።
6፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ2406 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ3854 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ3204 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ7068 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ3505 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ5775 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

#NEWSALERTS
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን ዋዜማ ተረድታለች፡፡ ዝርዝሩን ያንብቡት
https://tinyurl.com/4cdun39m

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በብሔራዊ ባንክና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይወያያል። ምክር ቤቱ፣ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ገልጧል። ረቂቅ አዋጁ፣ የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ በተቀጥላ፣y ቅርንጫፍ በማቋቋም ወይም ወኪል ቢሮ በመክፈት በባንክ ዘርፍ እንዲሠማሩ የሚፈቅድ ነው። ምክር ቤቱ፣ የሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበለት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ጭምር እንደሚወያይ አስታውቋል።
2፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕዝብ ተመራጮቹ እነ ዮሃንስ ቧያሌው፣ ክርስትያን ታደለ እና ካሳ ተሻገር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ትናንት ውድቅ አድርጓል። ችሎቱ፣y ተከሳሾቹ በዓቃቤ ሕግ ላይ የሚያቀርቡትን የክስ መቃወሚያ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በሌላ በኩል፣ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢሕአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራን ጨምሮ አዋሽ አርባ ጊዜያዊ ማቆያ ታስረው የነበሩና ባለፈው ሰኞ ፍርድ ቤት በገንዘብ ዋስትና እንዲፈቱ የወሰነላቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች ጉዳይ በመጭው ዓርብ ለማየት ቀጥሯል። ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያመራው፣ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው የገንዘብ ዋስትና ውሳኔ ላይ ይግባኝ በመጠየቁ ነው።
3፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 178 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ትናንት ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከተመላሾቹ መካከል፣ እድሜያቸው ከአስራh ስምንት ዓመት በታች የኾኑ 18 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል። ኮሚቴው፣ ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ከ46 ሺሕ በላይ ፍልሰተኞችን መልሷል።
4፤ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ፣ መንግሥታቸው ከአልሸባብ ጋር ለመደራደር ዝግጁ እንደኾነ መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ ቱርክ ለጉብኝት በሄዱበት ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥታቸው ከአልሸባብ ጋር ለመደራደር እንደማያቅማማና ትናትም ኾነ ነገ ለድርድር ዝግጁ መኾኑን እንደጠቆሙ ተገልጧል። አልሸባብም ለድርድር ዝግጁ ይኾናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ተናግረዋል ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ ባኹኑ ወቅት ለምን ለአልሸባብ የድርድር ሃሳብ እንዳነሱ ግልጽ እንዳልኾነ ዘገባዎቹ ጨምረው አመልክተዋል።
5፤ አልሸባብ፣ አማርኛ እና ኦሮሚኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የፕሮፓጋንዳ ተንቀሳቃሽ ምስል ሰሞኑን አሠራጭቷል። ቡድኑ ያሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል፣ "ልዩ ኃይል" ያላቸውን ተዋጊዎች ወታደራዊ ሥልጠና የሚያሳይ ነው። የአልሸባብ ተዋጊዎች ከኹለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በርካታ ኪሎ ሜትሮች ዘልቀው መግባታቸውና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር መዋጋታቸው ይታወሳል። የሱማሊያ መንግሥት፣ አልሸባብ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ተዋጊዎችን ለመመልመል ሊጠቀምበት ይችላል በማለት ማስጠንቀቁ አይዘነጋም። ቡድኑ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከየመን ኹቲ ኃይሎች ወታደራዊ ድጋፍ እያገኘ እንደኾነ ይነገራል።
6፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ግብጽ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ስደተኞችን አባራለች በማለት ከሷል። ግብጽ፣ ከጥር እስከ መጋቢት ብቻ 800 የሱዳን ስደተኞች ጥገኝነት የመጠየቅና የመንግሥትን ውሳኔ በፍርድ ቤት የሚሞግቱበት እድል ሳያገኙ እንዳባረረች ገልጧል። የአገሪቱ ጸጥታ ኃይሎች በርካታ ሱዳነዊያን ስደተኞችንም አስራለች ተብሏል። የሱዳኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ 500 ሺህ ስደተኞች ግብጽ እንደገቡ ይገመታል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸውና በሚንቀሳቀሱባቸው ወረዳዎች የመንግሥትና የግል ባንኮች ካለፈው ሳምንት ዓረብ ጀምሮ አገልግሎት ማቋረጣቸውን ዋዜማ ተረድታለች፡፡ በመንግሥት ትዕዛዝ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል፣ መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንጾኪያ ገምዛ እና ቀወት እንደሚገኙበት ዋዜማ ከወረዳዎቹ የባንክ ቅርንጫፎች አረጋግጣለች። የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አካል በኾነችው ማጀቴ ከተማ ባንኮች አገለግሎት መቀጠላቸውን ዋዜማ ሰምታለች። የአካባቢው የመንግሥት የጸጥታ ዕዝ ትዕዛዙን ያስተላለፈው፣ ባካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን እስኪያጸዳ ድረስ እንደኾነ ገልጧል ተብሏል። የመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማና የግሼ ወረዳ ከተማ ራቤል ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ስዓት በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር እንደኾኑ ዋዜማ ተረድታለች።
2፤ እናት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ የመንግሥት ኃይሎች ምዕራብ ጎጃም ጅጋ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሰኔ 9 ቀን በንጹሃን ላይ የፈጸሙት ግድያ ባስቸኳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራና አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ፣ ወታደሮች ጎህ በተባለ ሆቴል በመመገብ ላይ የነበሩ 12 ሰላማዊ ሰዎችን አሰልፈው ረሽነዋል በማለት ከሰዋል። የመንግሥት ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ "የበቀል ርምጃ" የወሰዱት፣ ከጅጋ ከተማ ወጣ ብሎ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ እንደኾነ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። ከተገደሉት መካከል፣ የባንክ ሠራተኞች፣ መምህራንና የጉልበት ሠራተኞች እንደሚገኙበት የገለጡት ፓርቲዎቹ፣ የመንግሥት ኃይሎች ስድስት ሰዎችን ከንግድና መኖሪያ ቤቶች ጭምር እያስወጡ ረሽነዋል ብለዋል። ኹለት በጥይት ተመተው የቆሰሉ ሰዎች በባሕርዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ናቸው ተብሏል።
3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በብሔራዊ ባንክና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል። ምክር ቤቱ፣ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱንም ገልጧል። የብሄራዊ ባንክ አዋጅ፣ ለ16 ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ አዋጅ ነው። መንግሥት ረቂቅ አዋጁን ያዘጋጀው፣ የብሔራዊ ባንክን ሥልጣንና ተግባር እንደገና በመወሰን የባንኩን የቁጥጥር አቅም ማጎልበት አስፈላጊ በመኾኑ እንደኾነ ተገልጧል። ሚንስትሮች ምክር ቤት፣ የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ በባንክ ዘርፍ እንዲሠማሩ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ይታወሳል።
4፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚንስትሮች ምክር ባቀረበለት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ተወያይቶ ለፕላን፣ ፋይናንስና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ለቋሚ ኮሚቴው ለመምራት በሰጠው ድምጽ፣ ሦስት የተቃውሞ ድምጾች ተመዝግበዋል። ረቂቅ አዋጁን የተቃወሙ ኢዜማን እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የወከሉ የምክር ቤቱ አባላት፣ መንግሥት የሚጥላቸው ተደራራቢ ታክሶች ድሃውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ እንደኾኑ ተናግረዋል። የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ፣ ሕዝቡ የንብረት ታክስን ሊቋቋም የሚችልበት አቅም እንደሌለው ገልጠው ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀዋል። ረቂቅ አዋጁ፣ በከተሞች በግለሰቦች መሬት፣ በመሬት ላይ በሚደረጉ ማሻሻያዎች እና ሕንጻዎች ላይ መንግሥት ታክስ እንዲሰበስብ የሚፈቅድ ነው። የንብረት ታክስን የመሰብሰብ አዋጅ ለክልሎች እንዲኾን ቀደም ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ፌደሬሽን ምክር ቤት በጋራ መወሰናቸው ይታወሳል።
5፤ ማላዊ ውስጥ በጅምላ መቃብር ውስጥ ተቀብረው ከተገኙት 29 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የነበረው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ልጅ ነጻ እንደተባለ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሰዎችን ከማዘዋወር ወንጀል ጋር በተያያዘ፣ ፖሊስ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ልጅ ታዲኪራ ማፉዛን እና ሌሎች በግብረ አበርነት የተጠረጠሩ ሰባት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ያዋለው ባለፈው ዓመት ኅዳር ነበር። የ29ኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች አስከሬን በሰሜናዊ ማላዊ በጅምላ መቃብር ውስጥ የተገኘው ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ነበር። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከማላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያዊያኑን አሟሟት እንደሚያጣራ በወቅቱ አስታውቆ የነበረ ቢኾንም፣ ላለፉት በርካታ ወራት በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣው መረጃ የለም። ማላዊ በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች መተላለፊያ ናት።
6፤ ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ውስጥ የተከሰከሱ የቦይንግ ማክስ 8 አውሮፕላኖች ተጎጂዎች ቤተሰቦች ቦይንግ ኩባንያ ከ24 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቅጣት እንዲከፍል ጠይቀዋል። የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች በጠበቆቻቸው በኩል ለአሜሪካ ፍትህ መስሪያ ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ቦይንግ ኩባንያ ከፍተኛ ቅጣት መክፈሉ ተገቢ መኾኑን ገልጸዋል። የተጎጂ ቤተሰቦች ይህን ያሉት፣ ፍትህ መስሪያ ቤቱ ቦይንግ ከወንጀል ተጠያቂነት ለመዳን ለሦስት ዓመታት የገባውን ስምምነት አላከበረም ማለቱን ተከትሎ ነው። ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በተከሰከሰው ማክስ 8 አውሮፕላን የ137 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። የተጎጂ ቤተሰቦች አደጋዎቹ በተከሰቱበት ወቅት በነበሩ የኩባንያው ሃላፊዎች ላይ ጭምር የወንጀል ክስ እንዲመሠረትባቸው ጠይቀዋል። ፍትህ መስሪያ ቤት በኩባንያው ላይ የማጭበርበር ክስ መመስረት አላመመስረቴን በሰኔ ወር መጨረሻ አውስናለሁ ብሏል።
7፤ ሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች ከግዛቷ የሚወጡበት ጊዜ እንዲዘገይላት መጠየቋን ሮይተርስ ዘግቧል። የሱማሊያ መንግሥት በተያዘው ሰኔ ወር ከአገሪቱ ከሚወጡት 4 ሺህ የኅብረቱ ወታደሮች ገሚሶቹ እስከ መስከረም እንዲቆዩ ለኅብረቱ ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ እንደጠየቀ ዘገባው አመልክቷል። አውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ግን በገንዘብ እጥረት ሳቢያ የሰላም አስከባሪው ቁጥር እንዲቀንስ እንደሚፈልጉ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የኅብረቱ ጦር በመጭው ዓመት ታኅሳስ ጠቅልሎ ሲወጣ በሚተካው ተልዕኮ ይዘት ላይ፣ በአፍሪካ ኅብረት እና በሱማሊያ መንግሥት መካከል ስምምነት እንደሌለም ርሮይተርስ ሰምቻለሁ ብሏል። [ዋዜማ]

ባለፉት ዓመታት በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከብሄራዊ ባንክ የወሰደው መንግስት ከዚህ በኋላ እንደፈለገ የሚበደርበትን አሰራር የሚከለክል አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
ዋዜማ የተመለከተችው ረቂቅ አዋጅ እንዳሰፈረው መንግስት የከፋ ችግር ካልገጠመው በቀር ከብሄራዊ ባንክ ያለገደብ የሚበደርበት አሰራር ከዚህ በኋላ በህግ የተከለከለ ይሆናል። ዝርዝር ይዘቱን ያንብቡት- https://tinyurl.com/4yz2wvc7

ለቸኮለ! ዓርብ ሰኔ 14/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ መንግሥት የከፋ ችግር ካልገጠመው በቀር ከብሄራዊ ባንክ እንደፈለገ እንዳይበደር የሚከለክል አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ዋዜማ በተመለከተችው የብሄራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ በአዋጁ በግልጽ ካልተፈቀደ በስተቀር ባንኩ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ ለፌዴራል፣ ለክልል፣ ለታችኛዎቹ የመንግሥት አስተዳደር እርከኖች፣ ለከተማ አስተዳደሮች ወይም ለመንግስት ተቋማት ብድር መስጠት እንደማይችል ሠፍሯል። ረቂቅ አዋጁ፣ መንግሥት ሒሳቡ እየታየ ባንድ ዓመት ውስጥ የሚከፈል የአጭር ጊዜ ጊዜ ብድር ሊያገኝ እንደሚችል ደንግጓል። ኾኖም መንግሥት የአጭር ጊዜ ብድር ማግኘት የሚችለው፣ ያልጠበቀ የማኅበረሰብ ጤና ችግር፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ ድርቅ፣ አጠቃላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይም በመንግስት ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የውጭ ኢኮኖሚ ለውጦች ካጋጥሙ እንደኾነ ተገልጧል። መንግሥት ባለፉት ዓመታት ከባንኩ በመቶ ቢሊዮኖች የሚገመት ብር ተበድሮ አልመለሰም።
2፤ የተመድ የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተር ሞሃመድ ባቢከር፣ የኤርትራ ኃይሎች አኹንም በትግራይ ክልል እንዳንድ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽማሉ በማለት ከሰዋል። ባቢከር ለተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት ባቀረቡት አራተኛው ሪፖርታቸው፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ የዓለማቀፉን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ እንዲያከብሩና በአወዛጋቢ ቦታዎች የሚኖሩ ነዋሪዎችን መብት እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል። የኤርትራ መንግሥት በዜጎቹ ላይ የሚፈጽመውን የመብት ጥሰት አኹንም ቀጥሏል ያሉት ልዩ ራፖርተሩ፣ የኤርትራ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ይዞታውን ለማሻሻል አስቸኳይ ርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቀዋል።
3፤ አሜሪካ ከዘንድሮው ጥቅምት ወር ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠለሉ 2 ሺህ ስደተኞችን ተቀብላ ማስፈሯን የአሜሪካ ኢምባሲ የዓለም ስደተኞችን ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢምባሲው፣ አሜሪካ ተጨማሪ 2 ሺህ 400 ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች እንደኾነ ገልጧል። አሜሪካ ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 140 ሚሊዮን ዶላር መለገሷንም ኢምባሲው ጠቅሷል። በተያያዘ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ መንግሥት የስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን መብት ለማስከበር ቁርጠኝነቱን እንዲያረጋግጥ ጠይቋል። ስደተኞች ከጥገኝነት፣ ከደኅንነት፣ ከሕጋዊ ሰነድ፣ ከፍትህና ሰብዓዊ ድጋፍ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዲኹም የዘፈቀደ እስር ይገጠሟቸዋል ያለው ኮሚሽኑ፣ መንግሥት ፍትሃዊና ብቁ የኾነ የጥገኝነት አሰጣጥ አሠራር እንዲከተልና የስደተኞችን ደኅንነትና ክብር የሚያረጋግጥ ምቹ ከባቢ እንዲፈጥር አሳስቧል።
4፤ ምርጫ ቦርድ፣ ስኔ 16 በአራት ክልሎች ለሚያካሂደው ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ድምጽ በሚሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ አሳስቧል። ሆስፒታሎች፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት ሰጪዎች ግን አገልግሎት መስጠት መቀበል እንደሚችሉ ቦርዱ ገልጧል። ቦርዱ ይህን ማሳሰቢያ ያወጣው፣ የምርጫ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ ምግባር ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት እንደኾነ ጠቅሷል። ቦርዱ፣ ዜጎች ድምጽ በሚሰጡባቸው የምርጫ ክልሎች ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ኹነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይዙም ጥሪ ጠይቋል። ምርጫ ቦርድ በዕለቱ የ6ኛውን ዙር አገር ዓቀፍ ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ የሚያካሂደው፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ነው።
5፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ለኃይማኖታዊ ጉዞ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የተጓዙ አምስት ኢትዮጵያዊያን በደረሰባቸው የመኪና አደጋ እና በሕመም ሕይወታቸው ማለፉን እንደተናገረ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። አራቱ ኢትዮጵያዊያን የሞቱት፣ በሕመምና በጉዞ መጨናነቅ ሳቢያ እንደኾነ ምክር ቤቱ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። ባኹኑ ወቅት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በተከሰተው ሙቀት ሳቢያ፣ በትንሹ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል። ኾኖም ከኢትዮጵያዊያን ሐጃጆች በሙቀት ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ምክር ቤቱ ገልጧል ተብሏል።
6፤ ሱማሊያ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት በእጩነት ያቀረበቻቸው የቀድሞዋ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፋውዚያ የሱፍ አደም፣ ራሳቸውን ከእጩነት እንዲያገሉ መንግሥት ግፊት እያደረገባቸው መኾኑን እንደተናገሩ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፋውዚያ አደም፣ ከእጩነት ራሳቸውን እንዲያገሉ ግፊት የተደረገባቸው፣ የሱማሊያ መንግሥት ድጋፉን ለሌላኛው የምሥራቅ አፍሪካ እጩ ለጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሞሐመድ የሱፍ በማዞሩ እንደኾነ ገልጸዋል ተብሏል። ሙሳ ፋኪን የሚተካው የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ከምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚመረጠው፣ በቀጣዩ ዓመት የካቲት ነው። ከፋውዚያ አደም ሌላ ቀሪዎቹ እጩዎች፣ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና የኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ናቸው።
7፤ አሜሪካ፣ በኬንያ መሪነት በሔይቲ ጸጥታ ለማስከበር ለሚሠማራው የፖሊስ ኃይል 109 ሚሊዮን ዶላር መድባለች። ገንዘቡ፣ በአገሪቱ ዋና ከተማ ፖርቶ ፕሪንስ ለሚሠማራው የጸጥታ አሳሽ ቡድን ቁሳቁሶች መግዣ የሚውል እንደኾነ ተገልጧል። ኬንያ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በሔይቲ የታጠቁ ወሮበሎች የፈጠሩትን ኹከት ለመቆጣጠር 1 ሺህ ፖሊሶችን ለማሠማራት አቅዳለች። አፍሪካዊያኑን ቤኒን እና ቻድን ጨምሮ ሌሎች ስምንት አገራት በኬንያ መሪነት በሔይቲ ለሚሠማራው ዓለማቀፍ ተልዕኮ የፖሊስ ኃይል እንደሚልኩ ቃል ገብተዋል። ኬንያ የፖሊስ ኃይሏን በሔይቲ ለማሠማራት መወሰኗ በአገር ውስጥ ተቃውሞ እንደገጠመው ነው።
8፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ2653 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ4106 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ4105 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ7987 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ4457 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ6746 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ ሰኔ 15/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢሰመጉን ጨምሮ 12 አገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ መንግሥት እየፈጸመባቸው የሚገኙት ጫናዎችና ጥቃቶች መጨመራቸውን ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል። መንግሥት በሚያወጣቸው ሕጎችና ፖሊሲዎች አማካኝነት የሚፈጥራቸው ጫናዎች ጎልተው እንደሚታዩ የገለጡት ድርጅቶቹ፣ በአገሪቱ የሲቪክ ምኅዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ መሄዱን ገልጸዋል። በአመራሮቻቸውና ሠራተኞቻቸው ላይ ማስፈራሪያ፣ ሕገወጥና የዘፈቀደ እሥር፣ የቢሮ ሰበራ እና ንብረቶችን የመውሰድ ድርጊቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሱም ድርጅቶቹ በመግለጫቸው አውስተዋል። ድርጅቶቹ ጨምረውም፣ ከሥጋት ውጭ ሥራቸውን ማካሄድ እንዲችሉ መንግሥት ምቹ የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፎችን እንዲዘረጋ ጠይቀዋል።
2፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሰው ከኅብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ለመንግሥት ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ሰላማዊ ሕይወት የገቡት፣ 10 የታጣቂዎች አመራሮች እና 129 ታጣቂዎች እንደኾኑ ተገልጧል። የክልሉ መንግሥት በአገር ውስጥ እና ጎረቤት ሱዳን ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ታጣቂዎች ጋር በደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት፣ በመንግሥት ላይ ነፍጥ ያነሱ ታጣቂዎች በተከታታይ ወደ ሰላማዊ ሕይወት እየተመለሱ መኾኑን ካኹን ቀደም በተደጋጋሚ ገልጧል።
3፤ የደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ የኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጠይቋል። የአገሪቱ የኢምግሬሽን ባለሥልጣናት፣ ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ 470 ሺህ ስደተኞችን እንዳስጠለለች በመግለጽ፣ የስደተኛ ብዛት ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባት መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ባለሥልጣናቱ ከኢትዮጵያው ጋምቤላ ክልል የሄዱ ስደተኞች ጋምቤላ ባኹኑ ወቅት ችግር ስለሌለ እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጋቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ኹሉም ስደተኞች ከተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዳዲስ ክህሎቶችን እንዲለምዱም ባለሥልጣናቱ አሳስበዋል ተብሏል።
4፤ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት፣ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ጦር ሲወጣ አዲስ ኅብረቱ-መራሽ የኾነ ኅብረ ብሄራዊ ተልዕኮ እንዲሠማራ ትናንት ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ፣ በአገሪቱ የሚሠማራው አዲሱ ኃይል በተልዕኮው፣ በሚያካትታቸው አባላት ብዛት፣ በሰው ኃይል ስብጥሩ እና በቆይታ ጊዜው ርዝማኔ ጠንካራና አስተማማኝ ቁመና ያለው እንዲኾን መወሰኑን ገልጧል። የአዲሱ ተልዕኮ ዓላማ፣ በሱማሊያ አገር ግንባታ እና በጸረ-ሽብር ዘመቻዎች ለመንግሥት ድጋፍ ማድረግ ይኾናል ተብሏል። አዲሱ ተልዕኮ በአገሪቱ የሚሠማራው የኅብረቱ ጦር በመጭው ዓመት ታኅሳስ ጠቅልሎ ከወጣ በኋላ ሲኾን፣ ተልዕኮው እንዲሠማራ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚያጸድቀው ግን የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ቅዳሜ ሰኔ 15/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ "በትጥቅና በተሽከርካሪ የታገዘ" ያለውን የሰዎች እገታ ለመከላከል ከዛሬ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የከተማዋ ፖሊስ፣ 27 በሕገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ታርጋ የሌላቸው ባጃጆችን ሰሞኑን መያዙን እንደገለጠ የከተማዋ አስተዳደር ባሠራጨው መረጄ አስታውቋል። ከተማዋን ከእገታ ወንጀሎች ለማጽዳት ነዋሪዎች "በብሎክ አደረጃጀት" አካባቢያቸውን እንዲጠብቁም ፖሊስ ጥሪ አድርጓል ተብሏል። ኾኖም በባጃጆች የተጣለው ገደብ እስከመቼ እንደሚቆይ አስተዳደሩ አልገለጠም።
2፤ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የቤት አከራዮችና ተከራዮች ሕጋዊ የውል ስምምነት ውስጥ ሳይገቡ እስከ ሦስት ወራት ድረስ ከቆዩ፣ አከራዮች የኹለት ወር የቤት ኪራይ ራሳቸው እንዲሸፍኑ አስገድዳለኹ በማለት አስጠንቅቋል። ከመጋቢት 24 ጀምሮ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግና የኪራይ ውል ማቋረጥ ክልክል እንደኾነም ቢሮው ገልጧል። ኾኖም መንግሥት በሚያደርገው ጥናት መሠረት፣ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ ወር ላይ በኪራይ ተመን ላይ ጭማሪ እንደሚደረግ ቢሮው ጠቁሟል። ከሰኔ 1 ጀምሮ በ120 ወረዳዎች አከራዮችና ተከራዮች የውል ስምም ምዝገባ በወረዳዎች አማካኝነት እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለጠው ቢሮው፣ አከራዪች በቀሪዎቹ 15 ቀናት የውል ስምምነቶችን እንዲፈጽሙ አሳስቧል።
3፤ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ ደርሶብኛል ባሉት "ጫና እና ማስፈራሪያ" ምክንያት ከአገር መውጣታቸውን አስታውቀዋል። ዶ/ር ፍስሃ፣ ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ፣ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የፋኖ ታጣቂዎችን በመደገፍ፣ በሕገወጥ መሳሪያ ዝውውር እና በሽብር ወንጀሎች ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ጥርጣሬ፣ የባንክ ሒሳባቸው ከሦስት ሳምንት በፊት እንደታገደባቸው ገልጸዋል። ፍትህ ሚንስቴር ያገደብኝን የግሌንና የኩባንያውን የባንክ ሒሳቦች ለማስከፈት 200 ሚሊዮን ብር ተጠይቄያለኹ ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፣ ኾኖም ገንዘቡን "አልከፍልም" ብዬ ከአገር ለመውጣት ተገድጃለኹ ብለዋል። ዶ/ር ፍስሃ፣ በጉዳዩ ውስጥ የበርካታ ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበትና ፍትህ የሚጠብቁት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንደኾነ ገልጸዋል።
4፤ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ መኖሪያ ቤት ለመከራየት እንደከበዳቸው ያመለከቱ መምህራን በተማሪዎች ማደሪያ “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ መፍቀዱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የዩኒቨርስቲው መምህራን በጦርነቱ ወቅት የ17 ወር ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ከፍተኛ ውዝፍ የቤት ኪራይ እንደተጠራቀመባቸውና የኑሮ ውድነቱም ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ሲነገር ቆይቷል። በተማሪዎች ማደሪያ ውስጥ መኖሪያ እንዲሰጣቸው አመልክተው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር የፈቀደላቸው መምህራን፣ 55 ያህል እንደሚኾኑ ከመምህራኑ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም፣ ለመምህራኑ ማደሪያ የፈቀደላቸው በተማሪዎች ያልተያዙ በርካታ ክፍሎች በመኖራቸው እንደኾነ ማረጋገጡን ዜና ምንጩ አመልክቷል። ባኹኑ ወቅት መቐለ ከተማ ውስጥ አንድ ክፍል መኖሪያ ቤት ከ3 ሺህ 400 እስከ 4 ሺህ ብር ድረስ እንደሚከራይ ደላሎች ተናግረዋል ተብሏል።
5፤ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና ታንኮችን በመያዝ ትናንት ወደ ሱማሊያ ግዛት ዘልቀው እንደገቡ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ የተነሱት ወታደሮች ያቀኑት፣ ሒራን ወደሚባለው የሱማሊያ ግዛት እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የኢትዮጵያዊያኑ ወታደሮች ተልዕኮ ምን እንደኾነ ለጊዜው ግልጽ እንዳልኾነም የዜና ምንጮቹ ጠቅሰዋል። የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ባለፉት ኹለት ዓመታት ያገኛቸውን ወታደራዊ ድሎች፣ አልሸባብ ባለፉት ጥቂት ወራት ሙሉ በሙሉ እንደቀለበሳቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የአሜሪካ ዜና ምንጮች ሰሞኑን ዘግበው ነበር። የሱማሊያ ባለሥልጣናት ግን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ግምገማ የተሳሳተ በማለት እያጣጣሉት ይገኛሉ።
6፤ አፍሪካ ኅብረት፣ የሱዳን የፖለቲካና ሲቪል ኃይሎች በሐምሌ መጀመሪያ ላይ ለአምስት ቀናት በአዲስ አበባ "ኹሉን አካታች" ውይይት እንደሚያደርጉ አስታውቋል። ከአዲስ አበባው ውይይት ትንሽ ቀደም ብሎ፣ ካይሮ ላይ ሌላ ተመሳሳይ ውይይት እንደሚኖር ኅብረቱ ገልጧል። የኅብረቱ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት፣ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ የቀጥታ ንግግር እንዲያደርጉም ጥሪ አድርጓል። የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር የፊት ለፊት ንግግሩ "ባጠረ ጊዜ ውስጥ" እንዲካሄድ የሚያስተባብርና የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ የሚመሩት ኮሚቴ እንዲያቋቁሙም ተወስኗል። ኮሚቴው፣ ተፋላሚ ወገኖችን በጦር መሳሪያና ገንዘብ የሚደግፉ አገራትን ለይቶ እንዲያቀርብ ሃላፊነት ተሰጥቶታል። [ዋዜማ]

MEMO: Intent of New "Asset Recovery" Bill Vague, Fears It May Be Used Against Political Opponents
Security experts argue that the government's intention may be to cut off diaspora funding to armed groups in the country. Read details - https://tinyurl.com/ywcs5ubx

#NewsAlert
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ድርጅት ሠራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ላይ የስድስት ወራት ዕገዳ መጣሉን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። ዝርዝሩን ያንብቡት https://tinyurl.com/zcfp2s62

ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ምርጫ ቦርድ ትናንት በአራት ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ካካሄዳቸው ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫዎች መካከል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኹለት የምርጫ ጣቢያዎች ሊሰጥ የነበረውን ድምጽ ወደ ዛሬ አዛውሯል። ቦርዱ፣ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በሚገኙ ኹለት የምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ድምጽ ያልተሰጠው፣ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች ዘግይተው ከጣቢያዎቹ በመድረሳቸው እንደኾነ ትናንት ምሽት በሰጠው መግለጫ ገልጧል። የድጋሚና ቀሪ ምርጫዎች የተካሄዱት፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ 29 የምርጫ ክልሎች ነው። በተለይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተካሄደው ምርጫ፣ አዲስ የክልል ምክር ቤት ለማቋቋምና ክልሉ በፌደራል መንግሥት ተወካዮች እንዲኖሩት ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።
2፤ የፌዴራል መንግሥት ከዜሮ ነጥብ አምስት እስከ አንድ በመቶ የሚኾነውን ዓመታዊ በጀቱን ለአረንጓዴ አሻራና ለተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ እንዲመድብ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል። የልዩ ፈንዱ የሃብት ክፍፍል፣ ገንዘብ ሚንስቴር በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለፌዴራል መንግሥቱና ለክልሎች እንደሚደለደል ረቂቁ መደንገጉንና ገንዘቡ በየሦስት ወሩ ወደ ተጠቃሚ አካላት የሚተላለፈው በአፈጻጸማቸው መሠረት እንደሚኾን ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ለማቋቋምና ለማስተዳደር ያረቀቀውን ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።
3፤ ትናንት በትግራይ ክልል በብዙ ሺዎች የሚገመቱ የጦርነቱ ተፈናቃዮች በመቐለ፣ አክሱም፣ ዓድዋ፣ ሽረ እና ዓዲግራት ከተሞች ባደረጓቸው ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ መንግሥት ቃል በገባላቸው መሠረት እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወደ ቀያቸው እንዲመልሳቸው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ባግባቡ እንዲተገበርና የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲከበርም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ ተፈናቃዮች ከክረምቱ በፊት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፌደራሉና ከአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ንግግር ላይ መኾኑን ለሰልፈኞቹ ተናግረዋል።
4፤ የግብርና ምርቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክክ ነጻ የሚያደርገው መመሪያ ከነሃሴ 13 ጀምሮ ተግባራዊ መኾን እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል። ገንዘብ ሚንስቴር፣ በአገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችና በአገር ውስጥ የሚሰጡ አንዳንድ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መኾናቸውን እንዳረጋገጠ ዘገባው አመልክቷል። ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ከተባሉት መካከል፣ የእህልና ጥራጥሬ፣ የግብርና ምርቶችና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦችና መጠጦች ይገኙበታል ተብሏል። ከእህልና ጥራጣሬ ውስጥ፣ ጤፍ፣ ስንዴና ገብስ፤ ከግብርና ግብዓቶች ደሞ ማዳበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደማይከፈልባቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
5፤ ስዊዘርላንድ ወደ ኤርትራ አገናኝ ልዑክ ልትልክ እንደኾነና ልዑኩ ቋሚ ተቀማጭነቱ ናይሮቢ ላይ እንደሚኾን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ስዊዘርላንድ አገናኝ ልዑክ የምትልከው፣ የኤርትራ መንግሥት ኤርትራዊያን ስደተኞችን መልሶ እንዲቀበል ድርድር ለመጀመር መኾኑን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ባኹኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው 260 ኤርትራዊያን ስደተኞች ይገኛሉ ተብሏል። የስዊዘርላንድ ፓርላማ፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በሦስተኛ አገር በኩል ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የወሰነው በተያዘው ወር ነው። በኹለቱ አገሮች መካከል ስደተኞችን መልሶ ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል የተፈራረሙት ስምምነት የለም።
6፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ በሱማሊያ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ ይመክራል። በስብሰባው ላይ በሱማሊያ የተመድ ዋና ጸሃፊ ልዩ መልዕክተኛ ጄምስ ስዋን ሪፖርት ያቀርባሉ። ጄምስ ስዋን ለሱማሊያ የተመድ ዋና ጸሃፊ ልዩ መልዕክተኛ ኾነው የተሾሙት ባለፈው ወር ነበር። የአፍሪካ ኅብረት ጦር በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ሲወጣ ሌላ ኅብረቱ-መራሽ ልዑክ በአገሪቱ እንዲሠማራ ሱማሊያ ያቀረበችውን ጥያቄ፣ ኅብረቱ ባለፈው ሳምንት ከተቀበለ ወዲህ ጸጥታው ምክር ቤት በአገሪቱ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ ሲመክር ዛሬ የመጀመሪያው ይኾናል። አዲሱ አፍሪካ ኅብረት-መራሽ ተልዕኮ የሚሠማራው፣ ጸጥታው ምክር ቤት ሲያጸድቅ ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር አዲስ የብድር ስምምነት ላይ ለመድረስ ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ ሊያራዝሙ እንደሚችሉ መስማቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። አበዳሪዎች መንግሥት በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ ሰኔ 23 ከድርጅቱ ጋር የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰ ለኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜ የሰጡትን የእፎይታ ጊዜ ሊያጥፉት እንደሚችሉ አስጠንቅቀው ነበር። የዋና ዋና አበዳሪዎች ኮሚቴ፣ ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚያደርገው የአዲስ ብድር ድርድር በጥሩ ደረጃ ላይ እንደኾነ ተረድተናል ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል። አበዳሪዎች፣ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ መጨረሻ የሰጡትን የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ እስከ መቼ እንደሚያራዝሙት ግን የኮሚቴው ምንጮች መግለጽ አልፈለጉም ተብሏል።
2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከጥቅምት 2013 እስከ ኅዳር 2015 ዓ፣ም ባልተከፈለው የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ላይ በድጋሚ የ6 ወራት ዕገዳ መጣሉን ዋዜማ አስተዳደር ካሠራጨው ደብዳቤ ተረድታለች። አስተዳደሩ ዕገዳውን ያራዘመው፣ ጉዳዩ በጥናት የመጨረሻውን መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ነው። የውዝፍ ደሞዝ ጥያቄያቸውን ፍርድ ቤት እንዳይወስዱት ከታገዱት መካከል፣ የአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች እገዳው መራዘሙ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ለዋዜማ ተናግረዋል። በተለይ በኤፈርት ኩባንያ ስር ያሉ ድርጅቶች ሠራተኞች፣ በጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸውን ውዝፍ ደመወዝ ለማግኘት በፍርድ ቤት ክስ መስርተው እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል። ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዛቸው በቋሚነት እየተከፈላቸው ሲኾን፣ የድርጅቶችና ፋብሪካዎች ሠራተኞች ግን አብዛኞቹ ደመወዛቸው እስካኾን ተቋርጦ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
3፤ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን በድርቅ ለተጎዱና በግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሲያቀርቡት የነበረው አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ዘንድሮ ዓመት በ65 በመቶ መቀነሱን እንደተናገረ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የዞኑ አደጋ ሥራ አመራር ቢሮ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ ካልተሻሻለ መጭው የክረምት ወቅት የከፋ እንደሚኾንና የአደጋ ተጋላጩ ሕዝብ ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደኾነ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። በዞኑ ድርቁ ባስከተለው የመኖ እጦት የተነሳ በ11 ወራት ውስጥ ብቻ ከ14 ሺህ በላይ እንሰሳት እንደሞቱ መስማቱንም ዜና ምንጩ ጠቅሷል፡፡
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ባወጣው የመሬት ሊዝ ጨረታ ያሸነፉ 77 ተጫራቾች ሳይቀርቡ እንደቀሩ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። ይህንኑ ተከትሎ፣ አስተዳደሩ ኹለተኛ የወጡ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ውድድር የቀረቡትን ቦታዎች እንዲረከቡ ጥሪ ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ አስተዳደር ፒያሳን ጨምሮ በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች ባወጣው የሊዝ ጨረታ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለጨረታ ከቀረቡ 20 ቦታዎች መካከል ስድስቱ ተጫራቾች ቦታቸውን እንዳልተረከቡ ተገልጧል። 54 ተጫራቾች ያልቀረቡባቸው ቦታዎች የሚገኙት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ደረጃ ኹለት ቦታዎች እንደኾኑ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል፡፡ አሸናፊዎች ላልቀረቡባቸው ቦታዎች ኹለተኛ የወጡት ተጫራቾች ካለፈው ሳምንት ዓርብ ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ቀርበው እንዲረከቡ ጠይቋል ተብሏል።
5፤ የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ፣ በቦይንግ ኩባንያ ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከተከሰከሱት ማክስ 8 ቦይንግ አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ የማጭበርበር ወንጀል ክስ እንዲመሠረትበት ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። የአሜሪካ ፍትህ መስሪያ ቤት ባለሥልጣናት፣ ኩባንያው የወንጀል ተጠያቂነቱን ለማስቀረት ከሦስት ዓመት በፊት የገባውን ውል ባላማክበሩ የወንጀል ክስ ይመሠርቱ ወይም አይመሠርቱ እንደኾነ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ቀነ ገደብ አላቸው። የኢትዮጵያ አየር መንግድ ንብረት የኾነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መጋቢት 2011 ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስክሶ በርካታ መንገደኞች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። የአሜሪካ ዓቃቤ ሕግ ምክረ ሃሳቡን ያቀረበው፣ የኹለቱ አደጋዎች ተጎጂ ቤተሰቦች ፍትህ መስሪያ ቤቱ በኩባንያው ላይ ክስ እንዲመሠርትና የ25 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጥል አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።
6፤ አውሮፓ ኅብረት የሱዳንን ፖለቲካዊ ሽግግር አሰናክለዋል ባላቸው ስድስት ግለሰቦች ላይ ዛሬ የገንዘብ ዝውውር እና የጉዞ እገዳ ማዕቀቦችን ጥሏል። ኅብረቱ ማዕቀብ ከጣለባቸው መካከል፣ በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል የተባሉት፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ አብዱራህማን ጁማ ይገኙበታል። በሱዳን ጥር ሠራዊት በኩል ደሞ፣ የሱዳን አየር ኃይል አዛዥ እና የሱዳን መከላከያ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ሃላፊ ጀኔራል አል ጣሂር አል አሚን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። በተመሳሳይ፣ የቀድሞው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዓሊ አሕመድ ሞሃመድ ላይ የጉዞ እና ገንዘብ ዝውውር ማዕቀብ እንደጣለ ኅብረቱ አስታውቋል።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ2753 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ4208 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ0999 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ4819 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ1929 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ4168 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ሱማሊያ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ውጭ የኾኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ሉዓላዊ ግዛቴን ጥሰው ገብተዋል በማለት በተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከሳለች። በተመድ የአገሪቱ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር አቡከር ኦስማን ትናንት በሱማሊያ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ በመከረው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የመንግሥታቸውን አቋም ባሰሙበት ንግግር፣ የኢትዮጵያ ጦር በተለያዩ አቅጣጫዎች የሱማሊያን ድንበር ጥሶ በመግባት ከጸጥታ ኃይሎቻችን ጋር ተኩስ ልውውጥ አድርጓል ብለዋል። አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ራስ ገዝ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ባስቸኳይ እንድትሰርዝም ጠይቀዋል።
2፤ አሜሪካ፣ በኢትዮጵያና ሱማሊያ መካከል በባሕር በር ዙሪያ የተፈጠረው "ፖለቲካዊ ውጥረት" እና "ውጥረቱ በጋራ የጸጥታ ጥቅሞች" ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ "በእጅጉ እንዳሳሰባት" አስታውቃለች። ትናንት በሱማሊያ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ በመከረው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ልዑክ አምባሳደር ሮበርት ውድ፣ አሜሪካ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር አፍሪካ ኅብረትና ሌሎች አጋሮች የያዙትን አቋም ትደግፋለች ብለዋል። አምባሳደሩ፣ በኹለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ማርገቢያው መንገድ ንግግር እንደኾነም አውስተዋል። ቀጠናዊ ውጥረቶች፣ ከአልሸባብን ጋር በሚደረገው ውጊያ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ መውጣት በኋላ ተተኪ ተልዕኮ በማሠማራቱ ሂደትና በአገር ግንባታ ጥረቶች ላይ እንቅፋት መኾን እንደሌለባቸውም አምባሳደሩ አውስተዋል።
3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹሁኔታ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች በሚያቀርቡለት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ይወያያል። ምክር ቤቱ፣ የቋሚ ኮሚቴዎቹን ሪፖርት መርምሮ ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ምክር ቤቱ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበለት የውጭ ባንኮች በአገሪቱ እንዲሠማሩ በሚፈቅደው የባንክ ሥስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ጭምር ተወያይቶ ለዝርዝሩ እይታ ለቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ገልጧል።
4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለሰባተኛ ጊዜ የስካይትራክስ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመርጧል። አየር መንገዱ በተጨማሪም፣ የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ አሸናፊነትን ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ተሸላሚነትን ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመትና በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ የምግብ አገልግሎት ሰጪ የሚል ድል እንደተቀዳጀ ትናንት ማምሻውን አስታውቋል።
5፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከተመላሾቹ መካከል፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 20 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል። ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ከ49 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተመልሰዋል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ መንግሥት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ግንባታ ከ2017 ረቂቅ በጀት 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድቤያለኹ ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። መንግሥት አዳዲስ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች መገንባት ያስፈለገው፣ ባኹኑ ወቅት የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ለቢሮ ኪራይ የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ በመኾኑ፣ ኪራዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄዱና መስሪያ ቤቶች በተመቻቸ ኹኔታ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ታስቦ እንደኾነ ገንዘብ ሚንስቴር ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን ግንባታ የሚመራው፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ነው። መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለስንት የፌደራል መስሪያ ቤቶች ቢሮ መገንባት እንዳቀደ እና ባኹኑ ወቅት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ኪራይ ምን ያህል ገንዘብ እያወጣ እንደኾነ እንዳልገለጠ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። ቋሚ ኮሚቴው፣ አዲስ ቢሮዎችን ወይም ሕንጻዎችን የመገንባት አዋጭነቱ በጥናት የተደገፈ ነው ወይ? በማለት ላቀረበው ጥያቄ፣ የገንዘብ ሚንስቴር ሃላፊዎች ጉዳዩ የአዋጭነት ጥናት አያስፈልገውም በማለት መልሰዋል ተብሏል።
2፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹኔታ ለመወሰን የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ዛሬ በአራት ተቃውሞ እና በስድስት ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ፣ ከዚህ በፊት በልማት ምክንያት ተነስተው ካሳ ያልተከፈላቸውን ሰዎች እንደማያካትት ተገልጧል። አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፣ ለልማት ተነሺዎች ካሳ የመክፈሉን ኃላፊነት ለክልል መንግሥታት የሰጠ ሲኾን፣ የካሳ አቤቱታዎችም በክልል ፍርድ ቤቶች እንዲታዩ ደንግጓል። የምክር ቤቱ አባላት ግን፣ የክልል መንግሥታት ለሠራተኞቻቸው ደሞዝ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ በመጥቀስ፣ የካሳ ክፍያ በመክፈል ብቃታቸው ላይ ጥያቄ አንስተው ነበር።
3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ፣ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን መረምሮ ለዝርዝር እይታ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ የባንክ ሥራ አዋጅ ተሻሽሎ የቀረበው፣ የአገሪቱን የባንክ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ በቂ የፋይናንስና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል፣ የሥራ ዕድል እንዲስፋፋ ለማድረግ እንደኾነ ተገልጧል። ረቂቅ አዋጁ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች በአገሪቱ በባንክ ዘርፍ እንዲሠማሩ ፍቃድ የሚሰጥበትን፣ የውጭ ዜጎች በባንክ ሥራ የሚሳተፉበትን ኹኔታ፣ ስለ ባንክ አክሲዮኖች፣ ስለ ባንክ ሠራተኞችና ዳይሬክተሮች እንዲኹም ስለ ፋይናንስ ግዴታዎችና ገደቦች ድንጋጌዎችን ይዟል ተብሏል። የምክር ቤቱ አባላት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወን የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አሠራር እንዲዘረጋለት ቋሚ ኮሚቴው ባግባቡ ጉዳዩን እንዲያጤን ጠይቀዋል።
4፤ ዛሬ በመቀሌ ከተማ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ሰላማዊ ሰልፉን ያስተባበሩት፣ የሴቶች መብት ተሟጋቾችና የሴቶች ማኅበራት ናቸው። ሰልፈኞቹ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች እንዲቆሙና መንግሥት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። በቅርቡ አድዋ ከተማ ውስጥ ማኅሌት ተክላይ የተባለች ታዳጊ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ለሦስት ወራት ታፍና ከቆየች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ይታወሳል። አጋቾች ታዳጊዋን ለመልቀቅ ሦስት ሚሊዮን ብር ጠይቀው እንደነበር በወቅቱ ተገልጦ ነበር። በክልሉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተበራከቱ መሄዳቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
5፤ እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ዲዔታ ታዬ ደንደአ ጠበቆቻቸው ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደኾነ ዛሬ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተናግረዋል። ታዬ ፍርድ ቤቱ፣ በጠበቆቻቸው ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ማስፈራሪያ እንዲያስቆምላቸው ጠይቀዋል። ታዬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት፣ ከአምስቱ ጠበቆቻቸው አንዳቸውም እንዳልተገኙ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ችሎቱ በሥራ መደራረብ የተነሳ የተከሳሹን ጉዳይ ሳያይ እንደቀረ ገልጦ፣ ለሐምሌ 17 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ተብሏል።
6፤ የኬንያ መንግሥት ያወጣውን የታክስ ሕግ የተቃውሞ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ የአገሪቱን ፓርላማ ሕንጻ ጥሰው ገቡ። ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፓርላማውን ጥሰው ለመግባት ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት፣ ከ10 በላይ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት እንደተገደሉና እንደቆሰሉ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፓርላማውን ጥሰው የገቡት፣ የፓርላማ አባላት የታክስ ረቂቅ አዋጁን ባጸደቁ በደቂቃዎች ውስጥ ነው። የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ነው። ሳፋሪኮም ኩባንያ፣ ዛሬ በአገሪቱ ከፍተኛ የኢንተርኔት መስተጓጎል እንደተከሰተ አስታውቋል።
7፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ2915 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ4373 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ4508 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ6637 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ4509 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ6799 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ሰኔ 19/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በባሕርዳር ከተማ ለኹለት ቀናት የተካሄደው የሰላም መድረክ፣ በሰላም፣ ጸጥታ፣ ፖለቲካ፣ መልካም አስተዳደር፣ በማንነትና ራስን በራስ በማስተዳደር ጥያቄ እና በሕገመንግስት ማሻሻያ ዙሪያ ያነሳቸው ጥያቄዎች ለፌደራሉና ለክልሉ መንግሥታት እንዲቀርቡ በመወሰን ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።፡ መድረኩ፣ ታጣቂ ኃይሎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለውይይትና ድርድር እንዲያቀርቡና መንግሥት ወደ ሰላማዊ ንግግር መመለስ የሚፈልጉ ታጣቂዎችን በይቅርታ እንዲቀበላቸው ጠይቋል። የሕወሃት ኃይሎች በቅርቡ በኋይል ከተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች "በፍጥነት እንዲወጡ" እና በኹለቱ ክልሎች መካከል የሚነሱ ጥያቄዎች "በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ" መፍትሄ እንዲያገኙም መድረኩ ጥሪ አድርጓል።
2፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ'ለት በእስረኞች መካከል ተፈጠረ በተባለ ግጭት ቢያንስ አምስት ታራሚዎች እንደተጎዱ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ከታራሚዎች ቤተሰቦች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል። የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግን፣ ክስተቱ መፈጠሩን አረጋግጦ ጉዳት የደረሰው ግን ሕንድ ታራሚ ላይ ብቻ ነው ማለቱን ዘገባው አመልክቷል። በዕለቱ ግጭቱን ተከትሎ፣ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ማረሚያ ቤቱን ዙሪያውን ከበው እንደተመለከቱ የዓይን እማኞች ተናግረዋል ተብሏል።
3፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የጣሊያን ኩባንያዎች በታዳሽ ኃይል፣ ውሃ ልማት በማኑፋክቸሪንግ እንዲኹም ወደብ፣ የባቡር ሐዲድና መንገድን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ እንዲሠማሩ እንደጠየቁ የጣሊያን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢሳያስ ይህን ያሉት፣ ትናንት ከጣሊያን ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የኩባንያዎች ሃላፊዎችን ጋር አሥመራ ውስጥ በተወያዩበት ወቅት ነው። ኤርትራና ጣሊያን፣ በማዕድን፣ ግብርና፣ እንስሳት ሃብትና ቱሪዝም ዘርፍ ሊተባበሩ እንደሚችሉም ተገልጧል። የጣሊያን ልዑካን ቡድን በርካታ የኤርትራ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል ተብሏል። የኹለቱ አገራት ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ውዲህ እየተጠናከረ ሂዷል።
4፤ በኬንያ አዲሱን የታክስ አዋጅ በመቃወም ትናንት ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞችና ፖሊሶች መካከል በተካሄዱ ግጭቶች 13 ሰዎች እንደተገደሉ የውጭ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል። 12ቱ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የተገደሉት፣ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፣ "ጥቂት ሰርጎ ገብ ወንጀለኞች" ሲሉ የጠሯቸው ተቃዋሚ ሰልፈኞች ያካሄዱትን አመጽ "የአገር ክህደት" በማለት ጠርተውታል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ሰላም ለማስከበር በከተሞች የተሠማራ ሲኾን፣ ፕሬዝዳንቱም የአገሪቱን ብሄራዊ ደኅንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ ርምጃዎችን ኹሉ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ፓርላማው ትናንት ያጸደቀው የታክስ አዋጅ የአገሪቱ ሕግ የሚኾነው፣ ፕሬዝዳንቱ ከፈረሙበት ብቻ ነው። [ዋዜማ]

ለቸኮለ! ረቡዕ ሰኔ 19/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን የምግብ በጀት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን እንደሚያሻሽል አስታውቋል። የተማሪዎችን የምግብ በጀት ለማሻሻል የገንዘብና የትምህርት ሚንስቴር እንዲኹም ማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት በጋራ ጥናት እያደረጉ እንደኾነ የገንዘብ ሚንስቴር ሃላፊዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ተናግረዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ በተለይ በቀጣዩ ዓመት እስካኹን ባለው የበጀት ድልድል ለተማሪዎች ምግብ ማቅረብ እንደማይችሉ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል። ጥናቱ ተጠናቆ ሚንስትሮች ምክር ቤት ካጸደቀው፣ መንግሥት ከመጠባበቂያ በጀቱ ለተማሪዎች ምግብ ተጨማሪ በጀት እንደሚመድብ ተገልጧል። ባኹኑ ወቅት የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት 22 ብር ብቻ ነው።
2፤ ገንዘብ ሚንስቴር፣ በሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ ለማሻሻል ጥናት መጀመሩን ከሚንስቴሩ ምንጮች እንደሰማ ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል። አኹን ባለው አሠራር፣ መንግሥት ከ600 ብር በላይ በኾነ የሠራተኛ ደመወዝ ላይ የ10 በመቶ የገቢ ግብር የሚጥል ሲኾን፣ ከ10 ሺሕ ብር በላይ ገቢ በሚያገኙ ደመወዝተኞች ላይ ደሞ 35 በመቶ የገቢ ግብር ይጣልባቸዋል፡፡ ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረገ ነው የተባለው ጥናቱ፣ የገቢ ግብር የሚጣልበትን ዝቅተኛውን የደመወዝ መጠን እና 35 በመቶ ግብር የሚጣልበትን ከፍተኛውን የደመወዝ መጠን ከፍ የማድረግ ዓላማ እንዳለው ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጽያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ መንግሥት የደመወዝ ገቢ ግብር ቅናሽ እንዲያደርግና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲያቋቁም ሲወተውት መቆየቱ ይታወቃል።
3፤ ፍትህ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ ምንጬ ያልታወቀ ሀብት ማስመለስ፣ ማገድና መያዝን በመንግሥት ሠራተኞች ብቻ ተገድቦ የቆየው የሕግ ማዕቀፍ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትት ኾኖ እንደተዘጋጀ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ሚንስትሩ፣ ረቂቅ አዋጁ 10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ የንብረት ጉዳዮችን እንዲመለከት መደረጉ በሕገ-መንግሥቱ ከተቀመጠው ድንጋጌ ጋር እንደማይቃረን አብራርተዋል። በረቂቅ አዋጁ ላይ አዋጁ ወደኋላ ሂዶ ተፈጻሚነት እንዲኖረው የተደረገው፣ ለፍትሐ ብሔር ኃላፊነት እንጂ ለወንጀል ኃላፊነት አይደለም በማለት ጌዲዮን ተናግረዋል። ጌዲዮን፣ የረቂቅ አዋጁ ዋና ትኩረት የሕዝብንና የመንግሥትን ኃብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ እንደኾነ ጠቅሰዋል። ረቂቅ አዋጁ ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ አይዘነጋም።
4፤ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፀጋይ ብርሃነ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገብረ አምላክ የዕብዮ ባለፈው ሰኞ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የመልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት፣ በፍርድ ቤቶችና በፍትህ ሥርዓቱ ላይ የጀመሩትን የለውጥ ጅምር ለማሳካት የሚያስችል ኹኔታ በክልሉ ውስጥ እንደሌለ በመጥቀስ እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ኹለቱ አመራሮች መልቀቂያ ለማስገባት ምክንያት የኾናቸውን ምቹ ያልኾነ ኹኔታ ለጊዜው ከመግለጽ እንደተቆጠቡ ዘገባው ጠቅሷል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በአመራር ላይ የቆዩት፣ ለዘጠኝ ወራት ብቻ ነው።
5፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበትን አዲሱን የታክስ አዋጅ እንደማይፈርሙት ዛሬ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ የሰልፈኞችን ተቃውሞ በመስማት ረቂቅ አዋጁን ሙሉ በሙሉ ለማንሳት ወስኛለኹ ብለዋል። ትናንት በዋና ከተማዋ ናይሮቢና ሌሎች በርካታ ከተሞች በአዋጁ ላይ በተካሄዱ ተቃውሞዎች፣ በርካታ ተቃዋሚ ሰልፈኛ ወጣቶች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ተነግሯል። በናይሮቢው ተቃውሞ፣ በርካታ ተቃዋሚ ወጣቶች ፓርላማውን በኃይል ጥሰው እስከመግባት ደርሰው ነበር። ሩቶ አዋጁን ለማንሳት የወሰኑት፣ ወጣት ሰልፈኞች ነገ ጭምር ለተቃውሞ እንደሚወጡ በመግለጽ ላይ ሳሉ ነው።
6፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ3013 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ4473 ሳንቲም ኾኖ እንደዋለ በድረ ገጹ አስታውቋል። ባንኩ፣ የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 69 ብር ከ4377 ሳንቲም እና መሸጫው 70 ብር ከ8265 ሳንቲም እንደኾነም አመልክቷል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ61 ከ4213 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ62 ብር ከ6497 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። [ዋዜማ]

ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት፣ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ራስ ገዝ ጋር በደረሰችበት የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያ ሐሰተኛ መረጃዎች እየተሠራጩ እንደኾነ ትናንት ምሽት አስታውቋል። ሕዝቡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በበይነ መረብ ከሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቅ ያሳሰበው ጽሕፈት ቤቱ፣ በአገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኦፊሴላዊ መልዕክቶችን የሚያስተላልፈው በይፋዊ መገናኛ አማራጮች ብቻ እንደኾነ ገልጧል።
2፤ የዓለም የሥራ ድርጅት ባለሙያዎች ባደረጉት ጥናት፣ በኢትዮጵያ በመስሪያ ቤቶች የሠራተኛ አለመርጋት ዋናው ምክንያቱ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመኖር መኾኑን ማረጋገጣቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። ባኹኑ ወቅት በአገሪቱ አማካዩ ደመወዝ 3 ሺሕ ብር እንደኾነ የገለጡት ባለሙያዎቹ፣ መንግሥት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን መክረዋል። ዝቅተኛ ደመወዝ ለሠራተኞች እርካታ ማጣት ቀዳሚ ምክንያት እንደኾነና በተለይ በውጭ ባለሃብቶች ከተያዙ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች 48 በመቶ የሚኾኑ ሠራተኞች በዝቅተኛ ደመወዝ ሳቢያ እንደለቀቁ ጥናቱ ጠቅሷል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቢወሰንም ተቋማት ውጤታማ የሚኾኑት ግን፣ ሠራተኞች የመደራደር መብት ሲጎናጸፉ እንደኾነ ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል።
3፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ትናንት የመጀመሪያውን የሙዓለ ንዋይ ገበያ የኢንቨስትመንት አማካሪነት ፍቃድ ላንድ ግለሰብ መስጠቱን አስታውቋል። ኩባንያው የሙዓለ ንዋይ ገበያ የኢንቨስትመንት አማካሪነት ፍቃድ የሰጠው፣ በዘርፉ የ25 ዓመታት ልምድ ላካበቱት ኢትዮጵያዊው ሐብታሙ እሸቱ ገብሬ እንደኾነ ገልጧል። የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው በይፋ ወደ ግብይት ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ገደማ ነው።
4፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ከሳውዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 173 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መልሷል። ከተመላሾቹ መካከል፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 17 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኮሚቴው ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ከ50 ሺሕ በላይ ዜጎችን መመለስ ችሏል ተብሏል።
5፤ ግዙፉ ስፔስ ኤክስ ኩባንያ፣ ለኬንያዊያን የሚያቀርበውን የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ ሊቀንስ እንደኾነ አስታውቋል። በርካታ ኬንያዊያን፣ የስታርሊንክ ኢንተርኔት አገልግሎት ማስገቢያ ዋጋ ከፍተኛ እንደኾነ በመግለጽ ቅሬታ አቅርበው ነበር። በምሥራቅ አፍሪካ፣ የኢንተርኔት ኩባንያዎች አገልግሎት ባሕር ላይ በሚያጋጥም የኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመሮች ብልሽት ሳቢያ መቆራረጥ ያጋጥማል። ስታርሊንክ ለ50 ጌጋ ባይት የሳተላይት የኢንተርኔት ዳታ በወር የሚያስከፍለው 10 ዶላር ሌሎች ኩባንያዎች ከሚያስከፍሉት በከፍተኛ ደረጃ ያነሰ ሲኾን፣ መስመሩን ላንድ ጊዜ ለማስገባት ግን 343 ዶላር ይጠይቃል። [ዋዜማ]