Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
208K subscribers
28.3K photos
863 videos
47 files
11.8K links
እንኳን ደህና መጡ

ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed

ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ🙏
Download Telegram
የሽብር ጥቃትን ለመከላከል በተወሰደ እርምጃ ስምንት የሸኔ አባላት ተደመሰሱ፡-ፖሊስ
********************
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የሽብር ጥቃት ለመከላከል ለሁለት ቀን በተደረገ አሰሳ ስምንት የሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ዋና ሳጅን ጉተማ ሳፋየ ለኢዜአ እንደገለጹት እርምጃው የተወሰደው በሁለት ወረዳዎች ጥቃት ለመፈጸም በእንቅሰቃሴ ላይ በነበሩ የሸኔ የጥፋት ቡድን አባላት ላይ ነው፡፡
በዞኑ ጎሮ ዶላ ወረዳ ከትላንት በስቲያ በየገጠሩ በተደረገ አሰሳ እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ አምስት የጥፋት ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ በዞኑ ሊበን ወረዳ ትላንት ጧት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የሽብር ተግባር ለመፈጸም የተሰማሩ ሶስት የጥፋት ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንም አመልክተዋል፡፡
እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ አንድ የጥፋት ቡድኑ አባል ከአራት ክላንሽኮቭ ጠብመንጃ ጋር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም በአዶላ ከተማ በህዝብ ጥቆማ በህገወጥ መንገድ ክላንሽኮቭ ጠብመንጃ የያዘ አንድ ተጠርጣሪም በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጥፋት ቡድኑ አባላት በየአካባቢው ሊደርስ የሚችለውን የሽብር ጥቃት ለመከላከል በዞኑ የፀጥታ አካላት እየተደረገ ያለው የአሰሳ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ተጠናቀቀ
*********************
650 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኃይማኖት አባቶችና ከሲቪክ ማኅበራት ጋር ግድቡን በተመለከተ ዛሬ ውይይት አድርጓል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የኃይል መሥመር ዝርጋታው ከግድቡ ከተገነባበት ጉባ አንስቶ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት እስከሚገኝበት ሆለታ ድረስ ተዘርግቷል ተብሏል፡፡
የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል ዶክተር በለጠ ብርሃኑ፣ አሁን ላይ ከግንባታና ከኮንክሪት ሙሌት ጋር ተያይዞ የሚሰራው የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ሥራ 91.8 በመቶ መድረሱን ነው የጠቆሙት፡፡
የግድቡ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
በተጓዳኝም የግድቡ ሁለት ተርባይኖች የቅድመ ኃይል ምርት በመጪው ክረምት መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምርና ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር በለጠ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በጉጂ ዞን ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ ከ900 በላይ ሚሊሻዎች ተመረቁ።

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን 982 የሚሆኑ ሚሊሻዎች የተለያዩ ወታደራዊ ሥልጠናወችን ወስደው መመረቃቸውን የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ሚሊሻዎቹ ህግ ከማስከበር እንዲሁም በህብረተሰቡ ተሳትፎ የአከባቢውን ጸጥታ በማስጠበቅ ረገድ እና መጪውን ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ ሲል ቢሮው ገልጿል።
አማራ ልማት ማኅበር ለተፈናቃዮች ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በሰሜን ሽዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ ቁሳቁስ አስረክቧል፡፡ የተሰበሰበውን የቁሳቁስ ድጋፍ በሰሜን ሽዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው ያስረከቡት የአልማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ እንዳሉት የተሰበሰበው ቁሳቁስ ለ1 ሺህ 500 ቤቶች ግንባታ ይውላል ብለዋል፡፡ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረቡት የአልማ ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፋንታ ሌሎች አጋር አካላትም ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ቦጋለ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡በላይነህ ክንዴ ግሩፕ 15 ሺህ ሊትር ዘይት እና ሴንቸሪ ካምፓኒ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ተብሏል፡፡

[AMC]
የመገናኛ ብዙሃን አንድነትና አብሮነትን የሚሰብኩ፣ ለእዉነት የቆሙ መሆን ይገባቸዋል - ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
------------------------------------
ግንቦት 12/2013 (ዋልታ) – ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን የህዝቡን ፍላጎት ለይተው የሚሰሩ አንድነትና አብሮነትን የሚሰብኩ፣ ለእዉነት የቆሙ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከ”ፍሬድሪክ ኤርበርት ሰቲፍተንግ” ጋር በትብብር ያዘጋጀው መገናኛ ብዙሃን ለሰላም፣ ለአብሮነትና ለሃገር ግንባታ በሚል ርዕሰ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትርና የባለስልጣኑ የቦርድ ሰብሳቢ ሙፈሪያት ካሚል ሃላፊነት የሚሰማቸዉ ለሀገር ግንባታና ለሰላም የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃን በተጠናከሩ ቁጥር በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸዉ ሚና የማይተካ ይሆናል ሲሉ አንሰተዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ሀገር የማፍረስም የማዳንም ሃይል አላቸዉ ያሉት ሚኒስትሯ በተለይም ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የዲሞከራሲ ሽግግር ወቅት ሚናቸዉ የጎላ በመሆኑ ሃላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ኢድሪስ በበኩላቸው መገናኛ ብዙሃን በህዝብ የተጣለባቸውን ሃላፊነት የሚወጡ ለሰላም፣ ለአብሮነት፣ ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲ የሚሰሩ የህዝቡን ድምፅ ያለ አድሎ የሚያሰሙ መሆን አለባቸው ብለዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ለሰላምና አብሮነት ያላቸውን ሚና የሚያትት መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
በምክክር መድረኩ የመገናኛ ቡዙሃን ሃላፊዎች፣ ባለሞያዎች፣ ሙሁራንና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
(በህይወት አክሊሉ)
አባይ ባንክ በ10 ዓመት ውስጥ ተቀማጭ ገንዘቤ 23.5 ቢሊየን ብር ደርሷል አለ።

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 4.2 ቢሊየን ብር መድረሱን ተሰምቷል።የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 29 ቢሊየን ብር ደርሷል።አባይ ባንክ ከ 10 የአየር መንገዶች ጋር የበረራ ትኬት መቁረጥ የሚቻልበትንም መላ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግሯል።ዲጂታል ባንኪንግ ላይ በብርቱ እየሰራሁ ነው ብሏል።ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የበረራ ትኬት መቁረጥ የሚቻልበትን የዲጂታል የክፍያ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ተሰምቷል።የክፍያ አገልግሎቱ ጉዞ ጎ የተሰኘ የድጅታል ክፍያ መተግበርያ ነው።አገልግሎቱ 3 አማራጮችን ይዞ ወደ ስራ ገብቷል።

Via Sheger FM
ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ምርጫውን አሳልፎ ከሁለት አመት በኋላ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠየቁ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የሚያካሂደውን ምርመራ አቋርጦ ምርጫው ካለፈ በኋላ ለ2015 እና 2016 ቀጠሮ እንዲሰጣቸው አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ጠየቁ። ተከሳሾቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ዛሬ ሐሙስ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነበራቸው መደበኛ የክስ ሂደት የችሎት ውሎ ላይ ነው።

በመጀመሪያ ተቃውሟቸውን ያሰሙት አቶ በቀለ ገርባ ቀጠሮ ምንም ፋይዳ ስለሌለው ፍርድ ቤቱ ግንቦት 18 ቀጠሮ ከሚሰጥ ይልቅ ከሁለት ዓመት በኋላ ለ2015 ወይም 2016 ቢሰጥ ይሻላል ብለዋል።“ሰው በአደባባይ በሚረሸንበት አገር ፍርድ ቤት መቅረብ እድለኝነት ነው” ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፤ ይህም ሆኖ ግን ምንም ፍትህ ለማይገኝለት ነገር ፍርድ ቤት መመላለስ እንደሌለባቸው ጠቅሰዋል።

ይሄንኑ ተቃውሞ ደግፈው የተናገሩት አቶ ጃዋር መሐመድ “እናንተ ነፃ ናችሁ ብትሉንም እነሱ ግን አይለቁንም” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።በተጨማሪም መንግስት የሚፈልገው የእኛን መታሰር ስለሆነ የፍርድ ቤቱንም የእኛንም ጊዜ ከምንገድል ከሁለት አመት በኋላ ቀጠሮ ቢሰጥልን ይሻላል ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
#ሰበር_መረጃ

6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ለሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት በሆቴል ዲሊኦፖል እየተሰጠ በሚገኘው መግለጫ ላይ የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል ።

የመራጮች ምዝገባ ላይ ቅሬታ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ግን ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድ ገልፀዋል ።


<<…በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሃይል ላይ በአሜሪካ መንግስት እየቀረበ ያለው ውንጀላ አግባብነት የሌለው ነው።…>>
የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ኢፍትሐዊ እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የሚጥስ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጉባኤው በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ደብዳቤ ጽፏል፡፡

በደብዳቤውም በትግራይ ክልል እየተደረገ ላለው ሰብአዊ ድጋፍ እና እየታየ ላለው የሰብአዊ መብት መቆርቆር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

መማክርቱ በደብዳቤው የህወሃት ቡድን ለበርካታ አመታት ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጅ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ያወጡት መግለጫ የተሳሳተና አግባብነት የሌለው መሆኑን አውስቷል፡፡

የሚኒስትሩ መግለጫም የተመድ መርህ የሆኑትን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት እና ሉዓላዊነት ያለመጣስን የሚቃረን እና ኢ - ፍትሐዊ ነው ብሏል።

ሚኒስትሩ ከሚመለከተው አካል የምርመራ ውጤት ይልቅ ለህወሃት ቡድን የሃሰት ውንጀላ እውቅና መስጠታቸው አሳዛኝ መሆኑንም ነው መማክርቱ በመግለጫው ያነሳው፡፡

ከዚህ ባለፈም መግለጫው በህወሃት የሃሰት መረጃ የተመረኮዘ እና መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚክድ መሆኑንም መማክርቱ አንስቷል፡፡

በተጨማሪም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሃይል ላይ በአሜሪካ መንግስት እየቀረበ ያለው ውንጀላ አግባብነት የሌለውና መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ አይደለምም ነው ያለው።

ከዚህ ባለፈም የአሜሪካ መንግስት ከቦታና መሬት ጋር በተያያዘ ያወጣው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

የአሜሪካ መግለጫ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና መቋጫ አልባ ግጭት እና ሰብአዊ ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ አቋሙን በድጋሚ እንዲፈትሽ ጥሪ አቅርቧል።(via:FBC)
ኦነግ በዘንድሮው ምርጫ መሳተፍ አይችልም ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

በእነአራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ በምርጫው መሳተፍ አይችልም ተብሏል ።

ኦነግ ባደረገው የፍርድ ቤት ክርክር ምርጫ ቦርድ ያሳለፈው ውሳኔ ቢሻርም ቦርዱ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቋል
የ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን የፊታችን ሰኔ 14 ሰኞ እለት እንደሆን ቦርዱ ወስኗል።
ኦነግ በውስጥ ችግሩ ምክንያት ጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሂድ በመቆየቱ “የምርጫና የዕጩ ምዝገባ ጊዜ አልፎብናል” በማለት ቦርዱ ችግሩን ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለትና ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲያጸድቅለት ቦርዱን በደብዳቤ ጠይቆ ነበር።
ቦርዱም የቀረቡትን ሰነዶች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት መርምሮ ባሳለፈው ውሳኔ፤ አዲስ የተመረጡትን የኦነግ አመራሮች እና የተካሔደውን ጉባኤ እንደማይቀበል አስታውቋል፡፡
በዚህ መሰረት ኦነግ የቦርዱን ውሳኔ ተቃውሞ ወደ ፈረድ ቤት ወስዶ ሲከራከር ቆይቶ ፍርድ ቤትም የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል።
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረገውን የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እና በስብሰባው ያሳለፈውን ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲቀበለው ወስኖ ነበር።
የቦርዱ ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ የኦነግን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዴት ልታስኬዱት ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኦነግ በምርጫው መወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ስራዎች የጊዜ ሰለዳዎች ስላለፉት በዘንድሮው ምርጫ ላይ መወዳደር እንደማይችል ወይዘሪት ሶልያና ተናግረዋል።
ኦነግ በፍርድ ቤት ተወስኖልኛል እና በምርጫው ልሳተፍ ብሎ ቦርዱን እንደጠየቀ ወ/ሪት ሶልያና ተናግረዋል።
ይሁንና ፓርቲው ለምርጫ ፉክክር የሚያበቁ ስራዎች ስላለፉት ፓርቲው በምርጫው ለመሳተፍ የሚያበቃ ጊዜ ስለሌለው እንዳይሳተፍ ቦርዱ መወሰኑን ተናግረዋል።
ለአብነትም ፓርቲው የመራጮች ምዝገባ፤ የእጩ ተፎካካሪዎች ምዝገባ እና ሌሎች በምርጫው እንዲሳተፍ የሚያበቁ ስራዎችን አልፈውታል ብለዋል።
የኦነግ የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ቦርድ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ወ/ሪት ሶልያና ተናግረዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ የወሰነ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ቅሬታ በቀረበባቸው ምርጫ ጣቢያዎች እና በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቃይ ዜጎች ያሉባቸው አካባቢዎች ምርጫው ከሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ደግሞ ምርጫ እንደሚካሄድባቸው አስቀድመው በቦርዱ በተለዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች ላይ ምርጫው ከተካሄደ በኋላ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆንም ቦርዱ ገልጿል።
ከሰኔ 14 በኋላ ምርጫ የሚካሄድባቸው ቦታዎች መካከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው መተከል እና ሌሎች ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ቦታዎች አይካሄድም።
የመራጮች ድምጽ መስጫ ወረቀት በUNDP የገንዘብ እርዳታ በውጭ አገራት ታትሞ እስከ ግንቦት መጨረሻ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባም ተገልጿል።
(አል-ዐይን)
በኢትዮጵያ እየደረሠ ያለውን ጫና በተመለከተ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በሚል የተቃውሞ እንቀስቃሴ እየተደረገ ነው!

ብሄራዊ ክብር ለህብር በተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና በተመለከተ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በሚል መሪ ሃሳብ የተቃውሞ እንቀስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 10 ሰዓት ሁሉም ኢትዮጵያዊ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በማለት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተቃውሞውን እንዲገልፅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የብሄራዊ ክብር ለህብር አስተባባሪ አብይ ታደለ ሁሉም ለሀገሩ ያገባኛል የሚል እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ገልጸው፣ ከሲቪል ማህበራት፣ ከኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ፍሬያማ የሆነ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲዎች ዛሬ ባለመስራታቸው አልተሳካም ብለዋል።
ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎችችን ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 130 ሺ በላይ አስፈጻሚዎችን መልምሎ የመራጮች ምዝገባን እንዳጠናቀቀ አስታውሷል።

በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚካሄደው ድምጽ መስጫ ቀን ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መመልመል እንደሚፈልግ ዛሬ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ሀገራቸውን ለማገልገል የሚፈልጉ
- ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርተው የማያውቁ
- ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፈው የማውቁ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላቸው
- በአጭር ጊዜ ኮንትራንት ለመስራት ፍቃደኛ የሆኑ

በቦርዱ ድረገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚገኘውን ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማመልከት ይችላሉ።

ማመልከት የሚቻለው ኦንላየን ብቻ ሲሆን የማመልከቻ ሊንኩም የሚከተለው ነው : https://www.nebe.org.et/pworkers/
ከአማራ ክልል ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረባት ያለችው ደሴ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች አስገዳጅነት ህዝቡ ማስክ እንዲጠቀም እንቅስቃሴ ጀምራለች።

ያም ሆኖ ደሴ ከተማ አሁንም በየቀኑ ሰዎች በኮቪድ19 ህይወታቸውን እያጡ ነው።ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱልሃሚድ ሙሃመድ ገፅ በተገኘው መረጃ መሰረት
☞በቤት ለቤት ህክምና ክትትል የሚደረግላቸው=77
☞በጤና ተቋማት ህክምና ክትትል ላይ ያሉ=143
☞በከፍተኛ የባለሙያ ክትትል የሚደረግላቸው
(Critical cases) =42 የኮቪድ19 ህሙማን እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

<<እንጠንቀቅ ለጤናችን ሃላፊነታችንን እንወጣ!!!>>

ቴሌግራም Join👇
https://t.me/wasulife

የፌስቡክ ፔጅ like,follow👇
https://www.facebook.com/Wasu-Mohammed-Page-115860726917918/

ዩቲዩብ ቻናል Subscribe👇
https://www.youtube.com/channel/UCetMTJe9CoWYelZ1F8-Re0g/

ኢንስታግራም Follow👇
https://www.instagram.com/wasumohammed/

ቲክ ቶክ Follow👇
https://vm.tiktok.com/JYgPxGF/

ቲዊተር Follow 👇
https://twitter.com/wasu_mohammed/status/1065568009396326400
===================
እባካችሁ አሽከርካሪዎች በተለይም የባጃጅ ሹፌሮች ፍጥነት ገዳይ መሆኑን ተረዱ።የሰው ደም እንደዚህ አስፓልት ላይ የፈሰሰበት አደጋ የተከሰተው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 02 በባጃጅና ሚኒባስ መካከል ነው።በአደጋው የባጃጁ አሽከርካሪና አንድ ተሳፋሪ ህይወታቸው አልፏል።ሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ይህ ደም የፈሰሰው በብሄር ግጭት ቢሆን ስንቱ በነገደበት፣ስንቱ በጮኸ ነበር።የሚያሳስበን የሰው ህይወት ከሆነ ለትራፊክ አደጋ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ቴሌግራም Join👇
https://t.me/wasulife

የፌስቡክ ፔጅ like,follow👇
https://www.facebook.com/Wasu-Mohammed-Page-115860726917918/

ዩቲዩብ ቻናል Subscribe👇
https://www.youtube.com/channel/UCetMTJe9CoWYelZ1F8-Re0g/

ኢንስታግራም Follow👇
https://www.instagram.com/wasumohammed/

ቲክ ቶክ Follow👇
https://vm.tiktok.com/JYgPxGF/

ቲዊተር Follow 👇
https://twitter.com/wasu_mohammed/status/1065568009396326400
===================