Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
252K subscribers
33.6K photos
1.34K videos
48 files
14.7K links
እንኳን ደህና መጡ

📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed

📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ🙏
Download Telegram
አቶ ቻላቸው ጌጡ ለአቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ መልሰዋል

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር ለባለቤቱ መለሱ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር በታማኝነት ለባለቤቱ መልሰዋል፡፡

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከአዋሽ ባንክ አቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ የተባሉ ደንበኛ ወደ አሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለአቶ መሃመድ ኢብራሂም 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር እንዲላክላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ገንዘቡ በስህተት ወደ አቶ ቻላቸው ጌጡ አካውንት ገቢ ሆኗል፡፡

አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን ገንዘብ በታማኝነት ለባለቤቱ ተመላሽ በማድረግ አርዓያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል፡፡ (ትምህርት ቢሮ)
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
227🏆35👍34🥰10🫡9😱6😍6💔5🤔3🥴2🔥1
10😱3
ኤርትራውያንን በግብፅ እየታፈሱ ነው ተባለ

የግብጽ መንግስት ኤርትራውያንን እያፈሰ ወደ እስርቤት እያጋዘ ይገኛል። እስከአሁን በዋና ከተማዋ ካይሮ ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች ከ 317 በላይ ኤርትራውያን ታፍሰው የታስሩ ሲሆን 150 ኤርትራውያንን ደግሞ በግዳጅ ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ተዳርገዋል።ኤርትራውያንን ማፈሱና ወደ እስርቤት መውሰዱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ምክንያት የተባለው ጉዳይ በዝርዝር አልተጠቀሰም።
Via Abel Birhanu
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
74😁36👍17😢13🕊4🙊3👏1
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
በመ/ቤታቸው የፀረ ሙስና ቀንን ለማክበር በዝግጅት ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች በሙስና ተጠርጥረው በፌደራል ፖሊስ መታሰራቸው ተሰምቷል። በሙስና ተጠርጣሪዎቹ የፕላን ዘርፍ ኃላፊ ኢንጅነር ህይወት እሸቱና የቢዝነስ ዘርፍ ም/ኃላፊ አንዱአለም ሰኦ መሆናቸው ታውቋል። ኃላፊዎቹ በሠራተኞች ፊት እጃቸውን በካቴና ታስረው በፌደራል ፖሊስ እንደተወሰዱ ተነግሯል። ትናንት ህዳር 24/2018…
ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ እና እስር ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሁለት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ የከፍተኛ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ውቤ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

የክሱ ዝርዝር ሶስቱም ከፍተኛ አመራሮች ማለትም አቶ ሀብታሙ ውቤ፣ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ እና አቶ አንዱዓለም ሲዓ፤ በፌደራል ፖሊስ የተጠረጠሩበት ዋና ወንጀል፣ ከውጭ ሀገር ኮንትራክተሮች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ሀገር ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ ገቢ በማሳጣት እና በከባድ የሙስና ወንጀል መሆኑ ተረጋግጧል።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናከር ለታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።

የእስሩ ሂደት የጀመረው ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነበር። የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ተቋሙ በመግባት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕላኒንግ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ኢንጂነር ህይወት እሸቱን እና የቢዝነስ ዘርፍ ዋና ምክትል ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ አንዱዓለም ሲዓን ቢሮ ካስፈተሹ በኋላ በሰራተኞች ፊት በካቴና አስረው ወስደዋቸዋል።

ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ ያደረገው ደግሞ፣ እስሩ የተፈጸመው ተቋሙ "የፀረ-ሙስና ቀን"ን ለማክበር ዝግጅት እያደረገ በነበረበት ዋዜማ ላይ መሆኑ ነው። መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞቹ "ነገ ህዳር 25 የፀረ-ሙስና ቀን ይከበራል" የሚል መልዕክት አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም፣ የዝግጅቱ መሪ መሆን የነበረባቸው አመራሮች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው በተቋሙ ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መደናገርን ፈጥሯል።

በዚህ የሙስና መረብ ውስጥ እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩ ሌሎች ተጨማሪ የስራ ኃላፊዎችም የሚፈለጉ ሲሆን፣ እስሩ ወደ ሌሎችም ዘርፎች ሊስፋፋ እንደሚችል ተመላክቷል። ፖሊስ ጉዳዩን በምርመራ እያጣራ ይገኛል።
መረጃው ከዘሀበሻ የተወሰደ ነው።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
188🙏167👏37👍29😁24😍9🏆8😱7🎉6🕊5👌3
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል

💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!!

💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር
💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር
💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር
💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር
💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ

በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት!

✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት

✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል

✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው።

✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች:
💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር
💥 አምስት የዋና ገንዳዋች
💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ
💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ
💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች
@Dmcreales
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0940625843
27
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ይሄ ታፔላ የማቆም ዘመቻ በኋላ የብሽሽቅ መነሻ እንዳይሆን ያሰጋል።እነዚህ ነገሮች እጅግ የተከበሩና ስስ በመሆናቸው በተፈቀደላቸው ቦታ ተወስነው ተከብረው ተወደው ቢቀመጡ መልካም ነው።

የቤተ እምነቶቹን መገኛ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ታፔላዎች ብቻ በቂ ናቸው።እየቆየ ሲሄድ ከተሞች "ሰሉ አለ ነብይ"(የአሏህ ሰላም በአንቱ ላይ ይስፈን!)የሚል እጅግ የተከበረ ቃል ያረፈበትን ታፔላ በደንብ ማስከበር አነሳለሁ ቢሉ መቀያየሙ ይመጣል።አንዱ የወረቀት ማስታወቂያ አምጥቶ ቢለጥፍበት ራሱን የቻለ ሌላ ነገር ነው።እፀዳዳበታለሁ የሚልም ይመጣል።የእኔ እምነት ታፔላ ከፊት በትልቁ መቆም አለበት የሚልም ይከተላል።ስለዚህ ጉዳዩን ከአባቶችና ከወንድሞች ጋር ተነጋግሮ መስመር ማስያዙ መልካም ይመስለኛል።

በውስጥ ከመጡልኝ አስተያየቶች መካከል:-

📌"ከእምነት ቦታው ርቆ ደህንነቱ ባልተረጋገጠ ቦታ የረሱልን(ሶ.ዐ.ወ) ክብር የሚያስደፍር አከባቢ ማስቀመጥ ኋላ ክብራቸው ሲነካ ዝም የሚል አማኝ የለም ግን ማን ሊጠየቅ ነው? የኦለማዎች ፈትዋ ቢጠየቅ የተሻለ ነው።ተገቢ አይደለም"

📌"ታፔላው በኛ ሀገር ተጨባጭ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።እንደ ሳዑዲ ባሉ ሀገሮች ግን የበለጠ ውበት አለው። ይሄ ቀርቶብን ሌሎች መሠረታዊ መብቶቻችንን ማስከበር ላይ በህብረት ብንሠራ ይሻላል።"

📌"ሲቀጥል ሌሎች ቢያደርጉት የሚከፋንን ነገር ለእኛ ሲሆን ሊያስደስተኝ አይችልም መቆም ያለበት ጉዳይ ነው።"

📌"በጣም የሚያስጠላ ነገር ነው ክብራቸውን ከፍ አደረግን ብለን በማንም ልናዘልፉቸው ነው። መቆም አለበት ይህኔ በ ቀን አንድ ግዜ ስማቸውን ሳያነሳ የሚውል ነው ሲለጥፍ የሚውለው።"

📌" ይሄ አካሄድ ወደ ፊትም ሙስሊሙ ከሌላ አማኝ ጋር ተዋዶና ተከባብሮ እንዳይኖር ለፍረጃ የሚያነሳሳ ነው ይታረም"

📌"ታፔላላይ ፃፉ አይደለም የተባለው በምላሳችሁ በሉ እንጅ አሏሁመሶሊ ወሰሊም አላሰይዲና ሙሀመድ"

📌"በእንቶ ፋንቶ ጊዜ አናባክን።ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ብዙም አንገብጋቢ አይመስለኝም።"

📌"አንዳንዶቻችን ሀገራችን የብዙ እምነት መገኛ መሆኗን መዘንጋት ተገቢ አይደለም።ዝቅታ የሚሰማው ካለ ራሱ ላይ በመስራት ነው ከፍታውን ማምጣት የሚችለው።" የሚሉ በርካታ አስተያየቶች ከእናንተ ተልከው ተመልክቻለሁ የተወሰኑት ናቸው የቀረቡት።

ቤተእምነቶች ሁሉ እየተነሱ በየከተሞች መግቢያ እምነታችንን ይገልፅልናል የሚሉትን ነገር የሚሰቅሉ ከሆነ የፉክክሩ ነገር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋልና ኦለማዎችና ኡስታዞች መፍትሄ ስጡበት።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
248👍83👏13🙏7👌5🤔4🏆3🙉2😁1😢1😍1
9
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
Photo
ተጨማሪ ሰው ታሰረ

በቅርቡ በተካሄደው የቲክቶክ ሽልማት (TikTok Awards) ሥነ-ሥርዓት ላይ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ትናንት በፖሊስ መያዛቸው ከተገለፁት በተጨማሪ ጆሲ የተባለው ወጣት በተመሳሳይ ጉዳይ ትናንት መታሰሩ ታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታዩ ከባህል የወጡ የአለባበስ ጉዳዮችን እየመረመረ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን የተወሰደው እርምጃም የዚያ ክትትል አካል እንደሆነ ተዘግቧል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
👍10557😁36👏9🤔3🙊3😭2😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"... በነበረው የክፍለሀገር አደረጃጀት አሰብ የወሎ አካል ነበር..." አቶ አባዱላ ገመዳ ለጋዜጣ ፕላስ ከሰጡት የተወሰደ
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
99👍49😁7😱6🤝6🤔2
በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣል የ30 በመቶ ግብር እንደማይኖር ተነገረ

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር እንደማይኖር አስታውቋል።

ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የ30 በመቶ ግብር ይጣላል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር መቆየቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታው መኳንንት ተናግረዋል።

በመሆኑም ይህ ሲዘዋዋር የነበረው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ገልፀው ፣ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር አይኖርም ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ በጉዳዩ ላይ በየትኛውም የመንግሥት አካል የተሰጠ መግለጫ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይጣላል የተባለው ግብር በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ የተፈጠረ እንጂ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንም የሚያውቀው ከዚህ ወር ጀምሮ የሚጣል ምንም ዓይነት የግብር ጭማሪ እንደማይደረግና መንግሥትም ይህን የማድረግ ዕሳቤ እንደሌለው ተናግረዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

በዚህም ‹‹በሐሰተኛ መረጃ የተነሳ ኅብረተሰቡ ላልተገባ ሠልፍና እንግልት እየተዳረገ ይገኛል፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለ ምንም ይፋዊ የመንግሥት ውሳኔ ከወጣው የነዳጅ ዋጋ ውጪ ያለ አግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ የነዳጅ አከፋፍይ ኩባንያዎችና ማደያዎች ተጠያቂ እንደሚደረጉም አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በመደበኛ ሁኔታ ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን ተናገረው፣ ነገር ግን በዚህ ሐሰተኛ መረጃ ምክንያት ፍጆታ ላይ ጭማሪ መፍጠሩን ገልጸዋል።

በዚህም የተናፈሰው መረጃ ስህተት መሆኑን ለነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች በተደጋጋሚ እያሳወቁ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር ደስታው፣ ኩባንያዎች ባልተፈለገ መንገድ ተታለው ከጂቡቲ የተረከቡትን ነዳጅ ላልተገባ ጥቅም የማዋል ዕሳቤ እንዳይፈጠርባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል ሰሞኑን በነዳጅ ምርቶች ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ ደግሞ ኤክሳይዝ ቀረጥን ያካተተ አጠቃላይ 30 በመቶ ታክስ ይተገበራል መባሉ ይታወሳል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
126👏15😁7😍4😱3🥰2🙏2🏆2🙉2🤔1
ወላይታዎች ደስታቸውን እየገለፁ ነው

የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡

በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል።

"ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል።ይህንን ተከትሎ ወላይታዎች ደስታቸውን እየገለፁ ነው
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
66🙏15😱4😍3🔥1👏1😁1