Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
252K subscribers
33.6K photos
1.34K videos
48 files
14.7K links
እንኳን ደህና መጡ

📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed

📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ🙏
Download Telegram
"...ነፃ ሕክምና የማይሰጡ ተቋማት እና ሐኪሞች በሕግ ይጠየቃሉ"የመንገድ ደህንነት እና መድኅን ፈንድ

በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሕክምና ተቋማት ያመራ ማንኛውም ሰው እስከ 15 ሺሕ ብር የሚደርስ አስቸኳይ የነፃ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚፈቅደውን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማት እና ባለሙያዎች በሕግ ይጠየቃሉ ተብሏል።

የመንገድ ደህንነት እና መድኅን ፈንድ አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ የመንግሥትም ሆነ የግል የሕክምና ተቋማት ጉዳት ደርሶበት የሚመጣን ማንኛውም ግለሰብ በነፃ የመርዳት ግዴታ ቢኖርባቸውም አንዳንድ ተቋማት በመመሪያው የታዘዘውን አሰራር ተግባራዊ እያደረጉ አይደለም፡፡

"መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ የሕክምና ባለሙያዎች እና ተቋማቱ እርምጃ ይወሰድባቸዋል" ሲሉ ማስጠንቀቂያ የሰጡት የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ብርሃኑ፤ ሁሉም የሕክምና ተቋማት ለትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ መስጠት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ይህ ግዴታ የተቀመጠው ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ ያስታወሱት አስተባባሪው፤ በወቅቱ የወጣው ተቋማቱ እስከ 2 ሺሕ ብር የሚደርስ ሕክምና በነጻ እንዲሰጡ የሚያዘው መመሪያ ተሻሽሎ ወደ 15 ሺሕ ብር መሻሻሉን ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል።

አስተባባሪው አቶ ሱራፌል፤ "ምንም እንኳን ሥልጠና እና መመሪያ በተደጋጋሚ ቢሰጥም፣ ጥቂት የማይባሉ የጤና ተቋማት 'ሕጉን አላውቀውም' የሚል ምክንያት አገልግሎቱን ከመስጠት መቆጠባቸው ለቅጣት ይዳርጋቸዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ተመሳሳይ ጥፋት የተገኘባቸው ሕግን የማያከብሩ ተቋማትን በወጡ ደንብና መመሪያዎች መሠረት ተጠያቂ ለማድረግም ለሕግ አስከባሪ አካላት ሥልጠና እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

የጤና ተቋማት ለነፃ አስቸኳይ ሕክምና ያወጡት ወጪ ተመላሽ እንደሚደረግ ያስረዱት አቶ ሱራፌል፤ ፈንዱ ይህንን ነፃ አስቸኳይ ሕክምና ለማስፈጸም የሚያስችል ገንዘብ የሚያሰባስበው ከራሱ መዋጮ በተጨማሪ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንደሆነ ተገልጿል።

የተሰበሰበው ገንዘብ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለተጎጂዎች ድጋፍ ይውላል ተብሏል።(አሐዱ ሬዲዮ)
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
156🙏43👍9👏6😱5🏆3🎉1
Ads

መሳቅ ከፈለጉ ብቻ ወደ እኛ ኑ አርሂቡ ብለናል

እኛ ጋር የምትመጡት ዘና ለማለትና ለመሳቅ ብቻ ነው።ግን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ።
https://youtu.be/arxRKpyulvE
ለቀጣይ ለበለጠ መዝናናት ከፈለጋችሁ ብቻ Subscribe አድርጉን።ሊንኩ ከስር ተቀምጧል።
👇   👇    👇   👇
https://youtube.com/@mewamedia?si=WqTGSX0f_-rUm3ua

Mewa Media
የሳቅ ምንጭ
19👍3
የቱርክ ባይራክታር ከዕይታ ወሰን በላይ የሆነ የአየር-ለ-አየር ሚሳኤል ጥቃት....

የአገሪቱ ብሔራዊ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላን የሆነው ባይራክታር ኪዚልኤልማ በአይነቱ የመጀመሪያው በመሆን ከዕይታ ወሰን በላይ የሆነ የአየር-ለ-አየር ሚሳኤል ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን የመከላከያ ኩባንያው ባይካር (Baykar) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በሲኖፕ ግዛት አቅራቢያ ጥቁር ባህር ላይ በተካሄደው ሙከራ አውሮፕላኑ በአገር ውስጥ የተገነባውን ጎክዶጋን ሚሳኤል ከክንፉ ስር በመተኮስ በፍጥነት የሚንቀሳቀስ ኢላማ ጄትን በተሳካ ሁኔታ አውድሟል። ጥቃቱ የተመራው በሰው አልባው አውሮፕላን ሲስተሞች ውስጥ በተዋሃደው የአሰልሳን ሙራድ AESA ራዳር አማካኝነት ነው።

የባይካር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሃሉክ ባይራክታር "በብሔራዊ አውሮፕላን፣ በብሔራዊ ራዳር እና በብሔራዊ ሚሳኤል፣ የአየር-ለ-አየር ፍልሚያ ሰንሰለት ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ትስስር ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ አቅም ጨርሰናል ይህ ኩራት የሕዝባችን ነው" ብለዋል።

የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ኪዚልኤልማ በዓለም የመጀመሪያው ሰው አልባ ተዋጊ ጄት በመሆን በጀት የሚንቀሳቀስ የአየር ላይ ኢላማን ከዕይታ ወሰን በላይ ሚሳኤል በመጠቀም ማጥፋቱን አሞግሷል። ሚኒስቴሩ "እኛ የወታደሮች አገር እንደመሆናችን መጠን ለልጆቻችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ግስጋሴዎችን መምራታችንን እንቀጥላለን" ብሏል።(nejmudinawel)
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
141👏30👍22😍6😱3🔥2🎉2😢1
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት
አሁን ደግሞ በተለያዩ ሳይቶቻችን ላይ እስከ 35% ልዩ ቅናሽ ላይ ነን

#ይፍጠኑ

‼️ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
🎯የክፍያ አማራጭ 70/30
👉3 መኝታ 110ካሬ ሙሉ ክፍያ 8,547,000 ብር

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 110ካሬ
     10%ቅድመ ክፍያ 1,210,000ብር
     ሙሉ ክፍያ 12,100,000ብር

‼️ሀይሌጋርመንት African CDC ፊት ለፊት
  🎯የክፍያ አማራጭ 70/30
👉3 መኝታ 139ካሬ 10,216,500ብር ሙሉ ክፍያ

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉 ባለ 3መኝታ (139ካሬ)
ሙሉ ክፍያ = 14,595,000ብር
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,500ብር )

‼️አያት
🎯 65/35 የክፍያ አማራጭ
👉3 መኝታ 111 ካሬ ሙሉ ክፍያ 7,936,500ብር

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 111ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,221,000ብር
ሙሉ ክፍያ 12,210,000ብር

‼️አያት ፈረስ ቤት
🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 108ካሬ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 108ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ
ሙሉ ክፍያ 10,260,000ብር
ቅድመ ክፍያ 1,026,000ብር
   
#ልብይበሉ
ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል
      
        ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
24👏4
በዘንድሮው ሀጅ ለአንድ ሀጃጅ 740 ሺህ ብር ተጠይቋል

📌ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል

የኢትዮጵ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1447 ዓ.ሒ ወይም የ2018 ዓ.ል የሐጂ አገልግሎትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከዲያስፖራ ሙስሊሞች ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነው በሀገራቸው በኩል ሀጅ የማድረግ ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኝ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤት ለማምጣት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶውን እንግልት አልባ ለማድረግ የምዝገባ ማዕከላትን በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል ማደራጀትን ጨምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲያከናወኑ መቆየቱ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ አሰጣጡን ከማዘመን ባሻገር ተደራሽ ለማድረግም ሰፊ ስራ የተሰራ ሲሆን ለአገልግሎትና መስተንግዶ የሚከፈለው ዋጋ ከብር የመግዛት አቅም መቀነስ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይጨምር አስፈላጊ ስራዎች ስለመሰራታቸው ተብራርቷል፡፡

ጠቅላይ መክር ቤቱ ግልጽ ጨረታ በማውጣት በሳዉዲ አረቢያ አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች በስፋት እንዲወዳደሩ ማድረጉ የክፍያ ዋጋው ከዶላር አንፃር ቅናሽ እንዲያሳይ አስችሏልም ብሏል፡፡

ብር ከዶላር አንፃር ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተዳከመ በመሆኑ የሐጅ አግልጎት ክፍያው ከብር አንጻር እንዲጨምርም እንዳስገደደም ነው በመግለጫው የተገለጸው።

በዚህ መሰረት የሀጅ አገልግሎት ከባለፈው ዓመት በ693 ዶላር እንዲቀንስ ቢደረግም የብር አቅም በመዳከሙ ብቻ የክፍያ ዋጋው ወደ 7 መቶ 40 ሺህ ብር ከፍ ሊል እንደቻለ ተጠቅሷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ በሀሰተኛ መረጃዎች ሳይስተጓጎል ከዛሬ ኅዳር 22/ 2018 ዓ.ል ጀምሮ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች እየሄደ እንዲመዘገብም ጠይቋል፡፡

መግለጫውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባልና ዋና ጸሀፊ ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ በአማርኛ፣ የስራ አስፈጻሚ በአላልና የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በኦሮምኛ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባልና ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሀምዛ በሶማሊኛ ቋንቋዎች ለመገናኛ ብዙሀን ቀርቧል።
መረጃው የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትነው።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
149😱47👍28😭14😁9💩7😍7🙊7🏆3🔥1
የመንግስት ሠራተኞች ግብር

ከፍተኛ ግብር የሚጣልባቸው የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ከ150,000 ብር ጀምሮ እንዲሆን ተጠየቀ

📌የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ጥያቄ ቀርቧል።

📌 መንግሥት መነሻ ወለል ከ1,200 እስከ 2,000 ብር በሚል ረቂቅ አዋጅ አቅርቧል

ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡

የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር እንዳሉት፣ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡

ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡

አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡

ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈላቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል፡፡

ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈላቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል፡፡

አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል፡፡
የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
301👍53😢11🥴10🏆9🤝7🙏6🎉3👀3😍2👏1
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል

💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!!

💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር
💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር
💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር
💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር
💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ

በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት!

✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት

✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል

✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው።

✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች:
💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር
💥 አምስት የዋና ገንዳዋች
💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ
💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ
💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች
@Dmcreales
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0940625843
21👍2😱2👏1
ድንበር ተሻጋሪ ግዳጅ

‹‹አየር ኃይል የሚገነባው ለሰፈር ግዳጅ አይደለም፤ ድንበር ተሻጋሪ ግዳጆችን ማሰብ አለብን።አሁን ላይ የኢትዮጵያን አየር ክልልን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅ ዘመናዊ አየር ሃይል ተገንብቷል።››
ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በፋና ቴሌቪዥን ካደረጉት ቃለመጠይቅ የተወሰደ
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
👍6849😁33🤣11🎉3🏆3😱2🕊2🙈2👏1
10
በእሳት አደጋ የሶስት ህፃናት ህይወት አለፈ

በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ በሰሶ ቀበሌ በቀጠና ሁለት ልዩ ስሙ አበልቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በትላንትናው እለት 10:30 የእሳት አደጋ ደርሷል።

የሚቶ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሀላፊ እና ህዝብ ግንኙነት ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ህፃናቶቹ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየተጫወቱ በነበረበት ሰዓት በቦታው የነበረ ገለባ በእሳት በመያያዙ በውስጡ የነበሩ

📌 የ6 ዓመት ሁለት ወንድ እና
📌 ሴት መንታ ልጆች እና የ2 ዓመት ሴት ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ህይወታቸው ያለፉት ህፃናቶች የታናሽ እና የታላቅ እህትማማች ልጆች ሲሆኑ በአያታቸው መኖሪያ ቤት ይኖራሉ።

የሁለቱ መንታ ልጆች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን የ2 ዓመቱ ህፃን እናት ደግሞ ለስራ ከሀገር ውጭ በመኖሯ ህፃናቶቹ በአያታቸው ቤት እንደሚኖሩ ነው ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ የገለፁት።

የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ምክንያቱ ባለመታወቁ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን የህፃናቶቹ አስከሬን ለምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተልኳል።

ወቅቱ በጋ እና ነፋሻማ በመሆኑ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
😢5640💔7😱6👍2🙉2
Ads.

ይህ ከስር ያለው ሚስጥሮች የሚወጡበት ወሳኝ ቻናል ነው።ገብተው ሰብስክራይብ ካደረጉ አነጋጋሪ መረጃዎችን በቅድሚያ ያገኛሉ።👇
https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw
https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw
11
"አልነጋገርም" ግብፅ

ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር "ተጨማሪ ውይይት" እንደማይደረግ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዲላቲ ተናገሩ።

ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ላለፉት 13 ዓመታት የተደረጉ ውይይቶች "አንዳችም መፍትሔ" አላመጡም ብለዋል።

የሕዳሴ ግድቡ ከተመረቀ በኋላ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ያለው ግንኙነት "የበለጠ መሻከሩን" ጠቅሰው፤ በዚህ መካረር ምክንያት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "ስጋት ሊሰማው" እንደሚገባም ተናግረዋል።

ባለፉት 13 ዓመታት በአገራቱ መካከል የተደረገው ውይይት ውጤት ባለማስገኘቱ፤ ግብፅ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት "የውሃ ደኅንነቷን እንደምታስከብር" አክለዋል።

ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ምንም ውጤት ባለማስገኘታቸው "በቀጣይም ንግግር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም" ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

የግድቡ ጉዳይ "ከኢትዮጵያጋር ካለን የሁለትዮች ግንኙነት ጋር የሚያያዝ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ግድቡን "እንደተናጠል እርምጃ ነው የምንቆጥረው" ብለዋል። አክለውም "ሕገ ወጥ ነው" ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።

ግድቡን "ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚጣጣም አይደለም" ሲሉ የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ "ዓለም አቀፍ ሕግ በግልጽ እንደሚለው ማንኛውም ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች መመራት አለበት። ይህም ማለት ማሳወቅን እና ጉዳት አለማስከተሉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል" በማለት አብራርተዋል።

ከአንድ ወር በፊት ግብፅ ብሔራዊ ጥቅሟን እና የውሃ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ "አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም እርምጃዎች እንደምትወስድ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ መናገራቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ በሰጠችው ምላሽ፤ ግብፅ "ሕገ ወጥነት እና የበላይነት በተሞላው መንገድ" የዓባይ ወንዝን ለመቆጣጠር መሞከሯን ቀጥላለች ብላለች።

አል ሲሲ፤ ግብፅ በዲፕሎማሲ እና እንደ መንግሥታቱ ድርጅት ባሉት ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ መተማመኗ እንደ ድክመት መቆጠር የለበትም ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስተዳደር ረገድ እየተከተለች ያለውን "ኃላፊነት የጎደለው" አካሄድ አገራቸው "እጇን አጣጥፋ አትመለከትም" ብለዋል።

የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሰጠው ምለሽ፤ "ኢትዮጵያ በዓባይ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ" አስረግጧል። "ከኢትዮጵያ ጠላቶች በኩል በእጅ አዙር ጫና ቢበረታም" የኢትዮጵያ ዕድገት "አይቀለበስም" ሲልም አክሏል።
(ቢቢሲ)
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
128🤣37👍19👏6🎉4😱2🕊2🙈21
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት
አሁን ደግሞ በተለያዩ ሳይቶቻችን ላይ እስከ 35% ልዩ ቅናሽ ላይ ነን

#ይፍጠኑ

‼️ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
🎯የክፍያ አማራጭ 70/30
👉3 መኝታ 110ካሬ ሙሉ ክፍያ 8,547,000 ብር

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 110ካሬ
     10%ቅድመ ክፍያ 1,210,000ብር
     ሙሉ ክፍያ 12,100,000ብር

‼️ሀይሌጋርመንት African CDC ፊት ለፊት
  🎯የክፍያ አማራጭ 70/30
👉3 መኝታ 139ካሬ 10,216,500ብር ሙሉ ክፍያ

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉 ባለ 3መኝታ (139ካሬ)
ሙሉ ክፍያ = 14,595,000ብር
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,500ብር )

‼️አያት
🎯 65/35 የክፍያ አማራጭ
👉3 መኝታ 111 ካሬ ሙሉ ክፍያ 7,936,500ብር

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 111ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,221,000ብር
ሙሉ ክፍያ 12,210,000ብር

‼️አያት ፈረስ ቤት
🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 108ካሬ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ

🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ
👉3 መኝታ 108ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ
ሙሉ ክፍያ 10,260,000ብር
ቅድመ ክፍያ 1,026,000ብር
   
#ልብይበሉ
ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል
      
        ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
27👏2
ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ጠቅልሎ ለማምለጥ

📌ወላጆች ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት

ይህ  ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ ያጋጠመ ክስተት ነው።

ግለሰቡ ቆራሊዮ እያለ በየሰፈሩ ሲዞር ከቆዬ በኋላ በከተማው አርጉባ ቀበሌ ገርሞሃ ከተባለ ሰፈር በምስሉ ላይ የሚታየውን ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ጠቅልሎ ለማምለጥ ሰሞክር በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደራሼ ወረዳ አስታውቋል።

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲጠብቁና አጠራጣሪ ነገር በሰፈራቸው ሲያዩ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
76😢65👍22😱15💔8😭6🎉5
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
Photo
Update

ከሰሞኑ ደሴ ከተማና አካባቢው መብራት በፈረቃ ሲሰጥ ነበር።ምክንያቱ በኮምቦልቻ ቁጥር -1 ሰብስቴሽን አንዱ ትራንስፎርመር ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የሀይል መቆራረጥ ስላጋጠመ እንደነበር ተነግሯል።አሁን ላይ በአካባቢው በከፊል ተቋርጦ የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ መመለስ መቻሉን የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን እወቁልኝ ብሏል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
106👏29👍20🙏18🙊9🙉85🏆1